Injibara University @injiuniversity Channel on Telegram

Injibara University

@injiuniversity


Injibara University (English)

Are you interested in staying updated with the latest news and events from Injibara University? Look no further than our Telegram channel '@injiuniversity'! Injibara University is a leading educational institution in Ethiopia, known for its commitment to academic excellence and innovation. Our channel provides followers with valuable information about upcoming seminars, workshops, and campus activities. It also serves as a platform for students, alumni, and faculty members to connect and engage in meaningful discussions. Whether you're a current student looking for important announcements or a prospective student interested in learning more about our programs, our channel has something for everyone. Join us today and be a part of the vibrant Injibara University community!

Injibara University

11 Nov, 20:30


የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ኔትወርክ እና ሲስተም ኦፕቲማይዜሽን ፕሮጀከት የርክክብ ስነ ስርዓት ተደረገ፡፡

ዩኒቨርሲቲውን በአይሲቲ ዘርፍ ደረጃውን ከፍ ለማድረግ በ37 ሚሊዮን ብር ወጭ በዋሊያ ቴክኖሎጂስ ሲሰራ የነበረው ፕሮጀክት ተጠናቆ ርክክብ ተደርጓል፡፡

በርክክቡ የተገኙት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው መማር ማስተማሩን ከቴክኖሎጂ ጋር በማገናኘት በተለይም ኢ-ለርኒንግን ለመጀምር ከፍተኛ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው፣ በዛሬው ዕለትም ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲሰራ የነበረውን ኔትወርክ እና ሲስተም ኦፕቲማይዜሽን ፕሮጀክት ተጠናቆ ከዋሊያ ቴክኖሎጂስ መረከቡን ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር ጋርዳቸው አያይዘውም ፕሮጀክቱ ከ37 ሚሊዮን ብር በላይ መጨረሱን ጠቅሰው ፕሮጀክቱን በተፈለገው ጥራት ሰርተው በማስረከባቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የዋሊያ ቴክኖሎጂስ ፕሮጀክት ዋና ማናጀር ትግስት አምሳሉ እንደተናገሩት ዋልያ ቴክኖሎጂስ ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ጋር ከተዋዋለው ኔትወርክ እና ሲስተም ኦፕቲማይዜሽን ፕሮጀክት ሰርቶ ከማስረከብ በተጨማሪ የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ስልጠናዎችን በማቻቸት ለተቋሙ ባለሙያዎች ስልጠና መስጠቱን ገልጸው በቆይታቸው ዩኒቨርሲቲው ላደረገላቸው መልካም ትብብር አመስግነዋል፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአይሲቲ ስራ አስፈጻሚ አቶ አዱኛ አለበል እንደገለጹት ፕሮጀክቱ ከዚህ በፊት የነበረውን አጠቃላይ የኔትወርክ እና ሲስተም የሚያዘምን፣ ተደራሽነቱን እና ደህንነቱ እንዲጠበቅ የሚያደርግ በመሆኑ ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣የአይሲቲ ባለሙያዎች እና ዋሊያ ቴክኖሎጂስን አመስነዋል፡፡

#ጥቅምት 2/2017ዓ.ም፣እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

Injibara University

08 Nov, 13:47


የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች በወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ተወያዩ፡፡
በውይይቱ  የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር እና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም   ዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ  እና አስተዳደር  ሰራተኞች  ተገኝተዋል፡፡

በውይይቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር)  አጃንዳው በሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ ውይይት ለማድረግ መሆኑን ገልጸው  ሰላም እጅግ ውድ እና ለሁሉም ነገር መሰረት ነው ብለዋል።

ዶ/ር ጋርዳቸው አያይዘውም የዩኒቨርሲቲው ምሁራን በክልላችን እየተስተዋለ ባለው የሰላም እና ጸጥታ  ችግሮች  ዙሪያ የመፍትሄ እና አሻጋሪ ሀሳቦችን እንዲያመነጩ እና ሀሳባቸውን እንዲሰጡ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልጸው ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች እና ምሁራን የሰላም ዘብ እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳደሪ እና የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው በመክፈቻ ንግግራቸው እንተናገሩት የዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተለያዩ  አካላት ስብጥር መሆኑን ጠቅሰው ውይይቱ በዋናነነት ከሰላምና ጸጥታ አኳያ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ሚና ፣ከሰላም ዕጦት መውጫ መንገድ መወያየት እና አማራጭ የመፍትሄ ሀሳቦችን ለማሰባሰብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ የተገኙት ኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት የ302ኛ ኮር ም/አዛዥ ኮሎኔል ሰጤ አራጌ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰላምን ለማስጠበቅ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ሰላም እና መረጋጋት እንዲመጣ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ከፍተኛ ሃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በውይይቱ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳብ እና አስተያየቶች ተነስተው በሚመለከታቸው አካት ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

Injibara University

08 Nov, 05:27


#ማስታወቂያ
#ለትምህርት_ፈላጊዎች

Injibara University

07 Nov, 19:16


ለአካዳሚክ እና አስተዳደር ሴት ሠራተኞች የጡት ካንሰር የግንዛቤ ፈጠራ ሥልጠና ተሰጠ።

ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአካዳሚክ እና አስተዳደር ሴት ሰራተኞች ስለ ጡት ካንሰር ምንነት፣አጋላጭ ሁኔታዎች እና ቅድመ መከላከያ መንገዶች ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ፈጠራ ሥልጠና ተሰጠ፡፡

በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) የስልጠናው ዓላማ ብዙ ሴት እህቶቻችንና እናቶቻችንን እየነጠቀ ያለውን የጡት ካንሰር በተመለከተ የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር መሆኑን ገልጸዋል፡፡፡

ፕሬዘዳንቱ አያይዘውም "በዩኒቨርሲቲው ሴት ሰራተኞች ላይ መስራት ለዩኒቨርሲቲው ዕድገት እና ስኬት የራሱ ጉልህ አስተዋጽኦ አለው" ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው መሰል ስልጠናዎች እና የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች ላይ በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ባንቻለም ካሴ "በሴቶች ዙሪያ የተለያዩ ስልጠኛዎችን እና ግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን መስራት ሴቶች በስራቸው ብቁ እንዲሆኑ ያስችላል" ብለዋል።

ሥልጠናውን የእንጅባራ ዩኒቨርሰቲ መምህር እና ጠቅላላ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ዶ/ር ዜናው አማረ እና የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የሚድዋይፈሪ መምህርት እና CPD አስተባበሪ የውብምርት ሻረው(ረዳት ፕሮፌሰር) ሰጥተዋል።

ጥቅምት 28/2017 ዓ፣ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ