Medina Tube || መዲና ቲዩብ @medinatube Channel on Telegram

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

@medinatube


Medina Tube || መዲና ቲዩብ (English)

Welcome to Medina Tube, your go-to channel for all things related to Ethiopian culture, music, and entertainment! Known by the username @medinatube, this channel is dedicated to showcasing the rich traditions, vibrant music, and diverse entertainment of Ethiopia. From traditional dances and music to modern Ethiopian pop culture, Medina Tube offers a unique insight into the beauty and creativity of this East African country. Whether you're looking to discover new Ethiopian artists, learn more about the country's history, or simply enjoy some entertaining content, this channel has something for everyone. Join us on a journey through the sights and sounds of Ethiopia, and immerse yourself in the captivating world of Medina Tube || መዲና ቲዩብ. Subscribe now and never miss out on the latest updates and exclusive content!

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

05 Jan, 11:26


ከሚኒ ኬክ እስከ የሰርግ ኬክ እንሰራለን!
#ለልደት
#ለኒካ
#ለሰርግ
#ለምርቃት ለተለያዩ ዝግጅቶች የናንተን ፍላጎት ለሟሟላት ትዛዛቹን እየጠብቅን ነው።
አድራሻችን :-ለቡ ጀም አንድ
TELEGRAM
https://t.me/lihamcake

TIK TOK
tiktok.com/@liham.cake
ይዘዙን ባሉበት እናቀርባለን!

☎️☎️☎️ ለማዘዝ
0934303143
0943372899 ይደውሉ

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

05 Jan, 05:47


አብሬት || አብሬድ
____የጦሪቃው አውራድ ጎርፍ መፍሰሻ

አብሬድ ማለት ከአውራድ የተያዘ ሲሆን የጦሪቃችን አውራድ ጎርፉ የሚፈስበት ቦታ ነው::
<ቀደሠላሁ ሢረሁ>
▪️
አብሬቶች ድቅድቅ ባለው ጨለማ ወቅት 7ቤት ጉራጌ ሁላ ለአምልኮ ከሚጟዝላቸው ፥ ከሚገብርላቸው ፥ እንደ ንጉስ ከሚያዩዋቸው ከጣኦት አምላኪያን መሪ ቤተሰብ የወጡ ፀሀይ ናቸው:: ተተኪ የሀይማኖቱ መሪ ይሆናሉ ተብሎ ሲጠበቁ ኑረል ኢማንን ይዘው ብቅ ያሉ ፥ ሺርክን ከስሩ መንግለው የጣሉ ፥ ለኸልቁ እንደ ፀሀይ የበሩ የአላህ ኑር ናቸው:: ሠይዲ አባ ራሙዝ በአንዱ መድሀቸው መሽረብ ሸይኻቸውን ሠይድ ባኡ ሳኒ <በድቅድቁ ጨለማ መካከል የበሩ ፍጹም የሆኑ ሙሉ ጨረቃ> ብለው ያወድሷቸዋል::

▪️ሠላም ዐለይከ ሸምሠል ዲነል ኪራሚ
▪️በድሩል ዘማን ፊ ወሰጢ ዞላሚ

በጉራጌ እና አጎራባቾቹ ላይ ያለ ሙስሊም ሁሉ የሁዋላ ታሪኩን ቢያጤን አራት እና አምስት አባቱን ወደሁዋላ ቢቆጥር ከመቶ መቶ ወይንም ዘጠና ዘጠኝ ፐርሰንቱ ጨለማ ላይ የነበረ ህዝብ ነበር:: ሙሉ ሰባት ቤት ጉራጌ ማለት ይቻላል መብረቅ አምላኪ ህዝብ ነበር:: በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መልኩ ለዛሬው ማንነታችን ለሂዳያችን ሰበብ ከአብሬት ሸይኾች አንዱ ሆነው እናገኛዋለን:: በተለይም ለጉራጌ ማህበረሰብ:: ነገር ግን ከአብሬት የወጣው ፀሀይ በጉራጌና አጎራባቾቹ ብቻ ተገድቦ የቀረ አይደለም:: ብዙሀኑን የሀገራችንን ክፍሎች አካሎ ከሀገር ውጪም ፀሀያቸው በርቷል::
▪️
በታላቁ የረጀብ ወር በእነዚህ ከዋክብቶች ሀሪማ ሐረመል አብሬት የከውኑ ሁላ ንጉስ የነብያችንﷺ መውሊድ እጅግ ደማቅ በሆነ መልኩ ይከበራል:: የጦሪቃው አውራድ እንደ ጎርፍ ይፈሳል ፥ የአላህ ራሕመት ይዘንባል ፥ የነብያችንﷺ ኑር ይንቧቧል ፥ መላይካው እንደ ጉድ ይወርዳል ፥ የታላላቅ አውሊያዎች ሩሕ ይሀደራል። ከሚታየው የማይታየው ታዳሚ ይበልጣል:: እናልህ ወዳጄ አብሬት ለመግባት ጟዝህን ጠቅልል ከዚህ ማኢዳ ተቋደስ::

አ    ብ    ሬ    ት ..... ረ  ጀ  ብ

አላህ ይውስደን እዚህ የተከበረ ቦታ🤲🤲
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

05 Jan, 05:31


ይህ መቃብር የማን ይመስልሀል?

10.4 ቢሊዮን ዶላር ባለቤት ባለፀጋ የኩዌታዊ ታዋቂው ነጋዴ የናስር አል-ከራፊ መቃብር ነው።

ተመልከት አንድ ሳንቲም አብሮት አልተቀበረም ገንዘቡ ለወራሾች ጥሎት ነው የሄደው አላህ ይዘንለት መቃብሩም ከሌሎች የተለየ አይደለም ኢስላም የሀብታም እና የድሀ መቃብር ልዩነት የለውም።

ሀብት ያላችሁ አብሯችሁ ለማይቀበረው ገንዘብ ለተቸገሩት አጉርሱ ለታረዙት አልብሱ ሞት ሳይቀድማችሁ።
ሰጥቸህ ነበር ምን ሰራህበት ጥያቄ አለብህና።
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

05 Jan, 05:15


ዐርባ የሶለዋት ጥቅሞች
===============
ኢማም ኢብኑል‐ቀዪም [ረሒመሁላህ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«ዐርባ ሶላት ዐለን‐ነቢይ [ﷺ] ጥቅሞች: ‐
❶ የአላህን ትእዛዝ መፈፀም።
❷ አላህም በነቢዩ [ﷺ] ላይ ሶለዋት ስለሚያደርግ ከአላህ ድርጊት ጋር መሳሰል። በእርግጥ የእኛና የአላህ ሶለዋት የተለያየ ነው። [የአላህ ሶለዋት እዝነት ሲሆን ከኛ ሲሆን ደግሞ ዱዓ ነው።]
❸ ከመላኢካዎች ጋር መመሳሰል።
❹ አንድ ጊዜ ሶለዋት ያደረገ ሰው አላህ ዐስር ሶለዋት ያደርግበታል።
❺ ሰውየውን አላህ በዐስር ደረጃዎች ከፍ ያደርገዋል።
❻ ዐስር ሐሰና (የበጎ ሥራ ምንዳ) ይፃፍለታል።
❼ ዐስር ኃጢኣት ይሰረዝለታል።
❽ የዱዓን ተቀባይነት ያስገኛል።
❾ የሙስጦፋን [ﷺ] ምልጃ ያገኛል።
❿ ወንጀልን ለማሰረይ ምክንያት ይሆናል።
⑪ ሰውየውን አላህ ከጭንቀት ይገላግለዋል።
⑫ በቂያማ ቀን ሰውየው ከነቢዩ [ﷺ] ቅርብ ይሆናል።
⑬ ድኻ ለሆነ ሰው ሶለዋት የሶደቃን ቦታ ይሸፍናል።
⑭ አስቸጋሪ ጉዳይን ያገራል።
⑮ የአላህና የመላኢካዎችን ሶለዋት ያስገኛል።
⑯ ሰውየውን ከወንጀል ያፀዳዋል። ንፅህናን ያላብሰዋል።
⑰ ሰውየው ከመሞቱ በፊት በጀነት እንዲበሰር ያደርጋል።
⑱ ከቂያማ ቀን ድንጋጤ ይጠብቃል።
⑲ ሰውየው የረሳውን ነገር እንዲያስታውስ ያደርገዋል።
⑳ ለሰላምታው የነቢዩን [ﷺ] ምላሽ እንዲያገኝ ያደርገዋል።
21. ስብሰባን ያሳምራል። ሶለዋት የተደረገበት ስብሰባ በቂያም ቀን ቁጭት አይከተለውም።
22. ድህነትን ያስወግዳል።
23. ስስትን ያስወግዳል።
24. አፍንጫው ይታሽ (ውርደት ይንካው) ብለው ነቢዩ [ﷺ] ካደረጉት ርግማን ይድናል።
25. ወደ ጀነት መንገድ ያስገባል። ሶለዋት የተወ ሰው ደግሞ ከጀነት መንገድ ይርቃል።
26. ከስብሰባ ክርፋት ያድናል። ምክንያቱም አላህና መልክተኛው [ﷺ] የማይወሱበት ስብሰባ ሁሉ የከረፋና የገማ ነው።
27. ኹጥባንም ሆነ ሌላን ንግግር ያሳምራል።
28. ሰውየው በሲራጥ ላይ የሚኖረውን ብርሃን ያበዛለታል።
29. ሰውየውን ከጭካኔ ያፀዳዋል።
30. ሶለዋት የሚያደርግ ሰው በምድርም ሆነ በሰማይ መልካም ስም እንዲኖረውና እየተወደሰ እንዲኖር ያደርገዋል።
31. ሶለዋት የሚያበዛ ሰው የተባረከ ይሆናል። ስራውና እድሜውም በረካ ይሆንለታል።
32. የአላህን እዝነት ያገኛል።
33. ሰውየው ለአላህ መልክተኛ ﷺ ያለው ፍቅር ዘውታሪ እንዲሆን ያደርጋል።
34. ዘውታሪ የሆነ የአላህ መልክተኛን [ﷺ] ውዴታ ያገኛል።
35. ቀና መንገድ መመራትን (ሂዳያ) ያገኛል። ቀልቡም ህያው ይሆንለታል።
36. የሰውየው ስም በነቢዩ [ﷺ] ፊት እንዲጠራ ያደርጋል።
37. በሲራጥ ላይ የሰውየው እግር እንዲፀና ያደርጋል።
38. ሰውየው የነቢዩን [ﷺ] ሐቅ በከፊል እንዲወጣ ያግዘዋል።
39. ሶለዋት አላህን መዝከርና ማመስገንን ያካተተ በመሆኑ ሰውየው ከአመስጋኞችና ከዛኪሮች ተርታ እንዲመደብ ያደርገዋል።
40. ሶለዋት ዱዓም ነው። ምክንያቱም በሶለዋቱ ሰውየው አላህ በሚወዳቸው እና በመረጣቸው ነቢይ ላይ ውዳሴውን እንዲያደርግ መለመን ማለት ነው። በዚያውም ሰውየው ጉዳዩ እንዲፈፀምለትና ጭንቀቱ እንዲወገድለትም እየተማፀነ ነው።
--------------------------
📚 «ጀላኡል‐አፍሃም ፊ ፈድሊስ‐ሶላቲ ወስ‐ሰላሚ ዐላ ኸይሪል‐አናም ﷺ»

አህባቦቼ በዱኣ እና በዚክረ ሶላት ዓለ ነብይ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንበርታ



ፋጢመቱ✍️✍️✍️
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

28 Dec, 14:44



ሰላት የሌለው በምን ይረጋጋል??
ሰላት ባይኖረንስ በምን እንረጋጋ ነበር??


«يا بلالُ، أقِمِ الصَّلاةَ، أرِحْنا بها»
«ቢላል ሆይ! እስኪ ኢቃም በልና በሰላት አሳርፈን።»

@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

28 Dec, 14:44


ጭንቅ የበዛበት ሰለዋት ያብዛ የጋለ ብረት ውሃ ውስጥ እንደ መንከር እያየው ያሁሉ ጭንቅ ይወገዳል ።
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

28 Dec, 14:28


የፍቅር ሐይል ግን ዐጂይብ ነው.. ሩሀችንንና ጀሰዳችንን የሚያጣምር አንዳች ውበት... ናፍቆቱ የማያልቅ፤ ውዴታው የማይሰለች፤ ትውስታው የሚነዝር አንዳች ነገር!

🌹ያ..የዘይነልዉጁድﷺ ፍቅር...ዱንያ ላይ በሚኖረን ቆይታ ህይወታችንን ሙሉ እሳቸውን አለመናፈቅ አይቻለንም። የናፍቆታችንን ሮሮ ለማስታገስ...አሏህ ይወፍቀንና ጀነት ላይ እስክናገኛቸው በትንሹም የሚያረግብልን ደግሞ ሰለዋት ነው!

« أَوْلَى النَّاسِ بِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَكْثَرُهُمْ عَلَىَّ صَلاَةً »

«የዉመል ቂያማ ላይ ለኔ ቅርቡ ሰው ማለት እኔ ላይ ሰለዋትን የሚያበዛው ነው»አሉ ዘይነልዉጁድﷺ♥️

🌹اللهم صلّ وسلم وبارك على سيدنا محمد النبى الأمي الزكي البهي الصفي النجي الوفي وأمطر علينا سحائب لطفك الخفي وحبك الجلي وعلى آله وصحبه وسلم🌹

@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

25 Dec, 10:43


በነጠላ ስም እየጠራሁ የትኛውንም ሙስሊም አላከፍርም ' ሳዳቶቻችን እንደማያከፍሩት!

እንኳን ጭፍን ተከታዩን   ኢብኑ ተይሚያን እንኳን እማያከፍሩ ትላልቅ ኡለማኦች  ብዙዎች ናቸው ? እሚገርመው እነሱን ያላከፈረንም ማክፈር የመጣልን ግዜ ነው-   በአቂዳ ተመሳስለከው በ አካሄድ ያልተመቸህን ሁላ በቃ ልታከፍረው አስበሃል ?     እስኪ መወራረፉን ትተን በአደብ እናውራ  ' ምን ጃሂል ብንሆንኮ  "ካፊር" እሚለው ቃል ሳንቀራም ያስደነግጠናል

   ሳዳቶቹ ከወሃቢያም ጋር ቢሆን እምንወያይበትን ስልት እና አደብ  ሲጠቁሙ "ማንንም አንተ ካፊር አትበል 'በጅምላ ይሄ አስተምህሮ ለጥመት ይዳርጋል" ብለህ ሂድ ብለው ማስተማራቸውን በበቂ ማስረጃ ማቅረብ ይቻለናል -እናቀርባለንም በአላህ ፍቃድ!  ግን ከመከባበር ጋር በአደብኛ!     ህጻናት ሲሳደቡ አደቡን ማስታወስ እንጂ ሌላ ምን አለ ?

                   የዛሬ 4 አመት አካባቢ በወሃብያዎች ጉዳይ  ስሜታዊ ሆነን በጀመዐ እያወራን ሸይኽ ኸይሩዲን አል ቀጥበርይ (አላህ ይጠብቃቸው) አስተውለውን       አደብ እንዳልሆነ  ቆጣ ብለው የነገሩኝን አልረሳም ' እኛ በስሜታዊነት ስንቆጣ    እነሱ በብስለት ደረጃዎች ሺ እጥፍ ይቀድሙናል.... ቀጥተኛ መንገድ እንዲመሩ ከፈለግክ  እንደነሱ ችኩል አትሁን  ብለው ከአደብ አንጻር መርሳት የሌለብኝን ጠቆሙኝ.... ይህንን ይበልጥ  እምንረዳው እናት አባታችን የወሃቢያ ሸይኽ አሳስቱኣቸው  በአንድ ቤት እየኖርን እንዴት ከነሱ ጋር መኑኣኑኣር እንዳለብን  ስናስብ ነው - ዘለል ሲድ ደግሞ የነቢ ኡመት መሆን ያለውን ክብር ከትልልቆቹ አንደበት ስንሰማ!

         ለማንኛውም እንኳን እኔን እንጭጭ  ዒልም ፈላጊው እነ ሙሐመድ ሙተወሊይ አሻዕራዊይ  ፣ ኢማም  ረመዳን አልቡጢይ ፣የሻም ሱፊይ ሙሐዲሶች በጅምላ ' የአዝሃር  ሊቃውንት ሌላም ብዙዎቹ  ከዘመናችንም የየመን ተሪም አህለልበይቶች  ከማክፈር ዘመቻዎች አልተረፉም......  ከጦሪቃ መሻይኾች በነቅሸበንዲያው እነሸይኽ ናዚም አል ሃቃኒይ 'ሸይኻቸውን ሸይኽ አብዱላህ አዳጊስታኒይ እና ደረሶቻቸው "ከራሳቸው ከአብደሪይ ጦሪቃ ሪፋኢያዎች  በሃኡዲን ረዋስ እና መሻይኾቻቸው ' ከቃዲሪያም በርካታ እውቅ መሻይኾች " ኢብኑ ተይሚያን ሙብተዲዕ ከማለት ውጪ በካፊርነት አይገልጹም" ከሻዚሊያው አሁን ካሉት ሸይኽ ሙሐመድ ፈውዚይ አል ከርከሪይ ጀምሮ በሲልሲላው ያሉት ሳዳቶች  ሙስሊምን ከማክፈር የተቆጠቡ ናቸው (የሐበሻ ኡለማኦችን አቋም  እስኪ እናንተው ንገሩን?)
         

                ጌታው  የኡመቱ ዐሊም ' ሙሂቡ ማዲሀ ረሱሉ ' ቃዲ ዩሱፉ ነብሃንይ ይህንን 'የአላከፍርም' አካሄድ አንጸባርቀው "ጃሂል" ባስ ብሎም ካፊር  ተበለው የለም?  ነብሃኒይ የነቢው ገበር  "ኪታቦቼን ሁሉ ሳንሱር ያረጉልኝ የመዲናው ሙስጦፋ ናቸው" ያሉቱ ዩሱፍ አነብሃንይ.......  በኪታቦቻቸው " ኢብኑ ተይሚያ ረሂመሁላህ" ስላሉ ብቻ ካፊር የተባሉት? 
                            ብቻ የአካሄድ ልዩነት ላይ በ መከባበር መጓዝ ለኛው  እሚበጅ ይመስለኛል'ካልሆነ በአብደርይ (ሸይኽ አብዱላህ አልሃረሪይ ረሂመሁላህ) እና ቀዳሚ የአሻዒራ ሱፊያ ት/ቤቶች መሃከል የተፈጠሩ አለመስማማቶች አሉ የሚሉ ኡለማኦችን ኪታብ ለመግለጥ  ግድ ይሆናል  ወላሁ አእለም.....        አስተያየቶቻሁን እጠብቃለሁ

ሰላም ይድረሶት ሆዴ
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

23 Dec, 08:24


#ሰይዲ  ሁስኒ ሱልጣን  አዲስ || መንዙማ
@MEDINATUBE
@medina_tube

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

21 Dec, 17:36


ሙስሊም ሆነህ አረንጓዴ ልብስ ስታይ ውስጥህ የሚረበሽ ከሆነ ቢቀራብህ መልካም ነው:: የጀነት ሰዎች ልብስ ውስጥ በቁርአን ብዙ ቦታ የተጠቀሰው አረንጓዴ ልብስ ነው:: ወርቅ እና ሀር ለወንድ ተከልክሏል:: አረንጓዴ ልብስ ግን አልተከለከለም:: የነቢያችን صلى الله عليه وسلم ጥምጣም አረንጓዴ ነበር:: አሁንም ድረስ ቱርክ ሙዚየም ውስጥ አለ:: የኢማም ዐሊይ رضي الله عنه ጥምጣምም አረንጓዴ ነበር:: አረንጓዴ መልበስ የነቢያችን صلى الله عليه وسلم እና የጀነት ሰዎች ሱና ነው:: አላህ አድንቆ ነው የነገረን::
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

21 Dec, 17:29


ሙሀመድ ይባላል....ﷺ

አሏህ ብሎ ያለው ቀና በል አትዘን
የሰላም የፍትህ አርማና ማዕዘን
ደግነት ብቻ ነው ሙሀመድ ያዘዘን

         የኛ ነብይ..ﷺ

ራሱን ለአሏህ ሽቅብ ቀና አድርጎ
ከረሂሙ ጌታ እዝነቱን ፈልጎ
በሙሽሪኮች በደል እየደረሰበት
ስሙ እየጎደፈ ዋሽተው ቀጥፈውበት
ፍፁም በሌለበት እየተወቀሰ
ጌታየ ህዝቦቼን ብሎ ያለቀሰ

        ሙሀመድﷺ

የስልጣኔ አርማ የእድገት ከፍታ
ስሙ እማይረሳ ለሰከንድ ላፍታ
እንኳን ላመነበት በመንገዱ ፀንቶ
አያውቅም ጠላቱን በክፋት አንስቶ

ከመጥፎ ከልክሎ መልካሙን ያሳያል
ከማንም ከምንም ሙሀመድ ይለያል

መከራው ሲጠና በአሏህ ይወከላል
ችግር ሲደራረብ ሀስቢየሏህ ይላል
መደምደሚያው ነብይ ስሙ ማን ይባላል?

«ውዶቼ ሶለዋት እናውርድ
   መልካም ኢስነይን


✍️የሙሂቡን ግጥም
         

@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

21 Dec, 17:27


በስሙማ ስንቱ ተፈረጀ💛

ሰላሚያዓላ ጀበል ማብራቱ
ፈሪ አይወድም ጎበዝ ነው ብርቱ
ኑሩ ያበራል ዓለምን ሞልቶ 👏
@MEDINATUBE
@medinatube

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

08 Dec, 15:59


አሰላሙ አለይኩም😊 የመጀመርያው ግሩፓችን ስለተደለት አዲሱ ግሩፕ ነው ይቀላቀሉን ADD ❤️ በማረግ ቤተሰብ ይሁን!👍
@ethiomewild2

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

04 Dec, 18:23


ስለ ረሱል ምን ያህል እናውቃለን

ነብያቶች ባጠቃላይ በህይወት ባሉበት ጊዜ የሙሀመድ ነብይነት ካጋጠማቸው የእሱ ተከታይ እና አጋዥ ሊሆኑ ቃል ገብተዋል። እያንዳንዱ ነብይም ለተከታዮቹ ስለ ሙሀመድ ሳይናገር አላለፈም። በትክክለኛው ተውራትና ኢንጅል ውስጥ ሙሀመድ በመገለጫዎቹም ብቻ ሳይሆን በስሙም መጠቀሱ ለዚህ ግልፅ ማሳያ ነው።እንደ ወረቃ፣በሂራ፣ አቡ ተይሃን፣ ዐብደላህ ቢን ሰላም፣ ከዕቡ አልአህባር ፣ዐብደላህ ቢን ዐምር፣ የዐሙሪያው መነኩሴ እንድሁም የሩሙ ንጉስ ( ሂረቅል) አይነት የመፅሀፉ ባለቤቶች ስለሙሀመድ ምስክርነት መስጠታቸው ይሄንኑ አረጋጋጭ ነው። ሊላኩ አካባቢ ደግሞ የሙሀመድ መምጣት ወሬ በሰፊው ተሰራጨ። ጠንቋዮች ሳይቀሩ ስለሙሀመድ صلى الله عليه وسلم መተንበይ ጀምረው ነበር። ታዲያ የዚህ ወሬ መሠራጨት አንዳንዶች ሙሀመድን ዝግጁ ሆነው እንድጠብቁ ጥሩ እድል ፈጥሮላቸዋል። አንሷሮች እስልምናን እንድቀበሉ ፈር የቀደደላቸውም ይሄው ወሬ ነበር። ሰልማንም رضي الله عنه የመነኩሴውን ጥቆማ ተከታትሎ ሰለመ።
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

04 Dec, 18:23


ስለ ረሱል ምን ያህል እናውቃለን?

ነብዩ صلى الله عليه وسلم እድሜያቸው 12 አመት ሲሞላቸው ከአጎታቸውና ከቁረይሽ ነጋዴዎች ጋር በመሆን ለንግድ ስራ ወደ ሻም ተጓዙ። ቡስራ በተባለች ሰፈር ሲደርሱ በሂራ የተባለ መነኩሴ ጋር ተገናኙ። በሂራ በስላሴ የማያምን የጥንታዊዉ ክርስትና እምነት ተከታይ ነው። ለመንገደኞቹ ሰላምታ ካቀረበ በኋላ በመካከላቸው በማለፍ የሙሀመድን እጅ ያዝ አደረገና “የዐለማቱ ሁሉ አለቃ ፣ የዐለማቱም እዝነት ይሄ ነው” ሲል ተናገረ። በምን እንዳወቀውም ሲጠይቁት እናንተ ዳገቱን እንደወጣችሁ መላው ዛፍና ድንጋይ ሱጁድ ሲያደርግ አየሁ። ይሄ ደግሞ ለነብይ ብቻ የሚሰጥ ስጦታ ነው። በመፅሀፋችን ላይ በጀርባው በኩል ከትከሻው ዝቅ ብሎ የነብይነት ማህተም እንዳለው ስለተነገረን በዚህም ማረጋገጥ እችላለሁ አለና ትከሻቸውን ተመለከተ። የእርግብ እንቁላል የሚመስለውን ማህተም ( ከፍ ያለ ስጋ) አገኘ። ከዚያም አቡጣሊብን ሩሞች ተንኮል ስለሚያስቡበት እባክህ ወደ መካ ይዘኸው ተመለስ ብሎ ተማፀነው። አቡ ጣሊብም የንግድ ስራውን በመተው ሙሀመድን ይዞ ተመለሰ።
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

01 Dec, 05:55


በሼህ መሀመድ ሁሴን (ኮምቦልቻ)
👏 ሙሀመድ ባለጣው አምሳያው የታጣው።🥁🥁🥁🥁

👇👇👇👇👇👇👇👇👇ተቀላቀሉን
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

28 Nov, 18:12


👳‍♂ሼህ አብድልወሀብ

#አላሁመሶሌ አላ ሙሀመዴ➋
ኑሪዚልጀላሌ ጀማሌ ጀማሌ
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

28 Nov, 18:09


🎤ሼህ መሀመድ አወል ሀምዛ
ምርጥ መንዙማ
💞በስመላ

@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

24 Nov, 19:18


ያኢማመል ሀረም ከንዝ ሙጠልሰሙ

#የሸሆቹ_ሀድራ ሃያትትትት
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

24 Nov, 18:48


ኢድሪስ ማህሙድ ምርጥ መንዙማ😍
አሽቁ
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

24 Nov, 18:46


አዛን 🔊 ❤️🤲
መዲና 1373 ሂጅራ (ᎷᎪᎠᏆΝᎪᎻ ᎪᏞ ᴍᴜɴᴀᴡᴀƦᴀʜ🕌)
መታየት ያለበት ቪዲዮ⬆️
⬇️
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

24 Nov, 18:41


https://t.me/ethiomewelid

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

31 Oct, 20:21


ጁመዐ ሙባረክ 😍😍😍😍😍
""""""""""""""" """""""""""""""
""""""""""""""" """"
በዑመር ዘመን ሶስት ወጣቶች አንድ ስውዬን ጎትተው በማምጣት ያዐሚረል ሙእሚኒን
ይህ ሰው አባታችንን ገድሏል
ሀድ/ቅጣት/ እንደትወስንበት እንሻለን በማለት ተናገሩ።
‌‌
ለምን ገደልክ ? ሲል ዑመር ጠየቁ
‌‌
‹‹ እኔ የግመል እረኛ ነኝ አንደኛው ግመሌ የአባታቸው መሬት ላይ ካለ ዛፍ ቅጠል ቀንጥሶ ሲበላ አባታቸው ድነጋይ ወርውሮ ሲመታው ግመሌ ሞተ እኔም እሱ
የወረወረውን ድንጋይ አነስቼ ስወረውር ምታሁትና ሞተ…
ሲል ተናገረ።
‌‌
‹‹እንደዛ ከሆነ ቅጣት እወስንብሃለሁ! አሉ ዑመር
‌‌
‹‹እሺ ሦስት ቀናትን አቆየኝ……አባቴ ሲሞት ለኔና
ለወንድሞቼ የተወው ከንዝ የተደበቀ ሃብት አለ እኔ አሁን
እዚሁ ከሞትኩ ከንዙም ይጠፋል ወንድሞቼም ይጠፋሉ (ይቸገራሉ)..ስለዚህ ፍቀድልኝና ሄጄ ልምጣ አለ።
‌‌
ታዲያ እሰክትመለስ ዋስ የሚሆንሀ ማነው? በማለት ዑመር
ጠየቁ።
‌‌
ሰውዬው የተሰበሰቡትን ሰዎች ተመለከተ የሚያውቀው የለም……የእያነዳንዱን ፊት ተመለከተና ያ ሰውዬ ሲል ጠቆመ።
‌‌
ያ አባ ዘር ለዚህ ሰው ዋስ ትሆናለህ ? በማለት ዑመር ጠየቁ...
‌‌
አዎን ያ አሚረል ሙእሚኒን በማለት መለሰ።
‌‌
ይህ ሰው ካመለጠ ቅጣቱ አንተ ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን አታውቅም እንዴ? ሲል ዑመር ተገርሞ ጠየቀ ግድ የለም ያ አሚረል ሙእሚኒን እኔ ዋስ
እሆነዋለሁ….ሲል አቡዘር መለሰ።
ሰውየው ሄደ።
‌‌
አንድ ቀን አለፈ….ሁለተኛው ቀን ተከተለ… በሦስተኛው ቀን ሰውየው ካልመጣ ቅጣቱ አቡዘር ላይ ስለሚፈፀም ሰዎች
ተጨነቁ………ሆኖም የዛን ቀን ከመግሪብ በፊት …..ያ ሰው እያለከለከ መጣ…በጣም እንደደከመው ገፅታው መስካሪ
ነበር።....ከዑመር ፊት ለፊት መጥቶ በመቆም
‌‌
‹‹ከንዙን ለወንድሞቼ እና ለእናቴ ወንድሞች አስረክቤ
መጣሁ አሁን በቁጥጥርህ ስር ሆኛለሁ ቅጣቱን ፈፅምብኝ በማለት ተናገረ።
‌‌
ዑመርም ተገረሙ ; በዚያው ማምለጥ የምትችል ሆነህ እንዴት ተመለስክ? ሲል ጠየቀው።
‌‌
‹‹ ሰዎች ዘንድ ቃል አክባሪነት ጠባቂነት/ ጠፋ እንዳይባል
ፈርቼ ነው››በማለት መለሰ።
‌‌
ዑመር ወደ አቡዘር ዞረዉ ይህን ሰው እነዴት ዋስ ሆነከው? በማለት ጠየቀ…………
‌‌
‹‹እኔማ ዋስ የሆነኩት በሰዎች ዘንድ ኸይር /መልካም/ ስራ ጠፋ እንዳይባል ፈርቼ ነው››ሲል አቡ ዘር መለሰ።

በሁኔታው የሟች ልጆች ልብ ተነካ…በቃ አፉ ብለነዋል…
ቅጣቱ እንዳይፈፀምበት ሲሉ ተናገሩ…
‌‌‌
ዑመርም ለምን? ሲሉ ጠየቃቸው…..‹‹እኛ ደግሞ
በሰዎች መሃል ይቅር መባባል ጠፋ እንዳይባል እንፈራለን›› አሉ……ሱብሃነላህ
‌‌
እኔ ደግሞ ሰዎች የሰሙትን አያደርሱም እነዳይባል ሰጋሁና ነገርኳችሁ😊
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

31 Oct, 18:26


FULL AUDIO!!!
ነቢ ዘይኔ እና ነቢ ሰላም አላ ረሱል ሰላም አላ
መሀመድ ነብዬ ሰላላ አላ  ﷺ ❤️

በኢድሪስ 😍 🎤🔊🗣 wow

👏👏👏👏👏👏👏👏👏Join 👉 @MEDINA_TUBE
@medinatube

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

29 Oct, 10:09


አዲስ ከተማ ት/ቤት ፖሊስ አስገብተው በሰላማዊ መንገድ በኒቃብ ጉዳይ የጠየቁ ተማሪዎችን እያስረበሹ ነው። ፖሊስ ሰላማዊ ዜጎችን ትቶ ኒቃቢስቶችን አሸባሪና ጽንፈኛ ያለውን ርዕሰ መምህርና አጋሮቹ አይዝም እንደ? ወይንስ እነርሱም ይስማማሉ?
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

29 Oct, 08:09


ነቢ ሰላም አላ ረሱል ሰላም አላ
መሀመድ ነብዬ ሰላላ አላ 😍👏👏👏

ኢድሪስ በሚያሚር ደምፁ ...😍

👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏Join 👉 @MEDINATUBE 👈

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

29 Oct, 08:08


ጌታው ነቢ ዘይኔ ... ﷺ ❤️
ኢድሪስ 😍 🎤🔊🗣
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏Join @MEDINATUBE 👈

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

29 Oct, 08:07


መሰማት ያለበት !👂

#ሼህ_መሃመድ_አወል_ሃምዛ_እንጉርጉሮ

👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏Join 👉 @MEDINATUBE 👈

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

29 Oct, 07:22


መንዙማ የሚለው ቃል ኢስላማዊ መዝሙርን የሚገልፅ ሲሆን ይህም በተለያዩ ሰሂህ ሀዲሶች ላይ በግልፅ ተፈቅዶ እናገኘዋለን፡-
→ በሰሂህ ቡኻሪ ቅፅ 2፣ መፅሐፍ 15፣ ቁጥር 70 ላይ እናታችን አዒሻ እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፡፡ ‹ጥቁር ባሮች በቀስትና በጋሻ እየተጫወቱና እየዘመሩ ትዕይንት ያሳዩ ነበር፤ በዚህ ዝግጅትም ላይ እንድታደም ነብዩ (ሰለሏህ ዐለሂ ወሠለሞ ) ጠየቁኝ እኔም መስማማቴን ገለፅኩላቸው፡፡ ከዚያም ከጀርባቸው እንድቆም አደረጉኝ ክርኖቼንም በትከሻዎቻቸው ላይ አድርጌ ትዕንቱን መከታተል ጀመርኩ፤ ከዚያም እስኪበቃኝ ድረስ ታድሜ ተመለስኩ፡፡››
► ሰሂህ አልቡኻሪ ቅፅ 2፣ መፅሐፍ 15 ቁጥር 72 ላይም በተጨማሪ እናታችን አዒሻ እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፤ ‹‹አቡበከር ወደኔ ቤት ሲገባ ሁለት ትናንሽ የአንሳሪ ሴት ልጃገረዶች ከአጠገቤ ሆነው ስለ ‹‹ቡአዝ ጦርነት›› ቀን እየዘመሩ (እያዜሙ) ነበር፤ አቡበክርም በቁጣ ‹‹የሸይጧን የሙዚቃ መሳሪያዎች በአላህ መልእክተኛ ቤት ውስጥ፡፡›› አለ፤ ከዚያም የአላህ መልእክተኛ ‹‹አቡበከር ሆይ ለእያንዳንዱ ህዝብ የመደሰቻ ቀን አለው ይህ የኛ የመደሰቻ ቀን ነው፡፡›› ብለውታል፤ በሌላ ዘገባም ‹‹ተዋቸው ይዘምሩ›› ማለታቸው ተዘገቧል፡፡ መንዙማ የአላህን የበላይነትና የነብዩን ህይወት የሚዘክር ነው፡፡ የአላህንንና የነብዩንም ወዳጆች ያወድሳል፤ ስለሆነም ከሀራም ክፍል ውሰጥ አይመደብም፡፡ ሁሉም ሙዚቃን የሚያወግዙ ሀዲሶች አብረው መጠጥን እና ዝሙትን ያወግዛሉ፤ ይህም ማለት ወደነዚህና መሰል እኩይ ተግባራት የሚመራ ሙዚቃ በኢስላም የተወገዘ እንደሆነ ያሳየናል፡፡ በመንዙማ ላይ የሚዘመሩ ዜማዎች ግን ፈፅሞኑ ወደነዚህ መጥፎ ሰራዎች አይመሩንም ይልቁኑ ወደ አላህ እንድንጠጋ መንገዱን ያመቻቹልናል፡፡ በረሱል (ሰዐወ) ፊት ብዙውን ግዜ የመንዙማ ትዕይንቶች ተካሂደዋል አብዛኛውንም ግዜ ሀበሻ ሶሀቦች በመንዙማቸው ይታወቁ ነበር፤ ነብያችንም መንዙማ ሀራም ቢሆን ኖሮ ፊትለፊታቸው ሲደረግ እያዩ ያስቆሙት ነበር ግን አላደረጉትም፤ ይልቁኑም ሌሎች ሶሃቦች ለማስቆም ሲሞክሩ መንዙማው እንዲቀጥል ነበር የሚደርጉት፡፡
☼ ዱፍ ወይም ድቤ በመጠቀም መንዙማ ለመብቃቱ መረጃ
► በማሊክ ልጅ አነስ በኩል በደረሰን ኢብን ማጃህ በዘገቡት ሐዲሥ ተጨማሪ መረጃ፣
ﺭﻭﻯ ﺍﺑﻦ ﻣﺎﺟﻪ ﻋﻦ ﺃﻧﺲ ﺑﻦ ﻣﺎﻟﻚ ﺃﻥ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻣﺮّ ﺑﺒﻌﺾ ﺍﻟﻤﺪﻳﻨﺔ ﻓﺎﺫﺍ ﻫﻮ ﺑﺠﻮﺍﺭ ﻳﻀﺮﺑﻦ ﺑﺪﻓﻬﻦّ ﻭﻳﺘﻐﻨﻴﻦ ﻭﻳﻘﻠﻦ : ” ﻧﺤﻦ ﺟﻮﺍﺭ ﻣﻦ ﺑﻨﻲ ﺍﻟﻨﺠﺎﺭ __ ﻳﺎ ﺣﺒﺬﺍ ﻣﺤﻤﺪ ﻣﻦ ﺟﺎﺭ .“ ﻓﻘﺎﻝ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ”: ﺍﻟﻠﻪ ﻳﻌﻠﻢ ﺍﻧﻲ ﻷﺣﺒﻜﻦ “
► የሐዲሡ ትርጉም፣
ከእለታት አንድ ቀን የአሏህ መልእክተኛ (ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም) መዲና መንገድ ላይ እየሄዱ ሳለ ልጃገረዶች ዱፍ እየመቱና «እኛ በኒ ነጃር ጎሳ ልጃገረዶች ነን፣ ከሙሐመድʷ ጋር ጎረቤት መሆናችንን እንወዳለን፣» እያሉ ሲዘፍኑ አዩአቸው፣ ያን ጊዜ የአሏህ መልእክተኛም (ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም) «አሏህ ያውቃል እኔም እንደምወዳቹህ» ብለው መለሱላቸው፡፡ በዚህ ሐዲሥም ልጃገረዶቹ ዱፍ እየመቱ የአሏህ መልእክተኛን ሲያወድሱ ነቢያʷችን (ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም) ዱፍ መምታትና መንዙማ ክልክል ቢሆን ኖሮ “አሏህ ያውቃል እኔ እንደምወዳቹህ” ከማለት ይልቅ የምታደርጉት ሐራም ነው በማለት ሐራምነቱን ያሳውቋቸው ነበር፣ ምክንያቱም እርሳቸው የተላኩት አሏህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) ባዘዘው ለማዘዘና በከለከለው ለመከልከል ነው። አንዳንድ ሰዎች ነቢያʷችን (ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም) ሐራም ያላደረጉትን (ክልክል ነው ያላሉትን) ሐራም ለማድረግ ይሞክራሉ፣ በዚሁ ሐዲሥ በመጨረሻው ላይ የአሏህ መልእክተኛ (ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም) ለዑመር ያሉትን ቃል በመጠቀም «አንተ ዑመር ሆይ ሸይጣን አንተን ይፈረሃል እኮ!» ያሉትን እንደ መረጃ በመውሰድ ዱፍ ወይም ድቤ በመጠቀም መንዙማ ማድረግ የሼይጣን ስራ ነው፣ ሐራም ነው ይላሉ፣ ግን ቃላቸው ውድቅ መሆኑን ከሐዲሡ መጀመሪያው ላይ ዱፉን በመምታት ነዝሩዋን (ስለቷን) እንድታሟላ ከመፍቀዳቸውም በላይ ፊትለፊታቸው ሆና እየዘፈነች ዱፉንም እየመታች ዝም ማለታቸው ሐራም እንዳልሆነ ትልቅ መረጃ ነው። ስለዚህ በዝህኛውም ሐዲሥ ዱፍ መምታትና መንዙማ የሚፈቀድ ለመሆኑ ተጨማሪ መረጃ ነው። አንዳንዶቹም ልከዱት የማይቻል የተለያዩ ሐዲሦች በመኖራቸው ዱፍ መጠቀምን ለዒድ፣ ለሰርግና፣ ከውጭ ሀገር ቆይቶ ወደ ሀገሩ ለተመለሰ ሰው ያለንን ደስታ ለመግለጽ፣ እንድሁም ለስለት ብቻ በማለት ይወስኑታል። ለነኝህ ምላሻችን ለዒድ፣ ለሰርግና ከውጭ ሀገር ቆይቶ ወደ ሀገር ቤት ለተመለሰ ያለን ደስታን ለመግለጽ የምፈቀድ ከሆነ ለዘላለም መኖሪያችን የምሆን ገነትን እንድናገኝ ከእምነት (ከኢማን) ጋር መጥተው ተውሒድን ያስተማሩን ለነቢያʷችን ሙሐመʷድ (ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም) ካለን ደስታ ይበልጥ ደስታ ይኖራል እንዴ?
አሏህ ተዓላ አዕለም ወአሕከም።
►አላህ በጭፍን ከመመራት ይጠብቀን፤ በመረጃ ከሚመሩትና ውዴታውንም ከሰጣቸው ሰዎች ያድርገን አሚን፡፡ 🙏
{ @MEDINATUBE }

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

29 Oct, 07:22


#ስለ መንዙማ አንዳንድ ነገር አቅርብልን ላላቹ!👇

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

26 Oct, 14:18


🤍ቁርዐንን ጨምሮ ሁሉን በአንድ የያዘውን ሁለገብ ቻናላችንን ተጋበዙልኝ 🕌

🚫ወላሂ የውሸት ማስታወቂያ አይደለም🚫

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

26 Oct, 07:53


📍ተወዳጅና አዝናኝ ቂሳዎች፣ ከውብ ንግግሮችና ቁርዓን😘 ጋር የያዘች ቅመም የሆነች ቻናል ተቀላቀሉ 😇

🚫ወላሂ የውሸት ማስታወቂያ አይደለም🚫
ሙስሊም አይዋሽም

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

25 Oct, 20:34


Full Audio !!!
የመካው ጨረቃ...🙏❤️😍
@MEDINATUBE
አሽቁ 😍👏😍👏😍👏

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

25 Oct, 12:26


የመካው ጨረቃ...🙏❤️😍
@MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

23 Oct, 14:29


🤍ቁርዐንን ጨምሮ ሁሉን በአንድ የያዘውን ሁለገብ ቻናላችንን ተጋበዙልኝ 🕌

🚫ወላሂ የውሸት ማስታወቂያ አይደለም🚫

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

20 Oct, 21:55


👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏Join 👉 @MEDINATUBE 👈

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

20 Oct, 21:31


የነብዩ ሙሐመድ ({ሰ.ዐ.ወ})መነካትን ያስቋጣው
ተአምረኛው ውሻ ምን ሰራ?!!

ኢብኑ ሐጀር አል ዐስቃለኒ አዱረሩል
ካሚና በተባለው ኪታባቸው ቀጣዩን
ታሪክ አስፍረዋል!!
(ሞንጎላዊያን)ሙስሊም ሀገራትን በወረሩበት ወቅት፤ሆላኮ ሚስቱ ዞፈር ኻቱን ክርስቲያን በመሆኗ ለክርስቲያን አክፍሮት ሀይላት ሰበካ እንዲያደርጉ በፈቀደላቸው መሰረተ(ለሞንጎላዊያን)መሪዎችን ቢከፍሩልን ብለው በማሰብ ሰበካቸው አጧጡፈው ነበር፤ በአንድ ጊዜ ታድያ አንድ ሞንጎላዊ ባለ ስልጣን፤ክርስትናን በመቀበሉ ታድያ
ትልቅ ድግስ አዘጋጁ፤በዝግጅቱም ትላልቅ የእምነቱ ተከታዮች እና መሪዎች ተጋብዘው ነበር፤በፕሮግራሙም መሰረት አንድ ታዋቂ የእምነቱ ሰባኪ ንግግር ለማድረግ ወደ መድረኩ በመውጣት ነግግር ማርግ ጀመረ፤ታድያ ገና ከጅምሩ፤የአላህ መላክተኛን
({ሰ.ዐ.ወ})አንቋሾ መሳድብ ጀመረ፤
በቅርብ እርቀት ላይ የታሰር አንድ የአደን ውሻ ታስሮ ነበር፤ሰባኪው ነብዩን ሙሐመድን({ሰ.ዐ.ወ}) ምን መሳደቡን አላቆመም ነበር ታድያ በሚገርም ሁኔታ.የእሳቸውን መነካት ክፉኛ አስቆጥቶት፤ዘሎ ያዘው፤እንደምን ብለው አስለቀቁት እና ራቅ አድርገው አሰሩት፤ታድያ አንድ የውሻው ቁጣ የገባው ለሰባኪው እንዲህ አለው! ይሄ ውሻ ነብዩ ሙሐመድን ({ሰ.ዐ.ወ})በመሳደብህ ነው የተቆጣ
እና ከድርጊቱ እንዲ ቆጠብ ምክር ቢጤ ነገረው፤ታድያ ሰባኪው ግን ሽንፈት መስሎ ስለታየው፤ መሳደቡን ማቆም አልደፈረም ነበር፤እንዲህ አለ ውሻውን ዞር ብሎ በጣቱ እያሳየ ይህ ውሻ በጣም ልበ ሙሉና ቁጡ ነው እጄን እያወራጨሁ ሳወራ ልመታው መስሎት ነው እንጂ ሙሐመድን ስለተሳደብኩኝ
አይደለም ብሎ ለህዝቦቹ አስተባብሎ ንግግሩን ቀጠለ፤
እንደውም ከመጀመሪያው በበለጠ ነብዩን ሙሐመድን ({ሰ.ዐ.ወ})ማንቋሸሹን
ቀጠለ፤ታድያ ይሄ የአላህ መላክተኛን መሳደቡን ውሻን በጣም አስቋጣው፤የውሻውን ቁጣ ከምንም፤ሳይቆጥር መሳደቡን ቀጠለ፤ታድያ ውሻው ይባስ ስላስቆጣው፤ሰንሰለቱን በመበጠስ፤ዘሎ አንገቱን ያዘው፤ሰዎች
ከተቀመጡበት፤እስኪ ነሱ አንገቱን ቀንጥሶ ጣለው፤ታድያ 40 ሺ የሚቆጠሩ የሞንጎላዊያን ሰዎች ድግሱ ላይ ተሳትፈው ነበር፤ያለማንም ቀስቃሽነት
እስልምናን ተቀበሉ፤(ሱብሀነሏህ)
((አዱረሩል-ካሚና-ቅፅ-3-ገፅ-202))
ፊዳከ አቢ ወዑሚ ወነፍሲ ወሩሂ ወደሚ ወኩሉ ማአምሊኩ ያሀቢቢ
ያረሱለላህ({ሰ.ዐ.ወ})
ኢሽተቅናክ ያረሱለላህ!!

join @MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

20 Oct, 21:26


Artist: FUAD Mohammed
Catagory: Menzuma
About: Qiyamah
#Part: 1
😍😍😍😍😍😍😍🙏😍😍🙏😍
Join 👉 #MEDINATUBE 👈

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

20 Oct, 21:22


من طرائف رأفة النبي ﷺ ﷺ ﷺ
ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ
ለኡመቴ የሚደርሰውን ፈተና ግማሹን እኔ ተፈትኘዋለሁ ከመካከላችሁ አንዳችሁ ፈተና በደረሰባችሁ ግዜ የኔን ፈተና አስታውሱ የኔ ትልቅ ፈተና ነው እና
ይህን ታላቅ ሰው እንየው እስኪ ለኡመቱ ሲል ምን አሳለፈ??
ከእለታት አንድ ቀን በመካ ዙሪያ እያሉ ኡቅበቱ ኢብኑ አቢ ሙአይጥ የተባለ የካፊሮች ባለ አባት በሁዋላቸው መጥቶ ትከሻቸውን ይዞ አንገታቸውን በጨርቅ በጣም አነቃቸው ማንን???😰😰😰
ለኛ ሲሉ የሚንሰፈሰፉትን ታላቅ ነብይ 😢😢
በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳሉ አቡ በክር አሲዲቅ ይደርሱና የኡቅባን ትከሻውን ይዘው ይገፈትሩታል
ያ አሏህ!!!!  ምን ይሰማቸው ይሆን አቡ በክር እኛስ ይህን ክስተት ብናይ ምን እንል ነበር
አቡ በክርም ቃላቸው ይህ ነበር
ጌታየ አንድ አሏህ ነው ስላለ ልትገድሉት ነው እንዴ?????
እስኪ ለኛ ብለው ለደሙት ነብይ ሶለዋት እናውርድ
ያ ሀቢቢ ያ ረሱለሏህ😥😥😥 ﷺ  ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
JOIN 👉 @MEDINATUBE

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

06 Oct, 17:59


#AddisAbaba : በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የመሬት ንዝረት እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በአንዳንድ ቦታዎችም ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች በስጋት ወደ መሬት ወርደው ተሰብስበዋል።

©tikvahethiopia
@medinatube

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

06 Oct, 14:17


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ  እንደት ናችሁ ያጀመዓ 🌷

ቀላል ጥያቄ
🍹ሁላችሁም ተሣተፉ ባረከላሁ ፊኩም 🍹
@medinatube

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

05 Oct, 15:44


ህይወት የፈተነቻት የትዳር ህይወቶ በእጅጉ የከበዳት አንዲት ሴት ወደ አንዱ ሀብታም ትሄድና በሩን ታንኮኮለች

ከቤቱም አንድ ሰራተኛ ይመጣና ምን ፈልገሽ ነዉ ይላታል?

እሷም አለቃህን ማገኘት ፈልጌ ነዉ ስትል መለሰች
ሰራተኛዉም ማነሽ አላት ..?

እህቱ እንደሆንኩ ንገረዉ አለቺዉ...

ሰራተኛዉ እህት እንደሌለዉ ቢያቅም ለአለቃዉ ገብቶ የሆነች ሴት እህቱ ነኝ ብላ በር ላይ ቁማለች አለዉ ::

አለቃዉም አስገባት አለዉ ...

ሴትየዋም እንደገባች አላህ ይዘንልሽና የምን እህቴ ነሽ አላት?

እህትህ በአደም አለይሂ ሰላም አለቺዉ

ሰዉየዉም በልብ የተሰበረች ትመስላለች የሚጠግናት
የመጀመሪያዉ እሆናለሁ ሲል ነየተ

እሷም ወንድም መቼስ ላንተ አይነቱ ሰዉ የድህነት ጠአም ላታቅ ትችላለህ በዚህ ችግር እኔና ባሌ ለፍቺ በር ላይ ቁመናል እናንተ ዘንድ ለመገናኛዉ ቀን የሚሆናቹህ ይኖራል ወይ! እናንተ ዘንድ ያለዉ ያልቃል አላህ ጋር ያለዉ የማያልቅና በላጭ ነዉ አለቺዉ ...
@medinatube
ድገሚልኝ አላት .....

ላንተ አይነቱ ሰዉ የድህነት ጠአም ላታቅ ትችላለህ በዚህ ችግር እኔና ባሌ ለፍቺ በር ላይ ቁመናል እናንተ ዘንድ ለመገናኛዉ ቀን የሚሆናቹህ ይኖራል ወይ! እናንተ ዘንድ ያለዉ ያልቃል አላህ ጋር ያለዉ የማያልቅና በላጭ ነዉ አለቺዉ


ሶስት ጊዜ ድገሚልኝ እያላት ደገመቺለት በአራተኛዉም ድገሚዉ ሲላት የገባህ አይመስለኝም መደጋገም እኮ ዉርደት ነዉ እኔ ደሞ ከአላህ ዉጪ ራሴን ማሳነስ አሎድም አለቺዉ

እሱም በአላህ ይሁንብኝ ንግግርሽ ስላማረኝ እንጂ ሌላ አልነበር መቶ ጊዜ ደጋግመሽ በነበር ለአንዱ መቶ ዲርሀም እሰጥሽ ነበር

ለሰራተኛዉም ከግመል አስር ከበግ የፈለገቺዉን ያሀል
ከገንዘብም የፈለገቺዉን ስጣት ለመገናኛዉ ቀን እንዲሆነን እኛ ዘንድ ያለዉ አላቂ ነዉ አላህ ዘንድ ያለዉ የተሻለ ነዉ

ሴትየዓም ደስተኛ ሁና ወደ ቤቷ ተመለሰች
@medinatube

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

05 Oct, 15:32


#ፍቅር ማለት፦ቁረይሾች ነብዩን ﷺ በተኙበት ሊገድሏቸው ሲመጡ አልይ እብን አቢ ጧሊብ 'እርሰዎን ከሚገድሉ እኔን ይግደሉኝ 'ብለው በቦታቸው ላይ ተኝተው መገኘታቸው ነው።
---------
#ፍቅር ማለት ፦ነብዩ ﷺ ሚስታቸው ዓኢሻ በጠጡበት እቃ በጠጡበት ቦታ ላይ መርጠው መጠጣታቸው ነው።
--------
#ፍቅር ማለት፦ነብዩ ﷺ ለባልደረባቸው ሰውባን ረ.ዐ ምንድነው ፊትህን የቀየረው? ብለው ሲጠይቁት «በሽታም ሆነ ህመም የለብኝም፤ ግን አንቱን ሳላገኝ ስቀር ከባድ የሆነ ብቸኝነት ይሰማኛል፤ አንቱን እስከማገኞዎ ድረስ» ማለቱ ነው።

---------
#ፍቅር ማለት፦አቡበከር አስ-ሲዲቅ ረ.ዐ ከነብዩ ﷺ ጋር በሂጅራ ጉዟቸው ወደ ዋሻ ከመግባታቸው በፊት «ወሏሂ ካንቱ በፊት ካልገባው በስተቀር አትገቡም፣ የሆነ ነገር ቢኖር እንኳ ካንቱ በፊት እኔን ይጉዳኝ» ማለታቸው ነው።

--------
#ፍቅር ማለት፦ቢላል አል-ሐበሺይ ረ.ዐ ነብዩ ﷺ ሲሞቱ የነብዩ ﷺ ፍቅር መዲና አላስቀምጥ ብሎት አዛን ማድረጉን መተዉና መዲናን ጥሎ መሄዱ ነው፤ ይህ ብቻም ሳይሆን ነብዩ ﷺ በህልሙ መጥተውበት ለምን አትዘይረንም? ሲሉት ገና ሌሊቱ እንደነጋ የነብዩን ﷺ ቀብር ዚያራ ለማድረግ መጓዛቸው ነው፤ ከዛም አዛን እንዲያደርግ ለምነውት ያን አዛን ሲያደርጉ የመዲና ህዝብ በሙሉ በእንባ መራጨቱ ነው። ነብዩ ﷺ ከሞቱ በኃላ እንጂ እንደዛ አይነት እልቅሻ አልታየም ተብሎ በታሪክ ኢስኪፃፍ ድረስ።

---------
#ፍቅር ማለት፦ ከበኒ ዲናር የሆነች ሴት ባሏ፣ አባቷና ወንድሟ ወደ «ኡሑድ» ዘመቻ ወጥተው ሳለ ሙስሊሞች ከውግያው ሲመለሱ ሁሉም እንደሞቱ ሲነገራት «ነብዩ ﷺ እንዴት ሆኑ? ብላ መጠየቋ ነው፤ ከዛም እሳቸው አልሞቱም ሲሏት እሳቸውን ካላየው ብላ ነብዩን ﷺ ስታያቸው «ካንቱ በኃላ ያለ ሙሲባ ሁሉ ለኔ ገር ነው» ማለቷ ነው።

--------
#ፍቅር ማለት፦ ዙበይር ረ.ዐ የ15 አመት ወጣት ሆኖ የነብዩን ﷺ መገደል የውሸት ወሬ ሲሰማ የመካ መንገዶች ላይ ሰይፉን እየጎተተ መውጣቱ ነው።

---------
#ፍቅር ማለት፦ረቢዐተ ኢብን ከዕብን ረ.ዐ ነብዩ ﷺ ምንድነው ሓጃህ (ጉዳይህ) ሲሉት ካንቱ ጋር በጀነት ጓደኛ መሆን ነው ማለቱ ነው።
ፍቅርን ፍቅር ከሆነ ሰው ተማር!!!

/እኛም ነብዩን ﷺ ትክክለኛ ፍቅር የምናፈቀርና ከርሳቸው ጋር የምንቀሰቀስ አላህ ያድርገን --ሰው ከሚወደው ጋር ነውና የሚቀሰቀሰው

@Medinatube

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

05 Oct, 15:08


አንድ ሰዉ ነበረ ወራቱን የሚያዉቀዉ
እልፍ ብሎ ሔደ ዘበን ሳንጠይቀዉ😥💔

ወንድሜን ያመዋል
እኔንም ያመኛል

እሱ ሲሽርልኝ እኔም ይሻለኛል
አንቱ ስትጠሩን እኛን ይተወናል

ላንቱ መንገር ትቸ ለሰው ነገርኩና
ገራ ያለው ነገር ተመልሶ ጠና
ባመትም ባመትም ይበላል እሸት
እንደምነሁ አባ የድሃዉ አባት

የኔማ በሻሻ
የድሃ መሸሻ

ነሁና ወጌሻ

ለራበዉ መጉረሻ
ለታረዘዉ መልበሻ
የርሃብ ማስታገሻ

ወንድም አይረሳም ቢርቅም ሃገሩ
ሷሂብ አይረሳም ቢርቅም ሃገሩ
የኔማ ወንድሜ ገታ ነዉ መንደሩ
የኔማ ሪዷን ገታ ነዉ ሰፈሩ💚

የኔማ እህቶች ገታ ሲሳፈሩ
ለጉድ ይገረማሉ ደዉር ሲደዉሩ
ባሏሁመሶሌ ሃድራዉን ሲመሩ
የዱአ ሚሳኤል ከቶም ሲጀባቡ
ያሰኛል አጃኢብ መጅሊሱ ድባቡ

ገታ ከተማ ስር በቅለዉ ሙጘየቡ
ስምወ ይባላል ሙሕይዲን አረቡ
ፈጥኖ ደራሽ ነወት ከቶ ለተራቡ
አይኔ እንባ ሲያፈስ ለሆዴ መራቡ
ጠራንሁ ጌቶቸ አንዴ ለኛ ግቡ
ከተማችን ይድመቅ በሻሻዬ አህሪቡ
ወቁረቲይ አይኒ ሹርቡል ወመህቡቡ
የጠናዉ ይገራል ቁጥቤ ሙጘየቡ🥰
@medinatube

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

04 Oct, 15:49


ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:-
እኔ አምስት ስሞች አሉኝ:-
① እኔ ሙሀመድ ነኝ፣
② እኔ አህመድ ነኝ
③ እኔ ማሂ ነኝ፣
④ እኔ ሃሽር ነኝ፣
⑤ እኔ ዓቂብ ነኝ።
📒ቡኻሪ ዘግበውታል
@medinatube
ትርጉማቸው👇
❶)ሙሐመድ:- ማለት ምስጉን ማለት ነው፣
❷) አሕመድ:-ጌታውን በጣም የሚያመሰግን ወይም ራሱ በጣም የተመሰገነ፣
❸)ማሒ:-ማለት አላህ እኔን በመላኩ ክህደትን የማስወግድ የማብስ ነኝ ብለዎል፤
❹) ሓሺር:- ማለት ሰዎች ሁሉ ከእግሬ ስር የሚቀሰቀሱት ነኝ ብለዎል፤
❺) ዓቂብ:-ከእኔ በኋላ ነቢይ የለም ብለዎል።
||
ካነበባችሁ በሓላ ሼር አድርጉት ‼️
@medinatube

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

04 Oct, 14:05


Medina Tube || መዲና ቲዩብ pinned «https://youtu.be/cXolINBMYoY?feature=shared»

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

04 Oct, 14:04


https://youtu.be/cXolINBMYoY?feature=shared

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

04 Oct, 14:04


#ሰለዋት…

የላቀውና ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል፦

﴿اِنَّ اللّٰهَ وَمَلٰٓٮِٕكَتَهٗ يُصَلُّوۡنَ عَلَى النَّبِىِّ ؕ يٰۤـاَيُّهَا الَّذِيۡنَ اٰمَنُوۡا صَلُّوۡا عَلَيۡهِ وَسَلِّمُوۡا تَسۡلِيۡمًا‏﴾

“አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡”

📚 አል‐አህዛብ: 56

ረሱልም (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنَّ مِن أفضَلِ أيّامِكم يومَ الجُمعةِ، فأكْثِروا عليَّ الصلاةَ فيه؛ فإنَّ صلاتَكم مَعروضةٌ عليَّ.﴾

“ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።”
@medinatube
📚 አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል: 1531

በሌላ ሀዲሳቸው ﷺ፦

﴿أكثِروا الصَّلاةَ عليَّ يومَ الجمُعةِ و ليلةَ الجمُعةِ، فمَن صلّى عليَّ صلاةً صلّى اللهُ عليهِ عَشرًا.﴾

“በጁምዓ ቀንና ሌሊት በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዙ። በኔ ላይ አንድን ሰለዋት ያወረደ አላህ አስር ሰለዋትን ያወርድለታል።”
@medinatube

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

04 Oct, 11:48


የሐጅ አስማማው ዩሱፍ አ/ቃድር የቀብር ስነ ስርአት በኮልፌ ሙስሊም መካነ መቃብር ተከናወነ
**
በቀድሞው የኢ/እ/ጉ/ጠ/ምክር ቤት የጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን ያገለገሉትና የተለያዩ የሙስሊሙን ክይወትና ማህበራዊ መስተጋብር የሚቃኙ ፅሁፎች ደራሲ የነበሩት ሐጅ አስማማው ዩሱፍ ስርአተ ቀብራቸው ዛሬ መስከረም 23/2017 በኮልፌ ሙስሊም መካነ መቃብር ተከናወነ::

አላህ በጀነተል ፊርደውስ ይቀበላቸው ለቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው ሰብሩን ያድል! አሚን!
@medinatube

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

04 Oct, 08:25


"ኢሬቻ ላይ ሄዶ የመጣ ሙስሊም ገላውን ታጥቦ ሸሃዳ ይዞ ካልሆነ በስተቀር ወደ መስጂድ መግባት አይችልም" ታላቁ ዓሊም ሙፍቲ ሸይኽ አደም ቱላ (ረሒመሁላህ)
@medinatube

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

03 Oct, 19:32


ዱኒያ‼️
~~~~
ዱኒያ ማለት ፈተና የበዛበት የውሸት አለም ነች፣ በአጭሩ ይች ዱንያ ማለት ወደ አኼራ የምንሸጋገርባት አጭር ድልድይ ነች!!

አንድ ኡስታዝ ዱኒያን ሲገልፅ የማረሳውን አገላለፅ ላካፍላችሁ እንዲህ አሉ:-

ዱንያን ሲመስላት «ዱኒያ ማለት አደባባይ ላይ የቆመች ቆንጆ ሴት ነች! አንዱ መጥቶ በቁንጅናዋ ተማርኮ "ላግባሽ ይላታል" እርሷም እሺ! ትለዋለች። ቆንጆይቱ የቆመችው አደባባይ ላይ ነው ሁሉም ያያታል! በመቀጠልም ሌላኛው መጣ፤ እርሱም "ላግባሽ" ይላታል። እርሷም እሺ! አግባኝ የሚል መልስ ለሁሉቱም ትሰጣለች። በዚህ ግዜ ሁለቱ ሰዎች አደባባይ ላይ ባለችው ቆንጆ ይጣላሉ።

ይህንንም ተከትሎ ወደ ፍርድ ቤት ያቀናሉ። ፍርድ ቤት ቀረቡ። ዳኛውም በምን ተጣልታችሁ ነው እዚህ የመጣችሁት ይላቸዋል። መጀመሪያ ላይ ላግባሽ ያላት እንዲህ አለ "እኔን እንደምታገባኝ ከእኔ ጋር ቃል ገብታ ነገር ግን ይኸኛው በእኔ ላይ ጣልቃ ገብቶብኝ ነው የተጣላነው" የሚል ክሱን አቀረበ። ዳኛውም እስኪ አንድ ግዜ ሁለታችሁም ውጭ ቆዩ እርሷንም በምን እንደተጣላችሁ ልጠይቃት ይላቸዋል።
እነርሱም ተያይዘው ወጡ።

ዳኛው በቁንጅናዋ ተማርኮ፤ ቆንጆዋን "ለምን ከዚህ ሁሉ እኔ አላገባሽም" ይላታል። እርሷም እሺ! ትለዋለች።

በዚህም ምክንያት ሊካሰሱ የመጡትና ዳኛው በልጅቱ ይጣላሉ።
ነገር ግን በዚህ መሀል እርሷ እንዲህ አለች:- "ከዚህ ሁሉ ሶስታችሁንም የሚያስታርቅ ሀሳብ አለኝ ከተስማማችሁ?" ትላቸዋለች።

" እኔ ወደፊት እሮጣለሁ እናንተ ከሗላ ተከተሉኝ፤ እኔን መጀመሪያ የያዘኝ ያገባኛል ነገር ግን በዚህም ውስጥ አንድ መስፈርት አለኝ፤ እርሱም ስትሮጡ እኔን ብቻ ተመልከቱ ወደ ጎን መዞር፣ እርስ በእርስ መተያየት አይቻልም ይህ ነው ሀሳቤ" ትላቸዋለች። በዚህ ሀሳቧም ይስማማሉ።

ሩጫውም ተጀመረ እርሷ ላይ ለመድረስ ሲሮጡ፤ ዳኛው ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ወድቆ ይሞታል፣ ሁለቱ አላዩትም! በመቀጠልም አንድኛው ይከተላል፣ ሌላኛውም ይቀጥላል።

በመጨረሻም ሶስቱም አግቢኝ ባዮች ቆንጆይቱን ሳይደርሱባት ሞቱ።

ይህቺ ናት ዱኒያ እኛ ዛሬ አንዱን ወንድማችንን ወደ አኼራ ሽኝተን በዱኒያ ቁንጅና ተማርከን መሮጣችንን ቀጥለናል፤ ከጎናችን ዱኒያን ትተዋት የሄዱትን አንመለከትም ነገ ከነገ ወዲያ እኔ፣ አንተ፣ አንቺም ተረኞች ነን።

በመጨረሻም ሽይኹ ይህንን ጨመሩ «ዱኒያ ማለት አደባባይ ላይ የቆመች የአሮጊት ቆንጆም ናት» አሉ። አባባሉን ሲያብራሩም እንዲህ ይላሉ:-
ዱኒያ አደባባይ ላይ የቆመች ናት ሲባል:- ዱኒያን ሁሉም ያያታል፣ ለመያዝም ይፈልጋታል፣
የአሮጊት ቆንጆ ነች ሲባል ደግሞ:- ዱኒያ ያኔ የእኛን ቅድመ አያቶች፣ አባቶች አድክማ ሳይዟት ትተዎት የሄዱ፣ እንዲሁም እኛም የምንይዛት እየመሰለንና ሁሌም ቆንጆና፣ አዲስ መስላ እየታየችን እርሷን ለመያዝ እንደክማለን ለዚያም ነው ዱኒያ የአሮጊት ቆንጆ ናት ያልኳችሁ» ብለው ዱኒያን ገለፁ።

ዱኒያ ላይ ዛሬ ተደስተህ፣ ነገ ታለቅሳለህ ዛሬ አግኝተህ፣ ነገ ታጣለህ ፈተናውን ሁሉ አልፌ ጥሩ ደረጃ ላይ ደርሻለሁ ብለህ ኡፎይ ስትልና የእረፍት ኑሮ መኖር ስትጀምር፤ ድንገት ሳታስበው የሰበሰብከው ሁሉ ይበተናል።
ለእኛ ለሙስሊሞች ዱኒያ እዚህ ምድር ምንም አይደለች፣ እንደውም እስር ቤት ናት።

የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-
«ዱኒያ ለሙዕሚኖች እስር ቤት ናት ለካፊሮች ደግሞ ጀነት ነች»።@medinatube
ﻗﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ - ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ:
«ﺍﻟﺪﻧﻴﺎ ﺳﺠﻦ ﺍﻟﻤﺆﻣﻦ ﻭﺟﻨﺔ ﺍﻟﻜﺎﻓﺮ.»
አምላካችን አላህም እወቁ ዱንያ የመታለያ ጥቅም እንጅ ሌላ አይደለችም ይለናል:-
اعْلَمُوا أَنَّمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا لَعِبٌ وَلَهْوٌ وَزِينَةٌ وَتَفَاخُرٌ بَيْنَكُمْ وَتَكَاثُرٌ فِي الْأَمْوَالِ وَالْأَوْلَادِ ۖ كَمَثَلِ غَيْثٍ أَعْجَبَ الْكُفَّارَ نَبَاتُهُ ثُمَّ يَهِيجُ فَتَرَاهُ مُصْفَرًّا ثُمَّ يَكُونُ حُطَامًا ۖ وَفِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَمَغْفِرَةٌ مِّنَ اللَّهِ وَرِضْوَانٌ ۚ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ
ቅርቢቱ ሕይወት ጨዋታና ዛዛታ፣ ማጌጫም፣ በመካከላችሁም መፎካከሪያ፣ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መኾንዋን ዕወቁ፡፡ (እርሷ) በቃዩ ገበሬዎችን እንደሚያስደስት ዝናም፣ ከዚያም በቃዩ እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደምታየው፣ ከዚያም የተሰባበረ እንደሚኾን ብጤ ናት፣ በመጨረሻይቱም ዓለም ብርቱ ቅጣት ከአላህም ምሕረትና ውዴታ አልለ፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ ጥቅም እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
[ሱረቱል-ሐዲድ (20)]

ጭንቀትህ ለዱኒያ ሳይሆን ለአኼራ መሆን ሲጀምር የውስጥ ሠላምና መረጋጋት ታገኛለህ።

ጀሊሉ እንኳን ርካሿን ዱኒያን ውድና ውብ የሆነቺዋን ፊርደውሰል አዕላን ይሰጣል!
ብዙ አትጨነቁ ዱኒያ ለተጨነቀላትና ለጓጓላት አትሆንም።
ረሱላችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በሀዲሳቸው «ጭንቀቱ ዱኒያ የሆነች፣ አላህ (ሱብሃንሁ ወተዓላ) ድህነትን በዓይኖቹ መሀከል ያደርግበታል፣ ነገሩን ሁሉ ይበትንበታል፣ ከዱኒያም የተወሰነለት እንጂ ወደሱ አይመጣም» ብለዋልና!

ራስን ሳያስጨንቁና ድንበር ያለፈ ጉጉት ሳይኖር የተከተበልንን በሀላሉ መፈለግ ነው።
እና ለዱኒያ ብዙ መጨነቅ አያስፈልግም።
ለዱኒያ ኑሮ፣ ጣጣ፣ የምንጨነቅ ሳይሆን ለአኬራችን የምንጨነቅ አላህ ያድርገን።
መልክቱ ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ሼር አድርጉት።
#ሼር!
@medinatube

Medina Tube || መዲና ቲዩብ

03 Oct, 17:58


ሃያት ሸሆቹ!
@Medinatube

3,705

subscribers

235

photos

58

videos