Afri ፈጣን መረጃ @afritoday Channel on Telegram

Afri ፈጣን መረጃ

@afritoday


እንኳን ደህና መጡ። ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎች በፍጥነት የሚያገኙበት ትክክለኛው የAfri today (Afri ፈጣን መረጃ )
የቴሌግራም ቻናል ነው ። እናመሰግናለን።
📢 ፈጣን ሀገራዊ መረጃዎች
📢 ዓለም ዓቀፍ መረጃዎች
📢 አዝናኝ እና አስተማሪ መረጃዎች
📢 ወቅታዊ ጉዳዮች
📢 ሁሉንም በአንድ የሚያገኙበት ቻናል ነው ።

Afri ፈጣን መረጃ (Amharic)

እንኳን ደህና መጡ። ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎች በፍጥነት የሚያገኙበት ትክክለኛው የAfri today (Afri ፈጣን መረጃ) የቴሌግራም ቻናል ነው። በዚህ ቻናል ውስጥ በፈጣን ፋሲል ሀገራዊ መረጃዎችን ስለአዲስ መሣሪያዎችና ቅርስ ሀላፊዎች ይመልከቱ። በማንኛውም በትምህርት ወደ መሳሪያው እንደገና እባኮት። የባለሙያ በጣም መሠረት ላይ ስለመለያየት እንቅስቃሴ።

Afri ፈጣን መረጃ

07 Dec, 17:00


ንብረት እየወደመ እንደ ዜጋ ሀላፊነቱን የማይወጣ ሰው መብዛቱ የጤና አይመስለኝም!

Afri ፈጣን መረጃ

07 Dec, 06:30


ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ ለጉልበት ንቅለ ተከላ ህክምና የሚያስፈልገውን 3 ሚሊየን ብር አገኘ

ትናንት ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት በሸራተን አዲስ ሆቴል ላሊበላ አዳራሽ በተዘጋጀው ”ነፃነት“ የስዕል አውደርዕይና ጨረታ ሽያጭ ለህክምና የሚያስፈልገውን ወጪ ሙሉ በሙሉ ማግኘት መቻሉን አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡

በኹነቱ ላይ ጓደኞቹ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በብሩክ የሺጥላ የቀረቡ የእጅ ስራ የጥበብ ውጤቶችን በጨረታና በመደበኛ ግዢ በመፈፃም ወጪው እንዲሳካ ማድረጋቸው ታውቋል።

በተለይ አንድ ማንነታቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ደግ ልብ ያላቸው ግለሰብ ከፍ ያለ ድጋፍ በማድረግ ብሩክንም ሆነ በአዳራሹ የታደሙ እንግዶችን አስደስተዋል፡፡

ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላ በበኩሉ ህክምናው እንዲሳካ ላደረጉት ሁሉ ምስጋናውን አቅርቦ አጠቃላይ ዝግጅቱ የተሳካ በመሆኑ መደሰቱን አስታውቋል፡፡

የህክምና ወጪው እንዲሳካ በማድረግ እገዛ ላደረጉለት ተቋማትና ግለሰብ የምስጋና ስጦታ አበርክቷል፡፡

በጨረታ ከቀረቡት የስዕል ስራዎቹ መካከል
ይቅርታ፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ ምስጋና፣ ሰኔ 30 እና ጦርነትን ማብቃትና ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው፡፡

Via:- 👉አራዳ ኤፍ ኤም

Afri ፈጣን መረጃ

05 Dec, 20:32


ጠ/ሚ ዐቢይ(ዶ/ር) ከትግራይ ክልል የፖለቲካና የጸጥታ አመራሮች ጋር ተወያዩ

ሕዳር 26፣ 2017 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከትግራይ ክልል የፖለቲካና የጸጥታ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

የፌዴራል መንግስትና የትግራይ ክልል አመራሮች በክልሉ የጸጥታና የፖለቲካ አስተዳደር ጉዳይ ላይ ያተኮረ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ፥ በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን እንዴት በጋራ መፍታት እንደሚገባ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ በተለዩ አንኳር ጉዳዮች ላይ በተቀመጡ የጋራ አቅጣጫዎች መሠረት በጋራ ለመስራትና የክልሉ ህዝብ የፀጥታ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ፍላጎት ለማሟላት አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠር መግባባት ላይ መደረሱም ነው የተገለጸው፡፡

በተለይም ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቀያቸው የሚመለሱበትን ሁኔታና ታጣቂዎችን ወደ መደበኛ ህይወት የመመለስ ሂደት በትኩረት የሚሰራበት እና የሚሳለጥበት ሁኔታ ላይ መግባባት ላይ ደርሰዋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ሃብቶች አጠቃቀም ህጋዊ በሆነ አግባብ የህዝብንና የሀገርን ጥቅም የሚያስጠብቅ እንዲሆን፣ ለህዝብ የሚቀርቡ የመንግስት አገልግሎቶች የሚሻሻሉበትና የህዝብን ፍላጎት የሚመጥኑ እንዲሆኑ ቀጣይነት ያለው ጠንካራ ስራ እንዲሰራ ተገቢው አቅጣጫ በውይይቱ መለየቱም ተጠቁሟል፡፡

በመጨረሻም ጊዚያዊ አስተዳደሩ ክልላዊ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ያለበትን ሃላፊነት ለመወጣት በሚያስችለው አግባብ ላይም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

Afri ፈጣን መረጃ

03 Dec, 17:08


የሲሚንቶ ዋጋ በሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች እንዲወሰን ተደረገ

I የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለሲሚንቶ ፋብሪካ ድርጅቶች በጻፈው ደብዳቤ ከጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ምርታቸውን በፍትሃዊ ዋጋ እንዲያቀርቡ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም የሲሚንቶ ምርት የፋብሪካ መሸጫ ዋጋ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተወሰነ ለገበያ ሲሰራጭ የቆየ ቢሆንም በአዲሱ የአሰራር ሂደት ግን አምራች ፋብሪካዎች ሙሉ ሀላፊነቱን በመውሰድ በነጻነት ምርታቸውን ለገበያ እንዲያቀርቡ እና ገበያውን እንዲያረጋጉ ሃላፊነት መስጠቱን ሚኒስቴሩ እውቁልኝ ብሏል፡፡

የሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ የተሰጣቸውን ሀላፊነት በተጠያቂነት ስሜት እና በፍትሃዊ የዋጋ ተመን ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉም መወሰኑን ገልጾ ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ይውል የነበረውን መመሪያ 940/2015 ማንሳቱን ይፋ አድርጓል ሲል አዲስ ማለዳ ነው ያስነበበው።

Afri ፈጣን መረጃ

02 Dec, 17:13


አትሌት ሲምቦ አለማየሁ እና አትሌት ታምራት ቶላ የ2024 ምርጥ አትሌት በመባል ተመረጡ

አትሌት ሲምቦ አለማየሁ የ2024 የዓመቱ በሴቶች ተተኪ ወጣት በመሆን በዓለም አትሌቲክስ ተመርጣለች።

በተያያዘ ዜና አትሌት ታምራት ቶላ ከስታዲየም ውጭ በተደረጉ ውድድሮች የ2024 የዓመቱ ምርጥ በመባል በዓለም አትሌቲክስ መመረጡን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመለክታል።
(AMN)

Afri ፈጣን መረጃ

02 Dec, 17:12


የኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ።

ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ነው ከአቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር የሰላም ስምምነቱን የፈረሙት፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት÷ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ምስጋና አቅርበዋል።

ከጦረኞች በላይ ጦርነትን የሚያባብሱት ስለጦርነት የማያውቁ ናቸው ያሉት ፊልድ ማርሻሉ÷ እኔ ካለኝ ልምድ አንፃር ጦርነት ጎጂ በመሆኑ የሰላምን መንገድ መርጣችሁ በመምጣታችሁ ልትመሰገኑ ይገባል ብለዋል።

ይህ አይነቱ ተግባር በሌሎች አካባቢዎችም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ መግለጻቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

አቶ ሽመልስ በበኩላቸው የኦሮሞ ሕዝብ በባህሉ መሰረት ሰላም ይውረድ ብሎ ያቀረበውን ጥሪ ተቀብላችሁ በመምጣታችሁ በክልሉ መንግሥት ስም አመሠግናለሁ ብለዋል።

የመከላከያ ሠራዊቱ ለሰላም ስምምነቱ ላበረከተው አስተዋፅኦም አቶ ሽመልስ አመሥግነዋል፡፡

በዚህ ዓለም የሰው ልጅ የፖለቲካ ልዩነት ያለው መሆኑን ያወሱት ጃል ሰኚ ነጋሳ÷ እኛም ያለንን የፖለቲካ ልዩነት በጠመንጃ ከመፍታት በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት ወስነን ነው ስምምነቱን የመረጥነው ብለዋል።

ስምምነቱ ለኦሮሞ ሕዝብ ትልቅ እፎይታን እንደሚሰጥም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
(ኤፍ ቢ ሲ)

Afri ፈጣን መረጃ

02 Dec, 17:02


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባልደረባ ወድቆ ያገኙትን 50 ሺህ ዶላር (6 ሚሊዮን ብር በላይ) ለባለቤቱ አስረከቡ

👉የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሴኪዩሪቲ ክፍል ባልደረባ ፍሬዘር በቀለ ወድቆ ያገኙትን 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለባለቤቱ አስረከቡ፡፡

👉ገንዘቡን አቶ ፍሬዘር ሕዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከመንገደኛ ወድቆ ማግኘታቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

Afri ፈጣን መረጃ

30 Nov, 11:31


ሰበር — ምርጥ 30 የአፍሪካ ከተሞች ደረጃ ❗️

🌱🥇🌿

The Africa Report የ2024 ምርጥ 30 የአፍሪካ ከተሞችን ዝርዝር በደረጃ ያወጣ ሲሆን የጥቁር ህዝቦች መዲና የእኛዋ አዲስ አበባ #14ኛ ደረጃን ይዛለች።

አዲስ አበባ በምርጥ ከተሞች ዝርዝር ውስጥ ስተካተት ይህ የመጀመሪያ ሲሆን በጅምር ሂደት ላይ የነበረው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት 1 (CDP -1) ለዚህ እንድትበቃ አድርጓታል።

በግንባታ ሂደት ላይ ያሉት የኮሪደር ልማት 1 እና 2 ሲጠናቀቁ ፣ የጫካ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ፤ የሸገር ኮሪደር ልማት ሲያልቅ እንዲሁም የሸገር ወንዞች ጽዳትና ልማት ፕሮጀክት ፍጻሜ በ 2030 (ከአምስት ዓመት በኋላ) አዲስ አበባን በምርጥ 3 ከተሞች ውስጥ የሚያካትታት ይሆናል።

ለመላው የኢትዮጵያ በዋነኝነትም ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ። ይህ እንዲሆን በየደረጃው ለሰራችሁ አመራሮችና ባለሙያዎች የልፋታችሁን ፍሬ ለማየት እየበቃችሁ ነውና በርቱ ለማለት እወዳለሁ።

Afri ፈጣን መረጃ

29 Nov, 15:30


ሰበር — የኑክሌያር ሳይንስ ማዕከል ግንባታ ❗️

☢️

የሩሲያ ፌድሬሽን ግዙፍ ኒውክሌር አምራች የሆነው ሮሳቶም ኩባንያ የኢትዮጵያ ኑክሌያር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ማዕከል (Ethiopian Nuclear Science and Technology Center - ENTC ) ግንባታ የአዋጭነት ጥናት ለማድረግ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር ተፈራረሟል።

በሥምምነት ሰነዱ እንደተገለጸው ኩባንያው የግንባታውን አዋጭነት፣ በዘርፉ ያለውን ፍላጎት፣ የግንባታ ቦታ ልየታና ማዕከሉን ዕውን ለማድረግ የሚያስፈልገውን ወጭ እና ሌሎች ተየያዥ ዝርዝር ጉዳዮችን የሚያጠና ይሆናል።

Afri ፈጣን መረጃ

29 Nov, 11:34


ሰበር ❗️ሰበር ❗️ ሰበር ❗️

🚁

ከድፍን ሰማንያ ዘጠኝ ዓመት በኋላ (1935 - 2024 = 89) እንሆ ኢትዮጵያውያን “ፀሐይ - ፪” ሲሉ የሰየሟትን ተዋጊ አውሮፕላን በእጆቻቸው ሰርተው የአብርሆት መሪ በሆነው የኢትዮጵያ እንቁ ልጅ Abiy Ahmed Ali (ዶ/ር) አማካኝነት ተመርቃ ለግዳጅ ዝግጁ ሆናለች። እንኳን ደስ አለን ❗️

እ.ኤ.አ በ 1935 ዓ.ም በጀርመናዊው ኢንጂነር እና የቀኃሥ ፓይለት በነበረው ሄር ሉድዊግ ዌበርና በኢትዮጵያዊያን ባለሞያዎች ትብብር ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራችውን “ፀሐይ” አውሮፕላንን በመከተል "ፀሐይ -፪” የሚል ስያሜ የተሰጣትና ዛሬ በይፋ የተመረቀችው ተዋጊ አውሮፕላን ቴክኒካዊ እና የመስክ ፈተናዎችን በብቃት ተወጥታለች።

ፀሐይን ከሮም ያመጣው የአብርሆት መሪያችን የዘመኑን ፀሐይ ሪባን ቆርጦ መርቋል!... 👏 👏

Ethio Tsehay Aerospace Industries is loading...

Afri ፈጣን መረጃ

24 Nov, 11:03


የመልሶ ማቋቋም ስራው ከጦር መሳሪያ ማስፈታት ባለፈ የትግራይ ክልልን ሰላምና ደኅንነት ግምት ውስጥ ባስገባ መንገድ የሚከናወን ነው - ጌታቸው ረዳ

👉በትግራይ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም ስራ ከጦር መሳሪያ ማስፈታት ባለፈ የትግራይ ክልልን ሰላምና ደኅንነት ግምት ውስጥ ባስገባ መንገድ የሚከናወን መሆኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

👉በትግራይ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎች የተሀድሶና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መለስ ዜናዊ ካምፓስ ቅጥር ግቢ ተካሂዷል።

👉በመርሃ ግብሩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን የቦርድ ሰብሳቢ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር)፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ(ዶ/ር)፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሌተናል ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ እና የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እንዲሁም ሌሎች የፌደራልና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Afri ፈጣን መረጃ

23 Nov, 14:33


የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ ተጀመረ

ኅዳር 12/2017 (አዲስየቀድሞ የትግራይ ክልል ታጣቂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ወደ ተሀድሶ ስልጠና ማዕከላት የማስገባት ስራ ተጀምሯል።

ወደ ተሀድሶ ስልጠና ማዕከላት የሚገቡ የቀድሞ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች የጦር መሳሪያ ትጥቃቸውን ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።

በዚሁ መሰረትም የመጀመሪያ ዙር የመቀሌ የተሀድሶ ስልጠና ማዕከል የሚገቡ የትግራይ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎች የነፍስ ወከፍ እና የቡድን የጦር መሳሪያ ትጥቃቸውን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አስረክበዋል።

የቀድሞ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በየስልጠና ማዕከላቱ የሚኖራቸውን ቆይታ ካጠናቀቁ በኋላ ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው መደበኛ ህይወታቸውን የሚመሩበት የገንዘብና የቁሳቁስ መቋቋሚያ ድጋፍ ይደረግላቸዋል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በትግራይ ክልል መቀሌ፣ እዳጋ ሀሙስ እና ዓድዋ በተዘጋጁ ሶስት ማዕከላት በሚቀጥሉት አራት ወራት 75 ሺሕ የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ በማስፈታት በዘላቂነት የማቋቋምና ወደ ማኅበረሰቡ የመቀላቀል ስራ እንደሚከናወን ማሳወቃቸው ይታወሳል።

Afri ፈጣን መረጃ

23 Nov, 10:30


ሞቢሊቲ ኢ ከድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በመተባበር ለድንበኞቹ 20 መኪኖችን አስረከበ

ሞቢሊቲ ኢ ከድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በመተባበር 50% ክፍያ ለከፈሉና ቀሪውን የብድር አማራጭ በመጠቀም ለገዙ ድንበኞቹ በዛሬው እለት 20 መኪኖችን አስረክቧል

በአንድ ወር ግዜ ውስጥ ለሁለተኛ ግዜ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለደንበኞቹ ያስረከብው ሞቢሊቲ ኢ ድርጅት Sino Africa trading P.L.C በንግድ ስያሜ ሞቢሊቲ ኢ ከድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በመተባበር የBYD የኤሌክትሪክ መኪና በ50% ክፍያ እና ቀሪውን የብድር አማራጭ በመጠቀም የገዙ ድንበኞችን በደማቅ የርክክብ ስነስረአት ከዚህ በፊት ማስረከቡ ይታወሳል፡፡

በብዙ የBYD የኤሌክትሪክ መኪና ለመግዛት ፍላጎት ባላቸው ሰዎች ቃሉን በማክበሩ እና በታማኝነቱ የሚታወቀው ሞቢሊቲ ኢ ከድጋፍ ማይክሮፋይናንስ ጋር በተመቻቸው የብድር አማራጭ እና ዝቅተኛ የወለድ ፐርሰንት ተጠቅመው የደንበኝነት ውል ለፈጸሙ 20 ደንበኞቹ በዛሬው እለት ለሁለተኛ ግዜ አስረክቧል፡፡

በዚህኛው ዙር የተረከቡት የመኪና አይነቶች BYD seagull, BYD E2, እና Song plus ሲሆኑ በቀጣይ ከኤሌክትሪክ መኪና በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ስኩተሮች እና ኤሌክትሪክ ባይክ አማራጮችን ከድጋፍ ማይክሮፋይናንስ ጋር በመተባበር ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገልጿል
(በድሬ ትዩብ ሪፖርተር)

Afri ፈጣን መረጃ

21 Nov, 14:33


#BREAKING

ራሺያ ወደ ዩክሬን ዩክሬይን አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል(ICBM) ተኮሰች

ራሺያ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ICBM ስትጠቀም የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
በሰው ልጅ የጦርነት ታሪክ አንዲት ሀገር ሌላዋን በ  ICBM ስትመታ ራሺያ የመጀመሪያ ሀገር ስትሆን ዩክሬይን ለመጀመሪያ ጊዜ በ ICBM የተመታች ሀገር ሆናለች። የሩሲያ ጥቃት በዲኒፕሮ ላይ ያነጣጠረ ሲሆን "የተለያዩ ሚሳኤሎች" እንዳለው ተነግሯል።
ዩክሬን ከቀናት በፊት በአሜሪካ ትዕዛዝ ወደ ራሺያ ሚሳኤል መተኮሷ ይታወሳል።

Afri ፈጣን መረጃ

21 Nov, 14:30


በትግራይ ክልል  የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ ተጀመረ

👉የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም ዛሬ በይፋ በተጀመረው ስራ፣ በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ተሃድሶ ማዕከላት ማስገባት መጀመሩን የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

👉የቀድሞ ተዋጊዎች  ወደ ተሀድሶ ማዕከላት ለመግባት በእጃቸው ያለውን ቀላል ትጥቅ  ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።

👉በዚሁ መሰረት የመጀመሪያው ዙር የነፍስ ወከፍ እና የቡድን ጦር መሳሪያዎች ርክክብም የአፍሪካ ህብረት፣የመንግስታቱ ድርጅትና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች በተገኙበት ተከናውኗል።

👉በመቐሌ፣ እዳጋ ሀሙስ እና ዓድዋ የመጀመሪያ ዙር ተዋጊዎች ስልጠና የሚወስዱባቸው ማዕከላት መዘጋጀታቸውን የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ማስታወቁ ይታወሳል።

👉የቀድሞ ተዋጊዎች በተዘጋጁ ማዕከላት ስልጠናዎችን ከወሰዱ በኋላ የመቋቋሚያ ድጋፍ ተደርጎላቸው  ወደ ማህበረሰቡ በመቀላቀል  መደበኛ ሕይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል ተብሏል።
Via :- FBC

Afri ፈጣን መረጃ

21 Nov, 11:34


በቪዲዮ ማየት ለሚፈልግ ☝️

Afri ፈጣን መረጃ

21 Nov, 11:32


ሰበር ዜና — የኑክሌያር ጦርነ'ት


በትናንትናው እለት አሜሪካ ሰራሽ አታካም (ATACAMS) ሚሳኤል በመጠቀም ሩሲያ ግዛት ውስጥ ዘልቃ ጥቃት የፈጸመችው ዩክሬን ዛሬ ደግሞ እንግሊዝ ሰራሽ ስቶርም ሻዶው ሚሳኤል (Storm Shadow Missiles ) ተጠቅማ ራሽያን ማጥቃቷ ተረጋግጧል።

የፑቲን ምላሽ ይጠበቃል። አሁን ጥያቄው ቭላድሜር ፑቲን ኬቭን ጥንታዊ ሰዎች ሲኖሩበት ወደነበረው መሰል ዋሻ ይቀይሯታል ወይስ ከጀርባ ሆነው የሚያስተኩሱትን አይዞህ ባይ አጃቢዎች ይነርታ¯ሉ የሚለው ነው። የእኔ ምርጫ የመጀመሪያው ነው? የእርስዎስ?
🌼🌼🌼 🎉🎉🎉🎁🎁🎁 🌼🌼🌼
         📢📢📢📢📢📢📢📢
🌼🌼🌼 🎉🎉🎉🎁🎁🎁 🌼🌼🌼
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት 👇👇👇
🛑 👉  https://t.me/Afritoday
🛑 👉  https://t.me/Afritoday
🛑 👉  https://t.me/Afritoday

Afri ፈጣን መረጃ

20 Nov, 11:58


ዩክሬን ከትናንት በስተያ በአሜሪካ ትዕዛዝ ወደ ራሽያ 6 ረጅም ርቀት ሚሳኤል ተኩሳ መተኮሷን ተከትሎ ሁኔታው አሳሳቢ ሆኗልሆኗል።

5ቱ ከሽፎ አንዱ ጉዳት ማድረሱን ተከትሎ ፑቲን አስፈሪውን የዘመነ የኑክሌር ሰነድ በፊርማቸው አፅድቀዋል።

ሩሲያ ለራሷ እና ለቤላሩስ ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት አደገኛ ከሆነ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ልትጠቀም ትችላለች ተብሏል።ይህ የሚወሰነው በሩሲያ ፕሬዚዳንት ፑቲን ነው::

የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በአውሮፓ በተፈጠረው የደህንነት ስጋት ኔቶን የተቀላቀሉት የኖርዲክ ሀገራት ኖርዌይ ፣ ስዊድን እና ፊንላንድ ዜጎች ለተወሰኑ ጊዜያት የምግብ እና ሌሎች መሰረታዊ ቁሶችን ገዝተው እንዲያከማቹ አዘዋል።

Afri ፈጣን መረጃ

19 Nov, 18:59


ሰበር — የኑክሌያር ጦርነት


ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎችን ተጠቅማ ዩክሬን ራሽያ ግዛት ውስጥ ዘልቃ እንድታጠቃ የሰጡትን ፈቃድ ተከትሎ በዛሬው እለት ዩክሬን 6 አታካምስ ሚሳኤል ወደራሽያ የተኮሰች ሲሆን የራሽያ መከላከያ አምስቱን S-400 and Pantsir AA Systems በመጠቀም ያወደማቸው ሲሆን የአንደኛው ሚሳኤል ስብርባሪ ወታደራዊ ጣቢያ ውስጥ አርፎ ቃጠሎ ማስነሳቱ ተዘግቧል።

የራሽያ መልስ ይጠበቃል። ታክቲካል ኑክሌያር ወይስ?...

Afri ፈጣን መረጃ

18 Nov, 17:53


አሰብ የኢትዮጵያ ናት

ከኢትዮጵያ በግፍ የተዘረፈው የቀይ ባህር በራችን የአሰብ ወደብ የታሪካዊ ጠላትችን ግብጽ የጦር መደብ አይሆንም !!

ኢትዮጵያ ቆርጣለች። ከዛሬ ተሻግረው ነገን በሚያልሙ ቆራጥ ልጆቿ መሪነት በጥልቀት በማሰብ የአሰብ ወደብን ወደቀደመ ባለቤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ በማስመለስ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንዲሉ ሻዕቢያንና ግብጽን ቀይ ባህር ላይ እንቀብ-ራቸዋለን — አንጠራጠርም !

Afri ፈጣን መረጃ

18 Nov, 05:41


24 ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስኬት ተጠናቀቀ

🏃🎖️🏃‍♂️

ከ 50 ሺሕ በላን ዜጎች የተሳተፉበት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስኬት መጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት ጋር ተቀናጅቶ የሩጫው ተሳታፊዎች ደኅንነት ተጠብቆ በሰላም እንዲጠናቀቅ የድርሻውን መወጣቱ ተገልጿል፡፡

ታላቁ ሩጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ ለፀጥታ አካላት ትብብር ላደረጉት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ፣ ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታና ደኅንነት አካላትም የፌደራል ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል፡፡

Afri ፈጣን መረጃ

16 Nov, 17:02


የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የወጣ ወጣት በተአምር ህይወቱ ተረፈ

በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የወጣ ወጣት ኃይል እንዲቋረጥ ማድረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታውቋል፡፡

በዘርፉ የደቡብ ሁለት ሪጅን እንደገለፀው ወጣቱ ዛሬ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ከወላይታ ሶዶ ወደ ሳውላ በሚሄደው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ወጥቶ አልወርድም በማለቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ጎፋ ዞን፣ አሪ ዞን፣ ባስኬቶ ዞን እና ኦሞ ዞን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ጋሞ ዞን በከፊል ከሦስት ሰዓታት በላይ ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል፡፡

በምን ምክንያት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ እንደወጣ ያልታወቀው ወጣት በአካባቢው ሽማግሌዎችና የመስተዳድር አካላት ቢለመንም ለመውረድ ግን አስቸግሮ እንደነበር መምሪያው ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎች ኃይል በማቋረጥ ወጣቱ ሳይጎዳ በገመድ አስረው በማውረድ በተአምር ህይወቱን ታድገዋል፡፡

የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የሚያስተላልፉት የቮልቴጅ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መምሪያው አሳስቧል።

Afri ፈጣን መረጃ

16 Nov, 11:38


ጦርነቱ በቅርቡ ሊያበቃ ይችላል
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የዩክሬን እና የራሺያ ጦርነት በቅርቡ ሊቆም እንደሚችል ተናገሩ

የዶላንድ ትራምፕን መመረጥ ተከትሎ አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገው ድጋፍ ሊቆም እንደሚችል በመጠቆም የራሺያ እና ዩክሬይን ጦርነት በቅርቡ መቆሙ አይቀርም ሲሉ ለአንድ የዩክሬን ሚዲያ ተናግረዋል።

"ጦርነቱ በይፋ መቼ ይቆማል"? የሚል ጥያቄ ተነስቶላቸው " ጦርነቱ መቼ እንደሚቆም የተቆረጠ ቀን ባይኖርም፣ነገር ግን በቅርቡ መቆሙ አይቀርም "ሲሉ መልሰዋል።

ዶናልንድ ትራምፕ ዘለንስኪ ወደ አሜሪካ እየመጣ ቢሊዮን ዶላር አፍሶ የሚሄድበት ዘመን ያበቃል ማለታቸው ይታወሳል።

Afri ፈጣን መረጃ

16 Nov, 11:29


ማይክ ታይሰን በጄክ ፖውል ተሸነፈ

👉ዝነኛው አሜሪካዊ የከባድ ሚዛን ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ራሱን ከፕሮፌሽናል ውድድር ካገለለ ከ19 ዓመታት በኋላ ወደ ውድድር ተመልሶ ከ27 ዓመቱ ጄክ ፖውል ጋር ቢጋጠምም ተሸንፏል።

👉ጄክ ፖውል ጋር በኤቲ ኤንድ ቲ ስታዲየም በተደረገው ፍልሚያ ማይክ ታይሰንን በማሸነፍ በቦክስ ሕይወቱ ትልቁን ድል ማግኘት ችሏል።

👉የ27 ዓመቱ ፖል ፍልሚያውን ድል በማድረጉ እስካሁን ካደረጋቸው 11 ውድድሮች በአንዱ ብቻ የተሸነፈ ሆኗል።

Afri ፈጣን መረጃ

15 Nov, 06:33


ጁባላንድ፣ ከሞቃዲሾ ፌደራል መንግሥት ጋር ያላትን የሥራ ግንኙነት ማቋረጧን አስታውቃለች

ጁባላንድ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግንኙነቷን ያቋረጠችው፣ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ በመላዋ ሱማሊያ የቀጥተኛ ምርጫ ሥርዓት ተፈጻሚ እንዲኾን ያወጡትን ሕግ ውድቅ በማድረግ ቀጥተኛ ያልኾነ ምርጫ ለማድረግ መወሰኗን ተከትሎ ነው።

የጁባላንድ አስተዳደር፣ የአገሪቱ ጦር አልሸባብን ከጁባላንድ እንዳያጸዳ ፌደራል መንግሥቱ እንቅፋት ፈጥሯል በማለትም ከሷል። ራስ ገዟ ፑንትላንድ ቀደም ሲል ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግንኙነቷን ማቋረጧ አይዘነጋም።

Afri ፈጣን መረጃ

14 Nov, 13:34


የጥበብ ሥራዋ ከ1 ሚሊየን ዶላር በላይ የተሸጠላት ሮቦት

የጥበብ ሥራዋ ከ1 ሚሊየን ዶላር በላይ የተሸጠላት ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሮቦት አዲስ ሪከርድ አስመዘገበች።

በአይ-ዳ ሮቦት የተሳለው ሥዕል ከ120 ሺሕ ዶላር እስከ 180 ሺሕ ዶላር ለመሸጥ የተገመተለትን እስኬል አልፎ በ1 ሚሊየን 84 ሺሕ 800 ዶላር ተሽጧል።

በዓለም ላይ ካሉት እጅግ በጣም የላቁ ሮቦቶች አንዷ በሆነችው አይ-ዳ የተሠራው ሥዕል የሒሳብ ሊቁ አላን ቱሪንግ ነው።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ በኪንግ ኮሌጅ ካምብሪጅ የተማረው የሂሳብ ሊቁ ቱሪንግ የኮምፒውተር ሳይንስ ፈር ቀዳጅ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) አባት በመባል ይታወቅ ነበር።

የአይ-ዳ ሮቦት ስቱዲዮ ዳይሬክተር የሆኑት አይዳን ሜለር የአይ-ዳ የጥበብ ሥራ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እያደገ መምጣቱን ማሳያ ነው ብለዋል።

Afri ፈጣን መረጃ

13 Nov, 16:30


ፔሬግሪን ጭልፊት(peregrine falcone) በፍጥነት(320 ኪ.ሜ. በሰአት) በሚጠልቅበት(በሚበርበት) ጊዜ ወደ አፍንጫው ውስጥ የሚገባው አየር ሳንባው እንዲፈነዳ ሊያደርግ ይችላል፣ ነገር ግን በአፍንጫው ውስጥ ያሉት የአጥንት መጋጠሚያዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የአየር መተላለፊያን ይቆጣጠራሉ። ታዲያ የአውሮኘላን መሐንዲሶች አየርን ወደ አውሮፕላን ሞተሮች የማስተላለፍን ችግር በተመሳሳይ መንገድ ነበር የፈቱት ።
🌼🌼🌼 🎉🎉🎉🎁🎁🎁 🌼🌼🌼
         📢📢📢📢📢📢📢📢
🌼🌼🌼 🎉🎉🎉🎁🎁🎁 🌼🌼🌼
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት 👇👇👇
🛑 👉  https://t.me/Afritoday
🛑 👉  https://t.me/Afritoday
🛑 👉  https://t.me/Afritoday

Afri ፈጣን መረጃ

13 Nov, 11:08


ኢትዮጵያ እያስተማረች ጎረቤቶቿም እየተማሩ ነው ❗️

🧑‍🏫

ኢትዮጵያ በፀረ-ባርነት ትግል የአፍሪካዊያን መሪና አታጋይ ነበረች። ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ እንዲሉ ከፊት የነበረችው ኢትዮጵያ ከኋላ መቅረቷ ሳያንስ መዘባበቻ ሆና መክረሟ የአደባባይ ሐቅ ነበር። “የአፍሪካ ሕብረት ቆሻ-ሻ ከሆነችው አዲስ አበባ ተነስቶ ጽዱ ወደሆነ ከተማ መቀየር አለበት” የሚል ዘመቻ በአደባባይ ይከፈት ነበር። እንሆ ዛሬ ታሪክ ተቀይሯል፤ ኢትዮጵያ ወደቀደመ ክብሯ እየተመለሰች ነው።

እንሆ አብነት፦
~~~

❶ ዶ/ር ዐቢይ አረንጓዴ አሻራ ሲል የሩዋንዳው ፖልካጋሜ
አረንጓዴ አሻራ ብሎ ወዝወዝ አለ። ዶ/ር ዐቢይ በስንዴ
እራሳችንን መቻል ግዴታ ነው ሲል ካጋሜ ቱታ ለብሶ እርሻ
ሜዳ ወርዶ ትራክተር ተደግፎ ፎቶ ለቀቀ። በመቀጠል
ዶ/ር ዐቢይ “መጪውን ትውልድ STEM ላይ የበቃ የነቃ
እንዲሆን በማዕከል ደረጃ የሳይንስ ማስተማሪያ ሙዚየም
ግንባታ የውዴታ ግዴታ ነው” በሚል የሳይንስ ሙዚዬም
ግንባታ ሲያስጀምር የሩዋንዳው ፕ/ት ደከማቸው መሰለኝ
ጠፉብን... 🤔

❷ ዶ/ር ዐቢይ የመንግስትን ሥልጣን በጉልበት ለመንጠቅ
የተደራጀን አማጺ ድባ'ቅ ሊመታ “ምታ ነጋሪት ክተት
ሰራዊት” ብሎ ግንባር መዝመቱን ተአትሎ ከዩክሬኑ
ዘለንስኪ እስከ ሱዳኑ አልቡርሃን ደፋ-ቀና እያሉ ነው።
ፈጣሪ ይሁናቸው እንግዲህ!...

Afri ፈጣን መረጃ

11 Nov, 10:31


የኢትዮጵያ አየር መንገድ — የመሻገራችን ምልክት ❗️

✈️

ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር በስኬት ላይ ስኬትን እየተቀዳጀ በላቀ ከፍታ በመገስገስ ላይ የሚገኘው የአፍሪካ ኩራት የሆነው አየር መንገዳችን እየተጎናጸፈ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከደቡብ ሱዳን መንግስት በጋራ የደቡብ ሱዳን አየር መንገድን ለማቋቋምና አየር መንገዱን የማስተዳደር ሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲሆን ውል አስረው ወደስራ ገብተዋል።

Afri ፈጣን መረጃ

10 Nov, 15:20


🇮🇷🇸🇦 ታስኒም የዜና ወኪል፡ የሳውዲ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ከኢራን ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጋር ዛሬ በቴህራን ተወያይተዋል።

የኢራኑ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጀር ጀነራል መሀመድ ባገሪ፡- 'ሙስሊም ሀገራት ተባብረው መስራት የግድ ነው፣ ጠላት እንዲከፋፍለን መፍቀድ አንችልም' ብለዋል።

Afri ፈጣን መረጃ

10 Nov, 11:10


ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ አባል በምትሆንበት ዙሪያ ወይይት ተጀምሯል።

ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ (1929 — 1968) “There is power in unity and there is power in numbers” የሚል ዝነኛ አበባል አለው። በግርድፉ አንድነት እና ሰብሰብ ብሎ በጋራ መቆም የሃይል ምንጭ ነው ብለን ልንተረጉመው እንችላለን።

አረብ ሊግ አረባዊ ማንነትን እንደማሰባሰቢያ አጀንዳ ተጠቅሞ የግብጽን ጥቅምና ፍላጎት (የእኛው ዓባይ/ናይል ቀዳሚው ነው) በግብጽ አማካኝነት የተፈጠረ ሰብሰብ ነው። ሌላውን ትተነው ሱዳን፣ ጅቡቲና ሶማሊያ እንዴት አረባዊ ማንነት ሊኖራቸው እንደቻለ አንድየ ነው የሚያውቀው።

ጥልቅ ጥናት ማድረግ የቀጣይ የቤት ስራ ሆኖ የአረብ ሊግ ቃለ-ጉባኤ ቢፈተሽ ከ 80% በላይ አጀንዳው ኢትዮጵያ ነች። ሴለኢትዮጵያ ይመከራል/ይዶለታል/... እና ጓዶች በሌለንበት አጀንዳ ከምንሆን በስሚ ስሚ የተቃውሞ መግለጫ ከምናወጣ ከተቻለ በአባልነት ካልሆነም በአባልነት የአረብ ሊግ አባል ሆነን በእኛ ጉዳይ ድምጻችንን እናሰማለን። በእኛ ጉዳይ እኛው እራሳችን በቀጥታ መልስ እንሰጣለን። ከጎናችን የሚቆሙ ወገኖችን በመድረኩም ሆነ ከመድረኩ ውጭ እናደራጃለን...

ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ አባል በመሆኗ ጥቅሙ ህልቆ መሳፍርት ነው።

Afri ፈጣን መረጃ

08 Nov, 17:16


ይህን ያውቃሉ ?????

በአሁኑ ወቅት የአለማችን የፋይናንስ ተቋማት መረጃ እንደሚያመለክተው የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ GDP 59.5 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን ይህ GDP ከጎረቤት ሀገራት GDP ጋር ሲነፃፀር

ሶማልያ 11.68 ቢሊዮን ዶላር

ሱዳን 29.79 ቢሊዮን ዶላር

ደቡብ ሱዳን 5.27 ቢሊዮን ዶላር

ዩጋንዳ 55.59 ቢሊዮን ዶላር

ኤርትራ 2.13 ቢሊዮን ዶላር

ከ2024 ጀምሮ የአዲስ አበባ ጉህዴፓ $59.5 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህም የኢትዮጵያ 29% ነው።

$ከ 2023 ጀምሮ የሶማሊያ GDP $11.68 ቢሊዮን ይገመታል።

$ስታቲስታ እንደዘገበው የሱዳን አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) በ2024 $29.79 ቢሊየን ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

$ስታቲስታ እንደሚለው ከሆነ፣ የደቡብ ሱዳን አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) በ2024 $5.27 ቢሊየን እንደሚሆን ተገዷል። ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ግን የደቡብ ሱዳን GDP በ2024 መጨረሻ 9 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ይገመታል

$የኡጋንዳ GDP በ2024 አሁን ባለው ዋጋ መሰረት $55.59 ቢሊየን እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

$የኤርትራ GDP በ2024 መጨረሻ 2.13 ቢሊየን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ የኤርትራ ትክክለኛ GDP በ2024 በ3.1% ያድጋሉ።

Ethiopia An African Mega-Trend
🌼🌼🌼 🎉🎉🎉🎁🎁🎁 🌼🌼🌼
         📢📢📢📢📢📢📢📢
🌼🌼🌼 🎉🎉🎉🎁🎁🎁 🌼🌼🌼
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት 👇👇👇
🛑 👉  https://t.me/Afritoday
🛑 👉  https://t.me/Afritoday
🛑 👉  https://t.me/Afritoday

Afri ፈጣን መረጃ

08 Nov, 17:14


ዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያቸውን ትልቅ የተባለ ሹመት ሰጡ

👉 ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያቸውን ትልቅ የተባለ  ሹመት ሰጥተዋል፡፡

👉 ድብቋና ስትራቴጂስት በመባል የሚታወቁት የ67 ዓመቷ ሱዚ ዋይልስን የነጩ ቤተ-መንግስት የጽህፈት ቤት ኃላፊ (ቺፍ ኦፍ ስታፍ) አድርገው ሾመዋል፡፡

👉 ሱዚ ዋይልስ በነጩ ቤተ-መንግስት ትልቅ የስልጣን ቦታ ነው የሚባለውን በመያዝ የመጀመሪያዋ ሴት አሜሪካዊ በመሆን ታሪክ አስመዝግበዋል፡፡

👉 ሱዚ ዋይልስ ከ73 ቀናት በኋላ ወደ ነጩ ቤተመንግስት ለሚመለሱት ዶናልድ ትራምፕ የፖሊሲና የዕለት ተዕለት ተግባራት አማካሪ ሆነው ያገለግላሉ ተብሏል፡፡

(ኤፍ ቢ ሲ)

🌼🌼🌼 🎉🎉🎉🎁🎁🎁 🌼🌼🌼
         📢📢📢📢📢📢📢📢
🌼🌼🌼 🎉🎉🎉🎁🎁🎁 🌼🌼🌼
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት 👇👇👇
🛑 👉  https://t.me/Afritoday
🛑 👉  https://t.me/Afritoday
🛑 👉  https://t.me/Afritoday

Afri ፈጣን መረጃ

08 Nov, 17:11


በ24 ሰዓት የሩሲያ-ዩክሬንን ጦርነት አስቆማለሁ ያሉት ዶናልድ ትራምፕ

“ከተመረጥኩ ጦርነቱን በ24 ሰዓት ውስጥ አስቆመዋለሁ፤ እንዲያውም በዓለ ሲመት ሳላደርግ ነው በፍጥነት የምፈጽመው” አሉ የሩሲያ-ዩክሬንን ጦርነት በተመለከተ 47ኛው ተመራጭ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ. ትራምፕ ከመመረጣቸው በፊት።

Afri ፈጣን መረጃ

07 Nov, 17:48


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፈው ዓመት "በሲስተም መበላሸት" ከተወሰደበት ገንዘብ ያልተመለሰው 217 ሺሕ ብር ብቻ መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሳይበር ድህንነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ የሳይበር ድህንነት ቀን እያከበረ ይገኛል።

በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ፤ ባለፈው ዓመት በራሳችን ስህተት በተፈጠረው የሲስተም ችግር ምክንያት ከተወሰደው ገንዘብ ሁሉም ተመልሶ የቀረው 217 ሺሕ ብር ብቻ ነው ብለዋል።

"የሳይበር አለም አስፈሪ ነው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ ሥራ ይፈልጋል ብለዋል።

"ባለፈው ዓመት የተፈጠረው ችግር በፍጥነት አጥፍፊዎች መታወቃቸው ነው እንጂ፤ ችግሩ ከውጪ የመጣና መቆጣጠር የማንችለው ቢሆን ጥፋቱ ከፍተኛ ይሆን ነበር" ብለዋል።

ባንኩ ባለፈው ዓመት መጋቢት 6 ለሊት የሲስተም ችግር በገጠመው ወቅት 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር (40 ሚሊዮን ዶላር) እንደተወሰደበት ይታወሳል።

10 ሺሕ የሚሆኑ ግለሰቦች የገንዘብ ዝውውር ማድረጋቸውም ተገልጾ ነበር።

አሐዱ ሬዲዮ

Afri ፈጣን መረጃ

06 Nov, 16:52


የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር የመከላከያ ሚንስትራቸውን ከስራ አሰናበቱ

በጋዛው ጦርነት ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዩአቭ ጋላንት ከኔታንያሁ ጋር ለወራት አለመግባባት ውስጥ ነበሩ
ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ታዋቂው የመከላከያ ሚንስትራቸው ዮአቭ ጋላንትን ከሀላፊነት ማንሳታቸው ተሰምቷል፡፡

እስራኤል በተለያዩ የጦርነት ግንባሮች ከባድ ውግያ እያደረገች በምትገኝበት ወቅት የተወሰነው ይህ ድንገተኛ ውሳኔ ተቃውሞን አስነስቷል፡፡

ዘገባውን  ያጠናቀረው AL AIN ነው

Afri ፈጣን መረጃ

06 Nov, 16:51


ትራምፕ ዳግም በነጩ ቤተ-መንግሥት ነግሷል።
በእውነቱ የሃሪስ ዘመቻ አስተባባሪ ሊቀመንበር ሴድሪክ ሪችመንድ ሃሪስ በሐዋርድ ዩኒቨርስቲ ሲጠብቃት ለነበረው ደጋፊዎቿ ተገኝታ ንግግር እንደማታደርግና ለነገ እቅድ ይዛለች ብሎ ሲናገር ታዳሚው እየወጣ ሲበተን ነበር የአሸናፊው ውጤት ግልጽ የሆነው(ፐ ትንታኔ)😎
ውጤቱ ምንም ይሁን ሃሪስ ግን ተገኝታ ንግግር ልታደርግ ይገባት ነበር። ተሳስታለች። ጥሩ አልሰራችምና ወጥታ ደጋፊዎቿን ይቅርታ ልትጠይቅ ይገባል😂


እግዚአብሔር ከሞት ያተረፈኝ አላማ ስላለውና አሜሪካን ለማዳን ነው ያለው ትራምፕ በቀጣይ አራት ዓመት ለአሜሪካም ሆነ በጦርነት ስጋት ውስጥ ለተዘፈቀው ዓለም ምን ተስፋ ይዞ ይመጣል የምንለው አብረን የምናየው ይሆናል።

Afri ፈጣን መረጃ

05 Nov, 16:27


ገብቷል — አርፏል ❗️

✈️

ከፈረንሳይ ቱሊስ ተነስቶ ሲገሰግስ የነበረው በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነው ቅንጡው ኤርባስ A350-1000 አዲስ አበባ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮጵላን ጣቢያ አርፏል።

Afri ፈጣን መረጃ

05 Nov, 16:26


ድሮን ለመሸጥ በዝግጅት ላይ ነን ❗️❗️❗️

የኢትዮጵያ መንግስት ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ለሚያገናኝ የመንገድ ግንባታ የሚውል $738.2 ሚሊዮን ዶላር ብድር ፈቅዶ ይሄው ብድር በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በመጽደቁ ብዙዎች ተገርመዋል። በነገራችን ላይ “ከእከሌ ሃገር የተገኘ ብድር” በሚል ሲመረምርና ሲያጸድቅ የኖረው ፓርላማችን ከዚህ በኋላ “ለእገሌ ሃገር የተፈቀደ ብድር” በሚል አጀንዳ ዙሪያም ሰፊ ውይይት በማድረግ የሚያጸድቅ ይሆናል።

በነገራችን ላይ በአዲስ መልክ እየተደራጀ ካለው የኢትዮጵያ ኤሮስፔስ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (EASEC) አራት የአፍሪካ ሃገራት ለወታደራዊ እና የቅኝት አገልግሎት የሚውል የሰው አልባ ተሽከርካሪ (UAV/Drone) ግዥ ለመፈጸም የፍላጎት መግለጫ (EOI) አስገብተው በሚመለከተው አካል ሰፊ ግምገማ እየተካሄደበት ነው።

Afri ፈጣን መረጃ

04 Nov, 18:14


ሶማሊያ የኢትዮጵያን ኤምባሲ ከፕሬዝዳንቱ ቅጥር ግቢ ልታስወጣ መሆኑን ገለጸች

የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አህመድ ሞአሊም ፊቂ በአሁኑ ወቅት በፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት ውስጥ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወደ ሌላ ባዶ ቦታ ለማዘዋወር መታቀዱን አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ ትናንት ጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ለሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ "ውሳኔው የተወሰነው በፕሬዝዳንቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የውጭ ሀገር ኤምባሲ መገኘቱ፤ ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ ማስነሳቱን ተከትሎ ነው" ብለዋል።

"የሶማሊያ ሕዝብ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚገኝበት ቦታ ላይ ያቀረቡት ቅሬታ ተገቢ ነው።" ያሉት ሚኒስትሩ፤ "በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት ውጭ ወደሚገኝ አዲስ ቦታ እንዲዛወር ለማድረግ ፈጣን እርምጃ እንወስዳለን" ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም "ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይገኝበት የነበረው አከባቢ በአሁኑ ሰአት ምንም አይነት ጥቅም እየሰጠ አይደለም፤ እሱን አድሰን ኤምባሲው ወደዚያው እንዲዛወር እናደርጋለን" ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህ ካልሆነ ግን በተመሳሳይ "በአዲሰ አበባ የሚገኘውን የሶማሊያ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ግቢ ውስጥ እንዲሆን የሚል ጥያቄ እናቀርባለን" በማለት ተናግረዋል።

ይህ እርምጃ በፕሬዝዳንት አብዱላሂ ዩሱፍ አህመድ መንግሥት ፍቃድ ተሰጥቶታልም ተብሏል።

ይህ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለጫ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነትን መፈራረሟን ተከትሎ፤ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል እየተካረረ የመጣውን ልዩነት የሚያንጸባርቅ መሆኑ ተዘግቧል።

Via Ahadu

Afri ፈጣን መረጃ

04 Nov, 18:10


የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦
➡️ በዌብሳይት : https://placement.ethernet.edu.et 
➡️ በቴሌግራም : https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

tikvahethiopia

Afri ፈጣን መረጃ

04 Nov, 07:15


አሪቲ ለጤናችን

በአብዛኛው በሀገራችን ገጠራማ አካባቢ የሚገኘው አሪቲ ተክል ለጤና ስላለው ጥቅም ምን ያህል ያወቃሉ?

በዓላት ሲመጡ ለጉዝጓዝና ለመልካም መዓዛነት የሚውለው አሪቲ ከጉዝጓዝ ባለፈ ብዙ ጥቅም አለው።

አሪቲ እጅግ ብዙ የመድኃኒትነት ባህሪዎች አሉት፤ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በባሕላዊም ሆነ በዘመናዊ ሕክምና ብዙ መድኃኒቶች ይቀመሙበታል፡፡

ለጤናችን ከሚያስገኛቸው ጥቅሞችም መከካል👆👆👆

Afri ፈጣን መረጃ

04 Nov, 07:13


🇮🇱🇱🇧 እስራኤል ከ150 አመት በላይ የቆየውን በደቡብ ሊባኖስ ያሩን ከተማ የሚገኘውን የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አወደመች።

Afri ፈጣን መረጃ

03 Nov, 19:19


በከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ ልዑክ ማሌዢያ ኳላላምፑር ከተማ ገባ

👉በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ ማሌዢያ ኳላላምፑር ከተማ ገብቷል።

👉የጉብኝቱ ዓላማ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማሌዢያ ጉብኝትን ተከትሎ ከፍተኛ እና ፈጣን የልማት ለውጥ ያስመዘገበችው ማሌዢያ የተከተለችው የትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ከአዲስ አበባ ከተማ ፈጣን ለውጥ ጋር ሲነፃፀር የልምድ ልውውጥ ማድረግ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ ነው ተብሏል።

👉የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በትላንትናው ዕለት ኳላላምፑር፣ ሳይበርጃን እና ሳንዌይ ከተሞችን የጎበኙ ሲሆን በዛሬው ዕለት የገንቲንግ የቱሪስት መዳረሻን በመጎብኘት ላይ እንደሚገኙ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል::

Afri ፈጣን መረጃ

02 Nov, 17:42


ዜና፡ በአለባበስ ምክንያት የታገዱ ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ከስምምነት ላይ መደረሱን መጅሊሱ አስታወቀ

በ አዲስ አበባ ከተማ በአለባበስ ምክንያት ለሁለት ሳምንት የታገዱ ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱና ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከስምምነት መደረሱን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስታወቀ።

ትናንት በተካሄደው 6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ የምክር ቤቱ ተወካይ የሆኑት እዝታስ ካሚል ሽምሱ የሙስሊም ተማሪዎች አለባበስ ጋር በተያያዝ የተፈጠረው ችግር መፍትሄ እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለጥያቄው በሰጡት ምላሽ፤ “ የአለባበስ ጉዳይ እና ሃይማኖትን በተመለከተ ችግር የለም ማለት አልችልም። ግን ትልቅ እድገት አለ፤ ከተቋማት አንጻር መሰራት ያለበት ነገር ካለ እንሰራለን” ብለዋል።

Afri ፈጣን መረጃ

02 Nov, 11:24


መምህራን በምገባ መርሐግብር እየታቀፉ ነው

በሸገር ከተማ አስተዳደር በሁሉም የመንግስት ቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪና መምህራን የምግብ ፕሮግራም በመተግበር ላይ ይገኛል።

በዚህ ፕሮግራም የተማሪዎች ትምህርት ማቋረጥን ማስወገድ የተቻለ ሲሆን መምህራንም በማስተማር እና በመማር የበለጠ እንዲተጉ አድርጓል ተብላል።

በሸገር ከተማ በሚገኙ 256 ትምህርት ቤቶች የተማሪ እና የመምህራን ምግብ ፕሮግራም እየተካሄደ ሲሆን እስካሁን ለ148 ሺ 795 ተማሪዎች እና ለ3 ሺ 707 መምህራን መስጠት ተችሏል።

የኔታ

Afri ፈጣን መረጃ

02 Nov, 06:30


ጭምጭምታ ❗️

ደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያ የሚያቋርጥ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር በመዘርጋት የነዳጅፐሽያጯን በበርበራ ወደብ (ሶማሊላንድ) በኩል የማቀላጠፍ ፍላጎት እንዳላት ለዚህ ይረዳት ዘንድ ኢትዮጵያን በመከተል ለሶማሊላንድ ሕጋዊ እውቅና (De jure recognition) ለመስጠት ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች።

የኢትዮ-ሶማሊላንድ ግንኙነነት ለቀይ ባህር ቀጠና ሰላም !

Afri ፈጣን መረጃ

01 Nov, 02:58


ያሸንፉናል ብለን ስጋት ገብቶን አያውቅም:-ጠ/ሚንስትሩ

በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ጋር ንግግር ጀምረናል፣አሁንም እየተነጋገርን ነው። ነገር ግን በጎን ከመንግሥት ጋር ለምን ተነጋገራችሁ ብለው የሚወቅሱ ሰዎች አሉ ብለዋል። እኛ ይሄንን ንግግር የጀመርነው ያሸንፉናል ብለን ሳይሆን ስለማይጠቅም ነው ብለዋል። በዚህ መንገድ በጭራሽ አያሸንፉንም፣ስጋት ገብቶን አያውቅም ብለዋል።

🌼🌼🌼 🎉🎉🎉🎁🎁🎁 🌼🌼🌼
         📢📢📢📢📢📢📢📢
🌼🌼🌼 🎉🎉🎉🎁🎁🎁 🌼🌼🌼
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት 👇👇👇
🛑 👉  https://t.me/Afritoday
🛑 👉  https://t.me/Afritoday
🛑 👉  https://t.me/Afritoday

Afri ፈጣን መረጃ

31 Oct, 14:43


"ባደረግነው የቤተመንግስት ዕድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አስገብተናል"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Afri ፈጣን መረጃ

31 Oct, 08:43


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምርጡ የአፍሪካ አየር መንገድ በሚል ተሸለመ
******

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2025፣ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ “Best Overall in Africa award” ሽልማትን አሸንፏል፡፡

አየር መንገዱ በዚህ የሽልማት አሰጣጥ መርሓ ግብር ላይ በምርጥ የበረራ ላይ መስተንግዶ፣ በምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ አገልግሎት፣ በምርጥ የበረራ ላይ የምግብ እና መጠጥ አገልግሎት፣ በምርጥ የአውሮፕላን ውስጥ መቀመጫ ምቾት እንዲሁም በምርጥ የበረራ ላይ ገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመሆን ተሸልሟል።

ይህ በ “Airline Passenger Experience Association” (APEX) የመንገደኞችን ድምፅ መሰረት በማድረግ ለአየር መንገዶች ዕውቅና የሚሰጥበት መድረክ በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሽልማቶች አንዱ ሲሆን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ አየር መንገዶች ለሚያቀርቡት የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ዕውቅና የሚሰጥበት መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ያመለክታል።

Afri ፈጣን መረጃ

30 Oct, 17:08


ኢትዮጵያ በየትኛዉም ሃገር ላይ ጦርነት የማወጅ ፍላጎት የላትም!

ሰሞኑን የቤላሩስ ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያን የባህበር በር ፍላጎት በማስመልከት ያነሱትን ሃሳብ በርካቶች በተሳሳተ መንገድ እየተረጎሙት ያለ ይመስላል። በዚህም አንዲት ቁንፅል ሃሳብ በመያዝ ኢትዮጵያ የወደብ ጥያቄዋን በሃይል የመመለስ ፍላጎት እንዳላት አድርገዉም የተሳሳተ መረጃ ሲያሰራጩ ይስተዋላል። ሆኖም ኢትዮጵያ የወደብ ጥያቄዋን በሰላማዊ መንገድ እንጂ በፍፁም በሃይል የማስመለስ ፍላጎት እንደሌላትም ሁሉም ሊያውቀው ይገባል። የቤላሩስ ፕሬዝዳንትም ይሁኑን ለማስረዳት እንጂ ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጉልበት ትጠቀማለች ለማለት አይመስለኝም። ነገር ግን ማንም የፈለገዉን ቢል ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋን ከሰጥቶ መቀበል መርህ እና በህጋዊ መንገድ ውጭ የማስመለስ ፍላጎት እንደሌላት በደምብ ሊሰመርበት ይገባል።

Afri ፈጣን መረጃ

30 Oct, 16:56


ሰበር ዜና‼️

ሶማሊላንድ በድጋሚ አቋማን በግልፅ አሳወቀች
ሶማሊላንድ ከየትኛውም ወገን ተቃውሞ ቢመጣ ከ ኢትዮጵያ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል ገለጸች

ከየትኛውም ወገን ተቃውሞ እና ጫና ቢመጣ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል የሶማሊላንዱ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ተናገሩ።

Afri ፈጣን መረጃ

30 Oct, 15:04


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገ በፓርላማ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ይሰጣሉ

👉 ትናንት ፓርላማው ያፀደቀው የሚኒስትሮች ሹመት የአሠራር ጥያቄን በተመለከተ እንዲሁም በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ነገ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሚነሱላቸው ጥያቄ ምላሽ እንደሚሰጡ ታወቋል፡፡
ምንጭ አዩዘሀበሻ

Afri ፈጣን መረጃ

30 Oct, 10:51


በዎላይታ ዞን በከፍተኛ መጠን በጣለው ዝናብ በተከሰተው የመሬት ናዳ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ

በዚሁ በትላንትናው ዕለት ማታ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በካዎ ኮይሻ ወረዳ 01 ቀበሌ የአንድ ቤተሰብ አባለት በሙሉ እና ሌሎች ላይ አደጋ ደርሷል።

በዎላይታ ዞን በካዎ ኮይሻ ወረዳ በኮይሻ ላሾ ቀበሌ ሞግሳ ቀጠና በተከሰተው መሬት ናዳ 4 ሰውና በ01 ቀበሌ 3 ሰው አጠቃላይ የ7 ሰው ሕይወት አልፏል።

Afri ፈጣን መረጃ

29 Oct, 17:48


የኛ ሰው በቶማስ ሳንካራ ሀገር ቡርኪናፋሶ

I የቶማሥ ሣንካራ ሃገር ቡርኪናፋሶ ከየአሁኑ ፕሬዝዳንታቸው ካፒቴን ኢብራሂም ትራዎሬ ጋር የማሽነሪ የማምረት ሥምምነት አድርገናል ሲል ኢትዮጵያዊው ኢንጂነር ቤጃይ ኔርሽ ናይከር ገለፀ።

ስምምነቱ ፋብሪኬሽን ኢንጂነሪንግ ኢንደሥትሪያላይዜሽንን፣ ግብርናን፣ ኢንዱሥትሪን፣ ሥማርት ፋርሚንግን.... ወዘተን ያሣልጣል ተብሏል።

Afri ፈጣን መረጃ

29 Oct, 07:32


ሮድሪ የወንዶች ባሎን ዶር አሸናፊ ሆነ

በፍራንስ ፉትቦል አዘጋጅነት ለ 68ተኛ ጊዜ በተካሄደው የአመቱ የወንዶች ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች የሽልማት ስነ-ስርዓት ሮድሪ አሸናፊ መሆኑ ይፋ ሆኗል።

የ 2024 የአመቱ ምርጥ የወንድ እግር ኳስ ተጫዋች በመባል የተመረጠው ስፔናዊው የማንችስተር ሲቲ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ሮድሪ በአመቱ ከሀገሩ ስፔን ጋር የአውሮፓ ዋንጫን ከክለቡ ማንችስተር ሲቲ ጋር ደግሞ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አሳክቷል።

በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይም ሮድሪ የባሎን ዶር ሽልማቱን ከጆርጅ ዊሀ እጅ ተቀብሏል።

በአንፃሩ ቪንሰስ ጁኒየር 2ኛ ፣ ቤሊንግሀም 3ኛ እንዲሁም ካርቫል 4ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

Afri ፈጣን መረጃ

29 Oct, 07:30


የደቡብ አፍሪካ መንግሥት እስራኤል ቅኝ በምትገዛቸው ፍልስጤማውያን ላይ እየፈጸመች ያለችውን ጄኖሳይድ ለማስቆም ለመሠረቱት ክስ ፎቶው ላይ የምታዩትን ከ5 ሺህ ገጽ በላይ ማስረጃ አገራት ለሚዳኙበት ለዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት (International Court of Justice) አቀረበች! እስራኤል ደቡብ አፍሪካ በአፓርታይድ ሥር በነበረችበት ወቅት ለዘረኛው የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ከፍተኛ ድጋፍ ያደርጉ ከነበሩ አገራት አንዷ የነበረች መሆኗ ይታወቃል።
@afritoday @afritoday

Afri ፈጣን መረጃ

28 Oct, 17:31


እስራኤል ለተኩስ አቁም ስምምነት ከግብጽ የቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ አደረገች

👉 የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ግብፅ በጋዛ ሰርጥ ከሃማስ ጋር ለአጭር ጊዜ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ አድርገውታል።

👉 አራት እስራኤላውያን ታጋቾችን በተወሰኑ የፍልስጤም እስረኞች ለመለዋወጥ ለሁለት ቀናት በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ከዚያም ወደ ዘላቂ እርቅ ለመቀየር በ10 ቀናት ውስጥ ድርድር ለማድረግ ሀሳብ አቅርበናል ሲሉ የግብጹ ፕሬዝዳንት አልሲሲ ገልጸው ነበር።

👉 አብዛኞቹ የእስራኤል ሚኒስትሮች ለቀረበው ሃሳብ ድጋፍ ቢያደርጉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን ሀሳቡን በመቃወማቸው ቴል አቪቭ ስምምነቱን ውድቅ አድርጋለች።

@afritoday @afritoday

Afri ፈጣን መረጃ

28 Oct, 17:08


👉በድሬደዋ እና ሱማሌ ክልል ሲቲ ዞን መካከል አሁን በተከሰተው የሰደድ እሳት ምክንያት ለግዜው የባቡር እንቅስቃሴ የቆሜ ቢሆንም ፣ እሳቱን ለመቆጣጠር እና አገልግሎቱን ለማስጀመር የድሬደዋ የእሳት አደጋ እና የሽንሌ ዞን ሀላፊዎች ከጣቢያው ሰራተኞች ጋር በመሆን ባደረጉት ርብርብ እሳቱን ማጥፋት ተችሏል።

በዚህ አጋጣሚ ለተረባረቡት ሁሉ ምስጋናየ ከፍ ያለ ነው።
ታከለ ኡማ (ኢ/ር)

Afri ፈጣን መረጃ

27 Oct, 19:03


የኢራን ዛቻ

"እስራኤል በኢራን ላይ ለሰነዘረችው ጥቃት የሉዓላዊነት ክብራችንን በዘላቂነት ለማስጠበቅ በሙሉ አቅማችን እና ኃይላችን አብርካሪዋን የሚሰብር ምላሽ እንሰጣለን። የምንሰጠው ምላሽ ካሁን ቀደም ከነበሩት ሁለት እርምጃዎች በዓይነቱም ፣ በስፋቱም በብዙ እጥፍ የተለየ ይሆናል።"

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

Afri ፈጣን መረጃ

26 Oct, 18:40


ሰበር መረጃ

የኢራን ተዋጊ ጄቶች ከእስራኤል ጥቃት በኋላ ከወታደራዊ ሰፈራቸው መነሳታቸው ተሰምቷል

የእስራኤል ጦር ሬድዮ ከወታደራዊ ቃል አቀባይ፡-
👉የእስራኤል እና የአሜሪካ የአየር መከላከያ ዘዴዎች በክልሉ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ተዘጋጅተዋል።
👉የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጦር ትላንት ምሽት ግዳጅ ሲወጡ የነበሩ የአየር መከላከያ ሰራዊት አባላት 2 ወታደሮች እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት መሞታቸውን አስታውቋል።
በመካከለኛው ምስራቅ አስከፊ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ተሰግቷል።

Afri ፈጣን መረጃ

26 Oct, 17:35


117ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን‼️

117ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን "በፈተናዎች እየተገነባ የመጣ ሠራዊት" በሚል በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል።

Afri ፈጣን መረጃ

25 Oct, 18:32


ኒው ዮርክ ታይምስ:- እስራኤል ኢራን ውስጥ ስሱ ኢላማዎችን የምታጠቃ ከሆነ ኢራን ከመካከለኛው ምስራቅ የምትልከውን ነዳጅ ዘይት አቅርቦት ታቋርጣለች።

እስራኤል በኢራን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰች ከሚሰጡ ምላሾች መካከል በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ተቃዋሚ ቡድኖች ከባድ ጥቃቶች እና በፋርስ ባህረ ሰላጤ ፣ በሆርሙዝ ባህር ውስጥ የሚጓዙትን የአለም አቀፍ የኃይል አቅርቦቶች እና የመርከብ ጭነት አገልግሎት ፍሰት ማቋረጥ!!

በተጨማሪም መልሱ ከኢራን እስከ 1,000 የሚደርሱ የባሊስቲክ ሚሳኤሎች ጥቃትን ያጠቀላለ እንደሚሆን ኒው ዮርክ ታይምስ የኢራን ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።

Afri ፈጣን መረጃ

25 Oct, 16:15


ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የባለብዙ ወገን አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

👉ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) እና ዓለም ባንክ በኩል ያለውን ትብብር ጨምሮ የባለብዙ ወገን አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።

👉በገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ የተመራ ልዑክ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ሞሊ ፊ እና የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ግምጃ ቤት ረዳት ሚኒስትር ብሬንት ኒማን ጋር ተወያይቷል።

👉የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ያተኮረው ውይይቱ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ 2024 ዓመታዊ ስብሰባዎች ጎን ለጎን መካሄዱን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ አመላክቷል።

👉የገንዘብ ሚኒስትሩ መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሂደት እና በጂ 20 የጋራ ማዕቀፍ መሰረት ከልማት አጋሮች የሚጠበቀውን ወሳኝ ድጋፍ አስመልክቶ ለአሜሪካ ባለስልጣናት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

👉የአሜሪካ ባለስልጣናትም መንግስት እያከናወናቸው ያሉትን የለውጥ ስራዎችና የተመዘገቡ ስኬቶችን አድንቀዋል።

👉የዕዳ ማሸጋሸግ ድርድሩን በሚመለከት በዓለም አቀፍ የሉዓላዊ ዕዳ ድርድር እና በሁለትዮሽ በኩል እንዲታይ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

Afri ፈጣን መረጃ

24 Oct, 20:07


የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ

👉 በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

👉 ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

Afri ፈጣን መረጃ

24 Oct, 20:05


😭ሶሻል ሚዲያ ላይ ሲዘዋወር አገኘሁት 😱

👉ያላገባችሁ፣ ያገሬ ልጆች እንዲህ ያለ የትዳር አጋር ይስጣችሁ 🙏 ያገባችሁ፣ ትዳራችሁን እንዲህ በፍቅር ያርዝምላችሁ 🙏 የተፋታችሁ፣ በዳግም የትዳር ሙከራችሁ የልባችሁን አውቃ ይስጣችሁ 🙏

Afri ፈጣን መረጃ

23 Oct, 17:13


የሀሰን ሼክ የጅቡቲ ውርደት በኬንያ ተደገመ ❗️

💧 ⚓️ 💧

“... የውስጥ ችግርህን እራስህ ፍታው። የሶማሊያ ብሔራዊ ምክክር ካውንስል (National Consultative Council - NCC) ውጤታማ እንዲሆን እንመኛለን።

👉 ነገርግን በሶማሊያ የውስጥ ጉዳይ ገብቼ አንተን ከጁባላንድ መሪ አህመድ ማዶቤ ጋር ላሸማግልህ አልችልም። አልሸባብ ከኬንያ ጋር በደ*ም የተቃባ ይቅር የማንለው ጠላታችን ነው። ይህንን ደመኛ ጠላታችንን ለአትሚስ ሰራዊት ካዋጡ ሃገራት (TCC) ጋር በመሆን ተፋልመነዋል፤ ወደፊትም እንፋለመዋለን።

👉በእኔ እምነት የፀረሽብር መሃንዲስ የሆነችው ኢትዮጵያን ሳያካትቱ አልሸባብን መፋለም ከንቱ ቅዠት ነው። ኬንያ በጋራ መልማት በጋራ ማደግ የምትፈልግ ከሶማሊያም ሆነ ከኢትዮጵያ ጋር ጥብቅና የቆየ ወዳጅነት የመሰረተች ሃገር ነች።

👉ሶማሊያን በመምራት ሂደት የግል ስሜትህንና ጥቅምህን ሳይሆን የሃገርህን ብሔራዊ ጥቅም አስቀድም። ወደኢትዮጵያ ሂድና ከዐቢይ_አህመድ ጋር ተመካከር...”

Afri ፈጣን መረጃ

23 Oct, 10:43


ኢትዮጵያ የግብፅን ሥጋና ነፍስ ተቆጣጥራለች ሚ/ጀኒራል  ጊዮራ ኢላንድ

👉የእስራኤል ጀኔራልና የቀድሞው የጠቅላይ ሚኒስቴሩ የደህንነት ኃላፊ በቅርቡ በቴላቪቭ እንድ የወታደሮች ምረቃ ላይ ተገኝተው "ኢትዮጵያ የዓባይን ወንዝ መገዳቧ የግብፅን በዓባይ ወንዝ ላይ ያላትን የበላይነትና  ኢንፓየርነት  እንዲያበቃ ያደረገ ነው ብለዋል።
👉በዚህም ግብጽ ተጨማሪ የውሃ አማራጭ ካልፈለገች የውሃ እጥረት ሊገጥማት ይችላል ማለታቸውን ከኢንሳይድ አፍሪካ ያገኘሁት መረጃ ያመላክታል።

👉ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ አንዳች ነገር ብታደርግ እስራኤል እጇን አጣጥፋ አታይም ማለታቸው የሚታወስ ነው።
እስራኤል በሶማሊላንድ የጦር ቤዝ የመገንባት ሀሳብ እንዳላት በቅርቡ መዘገቡ ይታወሳል።

Afri ፈጣን መረጃ

23 Oct, 10:30


መነጋገሪያ የሆነው ወጣት 👏

Afri ፈጣን መረጃ

22 Oct, 14:48


አልሀምዱሊላህ!
በውሳኔህ ተሳስተህ አታውቅም !
ብዙ ሰተኸኝ ነበር ጥቂት ወስደህብኛል ክብርና ልቅና ላንተ የተገባ ይሁን!

አሁንም ቢሆን የጉዳት መጠናችን በውል አልታወቀም ቢሆንም የብዙዎች ወንድሞቼ ንብረት በአጠቃላይ በሚባል መልኩ ወድሟል አላህ ለሁላችንም መፅናናትን ይስጠን የተሻለውን አላህ ይተካልን!!

ሲቀጥል ብዙዎቻችሁ CBE account እየተቀባበላችሁ ልታግዙኝ እየሞከራችሁ ነው!!! በጣም አመሰግናለው!! ግን እኔ ከብዙ አላህ ከሰጠኝ ፀጋ በጥቂቱ ስለሆነ የነካኝ ለኔ የምታረጉትን ገቢ ለወንድሞቼ እንድታረጉ በትህትና እጠይቃለው!!! እንዲሁም የኔን የለጠፋችሁትን እንድትሰርዙት በአክብሮት እጠይቃለው!!!!

Via: ሐሩን_ሰዒድ

Afri ፈጣን መረጃ

22 Oct, 11:48


መንገድ ለምን መስፋት እንደሚያስፈልግ ትላንት ምሽት ተረዳሁ!

መንገድ የሌለው እና አንድ መግቢያ ብቻ ያለው በመሆኑ ትላንት አደጋው ከፍቷል። ጥረቱ ባይሳካ ከበባው ባይፋጠን ከዚህም ይከፋ ነበር። ግን ፈጣሪ ረድቶናል፣ ተመስገን እንበል! መንገድ ግን ለምን መስፋት እንደሚያስፈልግ ትልቅ ትምህርት ሰጥቶናል። መንገድ አለመኖር አማራጭ አሳጥቶ ስንመለከት በጣም አዝነናል። በጉልበት መንገድ እያበጁ ነበር አስተባባሪዎች እሳቱን ለመቆጣጠር ሲጥሩ የነበሩት።

Afri ፈጣን መረጃ

22 Oct, 11:42


የእሳት አደጋው በከፊል 🔥

Afri ፈጣን መረጃ

22 Oct, 05:10


" እኔ የመርካቶ ልጅ ነኝ፤ እዛውም ነው የምሰራው።

ዛሬ በአይኔ ያየሁት የእሳት አደጋ እጅግ አስከፊ ነው።

በጣም ብዙ ንብረት ወድሟል። የአላህ ጥበቃ ሆኖ እኔ በአካባቢዬ ላይ የሰው ህይወት አልተጎዳም።

ነገር ግን በእሳት አደጋው እጅግ በጣም አዝነን እያለ ተጨማሪ ሃዘን የፈጠረብን ብዙ አለ።

አንዱ የተለያዩ አካላት ለዝርፊያ ያደረጉት እንቅስቃሴ ነው።

አንዳንዶቻችን ህሊናችንን በዚህ ልክ ማጣታችን እጅግ አሳፋሪ ነው። ነገ እኛን ምን እንደሚገጥም እኮ አናውቅም።

ይህ ከባድ አደጋ እውነተኛ መንስኤው እና የጉዳቱ መጠን በፍጥነት እንዲጣራልን እንፈልጋለን።

ብዙ ለፍቶ አዳሪ ዜጋ እጅግ የደከመበት ፣ የለፋበት ንብረቱ በአንድ ምሽት ወደ አመድነት ተቀይሯል። " - ሃሚ (መርካቶ)

Afri ፈጣን መረጃ

21 Oct, 18:07


መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ ተከስቷል። የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታው መድረሳቸውንና እሳቱን ለማጥፋት በጥረት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

Afri ፈጣን መረጃ

21 Oct, 07:24


ኢራን የአሜሪካን ደህንነት ሰብራ የሞነቸፈቺው መረጃ በጣም ጨዋታ ቀያሪ ነው።

👉ይህ የደህንነት መረጃ እስራኤል ኢራንን እንደት ማጥቃት እንዳለባት ፤ ምን አይነት ጥቃት መፈፀም እንዳለባት ፤ የትኞቹን የኢራን ኢላማዎች መምታት እንዳለባት ፤ ኢራንን ለማጥቃት ኑክሌየር መጠቀም አለመጠቀሟን ፤ አሜሪካና አጋሮቿ ምን አይነት የማጥቃትና የመከላከል እገዛ ለእስራኤል ማድረግ እንዳለባቸው የሚያትት ሰፊ የስለላ መረጃ ነው የኢራን ሀከሮች ሰብረው በመግባት የሞነቸፉት።

👉ይህ መረጃ የሚቀመጠው አምስት አይኖች " Five eyes" በሚል ጥምረት በሚታወቁት በአሜሪካ ፤ እንግሊዝ ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ ብቻ ቢሆንም ኢራን በርብራ ሰብራው ገብታለች። የጠላቶቿን እቅድም በሙሉ አግኝታዋለች።

👉በዚህ የተደናገጡት አሜሪካና እስራኤል በከፍተኛ ሁኔታ አደገኛ ክስተት ነው የተከሰተው ያሉ ሲሆን ጉዳዩን እያጣሩ መሆኑን ገልፀዋል።

👉የሆነው ሆኖ የጠላትን እቅዶች ማግኘት እጅግ ትልቅ ድል ነውና ኢራን አሳክታዋለች።

Afri ፈጣን መረጃ

19 Oct, 18:39


4ኛው የብሪክስ ዋና አስተባባሪዎች ስብሰባ በካዛን ሩስያ መካሄድ ጀመረ


አራተኛው የብሪክስ ዋና እና ምክትል አስተባባሪዎች ስብሰባ ካዛን ከተማ ሩስያ እየተካሄደ ነው።

በሩስያ የወቅቱ ሊቀመንበርነት እየተመራ ባለው ስብሰባ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታና የኢትዮጵያ የብሪክስ ጉዳይ ምክትል አስተባባሪ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ እየተሳተፈ ይገኛል።

የካዛን ረቂቅ ስምምነት ማዘጋጀት፣የብሪክስ አጋር አገራት አሠራር ማዘጋጀት ላይ አተኩረው ይሠራሉ።

16ኛው የብሪክስ አባል አገራት የመሪዎች ጉባዔ ከጥቅምት 12 እስከ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በካዛን ከተማ ሩስያ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል

Afri ፈጣን መረጃ

19 Oct, 18:14


በሶማሌ ክልል ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈፀም በተንቀሳቀሱ 60 የአልሻባብ የሽብር ቡድን አባላት ላይ እስከ ዕድሜ ልክ የፍርድ ውሳኔ መተላለፉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

በሀገራችን ሶማሌ ክልል አፍዴር እና ሸበሌ ዞኖች በኩል ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 60 የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር ውለው በ10 የምርመራ መዝገብ ተከሰው እስከ ዕድሜ ልክ እስራት የፍርድ ቤት ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ፖሊስ በ60 የሽብር ቡድኑ አባላት ላይ በቂ የቴክኒክና የታክቲክ ማስረጃ በማቅረብ በሽብር ወንጀል ምርመራ አጣርቶ ለፍትህ ሚኒስቴር በመላክ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ተዘዋዋሪ ችሎት ሁለት የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች በዕድሜ ልክ እስራት፣ 56 ተከሳሾች እንደወንጀል ተሳትፎአቸው ከ6 ዓመት እስከ 18 ዓመት ፅኑ እስራት እና በአልሸባብ የሽብር ቡድን አባልነት የተከሰሱ ሁለት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው 2 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንዲፈረድባቸው ማድረጉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል፡፡

Afri ፈጣን መረጃ

18 Oct, 18:37


የኢትዮጵያ መንግሥት ራስ ገዟ ሶማሌላንድ አዲስ አበባ ላይ ኢምባሲ እንድትገነባ በነጻ ቦታ ሰጥቷል

👉የሶማሌላንድ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኢሳ ካይድ፣ ለግዛቲቷ በተሰጣት ቦታ ላይ ትናንት የኢምባሲውን የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

👉መንግሥት ለኢምባሲ መገንቢያ ቦታ መስጠቱቱ፣ በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ መካከል ያለውን የኹለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚጠናክረው የግዛቲቷ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ገልጧል።

Afri ፈጣን መረጃ

18 Oct, 05:26


ሽንፈቱን የአለም ፍፃሜ አታድርጉ ገኒን የገጠምነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ይዘን ነው ብለዋል አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ

"ምን እንደሚያስጨንቃችሁ አላውቅም ውሌ የሚጠናቀቅበት ጊዜ ጥቅምት 23 ነው አትጨነቁ እለቅላቹሀለው''

" በ2 ጨዋታ 4ለ1 እና 3ለ0 ተሸነፍን እንጂ ለማጋነን ተብሎ 7ለ1 መባል የለበትም ልክ አይደለም"

"7ለ1 ተሸነፍን ተብሎ መጋነን የለበትም ክሬዲት ለማሳጣት እንዳይህንባችሁ እሰጋለሁ 8 ለ0 ተሸንፈንም እናውቃለን''

"ሽንፈቱን የዓለም ፍጻሜ አታድርጉት ጊኒን የገጠምነው ትልቅ ቡድን ይዘን አይደለም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ይዘን ነው " ( ዮሴፍ ከፈለኝ )

Afri ፈጣን መረጃ

17 Oct, 19:44


በሞቃደሾ ጥቃት ተፈፀመ

በሶማሊያ ሞቃደሾ በሚገኘው የፓሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ላይ ከፍተኛ ጥቃት መፈፀሙ ታወቀ።

እንደዘገባው ከሆነ ግብፅ ወደ ስማሊያ ካስገባችው መሳሪያ መካዘን አካባቢ መሆኑ ተነግሯል። በጥቃቱ እስካሁን ሰባት ሰዎች ሞተዋል ሲል inside Africa ዘግቧል።

Afri ፈጣን መረጃ

17 Oct, 11:18


ጠቅላይ ፍርድ ቤት እነ ጆን ዳንኤል ላይ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን የዋስትና ብይን አጸና

ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከአውሮፕላን አንወርድም በማለት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ተብለው የተከሰሱት ስድስት ግለሰቦች ላይ በስር ፍርድ ቤት ውድቅ የተደረገባቸውን የዋስትና ጥያቄን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አፀና።

ከ15 ቀናት በፊት በስር ፍርድ ቤት የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ብይን መስጠቱ ይታወሳል።

ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤልያስ ድሪባ፣ ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ የተባሉ ተከሳሾች ግን በጠበቆቻቸው አማካኝነት የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ መደረጉ አግባብ አለመሆኑን ጠቅሰው ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለው ነበር።

ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ የይግባኝ ባዮችን አቤቱታን እና የከሳሽ ዐቃቤ ሕግ መልስ፣ የግራ ቀኝ ክርክርን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት ዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ ከህግ አንጻር ተገቢ ነው በማለት ብይኑን በማጽናቱ ተከሳሾች በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ይከታተላሉ።

ዘገባው የፋና ነው።

Afri ፈጣን መረጃ

16 Oct, 19:30


የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ (ፐርሰንት) 100 ሚሊዮን ብር መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አሳወቀ


ለኢትዮጵያውያን ክፍት የተደረገው የአክሲዮን ሽያጭ ዛሬ በይፋ የተበሰረ ሲሆን፤ ዝቅተኛው የሼር ወይም የአክሲዮን መጠን 33 እንዲሆን የአንዱ አክሲዮን ዋጋም 300 ብር እንዲሆን መወሰኑን ኢትዮ ቴሌኮም አሳውቋል።

ከፍተኛው የክሲዮን ወይንም የሼር መጠን 3 ሺህ 333፤ የአንዱ አክሲዮን ዋጋም 300 ብር እንደሆነ ፍሬህይወት ታምሩ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ገልፀዋል።

የአክሲዮን ሽያጩ በቴሌ ብር የሚፈፀም ሲሆን፤ ሽያጩ ከጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ይቆያል ተብሏል።

Afri ፈጣን መረጃ

16 Oct, 17:40


ልዩ መረጃ፡ የመንግሥታዊው ባንክ የዶላር መሸጫ ዋጋ መቀነስ

በመንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዶላር ከብር አንጻር ያለው ምንዛሬ በመሸጫው ቅናሽ አስመዝግቧል። ባንኩ በመሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ ሲያደርግ በመግዣው ላይ መጠነኛ ጭማሪ አድርጓል። ባንኩ የባለፈውን ሳምንት ቀናት እንዲሁም ትናንት ጥቅምት 4/2017 ድረስ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ112.39 ሲገዛ የነበረ ሲሆን፣ መሸጫው 123.63 ነበር።

ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 5/2017 ባወጣው አዲስ ዋጋ የመግዣ ዋጋው ላይ መጠነኛ ጭማሪ በማድረግ አንድ ዶላር 113.13 እንደሚገዛ አሳውቋል። በአንጻሩ ባንኩ በመሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ በማድረግ ለአንድ ዶላር 115.39 ዋጋ አስቀምጧል። በመሸጫ ዋጋ ላይ የተመዘገበው ቅናሽ 8.24 ብር ነው።

Afri ፈጣን መረጃ

14 Oct, 18:44


በዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ሊያደርግ የነበረ ተጠርጣሪ ተያዘ

የሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ካሊፎርኒያ ግዛት ያልተመዘገበ እና የተቀባበለ መሳሪያ የያዘ ሰው በቁጥጥር ስር ውሏል።

ኮቸላ በተባለች የካሊፎርኒያ ከተማ ውስጥ የተያዘው ተጠርጣሪ በተለያየ ስም የተለያዩ ፓስፖርቶች፣ የሀሰት ታርጋ የተለጠፈበት መኪናና የተቀባበለ መሳሪያ ይዞ መገኘቱን የከተማዋ ፖሊስ ኃላፊ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

የፖሊስ ኃላፊው ጨምረውም በእጩ ፕሬዝዳንቱ ላይ የተቃጣ ሶስተኛ የግድያ ሙከራ እንዳከሸፍን ነው የምረዳው ብሏል።

ተጠርጣሪው ቪም ሚለር የተባለ የ49 ዓመት ጎልማሳ መሆኑንና የኔቫዳ ግዛት ነዋሪ ስለመሆኑ ፖሊስ ጠቅሶ ሁለት ሕገ ወጥ መሳሪያ እና ከፍተኛ የመምታት ኃይል ያላቸው ጥይቶችን ይዞ በመገኘት ወንጀል እንደሚከሰስ መግለጹን አልጄዚራ ዘግቧል።

ሆኖም ተጠርጣሪው በዋስ የተለቀቀ ሲሆን ለሚዲያ በሰጠው መረጃ ክሱ ፍጹም ሀሰት እንደሆነና የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ መሆኑን ተናግሯል። “እኔ አርቲስት ነኝ፤ በፍጹም በማንም ላይ አደጋ የማደርስ ሰው አይደለሁም” ሲል አስተባብሏል።

ካሁን በፊት በዶናልድ ትራምፕ ላይ ሁለት ጊዜ የግድያ ሙከራዎች መደረጋቸው ይታወሳል።

Afri ፈጣን መረጃ

14 Oct, 18:23


የቱርኩ ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን እስራኤል የዓለማችን ዋነኛ ስጋት ነች አሉ

👉የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶሃን እንዳሉት እስራኤል የመካከለኛው ምስራቅ እና የዓለማችን ሰላም ዋነኛ ጠላት ናት ብለዋል።

👉ፕሬዝዳንቱ አክለውም እስራኤል በሶሪያ በተደጋጋሚ ጥቃት እየፈጸመች መሆኗን ተናግረው በቅንጅት ሊያስቆሟት ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

👉በሶሪያ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ኢራን፣ ሶሪያ እና ሩሲያ የተቀናጀ ጥቃት በመክፈት ሊያስቆሟት ይገባልም ብለዋል።

Afri ፈጣን መረጃ

13 Oct, 05:46


ኢትዮጵያ በአፍሪካ ተቀዳሚ ኤር ባስ ኤ-350-1000 ግዙፍ አውሮፕላን ባለቤት ሆነች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የአፍሪካዊያን ኩራት 🥰

Afri ፈጣን መረጃ

12 Oct, 18:04


የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ፣ በአጠረ ጊዜ፣  ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓዙ የሶማሊላንድ መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ይገኛሉ።
የፕሬዝዳንቱ ልዑካን ቀድመው አዲስ አበባ መግባታቸውንም ዘግበዋል።

Afri ፈጣን መረጃ

11 Oct, 17:56


አስደሳች ዜና 😱

👉የፖስፖርት የግዜ ቆይታ ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ እንደሚል ተገልጿል።

👉የኢሚግሬሽን ዜግነትና አገልግሎት የፖስፖርት የግዜ ቆይታ ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ እንደሚል ገልጿል።

👉ፖስፖርት ለማደስ 5 ዓመት ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ከአንድ ወር በኃላ ወደ ሥራ በሚገባው አሰራር መሰረት ግን ከ25 ዓመት በላይ ለሆናቸው ዜጎች በየ10 ዓመቱ እንደሚታደስ አገልግሎቱ ገልጿል።

@Afritoday