ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር @ibnugarad Channel on Telegram

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

@ibnugarad


يا مقلب القلوب
ثبت قلبي على دينك

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር (Amharic)

እናቴ በማህበረሰብ የተጻፈበት አምስት ቀናት ሰዓት ላይ ለተመዘገበ ተግባር እና መረጃ ከሚፈልጉት የህግ ዜናዎችን የምንከፍሉትን ዝግጅት በቀላሉ አስቦ እንዲሰጥ ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር በቀጥታ እንደሚጠቀሙ መረጃዎችን እና ቀናት ሰዓቱን በውጤቶች ለመታወቅ መጨረሻ አስተካክሉ። ከእንግሊዝ ናቸው ነገር ግን ከእርስዎ ጋር የምትከሰቱ የቴሌግራም መረጃዎችን ፈልጋላችሁ። ሌላ ቀናት ሰዓት ላይ በማህበረሰብ የተጻፈበት መነሻ ቢኖረኝ ማሰማጨኝ ነበር።

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

04 Jan, 04:09


የሞተውን ለምንድነው የሚከፋፈሉት?

““የአንድ ሰው በሬ የሌላውን ሰው በሬ ወግቶ ቢገድለው፣ በሕይወት ያለውን በሬ ሽጠው ገንዘቡንና የሞተውን እንስሳ እኩል ይካፈሉ።”
— ዘጸአት 21፥35 (አዲሱ መ.ት)

https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

03 Jan, 03:55


የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርዓቶች 
————— 
Sunnahs and rituals of Friday

1  ገላን መታጠብ
     

2  በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ


3  በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ  አ      
        አለመረማመድ(መስጂድ ውሰጥ )


  4  ሱረቱል ከህፍን መቅራት
 

5     ዱዓ ማብዛት


6 በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት 

اللَّهُمَّ صَلٌِ عَلَى مُحَمَّدٍ وَّ عَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ

اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَّ عَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد

7 ሽቶ መቀባት (ለወንዶች )

      

https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

19 Dec, 03:19


አሪፍ ጅማሮ ነው።
መበረታታት ያለበት

https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

13 Dec, 05:40


የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርዓቶች 
————— 
Sunnahs and rituals of Friday

1  ገላን መታጠብ
     

2  በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ


3  በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ  አ      
        አለመረማመድ(መስጂድ ውሰጥ )


  4  ሱረቱል ከህፍን መቅራት
 

5     ዱዓ ማብዛት


6 በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት 

اللَّهُمَّ صَلٌِ عَلَى مُحَمَّدٍ وَّ عَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ

اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَّ عَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد

7 ሽቶ መቀባት (ለወንዶች )

      

https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

04 Dec, 20:07


ታላቅ የሙሀደራ ግብዣ በጀብዱ ቀበሌ
በጣም አጓጊ እና ልዩ የሆነ የዳዕዋ ዝግጅት

ተጋባዥ  ኡስታዞቻችን

1ኛ ውዱ ና ተናፋቂው  ኡስታዛችን አቡ አብዱረህማን አብዱልቃድር ሐሰን ከአዳማ

2ኛ ኡስታዝ አብዱልቃድር ከድድላ

3ኛ ኡስታዝ ከድር ከአዳማ

ሌሎችም ኡስታዞች ይኖራሉ ኢንሻአላህ

የፊታችን ጁምዐ በቀን 27/03/2017

ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ

ቦታ በቀቤና ወረዳ ጀብዱ ቀበሌ ስለዚህ በ4ቱም አቅጣጫ የምትገኙ ቀበሌዎች ተጋብዛቹሀል

ስለዚህ አይደለም መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል
ከተማ ያላቹህ ወንድም እና እህቶች ቤተሰቦቻችንን በስልክ በመቀስቀስ እንረባረብ
ኢንሻአላህ ተውሂድ የበላይ የሚሆንበትና ሽርክና የሽርክ ባልተቤቶች የሚደመሰሱበት ቀን ይሆናል ኢንሻአሏህ በአሏህ ፍቃድ

ጁምዓ ለጀብዱ ልዩ ቀን ናት

https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

28 Nov, 09:58


ነጥብ አራት
"አምላኩ" 
ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ለማሳየት "አምላኩ" በማለት በሶስተኛ መደብ ተናግረዋል፦
ራእይ 1:6 መንግሥትም ""ለአምላኩ"" እና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥
ሚክያስ 5:4፤ እርሱም ይቆማል፥ በእግዚአብሔርም ኃይል ""በአምላኩ"" በእግዚአብሔር ስም ግርማ መንጋውን ይጠብቃል፤ እነርሱም ይኖራሉ፤ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናልና።

በተጨማሪም "የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ" በማለት ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ተናግረዋል፦
ኤፌሶን 1:17 የክብር አባት የጌታችን ""የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ"" እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።
2ኛ ቆሮንጦስ1:3 የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።
2ኛ ቆሮንጦስ 11:31 ለዘላለም የተባረከ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት እንዳልዋሽ ያውቃል።

መደምደሚያ
ኢየሱስ በንግግሩ እራሱን ሁለተኛው የአንዱ አምላክ አባል አድርጎ አስተምሮ አያውቅም። ከዚያ ይልቅ እራሱ ከአንዱ አምላክ ውጪ ያደርግ ነበር፦
ማርቆስ 10:18 ኢየሱስም። ስለ ምን ቸር እኔን ትለኛለህ? ከአንዱ አምላክ በቀር ቸር ማንም የለም።Why callest you me good? there is none good but one, that is , God.
ዮሐንስ 17፥3 እውነተኛ አምላክ ብቻህን የሆንህ አንተን እና የላከውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህቺ የዘላለም ህይወት ናት። (1980 አዲስ ትርጉም) 
ዮሐንስ 14:1 ልባችሁ አይታወክ፤ በአምላክ Θεοῦ እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።
ዮሐ7፥16-17 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ*myself አይደለም፤ ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከአምላክ Θεοῦ ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ*myself የምናገር ብሆን ያውቃል።

አንዳንድ ቂሎች "ኢየሱስ አምላክ አለው ግን ለስጋው ነው" ይሉናል፤ ስጋው ፍጡር እና የራሱ ማንነት ከሆነ በስጋው የሚያመልከው አምላክ ካለው ኢየሱስ አምላኪም ተመላኪም ከሆነ ሁለት አይሆንም ወይ? ሲቀጥል "ስጋ" ብቻውን "እኔ" ይላል ወይ? የሰው ሁለተንተና መንፈሱ፣ ነፍሱ እና ስጋው ናቸው፦
1ኛ ተሰሎንቄ 5:23 የሰላምም አምላክ ራሱ ""ሁለንተናችሁን"" ይቀድስ፤ "መንፈሳችሁም፣ ነፍሳችሁም፣ ፣ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።"

ኢየሱስ የራሱ መንፈስ ካለው፣ የራሱን መንፈስ ለአንዱ አምላክ ከሰጠ የራሱ መንፈስ ከአንዱ አምላክ ይለያል፦
ዮሐንስ13:21 ኢየሱስ ይህን ብሎ "በመንፈሱ" ታወከ መስክሮም።
ሉቃስ 23:46 ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ። አባት ሆይ፥ "መንፈሴን" በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ "መንፈሱን" ሰጠ። NIV

አንዱ አምላክ ደግሞ የመንፈስ ሁሉ አምላክ ከሆነ አንዱ አምላክ የኢየሱስ ሁለንተና አምላክ ነው፦
ዘኊልቅ 16:22 እነርሱም በግምባራቸው ወድቀው። አምላክ ሆይ፥ አንተ የሰው ሁሉ መንፈስ አምላክ(the God of the spirits of all flesh,)፥ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ አንተ በማኅበሩ ሁሉ ላይ ትቈጣለህን? አሉ።
ዘኊልቅ 27:16፤17፤ የእግዚአብሔር ማኅበር እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን፥ በፊታቸው የሚወጣውን በፊታቸውም የሚገባውን የሚያስወጣቸውንም የሚያስገባቸውንም ሰው የሥጋ ሁሉ መንፈስ አምላክ (the God of the spirits of all flesh) እግዚአብሔር በማኅበሩ ላይ ይሹመው።

ስለዚህ አንዱ ኣምላክ አምላክነቱ ለመንፈሱም ጭምር ከሆነ እና ባይብል ላይ 17 ቦታ ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ከተገለፀ እውነትም ኢየሱስ አምላኪ ፍጡር ነው፤ በእውነት ሊመለክ የሚገባው የኢየሱስ አምላክ ብቻ ነው። አምላካችን አላህም ኢየሱስ ተናገር ብሎ ያዘዘው ቃል "ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ" ማለትን ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል "ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ" ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

በኡስታዝ ወሒድ ተፃፈ
https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

27 Nov, 15:38


የኢየሱስ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡

14፥52 ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት፣ የአዕምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው፡፡ هَذَا بَلَاغٌ لِلنَّاسِ وَلِيُنْذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ " سورة إبراهيم

መግቢያ
ቁርኣን ከወረደበት ምክንያት አንዱ የአዕምሮ ባለቤቶችም አላህ አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት ነው፦
14፥52 ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት፣ የአዕምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው፡፡ هَذَا بَلَاغٌ لِلنَّاسِ وَلِيُنْذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ " سورة إبراهيم

ነገር ግን ይህንን አንድ አምላክ አንዴ በማንነት ሶስት ነው፣ አንዴ ሰው ሆነ፣ አንዴ ለሰው ኀጢአት ሞተ እያሉ በነውርና በጎዶሎ ባህርይ ያሻርኩታል፤ ይህ አንድ አምላክ በመለኮታዊ ቅሪት ሲናገር እንዲህ ይላል፦
ሆሴዕ 11፥9 እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥
ኢሳይያስ 44:6 ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።

አንዱ አምላክ እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁም፣ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም እያለን ተመልሰው ሰውም አምላክ ነህ ማለት ከአምላክ ይልቅ ፍጡራን ስለ አምላክ መገለጥ አለን ብለው መደምደም ነው፤ ነገር ግን ኢየሱስ በአንዱ አምላክ እና በሰዎች መካከል መካከለኛ ሆኖ ከአምላክ ሰምቶ የሚናገር ሰው ነው፤ በድንቆች በምልክቶችም ከአንዱ አምላክ ዘንድ ለእስራኤል ሰዎች የተላከ ሰው ነበረ፦
1ኛ ጢሞቴዎስ 2:5 አንድ አምላክ Θεοῦ አለና፥ በአምላክ Θεοῦ እና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም *ሰው* የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን ከአምላክ Θεοῦ የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤
የሐዋርያት ሥራ 2:22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ አምላክ Θεοῦ በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከአምላክ Θεοῦ ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤

እንግዲህ ኢየሱስ ሰው ከሆነ እና አንዱ አምላክ የላከው ከሆነ ሰው የሆነው ኢየሱስ እና አንዱ አምላክ ሁለት የተለያዩ ማንነት እና ምንነት ናቸው ማለት ነው፤ ኢየሱስ የሚያመልከው የራሱ አምላክ አለው፦

ነጥብ አንድ
"አምላኬ" 
"አምላኬ" ማለት "የእኔ" አምላክ ማለት ነው፤ "አምላኬ" በሚል የመጀመሪያ መደብ "እኔ" የሚል አገናዛቢ ተውላጠ ስም አለ፤ "የእኔ አምላክ"my God" የሚለው የኢየሱስ ሙሉ እኔነት አምላክ አለው፦
ማቴዎስ 27:46 በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፡- ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም፡- የእኔ አምላክ የእኔ አምላክ ፥ አንተ እኔን ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው። ""My God, my God, why have you forsaken me"".
ዮሐንስ 20:17 ኢየሱስም። ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ። እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ "አምላኬ" እና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።

በተለይ ኢየሱስ አንዱን አምላክ "አንተ" እራሱን ደግሞ "እኔ" በማለት "አምላኬ" ማለቱ ሰው የሆነው ኢየሱስ እና አንዱ አምላክ ሁለት ህልውናዎች መሆናቸው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ "ተውከኝ" ስላለም በተወው ባለቤት እና በተተው ተሳቢ መካከል "ተውከኝ" የሚል ተሻጋሪ ግስ"transitive verb" መኖሩ ኢየሱስን ከአምላኩ ይለየዋል፤ በተጨማሪም "ወደ" የሚለው መስተዋድድ*preposition* መጠቀሙ በሁለት ማንነት መካከል ለመለየት የሚመጣ ነው፣ ኢየሱስ ማርያምን *ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ* ማለቱ ወንድሞቹና ማርያም የተለያየ ማንነት እንዳላቸው እንደሚያሳይ ሁሉ "ወደ አምላኬ አርጋለው" ማለቱ አምላኩና ኢየሱስ ሁለት የተለያዩ ህላዌዎች መሆናቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል።

ነጥብ ሁለት
"አምላካችን"
ኢየሱስ "ወደ አምላኬ እና ወደ አምላካችሁ" አለ እንጂ "ወደ አምላካችን" ስላላለ አንዱ አምላክ ለኢየሱስ አምላክ የሆነበትና ለሃዋርያት አምላክ የሆነበት መደብ ይለያያል ይላሉ፤ ይህ ውሃ የማያነሳ ሙግት ነው፤ አንደኛ ይህ አነጋገር የተለመደ ነው፦
ዘፍጥረት 43፥23 እርሱም አላቸው፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ አትፍሩ፤ *አምላካችሁ እና የአባታችሁ አምላክ* በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ፤ ብራችሁስ ደርሶኛል።

"አምላካችሁ እና የአባታችሁ አምላክ" ስለተባለ አንዱ አምላክ ለአባታቸው ለያእቆብ እና ለልጆቹ አምላክነቱ ይለያያልን? ሁለተኛ ኢየሱስ "አምላካችን" በሚል አንደኛ መደብ ብዜት ተናግሯል፦
ኢሳይያስ61:1-2 የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል። የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት ""አምላካችንም"" የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ ልኮኛል፤ 
ማርቆስ 12:29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ ""አምላካችን"" አንድ ጌታ ነው፥

ነጥብ ሶስት
"አምላክህ"
መዝሙረኛ እግዚአብሔር ለኢየሱስ አምላክ መሆኑን ለማሳየት " አምላክህ" በማለት በሁለተኛ መደብ ተናግሯል፦
መዝሙር 45:7 ጽድቅን ወደድህ ዓመፃንም ጠላህ፤ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር "አምላክህ" የደስታ ዘይትን ቀባህ።
ዕብራውያን 1:9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር "አምላክህ" ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ።

ለኢየሱስ ባለንጀሮቹ ሲቀቡ የነበሩት ነብያት ናቸው፤ ክርስቶስ ማለት "የተቀባ" ማለት ሲሆን አምላኩ እግዚአብሔር ኢየሱስን የደስታ ዘይት በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ቀብቶታል፤ ቀቢው አንዱ አምላክ ከሆነ ተቀቢው ሰው ብቻ ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 10:38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና

ከኡስታዝ ወሒድ

ክ_2 ይቀጥላል...

https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

22 Nov, 04:07


የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርዓቶች 
————— 
Sunnahs and rituals of Friday

1  ገላን መታጠብ
     

2  በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ


3  በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ  አ      
        አለመረማመድ(መስጂድ ውሰጥ )


  4  ሱረቱል ከህፍን መቅራት
 

5     ዱዓ ማብዛት


6 በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት 

اللَّهُمَّ صَلٌِ عَلَى مُحَمَّدٍ وَّ عَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ

اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَّ عَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد

7 ሽቶ መቀባት (ለወንዶች )

      

https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

21 Nov, 18:33


ጥያቄ?

ለክርስትያኖች

ዘፍጥረት 6 (Genesis)
3፤ እግዚአብሔርም፡— መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፥ እርሱ ሥጋ ነውና፤ ዘመኖቹም መቶ ሀያ ዓመት ይሆናሉ፡ አለ።

በሌላ ቦታ ደግሞ

ዘፍጥረት 25 (Genesis)
7፤ አብርሃምም የኖረበት የዕድሜው ዓመታት እነዚህ ናቸው፤ መቶ ሰባ አምስት ዓመት ኖረ።


ጥያቄያችን?

እግዚአብሔር ሰው ምድር ላይ ስኖር ከ120 እድሜ በላይ መኖር እንደ ማይችል ከተናገረ በኋለ

እንዴት አብረሐም 175 አመት ልኖር ቻለ?

@hadiyya_comparative_channel

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

20 Nov, 17:20


إنا لله وإنا إليه راجعون

አላህ ጀነት ይወፍቀው!!!

ለቤተሰቦቹም አላህ ሰብር ይወፍቃቸው።

https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

20 Nov, 13:39


👇👇 እስራኤል ሆይ ስማ 👇👇👇

“ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ከሁሉ የሚበልጠው ይህ ነው፤ ‘እስራኤል ሆይ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፤”
  — ማርቆስ 12፥29 (አዲሱ መ.ት)

https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

20 Nov, 10:02


የንፅፅር ትምህርት እና በእስልምና ላይ ለሚነሱ ትችቶች መልስ የሚሰጡ ቻናሎች ለማግኘት
👇👇👇👇👇
የስልክ በመኝካት ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇

╭━━━━━━━╮
┃   ● ══        
┃███████┃ 👈ስልኩ
┃███████┃ 👈ነክታቹ
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃ 👈ተቀላቀሉ
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃        🔘       ┃
╰━━━━━━━╯

➶➶➶➶➶➶➶➶
እነዚ ውድ ቻናሉች ለማግኘት👆👆ከላይ ያለው የስልክ ምልኩቱ በመንካት ያግኑዋቸው ትጠቀሙበታላቹ ኢሻአላህ

የንፅፅር ቻናል ያላቹ wave ለመቀላቀል

በዚ አናግሩኝ➥
@mustef123
✍️በሰለምቴው ወድም ሙስጠፋ

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

19 Nov, 11:07


ከእስልምና በጣም ከምወዳቸው ነገራቶች ውስጥ ውሸት በየትኛው ሁኔታ ተቀባይት የለውም።

ሀይማኖትን በውሸት መርዳት አንችልም። በየ tiktoku የያችሁት ወሬ እውነት ብሎ አራት ና አምስት ዓመት ድረስ ሳያጣሩ መቀመጥ ምን የሚሉት ነው


https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

19 Nov, 03:10


በዚ ቻናል ዙርያ ምሰጡት ሀሳብ ከለ comment ላይ ፃፉልኝ እስኪ ውዶቼ🌹

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

18 Nov, 18:46


ሉቃስ 1:26-33
1980 እትም ነው

26ኤልሳቤጥ በፀነሰች በስድስተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ አንዲት ድንግል ተላከ ። ናዝሬት በገሊላ ክፍል ሀገር የምትገኝ ከተማ ናት ።
27 መልአኩ የተላከው ማርያም ወደሚትባል አንዲት ድንግል ነው። እርስዋ ከዳዊት ዘር ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው የታጨች ነበርች።
28 መልአኩም ወደ እርሱዋ መጥቶ አንቺ ጸጋን የሞላብሽ ፤ሰላም ለአንቺ ይሁን ፤እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት ።
29 እርሱዋም በመልአኩ አነጋገር በጣም ደንግጣ ይህ እንዴት ምን አይነት ሰላምታ ነው ይሁን? ብላ አሰበች ።

30 መልአኩም እንዲህ አላት ማርያም ሆይ! በእግዚአብሔር ፊት ፀጋ አግኝተሻልና አትፍሪ

31
እነሆ ትፀንሻለሽ???!

ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ???!

ስሙንም እየሱስ ትይዋለሽ???!

32 እርሱም ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል  ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊት ዙፋን ይሰጠዋል።
33 በእስራኤልም ላይ ለዘላለም ይነግሳል፤

እነኝህ አናቅፅት እየሱስ አምላክ አለመሆኑን የተፈጠረ ፉጡር መሆኑን ፍንትው አርጎ ያስረዳል።

1ኛመልአኩ ማርያምን ስያበስራት
እነሆ ትፀንሻለሸ ነው የላት ፅንስ
ደግሞ በሴት ልጅ መሐፀን የሚቀመጥ ብጣሽ ስጋ ነው
በማርያም ሆድ ውስጥ የነበረው
ፅንስ አምላክ ነበረን???????!
መፀነስ ማለት ካለ መኖር ወደ መኖር መምጣት አደለመምን??
ካለ መናር ወደ መኖር የሚመጣ አካል እንዴት አምላክ ልሆን ይችላል? እየሱስን እግዚአብሔር ግብርኤል እና እናቱም ድረስ ይቀድሙታል እየሱስ ከመፀነሱ በፊት ብቸኛ አምላክ የሆነው እግዚአብሔር ነበረ  ዮሐንስ 17:3
ዘዳግም 6:4 አንድና ብቸኛ መሆኑን ይናገራል ስለዚህ እየሱስን ብቸኛ የሆነው አምላክ እና በሱ የተፈጠሩ ፍጥረታት ይቀድሙታ ገብርኤል እናቱ ማርያም ኤልሳቤጥ  ወዘተ...
እና አምላክን ሚቀድመው ኣለን???!
2ኛ ገብርኤል ማርያምን ስያበስራት አምላክ ትወልጃለሽ ብሎ አላበሰራትም ብላትም ኡንካን አምላክ እንዴት ይወለዳል?
ገብርኤል ያበሰራት ወንድ ልጅ እንደ ሚቶልድ ነው ።
እሺ አምላክ እንዴት ፆታ ይኖረዋል ለምን አስፈለገው ለሰው ልጅ ፆታ
የሚያስፈልገው ምን ብያንስ ለሁለት ነገር ያስፈልገዋል።

1ኛ ከበላና ከጠጣ ቦሃላ የበላውን እና የጠጣውን በሌላ ነገር ተቀይሮ ከሰውነቱ ለማውጣት ያስፈልገዋል።

እየሱስ አምላክ ነው ካላቹ ፅታ ለምን አስፈለገው?

እየሱስ ይበላና ይጠጣ ነበር ሉቃስ 24:42-43   ዮሐንስ 4:7 ይመልከቱ!!  የበላውና የጠጣውን ከሰውነቱ ለማውጣት ወደ ሽንት ቤት  ጉዞ🚶ግድ ነው።

እና አምላክ በልቶ ጠጥቶ ወደ ሽንት ቤት ጉዞ ያደርጋልን???!
2ኛ ሚስት አግብቶ ራሱን ለማርካት
ፆታ ያስፈልገዋል ኢየሱስ አምላክ ነው
ከተባለ ፆታ ለምን አስፈለገው?

3ኛስሙንም እየሱስ ትይዋለሽ ነው
ያላት አጂብ ነው ለአምላክ ስም እያወጡለት ነው😜😅 እናም
እየሱስ የሚለው ስም ደግሞ የፉጡር ስም ነው በባይብል
ለፉጡር ያገለግል ነበር።

"እየሱስ" የሚለው ስም በግሪክ
"ኤሱስ"በቀዳማይ እብራይስጥ
"ያህሹአ" በደሃራይ እብራይስጥ
"ያሱአ" በአረማይክ"ዔሳዩ"በቀዳማይ አረብኛ "ዒሳ" በደሃራይ አረብኛ
"የሱዕ" ስሆን ትርጉሙ "ያህ መድሃኒት" የሚል ፍች ኣለው።

በአማርኛው ባይብል እያሱ የሚለው በግዕዙ እየሱስ ነው
የሚለው የአማርኛ ቶርጋምዎች ግን ቀይረውታል  አቤት ሌብነት🙊 🙊🙊🙊

ዘኁልቁም 11:28

ግዕዙ እንድህ ይላል
"ወይቤሎ ኢየሱስ ዘነዌ ዘይቀውም ቅድሜሁ ለሙሴ ዘውእቱ ኅሩዩ ይበሌ እግዚእየ ሙሴ ክልኮሙ"።
ትርጉሙ ፦ከልጅነቱ ጀምሮ የሙሴ
አገልጋይ የነበረው የነዌ ልጅ ኢየሱስ ጌታዬ ሙሴ ሆይ ከልክላቸው አለው።

ኢየሱስ ፉጡር ስለ ሆነ በፉጡር ስም ተጠርቶዋል።

4ኛ የልዑል ልጅ እንጂ ልዑል አልተባለም ።

ልጅ ሲባል እንዴት እንደሆነ ሮሜ 8:14 ገብተው ይመልከቱ።

5ኛ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል ይላል
የኢየሱስ አባቱ ማነው ዳዊት
ዳዊት ደግሞ ሚንድነው ሰው ነው
ፉጡር ነው ስለዚህ ኢየሱስ የሰው
ልጅ ነው የፉጡር ልጅ ነው አለቃ።

6ኛ በእስራኤል ቤት ለዘላለም
ይነግሳል ተብሎዋል ኢየሱስ አምላክ ከሆነ እንዴት ንግስናው
በእስራኤል ብቻ ይገደባል

እሄም ቁልጭ አርጎ ኢየሱስ አምላክ አለመሆኑን ያስረዳል።

ስለዚህ ኢየሱስ በአጭሩ የሰው ልጅና ፉጡር ነው ለእስራኤልም ብቻ የተላከ መላክተኛ ነው።

አሰተያት መቀበያ👇

@abdulaziz_student




link👇

t.me/ibnugarad


     


ሼር ሼር ሼር ያርጉ

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

16 Nov, 17:05


what happened

ምንም happened።

just gimme a little days.

I'm struggling with guyton and robbin. After the match ends we will have a nice time insha'a ALLAH.

https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

15 Nov, 05:12


የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርዓቶች 
————— 
Sunnahs and rituals of Friday

1  ገላን መታጠብ
     

2  በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ


3  በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ  አ      
        አለመረማመድ(መስጂድ ውሰጥ )


  4  ሱረቱል ከህፍን መቅራት
 

5     ዱዓ ማብዛት


6 በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት 

اللَّهُمَّ صَلٌِ عَلَى مُحَمَّدٍ وَّ عَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ

اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَّ عَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد

7 ሽቶ መቀባት (ለወንዶች )

      

https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

12 Nov, 18:11


አንዳንዴ ነገራቶች ከአቅም በለይ ሲሆኑብህ ለረጅም ጊዜ ከእይተ ራዳር ውጭ ልትሆን ትችላለህ።

ነገርግን ትክክለኛ ጓደኞችህ መመለስህን ሁልጊዜም ተስፋ ያደርጋሉ።

ሰላም እደሩ🌹🌹🌹

https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

10 Nov, 16:08


🌹🌹🌹መብሩክ ብለናል🌹🌹🌹

ወንድም ነጃ ና እህታችን መበዜ  አላህ እንኳን ለዚህ ቀን  አበቃችሁ

የምር ግን  አንድ ጓደኛህ ከሀራም ተጠብቆ ሀላል ሲወድቅ እንደማያት የሚያስደስት ነገር የለም።

መብሩክ ባልናን ቦሎቻም
መብሩክ ባልናን ድግላያም

እስቲ መብሩክ በሉት!!!!!

https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

08 Nov, 17:49


ሰሞኑን መብሩክ ልንል ነው መሰለኝ።

እንዳጠፋ.

ግዴታ ቦልቦሌ ካለሰተከፈተ እንዳትሉ እንጂ¡¡¡

stay tuned.

https://t.me/Ibnugarad

ኢብኑ ገራድ የንፅፅር ማኅደር

28 Oct, 05:34


የዘመናችን የፕሮቴስታንት ሥላሴ ሦስቱ አካላት የየራሳቸው ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ አላቸው በሚል "ማኅበራዊ ሥላሴ"Social Trinity" የሚታወቁ ሲሆን ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ አካልን እንጂ ባሕርይን ታሳቢ ስለማያረጉ ከዮሐንስ ተዐቃቢ ጋር ያመሳስላቸዋል። እሩቅ ሳንሄድ ዶክተሩ ተስፋዬ ሮበሌ ከዚህ ቀደም "የአስተምህሮተ ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት" በሚል መጣጥፋቸው ላይ፦ "ሦስት አካል ናቸው" ስንል ደግሞ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ የራሳቸው ስሜት፣ ፈቃድ እና ዕውቀት አላቸው" ማለታችን ነው፥ አካል የሚለውን ቃል የምንጠቀመው እግዚአብሔር የራሱ የሆነ ስሜት፣ ፈቃድ እና ዕውቀት እንዳለው ለማሳየት ብቻ ነው" በማለት እያንዳንዱ አካል የየራሱ ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ እንዳለው ጦምረዋል።

ወደ ነጥባችን ስንመለስ በዐረብ ዙሪያ ይኖሩ የነበሩ ማርያማውያን የክርስትና ጎጥ ሆነ ዐበይት ክርስትና "ሦስት ነው" የሚሉትን አምላካችን አሏህ «ሦስት ነው» አትበሉ" በማለት ሁለቱንም ድንበት አላፊያን ይገስጻቸዋል፦
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ይሉካል እንደዚህ ነው፥ ሦስቱን አካላት እነማን እነደሆኑ ቁርኣን ቢጠቅስ ኖሮ እያንዳንዱ አንጃ "የእኛን ሥላሴ በቅጡ አልተረዳውም፥ ቁልመማዊ ሕፀፅ አፅፆአል" ተብሎ ከሁለቱም ወገን ክስ ይቀርብ ነበር። ኢየሱስን የላከ አንድ አምላክ አሏህ ሆኖ ሳለ ያንን አንድ አምላክ ከሦስቱ ማንነቶች አንዱ ማንነት ነው" ማለት በእርግጥ ክህደት ነው፦
5፥73 እነዚያ «አላህ ከሦስቱ አንዱ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ ثَالِثُ ثَلَاثَةٍ
"Certainly they are unbelievers who say: "Allah is one of three". (Farook Malik Translation)
ተፍሢሩል ቁርጡቢይ 5፥73
የላቀው አሏህ ንግግር፦ "እነዚያ «አላህ የሦስት ሦስተኛ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ" ማለት "ከሦስቱ አንዱ ነው" ማለታቸው ነው። قوله تعالى: { لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوۤاْ إِنَّ ٱللَّهَ ثَالِثُ ثَلاَثَةٍ }. أي أحد ثلاثة.

ኢብኑ ዐባሥ ዐበይት የሥላሴ አማንያን የሚሉትን ታሳቢ በማድረግ «ሦስት» ያሉት "አባትን፣ ልጅን፣ መንፈስ ቅዱስ" ሲለን ጀላለይን ደግሞ ማርያማውያንን ዋቢ በማድረግ «ሦስት» ያሉት "አባትን፣ እናትን፣ ልጅን" እንደሆነ አስቀምጦልናል፦
ተፍሢር ኢብኑ ዐባሥ 5፥73 "እነዚያ «አሏህ ከሦስቱ አንዱ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፥ መርቁሢያህ፦ "አባትን፣ ልጅን፣ መንፈስ ቅዱስ" አሉ"። { لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوۤاْ إِنَّ ٱللَّهَ ثَالِثُ ثَلاَثَةٍ } وهي مقالة المرقوسية يقول أب وابن وروح قدس
ተፍሢር ጀላለይን 5፥73 «እነዚያ "አሏህ ሦስተኛ" ያሉ በእርግጥ ካዱ» አማልክት «ሦስት» አሉ፥ እርሱ(አሏህ) ከእነርሱ አንዱ ነው፥ ሁለቱ ኢየሱስ እና እናቱ ናቸው" ይህንን የሚሉት ከነሷሪይ ፊርቃህ ናቸው"።
{ لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُواْ إِنَّ ٱللَّهَ ثَالِثُ } آلهة { ثَلَٰثَةً } أي أحدها والآخران عيسى وأُمّه وهم فرقة من النصارى

"ፊርቃህ" فِرْقَة ማለት "ጎጥ" "አንጃ" ማለት ነው፥ ኮሊሪዲያን በአንድ ወቅት የነበረ አሁን ላይ የጠፋ የክርስትና ጎጥ"sect" ነው። ዐበይት የክርስትና ሥሉሳውያን ሥላሴያቸው ከሂንዱ ሥላሴ የተቀዳ ሲሆን የኮሊሪዲያን ሥላሴያቸው ደግሞ ከግብፅ ሥላሴ የተቀዳ ነው፥ "ክርስቲያን ነን" የሚሉት ሁለቱም የየራሳቸውን ሥላሴ በጥቅሉ ቁርኣን በአንድ ድንጋይ "ሦስት ነው አትበሉ" በማለት መቶቷል። ደግ አረገ! "ክርስትና የበቀለው ከዐረማዊነት ነው" የምንለው በምክንያት ነው። የክርስትና ታሪክ ምሁር ኤድዋርድ ጊቦን "History of christianity" በተባለው መጽሐፋቸው ላይ ስለ ክርስትና ዐረማዊነት"paganism" እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፦
"አረማዊነት በክርስትና ድል ቢነሳም ክርስትናም በዚያው መጠን በአረማዊነት ተበክሏል"።
History of christianity (Edward Gibbon) page XVI(16)

የሥላሴ አማንያን ክርስቲያኖች ሆይ! ነቢያት እና ሐዋርያት የማያውቁት ውስብስብ ከሆነ የክርስትና ሥላሴ ወጥታችሁ በተውሒድ እንድታምኑ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም