በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም @matter_of_facts Channel on Telegram

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

@matter_of_facts


የ በውቀቱ ስዩምና አሌክስ አብርሃም አንድሁም ሌሎች አዝናኝና አስተማሪ ጽሁፎች ለማገኘት ከፈለጉ join አደርጉን

🙏እባካችሁ ለሌሎችም አጋሩልን🙏

@matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም ፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም (Amharic)

በውቀቱ ስዩም ፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ጽሁፎችን እና አጋሩልንን መዝገበታችሁን ይመልከቱ። እባካችሁ ለሌሎችም አጋሩልን! በስልክና በጉዞ ላይ ያሉ ሁሉን አስተማሪ ጽሁፎችን እንዴት ተመልከቱ፣ አጋሩልንን ለመላክ፣ እባካችሁ ከባለዘር አቀፍ ውስጥ በላይ እየተመለከተ ለመጫወት ይዘግቡ። ከዚህም በላይ በየቀኑ መረጃዎችን ይጠቀሙ። ይህንን ይጫኑ @matter_of_facts ተይዞ፣ ለእኛ ቅናትን ተላይተዩ።

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

20 Nov, 13:55


https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

17 Nov, 09:12


የተወጋ ትዳር!
(አሌክስ አብርሃም)

በነገራችን ላይ ቆንጆ ሴት ስላገቡ ቆንጆ ልጆች መውለድ እንደሚችሉ የሚያስቡ ወንዶች አሉ። ስለዚህ ለትዳር ቆንጆ ሴት ያሳድዳሉ። በሰው ምርጫ መግባት አልፈልግም። ግን የአንድ ጓደኛየን ተሞክሮ ማካፈል እፈልጋለሁ። ለነገሩ የሱም ተሞክሮ ለህይወታችን ምንም አይጨምርም እንተወው። ዋናው ነገር ግን ልጆች ሲወለዱ ሜካፕ፣ሂውማን ሄር ፣የተወጋ ከንፈር፣ በሰርጀሪም ይሁን በኤክሰርሳይስ የተስተካከለ የሰውነት ቅርፅና የተጠና አማላይነት ከእናታቸው አይወርሱም። በኋላ የኔ አይደሉም እንዳትሉ!

በዘር የሚተላለፉ የጤና ችግሮች፣ ደከም ያለ አዕምሮ፣ ባህሪ ወዘተ ግን ሊወርሱ ይችላሉ። እና ስትጋቡ ከፍቅር አልፋችሁ "ስለምርጥ ዘር" እስከማሰብ የደረሰ የከብት እርባታ መንፈስ ካደረባችሁ ቢያንስ ለትውልዱ ስትሉ ጤናና ባህሪ ላይ ላይ አተኩሩ።

ሴቶችም እንደዛው "ከሚያምር ረዢም ወንድ የሚያምር ልጅ " የሚል መፎክር ውስጣችሁ ካደረ ፣ የምትመርጡት ለምርጥ ዘር የሚሆን ኮርማ እንጅ ባል አይደለም። መለሎው ኮርማ የቅድም አያቱን ስንዝሮ ቁመትና መጋፊያ እግር ለልጃችሁ ሊያወርስ ይችላል። ሆስፒታል አቀያይረውብኝ መሆን አለበት እስክትሉ የጀነቲክስ አልጎሪዝም እብድ ነው። የሆነ ሁኖ መሠረቱ ከተወጋ ትዳር ቆንጆ የምትሉትም ይወለድ መልከ ጥፉ ዋጋው ውድ ነው። ከምታፈቅሯቸው ውለዱ ፣ ከፍቅር የተወለዱ መልአክ ናቸው። ልጆች ምንጊዜም ውብ ናቸው። አስቀያሚ የሚያደርጓቸው አስቀያሚ ሒሳብ የሚሰሩ ወላጆች ፣ የእነዚህ ወላጆች ስብስብ የፈጠረው ማህበረሰብ ነው። የተወጋ ትዳር የተወጋ ማህበረሰብ ይፈጥራል።

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

16 Nov, 18:15


ሰሞንኛ
(በእውቀቱ ስዩም)

በአብማይቱ እምላለሁ፥ ማይክ ታይሰን ቢያሸንፍ ኖሮ ትንሽ ቅር ይለኝ ነበር፤ የአምሳ ስምንት አመት ሰውየ የሀያ ስምንት አመት ጎረምሳ ፕሮፌሽናል ቦክሰኛ ባፍጢሙ ደፋው ፥ ቢባል የሰውየው የፍጽምና ማሳያ ይሆን ነበር፤ ፍጹምና እንከን አልባ የሆነን ሰው ደግሞ አርአያ ማድረግ ያደክማል፤

ከትልልቅ ሰዎች የምጠብቀው ልከተለው የምችለው አይነት አርአያነት ነው፤ ለካ በአምሳ ስምንት አመቴ ፥ጡንቻ መገንባት እችላለሁ፥ ስምንት ዙር ሪንግ ውስጥ የሚያስቆይ ትንፋሽ ማካበት እችላለሁ፤ ለካ በዚያ እድሜ የልጆቼን እጅ ሳልጠብቅ በጥረቴ እንጀራ መብላት እችላለሁ ፥ ብለህ እንድታስብ የሚያደርግ አንጋፋ ጀግና ሲገጥምህ ልብህ በተስፋ ይሞላል፤ ማይክ ታይሰን ምን ፈየደልህ ብትይኝ መልሴ ይሄ ነው፤ አምሳ አመትን ከዘራ በማማረጥ እንዳልጠብቀው አድርጎኛል፤ ከዚህ በላይ አነቃቂ የለም!

“ምንም ደሀ ቢሆን ባይኖረውም ሀብት
ከደጃፍ ሲቀመጥ ደስ ይላል አባት “

የሚል ጥቅስ እየተመሰጥን ነው ያደግን፤ አብዛኛው ሰው ወጣትነትን ሲሻገር የአካል እንቅስቃሴ እንዲያቆም ውጫዊና ውስጣዊ ግፊት ያድርበታል፤ ውጫዊው “ ካልጠገቡ አይዘሉ፤ ካልዘለሉ አይሰበሩ “ እያለ ይለጉምሀል፤ ውስጣዊው ደግሞ አሁን ከዚህ “በሁዋላ ቀንድ አላበቅል” እያልህ የሰውነትህን እምቅ አቅም ሳትረዳ እንድትሞት ያደርግሀል፤

ታይሰን ሀያ ሚሊዮን ዶላር ይሸለማል ተብሏል፤ ቀላል ጥሪት አይደለም፤ አያትየው የልጅ ልጆቹን መጦር ይችላል፤ ባንድ ሚሊዮን ብሩ የተጠረመሱ ፥ የመንገጭላው አጥንቶቹን ያስጠግንበታል፤ የተዳጠ አፍንጫውን ያስበይድበታል፤ በቀረው ደግሞ አለሙን እንደ ጥንቅሽ ይቀጭበታል፤ ምናልባት ሳይንቲስቶች በጥቂት አመታት ጊዜ ውስጥ የእድሜ ማደሻ ቅመም መፍጠር ከቻሉ ደግሞ የመሸመት አቅሙን አዳብሯል፤

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ ደጃፍ ላይ የሚያስቀምጠውን መንፈስ በካልቾ ብላችሁ በነገው ታላቁ ሩጫ ላይ ተሳተፉ፤

ልዝብ ደሀ ቢሆን ባይኖረውም ሀብት
ታላቅ ሩጫ ላይ፥
ወልመጥ ወልመጥ ሲል። ደስ ይላል አባት🙂

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

15 Nov, 07:27


Anyone from Ethiopia can order a mastercard from bybit

https://www.bybit.com/fiat/cards?source=referral&campaignId=1686258086857150464&ref=4RRGJLB

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

13 Nov, 16:21


በመኖር አጸድ ውስጥ
(በእውቀቱ ስዩም)

ጊዜ ከሰው መሀል- መርጦ ሲያቀማጥል
ማጣት አለ ደሞ፥
የወለዱትን ልጅ፥ ጉድፍ ላይ የሚያስጥል
በተፈሰከ ቀን፥ ጾምን የሚያስቀጥል::

እድልና ትግል በሚጫወቱበት
በደልዳላው ስፍራ
አለቃና ጭፍራ-
-ቃል ሲለዋወጡ፥ ውልና መሀላ
“አብረን እናድጋለን” ቢባል ለይስሙላ
ወንዙን ሳያጎድል ፥ሐይቁ መች ሊሞላ፤

ጸሐይ ብትወጣ
ፍጥረት በጠቅላላው ጸጋዋን ቢቀበል
የደመናም ጠበል፥
ለሁሉ ቢደርስም
አንደኛው አያድግም፥ አንዱን ሳያከስም::

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

13 Nov, 05:03


(ተስፋዬ ሃይለማርያም)

ባሻዬ! አንዱ ካድሬ ሹመት ተሰጠውና ወደ አንዱ መሥሪያ ቤት በኃላፊነት ተመድቦ ሄደ። ሰውዬው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጓደኛ ለመምሰል ብዙ ይሞክራል።

አንድ ቀን ቢሮው ውስጥ ቁጭ ብሎ ሳለ የቢሮው በር ተንኳኳ። ሰውዬው ወዲያውኑ አጠገቡ ያለውን የቢሮ ስልክ አንስቶ ማውራት ጀመረ። በሩን ከፍቶ የገባው ሠራተኛ ኃላፊው ስልክ ላይ መሆኑን አይቶ ሊመለስ ሲል ሃላፊው እንዲገባ በእጁ ምልክት አሳየውና እንዲህ እያለ በስልኩ ወሬውን ቀጠለ፣

"አመሠግናለሁ ዶክተር አብይ... አዎ ልክ ነዎት ጌታዬ.... አዎ አውቃለሁ... ይህንን ኃላፊነት ሲሰጡኝ በእኔ ላይ ትልቅ እምነት አሳድረው ነው....ኧረ በፍፁም አላሳፍሮትም... አዎ ኦቦ ሽመልስ ደውሎልኝ ነበር...አዎ ወይዘሮ አዳነችም ነግረውኛል...ምንም ችግር የለም... እሺ አመሠግናለሁ ጌታዬ... እሺ እላለሁ... ለእኔም ወይዘሮ ዝናሽን ሰላም ይበሉልኝ...አመሠግናለሁ ጌታዬ ...ቻው"

ኃላፊው ይህንን ተናግሮ ስልኩን ዘጋና ቢሮ ውስጥ ቆሞ ሲያዳምጠው ወደነበረው ሠራተኛ ዞሮ በፈግታ ጠየቀው፣

"እሺ ምን ፈልገህ ነው?

"የጠቅላላ አገልግሎት ሠራተኛ ነኝ። አሁን ያወሩበት የቢሮ ስልክዎ ስለተበላሸ ለመጠገን መጥቼ ነው"

ባሻዬ! የብልጽግና ፓርቲያችንን ስም የሚያስጠፉት እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ናቸው።

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

10 Nov, 09:40


ቸርቿ ልትሸልመኝ ይገባል!
(አሌክስ አብርሃም)

አንዱ የቤተክርስቲያን ኪቦርድ ተጨዋች ትልቅ ስህተት ይሳሳታል። እሱ እንኳን ጥሩ ልጅ ነበር ፣ያ የተረገመ ሰይጣን የሆነ ቀን ኪቦርድ ከሚያስተምራት የፓስተሩ ሚስት ጋር አሳስቶት እንጅ። እሷም ጥሩ ልጅ ነበረች ዕድሜዋ ከባሏ በ22 ዓመት ከማነሱ ውጭ! እና ከማንኛውም አገልግሎት ይታገዱ በሚሉና ለዛሬ በምክር ይታለፉ በሚል ምእመኑ ለሁለት ተከፈለ። መከፈል ብቻ አይደለም በዓለም እንኳን ተሰምቶ በማይታወቅ ፣ማንም ከዚህ በፊት ባልተሳደበበት ፣ ገና በዛ ዓመት ከጥልቁ ተመርቶ ለገበያ በቀረበ ዜሮ ዜሮ ስድብ ጉባኤው ይሞላለጭ ጀመር። ከቃል አልፎ በጣት ምልክት ሁሉ እንካ እንች ምናምን እየተባባሉ። እና ልጁ በግርምት ስድድቡን ዛቻውን ሲኮመኩም ቆየ። የሱ ድርጊት ከሚያየው ጉድ አነሰበት። ሲወጣላቸው ሲረጋጉ "እሽ አስተያየትህ ምንድነው ይሉታል ንስሀ ትገባለህ ወይስ?"

ወገኖቸ ! የገረመኝ የእኔ መባለግ አይደለም። እኔኮ ስትቅለሰለሱ ስትፀልዩና ስትሰብኩ በትእግስት የጌታን መምጣት የምትጠባበቁ ነበር የመሰለኝ። ለካ እዚህ ተሰብስባችሁ ብልግናችሁን የምትተነፍሱበት አንድ ባለጌ ስትጠብቁ ነው የቆያችሁት። ሰበብ ሆንኳችሁ፣ ለዓመታት በፆሎት ያልተገለጠ አጋንንታችሁ በብልግናየ እየጮኸ ወጣ....ቸርቿ ልትሸልመኝ ይገባል😀

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

09 Nov, 18:59


ጉተታው
(አሌክስ አብርሃም)

ኤለመንታሪ ተማሪወች እንደነበርን አስማተኛ ነኝ የሚል ሰው በጆሮየ መኪና እጎትታለሁ ሃምሳ ሳንቲም ትኬት ቁረጡ እያለ ወደትምህርት ቤታችን መጣ..ማንም አልቆረጠለትም፤ እንደውም መፈንከት አምሮን ነበር። ከዛ በፊት ተታለን ነበራ! ጅል መሰልነው እንዴ?! ይህን የሰሙ ወላጆች ሁሉ ሳይቀር ተቆጡ። በኋላ እኛ ፈላወቹ የባነንበት ሰውየ ሀይስኩል ሄዶ መኪና በጆሮው እንደሚጎትት እና ትኬቱም አንድ ብር እንደሆነ ሲነግራቸው እንኳን ተማሪ አስተማሪና ወላጆች ሳይቀሩ ትኬት ለመቁረጥ ግድያ ሆነ። የተቆጡ ወላጆች ሁሉ ሐሳባቸውን ቀይረው ይጋፉ ጀመር። ግራ ገባን። እንደውም ቦታ ጠቦ ብዙ ትርኢቱን ሊመለከቱ የሄዱ ሴቶች እያዘኑ ተመለሱ። "በአጥርም ቢሆን ይሄን ጉድ እናያለን" ያሉም ነበሩ።

የገረመን ለመመልከት ከሚጋፉት ሴቶች ይበዙ ነበር። ሰውየው እውነትም አስማተኛ ነው ...ከኋላ ከፍሎ ባሰማራቸው ሰወቹ መኪናውን የሚጎትተው በጆሮው አይደለም ልጅ ፊት እንደዛ ስለማይባል ነው እንጅ በእንትኑ ...ነው የሚጎትተው" ብለው አውርተው ነበር። ህዝቡ ነቅሎ ገባ። ብለው ብለው መኪና ሊጎትቱበት? እየተባባለ። ልጆች እዛች ግድም እንዳንደርስ ተከለከልን። በኋላ ሰውየው አንዲት ታክሲ እንደምንም በጆሮው ትንሽ ጎተተ ። ህዝቡ አልተደነቀም፣ ልቡ የተሰቀለው ሌላው ጉዳይ ላይ ነበር። ቀጣዮን ለማየት አዳሜና ሂዋኔ እንደጓጓ "ትርኢቱ አለቀ" ብሎ ኩም አደረጋቸው አስማተኛው።

እንዴ እንትኑሳ?
ምኑ?
መኪናውን የምትጎትተው በእንትንህ...ነው አልተባለም እንዴ? አሉ ወደእንትኑ እየጠቆሙ።
ፈገግ ብሎ የሱሪውን ዚፕ እየነካ "በዚህማ ይሄን ሁሉ አንድ ከተማ ህዝብ ጎተትኩበት!!"😀

ይሄው እስከዛሬ እንትን ጋር የተያያዘ ወሬ እንደጉድ እየጎተተ ይሰበስበናል። እንዳለ ህዝቡ አስማት ሊያይ ኢኳቶሪያል ጊኒ ጠቅልሎ ገባኮ ጓዶች።😀 ያ የተረገመ ሰውየ በእንትኑ ጎትቶ ጊኒ አጎረን።

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

05 Nov, 14:43


እኛ የምንኖርባት ኢትዮጲያ ናት ወይስ ሌላ ?
ፖለቲከኞቹ የሚኖሩባት ኢትዮጲያ ግን ደስ ስትል።
ዜጋው መብላት ከብዶት 738 ሚሊዮን ዶላር ብድር መስጠት ትንሽ አይጋጭም?

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

02 Nov, 13:52


ከአልፎጂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ

(በእውቀቱ ስዩም)

ከብዙ መጠፋፋት በሁዋላ ፥ በቀደምለት ከምኡዝ ጋራ ተገናኘን፤ ኑሮ እና እድሜ ለውጦታል፤ ተጫዋች የነበረው ሰውየ ተነጫናጭ እና ተናዳፊ ሆኖ ቆየኝ::

አሳዘነኝ!

ገና እንደተገናኘን “ እንዴት ነው አልዘነጥሁም?” አልሁት በወፍራሙ ፈገግ ብየ ::
“ላለፉት አስራ አምስት አመታት አንድ የቆዳ ጃኬት ለብሰህ ነው የማውቅህ ፥ከቻልክ ቀይረው ካልቻልክ አስቀልመው “ ብሎ ለከፈኝ፤

የእግር ጉዞ ጋበዝኩትና ፒያሳ ስንደርስ አስፋልቱ ዳር ድንክየ የመንገድ መብራት ተተክላ ተመለከትን :
:
“ ይቺ ደግሞ ምንድናት?” ስለው ፥

“ የአብሪ ትል መታሰቢያ ሀውልት መሆን አለባት “ ሲል መለሰልኝ፤

ትንሽ እንደ ሄድን እኔ በአዲሱ የእግረኛ መንገድ ዳር የለመለመውን ሳር እያየሁ ማድነቅ ጀመርሁ ፤” አሁን ደሞ በሳሩ ላይ የወተት ላም ቢያስማሩበት ጥሩ ነው፤ “ አለ ምኡዝ ::

“ ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም፤ ድሀ የአካባቢ ውበት አይወደለትም ያለህ ማንነው “ ብየ ሞገትኩት፤

እጁን በንቀት አወናጨፈና “ ለነገሩ አንተ የዘወትር ጎመን ተመጋቢ ስለሆነህ ሳር ግጣችሁ እደሩ ቢባል ሽግግሩ ብዙ የሚከብድህ አይመስለኝም”

አራት ኪሎ በስላሴ ትዩዩ ባለው መንገድ ስንደርስ ምኡዝ አንዲት አልፎሂያጅ ሴት አስቆሞ ጀነጀነ፤ “አላማ “አለኝ ብላ ፊትም ደረትም ነሳችው፤ “ከአራት የመሬት መንቀጥቀጥ እና ከሁለት የእርስበርስ ጦርነት ለጥቂት ተርፈሽ ስለ ምን አላማ ነው የምታውሪው? “ሲላት ጥላው ሄደች፤

በመልስ ጉዞአችን ላይ ከቀበና ድልድይ ስር በሚገኘው ፓርክ ውስጥ ወጣት ፍቅረኛሞች ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፈው ሲያጠኑ ተመለከትን፤ ምኡዝ የድልድዩን አግዳሚ ተደግፎ ቁልቁል እያያቸው ” ይሄንን መናፈሻ “መፈሳፈሻ “አደረጋችሁት አይደል?” ብሎ ቆሊያቸውን ገፈፈው፤

ሰፈር ስንደርስ ፥ምግብ ቤት ገብተን ምሳ አዘዝን፡ ፡
ከፊትለፊታችን አንድ የማውቀው የሰፈራችን ልጅ ቁጭ ብሎ ሻይ ይጠጣል፤
ሲያፈጥብን “እንብላ “ ብየ ጋበዝኩት::
ልጁ ብዙ ሳይግደረደር ወንበር ስቦ ማእዱ ላይ ተጣደ፤

እኔና ምኡዝ እየበላን በአፍሪካ ቀንድ ዙርያ ይከሰታል ስለተባለው የመሬት መንሰንጠቅ መወያየት ጀመርን ::
ተጋባዡ የጥያን ደንጋይ የሚያክል ጉርሻ የዳጠውን ጉሮሮውን እህህ ብሎ ካጸዳ በሁዋላ፤

“ የመሬት መሰንጠቁ የሚከሰት ከሆነ፥ ኢትዮጵያ የባህር በር ብቻ ሳይሆን የባህር መስኮት ይኖራታል” አለ፤

ይኸኔ ምኡዝ በንዴት ፤-

“እጅህን የሰነዘርከው አንሶህ ሀሳብ ትሰነዝር ጀመር ! ተነስ!”

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

28 Oct, 08:56


ያከሸፈቻቸው ያከሸፏት አገር!
(አሌክስ አብርሃም)

የ8ኛ ክፍል ተማሪወች እንደነበርን ነው። አንድ ቀን የሆነ አስተማሪ ቀረ። በዛ ክፍት ክፍለጊዜ ሁላችንም ደስ ያለንን ስንሰራ (አብዛሀኞቻችን ወሬና መንጫጫት) አንድ ምስጋናው? የሚባል ስዕል መሳል የሚችል የክፍላችን ልጅ ብላክቦርድ ላይ በወዳደቀ ቾክ ሁለት ሰወችን ሳለ። ስዕል ስላችሁ ይሄ ዝም ብሎ የልጅ ስዕል አይደለም፣ ባስታወስኩት ቁጥር የሚገርመኝ የፊታቸው መስመር፣ ፊታቸው ላይ ያረፈው ጥላ፣ ልብሳቸው ላይ ያለው ፓተርን እና ጌጣጌጥ ሳይቀር ፎቶ የሚመሳስሉ ፖርትሬቶች። ደግሞ የሳለው ምንም እያየ አልነበረም። እማሆይ ቴሬሳ ሁለት እጆቻቸውን እንደህንዶች ሰላምታ አገናኝተው ግንባራቸውን እንዳስነኩ እጃቸው መሀል መቁጠሪያ ተንጠልጥሎ፣ እንዲሁም ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ከነንጉሳዊ ልብሳቸው ወደጎን ዞር ብለው። ሁላችንም ተገረምን ተደነቅን። የስእሎቹ መጠን የእውነት ሰው ያካክሉ ነበር።

ቀጣዮ ክላስ ጅኦግራፊ ። ኮስታራው አስተማሪያችን ገባና ስዕሎቹን አየት አድርጎ "ማነው የሳለው?" አለ ። በአንድ አፍ "ምስጋናው" አልን በአድናቆት ጭምር። ራሱ ወደምስጋናው ወንበር ተራምዶ ለአንድ ክፍል ልጅ የያዘው ልምጭ ተሰባብሮ እስከሚያልቅ ቀጠቀጠው። ምስጋናው በህመም ተንሰፈሰፈ። እና በቁጣ "ይሄ የተከበረ የትምህርት ገበታ ነው ! ማንም እየተነሳ የሚሸናበት አይደለም፤ ደደብ!" ብሎ ደነፋ። ዳስተሩን አንስቶ አንዴ እጁን ሲያስወነጭፈው ሀይለስላሴን ለሁለት እማሆይ ቴሬሳን አናታቸውን ገመሳቸው። አጠፋፍቶ ማስተማሩን ቀጠለ። ምስጋናው ከዛ በኋላ እንኳን ሰሌዳ ላይ ወረቀት ላይ ሲስል አላስታውስም።

ብዙ ዓመታት አለፉ። አንድ ቀን አዲስ አበባ ፒያሳ መርከብ የምትባል ምግብ ቤት ምሳ በልተን ስንወጣ በር ላይ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ በፌስታል ፍርፋሪ ሲበላ አየሁ ምስጋናው ነበር። ቢጎሳቆልም አልጠፋኝም። ዛሬ በምን አስታወስኩት? አንድ አሜሪካዊ ህፃን ሰሌዳ ላይ በቾክ የሳለው ስእል በአስተማሪዎቹና በትምህርት ቤቷ ርዕሰ መምህር ስለተደነቀ በቀስታ ሰሌዳውን አንስተው አንድ ቢሮ ግድግዳ ላይ እንደሰቀሉት አነበብኩ። ስዕሉ ለዓመታት እንዲቆይ የሆነ ነገር እናስደርጋለን ብላለች ርዕሰ መምህርቷ። አገር ባከበረቻቸው ትከብራለች ባከሸፈቻቸው ትከሽፋለች። ይህ ሒሳብ የገባቸው ብፁአን ናቸው። ለትውልድ ፍቅር ያወርሳሉና።

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

27 Oct, 05:58


ከ150 አመት በኋላ ዛሬ በህይወት ካለነው ሰዎች አንዳችንም በህይወት አንገኝም።

ዛሬ ላይ ከምንታገልላቸው ነገሮች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ150 አመት በኋላ አንዳቸውም ለምልክት እንኳ አይገኙም፡፡ ፈጽመው ይጠፋሉ ይረሳሉ፡፡

እስኪ ወደ ኋላ 150 አመት እንሂድ፡፡ ወቅቱ 1872 ገደማ ነው የሚሆነው፡፡ ያኔ የሰው ልጅ እንደ እቃ በአደባባይ ተደርድሮ የሚሸጥበት ወቅት ነበር፡፡

በወቅቱ ብርቅ የነበረውን የፊት መስታወት ለማግኘት ሲሉ የገዛ ዘመዶቻቸውን የሸጡ ሰዎች ዛሬ የታሉ?

መስታወትንስ ዛሬ ላይ እንደ ሀብት የሚያስበው ማን ነው?

ማንም ጨው ወይም ጌጥ ወይም ሌላ ነገር ለማግኘት ሲሉ የተሻሻጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡

ዛሬ ላይ እነዚያ ሰዎች የሞቱላቸው የገደሉላቸው የተካካዱባቸው የተሻሻጡላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ይህ ነው የሚባል የረባ ዋጋ ያላቸው አይደሉም፡፡

በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት ነበሩ፡፡

የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ በጣም የሚያስቁ ናቸው፡፡

አሁን አሁን ላይ ዘመኑ የኢንተርኔት በመሆኑ ኢንተርኔት ትዝታችንን ያስቀምጥልናል ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ግን ይህም አስተማማኝ አይደለም።

#ማጠቃለያው
ህይወትን ቀለል አርገህ ኑር፡፡ ምንም ሆነ ምንም ዘላለም የሚኖር የለም፥ ከዚህች ምድር በህይወት የሚወጣ ሰውም የለም፡፡

ዛሬ ልትሞትለት እና ልትገድልለት የተዘጋጀኸው መሬት ከዚህ ቀደምም ብዙዎች ተጋድለውለት ሞተው ጭራሽ እንዳልነበሩ ሁሉ ተረስተዋል፡፡

ከ150 አመታት በኋላ ዛሬ አንተ እንደ ትልቅ ሀብት የምታያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡

እና ምን ለማለት ነው ፥ ፍቅር ይግዛን ፥ መጠላለፍ ከጀርባ መወጋጋት መቀናናት መፎካከር ይቅርብን፡፡ ህይወት ከማንም ጋር የምታደርገው ፉክክር አይደለችም፡፡

ቀደምንም ዘገየንም መጨረሻችን መቃብር ነው፡፡

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

26 Oct, 17:13


ልስን ድሃ
(አሌክስ አብርሃም)

የዛሬን አያድርገውና "ያጣ የነጣ" የሚለው አባባል ድሃና ድህነትን የሚገልፅ አባባል ነበር። አሁን ላይ በተለይ የከተማ ድሃ ያጣል ግን አይነጣም። ከምግብ ሳይሆን ከሜካፕ እና ከፊልተር በሚፍለቀለቅ ወዝና ውበት በአካልም በሚዲያም እያማረ ይራባል። ድሃ ነው ግን አይነጣም ፣አይገረጣም። ሜካፑና ገፅታው እንዳይበላሽ የሚያለቅሰው ወደውስጡ ነው። ይህ ውበት የነጣና ያገጠጠ ድህነትን ከላይ በሚያብረቀርቅ ነገር በመለሰን የሚሸፋፍን ሲበዛ አሳሳች ውበት ነው። አንዳንዴ ባለቤቱን ራሱን ጭምር ይሸውዳል።

ልክ እንደመቃብር ሃውልት የውጩ ውበት የውስጡን አፅም ይሸፍንብናል። በዛ ላይ ሀውልቱ ላይ የሚፃፈው የተጋነነ ታሪክና የሚለጠፈው ፎቶ ለሟች ከማዘን ይልቅ በሀውልቱ እንድንደመም ያደርገናል። የሟች ቤተሰቦች ከሟቹም በላይ አንጀታቸውን አስረው ለሀውልት ባወጡት ወጭ ያለቅሳሉ። መፅሐፉ "እናተ በኖራ የተለሰናችሁ መቃብሮች ናችሁ" ያለውኮ እንዲህ ያለው የውስጥና የውጭ ባህሪ አልገጥም ቢለው ነው። ነገሩ ግለሰባዊ ብቻ አይደለም ከተሞችም ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው። ለምሳሌ አዲስ አበባን ተመልከቱ። በመብራት፣ በቀለም፣ በህንፃ ተለስና ስትታይ ከምድራችን የድሃ ድሃ አገራት የአስከፊዋ ድሃ አገር ዋና ከተማ ትመስላለች? የድሀ ድሀ ፣ ልዝብ ደሃ፣ መራር ደሃ ከሚሉት ማዕረጎቻችን በተጨማሪ " ልስን ድሃ" የሚል የድህነት ደረጃ ጨምረናል።

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

21 Oct, 14:48


😂🤣🤣🤣😭😭A handsome man went into a hotel and asked to see the boss. When the boss came, the story began.

-The client: is room 39 empty?
-The boss: yes, sir.
-The client: can I book it?
-The boss: of course you can.
-The client: thank you.

Before going to the room, the client asked the boss to provide him with a black knife, a white thread 39 cm and an orange 73g.

The boss agreed though he was surprized at the weird things the client asked to have.

The client went into his room, he didn't ask for food or anything else.

Unfortunately for the boss, his room was next to room 39.

After midnight, the boss heard strange voices and noise in that client's room. Voices of wild animals and of utensils and dishes being thrown on the floor.

The boss didn't sleep that night. He kept thinking and wondering what might be the source of the noise.

In the morning, when the client handed the keys to the boss, the latter asked to see the room first.

He went to the room and found everything alright. Nothing unusual. He even found the thread, the black knife and the orange on the table.

The client paid the bill and gave the bellboys a very good tip and left the hotel smiling.

The boss was in a shock but he didn't reveal what he heard to the bellboys. In fact, he started to doubt himself.

After one year, the client showed up again. He asked to see the boss again. The boss was in a puzzle.

The client asked the same things: room 39, black knife, white thread 39cm and an orange 79g.

This time, the boss wanted to know the truth by all means possible. He spent a sleepless night, waiting for something to happen. After midnight, the same voices and noises started, this time louder and more indecipherable than the year before.

Again, before leaving, the client paid his bill and left a large tip on the table for the bellboys. The smile didn't leave his face.

The boss started searching for the meaning of everything the client asked to have. Why did he ask room 39? why the white thread? why the black knife??? In fact, the boss didn't arrive to any convincing answer to all these questions.

The boss now was eagerly waiting for the month of March, the month in which the client showed up.

To his surprise, on the first day of March, the same client showed up. He asked the same questions. Wanted to book the same room, wanted to have the same things as before.

The boss again heard the same noises, this time more louder than before.

In the morning, when the client was leaving the hotel, the boss apologized politely to the client and asked to know the secret behind the noises in the room.

-''If I tell you the secret, do you promise to never reveal it to anyone else?''
-''I promise I will never let anyone know''.
-''Swear''
-''I swear I won't reveal your secret''
So finally, the client revealed his secret to the boss.

Unfortunately, the boss was a sincere person. Until now he hasn't revealed his secret to anyone.

When he does, I will let you know... thank you for reading.

Do you want to come and bëãt me?

Me too, I'm looking for the guy who sent me this! 😆😆😳😳🕺🕺

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

20 Oct, 06:57


በዜሮ ...
(አሌክስ አብርሃም)

አንድ ጓደኛየ መንጃ ፈቃድ አውጥቶ መኪና መንዳት በጀመረ በመጀመሪያው ቀን በሰላም በእግሬ ከምሄድበት ጠራኝና
"ና ግባ አደባባዮን ላሻግርህ" አለኝ
"ግዴለም በእግሬ እሻገራለሁ" አልኩ። ነዝንዞ አስገባኝና ጋቢና አስቀመጠኝ። መንግስትና ህዝብ ንዳ ብሎ ፈቃድ ከሰጠው እኔ ማነኝ ችሎታውን የምጠራጠር ብየ ተመቻቸሁ። ገና በሩን ከመዝጋቴ ስለመኪና ባህሪና ስለአነዳድ ቴክኒክ ልቤ እስኪደክም ያስረዳኝ ጀመር። ያለምንም ዓላማ ከተማችንን አንድ ጊዜ አዞረኝ። እስከዚህ ደህና ነበር። "ይሄ ፍሬን ይባላል፣ ድንገተኛ ነገር ሰው ፣ አህያ ወይም የተናኘ ባል የሚነዳው መኪና ቢገቡብህ ማቆሚያ ነው" አለና አጎንብሶ ፍሬኑንን ይፈልግ ጀመረ...(ተናኘ ሹፌር ያገባች የቀድሞ ፍቅረኛው ናት ከነቂሙ ነው መንጃ ፈቃድ የያዘው) "ፍሬኑን እስክትፈልግ ግን ....ከማለቴ ፍሬኑን አግኝቶ ባለ በሌለ ሀይሉ ረገጠው። ወደፊት ተወርውሬ የሆነ ነገር ጋር ተጋጭቸ ተመለስኩ። ዘና ብሎ "አሁን የገጨኸው ዳሽ ቦርድ ይባላል የትም አገር የሚያጋጥም ነገር ነው" አለና ቀጠለ። ደረቴን ደግፌ እያሳልኩ ዝም አልኩ።

ብቻ እንዲህ አሰቃይቶኝ በመጨረሻ "አንዲት ብዙ ሹፌሮች ያልባነኑባት ቴክኒክ ላሳይህ ወደፊት ይጠቅምህ ይሆናል" አለኝ። ወይ እዳየ። ከዚህ ሁሉ ለዓመታት የነዳ ሹፌር ተደብቆ ገና በአንድ ቀን ምን ተገልጦለት ይሆን እያልኩ ሳስብ በከተማችን አለ ወደሚባለው ቁልቁለት መንገድ ወሰደኝና "አሁን እዚህ ቁልቁለት ላይ ሞተሩን ታጠፋውና በዜሮ ትሄዳለህ ...መሪዋ ላይ ብቻ መጫወት ነው...ነዳጅ አተረፍክ ማለት ነው አባቴ" ብሎ ትልቅ ግኝት እንደነገረኝ አይነት በኩራት ሀሀሀሀሀ ብሎ ሳቀ። እኔ ግን ነፍሴ ተጨነቀች። መኪናው ወደታች ፍጥነት እየጨመረ መምዘግዘግ ጀመረ ። ወገኖቸ ባጭሩ ፍሬን ቢረግጥ ምን ቢረግጥ (እኔን ሁሉ እግሬን ቢረግጥ) መኪናው አልቆምም አለ። አታምኑኝም ዞር ስል የሹፌሩ በር ተከፍቶ አጅሬው ሲዘል ተገጣጠምን። ለደይቃወች ራሱን በሚነዳ መኪና ከተጓዝኩ በኋላ .... መኪናዋና እኔ ለግንባታ ፒራሚድ መስሎ የተከመረ አሸዋና ጠጠር ክምር ጫፍ ላይ ጉብ አልን። እዚህ ቴውድሮስ አደባባይ ያለውን የአፄ ቴውድሮስን የመድፍ ሀውልት ነበር የምንመስለው።

አሁን ያለንበትን የኑሮ ሁኔታ ሳየው፣ የሆነ ቴክኒክ ላሳያችሁ ብሎ ያሳፈረን ሹፌር ዘሎ የወረደ እስኪመስለኝ ቀላል እየተምዘገዘግን ነው?! ብቻ ማረፊያችንን ያሳምረው። ለእኔ በነጠላው የደረሰ አምላክ በጅምላ ይድረስልን።

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

19 Oct, 19:39


መዘበራረቅ
(አሌክስ አብርሃም)

ዝብረቃ 1.

ተኝታችሁ ከተስማማችሁ በኋላ ተንበርክካችሁ "ታገቢኛለሽ?" ማለታችሁ ትንሽ የቅደም ተከተል ችግር አለበት ልበል? ለፆለት የሚንበረከከው ወንድ ከዚህኛው መንበርከክ በቁጥር እያነሰ መምጣቱ እንዳያስቀስፈን ጓዶች።

ዝብረቃ 2.

ፊልሙን ለመስራት 1.5 ሚሊየን ብር አወጣን ካላችሁን በኋላ የዋናዋ ገፀ ባህሪ ሰራተኛ እህት ልጅ ሁና የተወነችው እንስት የሽልማት መድረኮች ላይ 2.666 ሚሊየን ብር የፈጀ ቀሚስ(አውትፊት ይሉታል) ለብሳ የምትታይበት ሳይንስ ትንሽ ግራ ያጋባል። አንዳንዴ በውበትም በዋጋም ከፊልሙ የሚበልጥ ቀሚስ ስናይ የልብስ ሰፊወች አዋርድ እየመሰለን ተቸግረናል። ለነገሩ የትም አለም የተለመደ ነው።

የውጭ ዝብረቃ 3.

ኤለን መስክ የሚባል በቴክኖሎጅ ፍቅር ልብሱን ጥሎ ያበደ ሰውየ፣ የሆነ መሪ የሌለው መኪና እያስተዋወቀ ነው። በዓለም የመጀመሪያው ካለመሪ የሚንቀሳቀስ መኪና ነው አለ። እንኳን መኪና እእእእእ 😀 እሽ ይሁን። የሆነ ሆኖ መኪናው እናንተ ቤታችሁ ተቀምጣችሁ ብቻውን ሄዶ ኡበር /ታክሲ/ ይሰራል ይሸቅላል ሲል ነበር። እና ሮቦቶች የሰወችን ስራ አይነጥቁም? ሲባል ምናለ? ይንጠቋ! ሮቦቶች ይሰራሉ ሰወች ዘና ብላችሁ የኪስ ገንዘብ እየተሰጣችሁ ትኖራላችሁ። ከመጠግረር ምን አላችሁ? የምርጫ ቅስቀሳ የመሰለ ነገር።

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

17 Oct, 10:19


እንደምን ሰነበታችሁ ወገኖቸ?
(አሌክስ አብርሃም)

ቆይ ቆይ በየተራ ተናገሩ ምንድነው ለመርዶ እንዲህ መጣደፍ?! ስለኑሮው ሰምቻለሁ። ሶስት ሽ ዘመን የተኛ ኑሮ ምን እንዲህ አስፈንጥሮ እንዳስነሳው አልገባህ ብሎኛል። መነሳቱን ይነሳ ትንሽ እንኳን ሳይረጋጋ አይኑን እንደገለጠ ልብሱን እንኳን ሳይለብስ ሩጫው።

ሰው ልሸኝ ብየ በነጠላ ጫማና በቱታ እዚች ጋ ወጣ ብየ ስመለስኮነው ሶስት የመሬት መንቀጥቀጥ፣ አንድ የመሬት መንሸራተት፣ ሁለት ከተማ የሚያካክሉ ታሪካዊ ሰፈሮች መፈራረስ፣ አንድ ታሪካዊ የፖለቲካ ፓርቲ መንፈሽፈሽ ፣ አራት " እንደጦር የሚዋጋ የዋጋ ማስተካከያ" ሁለት ፌክ እና ሶስት የእውነት ታዋቂ ሰዎች ሞት፣ቁጥር ስፍር የሌለው ጦርነት፣ ሁለት "እንኳን ደስ አላችሁ" ፣ ወደሁለት አገር አየር መንገዳችን እንዳትመጣብን ጭቅጭቅ፣ የግብፅ ጦር ተግተልትሎ እዚህ አፍንጫችን ስር መምጣት...ጨምሩበት! የዛሬን አያርገውና ይሄኮ በአራት ትውልድ እንኳ ሊከሰት የማይችል ነገር ነበር። የሆነ ሆኖ ምናባቴ ልሰራ ነው ወደ ሶሻል ሚዲያ የተመለስኩት እስከምል ደህና ተዘባርቃችሁ ጠብቃችሁኛል። እስኪ አብሬ ልዘባረቅ😀

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

16 Oct, 14:58


እንደ ሰርከስ
(በእውቀቱ ስዩም)

መኖር በሀገርህ
የሰርከስ ትርኢት እንደማሳየት ነው
ስልጠናው ሳይኖርህ ::

በሚያድጥ ዳገት ላይ ፥በብጤህ መጋለብ
በሁለት መዳፎች፥ ሳይፎርሹ መቅለብ
-ደርዘን ሙሉ አሎሎ፥
አሎሎ ቢጠፋ ፥እሾህ ተደብልብሎ
በሳት ቀለበት ውስጥ ፥ማለፍ ሹልክ ብሎ፤

እንደ ህልም እሪታ፥ በሰለለ ገመድ
ባንድ እግር መራመድ፤

ይሄን ሁሉ አድርገህ፤ ትርኢቱም አልቆ
ካጥንቶችህ መሀል፥ አንዱ ተሰንጥቆ
አንደኛው ደንድኖ
እንደ በላኤ ሰብ፥ እጅህ ወንፊት ሆኖ፤

ምንም ባትታደል፥ አንቱ የሚባል ስም
አሞጋሽ ለክብርህ፥ ነጋሪት ባይጎስም
ምናልባት ካተረፍክ-
ያልተራገፈ ጥርስ ፥ያልተሰበረ ቅስም
የድል ሳቅህን ሳቅ፥ በተረፈው ጥርስህ
በወንፊት መዳፍህ፥ አጨብጭብ ለራስህ::

https://t.me/matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

15 Oct, 17:34


በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ፡፡

ግን እኔ ብቻ ነኝ መንግስት ምንም እያመጡም የሚል እልክ ውስጥ የገባ የሚመስለኝ🤔

@matter_of_facts

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

11 Oct, 17:55


ሰሞኑን የማነባቸው ዜናዎች .....

ኢትዮ ቴሌኮም ባንዳንድ አገልግሎቶቹ ላይ የታሪፍ ማስተካከያ አደረገ።

የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ተደረገ።

መንግስት ዋጋ ሲጨምር ማስተካከል ነው የሚባለው ማለት ነው🤔

https://t.me/matter_of_facts