አዲስ ለመጡ #የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ እህት ወንድሞቻችን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
መርሐግብሩ በ ሴቶች፣ ኤችአይቪ እና ልዩ ፍላጐት (Gender office)፤ የኢትዮጵያ ጤና ሙያ ተማሪዎች ማሕበር (EHPSA Bahir Dar) እና የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ተማሪዎች ሕብረት የተዘጋጀ ሲሆን በመርሐግብም:-
በሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሴቶች፣ ኤችአይቪ እና ልዩ ፍላጐት አገልግሎት ዳይሬክተር ወ/ሮ #አልማዝ (Ass.Professor) ፤
የኮሌጁ የሬጅስትራር ዘርፍ ኃላፊ አቶ #ደሳለኝ፤ እና
የሕፃናት ስፔሻሊስት ሐኪም ዶ/ር #ያለምወርቅ በመርሐግሩ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት እና ሰፋ ያለ አጠቃላይ ማብራሪያ ከሕይወት ተሞክሮአቸው ጋር አስተላልዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ጤና ሙያ ተማሪዎች ማኅበር ባህር ዳር ቅርንጫፍ (EHPSA Bahir Dar) ፕሬዝደንት #አንተነህ ኑርልኝ ስለ ማሕበሩ አጠቃላይ ገለፃ እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የ EHPSA ባህርዳር ምክትል ፕሬዝደንት #ሄርሜላ እዮብ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶችም የሕይወት ተሞክሯቸውን አጋርተዋል።
መርሐግብሩን ላዘጋጁልን እና ለተባበሩ አካላት በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን!!
ቀን 30/02/2017
Join us: https://t.me/EHPSA