نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے @abdu_rheman_aman Channel on Telegram

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

@abdu_rheman_aman


فليس العلم بكثرة الرواية ولا بكثرة المقال.
ولكنه نور يقذف فى القلب يفهم به العبد الحق
ويميز به بينه وبين الباطل. /هـ

አስታያየቶዎንና ምክሮዎን⇩

@Nehnu_abnau_aselefiyin_bot

በዚህ ያድርሱን👆

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے (Arabic)

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے هو قناة تيليجرام تقدم محتوى علمي وديني لأبناء السلف الصالح. يتميز القناة بتقديم النور والفهم العميق للمعلومات الدينية، حيث يتم إلقاء الضوء على العلم النافع الذي يميز بين الحق والباطل. من خلال قناتنا، ستجد محتوى غني بالمعلومات القيمة والتوجيهات الدينية الصحيحة. إذا كنت تبحث عن قناة تقدم لك المعرفة والفهم العميق في الدين، فنَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے هي القناة المناسبة لك.

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

13 Jan, 18:58


የሌላ ዓለም ሰዎች አሉ… ስለ ዓቂዳ ስታወራቸው ስለ ግለሰቦች መንሀጅ የሚያወሩህ… ስለ ሀሳብ ስታስረዳቸው ስለ ጎጠኝነት የሚሰብኩህ ፣ ስለ መላኢካዎች ስታነሳ… ስለጂኖች ሊነግሩ የሚፈልጉ…  በቃ የሆነ የተለየ ዓለም ውስጥ ናቸው። የድርቅና ሰመመን ውስጥ…።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

13 Jan, 18:33


ምን አለ መሰለህ? … ሰው ስለህመም ሲያወራህ ሊያሳምንህ የሚገባ ሎጂካል ምክንያት አትጠብቅ። አንዳንድ ሰው መተንፈሻውን ሜዳ ብቻ ነው የሚፈልገው። በሀሳብና ጭንቀት ዓለሙ ውስጥ አብረህ እንድትሸኘው ብቻ ነው መሻቱ።   "ለምን? እንዴት? በምን?" ምናምን እንድትለው አይደለም። መደመጥ ነው በቃ። እዚህ የህመም ሰፈር ከመጣህ  ምክንያትና ሰበብን ተዋቸው። ምክንያት የማይገዛው ብዙ ህመምም አለ።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

12 Jan, 20:30


ሰማይ ድምፅህን ልጣታው አይገባም።  ስትለምን መላኢኮች ድምፅህን የሚያውቁት ባሪያ ሁን።
  "ጌታዬ ሆይ… " ስትል… "ታዋቂ ድምፅ ከታዋቂው ባሪያ" ይላሉ። ልብ በል! በዱዓህ ታዋቂ የምትሆነው አሏህ ዘንድ ነው።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

12 Jan, 13:54


ዒልምና ጋት ካልጠቡት ይደርቃል!።

         🎙 ኡ/ዝ አቡ ሙዓዝ
Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

11 Jan, 19:39


የሳቸውን ድምፅ ለመስማት 👆

በዛውም ተዋወቋቸው። ሸይኽ ሙሐመድ አሊ አ^ደም አል-ኢቲዮጲይ፣ አል-ወሎዊይ፣ አል-ቦረኒይ ይባላሉ።

ታሪካቸውን ለማንበብ 👇 ይሄን ይጠቀሙ
t.me/abdu_rheman_aman/1735
t.me/abdu_rheman_aman/1735

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

11 Jan, 19:08


ልጁን "አብዱ'ሰታር" ብሎ የሰየመ  "አብዱ'ሰቲር" በሚል ይቀይረው። ሰታር የሚባል ለአሏህ ስም የለውም። ያሰታር ሳይሆን ያሰቲር ነው ሊባል የሚገባው!። አንዳድ ዑለሞች "ሰታር" የሚለውን ስም ከአሏህ ስሞች ውስጥ አድርገው ቢጠቅሱትም፣ መረጃ ግን የላቸውም። የአሏህ ሲፋዎች ሁሉ "ፈዒል በሚል ወዝን ነው የመጡት!" ልክ ፦ ሐሊሙን፣ ሰቲሩን፣ ከሪሙን፣ ቀዲሩን እንደሚባለው።

ሸይኽ ሙ/ድ አሊ አደም አል-ኢቲዮጲይ
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

11 Jan, 18:03


የሶሀቦች ቅሬታ
ባለሀብቶቹ አጅሩን ሁሉ ጠቀለሉብንኮ ስለዚህ ለደሃዎች ብቻ የተገደበ ስራ ይጠቆመን የሚል ነበር።

የኛ ቅሬታ ደግሞ እነሱ ሀብታም ሆነው
ለምን እኔ ደሃ ሆንኩ የሚል ይመስላል።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

11 Jan, 12:18


ለምን ይሁን ግን ብዙ ኪታቦች ላይ ብዙ ግዜ ስለ ንጽህና የሚያወራው ክፍል ቀድሞ እየመጣ ስለ ጂሃድ የሚያወራው ግን መጨረሻ የሚመጣው ተብለው ተጠየቁ።

"ስለ ንፅህና የማያውቅ ስለ ጂሃድ እንዳያወራ ነው።" ብለው መልሰዋል ቀደምት ሰለፎች
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

09 Jan, 18:59


[وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ] المائدة 8

ለሰዎች ያላችሁ ጥላቻ ፍትሃዊ እንዳትሆኑ አይገፋፋችሁ ብሎን አዞናል!። ብርቱ የሆነ ጥላቻም ይሁን ውዴታ ባለቤቱን አጥፊ ነው። ነቢዩሏህ ዩሱፍ عليه السلام ተፈትኖበታል።የወንድሞቹ ብርቱ የሆነ ጥላቻ ጉድጓድ ውስጥ እንዲጣል አድርጓል። ብርቱ የሆነ ውዴታም ለእስር  ዳርጎታል።

እኛ የልባችንን አቋም መቋቋም ሊያቅተን ይችላል።በየትኛውም ሁኔታ ወደድንም ጠላን ፍትሃዊ እንድንሆን ግን ታዘናል።

ስለምትወደው ብለህ የምትወደውን ሰው ወንጀል መልካም ስራ አታድርግ። ስለምትጠላው ብለህ የምትጠላውን ሰው መልካም ስራ ደግሞ ወንጀል አታድርግ።

በየትኛውም ሁኔታ ፍታሃዊ ሁን!።

رسائل من القرآن
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

09 Jan, 18:40


"የነገ ሟች የዛሬን ሟች ይቀብራል።"

ሀሰን አል-በስሪይ
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

08 Jan, 18:42


«فهل تستطيع أن تغيب وجهك عني؟! »

ይቅርታ የምታደርግላቸው ግን ደግሞ ስብራቱን የማትረሳላቸው ሰዎች አሉ። እነሱን ማየት የሚፈጥርብህ መጥፎ ስሜት ስላለ ይቅር ብያችኋላሁ ባይሆን ግን እንዳላያችሁ እሻለሁ የምትላቸውም አሉ። ይህን ማድረግህ ያደረግከውን ይቅርታ ደረጃውን ዝቅ የሚያደርግ፣ ዋጋውን የሚያሳጣ ሆኖ አይደለም። ግን በቃ ልታስወግደው የማትችለው ሰዎች ባንተ ላይ ጥለውት የሚያልፉት፣ ሰዎቹን ባየሃቸው ቁጥር ያ መጥፎ ትዝታቸውና ግፋቸው እየታወሰህ የሚያሳምምህ መጥፎ ጠባሳ ስለሆነ ነው።

ልክ ነብዩ ﷺ የአጎታቸውን ገዳይ ወህሽዪን رضي الله عنه ይቅርታ አድርገውለት "ምናለ ፊትህን ዞር ብታደርግልኝ" እንዳሉት። ይህንን የረሱልን ሃዘን ላለማስታወስ ሲል ረሱል ሲመጡ መንገድ ሁላ ይቀይር ነበር።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

08 Jan, 18:25


አንድ ሰውዬ የራሱን ጥላ ለመያዝ ያስባል አሉ። ወደ ጥላው በቀረበ ልክ ጥላው ከሱ ይሸሻል። ከጥላው በላይ መፍጠን አለብኝ ብሎ ያስብና መሮጥ ይጀምራል። በሮጠ ቁጥር ጥላውም ይሮጣል። ልይዘው አልቻለም፣ ደከመውና ተስፋ ቆርጦ ወደኋላ መመለስ ይጀምራል። ጥላው ይከተለዋል። ቅድም ሲያሳደው የነበረው ጥላ አሁን አሳዳጅ ሆኖ መጥቶበታል። ሰውዬው ሩጫውን ጀመረ ጥላውም ከኋላው ይሮጣል፣ ራሱን እስኪስት ድረስ ሮጠ፣  ጥላው አለቀቀውም። በመጨረሻም በቃ የምርም ሊበቀለኝ ነው ብሎ አሰበ ይባላል!

ይህ የዱንያ መገለጫ ነው። አንዳንዴ በህይወታችን አንዳንድ ነገሮችን እስካልተውናቸው ድረስ አናገኛቸውም።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

08 Jan, 04:58


ወዳጄ ምንም መልካም ሰሪ ብትሆን ባንተ ጉዳይ የሚጠመዱ ሰዎች አይጠፉም። ይህን ግሩም አንቀጽ ተመልከት

﴿وَقَالُوا مَا لَنَا لَا نَرَىٰ رِجَالًا كُنَّا نَعُدُّهُم مِّنَ الْأَشْرَارِ﴾

ዱንያ ላይ በመጥፎ የምናያቸው የእሳት እንደሆኑ የምንቆጥራቸው ሰዎች የት ጠፉ? ይላሉ።

እጅግ አቃጣይ በሆነው እሳት ውስጥ፣ በዛ ከባድ ህመም ውስጥ ሆነው እንኳን ስለ ሌሎቹ የህመም ደረጃ ለማወቅ የሚፈልጉ ሰዎች አሉ። የራሳቸው ህመም ስለሌሎቹ ለማወቅ ከመፈልግ አላገዳቸውም።

እሳት ውስጥ እንዲ ካሉ፣ በዱንያስ?
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

07 Jan, 18:17


"ኡምሩቀይስ" የተባለ ጀግና ሰው ነበር ፣ በፍቅር ተሸንፎ…ከታች ያሉትን ግጥም ሰደራቸው ፦

رجُلٌ وما استسلمْتُ قَبْلُ لفارسٍ
‏ مالي أمام عيونها مُستسلِمُ !؟
‏⠀⠀⠀
‏أأعودُ منتصِرا بكل معاركي
‏وأمام عَيْنيها البريئة أُهْزَمُ !

ከዚህ በፊት ለፋርስ - እጅ ያልሰጠሁ
ምነው ከዓይኗቿ ፊት - እጄን  ሰጠሁ

በጦርነቴ ሁሉ በድል እመለሳለሁ
በፈካ ዓይኖቿ ፊት - እሸንፋለለሁ

አብደረህማን አማን
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

07 Jan, 17:38


በፍቅር ውስጥ ከባድ ወይም ኃያል ተብሎ የሚጠራ ሰው የለም። የተጨበጨበለት ስኬት ላይ ብትደርስም በፍቅር ቤት "አንቱ" ተብሎ አይሰገድልህም። የቱንም ያህል የገነነ ስም ቢኖርህም ስታፈቅር ቅጣምባሩ ሌላ ነው። ነብይ ብትሆን እንኳን እንደነብይህ ባለቤትህ ጉልበትህን እንድትረግጥ አድርገህ ግመሉ ላይ እንድትወጣ ማድረግ ይኖርብሃል ፣ ሩጫ ውድድር በማጫወትና አጋርህ ውሃ የጠጣችበትን የእቃው ቦታ እየፈለግህ በመጠጣት ስለፍቅር ትሸነፋለህ፣ ዝቅም ትላለህ። ስትወድ እንደህፃን ልጅ ትከሻ ላይ ትንጠለጠላለህ፣ ተለምዶና ህግ ብዙም ቦታ አይኖራቸውም። እና የወንድነት ትርጉሙም እዚህ ቦታ ላይ ለየት ብሎ… በመሸነፍ ይተካል። መሸነፍ በቃ…
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

06 Jan, 19:57


የሸሪዓ ህግ "የገደለ ይገደል"  የሚለው ተፈፃሚ እስካልሆነ ድረስ…የሰው ሂዎት እንደቅጠል መርገፉ አይቀርም። በዚህ ልክ የሰውን ነፍስ መቅጠፍ ምን አይነት ጭካኔ ቢሆን ነው። አሏህማ! እዝነቱ ሰፊ ነው። ይህ ሁሉ ግፍ እያለ እሳትን አለማዝነቡ…ዕውነትም አዛኝ ነው።

በቃ ዱንያ እንዲህ ነች!። ደስታና ሀሰን፣ ሳቅና ለቅሶ፣ እዝነትና አረመኔነት የተቀላቀለባት ባለ ብዙ ቀለም…ሰባራ ሸክላ ናት። አያቹህ! ሞት መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

06 Jan, 18:50


የሰው ልጅ ይለምዳል። ሙያ ብቻ ሳይሆን ስሜትንም በመልመድ ይኖራል። በህይወቱ እንዳይከሰቱ ይፈራላቸው የነበሩ ቀናት ተከስተው መመልከት ይጀምራል። የቅርብ ቅርብ ሰዎቹ መሞት፣ የእጅ ማጠር፣ ወዳጆቹን ማስታመምና ከብዙ አብሮነት በኋላ የሚመጣ ብቸኝነት… የሚፈራቸውን ያህል ተፈጥረው ያገኛቸዋል። መጀመሪያ ነገር… ያለቅሳል፣ ይጨነቃል፣ ልዩ የሀዘን ስሜት ያጋጥመዋል። ከዚያስ? አይለመድ ነገር የለምና መላመድ ይመጣል። በየትኛውም ክስተት ውስጥ የማይሰብርህ ግን የአላህ ፍቅር ነው። አላህን መልመድ ከቻልን ነገርዓለሙ ሁሉ ይግራራል። መጥፎ ሁኔታ ውስጥ እንኳን ብናልፍ!!
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

06 Jan, 18:32


አሁን ላይ የቱንም ያክል ረሺ ብንሆንም
እያንዳንዷን ጥቃቅንና ዝርዝር ስራችንን የምናስታውስበትና ከዚያም እነሆ የስራ መዝገብህ ያውልህ። ራስህም አንብበው የምንባልበት ቀን ከፊታችን ይጠብቀናል።

              "يوم يتذكر الإنسان ما سعى
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

05 Jan, 18:49


ከ20 ምናምን ዓመት  ቡኃላ እማዬ ወጥ ጭማሬ ማለት ተገቢ አይደለም። ትዳር እየያዛቹህ'ጂ!።

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

05 Jan, 18:40


ነፍስህም ሀቅ አላት። ሁሉም ሰው በራሱ በኩል አንተን ስሌት ውስጥ ሳያስገባህ ቅድሚያ የሚሰጣቸው በርካታ ነገሮች አሉት። ለሆኑ ድንገታዊ ስሜቶች ብለህ የምትከፍላቸው  "እውር መስዋትነቶች"  ሊኖሩ አይገባም ብዬ አስባለሁ። ራስህን እንደሻማ ስላቀለጥክ ቆሞ የሚያጨበጭብልህ አይኖርም። ቢኖርም ምንም አይጠቅምህም። የሻማን ፍልስፍና ተወውና ራስህን ሳትጎዳ ሌሎችን ስለመጥቀም አስብ።  አንዳንድ ሰዎች  ለሰዎች መልካም መሆንና ራስን መበደል መሀል ያለው ልዩነት ገና አልገባቸውም። ኧረ የነፍስህን ሀቅ በመወጣት አሳርፋት።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

05 Jan, 03:38


አንዲት ሴት: ኢማሙ ማሊክ ላይ የተማረን "ኢስማዒል" የተባለን የዕውቀት ባለምዋልን አገባች፣ የዚህ የጋብቻ ፍሬ "ሙሐመድ" የሚባልን ልጅ አሏህ ሰጣቸው። ነገር ግን ባሏ: እሷንና ልጃቸውን ‹ሙሐመድን›ና የተወሰነ ገንዘብ ትቶላቸው የሞትን ፅዋ ተጎነጨ፣ ይህች ደግ እናት ልጇ የሙስሊሞች አይን ማረፍያ እንዲሆን በጅጉኑ ሰለቋመጠች በኢስላማዊ አደብ ትኮተኩተው ታንፀው ጀመረች፣ ነገር ግን በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ የልጇን የአይኑን ብርሃን አሏህ ነጠቀባት። ልቧ ተሰበረ፣ በጣም አዘነች፣ ግን በልጇ ላይ ያላትን ተስፋ ፈፅሞ ልትቆርጥ አልቻለችም። ወደ መድረሳ ይዛው ትሄዳለች፣ ተምረው ሲጨርሱ ይዛው ወደ ቤቷ ትመለሳለች፣ ከሃገር ወደ ሀገር ዕውቀትን እንዲቀስም ይዛው ትንቀሳቀሳለች፣ አሏህ የልጇን ብርሃን እንዲመልሰላት በኢኽላስ ዱዓ ተያያዘች፣ ከዕለታት በአንዱ ለሊት በህልሟ ነቢዩሏህ ኢብራሂምን አየቻቸው፣ እንዲህም አሏት፦
ياهذه قَدْ رَدَّ اللَّهُ عَلَى ابْنَك بَصَره بِكَثْرَة دُعَائِك
"አንቺ ሴት ሆይ! በተደጋጋሚ ዱዓ በማድረግሽ ምክንያት አሏህ የልጅሽን ብርሃን መልሶለታል"‹አሏት›
:
ከእንቅልፋ ተነስታ ልጇን ስትመለከትው: የአይኑን ብርሃን አሏህ መልሶለት ዳግም ማየት ችላል፣ በጣም ተደሳች፣ ሀሴት፣ ፎሽታ ተሰማት፣ ከአሁን ቀደም ከምታደርገው ጥረት በተሻለ መልኩ ልጇን ሸሪዓዊ ዕውቀትን እንዲቀስም ታነሳሳው፣ ታበረታታው፣ ታንፀው ጀመረች፣ አሏህም በናቱ ዱዓ አማካኝነት የመሸምደድ ብቃትና የዕውቀት ባለምዋል አደረገው። በእጆቹ የተለያዩ ወደር-የለሽ ድርሳናትን መፃፍ ጀመረ፣ ከፃፋቸው ድርሳናት ውስጥ በዋነኝነት የሚጠቀሰው  "ከአላህ ንግግር (ቁርኣን) በኋላ ትክክለኛ ንግግር (የነቢዩን ንግግር የያዘ የሆነው) "ሶሒሕ አል-ቡኳሪይ" የተሰኝ ትልቅ ድርሳናትን ማበጀት ችላል።

እሱም "ሙሐመድ ኢብን ኢስማዒል አል-ቡኻርይ" ይባላሉ። [አሏህ ይዘንላቸው]

[ሲየሩ አዕላሚ አኑበላእ: ሊዘሀቢይ 14/392]
[አል-ቢዳያህ ወኒሃያህ: ሊብኒ ከሢር 14/527]

አብደረህማን አማን
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

04 Jan, 19:17


ግንኮ ልቤ ነበር…!
~~~
ትውልደ ፍልስጤማዊው መህሙድ ደርዊሽ  "ሪታ" የተሰኘችን እስራኤላዊት ወጣት ወዶ እንዲህ ፅፎ ነበር “ጎሳዬን፣ ሰፈሬንና የመጣሁበት ባህሌን በሙሉ ትቼ እወድሻለሁ። ግን ሁሉንም ሽጬ ስጨርስ አንቺ እኔን እንዳትሸጪኝና ከዚያም አመድ አፋሽ እንዳልሆን እፈራለሁ።”

ከዚያም… ሪታ ከእስራኢል ሞሳድ የስለላ ድርጅት ጋር የምትሰራ መሆኑን ሲደርስበት እንዲህ ፃፈ “የትውልድ ሀገሬ እንደገና እንደተያዘች ተሰማኝ…
እንዲህም አለ ፦
ربما لم يكن شيئا بالنسبة لك ياريتا، لكنه كان قلبي

ምን አልባት ላንቺ ያን ያህል ዋጋ ላይኖረው ይችላል፣ ግንኮ ልቤ ነበር!"
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

04 Jan, 18:43


ሙሉ ለሙሉ የሚያስማማኝ የግብፃዊው ፀሓፊ አህመድ ኻሊድ ተውፊቅ ንግግር አለ። “ሁሌ የመከላከል ሁኔታ ውስጥ የሚከቱኝን ሰዎች መቀላቀል አልወድም። ስለአስተሳሰቤ፣ ስለ ነፍሴ ፣ ስለመብቴና ስለተስፋዎቼ እንድከላከል የሚያደርጉኝ”
አህመድ ምን እያለ ነው? ሁል ጊዜ ወቃሽ ሆነው የሰወራኸውን ነገር ለምንና እንዴት እንዳደረግከው ተሟጋች ሆነህ እንድትመጣ የሚፈልጉ ሰዎች አሉ። "የዲፋዕ ስሜት ውስጥ የሚከቱህ"። ምክንያታዊ ቢሆኑ እሰየው። ግን አይደለም። እነዚህ ሰዎች እዚህ ጉዳይ ውስጥ ሲያስገቡን

" هَذَا فِرَاقُ بَيْنِي وَبَيْنِكَ"
አሪፍ መልስ ነው።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

04 Jan, 05:51


የሚገርም ክስተት
~~~
የታላቁ ኢማም አቡ ሐኒፋ አባታቸውም አያታቸውም ነጋዴ ነበሩ (ረሒመሁሙላህ) ከእስላማዊ ዕውቀት መማር ማስተማር ጎን ለጎን እሳቸውም እስከሕይወታቸው መጨረሻ ድረስ በንግዱ ዓለም ነበሩበት፣ ሲበዛ ፆመኛ ሲበዛ ለይል ሰጋጅም ነበሩ፣ ይህ ዓቢድነታቸው በንግዱ ስራ ላይ ሀቀኛ እንዲሆኑ ተፅዕኖ አሳድሮባቸዋል,

ገበያ መኃል አንዲት ሴት "የሀር ልብስ" ይዛ ነበርና ስንት ተሸጭልኛለሽ ሲሏት በ100 ትላቸዋለች "ይሄማ ከ100 በላይ ያወጣል ንገሪኝ ዋጋው  ስንት ነው?" አሏት 200 ይሁና አለች፣ እሳቸውም እንደዛ አይደለም ከ200ም በላይ ነው ስንት ትይዋለሽ?" ሲሉ ጠየቋት እየጨመረች 400 ደረሰች "ከዛም በላይ ነው ስንት ትይዋለሽ?" ሲሏት "እያሾፍክ ነው እንዴ?" አለቻቸው አይ አይደለም ብለው ሌላ ሰው  ጥሪ አሏት ተጠራና ገምተው ተባለ 500 ያወጣል አለ ገማቹ! የዚህኔ አቡ ሐኒፋም 500 አውጥተው ሰጧት!።

(ሲያስጨምሩ ገዢ አይመስሉምኮ፣ ልብ በሉ! ገዢ ሁነው ርካሽ አገኘሁ ብለው አጋጣሚውን ልጠቀም አላሉም)

ወዳጆቼ! አሁን ላይ ያለነውስ አየሩን ያልባነነ ሻጭ ከተገኘ አጣድፈን ከእጁ እንዲወጣ አይደለም ወይ የምናደርገው? የኛ ዒባዳ አለአግባብ የሰውን ሐቅ ከመውሰድ መቼ ነው የሚመልሰን? እስቲ ራሳችንን  እንታዘብ
የታሪኩ ዘገባ ምንጭ:—መናቂብ አልኢማም አቢ ሐኒፋተ ወሳሒበይሂ
(مناقب الإمام أبي حنيفة وصاحبيه، شمس الدين أبو عبد الله محمد بن أحمد...صفحة 38)
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

03 Jan, 10:51


በአፋር ክልል ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የተከሰተው እሳተ ገሞራ
:
አፋር ክልል የተለያዩ ቦታዎች ላይ  ሰሞኑን በተከታታይ የተከሰተው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ወደ ከባድና አስፈሪ እሳተ ጋሞራ እየተቀየረ ይገኛል

[መረጃ: ከውሰር ቲዩብ]
ሲታይ በጣም ያስፈራል፣ ያረቢ እዝነትህን
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

02 Jan, 19:09


መልዕክተኛው በእድሜ ከሳቸው የምትበልጠዋንም የምታንሰዋንም አግብተዋል። ከሀብታሟም ከድሃዋም ጋር አብረው ኖረዋል። ከተፈታችም  ባሏ ከሞተባትም ጋር ጎጆ መስርተዋል።  መልዕክቱ ምን መሰለህ…  ሴት ልጅ ከስነምግባሯ ጉድፈት ውጪ  እንደ ነውር የሚታይባት ሌላ ነገር አይኖርም።

ለሴቷ አግብቶ መፈታትና የባል መሞት  እንደ ጉድለት የሚያዩ ማህበረሰቦች አሁንም ድረስ አሉ። ነብዩ ይህንን በተግባር ሰብረውታል። ልቦች በዚህ አይነት የጃሂሊያ አስተሳሰብ ውስጥ ሟሙተው የእንስቶች ክብር ላይ እንዳይረማመዱ አድርገዋል።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

02 Jan, 06:37


ፂማሙን አግቢ…
በምግቡ ውስጥ ፀጉር ቢያገኝ እንኳን
ከፂሙ እንደሆነ ትነግሪዋለሽ

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

01 Jan, 20:00


በነዚህ በሁለት ኪታቦች መካከል "የተርጂህ" ልዩነት አለ። አንድኛው ኪታብ "ሚስት በሷ ላያ ላያገባባት መስፈርት ካደረገች…መስፈርቱ ይጠበቅላታል!" የሚል ሲሆን፣ በቀይ ያከበብኩት ላይ ደግሞ" ሚስት በሷ ላይ ላያገባባት መስፈርት ካደረገች…መስፈርቱ ውድቅ ነው፣ ኒካሁ ትክክል ነው፣ መስፈርቱን መጠበቅ ግዴታ አይሆንም!" የሚል ነው።
ሁለቱም የሚያቀርቡት መረጃ ጠንከር ያለ ነው። ለኔ የሸይኽ ሱለይማን አር'ሩሐይሊይ መልስና የመረጃ ፍሰታቸው ገዝቶኛል። ድምፃቸውን ከታች ባለው ሊንክ ያገኛሉ
t.me/abdu_rheman_aman/3674
መልሳቸው ፦
"ሚስት በሷ ላይ ላያገባባት መስፈርት ስታደርግ…ከሓላል ነገር ከለከለቺው እንጂ ሐላልን ሐራም አላደረገቺም።  ስለዚህ መስፈርቱ ይቻላል፣ መስፈርቱን አምኖ ከተቀበለ መጠበቅ ግዴታው ነው!። "
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

01 Jan, 18:46


ጠልሓ ቢን ዐውፍ ቸር ነበር። እጅግ በጣም ቸር። አንድ ቀን ባለቤቱ እንዲህ አለችው
“ከወንድሞችህ የበለጠ የመጨረሻ እርኩስ የሆኑ ሰዎችን አላየሁም።”
“ለምን እንደዚህ አልሽ”  አላት
“ገንዘብ ሲኖርህ  ይጣበቁብሃል፣ ምንም ከሌለህ ግን ጭራሽ አይጠጉህም።” አለችው
“ወላሂ… ይህ የመልካም ስብዕናቸው ውጤት ነው። ለነርሱ መስጠት በምንችልበት ጊዜ ወደኛ ይመጣሉ…  ሀቃቸውን መወጣት በማንችልበት ጊዜ ደግሞ ለራሳችን ይተውናል።” አላት።

ልብህ ንፁህ ይሁን።  ነገሮችን ሁሉ በመልካም መልካቸው ለማስተናገድ ሞክር። አዕምሮህ ሰላም እንዲሆንም ከፈለግህ  ሁሉንም ነገር አትፈልፍል። ሁሉንም ምክንያት ልወቅ አትበል።  ሰላም ትሆናለህ።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

01 Jan, 13:39


የ 23 አመቱ የሰላም መስጊድ ኢማም እና ኡስታዝ አቶ ሙሀጀር አህመድ (acute leukemia) በደም ካንሰር ህመም በፀና ታሞ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተኝቷል።

ናሙናው ወደ ባንኮክ ተልኮ በተደረገው የመቅኔ ምርመራ ወንድማችን በደም ካንሰር መያዙ ስለተረጋገጠ ጥቁር አንበሳ የህክምና ማእከል ከላይ የተያያዘውን ያያያዝነውን ማረጋገጫ የሰጠው ሲሆን የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የእርዳታ ማሰባሰብያ ፍቃድ ደብዳቤ ፅፈውለታል።

እና ሁላችንም ሙስሊሞች ይህን ለጋ የኡማው ሀብት ከሞት የመታደግ ሰበብ በማድረስ ለአኼራ እና ለአዱኒያ የሚሆነንን ስንቅ እንያዝ

ማስታወሻ:- ለመታከሚያ ይሆነው ዘንድ የምንችለውን የገንዘብ መጠን ወደ አካውንቱ ከመላክ ጀምሮ ሄዶ በመጠየቅ ትላልቅ ወጪዎችን በመሸፈን እና በተያያዥ ጉዳዮች ቤተሰቦቹን በማማከር እንሳተፍ። ባረከላህ ፊኩም!

የወንድሙ አብዱል ሰመድ አህመድ ስልክ እና ሂሳብ ቁጥር 0932512569
1000362457468 ንግድ ባንክ

share ማድረግ አትርሱ አደራ
ሚዲያ ካላችሁ እዛ ላይ ይህን ፅሁፍ አጋሩት

ባረከላህ ፊኩም

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

06 Dec, 19:19


የተደበቀ ደስታ አለ። ግን ለመውጣት ያንተን ኢስቲጝፋር ይጠብቃል። ኃጥያት ብዙ መልካም ነገሮችን ይደብቅብሃል። ግን በዋናነት  የመኖርን ደስታ ሲሸፍንብህ ይኖራል። በኢስቲጝፋር ግለጠው። ምህረትን ጠይቅ!

«መኖርህ ካልቀረ የላቀ ኑሮ ምረጥ»
Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

06 Dec, 05:13


"ጁሙዓ ሙባረክ" ማለት ይቻላል። ስህተት የሚሆነው "ጁሙዓ ሙባረክ" ማለት ሱና ነው ብለህ ያመንክ ግዜና ነው!።…በሁለት መስፈርት "ጁሙዓ ሙባረክ " ማለት ይቻላል፦
1, ሱና አለመሆኑን አምነህና
2, ሁልግዜ ላታዘወትረው ነው።

🎙ሸይኽ ዐብደሰላም አሹወይዒር]
👇በዚህ ገብታቹህ ድምፃቸውን ያድምጡ
https://youtu.be/aV-XKDUtjNM?si=NzU7SOwJjURfV34p

"ጁሙዓ ሙባረክ" ማለት ከዱዓ ውስጥ አንዱ ነው። ሁልግዜና አዘውትሮ ካላለው ችግር የለውም። ግን በተህኒኣ መልኩ ከሆነ መሰረት የለውም።…ጁሙዓ ሙባረክ የሚልን ሰው አናበድዕም።

🎙ሸይኽ ሱለይማን አር'ሩሐይሊይ]
👇ሙሉ ድምፃቸውን በዚህ ያድምጡ
https://youtu.be/Px6Ik8N7ZYg?si=rGjaRvPkktVJWZci

|| ማሳሰብያ፦
ሸይኽ ፈውዛንና ሌሎች ከልክለዋል የምትሉኝ ወንድሞች ትኖራላቹህ፣ ግን ለሽይኽ ፈውዛን የቀረበላቸውን ጥያቄ አስተውላቹህ ከሆነ (في كل جمعة) በሚል መልኩ ነው የቀረበላቸው። በዚህ መልኩ ከሆነ: (علىٰ وجه الإستمرار) እነዚህኞችም አልፈቀዱም። ሲቀጥል የሸይኽ ፈውዛን መልስ ተፍሲል የለውም። *ወሏሁ አዕለም*

አብደረህማን አማን
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

06 Dec, 04:02


የሂስኑ'ል ሙስሊም ኪታብ ባለቤት የሆኑቱን ሸይኽ ሰዒድ ቢን ዓሊይ ቢን ወህፍ አል-ቀህጧኒን ታሪክ ለማንበብ ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ያንብቡ።
👇
t.me/abdu_rheman_aman/3447
t.me/abdu_rheman_aman/3447

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

05 Dec, 19:04


ምድር ላይ የታላቅነትን ዘውድ አጥልቆ የተወለደ ሰው የለም። የልጅነትን ህይወት ሳያይ  እጅግ ዝነኛ የሆነ ፍጡርም የለም።  የትኛውም የተሳካ ታላቅ ግብ  መነሻው ህፃን ህልም ነበር። መስከረም አምልጦህ ከነበር ፣ ከጥቅምት መጀመር  ነውር አይምሰልህ። መሬት ወድቀህ ካልተነሳህ ትበሰብሳለህ። መውደቅህ ሳይሆን ወድቀህ መተኛትህ ያበሰብስሃል።  እርግጠኛ ሁን! ከእናቱ ሆድ  ፒኤችዲ ሰርቶ የወጣ ፣ የገንዘብ ባለፀጋ ሆኖ የተፈጠረ የለም። አንድ ሰው የደረሰበት ቦታ ላይ መድረስ ያቅተኛል ብለህ ታስባለህ?
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

05 Dec, 11:14


አላህ በሁለት ጥንዶች መካከል ይኖራል ያላቸው “መወዳህ ወ ራህማህ” የራሱ መገለጫዎችም ናቸው(ወሊላሂ መሰሉል አዕላ)። "ሑብ" ን የሚበልጡ ጥልቅ መልዕክቶችን አቅፈዋል። በፌሽታ ጊዜ መወዳህ ይኖራል፣ በጭንቅና በረብሻ ጊዜ ራህማህ ይኖራል። በህይወት ውስጥ ለሚፈጠሩ ሁሉም አይነት መገለባበጦች መፍትሄ ሆነው የመጡ ሁለት ውበቶች። መወዳህ… አብሮነትን፣ ልስላሴን፣ መሳብን፣ በፍቅር መነደፍን፣ መመሰጥን ቀላቅሎ ሲይዝ ራህማህ ደግሞ ይቅር ባይነትን፣ አቃፊነትን ፣ ሆደሰፊነትን፣ ትዕግስትንና እዝነትን ይቀላቅላል። የሁለቱንም ጥንዶች ልብ የሚያረጋጋ ጥልቅ መልዕክት። «ወጀዓለ በይነኩም መወደተን ወራህማህ።»
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

05 Dec, 06:49


ሸይኽ ሙ/ድ አሚን አል-ሀረሪይ👆

ልጃቸው አብደሏህ የዒሻ ሶላት በአዳማ ከተማ እያሰገደ የተቀዳውን የቁርኣን ቅጂን ለማድመጥ ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ያድምጡ።👇
t.me/abdu_rheman_aman/2615
t.me/abdu_rheman_aman/2615

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

04 Dec, 09:18


ስማቸው "ሸይኽ ሙሐመድ አሚን ቢን አብዲላህ ቢን ዩሱፍ አል-ሀረሪይ አል-ኢቱዮጲይ ይባላሉ።
|
የሒዎት ታሪካቸውን ባጭሩ፦
|
እኜህ ሸይኽ…በሒጅርያ አቆጣጠር በ'1348 በሐረር ከተማ ከርዮ አከባቢ "ቡዩጢይ" የምትባል መንደር ተወለዱ።  የእናትን ፍቅር ሳያጣጥሙ በልጅነታቸው እናታቸውን እንዳጡ ይነገራል። ገና እድሜያቸው ሳይፀና'ና እንደልጆች ቦርቀው ሳይጨርሱ ነበር፣ አባታቸው በአራት አመታቸው ቁርኣንን እንዲማሩ  ወደ መድረሳ ይዟቸው ይሄድ እንደነበረና ዕድሜያቸው ስድስት አመት ሲደርስ ቁርአንን እንዳኸተሙ የሚነገረው።

ቁርኣንን ካኸተሙ ቡኃላ የተለያዩ የኢስላማዊ እውቀትን ለመሸመት ለአፍታምዃን ዘንግተው አያውቁም ነበር። ፊቅህንና የተለያዩ የዓረበኛ ሰዋሰ (የነህዉ፣ የሶርፍ፣ የበላጟና የመንጢቅን) ዒልሞችን ባገራችን (በኢቲዮጲያ) ባሉ መሻይኾች ላይ ተምረው የነሕዉ ጠቢብ የሚል ደማቅ ስምን አፍርተዋል። በሳቸው ላይ አሻራቸውን በስፋት ካሳረፉባቸው መሻይኾቻቸው ውስጥ « አቢ ሙሐመድ ሸይኽ ሙሳ ቢን አህመድ አል-አዲሊይ» ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ። ዕድሜቸው 25 አመት ሲሞላ የተለያዩ ፈኖችን በማስተማር በኢቲዮጲያ ሲያገለግሉ ነበር።

በ'1389 አመተ ሒጅሪያ በ'37 አመታቸው ወደተከበረቺው ሀገር "ሱዑዲያ" ከተሙ። "በዳሩል ሐዲስ አል-ኸይሪያህና በመስጂደል ሐረም በአስተማሪነት ያገለግሉ ነበር።
የፃፏቸው ኪታቦች ከ'45  በላይ ለሙስሊሙ ኡማ አበርክተዋል።
ከፃፏቸው ኪታብ ውስጥ አራቱን ብቻ፦
1, "ዑምደቱ አተፋሲር ወል ሙዕረቢን ዓላ ረቢል'ዓለሚን" ከሰላሳ ሙጀለድ በላይ ሲሆን፣ ግን አልጨረሱቱም።
2, "አል-ባኩረቱ'ል ጀኒያህ ሚን'ቂጧፊ ኢዕራቢ-ል-አጁሩሚያህ" ኢቲዮ እንዳሉ የፃፏት ኪታብ ስትሆን፣ ሱዑድያ ከገቡ ቡኃላ በአዲስ መልኩ ፅፈውታል።
3, "አል-ፉትሐቱል'ቀዩሚያህ ፊዒለሊ ወደዋቢጢ'ል አጁሩሚያህ" ስትሆን በስፋት ሀገራችን ላይ የምትታወቀው እቺው ኪታብ ነች።
4,ሐሺየቱን ዓላ'ከሽፊን'ኒቃብ ዓላ'ሙላሐቲል ኢዕራብ

ህልፈታቸው፦
በ'1441 ዓ.ሒ ዕለተ ሰኞ በቀን 7 በወረሃ ሪቢዒል-አወል ከመጝሪብ ሶላት ቡኃላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ከ90 ዓመት በላይ ዱንያ ላይ ቆይተዋል። አሏህ በጀነት ጨፌ ያኑራቸው።

አብደረህማን አማን
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

04 Dec, 03:51


የእኝህን ሸይኽ ስም የነገረኝ እሸልመዋለሁ!።
:
:
• በጦለበተል ዒልም ላይ ያላቹህ ወንድሞች እንደምታውቋቸው ተስፋ አደርጋለው። ቢሆንም ግን… ማን ናቸው?
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

03 Dec, 19:47


የምድር ኮኮብ፣ የዒልም አባት የሆኑት ሸይኽ ዐብደር-ራህማን ቢን ናሲር አስ-ዕዲይን ለመጀመርያ ግዜ በዚህ ቪድዮ ነበር ያየኃቸወ።

በድጋሜ ታሪካቸውን ለማንበብ ከታች ባለው ሊንክ ይግቡና ያንብቡ።👇
t.me/abdu_rheman_aman/1324
t.me/abdu_rheman_aman/1324

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

03 Dec, 18:00


ወላጆችን መታዘዝ አንተ የምትፅፈው
ታሪክ ሲሆን ልጆችህ ደግሞ ይተርኩልሃል!።
:
:
• ወልደህ ቅመሰው!። ☞ ምርቃን ወይም እርግማን ነው!።
Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

03 Dec, 04:28


የሽይኽ ሷሊህ ቢን ፈውዛን ቢን አብደሏህ አል-ፈውዛንን ታሪክ ለማንበብ ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ያንብቡ👇

t.me/abdu_rheman_aman/3452
t.me/abdu_rheman_aman/3452

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

02 Dec, 11:38


ኦሮሚያ ክልል አይደለም!። ለሚዛን አማን ወይም ለሚዛን ቴፒ ብዙም አይርቅም። ጎረቤት ናቸው። ሸይኽዬው ምራቅ ዋጥ ያደረገ ሸይኽ ቢሆን የተሻለ ነው። በዒልም የበለፀገ ሸይኽ ቢሆን አንጠላም፣ ግን ባይሆንም (ኹጥባና ሙኽተሶራቶችን የሚያቀራም ቢሆን ችግር የለውም።

በዚህ ቦት አሳውቁኝ👇
@Nehnu_abnau_aselefiyin_bot

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

02 Dec, 11:22


السلام عليكم

ያጀማዓ! አንድ ነገር ተባበሩኝ፣ ለሆነ መስጂድ (ደቡብ ክልል "ልዩ ቦታው: መንገጠያ ከተማ") ላይ ኢማም መሆን የሚችል ሸይኽ የምታውቁ ከሆነ ጠቁሙኝ፣ አገናኙኝ።

በዚህ ቦት አሳውቁኝ👇
@Nehnu_abnau_aselefiyin_bot

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

02 Dec, 05:11


ያረብ ከፀጋህ አትከልክለን!። ውደድን፣ ወዳተው አስጠጋን።

. نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

02 Dec, 04:26


ከዋሸህ አትማል፣ አንድ ወንጀል ይበቃሃል!።

Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

01 Dec, 18:06


አንዱ ጓደኛው ጋር መጣና  እንዲህ አለው:
" ልቤ ለእከሌ ጥሩ ነገር አያስብም።
ጓደኛውም: እኔም ልክ እንዳንተው ነኝ፣ ነገር ገን ምን ይታወቃል ደጋግ ሰዎችን እንዳንወድ አሏህ ልቦቻችንን ከድኖ ቢሆንስ??
:
:
የጓደኝነት ሚስጥር!
Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

01 Dec, 06:50


የሸይኽ አህመድ ቢን ዓሊይ ቢን ሙሐመድ…ቢን ሀጀር አል-አስቀላኒይን ታሪክ ለማንበብ ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ያንብቡ!።👇

t.me/abdu_rheman_aman/3085
t.me/abdu_rheman_aman/3085

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

30 Nov, 18:29


ትዝብቴ ከሴቶች
~~~
አንዳድ እህቶች በወጣትነታቸው ዕድሜ እንደፈለጉ (ላይፍ ነው እያሉ) ሲጃጃሉ ይከርሙና ለማግባት ሲፈልጉ ይስተካከላሉ፣ የመድረሳንም ደጅ ይጠናሉ።……ግን ለምን !?

አሁን ላይ: ላይፌ ነው እያልሽ የምታሳልፊው ሒዎት፣ አሏህ እንደማይወድው እያወቅሽ ለምን አሏህን ትወነጂላለሽ? "መልካሙ ለመልካሚቷ ነው" ማለቱን አትዘንጊ። አመሻሽ ላይ የሚመጣ ነገር ወጋ ያስከፍላል!።

؏ــبــد الرحمـٰن أمان
Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

30 Nov, 17:25


ቆይታህ ወደ ማለቅ ነው፣ ማለቂያህ
ደግሞ ወደ ቆይታ ነው፣ ከማይቆየው
ቆይታህ ለማያልቀው ቆይታህ ስንቅ ያዝ!።

Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

16 Nov, 06:39


አንዱ ባጫት እንስት ላይ፣ ጣልቃ ገብቶ እሷን ማጨት ክልክል ነው። ነብያችን ﷺ እንዲህ ይላሉ ፦
"لايخطب الرجل علىٰ خطبة أخيه حتى يترك الخاطب قبله. او يأذن له الخاطب

" አንድ ሰው በወንድሙ ማጨት ላይ እንዳያጭ፣ ቀድሙ ያጫት እስኪታው፣ ወይም እስኪፈቀድለት ድረስ። "

በዚህ ሐዲስ መሰረት: የታጨችው ወይም ወልዯ ለመጀመርያው ሰው ፍቃዳቸውን ከቸሩት ቡኃላ ጣልቃ ገብቶ እሷን ማጨት ክልክል ነው።
አንዱ ያጫትን ለማጨት፦
1, መጀመርያ ያጫት ሰው ተቀባይነት አለማገኘቱን ካወቅን ቡኃላ።
2, መጀመርያ ያጫት ሰው ለሁለተኛው ሰው ከፈቀደለት ቡኃላ።
3, መጀመርያ ያጫት ሰው እሷን ከማጨት መተውን ያወቅን ግዜና ነው የሚቻለው።

تماما المنة في فقه الكتاب وصحيح السنة

ቅፅ 3: ገፅ 17 ላይ የወሰድኩት ነው።

አብደረህማን አማን
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

15 Nov, 18:38


የኪታብ ስጦታ!

ብዙ ግዜ በ'PDF ስንፈልገው የነበረው
" حاشية الصبان شرح الأشموني علىٰ ألفية ابن مالك. ومعه شرح الشواهد للعيني

ብዙ ግዜ ኪታቡ ገባዬ ላይ ስለማይገኝ አልፍያ ለሚቀሩ ልጆች ሼር አርጉላቸው።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

15 Nov, 17:49


አቡ ለሐብ በዚህ ዘመን ቢኖር ንሮ፣ አንዳንድ ወንዶችን…ሴት መስለውት እስከነሒዎታቸው ይቀብራቸው ነበር።
:
እረ ወንዶች ወንድ ሁኑ!።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

14 Nov, 18:25


መልስ፦

የመጀመርያው ክብ ላይ ያለቺው ( በደንብ ዜሮ " 0 " የምትመስለው) " ዓላመቱ'ሲፍር አል-ሙስተጢል" (علامة الصفر المستطيل ) ትባላለች። ጥቅሟም: በምናቆም ጊዜ በአሊፍ ነው የምናቆመው፣ ማለትም: ሳ..ብ አድርገን  "ቀዋሪ..ራ" ብለን። አያይዘን በምንቀራ ሳዓት ደግሞ ሳንስብ "ቀዋሪ.ረ…" ብለን እንድንቀራ ትጠቅመናለች። ጥቅሟም ይሄው ነው።

2ኛዋ ድግሞ ( ጭምት ብላ ዜሮ  ° የምትመስለዋ) "ዓላመቱ ሲፍር አል-ሙስተዲር"(علامة الصفر المستدير) ትባላለች። እዚህ ላይ ያለቺው " ° "  አያይዘን ስናነብም ሆነ ስናቆም አንድ አይነት ንባብ ነው ያላት። እሱም: አያይዘን ስንቀራ "ቀዋሪ.ረ…" ብለን ሲሆን፣ ስናቆም ደግሞ "ቀዋሪ.ር…" ብለን እናቆማለን ማለት ነው።

(ተሸላሚ: ወንድም አህመድ ነው)

በደንብ እንዲገባቹህ ከታች ቪዲዮ እልክላቹኃለው👇

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

13 Nov, 18:48


ጥያቄ……?

ከላይ እንደምታዩት በቀይ የተከበበ 2 ክብ አለ። ሁለቱም ክብ ውስጥ አሊፍ "ا" አለ። ሁለቱም አሊፍ ላይ…ከላያቸው ዜሮ "0" የምትመስል ክብ ነገር አለች፣ እና ጥያቄው ምን መሰላቹህ! "ልዩነታቸው ምንድን ነው? ለምንስ ይጠቅማሉ? አቀራራቸውስ እንዴት ነው?


፨ አብራርቱ የመለሰ፣ እሸልመዋለሁ
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

13 Nov, 18:02


ማስታወሻ!

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته.

እንደሚታወቀው በ'ዕለት ሀሙስ የሚካሄደው (የተማሪዎች) ፕሮግራም እንደተጠበቀው ይቀጥላል። በዕለቱ ለየት ያል (በልጆች የሚቀርብ) ፕሮግራም ስላለ፣ እንድትታደሙ ስንል በአፅንዖት እንገልፃለን።

የአጅሩ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ተማሪዎችን ይጋብዙ፣ ይጥሩ፣ የኸይር ምንገድ ስበብ ይሁኑ!።
t.me/Werebabo_wetatoch_jemea

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

13 Nov, 17:34


የተኛ ሰው ህልም ላይ እንዳለ…
ከነቃ በኋላ እንጂ አያውቅም
እንደዛውም ከአኺራ የተዘናጋ ሰው…
ሞት ሲመጣበት እንጂ ያከሰረውን ነገር አያውቅም!።

Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

13 Nov, 04:28


“ጌታዬ እኔ አንተ የምታውቀው ዑመር እንጂ ሰዎች የሚያውቁት ዑመር አይደለሁም።”
ዑመር ቢን የዕቁብ በሌሊት ስግደቱ ላይ እያለቀሰ ሲደጋግመው የነበረው ቃል ነው።

በሰዎች መሀል ተራራ ልትሆን ትችላለህ። የማይገፋ የሚመስል ፣ የማይናድ ስብዕና ባለቤት። በአንዳንዶች ዘንድ የቅድስና ምልክት ተደርገህ ልትያዝም ትችላለህ። የማያጠፋ የሚመስል የመልካም አባት። ግን እነርሱ ስንት የነፍስ ፈተና እንዳንበረከከህ አያውቁም። የድካም ቀዳዳህ በየትኛው በኩል እንደሆነም አልተገለጠላቸውም። አላህ ነው የሚያውቀው። እናም አንተ ሰዎች የሚያውቁህ አንተ ሳትሆን አላህ የሚያውቅህ አንተ ነህ።

Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

12 Nov, 17:54


"ማር የተሰራው አህያ እንዲልሰው
አይደለምና ማረፊያህን ለይ!"

Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

12 Nov, 11:53


በቀዝቃዛ ምጣድ ላይ ዳቦ አትጋግር!
~~
ወንድሜ እስቲ  ልጠይቅህ፤ ፀጥ ረጭ ባለች ውድቅት ሌሊት ላይ ሁሉም በተኛበት ሰዓት ተነስተህ ለጌታህ የሰገድክባቸውን ቀናት ታስታውሳለህ?  
በመስጂድ ውስጥ ማንም በሌለበትስ ብቻህን ሁነህ ቁርአን አኽትመህ የተደሰትክበት ቀን ትዝ ይልሃል?
የምትሰራውን ሰናይ ተግባር ከእይሉኝና ከይስሙልኝ  የደበቅክበት ቅፅበትስ ይታወስሃል?
  የህይወት ምዕራፍ  አንድ አይደለችምና ቆም ብለህ ነፍስህን ጠይቃት!  ከዚያም መልሱን ንገራት! 

     ታላቁ ታቢዒይ ረቢዕ ቢን ኹሰይም ሁል ቀን ቤቱ ውስጥ ቁርአን ይቀራ ነበር። ሰዎች ወደ ቤቱ ሲገቡ ቁርአኑን በጨርቅ ይሸፍነዋል።
ለምን መሰላችሁ? አቀራሬ ጥሩ አይደለም ብሎ ትችትን ፈርቶ  እንዳይመስላችሁ፤ መልካም ስራውን ከሰዎች መደበቁ ነው!
አይገርምም?  እየቀራ ከሚያየው ሰው ይደበቃል!
   እኛ ደግሞ ሳንቀራ የሚያወድሰንን ፍለጋ ስንኳትን፤ ስንቀራም የሚያሞካሸንን ክጀላ ስንተጋ ከርመናል።
  አስተውል!  እነርሱ የሰሩትን መልካም ስራ ሰርተው ልቦናቸው ስጋት ይገባዋል! ቅንነታቸው ተግባራቸውን ሲያረጋግጥ ኖረዋል። ሰው ሲባል ከማየትና ከመስማት በስተኋላ ወይ ማወደስ አሊያ አቃቂር አውጥቶ መተጨት እንጂ ምንም ማድረግ እንደማይችል ተገንዘበዋልና ለሰዎች የጎመን ፍሬ ያህል ደንታ የላቸውም!
  እኛጋ ስንመጣ ደግሞ በቀዝቃዛ ምጣድ ዳቦ የሚጋግር ሞልቷል፤ የጀነትን ሰርተፍኬት ከሰው ውዳሴ የሚፈልግ በዝቷል! ይህንንም አስመልክቶ፡
  «ለአላህ በኢኽላስ የሚሰራ ሰው ምንኛ አነሰ!» ይሉናል ኢብኑል ጀውዚ!
አደራህን! ስለ ሰዎች አትጨነቅ ምንም አይፈይዱህም፤ ስራህን በቅንነትና በታማኝነት ለጌታህ ብቻ አጥራ!
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

11 Nov, 06:39


የከንፈሮችን ሁኔታ ልብ ብላቹህ ተመልከቱት

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

11 Nov, 06:31


መልስ፦

"ላተኧመና" የሚለው ቃል አስሉ " تَأْمَنُنَا " ላተኧመኑና" ነበር፣ የመጀመሪያዋ "ኑን" ዶማ ስትሆን የሁለተኛዋ "ኑን" ደግሞ ፈትሓ ናት። እነዚህ ሁለት ተመሳሳይ ፊደላቶች ኢድጛም ተደርጉና በአንድ ፊደል ብቻ ይቀራሉ ማለት ነው። ከላይ ዜሮን የምትመስለዋ ደግሞ የመጀመሪያዋ ኑን ዶማ ለመሆኗ ምልክትና የአነባበቡ ስልት ከንፈርን ከከፈርጋር አገናኝቶ፣ ትንሽ ወደፊት ከንፈሮቻችነን ገፋ አድርገን እንድንቀራ ምልክት ነች።

የአቀራሩ ስልት እንዲገባቹህ ከታች የምለቅላቹህን ቪዲዮን ይመልከቱ👇

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

10 Nov, 19:36


ጥያቄ?
لا تـأ مـنـا

እዚህ ላይ ያለቺው ዜሮ የምትመስለዋ ለምን መጣች? እንዴትስ ነው የሚቀራው? ለምንስ መጣች?

በኮሜንት መስጫው ላይ መልሱ
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

10 Nov, 19:22


የቆሸሸ ልብሱን - እድፉን ሊያጠራ
ሲኳትን ይውላል - ከሳሙና ጋራ
እድፉና ነውሩን - ከልቡ ደብቆ
አንድ ቀን ይጓዟል - እድፉን ወሽቆ
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

10 Nov, 14:29


የነገሮችን መጠራቀም ተጠንቀቁ። እነዚህ መጠራቀሞች የፈነዱ እለት ወዳጅ አይለዩም፣ የልብ ሰውንም አያስቀሩም። … የቸልተኝነት፣ የራስ ወዳድነትና የብዙ ጥፋቶች መደጋገም የሆነ ቀን የለየለት መጠላላትን ያመጣል።  "ለዚህች ጥፋት?" ትሉ ይሆናል በሰዓቷ ምክንያት…   እነርሱ ጋር ግን ትዕግስት  እንዲያጡ ያደረጋቸው የተጠራቀሙና የተቆጠሩ ጥፋቶች አሉ። ይሻሻላሉ ተብለው የተጠበቁ እልፍ ትዕግስቶችም ነበሩ…
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

09 Nov, 07:37


ታላቅ የኸይር ስራ ጥሪ

የመስጅደል ፉርቃን ግንባታ ፕሮጀክት በወሎ ወረባቦ  ቢስቲማ ከተማ። ይመልከቱና በዱዓና በገንዘብ ይገዙን
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

09 Nov, 07:12


ይህ ትላን ጁሙዓ ከዓሱር ቡኃላ የነበረው ድባብ ነው። የድካምን ውጤት እንደማየት የሚያስደስት ነገር የለም። በዚህ መስጂድ ላይ አሻራቹሁን ብታሳርፉ ሚንዳው ቀላል አይደለም።
||
ይህ ጉሩፕ የወረባቦ "ቢስቲማ" የወጣቶች ጀመዓ ነው። ተቀላቀሉ👇

t.me/Werebabo_wetatoch_jemea

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

09 Nov, 07:04


ምንኛ ደስ የሚያሰኝ ርብርብ ነው! ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የሚችለውን እያደረገ ነው። በዚህ የመስጂድ ግንባታ ላይ የሶደቀቱን ጃሪያ ድርሻ እንዲኖረው የሚሻ ያቅሙን በማገዝ ለኣኺራው ስንቅ ያስቀምጥ።
መስጅደል ፉርቃን በወረባቦ ወረዳ ዋና ከተማ ቢስቲማ ላይ እየተሰራ ያለ መስጂድ ነው። መስጂዱ ለከተማው ድምቀት ነው። ከዚያ በላይ ግን ለከተማውም በዙሪያው ላሉ ቀበሌዎችም ጥሩ የደዕዋ መነቃቃት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፣ ኢንሻአላህ።

መርዳት ለምትፈልጉ ከታች በተለጠፈው አካውንት ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ።
#ወረባቦ ፉርቃን መስጂድ
ንግድ ባንክ - 1000401221957
አቢሲኒያ - 64828638
ዳሽን - 2935824167011

መልእክቱን በማሰራጨት ተባበሩን። ምናልባት በናንተ በኩል ተሳትፎ የሚያደርግ ቢኖር ከአጅሩ ተካፋይ ትሆናላችሁ።
{ مَنْ دَلَّ عَلَى خَيْرٍ فَلَهُ مِثْلُ أَجْرِ فَاعِلِهِ }
"ሌሎችን ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የተገበረውን ሰው አምሳያ ምንዳ ይኖረዋል።"
=
ቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

09 Nov, 04:39


አንተስ ዛሬ ለማን ትላለህ?
-------
አንድ ሰው መጣና ለሀሰን አል-በሰሪይ እንዲህ አላቸው፦
  "ለልጄ ብዙ ሰዎች የጋብቻ ጥያቄ አቅርበዋል። ለማን ልዳራት?"
  ኢማም ሀሰንም፦
ﻣِﻤَّﻦْ ﻳَﺘَّﻘِﻲ ﺍﻟﻠَّﻪَ ، ﻓَﺈِﻥْ ﺃَﺣَﺒَّﻬَﺎ ﺃﻛﺮَﻣﻬﺎ، ﻭﺇﻥْ ﺃﺑﻐَﻀَﻬﺎ ﻟﻢ
ﻳَﻈْﻠِﻤْﻬﺎ
«አላህን ለሚፈራው ሰው (ዳራት)። ከወደዳት ክብርን ለሚቸራት፤ ከጠላት ደግሞ ለማይበድላት።» አሉት
[ኢህያእ ዑሉም አድ-ዲን] ( /2 41 )

      ይገርማል የኢስላም ፍትህ!
ከምንም በላይ የላቀ ዋጋ ያላት ብርቅ ፍጡር አደረጋት። የላሸቀ አኗኗር እንድትኖርም አልፈቀደም።  ጥሩ ሴት ለጥሩ ወንድ እንደምትገባም አረጋገጠ!

ድሮ ድሮ  በጨለማ(ጃሂልያ) ዘመን  አንድ ሰው የጋብቻ ጥያቄ ሲያቀርብ  "ጎሳዋ (ዘሯ) ምንድነው?"  " ጎሳው (ዘሩ) ምንድነው?" ነበር የሚባለው!
    ቆይ ግን በዘር ብቻ ተጋብተው  ሊፋቀሩ ነው ወይስ ስለዘራቸው ሊተራረኩ?

     አሁን አሁን ደግሞ  ጎረምሳው  "ምን አላት?" ልጂቱም "ምን አለው?"
      በዚህ የጥቅማጥቅም ምህዋር ዙሪያ የምትሽከረከረውና በዚህ መረብ የታሰረችው ትዳር  ዕጣዋ ምን ሊሆን እንደሚችል አስባችሁታል?
አላውቅም ሰዎች እንዴት እንደሚዋጥላቸው!
የሚገርማችሁ ለአንድ ወንድሜ  "ለምን አታገባም?" ስለው፥ "ቤትና ብር ያላት አጣሁ። በአሁን ሰዓት የጋብቻ ጨዋታ በካሬ ሜትር ሆኗል ባክህ።" አለኝ!
ሱብሃነሏህ!
ለጥቅም ተጋቡ ከዛስ ጥቅሙ ሲያልቅ ወይም ሲወድም ሊፋቱ?

   ኢስላምስ ምን አለ?
  "ዲኗ ፣ ስነምግባሯ እንዴት ነው?"  "ዲኑ፣ ስነምግባሩ እንዴት ነው?"
    ያ ሰላም!
ከዛም ማንነቷን ወዶላት ይኖራሉ።  እውነተኛ የፍቅርን መዓዛ ያጣጥማሉ፤  ጎጇቸውንም በውዴታ ፈርጦች ያሸበርቃሉ፤ጣፋጭ የእዝነት ምስልንም በህይወት መዝገባቸው ላይ ያሰፍራሉ……!
  ለማንነቷ ነውና የትዳር አጋሩ እንድትሆን የፈቀደው  እስከ መጨረሻም አብረው ይዘልቃሉ! ምክንያቱም ምንም ጥቅም አላያያዛቸውም!
 
   እንግዲህ መልካም… ጋብ…  
    ስቀልድ ነው! ቻው!
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

08 Nov, 05:13


እናታችን ከዲጃህ ነብዩን ስታገባ 28 አመቷ ነበር።
~  ~  ~
ብዙን ግዜ ነቢያችን ﷺ ኸዲጃን ሲያገቧት 40 አመቷ ነበር የሚባል ነገር እንሰማለን። በኢብኑ ኢስሐቅ በኩል የመጣው ሪዋያ ደግሞ በ28 አመቷ ነው ያገቧት የሚል ነው። በአረባ አመቷ ነው ያገቧት የሚለውን ያወራው "አል-ዋቂዲይ" ነው። ይሄ ግለስብ ደግሞ በሙሐዲሶች ሚዛን ደረጃ ውሸታም ነው።  የሐዲስ ጠቢባኖች በኢብኑ ኢስሐቅ በኩል የመጣውን በ28 አመቷ ነው የሚለውን ያጠናክራሉ። ምክንያቱም በ28 አመቷ የተገባች ሴት መሃፀኗ 6 ልጆችን አፍርቶ የመውለድ ችሎታ አለው። በ40 አመቷ ከተገባች ሴት አገልባጭ። {[ከዓረበኛ ወደ አማረኛ የተዞረች]}

• በተጨማሪ ከላይ ያየያዝኩት ፎቶ ላይ እንዲህ ይላል፦
ويذهب ابن اسحاق إلى أن خديجة كانت في الثامنة والعشرين من العمر. في حين تذهب رواية الواقدي إلى أنها كانت في الأربعين. وقد أنجبت خديجة من رسول الله ذكرين وأربع إناث ممايرجح رواية ابن اسحاق، فالغالب أن المرأة تبلغ سن اليأس من الإنجاب قبل الخمسين.

[አሲረቱ ነበዊያቱ ሶሒሃህ: ቅፅ 1 ገፅ 113]

አብደረህማን አማን
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

07 Nov, 19:35


እህቱን ወይም ልጁን ሊድር የሚሻ ሰው ቀድሞ ከቁሳዊ እሳቤ ጭንቅላቱን ማፅዳት አለበት። ገና ለገና ደህና ኢኮኖሚ ካለው ጋር ስለመዛመድ ብቻ እያሰበ የሴቲቷን ህይወት የፅልመት አረንቋ ውስጥ መጨመር ትልቅ በደል ነው። «ዲኑንና ስነምግባሩን የምትወዱለት ሰው ከመጣ ዳሩት» ያሉት መልዕክተኛው ዝም ብሎ እንዳይመስልህ። አንድ ቤት ቤት ሆኖ እንዲቆም የባል ምግባር ትልቅ ሚና አለው። ለዚያም ነው ረሱለላህ "አኽላቅን" ዲን ውስጥ የሚካተት ነገር ሆኖ ሳለ ከዲን ነጥለው ለብቻው የጠቀሱት።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

07 Nov, 04:16


ማንም በማያይህ ግዜ……አንተ ማነህ ?

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

06 Nov, 19:56


وَيلِي كُلمَا طَالَت أَيامِي كَثرت آثَامِي

ዋኔ! ቀናቶቼ በረዘሙ ቁጥር ወንጀሎቼ በዙ!
ዋኔ! እድሜዬ በተለቀ ቁጥር፣ መከራዎቼ በዙ
ስንቴ ንሳሃ ገባው፣ ስንቴ (ወደ ወንጀል) ተመለስኩ፣ ዋ! ወጣትነት

ዋ! ወጣትነቴ
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

06 Nov, 07:18


ህይወት ሁሌም ወደፊት ትራመዳለች። በየትኛውም መጨረስ ውስጥ የሚፈጠር ሌላ መጀመር አለ። የምታስበው የስኬት ማማ ላይ ላይ ስትደርስ ለሌላ ውጥን መሰላል ታዘጋጃለህ። በህይወትህ ውስጥ አንድ አስጨናቂ  ጉዳይ ያልፍና ሌላ አንገብጋቢ ጉዳይ ይከሰታል። የምትናፍቀውን ስታገኝ ያልናፈቅከውን ትናፍቃለህ። ሌሊትና ቀን በህይወትህ ውስጥ በማለፍና በመምጣት የሚተካኩትን ያህል ጉዳዮችህ በአንተ ውስጥ ማለቂያም፣ ማረፊያም አይኖራቸውም። ቀኑ ሲደብርህ ሌሊትን ትናፍቅ ይሆናል፣ ሌሊቱን አግኝተህ ስታበቃ  ደግሞ ቀኑን ትናፍቅ ይሆናል። ፍጥረተ ዓለሙ ትናንትም ዛሬም በማይቆም እንቅስቃሴ ውስጥ ነው።አንተ  ደግሞ የፍጥረተ ዓለሙ አንድ አካል ነህና "አትቁም፣ ወደፊት ሩጥ፣ አሳካ!"።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

06 Nov, 04:37


መልስ፦
“ ኡሙ ሂንድ በመባል ትጠራለች። ከቀድሞ ባሏ "ከ'አቢ ሃላህ" የወለደቺው ልጇ ነው። ”

-------
መላሽ፦ N ነው።

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

05 Nov, 19:09


ጥያቄ…..?

ነቢያችን ﷺ አቡ'ል-ቃሲም በመባል ይጠራሉ፣ እናታችን ኸዲጃ ኡሙ….ማን በመባል ትጠራ ነበር ?

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

26 Oct, 07:42


በሌሎች መፅሃፍቶቻቸውም ላይ ፈተናዎችና ክስተቶች ለልቅና መሰላል እንደሆኑ ይመክረኝ  ነበር ሲሉ ያወሳሉ። ሸይኹል ኢስላም ለኢማም ኢብኑል ቀይዪም ታላቅ ባለውለታቸው ናቸው።  ከርሱ ጋርም በ ወህኒ ቤት የታሰሩበት አጋጣሚ ተከስቶ ነበር። 
ሸይኽ ኢብኑ ዐብዱ አድዳኢም ፣ ሸይኽ ኢብኑ መክቱም ፣ሸይኽ በድሩዲን ቢን ጀማዐህ፣ ሸይኽ ሰፊይዩ አድዲን አልሂንዲ፣ሸይኽ ኢስማዒል ቢን ሙሀመድ አል ሓራኒ፣ ሸይኽ መጅዱዲን አትቱንሲይ፣ ሸይኽ ኢብኑ አቢል ፈትህ፣ ሸይኽ አህመድ ቢን ዐብዱርራህማንና ሌሎቹም   ሸይኹ ትምህርትን የቀሰመባቸው ሊቃውንት ናቸው።
ከዚህ ድንቅ የኢስላም ምሁር ማዐድ ተቀምጠውና ጥበብን ቀስመው ካለፉት ገናና ተማሪዎቻቸው መካከል ኢብኑ ከሲር ፣ ኢብኑ ረጀብ፣ ዐሊይ ቢን ዐብዱል ካፊ፣ ኢብኑ ዐብዱል ሓዲና ሌሎቹም እንደ ምሳሌ ተጠቃሾች ናቸው።
ህልፈት
ሸይኹ በተወለዱ በ60 ዓመታቸው በሀሙስ ሌሊት  በወርሃ ረጀብ  በ751 ዓመተ ሂጅራ  ለማንም በማይቀረው ሞት ከዚህ ዓለም ተሰናበቱ። ብዙ ሰው በተሰባሰበበት የ ጀናዛ ሰላት ከተሰገደባቸው በኋላ  በ"ባቡ አስሰጊር" መካነ መቃብር ተቀበሩ።

ዝናቸው ሲነገር በሊቃውንት አንደበት፦
"በበርካታ የእውቀት ዘርፎች መጥቋል። በእውቀት የተጋሩት ጓዶቹን በልጧል። በአፅናፋትም ስሙ ተሰራጭቷል። የአበው ትውልድ መዝሀቦችንም በጥልቀት ተገንዝቧል።" ኢማሙ አሽሸውካኒ
"በብዙ የእውቀት ዘርፎች ላይ ጥልቀት ነበረው። በተፍሲር፣ በፊቅህ፣ በዐረብኛ ሰዋሰውና በሐዲስ  እውቀት ላይ(ከፍተኛ እውቀት ነበረው)።" ኢብኑ ቱጝሪይ

  እኔም ወጉ ደርሶኝ ስለ ዝናዎ ብፅፍ …"በርግጥም እርሶ የልበ ብሩህ መፍለቂያ ከነበረችው ደማስቆ ከተማ የፈለቁ  የሰባ ብዕረኛ ነዎት።   እርሶ በድንቁርና የተደፈኑ ጎጠኛ ባህረኞችን በልከኛው አቀዛዘፍ መንገድን የሚጠቁሙ ጀግና ቀዛፊ ነዎት። ከጨዋ ባህሪ የመነጨ ክቡር ማንነቶን ሳስታውስ ሁለንተናዊ ብልፅግናዎ ትዝ ይለኛል። አዎን በነጠረ እውቀት የተከበቡና በጥበብ  ንፅብራቅ የተጥለቀለቁ  ግዙፍ የደማ…ስቆ  ተራራ! የተይሚያህ ልጅ ምትክ!"
ይሄ ከታሪካቸው ውቅያኖስ በጭልፋ የመጭለፍ ያህል ነው። ብ…ዙ ይቀራል።  ለታሪካቸው የህይወት እርከን ወደል ድርሳን ያሻዋል። ሸይኽ በክር አቡ ዘይድ "ኢብኑ ቀይዪም አልጀውዚያ" በሚል 400 ገፆችን  ፅፏል። ሌሎችም እንዲሁ…ፅፈዋል።
አላህ መልካም ይመንዳቸው። እኛም የነርሱን ፈለግ የምንከተል ጀግኖች ያድርገን!
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

26 Oct, 07:41


የደማስቆው ተራራ!
~         ~        ~
   "በበርካታ የእውቀት ዘርፎች መጥቋል። በእውቀት የተጋሩት ጓዶቹን በልጧል። በአፅናፋትም ስሙ ተሰራጭቷል። የአበው ትውልድ መዝሀቦችንም በጥልቀት ተገንዝቧል።" ኢማሙ አሽ-ሸውካኒ
  "እርሶ በድንቁርና የተደፈኑ ጎጠኛ ባህረኞችን በልከኛው አቀዛዘፍ መንገድን የሚጠቁሙ ጀግና ቀዛፊ ነዎት።…… አዎን! በነጠረ እውቀት የተከበቡና በጥበብ  ንፅብራቅ የተጥለቀለቁ  ግዙፍ የደማ…ስቆ  ተራራ! ገናናው የተይሚያህ ልጅ ምትክ!"
"ኢማም አቡ ዐብዲል-ላህ ሙሀመድ ቢን አቢበክር  «ኢብኑ ቀይዪም አልጀውዚያ»!" ይባላሉ
ሸይኹ በ691 [ሂጅሪ] በወርሃ ሶፈር በ7ኛው ቀን መገኛዋን መካከለኛ  ምስራቅ ፡ ምዕራበ እስያ ባደረገችው  "ሶሪያ" ምድር ውስጥ ተወለደ። የተወለደበት ስፍራ ልዩ መጠሪያው የሀገሪቷ ዋና ከተማ  ደማስቆ ይሰኛል። ወይንም (አንዳንድ የታሪክ ፀሃፊያን እንዳስቀመጡት)  ከደማስቆ በደቡብ በኩል ከምትገኘው ሌላኛዋ ከተማ "ኢዝራ"  ይሰኛል።
     ደማስቆ ያኔ የስልጣኔ ማዕከልና የጥበብ ብርሃን የሚፈስባት ምርጥ ከተማ ነበረች። ለዚህም  ቤተሰቡ በሙሉ ሸሪዓዊ እውቀትን እየጠጡ ያደጉና ለሌሎችም እውቀታቸውን በማስተላለፍ አደራቸውን ሲወጡ የነበሩ በሳል ሰዎች ነበሩ።አባትየው "ቀይዪም አልጀውዚያህ" በሚል መጠሪያ የሚታወቅ የ"ጀውዚያ" መድረሳ ኃላፊና አስተዳዳሪ ነበር። 
   ህፃኑም "ኢብኑ ቀይዪም አልጀውዚያ" የተሰኘው ከአባቱ የማዕረግ መጠሪያ ጋር ተቆራኝቶ እንደሆነ ልብ ይሏል። አባት፣ ወንድም ፣ የወንድም ልጅ ወዘተ  መበጠስ በሌለው የወርቅ ሰንሰለት የተያያዙ የእውቀት ኃይሎችና የስብዕና ልዕልናዎች ናቸው። ከዚህ ለምለም የዒልም አየር በነፈሰባት ቤተሰብ ውስጥ ይህ ልጅ ተወልዶ ዒልም እየጠጣ ማደግ ጀመረ። ገና ከመነሻው ሁለት መልካም ስንቆች በእጣ ፈንታ ተቋጥሮለት የጠበቀው ይመስላል። የመጀመሪያው የቤተሰቡን የእውቀት ጥሪት የማፈስ ተስፋ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የብሩህ አዕምሮ ስጦታ ነበር። ከወላጅ አባቱ ባሻገር አካባቢው በሚገኙት የኢስላም ሊቃውንት ጥበብን ለማግኘት የኳተነው ገና በልጅነቱ ሲሆን በዘመኑ ከነበረው ትልቅ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ዐብዲልላህ ጋር ትምህርቶችን ያደምጥና ከሸይኽ አቡል ፈትህ አልበዕለብኪይ ጋር ደግሞ የዐረብኛ ሰዋሰውን መሰረት ያደረገው "አልፊየት ቢን ማሊክ" ን ይማር ነበር። ገና እድሜው 19 ሳይሆን የዐረብኛ ሰዋሰውን አብጠርጥሮ የሚያውቅና ወደል ድርሳናትን የሚቀራ በመሆኑ የወደፊት የሊቅነት ስሜት ከውስጡ ይወለድ፤ በዐይነ ህሊናውም ይመለከተው ነበር። በጊዜው ደማስቆ ላይ በቂ የእውቀት ትምህርቶች ቢኖሩም ወጣቱ ግን ተጨማሪ እውቀትን ፍለጋ ወደ ግብፅ ጉዞ እንዳደረገ ይነገራል። ከብዙ ሸይኾች በርካታ የእውቀት ዘርፎችን ቀሰመ።  ጥቅጥቅ ባሉ የእውቀት መንገዶች ነጉዶ ሲያሰላስል የኖረ ተመራማሪ በመሆኑና በነጋ ጠባ ያለ መታከት የሚንከራተት ጥበብ ፈላጊ በመሆኑ የተነሳ ከደማስቆ ሊቃውንት ተርታ በመሰለፍ የላቀ ክብርን ተጎናፅፏል።
(ከአሁን ቡኋላ የኢስላም ሊቅ ሆኗልና በአንቱታ ልጥራው)
  ሸይኹ ህይወታቸው ከእውቀት ጋር ነፍስ ከአካል ጋር የተያያዘውን ያህል የተሳሰረ ነበር። ስማቸው በአፅናፋት እየተወሳ ማንነታቸው በጥሩ እየተነሳ ነው። ደማስቆ ባቀፈቻት ትልቋ የጀውዚያ መድረሳ ውስጥ ኢማም ሆነዋል። ያጠራቀሙትን እውቀት ለመርጨት ተነስተዋል። ለርሳቸው የዚህ ደረጃ መድረስ መዋጮ ያደረጉ ሊቃውንት እንዳሉ ሁሉ እሳቸውም ለሌሎች የልቅና ህይወት መዋጮ ማድረግ እንዳለባቸው ያመኑ ይመስላል። "በርካታ ሊቃውንቶች በርሱ ተጠቅመዋል። በበርካታ ስፍራዎችም ትምህርት ሰጥቷል።" ብለው ይመሰክራሉ ሓፊዝ አስሰኻዊ!
ፈትዋ በመስጠትና ድርሰቶችን በማዘጋጀት ማህበረሰቡን እያገለገሉ ቆይተው ነበር።
ስለ ሸይኹ ስነምግባር ለመክተብ ሳስብ የተማሪያቸው ኢማም ኢብኑ ከሲር ንግግር ፊትለፊቴ ድቅን ይላል፦ "በውብ ቂርአትና ስነምግባር የተሞላ ፣ እጅግ የሚወደደ ሰው ነበር። በማንም ላይ ምቀኝነትን አያንፀባርቅም፤ ችግርም አያደርስም። በማንም ላይ ጥላቻን(በቀልን) የማይሸከም ሰው ነበር።…… መልካምነትና ምግባረ ልዕልና በብዛት በርሱ ላይ ይስተዋላሉ።" ይላሉ ኢብኑ ከሲር (ወደ ማዋረስ በተጠጋ ትርጉም)! በዚህ ሰናይ ማንነት የተሸበረቁና በንፃተ ህሊና የተዋቡ በመሆናቸው የተነሳ ይመስላል ነገሮችን በውብ ስነምግባር ማከም ተገቢ እንደሆነ የሚመክሩን  «አንድ ሰው ወደ አንተ መጥፎ ፈፅሞ ሲያበቃ ከዚያም ለሰራው ጥፋት ይቅርታን ሊጠይቅ ከመጣ ባንተ ላይ መተናነስ ይቅርታውን መቀበል ያስገድድሃል።» ይላሉ ኢብኑ ቀይዪም!
ቸርነታቸው፣ ጀግንነታቸው፣ ታማኝነታቸው፣ ፍትሃዊነታቸው፣ ቁጥብነታቸው፣ ቻይነታቸው፣ ቃል አክባሪነታቸውና ለዱንያ እምባዛም አለመጨነቃቸው  በዘመኑ እኩያ ያልነበራቸው ያህል ያስመስል ነበር።
በዒባዳቸው እጅጉኑ ብርቱ፣ ከአላህ ጋር ያላቸውን ትስስር ለማሳመር ቀን ከሌት የሚተጉ ብርቅ የኢስላም ሊቅ!  ጥበብና አምልኮ በሚባሉ ሁለት ክንፎች የሚበሩ ድንቅ የኢስላም ጠቢብ!
ካበረከቷቸው መፅሓፍት ውስጥ
"ዛዱል መዓድ"፣ "መዳሪጁ አስሳሊኪን" ና "ኢዕላሙል ሙቂዒን"  ዝነኞቹ ሲሆኑ
"ሓዲዪል አርዋህ ኢላ ቢላዲል አፍራህ"
"ረውደቱል ሙሒብቢን"
"በዳኢዑል ፈዋኢድ"
"አስሰዋዒቁል ሙርሰላህ"
"ኢጋሰቱ አልለህፋን"
"አጥጢቡ አንነበዊይ"
"ኢጅቲማዑል ጁዩሽ አልኢስላሚያህ"
"አልካፊያህ አሽሻፊያህ"
"ጠሪቁል ሂጅረተይን" ና የመሳሰሉት ለአብነት ተጠቃሾች ናቸው።
መፅሃፍቶቹን ለማንበብ የታደለ ሰው በርግጥም አንባቢን መርታት የሚችሉና በድንቅ የብዕር ባለቤት የተከተቡ ስለመሆናቸው አይጠራጠርም።
ሸይኹ ላይ በደማቁ አሻራቸውን ካሳረፉ የኢስላም ሊቃውንት መካከል  ታላቁ የኢስላም ጠቢብና የጥበብ አባት ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ይገኙበታል።  ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ከግብፅ ወደ ደማስቆ ከተመለሱ በኋላ ከኢማም ቢን ቀይዪም አልጀውዚያ ጋር ተገናኝተው ነበር። ለ16 ዓመታት ከኢብኑ ተይሚያህ አጠገብ በመሆን የተለያዩ የእውቀት ዘርፎችን ቀሰመ።  ኢብኑ ተይሚያም አጠገቡ ያለውን ተማሪ ኢብኑ ቀይዪምን አስተዋለው። ትልቅ ምኞቱ እውቀትን በንቃት ሽቶ ኢስላምን ማገልገል እንደሆነ ስለተረዳም የብርቱዎችን ሙያ ያሰለጥነው፣ የጠንካራነትን ህልውና ያስተምረው፣ የእውነትን ሚስጥር ያስገነዝበውና ከልብ የመነጩ ምክሮችን ይለግሰው  ያዘ።  አማም ኢብኑል ቀይዪም "ሚፍታሑ ዳሪ አስሰዓዳህ" በተሰኘው ድርሳናቸው ላይ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ እያሉ ይመክሩኝ ነበር ብለው ያስቀምጣሉ።“ልቦናህን ለፍላጎቶችና ውዥንብሮች እንደ እስፖንጅ አታድርገው። እነርሱን መጥጦ ከነርሱ ውጪ የሚተፋው የለውምና! ነገር ግን እንደ ጠንካራ መስታወት አድርገው፦ውዥንብሩ ከላይ በኩል ያልፋል ወደ ውስጥ ግን አይዘልቅም። በጥራቱ አሳልፎ ያያቸዋል፤በጥንካሬውም ይቋቋማቸዋል። በአንተ ላይ የሚያልፉ ውዥንብሮችን ሁሉ ለልብህ የምታጠጣው ከሆነ ግን የውዥንብር መጠራቀሚያ ይሆናል።”

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

26 Oct, 06:02


ይህ ነው እንግዲህ፦

ነገ በጌታው ሚክደው!
ነገ የጌታውን ፀጋ ሚያስተባብለው!
ነገ በራሱ ሚኮፈሰው!
ነገ ሰዎችን ሚበድለው!
ነገ የቲምን ገፍትሮ ፣ ድሃን አዋርዶ የሚኖር!

{ﺃَﻭَﻟَﺎ ﻳَﺬْﻛُﺮُ ﺍﻟْﺈِﻧﺴَﺎﻥُ ﺃَﻧَّﺎ ﺧَﻠَﻘْﻨَﺎﻩُ ﻣِﻦ ﻗَﺒْﻞُ ﻭَﻟَﻢْ ﻳَﻚُ ﺷَﻴْﺊً } [ ﻣﺮﻳﻢ : 67]

." ሰው ከአሁን በፊት ምንም ነገር ያልነበረ ሲኾን እኛ የፈጠርነው መኾኑን አያስታውስምን?"
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

25 Oct, 14:20


ዱዓ አድርጉላቸው!
~ ~ ~
ኢብኑ ከሲር "አልቢዳያ ወንኒሃያህ" ላይ [14/640] ስለ አንድ በኢስላም ውስጥ ስለነበረ ታጋይ ሰው ያወራሉ። በአንዱ ዘመቻ ላይ አንዲትን የሮም እንስት ይመለከትና ያፈቅራታል። ከዚያ ለርሷ ብሎ ክ*ህደት ውስጥ ይወድቃል። በዚያን ወቅት ሙስሊሞች በጣም ተጨነቁ “አላህን ካወቀ በኋላ በሴት ምክንያት እንዴት ይ*ክዳል?” ብለው ሀሳብ ገባቸው። ከሆኑ ጊዜዎች በኋላ በዚያ በኩል ሲያልፉ ከርሷ ጋር ሆኖ አገኙት። “እገሌ ሆይ! ቁርአንህ እንዴት ሆነ?” ብለው ጠየቁት። “ሙሉ ቁርአኑን ረስቼዋለሁ። ከዚህ አንቀፅ በስተቀር
(رُّبَمَا يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُواْ لَوْ كَانُواْ مُسْلِمِينَ (2) ذَرْهُمْ يَأْكُلُواْ وَيَتَمَتَّعُواْ وَيُلْهِهِمُ الأَمَلُ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ)

“እነዚያ የካ*ዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ፡፡ ተዋቸው ይብሉ፤ ይጠቀሙም፡፡ ተስፋም ያዘናጋቸው፡፡ በእርግጥም (መጥፎ ፍጻሜያቸውን) ያውቃሉ፡፡”[አል ሒጅር 2–3]

ምን ተረዳሁ መሰላችሁ? በዚህ አንቀፅ ውስጥ ያለው ሀሳብ ምን ያህል ሰላም ቢነሳው ነው ያልረሳው? የኢስላምን ጥፍጥና ከቀመሱ በኋላ በጓደኝነት፣ በጥቅም፣ በቤተሰብ ጫናና መሰል በሆኑ ምክንያቶች የሚሄዱ ሰዎችን እዘኑላቸው። ምንም በፊታቸው ፈገግ ሊሉ ቢፈልጉም ኢስላም አይለቃቸውም። ወላሂ የሀቂቃ ሰላም አያገኙም። ብርሃንን ትተው ጨለማ ውስጥ መኖራቸው ያሳምማቸዋል ። ውስጣቸው በማይመለሱ የቁስል ጥያቄዎች ይሞላል። ለነዚህ ሰዎች የሚመለሱበትን ሰበብ እስከጥግ ከማድረስና ከማገዝ አልፎ ዱዓ ያስፈልጋቸዋል። አሁንም በህይወት እስካሉ ድረስ የገቡበት ስህተት መጨረሻቸው አይደለምና ዱዓ አድርጉላቸው። ቁጭቱ እንዳለ ሆኖ ማራገቡ ምንም ጥቅም የለውም።

ነብያችን ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ ዓለይሂ በተደጋጋሚ ከሚያደርጓቸው ዱዓዎች መካከል። “ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ጌታ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አፅናልኝ።” የሚል ነው።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

22 Oct, 03:28


ድንቅ እናት!

"እናቴ ቁርአን ያዝሀፈዘችኝ ገና የአስር አመት ልጅ ሆኜ ነው። ከፈጅር ሰላት በፊት  ትቀሰቅሰኝና በነዚያ የበግዳድ ብርዳማ ሌሊቶች ላይ የውዱዕ ውሃ ታሞቅልኝ ነበር። ልብሴን ታለብሰኝና በሂጃቧ ተሸፍና ወደ መስጂድ ይዛኝ ስትሄድ አስታውሳለሁ። ያኔ  ቤታችን ከመስጂድ ሩቅ ሲሆን ጎዳናው በፅልመት የተወረረ ነበር።"
ይላሉ ኢማሙ አህመድ ቢን ሀንበል!
·
·
«ከጀግና ወንድ አጠገበ  የሃላፊነት ስሜትን አስጨብጣ ቀርፃና ኮትኩታ ያሳደገችው ጀግና 'እናት' ወይንም ቁርጠኝነትንና ታታሪነትን እንዲላበስ ከጎኑ ሁና የምትገስፀው ብርቅ 'እህት' አልያም
ሁለመናዋን ለርሱ ችራ በፍቅር የምታበረታታውና የርሱን ስኬት ለማየት ቀን ከሌት የምትጓጓ ምርጥ 'ሚስት' መኖሯን ተገንዘብ!»
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

29 Sep, 11:19


ይ ዱቁር የተወደሰላቸው ኪታብ ነው።

አርረውዷህ፦
" እርሷ በነኚህ ከተሞች የመዝሀቡ ተከታዮች መደገፊያ ናት። እንዲያውም የመፅሃፏ ዝና አፅናፋትን አዳርሳለች።… ንቁ ተማሪ ወደርሷ ይጠጋል። ዳኛ በፍርዱ ላይ፣ ፈትዋ ሰጪም በፈትዋው ላይ ወደርሷ ይደገፋል። ይሄ ደግሞ የልበ ውሳኔን ማማርና የስራን ኢኽላስ
የሚጠቁም ነው።" ብሎ አወድሶላቸዋል ሸይኽ አል አዝረዒይ!
ሪያዱስሷሊሂን:
"በእውነቱ እርሱ በጣም አዋቂ ነው። አላህ ይወቅና በውጪው ሲታይ በድርሳን አዘገጃጀት ላይ በጣም ኢኽላስ አለው። ምክንያቱም መፅሃፍቶቹ በኢስላም የዓለም ክፍሎች ውስጥ ተሰራጭቷል። የትኛውም መስጂድ ላይ "ሪያዱ አስሷሊሂን" ሲቀራ ታገኛለህ። ድርሳኖቹ በዓለም ላይ መሰራጨታቸው የልበ ውሳኔውን ጥሩነት የሚያመላክት ነው። ሰዎች መፅሃፍቶችን (በሙሉ ልብ) መቀበላቸው በልበ ውሳኔ ኢኽላስ መኖሩን የሚጠቁም ነው።"ብለው ሸይኽ ቢን ዑሰይምን ምስክር ሰጥተዋቸዋል።
"አል ሚንሃጅ"
"አልኢዳሁ ፊል መናሲክ"
"ተስሂሁ አትተንቢህ"
"ሙኽተሰር አሰዱል ጋባህ"
"ቡስታኑል ዓሪፊን"
"ደቃኢቁ ሚንሃጂ ወርረውዷ"
"ሩኡሱል መሳኢል"
"ተህሪሩ አትተንቢህ"ና ሌሎችም ለአብነት የሚጠቀሱ መፅሃፍቶቻቸው ናቸው።

ሸይኹ በተለያዩ የእውቀት ዘርፎች ላይ በመሳተፍ አንበሳውን ድርሻ እንደወሰደ ግልፅ ነው። በሀዲስ፣ በፊቅህ፣ በዐረብኛ ሰዋሰው፣ በኡሱልል ዒልም ላይና በሌሎችም። ለዚህ የምጥቀት ማማ እንዲደርሱ ከኋላቸው የኮተኮቷቸው የኢስላም ሊቃውንቶች ነበሩ። "ሸይኽ አቡ ኡብራሂም ኢስሃቅ ቢን አህመድ፣ ሸይኽ አቡ ሙሀመድ ዐብዱርራህማን አቡ ሐፍስ ዑመር ቢን አስዐድ፣ ሸይኽ አቡል ሀሰን ሰልላም ቢን አል ሀሰን፣ ሸይኽ ኢብራሂም ቢን ዒሳ፣ ሸይኽ አቡል በቃእ ኻሊድ ቢን ዩሱፍ" ና ሌሎቹም ገናና ሊቃውንት ስር ተምረዋል።
ብዙ ተማሪዎችም ከርሳቸው የዒልም ማዐድ ተመግበው ወጥተዋል። ዑለማኦችና ሁፍፋዞች እንኳ ከርሳቸው የዒልም የወይን ብርጭቆ ጨልጠዋል። ድንቅ ሰው!

ህልፈት
በ676 ዓ·ሂ በወርሃ ረጀብ በ24ኛው ሌሊት በ45 ዓመታቸው በተወለዱባት ነዋ ከተማ ላይ ለማይንም የማይቀረውን የሞት ፅዋ ተጎነጩ። እዚያውም ተቀበሩ። ለኚህ ሸይኽ ሞት ደማስቆና አካባቢዋ በእንባ ወንዝ ተጥለቀለቁ። ሙስሊሞች በለቅሶ የሀዘን ብርድልብስን
ተከናነቡ።

ዝናቸው ሲነገር በሊቃውንት አንደበት፦
"አስተማሪዬ፣ አርአያዬ! የጠቃሚ መፅሃፍትና የምስጉን ድርሳናት ባለቤት የሆነ ኢማም! የዘመኑ ብቸኛ!" ተማሪው ሸይኽ ቢን አጥጣር

"አርአያነትን የተላበሰ መሪና ገናና ዛሂድ ነው። ጌታውን አምላኪና ፈሪሃ አላህ ሰው። የጊዜው ሸይኽ፣ የዘመኑ እንቁ፣ የሰዓቱ በረከት! በዲኑ፣ በስራው፣ በጥንቃቄውና በዙህዱ በዘመኑ አምሳያ አልነበረውም።" ሸይኽ ሷሪሙድዲን ኢብራሂም!

"የህዝበ ሙስሊሙ ሙፍቲ፤ ሸይኹል ኢስላም ፤ ንቁ ሸምዳጅ ፤ከሊቀ ሊቃውንት ውስጥ አንዱ!" አልኢማሙ አዝዘሐቢ!

እኔም ዛሬ ወጉ ደርሶኝ ስላንቱ የውዳሴ ንግግሬን ወረቀቴ ላይ ባሰፍር… " አንቱ ብርቅ የኢስላም ልጅ ነዎት። የሐዲስ እውቀትዎ እንደ ውቅያኖስ የጠለቀ፣ የፊቅህ ጥበቦ እንደ ጅረት ወንዝ የሚፈስ የነዋ ተወላጅ! በርግጥም ድንቅ የብዕርዎ ውጤት አንበርክኮኛል። ደማቅ
ታሪኮትም ልቤን ገዝቶኛል። ከጨረቃ ጋር ይመሳሰላሉ! ከዚያች ነዋ ተወልዳ ደማስቆ ከቆየች የዒልም ጨረቃ ጋር! እውነትም ደማስቆን ያበራ የነዋ ጨረቃ!"
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

29 Sep, 11:18


የነዋው ጨረቃ!
~   ~   ~
"አርአያነትን የተላበሰ መሪና ገናና ዛሂድ ነው። ጌታውን አምላኪና ፈሪሃ አላህ ሰው። የጊዜው ሸይኽ፣ የዘመኑ እንቁና የሰዓቱ በረከት! በዲኑ፣ በስራው፣ በጥንቃቄውና በዙህዱ በዘመኑ አምሳያ አልነበረውም።" ሲሉ ሸይኽ ሷሪሙድዲን ኢብራሂም ተደመውበታል።
እኔም ስደመም " የሐዲስ እውቀትዎ እንደ ውቅያኖስ የጠለቀ፣ የፊቅህ ጥበብዎ እንደ ጅረት ወንዝ የሚፈስ የነዋ ተወላጅ! በርግጥም ድንቅ የብዕርዎ ውጤት አንበርክኮኛል። ደማቅ ታሪክዎትም ልቤን ገዝቶኛል። አንዳንዴም ከጨረቃ ጋር ይመሳሰሉብኛል! ከዚያች ነዋ ተወልዳ ደማስቆ ከቆየች የዒልም ጨረቃ ጋር! እውነትም ደማስቆን ያበራ የነዋ ጨረቃ!"

"ሸይኽ የህያ ቢን ሸረፍ ቢን ሙርሪ አን-ነወዊ" ይባላሉ!
ሸይኹ በ631 ዓመተ ሂጅራ በወርሃ ሙሀረም ላይ መካከለኛ ምስራቅ በምትገኘው ምዕራበ እስያዋ "ሶሪያ" ምድር ውስጥ ተወለደ። የተወለደበት ከተማም ልዩ መጠሪያ "ነዋ" ይሰኛል። "ነወዊ" በሚለው ስም በስፋት ይታወቅ የነበረው ከመወለጃ ከተማው ጋር ተዛምዶ እንደሆነ ልብ ይሏል።

ወላጅ አባቱ ሸረፍ ቢን ሙርሪ "የተባረከ ሸይኽ" ተብሎ በደማቅ የውዳሴ ብእር የተፃፈለት ሰው ነበር። ከዚህ ቤተሰብ የፈለቀው ይህ ህፃን ከአባቱ የእንክብካቤ ለምለም መስክ እድገቱን አኖረ። አባትየው አላህ ሲሳዩን ያገራለት ሰው ሲሆን የሚሸጥበትና የሚገዛበት የግብይት ስፍራ (መደብ)ም ነበረው። እናም ነወዊ ሰላማዊና ችግር ያልተወለደበት ምቹ እድገት ላይ ሆኖ አሳለፈ።

ጌታው ከህፃንነቱ ጀምሮ ለህዝበ ሙስሊሙ ባለ አደራና የነብያት የእውቀት ድልብ ወራሽ አድርጎ የመረጠው ይመስላል። (የታሪክ ፀሃፊያን እንዳሰፈሩት) ልጁ ወደ 7 ዓመት ገደማ በደረሰበት ወቅት በረመዷን 27ኛው ሌሊት ላይ ከወላጅ አባቱ አጠገብ ተኝቶ ሳለ በሌሊቱ አጋማሽ አካባቢ ነቃና አባቱን ቀስቅሶ " አባዬ! ይህ ቤቱን
የሞላው ብርሃን ምንድነው?" ሲል ጠየቀው።ቤተሰቡ በሙሉ ነቃ ግን ምንም አልተመለከቱም ነበር። [አጥ-ጠበቃቱል ኩብራ 7/ 396] ለህፃኑ ነወዊ ብርሃን እንዴት ሊታየው ቻለ? ምስጢር አንግቦ ይሁን?

ህፃኑ አስር አመት ሲደርስ አባትየው በግብይት ስፍራ(መደብ) ላይ ቢያደርገውም በመግዛትና በመሸጥ ከቁርአን መዘናጋትና መጠመድ ልማዱ አልነበር። በርሱ እድሜ የሚገኙ ህፃናቶች ከነርሱ ጋር እንዲጫወት አይሹምና በብዛት ከአጠገባቸው እየሸሸ አይኑ በእንባ ሲርስ ይስተዋላል። የጓደኞቹ እርሱን ማራቅ ውስጡን ያሳምመዋል። በዚህ የሀዘን ዝናብ ልቡን በሚያጥለቀልቅበት ወቅት እንኳ የስኬቱን ምንጭ ሳይዘነጋ ቁርአንን ያነባል። ይህን ትዕይንት ያስተዋለው ሸይኽ ያሲን ቢን ዩሱፍ እንዲህ ይላል "በጣም ወደድኩት! የቁርአን አስተማሪው ዘንድ አቀናሁና "ይህ ልጅ የዘመኑ ሊቅ ይሆናል፤ ሰዎችም ከርሱ ይጠቀማሉ ተብሎ ተስፋ ይደረጋል።" አልኩት። እርሱም "አንተ ኮከብ ቆጣሪ ነህ እንዴ?"
አለኝ። እኔም "በፍፁም! በዚህ አላህ ነው ያናገረኝ።" አልኩት።"

ህፃኑም ለአቅመ አዳም የተቃረበ ሆኖ ቁርአንን ለማኽተም በቃ። በ649 [ዓ·ሂ] ወደ ደማስቆ ከተማ አቀና። ደማስቆ ደግሞ የዑለማኦች መሰብሰቢያ ና የጥበብ ፋና ወጊ መሆኗ ግልፅ ነው። በከዋክብት መሀል ጨረቃዋ ጎልቶ የሚታይ ብሩህ ከተማ ነበረች። የዚህን ከተማ የስልጣኔ ማዕከልነትና የጥበብ አብረቅራቂነት የሚጠቁም በታሪክ ፀሃፊው ኢብኑ ዐሳኪር የተፃፈ ድርሳን አለ። ለየትኛውም ሀገር ያልተፃፈው ታሪክ ለዚህች ከተማ ውብ በሆነ አቀራረብ 80 ቅፆችን ባቀፈ ወደል ድርሳን ተሰናድቶላታል።

ወጣቱም ደማስቆ እንደገባ ከአንድ ዓሊም ጋር ትስስሩን አጠናክሮ መቅራት ነበር የጀመረው። ከዑለማኦች ውስጥ የጃሚዑል ኡመዊይ መስጂድ ኢማምና ኸጢብ ከነበሩት ሸይኽ ጀማሉ አድዲን ዐብዱል ካፊ ጋር ተገናኘ። ሸይኹም ወጣቱ ለእውቀት ያለው ጉጉትና በዘርፉ መድረስ የሚሻውን ግብ ስለተገነዘበ ወደ ሻሙ ሙፍቲ ታጁዲን ዐብዱርራህማን የዒልም ክበብ አመላከተው። ወጣቱም የተለያዩ የእውቀት ዘርፎችን ተማረ። በጥልቀት መመራመርም የየእለት ስራው ሆነ። ጥበብ የቀመሰ ሌላ ጥበብ ፍለጋ ትጋትን ይላበሳልና ወጣቱ እንቅልፍን አሸንፎ በጥናት ሲቸክል ያድር ነበር "እንቅልፍ ሲያሸንፈኝ ለአፍታ ያህል ወደ መፅሃፍት እደገፍና እነቃ ነበር።" ይላል ወጣቱ!

በአቢ ኢስሓቅ የተከተበውን "አትተንቢህ" መፅሃፍ ሸምድዷል። በቀን ውስጥ በሊቃውንት መንደር 12 ዱሩሶችን ይቀራል። ቢያንስ ለእያንዳንዱ የእውቀት ዘርፍ ትምህርት 1 ሰዓት ያስፈልጋል። ለጥናት
ደግሞ ለእያንዳንዱ ትምህርት ሁለት ሁለት ሰዓት መሆኑ አስፈላጊ ነው። ታዲያ መቼ ነው የሚበላው? መቼ ነውስ የሚተኛው? መቼ ነውስ ሌሎች አምልኮቶችን የሚፈፅመው? አላህ የጊዜን በረካ ቢያዘንብለት እንጂ! በጥበብ ፍለጋና በእውቀት ዘማችነት የፀና ሰው በመሆኑ የተነሳ ደማስቆ ከወለደቻቸው ሊቀ ሊቃውንቶች ተርታ ተሰለፈ።

(ከአሁን በኋላ የኢስላም ሊቅ ሆኗልና በአንቱታ ልጥራው)
ሸይኹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝናቸው አፅናፋትን አካለለ። እውቅና ባላት "ኢቅባሊያ" መድረሳ ላይ ለአስተማሪነት ታጩ። "ዳሩል ሀዲስ አል አሽረፍያ" ላይ በሀዲስ ዘርፍ በሰነዱ (የቅብብሎሽ ሰንሰለቱም) ይሁን በመትኑ ጥልቅ እውቀት ስለነበራቸው በኃላፊነት አገልግለዋል። በሌሎች የፊቅሂና የሀዲስ ትምህርት ቤቶች ላይ ሰናይ መስመርን
ዘርግተዋል።

ስለ ስነምግባራቸው ልፅፍ ብዕሬን ከወረቀት ጋር ሳገናኘው የተማሪያቸው ኢብኑል ዐጥጣር ንግግር ይስበኛል" የተወዳጅ ባህሪና የምግባረ ልዕልና ባለቤት ነበር።" ይላል ኢብኑል ዐጥጣር!
በአምልኮ ላይ የነበራቸውው ትጋት በርካታዎችን ያስንቃል። "ቁርአንን በብዛት የሚያነብና ዚክር የሚያበዛ ሰው ነበር።" ይላል የዘመኑ ሰው።
ክብር እንዲቸራቸው፣ እንዲወደሱና የበላይነትን መቆናጠጥ አይፈልጉም። ቅፅል ስማቸው "ሙህዪ ዲን" ነበር። እሳቸው ግን በዚህ ቅፅል መጠራትን አልመረጡም። ትርጉሙ "ዲንን ህያው አድራጊ" ማለት ነው። ዲን ሁሌም ቋሚ ነው ማንም ህያው አድራጊ አያስፈልገውም ብለው ከማሰባቸው ጋር የመተናነስን ልዩ ባህሪ ማንገባቸው ነው።

ለዱንያ እምብዛም ደንታ የሌላቸው፣ ለአኼራ ከፍተኛ ትኩረት የሰጡና ሁሉም የህይወት ጉዞዋቸው አላህን በመፍራት የተሸበረቀ ነበር። የማያውቃቸው ሰው ቢመለከታቸው ደማስቆን ሊጎበኝ የመጣ የነዋ ገበሬ ሰው ነው ብሎ ያስብ ነበር። ከዘመኑ ሊቃውንት ተለይተዋል። የዝና ምልክት አይታይባቸውም። የሚበሉት በቀን አንዴ ነው የሚጠጡትም በሌሊቱ የመጨረሻ ክፍል ነው። "ከምግብ የዱንያን ጣዐም የተወ ሰው ነበር።" ይላል ሸምስ ቢን አልፈኽር!
ሸይኹ የጋብቻን ህይወት አላይዩም። ልቦናቸው አላህን በመፍራት፣ በዒባዳና በእውቀት የተሞሉ ስለሆነም ይመስላል የቅርቢቱ ዓለም ነገር ጭራሽ ትዝ ሲላቸው አይታዩም። "ለምን አታገቡም? " የሚል ጥያቄ ሲሰነዘርላቸው "ረሳሁትኝ!" ብለው ምላሽ ሲሰጡ ይስተዋላሉ። ባህታዊ ሆነው ሳይሆን ጥቅጥቅ ባለ የጥረት ደን ውስጥ የእውነትን ባህሪ ፈልቅቀው ለማወቅና ለመኖር ስለሚባትሉ ነበር።

ሸይኹ በህይወታቸው አሟልተው ያበረከቷቸው መፅሃፍት አሉ። ሳይጨርሱት ያለፉት መፅሃፍትም አሉ። "ሸርህ ሙስሊም"፣ "አርረውዷህ" ፣ "ሪያዱ ስሷሊሂን" ዝነኞቹ ናቸው።

ሸርህ ሙስሊም፦
"ሰዎች በሀዲስ ኪታብ ላይ ነወዊ ከተነተነው የሙስሊም ሰሂህ ኪታብ በላይ የተሟላ ፣ የጎላ ድርሻ ያለውና የመጠቀ ትንተናን አያውቁም።" ተብሎ በሸይኽ ዐብዱል ጘኒ

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

29 Sep, 11:10


"አንተ ሰው ሆይ!  ከጀሃነም ክፍል ውስጥ ሆነህ ራስህ አስበው። ዘወትር እያለቀስክ፣ በሮቹ ተከርችመውብህ፣  ጣሪያው ተጣብቆብህ፣ በፅልመት የተወረረ ጥቁር ዛውያ ውስጥ!"



ኢብኑል ጀውዚይ
«አል ሙድሂሽ [185]»

Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

28 Sep, 16:05


አምላካዊ ፍትህ!
«እንደ ስራህ ትመነዳለህ።»

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

28 Sep, 15:56


በጉድጓዱ ውስጥ ተጥሎ የነበረው ህፃን፣ ከቅፍለቶች የውሃ ማውጫ ባልዲ ጋር ተጎትቶ የወጣውና በርካሽ ገንዘብ የተሸጠው ልጅ…  ከጊዜ በኋላ የግብፅ ንጉስ ይሆናል ብሎ የገመተ ፍጡር አልነበረም። ግን እነዚህን ጨካኝ ጊዜዎች አልፎ የግብፅ ንጉስ ሆነ።
ልብ በል! በህይወትህ መፅሃፍ ውስጥ ጨካኝ ገፆች ቢኖሩም ለህይወትህ ውብ ገፆች መንደርደሪያ ወይም መግቢያ ሊሆኑ እንደሚችሉም አስብ!
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

27 Sep, 07:40


«ስጦታው ሊበዛ ሲል የመሆን ምኞትህ ይዘገይ ይሆናል!»
               ~ ~ ~
ዩሱፍ ወደ ወህኒ ሲገባ ከርሱ ጋር በተቀራራቢነት የታሰሩ ሁለት ወጣቶች ነበሩ።  ዩሱፍ እጅግ የነፃ ማንነት ያለውና ኃጢያት ያልፈፀመ ሆኖ ሳለ እርሱ በእስር ቤት ውስጥ እንዲቆይ ተደርጎ  እነዚያ ሁለት ወጣቶች ከርሱ በፊት ከእስር ተለቀቁ። እርሱ ግን ለተወሰኑ አመታት እስር ቤት ውስጥ ቆየ። የፈጣሪ ጥበብ ግን ይደንቃል። አንዱ ከእስር የወጣው አገልጋይ ሊሆን ሲሆን ሌላው ደግሞ በሞት ፍርድ ሊሰቀል ነበር። ዩሱፍ ደግሞ ከነርሱ መውጣት ከተወሰኑ አመታት በኋላ  የግብፅ ንጉስ ሊሆን ከእስር ተፈታ። የነገሮችን መዘግየት አትጥላ። ምናልባትም በመዘግየታቸው ውስጥ የተለዩ የህይወት ስጦታዎች ይኖራሉ።
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

27 Sep, 07:38


"አንዳንድ ትዕግስቶች ሌላ ትዕግስት ይፈልጋሉ። ለሁኔታዎች ታገስ። ለትዕግስትህም ታገስ!"

Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

26 Sep, 03:05


ንፁህ የህይወት መዝገብ ተሰጥቶሃል። አንተ ደግሞ ብዕር ነህ። በነፃው መዝገብህ ላይ
የፈለከውን ትፅፋለህ። መልካም ከፃፍክበት መልካም ምንዳ ይጠብቅኻል። መጥፎ
ከፃፍክበት ደግሞ ነፍስህን እንጂ ማንንም አትውቀስ።

Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

26 Sep, 02:55


ፊርዓውን በሺህ የሚቆጠሩ ህፃናትን አረደ። ዓላማው በርሱ ዘመን ሙሳ የሚባል ፍጡር እንዳይኖር ነበር። ግን በሚደንቅ ተዓምር ሙሳን በቤቱ አሳደገው።

“የአላህ ውሳኔ ተፈፃሚ ነው። አትጠራጠር!”

Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

25 Sep, 03:43



ከዚህም በተጨማሪ ታታሪነታቸው፣ አዛኝነታቸው፣ ቁም ነገረኝነታቸው፣ ጀግንነታቸውና የትላልቅ ስብዕና ባለቤት መሆናቸው ይታወቃል።
ዳዕዋዎቻቸውና ድርሳኖቻቸው ብዙ ጊዜ ትኩረታቸው ተውሂድ ላይ ነው። ሰዎች ከአላህ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማጠንከር እንደሚገባቸው አበክረው ያስተምራሉ።
"ቅድሚያ ለዐቂዳ! ምክንያቱም ዛሬ የኢስላማዊው ዓለም ውዝግብና ዝቅጠት መንስዔው ለጉዳዩ ተስማሚ የሆነ አስኳል መጥፋት ነው። እሱም ጥርት ያለው ዓቂዳ!" ይላሉ ገናናው ሸይኽ ፈውዛን!
  ከፃፏቸው ድርሳናት መካከል፦
"አትተህቂቃት አልመርዲያ" ማስተርስ በሰሩበት ወቅት በውርስ ክፍፍል ርዕስ ላይ የፃፉት ድርሳን ነው።
“ኢርሻድ ኢላ ሰሒሂል ኢዕቲቃድ"
"ሙለኸሰል ፊቅሂይ"
"አልበያን"
"ሸርሁል አቂደቲል ዋሲጢያ"
"አቂደቱ ተውሂድ"
"ሚን አዕላሚል ሙጀዲዲን"
"አደያኡ ላሚዕ" ና ሌሎችንም መፅሀፍት ለሙስሊሙ ህብረተሰብ አበርክተዋል።
ከተማሩባቸው ሸይኾች መካከል ሸይኽ ቢን ባዝ፣ ሸይኽ አብዱረዛቅ አል ዓፊፊ ፣ ሸይኽ ሙሀመድአሚን ሺንቂጢ፣ ሸይኽ አብደላህ ቢን ሁመይድ፣ ሸይኽ ሷሊህ ቢን ኢብራሂም ፣ ሸይኽ ሀሙድ ቢን አቅላን፣ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህና ሌሎችም ይገኛሉ።

ሊቃውንት ስለርሳቸው ዝና ሲናገሩ!
ሸይኽ ቢን ኡሰይሚን ታመው “ያ ሸይኽ ማን ቀድሞ እንደሚሞት  አይታወቅም። ከርስዎ በኋላ አላህ እድሜ ሰጥቶን ከቆየን   ማንን እንጠይቅ? ማነው የፊቅህ ሊቅ?”  ተብለው ሲጠየቁ
"ሸይኽ ሷሊህ አልፈውዛንን ጠይቁ። እርሱ እጅግ የላቀ ግንዛቤ  ያለው የፊቅህ ጠቢብና የዲን ባለቤት ነው።”   ታሪክ የማይረሳው የምስክርነት ቃል።
 
“ሸይኽ ፈውዛን ከምርጥ ሊቃውንት ውስጥ አንዱ ነው።” ሸይኽ ቢን ባዝ።
°
"እጅግ የበቁ ሊቅ ሸይኽ ሳሊህ ቢን ፈውዛን። የትልቆቻችን ታላቅ። በዓቂዳ፣ በመንሀጅና በፊቅሂ መመለሻ የሆኑ አዋቂ። የዘመኑ ምጡቅ ጠቢብ ፤ የሰለፎች ቅሪት።… በዚህ ዘመን ይህ ስም የሚገባቸው እሳቸው እንደሆኑ አምናለሁ።” ሸይኽ ሱለይማን አርሩሀይሊ

እኔም ልደመምና እንዲህ ልበል
“እርስዎ በዚህ ባይተዋር ዘመን የእውቀትን ችቦ ያበሩ ፣ በጣፋጭ አንደበትዎ ወደ ልከኛው መንገድ የሚጣሩ ታላቅ ባለውለታ ናችሁ። እውነትም  የሰለፎች ቅሪት። ሸማሲያ ተነስቶ ሪያድን አልፎ አለምን እያበራ ያለ ኮከብ ናችሁ።"
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

25 Sep, 03:41


የሸማሲያው ተራራ፣ የሪያዱ ችካል!
         ~ ~ ~
"የ
ዘመኑ ምጡቅ ጠቢብ ፤ የሰለፎች ቅሪት።… በዚህ ዘመን ይህ ስም የሚገባቸው እሳቸው እንደሆኑ አምናለሁ።” ሸይኽ ሱለይማን አርሩሀይሊ
|
ሸይኽ ሷሊህ ቢን ፈውዛን ቢን ዓብደላህ አል ፈውዛን ይባላሉ።
ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን በ1354 በወርሃ ረጀብ 1ኛው ቀን በመካከለኛዋ ምስራቅ ሱዑዲያ ምድር  ቀሲም ክልል ውስጥ ተወለደ። የተወለደበት ከተማ ልዩ ስሟ "ሸማሲያ" ትሰኛለች። የዚህች ስፍራ የዕፅዋት ልምላሜ ውበት የብዙዎችን አይን ያረካል። ሙቀት ከሚለኩሰው ጠራራ ፀሀይ ጋር  በአረንጓዴ ቀለም ገፅታዋን ያሳመረች ስፍራ መመልከት ለነዋሪዎቹ ከምስጢር  አዘልነቱ አልፎ ተዓምር አለው። በተለይ የተምር ዛፎችና የስንዴ አዝርዕቶች። ፈውዛን  የልጅነት ህይወቱን ከአብሯ አደጎቹ ጋር  በዚህች ሞቃታማ ስፍራ የመስክ ስጋጃ ላይ ፋንኗል።  ከጓደኞቹ ጋር አቧራ ላይ እየተዘረገፉ መጫወት፣ በንፁህ አየር ውስጥ እየተሯሯጡ  መፈንደቅ ለፈውዛን ደስታን የሚያጭር ነገር ቢሆንም ሮጦ ሳይጠግብ ወላጅ አባቱ ዱንያን መሰናበቱ እጅግ ያሳዝነዋል። በጨዋታ መሀል እንደፊተኛው ያልሆነ፣ በረዶ የተቀላቀለበት ቀዝቃዛ ፈገግታ ይከተለዋል። አብሯ አደጎቹም በግርምት ይመለከቱታል።  ምን እያስታወሰ ይሆን? 

በዚያች ሰፈር  ጥላ ስር  አንዲት መስጂድ አለች። ፈውዛን ከሚኖርበት ቤተሰብ  ቤት እምብዛም አይርቅም። በመስጂዱ  ቅጥር ውስጥ ዘወትር የማይጠፉ፣ ነጫጭ ፀጉሮች አናታቸውና ፂማቸው ላይ የተነሰነሰባቸው  ኢማም አሉ። ሸይኽ ሀሙድ ቢን ሱለይማን አት-ተላል ይባላሉ። ህፃናትን ሰብስበው ቁርአን ያቀራሉ።በተለያዩ ግሳፄያቸውም ትውልድ ይቀርፃሉ። በትጋታቸው ብዙዎች ያወሷቸዋል። ከእናቶቻቸው የተወለዱ ልጆችን በቁርአን አስተምህሮ ደግመው ይወልዷቸው ነበር። ፈውዛንም እዚያ መስጂድ ውስጥ ተሰብስበው ቁርአን ከሚቀሩት ልጆች ውስጥ አንዱ ነበር። ስለኚህ ሸይኽ፣  ፈውዛን ታላቅ ሰው ከሆነ በኋላ “እጅግ የመጠቁ ሃፊዝ ፣  ድምፀ መረዋ ነበሩ።” ብሎ መስክሯል።

ያለመምህር የበቀለ ትልቅ ስብዕና የለምና ፈውዛን ከልጅነቱ ጀምሮ የህይወቱን ዓላማ በማሳወቅ የኮተኮቱት ሰዎች አሉ። እነዚህ መምህሮች  በፈውዛን ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታ አላቸው። ባለውለታነታቸውንም አይረሳውምና በሀሳቡ ብቻ ሳይሆን ከአንደበቱ ደጅ ፣ ከብዕሩ ጠብታ አይጠፉም።  በአስራዎቹ እድሜ ላይ ሸማሲያ ላይ የተከፈተ ትምህርት ቤት ውስጥ ገብቶ ተማረና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ቡረይዳ በምትገኘው  "ፈይሰልያ" ትምህርት ቤት ውስጥ አጠናቀቀ። በፈውዛን የዒልም ቆይታ ሸይኽ ኢብራሂም ቢን ደይፈላህ ለመነሻ እውቀቶች ትልቅ አስዋፅኦ ነበረው። "ስርዓተ ትምህርቱ ያፀደቀው ብቻ ላይ ሳይገደብ ለተማሪዎቹ በዓቂዳም በፊቅሂም በርካታ ጠቃሚ እውቀቶችን ያስተምር ነበር። በርሱ ብዙ መልካም ነገሮች ተገኝቷል። የእውቀት በሮችን ከፍቶልን አነሳስቶናል። አላህ መልካሙን ይመንዳው።" ይላል የትናንቱ ደረሳ የዛሬው ሊቅ ፈውዛን። 

ታጋይነቱ ለእውቀት ካለው ጉጉት ያስታውቃል። ቅሌን ጨርቄን ማለት አልለመደበትም። በቂርአት ጉዞው ለአፉ ምክንያት፣ ለእግሩም እንቅፋት አላደረገም። ሊቃውንት ያሉበትን ደጃፍ ያንኳኳል። ተቀምጦ ብዙ ይቀራል፣ ያዳምጣል። ዛሬ ትልቅ ሰው ሆኖ “እውቀት ፈላጊዎች  እጅግ እንዲጠነክሩና እንዲታገሉ እመክራለሁ” ይላል እውቀት በሚፈስበት አንደበቱ።  ለእውቀት የተነሳ ሰው ዝለት ሊጠናበትም ይሁን ጉልበቱ ሊብረከረክበት አይገባም። 

ቡረይዳ ከተማ  ላይ የዒልም ማዕከል ተከፍቶ እነ ሸይኽ አብዱረዛቅ አልዐፊፊና ሸይኽ ሳሊህ ቢን አብዱራህማን ሲያስተምሩ  ፈውዛን ግንባር ቀደም ተማሪ ነበር። የተለያዩ የፊቅሂ፣ የዐቂዳ፣ የኡሱልና ሌሎችም ዘርፎች ላይ በጥልቀት በበቁ ምሁራን ይሰጥ ስለነበር የእውቀት ጥማቱ ዕለት ዕለት አዲስ ነው።  በትኩስ ወጣት መንፈስ የታጠቀውን ወኔ በጥበብ ላይ እንጂ በሌላ ተራ ነገር ላይ ማድረግ አልፈለገም። በማዕከሉ ከሚሰጠው የሸሪዓ ስርዓተ ትምህርት በተጨማሪ ሸይኽ አብዱላህ ቢን ሁመይድ በሚያስተምሩበት የእውቀት ማዐድ ላይ ተድጦ ከሸይኽ አብዱላህ ቢን ሁመይድ አንደበት የሚርከፈከፉ ጥበብ ያዘላቸው ደርሶችን በማዳመጥ ይማራል። ለዚህ ደግሞ  ቆራጥነት ያስፈልጋል።   “በእውቀት ማዕከሎች ውስጥ ብዙ ጓደኞች ነበሩኝ። አብዛኞቹ በተለያዩ ምክንያቶች አቋርጠዋል። ከፊሉ በሲሳይ ፍለጋ ፣ ከፊሉ በሌላ ምክንያት አቋርጠዋል። አብረውኝ የቆዩ እምብዛም ናቸው።” ይላል ይህ ትልቅ ሰው።

ፈውዛን ቡረይዳ ከተማ ከሚገኘው “መዕሀድ አል-ዒልሚይ” በ1377 ዓ·ሂ ተመርቆ ከወጣ በኋላ ወደ "ሪያድ" ከተማ አቀና። ሪያድ ላይ "ኩሊየተ ሸሪዓ" (የሸሪዓ ኮሌጅ) ውስጥ ገብቶ በሸይኽ ቢን ባዝ፣ በሸይኽ ሙሀመድ አሚን አሺንቂጢና  በትላልቅ ሊቃውንት የመማር እድሉን አገኘ። ከሸሪዓው ኮሌጅ ውስጥ የሚመረቁበት የመጨረሻው አመት ላይ የፈውዛንን ብቃትና የእውቀት ጥማት የተመለከቱት ሀላፊዎች የነህውና የሌሎች ዘርፎች አስተማሪ እንዲሆን አደረጉት። ፈውዛን በፊቅሂ ዘርፍ የማስተርስ አልፎም የዶክተርነትን ደረጃ ተጎናፀፈ። ከዚያም በተማሪዎቹ የተከበረ ፣ በዒልሙ ከፍታ ቁንጮ ካሉት በክብር የሚሰለፍና በሚያገለግለው ማህበረሰብ ዘንድ ግርማው የላቀ ሊቅ ሆነ።( ሊቅ ሆነዋልና በክብር ልጥራቸው)

ሸይኽ ፈውዛን በተለያዩ ኮሌጆችና የእውቀት ማዕከሎች ላይ በተማሪነት ህይወታቸው የሰበሰቡትን ጥበቦች መስጂድ ለታዳሚው ያስጨብጣሉ።መስጂድ ውስጥ ማስተማር ከጀመሩ ከ35  ዓመት በላይ ሆኗቸዋል። በሸሪዓ ኮሌጅ ላይ፣ ኡሱሉ ዲን ኮሌጅ ላይ መዕሃድ አልዒልሚ ላይ በአስተማሪነት ታጭተው አስተምረዋል። መዕሀድ አል-ዓሊ ላይ ሃላፊ ተደርገውም ተሹመው ነበር። የሳውዲ ቋሚ የፈትዋ ሰጭ ኮሚቴ አባልም  ናቸው።
  。
ሲያስተምሩ ስክነታቸው ለጉድ ነው። የአቀራረብ ስልታቸው እጅግ ይማርካል። ስርዓቱን ጠብቆ እንደበጋ የወንዝ ጅረት ፈሰስ ይላል። ያለማጋነን ከአንደበታቸው ማር ይዘንባል። ያውም ለስለስ ያለ ማር።
መተናነሳቸውን የማይወድላቸው ሰው የለም። እንደ ጭስ በባዶነት የሚንጠራሩ ተራ የዘመናችን ሰው እንዳይመስሉህ። እጅግ በጣም አዋቂ ቢሆኑም "እውቀቴ ትንሽ ነው። ደካማ ነኝ" የሚል ቃል ከአንደበታቸውም ይሁን ከብዕራቸው ሰፈር አታጣም።  በአንድ መድረክ ላይ ለርሳቸው ቃለ መጠይቅ የሚያደርገው ሰው “የዛሬው እንግዳችን ከኡማው ጠቢቦች አንዱ የሆኑት ፣ ሁሌም የሚሰጧቸውን ትምህርት ለማድመጥ የምትጠባበቋቸው ትልቅ ሰው! በፊቅህ ብትሉ ፣ በአቂዳ ብትሉ ፣ በተፍሲር ብትሉ ልዩ ሊቅ ናቸው።…”   እያለ ካወደሳቸው በኋላ  "ያልደረስኩበት ደረጃ ላይ ስለሰቀላችሁኝ  እጅግ አሳፍራችሁኛል (ሀፍረት ተሰምቶኛል)። እኔኮ  ልክ እንደናንተ አንድ እውቀት ፈላጊ እንጂ ሌላ አይደለሁም። ምናልባትም ከናንተ ውስጥ እጅግ የላቀና የተከበረ ሰው ሊኖር ይችላል።”  ብለው የመተናነስን ትርጉም በተግባር ያስተማሩን ሸይኽ ናቸው።

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

25 Sep, 03:39


“ራስህን በግራ መጋባት መንፈስ ውስጥ ስታገኘው ኢስቲግፋር አድርግ። አላህ በኢስቲግፋር  የተደበቀን ይገልጣል፣ የተዘጋንም ይከፍታል።”

ሸይኽ ቢን ዑሰይሚን
Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

23 Sep, 07:45


''ኒቃብ ለብሳ መጥፎ የምትሰራ አውቃለሁ'' ካሉህ" ሙናፊቅ ሆኖ ከነብዩ ጀርባ ሶፈል አወል የሚሰግድ ሰው አውቃለሁ" በላቸው። ኒቃብ ስለለበሰች ወይም ፂሙን ስላሳደገ ብቻ ፍፁም እንዲሆኑ መጠበቅ አላዋቂነት ነው!!

Te» @abdu_rheman_aman
Te» @abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

23 Sep, 07:39


አንድ ሌባ እጁን ሊያስቆርጠው የሚያስፈርድ ስርቆት ሰርቆ የምእመናን መሪ ዑመር ቢን ኸጧብ ዘንድ ቀረበና ዑመርም እጁ እንዲቆረጥ አዘዙ።
ከዛም:—
ﻓﻘﺎﻝ : ﻣﻬﻼ ﻳﺎ ﺃﻣﻴﺮ ﺍﻟﻤﺆﻣﻨﻴﻦ، ﻓﺈﻧﻤﺎ ﺳﺮﻗﺖ ﺑﻘﺪﺭ ﺍﻟﻠﻪ
" አንተ የምእመናን መሪ ሆይ! ቆየኝ እስቲ አንዴ! እኔኮ የሰረቅኩት በአላህ ቀደር( ውሳኔ) ነው።" አለ
ዑመርም:
ﻓﻘﺎﻝ : ﻭﻧﺤﻦ ﺇﻧﻤﺎ
ﻧﻘﻄﻊ ﺑﻘﺪﺭ ﺍﻟﻠﻪ
« እኛም (እጅህን) ምንቆርጠው በአላህ ፍቃድ ውሳኔ ነው።» አሉት ይባላል።》
ምንጭ:–{ ሸርህ ኡሱል አል-ኢማን :57)
t.me/abdu_rheman_aman

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

22 Sep, 09:18


በሜካፕሽማ…
ልክ እንደኔ ሁሉ ማን ነዉ ያልታለለ
የበላሽ ቡዳ እንኳ፣
በነጋታዉ አይቶሽ ሲያስመልሰዉ ዋለ።
t.me/abdu_rheman_aman

4,397

subscribers

269

photos

159

videos