👳🏽ባለዕዳው✍️ @baledaw Channel on Telegram

👳🏽ባለዕዳው✍️

@baledaw


ሁሉም ስለእኛ ነው ።
የምከትበው እይታዬን ብቻ ነው ! ወይ ልክ ነው ወይ አይደለም ፤ ልክ ካልመሰላቹ እየፈተፈትን እንወያይበታለን ወቢላሂተውፊቅ🙌

👳🏽ባለዕዳው✍️ (Amharic)

በተከትለው የእኛ ቻንኩላቸው 'ባለዕዳው' የሚሆን ነው። ይቼሃል ይትነግሩብዕጣን በቀደም። እሞሞሰ አለማን ከመስዋዕደም በኃላ። ለዘላፍን ውኁቕ ምኽሚኡ አለምኽሚኡ ነገስት ከእንባኣ ዘዋወ እንባ። ኢንስተም-አይበከሳ ዘረበሓለ።

👳🏽ባለዕዳው✍️

23 Nov, 04:34


ደስተኛ ለመሆን የሁለት ሰዓት interview መመልከት እና የ motivator ጩኸት አያስፈልገንም ። ስለየትኛውም መንገድ በሌላው ፍልስፍና አንጠመቅም ። ህይወት ውስብስብ አይደለችም ...ደስታ ዳመና ላይ የተንጣለለ ሩቅ ነገርም አይደለም ። ህይወታችንን በግድ አናወሳስባት !
ቀመር ሳይሆን ቅን አመለካከት ነው አስፈላጊው ።

ደስተኛ ህይወት ተመኘሁ 🫶

👳🏽ባለዕዳው✍️

22 Nov, 17:01


ይሄን ሀሳብ ያነሳሁት ብዙ ኢስላሚክ ቻናሎች እንዲሁም ኡስታዞች ችላ ስላሉት እንጂ ከዚህ ቻናል content ጋር እንደማይሄድ አውቃለው ። እኔም በግድ የምለቀው አስተማሪ ይሆናል በሚል እንጂ እንደሌላው ፅሁፍ በነፃነት አይደለም..... እንጂ አቆመው ነበር ።

ይህን እንደጨረስኩ ወደነባሩ ፅሁፍ እመለሳለው ድጋሚ አላነሳባችሁም 🙌

👳🏽ባለዕዳው✍️

22 Nov, 16:05


የቀጠለ........

[ባለዕዳው]


በዚህ አጭር ሂደት ውስጥ የሚከሰተው ራስን የመጥላት እና ራስን የመናቅ ዝንባሌ በመኖር ውስጥ ከሚከሰቱ ትላልቅ ስህተቶች ከሚመነጨው የበለጠ ነው ። በዚህ ጨለማ አለም ውስጥ የተዘፈቀ ሰው ድንጉጥ ነው ...ጥንካሬውን በተሳሳተ ሜዳ የጨረሰ ጦረኛ ነው ። ልፍስፍስ ነው ....ድፍረቱን ያባከነ ነውና ። እይታው ያጠረ ነው ....እይታውን በራሱ ላይ በመተኮስ አባክኗልና ።

ይህ ስራ ነፍስን ከማድከም እና ራስን ከመጥላት ባሻገር አካላዊ ጉዳቱም ከባድ ነው ....መኪና በረጅም መንገድ ላይ ሳለ በየሰዓቱ ነዳጁን እየደፋ ቢሄድ ምን ይሆናል ? በዚህ ተግባር ውስጥ ያለም ሰው ምሳሌው ይህ ነው ! ጉልበት ነው ያለአግባብ እየተደፋ ያለው ( ወደ ዶክተሮች ስራ አንገባም እንመለስ በቃ😁🙌)

በሚገርም ሁኔታ ለማይታየው አለምም ተጋላጭ ያደርጋል ...ጀናባ የሆነ አካል ነፍሱ ደካማ ትሆናለች እንደ አኸላለቃችን ጂኒዎች ለሰው ልጅ ፍራቻ ያላቸው ሲሆን በዛ ርክሰት ውስጥ እና ጀናባነት ውስጥ ያለን አካል አይፈሩም ....ይህም ማለት ለጂኒ ጥቃት ተጋላጭነታችንን ይጨምራል ! ይህ አሊሞች የተናገሩት ንግግር ነው ።

ማስተርቤሽን አለም ላይ ካመጣው ጉዳት በጣም ትልቁ የፆታ አመለካከትን ማዛባት ይመስለኛል ። በዚህ የጨለማ አለም ውስጥ ያለ ሰው አጠገቡ ያሉ ተቃራኒ ፆታዎችን ሰው ከሚል ፍቺ የፋቀ ይመስለኛል ። ወንዱ ሴቱን ሲመለከት የሚያየው አንድ የወሲ* መፈፀሚያ እቃ  ...ሴቷም ወንድ ስትመለከት የሚታያት በተመሳሳይ ከሆነ ከዚህ በበለጠ ምን አይነት ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ?

ይህ አይነት ትውልድ በመፈጠሩ ማን  ተጠቅሟል ? እንዴት ?

በቀጣይ ፅሁፍ ተመልክተን ይህን ርዕስ እንዘጋለን ።

👳🏽ባለዕዳው✍️

22 Nov, 03:59


መልካም ጁምዓ

اللهم صلى وسلم على نبينا محمد❤️

اللهم صلى وسلم على نبينا محمد❤️

اللهم صلى وسلم على نبينا محمد❤️

اللهم صلى وسلم على نبينا محمد❤️

اللهم صلى وسلم على نبينا محمد❤️

በሰላዋት የደመቀ🤩

👳🏽ባለዕዳው✍️

21 Nov, 17:51


እናንተዬ የሰው ልጅ የሚኖረው  በደም ስሩ ውስጥ በሚዘዋወረው ደም አይደለም ! የሰው ልጅ የሚያኖረው ተስፋው ነው ...በሞት ባህር ውስጥ ሆኖ ተስፋ ያለው ነው የሚድነው ።

ተስፋዎቻቸውን አታጥፉ ...የመኖር እቅዳቸውን አታክሽፉ!

👳🏽ባለዕዳው✍️

21 Nov, 16:13


ስህተትህን ሁሌም የሚያግራራልህ ሰው ምናልባት የውድቀትህ ናፋቂ ነው ። ውይ " ይወደኛል" አትበል ! ጥፋት ላይ ባለህ ጊዜ ጥላህ የሆነ ሰው እየከለለህ ያለው ከመልካም ነገር ነውና ንቃ ።

👳🏽ባለዕዳው✍️

21 Nov, 03:50


ማነው ዱንያ የብሶት ግዛት ናት ያለው ? የለም ! የደስታ ጊዜያቶችም አሏት....የሀሴት ጊዜያቶችም አሏት....ባላቹ ነገር ተደሰቱ...በተሠጣቹ ነገር ሁሉ ሀሴት አርጉ ። አጠገባቹ ባሉት የልባቹ ሰዎች ተደሰቱ...ባላቹ ጤንነት ተደሰቱ...ዱንያ ናትና ተደሰቱ ።

👳🏽ባለዕዳው✍️

20 Nov, 17:11


📓 ርዕስ፦ ቢስሚከ ነህያ
✍️ ፀሃፊ፦ ዶ/ር ዐምር ኻሊድ
ትርጉም፦ ሙሀመድ ሰዒድ
ዘውግ፦ የአላህ ስምና ባህሪያት(አስማእ ወሲፋት)

👳🏽ባለዕዳው✍️

20 Nov, 15:52


[ባለዕዳው]

አዕምሯችን የሚፀንሰውን የሚገልጠው በምንድነው ? በማስተርቤሽን (ራስን በራስ ማርካት ) ? በዝሙት ወይስ በሌላ ? ዛሬ አንዱን እንመለከታለን ።

#ማስተርቤሽን (ሴጋ)

አዕምሯችን የፀነሰውን ፅንስ ለመግለጥ የተለያዩ አማራጮችን ይጠቀማል ..ከዛም ውስጥ ምቹ እና ቀላሉ ማስተርቤሽን ይሆናል ። ይህን ተግባር በእርካታ ውስጥ ቅጣት ይሉታል ። የፅንሱ ሴሎች የምንላቸው በስልኮቻችን ስክሪን ውስጥ የምናገኛቸው ምስሎች እና ከውጪው አለም የሚንፀባረቁ ምስሎች እንደሆኑት ሁሉ በወሲ* አለም ውስጥ የተዘፈቁ ቀልዶች እና ፅሁፎች የራሳቸው ድርሻ አላቸው ። እንዲሁም ልቅ የሆነ የትዳር ፍላጎት የራሱ ተፅዕኖ አለው ። ( ይህ  የሚመለከተው ለትዳር በየትኛውም መመዘኛ ያልደረሱ አፍላ ወጣቶችን ነው !)
#ምናልባት የነፍስን ምንነን በደንብ አልተረዳንም ...ነፍስ ደስታን ስቃይ በሚያስከትልባት ነገር ውስጥ ስቃዩን ችላ በማለት ደስታን የምታሳድድ ሀይልም ናት ! የቂያም ለት የሰውነት አካሎች ሁሉ ሲመሰክሩ ነፍስ በድንጋጤ የምትዋልል የተለየች ነገር አይደለች ? ከላይ እንዳልኳቹ ማስተርቤሽን በእርካታ ውስጥ ቅጣት ነው ....አይን እና ሌሎች አካላቶቻችን ተባብረው ለሰሩት ቅጣቱን ነፍስ ላይ የመጫኛ መንገድ ነው ! ይህ ስራ የደስታ መንገድ ሳይሆን አንድ ራሱን የቻለ የቅጣት አይነት ነው ። ልክ ቁስሉ ያሳከከው ሰው በቻለው ልክ አኮ ቁስሉን ቢመለከት አጥንት እንደሚያየው ሁሉ በዚህ መንገድ በብዙ የተመላለሰ ሰው ነብሱን ሲመለከት እጅግ ደካማ ፣ ተስፋ የቆረጠች....የባከነች እና ራሷን የምትጠላ ነፍስ ያያል ።

ራስን በራስ ማርካት ከነፍስ ላይ ተስፋን...ህልምን...ጥንካሬን ...ደስታን መገንጠያ መሳርያ ነው ።


መግቢያ ነው አላለቀም🙌

👳🏽ባለዕዳው✍️

19 Nov, 16:50


ይሄን ነገር አልረሳሁትም እየፃፍኩ ነው....ግን በጣም ረዘመብኝ .... ረጃጅም ፅሁፍ ቢሆን ቅር አይላችሁማ ?

👳🏽ባለዕዳው✍️

19 Nov, 15:20


ሴትነት .....ልስላሴ ፣ ጥንካሬ ፣ እዝነት ፣ ፍቅር እንክብካቤ እና ብዙ ጥሩ ነገሮች ሲሆን ወንድነት ግን ስርዓት ነው ። ወንድን ልጅ ሴት ስትሰራው ወንድ ልጅ ደግሞ አለምን ይሰራል ።

የወንድ ልጅ የመጨረሻ አላማው ጠንካራ ሰውነት እና የተትረፈረፈ ሀብት አይደለም ። አሁን ላይ እንደምናያቸው እና እንደምናነባቸው ፅሁፎች ወንድ ልጅ በዛ አይገለጥም ። ወንድ ልጅ ስርዓት ነው ! ምቾት በማይሰማው ከባቢ ውስጥ ተላምዶ መኖር ሳይሆን ከባቢውን መቀየር ግዴታው ነው ።

እና ሰውነትን መገንባት እና በሀብት መደራጀት ለአላማችን የመጀመርያው እርምጃ እንጂ ሌላ አይደለም !  የኢስላሙ አለም ላይ አሻራ ማሳረፍ አለባቹ ...ሀገራቹ ላይ አሻራ ማሳረፍ አለባቹ ...ታሪክ ውስጥ ለናንተ የተዘለለ ቦታ አለና ሙሉት ! በሴራዎቻቸው አይናችን አይደብዝዝ ....አደራ ።

[ባለዕዳው]

👳🏽ባለዕዳው✍️

19 Nov, 03:36


:-ኡስታዝ ያሲን ኑሩ
📚:-የህይወት ግብህን ቅረፅ


የሆነ ሰው ጠይቆኝ ነበር ...

👳🏽ባለዕዳው✍️

18 Nov, 14:58


ውስጣችን ጨልሟል!

ውስጣችን ሲጨልም እየታመምን ..የነጋ ጊዜ ባለፈው ጨለማ እያዘንን ውስጣችን ይዳምናል ።


ለመዳን እንሞክር?

👳🏽ባለዕዳው✍️

17 Nov, 16:57


ስለኒቃብ ለመጨረሻ ጊዜ አንድ ነገር ልበል አፉ በሉኝና🙌

"ኒቃብ ዝም ብሎ አይለበስም ...ኒቃብ ያለ እውቀት አይለበስም ...እንዴት ኒቃብ ለብሳ መጥፎ ስራ ትሰራለች ....ኒቃቢስት አይደለች እንዴት ..ለምን ...ኡኡኡ"

ወገኖቼ ኒቃብ መልበስ ማለት መመነን አይደለም ... ገዳም መግባትና አለምን መጣል አይደለም ኒቃብ የለበሰች ሴት ኖርማል ሂጃብ ከለበሰች ሴት የምትለየው ኒቃብ በመልበሷ ብቻ ነው ። ኒቃብ የሆነ የኢማን ደረጃ ስለተደረሰ የሚለበስ የተለየ ልብስ አይደለም ...ኒቃብ የለበሰች ሴት ትሳሳታለች...ትወድቃለች ! ስንወቅስ ከልብሱ ጋር ማያያዙን እናቁም ከሚሊየን ስህተተኞች አስሩ ኒቃቢስት ቢሆኑ በነሱ ላይ ኡኡ ማለት ሌላ ነገር ያስጠረጥራል 👐

እና ያለእውቀት አይለበስም የምትሉ ደሞ ራሳቹን ማታለል አቁማቹ ልበሱ...ከዛ ዲናቹን እወቁ ....እስከዚህ ድረስ ቀላል ነው🙂

ያለበሳቹም ሂጃባቹን አደራ ❤️
[ባለዕዳው]

👳🏽ባለዕዳው✍️

17 Nov, 15:52


ያለፈውን እስከያዘው ነገር እርሳው ፤ ባለፉ ነገሮች ላይ መጠመድ እብደት ነው ።
ስለወደፊቱም አትጠበብ ፤ ምክንያቱም መጪው ከማይታየው ነው ። እስኪመጣ ድረስ አትጨነቅለት ።

" ጧት ላይ ሆነህ ማታን አትጠብቅ ፤ ማታ ላይ ሆነህ ጧትን አትጠብቅ " ረሱል ሰ.ዐ.ወ

የምን ሀዘን!

👳🏽ባለዕዳው✍️

17 Nov, 07:03


ከባዱ ነገር የአይን ዝሙት ነው !

የሴት ልጅ ማህፀን ልጅ እንደሚፀንሰው ሁሉ የሰው ልጅ አዕምሮም ይፀንሳል ...አዕምሮ ለመፀነስ የሚጠቀመው አካል ደግሞ አይን ነው ። በስልኮቻችን ላይ የምናያቸው ምስሎች እንዲሁም ወደማህበረሰቡ ወጥተን ትኩረት የምናደርግባቸው ነገሮች የፅንሱ ሴሎች ናቸው ። ሴት ልጅ ፅንሷን በ9 ወር እንደምትገልጠው ሁሉ አዕምሮ ፅንሱን ለመግለጥ የሆነ የራሱ ጊዜ አለው ። ትልቁ ጥያቄ  አዕምሮ የፀነሰውን ነገር የሚገልጠው በምንድነው ? በማስተርቤሽን ? በአካላዊ ዝሙት ? ወይስ በመድፈር ? እኚህ ነገሮች ሲልሲላ ናቸው... አንዱ ላይ ራሱን ያገኘ ወደሌላው ዙር ለመሸጋገር ስነልቦናዊ ልምምድ ውስጥ እንዳለ ማወቅ ይኖርበታል ።

ማስተርቤሽን ?
ዝሙት?
መድፈር ?

በተከታታይ እናያቸዋለን ኢንሻአላህ

[ባለዕዳው]

👳🏽ባለዕዳው✍️

17 Nov, 04:12


ልቤ ያምናል!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
የቆለፈኝ ችንካር፣
ያለሁበት ስካር፣
ያይላል. . .
ይፈላል. . .ለአፍታ አይቀንስም!
እንኳን ወደ ህልሜ. . .
ወደ አልጋ አያደርስም!
ግን ልቤ ያምናል. . .
የጠለፈው አዚም እያንገዳገደው፤
"መነሣት ይችላል፣መውደቅ ያልከበደው!"
.

👳🏽ባለዕዳው✍️

16 Nov, 16:04


ነበር.............

የማንለያይ .....ከተለያየንም አንዳችን ያለአንዳችን መኖር እንደማንችል አምነን ነበር ።
ሰዎች ሁሉ ጥሩ ....እኛም ለሁሉም ሰው ጥሩ የሆንን መስሎን ነበር ።

ነበር ቢያምም ነበር ውስጥ ሆነናል ።

👳🏽ባለዕዳው✍️

16 Nov, 10:47


አንድ ሀሳብ አዳምጬ ነበር .....እንዲህ ይላል

" እኛ ዘንድ ሙስሊም አይደሉም የምንላቸው አካላቶች ለትላልቅ ችግሮች መፍትሄ እያበጁ ነው ...ማየት የተሳናቸውን ማየት እንዲችሉ....መስማት የተሳናቸውን መስማት እንዲችሉ ...መውለድ ያልቻሉትን በተለያየ መንገድ መውለድ እንዲችሉ እያደረጉ ነው ። የኢስላሙ አለም ግን አሁንም ሴት መጨበጥ ዉዱዕ ያጠፋል አያጠፋም ? በሚል ጭቅጭቅ ውስጥ ነው ...አሁንም በነሺዳ ትልቅ ጭቅጭቅ ውስጥ ነን....አሁንም ሴትን ልጅ ማየት ይቻላል አይቻልም ? በሚል ሀሳብ ውስጥ ነው!"

በጣም ያስገረመኝ እና ያላየነው እይታ ነበር ።

ጤና...ሳይንስ...ቴክኖሎጂ ሁሉንም ከ ጅማሮዋቸው ብትመለከቱ የኢስላሙ አለም ትልቅ አሻራ አሳርፏል...even ፍልስፍና ላይ ለዘላለም የሚቀር አሻራ አሳርፏል ..ቁርዓን ሺ ያልተገለጡ እውነታዎችን ይዟል ....እጃችን ላይ ያለው ቁርዓን እስከአለም ፍፃሜ እያስገረመ የሚሄድ ትልቅ ሀይል አለው ....ግን አሁን ከሱ ርቀን የሙስሊሙ አለም በትናንሽ ነገር ተከፋፍሎ የጨለማው ዘመን ላይ ነው ።

ብቻ ሀሳቡ ስለተመቸኝና የምዕራቡ አለም ምን ያህል የሙስሊሙን አለም እንዳዳከሙት ለማስታወስ ነው ያጋራኋቹ ። አስታውሱ የመጨረሻው ኢስላማዊ ኺላፋ (Ottoman) የወደቀውም በእንግሊዝ እና አርቆ ማየት ባልቻለው የሙስሊም አለም ነው !

አንነቃምን ?🙂

[ባለዕዳው]

👳🏽ባለዕዳው✍️

15 Nov, 18:28


👳🏽ባለዕዳው✍️ pinned «humanity ......ሰብዓዊነት አለም ላይ ትልቁ ሚዛን ሰብዓዊነት ነው ። ከጊዜያቶች በኋላ ዘርና ሀይማኖትን ከአቅል ጋር ፍፁም በማራራቅ ሰው መሆን ላይ ተፅዕኖ አሳድረናል ። ዘር መነሻው ጭፍንነት እና ትርጉም አልባ የሆነ ነገር ስለሆነ እንዝለለው .....ሀይማኖተኝነት እንዴት ጭካኔን ሊያለማምደን ቻለ ? ሰው መሆንን ስህተት አርገን እስከመቁጠር ደርሰን ሰብዓዊነት ለምን ጠፋ ? ሰው መሆን ከምንም…»