Dr Abiy Ahmed Daily @drabiyahmeddaily Channel on Telegram

Dr Abiy Ahmed Daily

@drabiyahmeddaily


We will provide everything prime minister Dr Abiy Ahmed posts in his official social media and some important Gov't notifications!

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ በማህበራዊ ገፃቸው ያጋሩትንና የለቀቁትን እንዲሁም አንዳንድ ወሳኝ የመንግስት ኦፊሺያል መልክቶችን በዚህ ቻናል ያገኛሉ!!

N.B it is not official

Dr Abiy Ahmed Daily (Amharic)

የዕለተዋጋችን ክፍል በሰሓበኛው ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተሾመ ስልክ ነው፡፡ በዚህ ቦታ የሚያስተምርና ስናንቲፕያዎችን በእነርሱ መጨረሻ ለመግባት ክፍልን ለመከታተል ይህንን ቦታ እንዲቀጣለን የሚለውን መረጃ እንሰጣለን። የመነሻው ክፍል - drabiyahmeddaily በገላብተው የሚመጣውን ሁኔታንና አገልግሎት ፈቃድን ከማወቅ ታማኝ ቦታ ነው። ከኦፊሺነው ነገር እያየን አሁን አንዲፈው ለዚህ ቦታ የተለያዩ የአስተዳዳሪ ችግሩን በአግባብ ይኖርን። ከጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ በማህበራዊ ገፃቸው ያጋሩትንና የለቀቁትን እንዲሁም አንዳንድ ወሳኝ የመንግስት ኦፊሺያል መልክቶችን በዚህ ቻናል ያገኛሉ። ም.ብ: ይህ ቢሮዎች አንዱን መገኘት አስተያየት አስፈላጊ ነው።

Dr Abiy Ahmed Daily

13 Apr, 17:23


ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት መጽሐፍ ለሚለግሱ ግለሰቦች ምስጋናዬ የላቀ ነው። ዛሬ በአብርሆት ቤተ መጻሕፍት በነበረን መርሐ ግብር ፣ በእንግሊዝ ሀገር በትምህርት ላይ የምትገኘው ወጣት ቤተልሔም ሰሎሞን 5200 መጻሕፍት ከእንግሊዝ አምጥታ ማስረከቧ ለሌሎች አርአያ የሚሆን ነው። በጠቅላይ ሚኒስተር ጽህፈት ቤት አንድ ዐቢይ ኮሚቴ ያዋቀርን ሲሆን ከቀናት በኋላ ለአንድ ወር የሚቆይ የመጻሕፍት ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ይኖረዋል። በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምንገኝ ወገኖች በመጻሕፍት ማሰባሰቢያ ወር የመጻሕፍት ልገሳ ለማድረግ እንዲዘጋጅ፣ ለትውልድም ዕውቀት እንዲለግስ ጥሪ አቀርባለሁ።

Namoota dhuunfaa Mana Kitaabaa Abirihootiif kitaaba Arjoomaniif galatnikoo guddaadha. Sagantaa har'a Mana Kitaabaa Abirihootitti raawwanneen shamarreen biyya Ingilizitti barnootarratti argamtu, Beteliheem Salamoon Ingilizirra kitaabota 5200 fiddee arjoomuunshee warra kaaniif fakkeenya kan ta'udha. Waajjirri Ministira Muummee kitaaba walittiqabuuf koree olaanaa tokko kan hundeesse yoo ta'u, guyyoota muraasa booda qophii kitaaba walittiqabuu ji'a tokkoof turu ni jalqaba. Warri biyya keessas ta'e biyya alaa jirru ji'a kitaaba walittiqabuu kana keessa kitaaba arjoomuuf haa qophoofnu. Dhalootaaf beekumsa akka arjoomnun dhaama.
@DrAbiyAhmedDaily

Dr Abiy Ahmed Daily

02 Oct, 09:10


ባሳለፍነው የ #አረንጓዴዐሻራ ወቅት የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ ላይ ለሚገኙት ሁሉ አድናቆቴ ይድረስ። ባለፈው ዓመት ተክለናቸው ከጸደቁልን ችግኞች የተሻለ የጽድቀት መጠን እንድናገኝ ሁላችንም የተከልናቸውን ችግኞች መንከባከብ አለብን።

Warra biqiltuuwwan #AshaaraaMagariisaa yeroo darbe dhaabaman kunuunsaa jiran hundaaf galannikoo haagahu. Hamma isa bara darbe dhaabnee qabate caalaa akka qabtuuf hundi keenya biqiltuuwwan dhaabne kunuunsuu qabna.

Appreciating all who are maintaining and looking after seedlings planted in the recent #GreenLegacy season. To surpass the survival rate we achieved last year, it will take all of us taking care of what we planted. @DrAbiyAhmedDaily

Dr Abiy Ahmed Daily

30 Sep, 05:55


የሐሳብ ልዕልና ምልክት፤ የሰላማዊ ትግል አርአያ፣ ላመኑበት ነገር እስከ መጨረሻቸው ሞጋች፣ ላመኑበት እውነት ብቻ የሚቆሙት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በማረፋቸው ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል። ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን እመኛለሁ።
@DrAbiyAhmedDaily

Dr Abiy Ahmed Daily

29 Sep, 17:30


የተከበሩ የኩዌት ገዢ ልዑል ሼክ ሰባህ አል አሕመድ አል-ጃበር አል-ሰባሕ በማለፋቸው ኀዘን ተሰምቶኛል። ለቤተሰባቸው እና ለመላው የኩዌት ሕዝብ መጽናናትን እመኛለሁ።

Hoogganaan Kuweet, Sheek Saabah Al Ahmad Al-Jaber Al-Saabah lubbunsaanii du'aan boqochuutti gaddeera. Maatiisaaniifi uummata Kuweet hundaaf jajjabinan hawwa.

I would like to express my condolences on the passing of His Highness the Emir of Kuwait, Sheikh Sabah Al Ahmad Al-Jaber Al-Sabah. Comfort to the family and the People of Kuwait.
@DrAbiyAhmedDaily

Dr Abiy Ahmed Daily

29 Sep, 10:11


በሀገር ደረጃ ዓለም አቀፉን የጤና ቀውስ እንዲሁም በርካታ የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመቋቋም እየተረባረብን ነው። በዚህ ወቅት፣ ከክልል አቻዎቻቸው ጋር ተባብረው የበረሃ አንበጣን ለመከላከል በከፍተኛ ጥረት ላይ ለሚገኙት የፌደራል ተቋማት ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።

Sadarkaa biyyaatti rakkoo fayyaa idil-addunyaa, akkasumas balaawwan uumamaa hedduu dandamachuuf tumsaa jirra. Dhaabbilee federaalaa yeroo kanatti gitootasaanii naannoo waliin ta'uudhaan awwaannisa gammoojjii ittisuuf carraaqqii olaanaa taasisaa jiran galateeffachuun barbbada.

As we address a global health crisis and various natural disasters we are confronted with as a nation, I would like to recognize the efforts of Federal institutions working collaboratively with regional counterparts in fighting desert locust. @DrAbiyAhmedDaily

Dr Abiy Ahmed Daily

27 Sep, 08:49


የመስቀል ደመራ አከባበር ሥነ ሥርዓት በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ ላደረጋችሁ ተቋማት እና ግለሰቦች ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። የጸጥታው ዘርፍ ያደረገው ጥረት፣ እንዲሁም ዜጎች በሰላማዊ መንገድ በዓሉ እንዲከበር ያሳዩት ሥነ ምግባር እና ቆራጥነት በአርአያነት የሚጠቀስ ነው። ወጣቶች ለበዓሉ ድምቀትና ሰላም ያሳዩትን ትጋት በሌላም ነገር እንደሚደግሙት አምኛለሁ። ሰላማችንን ለመጠበቅ እና ለማስጠበቅ ተባብረን እና ተቀናጅተን ከመሥራት የተሻለ ውጤታማ መንገድ የለም። በድጋሚ መልካም በዓል::

Dhaabbileefi namoota ayyaanni Damaraa Masqalaa nagaan akk xumuramu gootaniif galannikoo isin haa gahu. Ayyaanichi karaa nagaatiin akka kabajamu Carraaqqii qaamoleen nageenyaa gootaniifi namusni uummanni argisiise kan akka fakkeenyaatti ilaalamudha. Dhamaatii dargaggoonni ayyaanichi akka miidhagu mul'isan waan biraa irratti akka dabalamun amana. Nagaa keenya eeguufi eegsisuuf waltaanrefi qindoomnee hojechuun alaa waan caalu hinjiru. Irra drebiidhaan ayyaana gaarii.

Thank you to all institutions and individuals involved who enabled the Meskel Demera celebrations to pass peacefully. The efforts of the security sector together with the discipline and commitment to peace shown by youth is exemplary. Let us continue building on this collaborative and concerted effort to guard our peace. Happy Meskel holiday once again.
@DrAbiyAhmedDaily

Dr Abiy Ahmed Daily

26 Sep, 11:51


የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ በ1954ቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅ ላይ የተደረገውን ማሻሻያ፣ የግልግል ዳኝነትን እና የዕርቅ አሠራር ሥነ ሥርዓት ረቂቅ አዋጅ እንዲሁም የአክሬዲቴሽን አገልግሎት ክፍያ ረቂቅ ደንብን ጨምሮ በልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ዐበይት ውሳኔዎችን አሳልፏል። በተለይም የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጁ መሻሻሉ በፌደራል ሥርዓት ውስጥ የሚና እና የኃላፊነት ክፍፍል በአግባቡ እንዲከናወን የሚረዳ ወሳኝ ርምጃ ነው።

Today the cabinet endorsed key decisions which include a critical revision to the 1954 national criminal law procedure and evidence code; a draft proclamation to provide for arbitration and dispute resolution working procedures and lastly an accreditation service fee regulation. The revision of the criminal law procedure in particular is a milestone that pays heed to the division of roles and responsibilities in a Federal system.
@DrAbiyAhmedDaily

Dr Abiy Ahmed Daily

25 Sep, 12:05


ገሩበትና ብሩህ ተስፋ የሚበሰርበት እለት ነው። ቤተሰብ ተሰባስቦ በደስታ የሚያሳልፈው፣ ስለ ቀጣዩ ጊዜ የሚመካከሩበት፣ ልጆች ከወላጆቻቸው ምርቃት የሚቀበሉበት፣ ማኅበረሰባዊ ዕሴት የሚጠናከርበት ዕለት ነው።

ይሄንን ሀገራዊ አንድነትና ትብብራችንን የሚጠናከርበት የመስቀል በዓልን ስናከብረው ከመብላት ከመጠጣቱ ጎን ለጎን የበዓሉን ሰሞን ቁም ነገር የምናከናውንበት እንዲሆን በዚሁ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ። በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በሰው ሰራሽና በተፈጥሯዊ አደጋዎች ምክንያት ችግር ላይ የወደቁ፣ በድንገተኛ ጎርፍ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን አስታዋሽ ይፈልጋሉ። ስለዚህ ከበዓሉ ጎን ለጎን የተቸገሩትን ከጎናችሁ አለን ልንላቸው፣ የድጋፍ እጃችንን ልንዘረጋላቸው ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል። ከዚህ ባለፈ ወቅቱ አንዳንድ ሰብሎች አፍርተው ለመሰብሰብ ዝግጅት የሚጀምሩበት ወቅት እንደመሆኑ መጠን በቀጣይ ሳምንታት አርሶ አደሩን ለማገዝ፣ በዝናብ የሚበላሽ ሰብል እንዳይኖር ተጠቃሎ እህሉ ጎተራ እስኪገባ ድረስ ከጎናቸው ሆነን ርብርብ ለማድረግ ከወዲሁ ልናስብበትና ቅድመ ዝግጅት ልናደርግ ይገባል።

በመጨረሻም፣ ችላ በማለታችን የተነሣ የመስፋፋቱ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የኮሮና ወረርሽኝ እንደ ሀገር እያደረሰብን ያለው ችግር ለመቀነስ የየበኩላችንን አስተዋጽኦ ከማበርከት መቦዘን የለብንም፡፡ በዓሉንም ስናከብር የበሽታው ሥርጭት ከሚጨምሩ ድርጊቶች በመቆጠብና ተገቢውን የጥንቃቄ ርምጃዎች ተግባራዊ በማድረግ እንዲሆን እያሳሰብኩ በዓሉ የሰላም፣ የመረዳዳትና የመተጋገዝ እንዲሆን እመኛለሁ።

በድጋሚ እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራ፣ ተከብራና በልጽጋ ለዘላለም ትኑር!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 15፣ 2013 ዓ.ም
@DrAbiyAhmedDaily

Dr Abiy Ahmed Daily

25 Sep, 12:05


እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!

በክርስቲያኖች ዘንድ መስቀል የድልና የፈተና ምልክት ነው። አባቶቻችን ያለ ፈተና ክብር አይገኝም ይላሉ። መስቀሉም በአንድ በኩል እስከ ሞት የሚደርስ መሥዋዕትነትንና ፈተናን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ማንም ሊያስቀረው የማይችለውን ድል አድራጊነትን ያስታውሰናል። ሀገር ልቃ እንድትወጣ በሁለቱም ውስጥ ታልፋለች። በፈተናና በድል ውስጥ። ፈተናው ብቻ ቢሆን ተስፋ በቆረጥን ነበር። ግን ድል እንዳለ ስለምናምን መከራውን ተቋቁመን እናልፈዋለን። ድል ብቻ ቢሆንም ተዘናግተን በተቀመጥን ነበር። የምትፈለፈል ቢራቢሮ ከዕንቁላሉ ለመውጣት የምታደርገው ትግል፤ ለጥንካሬዋ አስፈላጊ እንደሆነው ሁሉ፤ በፈተና ውስጥ በጽናትና በትግል ማለፋችንም መሠረተ ጽኑ ያደርገናል።

አንዳንዶች ስለፈተናው ብቻ ያወራሉ። ስለዚህም ተጨንቀው ሕዝብን ያስጨንቃሉ። ሰው ፈተናን ብቻ ካሰበ የዓለም መጨረሻ የደረሰ ይመስለዋል። ነገሮችን ሁሉ ያለቀላቸውና ያበቃላቸው አድርጎ ያያቸዋል። ንግሥት እሌኒ መስቀሉን ለማውጣት ስትነሣ ብዙዎቹ ስለመቀበሩ ብቻ ነበር የሚነግሯት። የት እንደተቀበረ እንደማይታወቅ፤ ከተቀበረ ብዙ ዘመናትን ያስቆጠረ፤ ለማውጣት አስቸጋሪ የሆነ፤ ሁኔታው ሁሉ ተስፋ እንደሚያስቆርጥ ነበር የሚነግሯት። እርሷ ግን እንደተቀበረ ብቻ ሳይሆን እንደሚወጣም ታምን ነበር። እንደጠፋ ብቻ ሳይሆን ሊገኝ እንደሚችልም ታምን ነበር። እነርሱ ስለ ፈተና ሲናገሩ፤ እርሷ ግን ከፈተናው ወዲያ ስላለው ድል ጭምር ነበር የምታወራው። ልዩነታቸው እዚህ ላይ ነበረ።
‹ፈተና› ደካማና ተሸናፊዎችን ሲሰብራቸው በተቃራኒው ለአሸናፊዎች የትምህርት ዕድል ነው። አሸናፊዎች ከፈተናው ትምህርት ወስደው ይለወጡበታል፤ እንደ ብረት ጠንክረው፣ እንደ ካስማ ጸንተው ይወጡበታል። ፈተና ለሚሸነፉ ሰዎች ተስፋ መቁረጫ ጥቁር ጭንብል ነው። በፈተናው ይማረራሉ እንጂ ከፈተናው አይማሩም፤ ድቅድቁን ጨለማ እንጂ ደማቁን ብርሃን ሊያዩ አይችሉም፤ የፈተናው መንገድ እንጂ የፈተናው ፍጻሜ በጭራሽ ዐይታያቸውም።

በክርስቲያኖች ዘንድ መስቀል ‹ኃይልና ቤዛ› ተደርጎም ይታሰባል። የእምነታቸው ምልክትም ነው። መጽናናትና መዳንን ያገኙበት ውድ ስጦታቸው ነው። ይሄን የሚያውቁ የዚያን ዘመን ጨቋኞች መስቀሉን ሲቀብሩት ዓላማ ነበራቸው። ክርስቲያኖቹ ትእምርት እንዳይኖራቸውና በተሸናፊ ሥነ ልቡና ውስጥ እንዲኖሩ ይፈልጋሉ። ልክ እንደ መስቀሉ ጭንቅላታቸውን እንዲቀብሩ፣ ዝቅ አድርገው እንዲያስቡና ዝቅ ያለ መንፈስ እንዲላበሱ የማድረግ ጽኑ ፍላጎት ነበራቸው። ነገር ግን ይሄ በመስቀሉ የሚያምኑትን አላሸነፋቸውም። ከዓመታት በኋላ ውድ ስጦታቸውን፣ ያንን የተቀበረ መስቀል በብዙ ጥረትና ትጋት ቆፍረው አውጥተውታል።

የብልጽግና ጉዟችን ለእኛ ለኢትዮጵያውያን እጅግ ወሳኝና ውድ ስጦታችን ነው። ለዘመናት በድህነትና ኋላቀርነት፣ በርሃብና በቸነፈር፣ በልዩ ልዩ ችግሮች ትከሻዋ የጎበጠው ሀገራችን ከሸክሟ የሚያሳርፏት፤ ብሩህ ነገዋን እንድታይ ቀና የሚያደርጓት፤ ክብርና ዝናዋን ከሚመጥን የብልጽግና ደረጃ ላይ የሚያደርሷት ልጆችዋን ትሻለች። በጥቃቅን ፈተናዎች ሳይሸነፉ፣ በእንቅፋትና በጋሬጣው ተጠልፈው ሳይወድቁ፣ ከመከራው ወዲያ የሚታየውን የሚጨበጥ ተስፋ ይዘው ወደፊት እንዲገሠግሡ ሀገራችን ትፈልጋለች።

ያኔ መስቀሉ ተቀብሮ ሳለ በመስቀሉ ፊት ሦስት ዓይነት ሰዎች ነበሩ። የመጀመሪያዎቹ መስቀሉን የማይፈልጉትና ከመሬት በታች የቀበሩት ሲሆኑ ዓላማቸው የመስቀሉን ደብዛ ማጥፋት ነበር። በሁለተኛው ረድፍ ያሉት ተስፋ ቆርጠው ሌላውን ተስፋ ለማስቆረጥ ታጥቀው የተነሡት ናቸው። በየአጋጣሚው መስቀሉን ቆፍሮ ስለማውጣት ሲነሣ የሚያከላክሉና አብዝተው ስለመከራው የሚናገሩ ነበሩ። ተአምር ተፈጥሮ እስካልወጣ ድረስ የመስቀሉ ነገር እንዳከተመለትም ያምናሉ። በተቃራኒው ሦስተኛ ላይ ያሉት መስቀሉ እንዲወጣ ጽኑ ፍላጎት ነበራቸው፤ ከሁሉም በላይ ‹መስቀሉ ይገኛል› የሚል ጽኑ እምነት የነበራቸው ብርቱዎች ናቸው።

እነዚያ ብርቱ ክርስቲያኖች የተቀበረውን መስቀል ለማየት የበቁት ተራራውን ንደው፤ ክምሩን ቆሻሻ ደረማምሰው፤ አፈሩን ምሰውና ብናኝ አቧራውን በአፍና በአፍንጫቸው ጠጥተው ነበር። ላብ ሳያስወጣ፣ ጉልበት ሳያብረከርክ፣ አቧራ ሳያለብስና ምንም ሳያስለፋ የሚሳካ መልካም ነገር የለም። የሀገራችን ዴሞክራሲ የሚሳካው፣ ነጻነትና እኩልነት እውን የሚሆነው ተገቢውን የዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት ተከትለን ስንሠራ እንጂ እንደ ተአምር ከሰማይ የሚወርድልን ነገር አይደለም። ፖለቲካችን የሚስተካከለው፣ ኢኮኖሚያችን የሚያድገው፣ ብልጽግናችን እውን የሚሆነው ዳር ቆመን በመመልከት ወይም እንደ ታዛቢ አፋዊ አስተያየት በመሰንዘር ሳይሆን ባለቤት ሆነን ስንሠራው፣ የበኩላችንን ማበርከት ስንችልና የውጣ ውረዱ አካል ስንሆን ብቻ ነው።

እኛ ኢትዮጵያውያን መከራችንን ከሚያብሱና ፈተናችንን ብቻ ከሚነግሩን መሠናክሎች ማምለጥ አለብን። እነሱ ዘላለም ፈተናችን ላይ ብቻ እንድንጣድ የሚፈልጉ ናቸው። ዘወትር በልቅሶና በትካዜ እንድንኖር ከማድረግ ውጭ ለቁስላችን መድኃኒት፣ ለተራበ ሆዳችን ምግብ፣ ለታረዘ ገላችን አልባስ አያቀርቡልንም። በጊዜያዊ ችግሮቻችን እንድንጠመድ ከማድረግ በዘለለ ሥር ለሰደዱ ችግሮቻችን ዘላቂ መፍትሔ አያቀብሉንም። ከማላዘን ፖለቲካ ምን ጠብ የሚል ነገር እናገኛለን ብንል መልሱ ኪሳራ እንጂ ትርፍ፤ መከራ እንጂ ዕረፍት አይሆንም።

ኢትዮጵያ እስካሁን ተፈትናለች፤ አሁንም እየተፈተነች ነው፤ መጠኑ ቢለያይም ወደፊትም ፈተና ማጋጠሙ አይቀርም። ዋናው ቁም ነገር ከፈተና በኋላ እንደ ወርቅ ነጥሮ መውጣት መኖሩን አለመርሳት ነው። እሳት ለወርቅ ማቃጠያው ብቻ ሳይሆን ማንጠሪያውም ጭምር ነው። ይበልጥ በእሳት ሲመታ፤ ይበልጥ ንጹሕ ይሆናል። ይለወጣል። ፈተናዎቻችን ነጥረን እንድንወጣ እንጂ ቀልጠን እንድንቀር አያደርጉንም።

ሀገራችን ወደፊት እንዳትራመድ አስረው የያዟት ትብታቦች የቱንም ያህል ቢበዙ ተበጣጥሰው ማለቃቸው አይቀርም። ግድግዳ ሆነው መንገድ የዘጉባት ቋጥኞች የቱንም ያህል ቢገዝፉ ተንደው ይወድቃሉ። ሕብዛችን ብሩህ ቀን እንዳያይ የሚያደርጉት የጽልመት መጋረጃዎች በብርሃን ሰይፍ ይቀደዳሉ። ገፍተው መስቀለኛ መንገድ ላይ ያቆሟት ሲያልፉ፣ ሀገራችን ተስፋ ባላቸው ኅሊናዎች፤ በተባበሩ እጆች፤ በቆረጡ ልቦች፤ በልዩነት ውስጥ አንድነትና ፍቅር እንዳለ በሚያምኑ ልጆችዋ ብርታት ከችግሮቿ በላይ ከፍ ትላለች፤ ብልጽግናዋም ያለጥርጥር እውን ይሆናል።

መስቀሉ ከተቀበረበት ቀን ይልቅ የወጣበት እለት እንደሚከበር ሁሉ ኢትዮጵያም የድል ታሪኳን እያከበረች መሄዷን ትቀጥላለች። ከእንግዲህ ሥልጣኔና ብልጽግናዋን አፈር ለሚያለብሱ አካላት ቦታ የላትም። ለጊዜው መኖራቸው እያወቀች፣ መንገዷን እንደሚቆፍሩ እያየች፣ ‹አንድ ቀን ወደ ቀልባቸው ሊመለሱ ይችላሉ› በሚል ተስፋ ዐይታ እንዳላየ ታልፋቸው ይሆናል። ነገር ግን በየትኛውም ዕንቅፋት ከመንገዷ አትገታም፡፡ አቧራውን ጠርጋ፣ አፈሩንም ንዳ ታሪክ መቀጠል እንደምትችል፣ ጉድጓድ ሲምሱላት የነበሩም ራሳቸው ሲገቡበት ታያለች። የኢትዮጵያ ድል የፈተናዎቿን ብቻ ሳይሆን የፈታኞቿንም ታሪክ እንደሚዘጋ ምንም ጥርጥር የለውም።

የመስቀል በዓል በሀገራችን ከሃይማኖታዊ ዋጋው በዘለለ ባህላዊ ትርጉምም ተሰጥቶት ይከበራል። በተለይም በደቡቡ የሀገራችን ክፍል መስቀል የተለየ ግምት ይሰጠዋል። የተነፋፈቁ የሚተያዩበት፣ የተለያዩ የሚገናኘበት፣ ዝምድና የሚጠነክርበት፣ አንዱን ምዕራፍ ጨርሰው ወደሌላ ምዕራፍ የሚሸጋ

Dr Abiy Ahmed Daily

24 Sep, 13:24


“ያፈጠጠውን እውነታ ለመረዳትና ለመጋፈጥ እስከማትችል ድረስ በሀገር ፍቅር ልትታወር አይገባም። ማንም ይናገረው ማንም ያድርገው ስሕተት ሁልጊዜም ስሕተት ነው።” - ማልኮም ኤክስ፣ ባይ ኤኒ ሚንስ ነሰሰሪ

"Dhugaa ifa jiru hubachuufi fudhachuu hamma sidhorkutti jaalala biyyaatiin jaamuu hin qabdu. Eenyuyyuu haa raawwatu, eenyuyyuu haa dubbatu dogoggorri yoomiyyuu dogoggora." Malcolm X, By Any Means Necessary

“You’re not to be so blind with patriotism that you can’t face reality. Wrong is wrong, no matter who does it or says it.” - Malcolm X, By Any Means Necessary
@DrAbiyAhmedDaily

Dr Abiy Ahmed Daily

21 Sep, 09:15


የአፋር ክልል ፕሬዚደንት በመሆን፣ ቀጥሎም ለኩዌት አምባሳደር በመሆን፣ እስከ ግዞታቸው ድረስ ሀገራቸውን ያገለገሉት ሱልጣን ሐንፍሬ አሊ ሚራ ማለፋቸውን በመስማቴ እጅግ አዝኛለሁ። ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ።

Pirezdaantii Naannoo Affaar, itti aansuudhaanis Kuweetitti Ambaasaaddara ta'uudhaan hamma jireenya baqaasaaniitti biyyasaanii tajaajilaa kan turan Sulxaan Hanfiree Alii Miirah lubbuudhaan boqochuusaanii dhagahuukootti baay'ee gaddeera. Maatiifi firootasaaniif jajjabinan hawwa.

Today I learned with great sadness the passing of Sultan Hanfare Ali Mirah who served his country as President of the Afar Region and as Ambassador to Kuwait, until his exile. My deepest condolences to his family.
@DrAbiyAhmedDaily

Dr Abiy Ahmed Daily

19 Sep, 15:57


የኮይሻ ሀይድሮፖወር ፕሮጀክት በኦሞ ወንዝ ዳርቻ የሚገኝ ሲሆን፣ 37 በመቶ ሥራው ተጠናቋል። ፕሮጀክቱ በከፍተኛ ሁኔታ ተጓትቶ የቆየ ቢሆንም፣ በቅርቡ ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል። በዓመት የ6400 ጊጋዋት አወርስ መጠን ያለው ኃይል እንደሚያመነጭ ይጠበቃል። እስካሁን ለ4000 ያህል ሰዎች የሥራ ዕድል ያስገኘ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ሲቀጥል ለተጨማሪ ሰዎች ሥራን ይፈጥራል። ግድቡ ከአዲሱ የኮይሻ ፕሮጀክታችን ጋር ተዳምሮ፣ አካባቢውን ወደ ልህቀት ያደርሳል።

Piroojektiin Humna Bishaanii Oomoo laga Oomoorratti kan argamu yoo ta'u, hojiinsaa dhibbeentaa 37 xumurameera. Piroojektich garmalee duubatti harkifamee kan ture yoo ta'u, dhiyeenya kana hojiinsaa cimee itti fufeera. Waggaatti GWH6400 akka maddisiisu eegama. Hamma yoonaatti namoota 4000 f carraa hojii kan uume yoo ta'u, ittifufiinsaanis namoota dabalataaf carraa hojii ni uuma. Hidhichi piroojektii Koyishaa isa haaraa waliin ta'ee naannicha haalaan jijjiiruuf murteessaadha.

Koysha hydropower project is an Omo River hydropower project currently at 37% completion. Recently reactivated following major project delays, it is expected to generate 6400GWH per year. So far it has created 4000 jobs and will continue to employ more as the project progresses. Together with our new Koysha project, the dam will be a critical catalyst to positively transforming the area.
@DrAbiyAhmedDaily