የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን @aaeqocaa Channel on Telegram

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

@aaeqocaa


https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን (Amharic)

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በመስራት የስራ አመራር ደረጃ ማንኛዉም እውን ሰርተናል። እነሆ፦ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በማህበረሰብ ምንጭ ከሆነ በፊት ተመልከቱ። ይሔንን ቡድን ምክንያት እንዴት ተማሪ ነዉበኞቹ? ታላቅ ትምህርትና ስልጠና መተዉል እና የጤና ዉሽጥ ከመስጠተዉ ጋር እንዴት የምንሞት ነበዉ? ከዚም ላይ። የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ድምፅ ከሆነ በሁሉም አካባቢ ቅንብሮች ላይ የሚግዛበት ትምህርት ነው።

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

21 Nov, 12:53


በመርሃ-ግብሩ ላይ ከባለስልጣኑ ጋር በቅንጅታዊ ትስስር ተግባር በጋራ የሚሰሩ ተቋማት አመራሮች እንደገለጹት ስራን በቅንጅትና በጋራ ማከናወንና መገምገም የተሻለ ውጤትን እንደሚያስገኝ ገልጸው ባለስልጣኑም ስራዎችን እንዲህ መገምገሙን በአርዓያነት አንስተዋል፡፡
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

21 Nov, 12:53


ባለስልጣኑ በቅንጅታዊ ትስስር ተግባር እቅድ አፈጻጸም ላይ ግምገማ አከናወነ፡፡

(ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም)በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት የቅንጅታዊ ትስስር ተግባራት አፈጻጸምን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ግምገማ አካሄደ፡፡
ባለስልጣኑ ተግባራትን በቅንጅትና በጋራ ከሚያከናውናቸው ሴክተር ተቋማት ጋር ለይቶ ያከናወነውን ተግባር በምን ያህል መከናወኑን ገምግሟል፡፡

አቶ ነብዩ ዳዊት የባለስልጣኑ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሪፖርቱን ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት በ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በቅንጅታዊ ትስስር ሰራዎች በየሴክተሩ የተከናወኑ ስራዎች፣ያጋጠሙ ችግሮች የተወሰዱ መፍሄዎች የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች በዝርዝር አስቀምጠዋል፡፡

አቶ ዳኛው ገብሩ የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ በመርሃ-ግብሩ ላይ እንደገለጹት ባለስልጣኑ ስራዎችን ከሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ሲያከናውን የምንሰራው ዜጎች ላይ በመሆኑ፣ ትምህርትና ስልጠና ደግሞ የሁሉም መሰረት በመሆኑ ትኩረት አድርገን ስራዎችን በክህሎት በመምራት ውጤታማ መሆን ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ እንደገለጹት ተወዳዳሪ የሆነ ክህሎት ያለው ዜጋን ማፍራት ለሀገር እድገት ቀዳሚ ተግባር በመሆኑ በጋራ ሆነን ተቀናጅተንና ተናበን ችግሮችን በመፍታት በሩብ ዓመቱ በቅንጅታዊ ስራ የታየውን የተሻለ አፈጻጸም በቀጣይም የበለጠ ውጤት ማስመዝገብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

20 Nov, 14:07


አዲስ አበባ በፈጣን የልማት ግስጋሴ ላይ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

19 Nov, 11:59


የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያቀረቧቸውን ተሿሚዎች በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡
በዚህም መሰረት ፡-

1.ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ - በም/ከንቲባ ማዕረግ የአ/አ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ
2. አቶ ተንኩዌይ ጆክ ሮም - የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ኃላፊ
3. አቶ ይመር ከበደ ይማም የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር
4. ዶ/ር ግዛቸው አይካ - በአዲስ አበባ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና መዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

የቦታ ለውጥ ያደረጉ

1. አቶ አደም ኑሪ - የፕላንና ልማት ቢሮ ሃላፊ
2. አቶ ቢኒያም ምክሩ - የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
3. ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ - የንግድ ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን አጠናቅቋል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

19 Nov, 08:11


የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማከናወን ጀምሯል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው አስተያየትና ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያዎችን የሚሰጡ ይሆናል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

18 Nov, 11:50


ይህንንም ለማከናወን ተግባሮቻችን ግቦቻችንን ለማሳካት ያላቸውን ጠቀሜታ፣የሚያመጡትን ውጤት ያላቸውን ተዛምዶ በመለየት በ(Priority Matrix) ያላቸውን ከፍተኛ ድርሻ ለይቶ በመከወን የሚገኝ ነው ያሉ ሲሆን በተጨማሪም በምናከናውናቸው ተግባራት ውስጥ የበርካታ ችግሮች የመነሻ ምንጭ (Root Cause) ወሳኝ ምክንያቶች በመሆናቸው እነዚህን ችግሮች መፍትሄ በመስጠት የተሻለ ምርታማ መሆንና ችግሮቻችንን መፍታት እንችላላን ብለዋል፡፡

አቶ ዳኛው ገብሩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ በመርሃ-ግብሩ ላይ እንደገለጹት እኔ ማነኝ? በህይወቴ፣በስራዬ ያለኝ ጠቃሚነትና ሚና ምንድነው?ህይወቴንስ ጠቃሚ አድርጌዋለሁ ወይ የሚለውን በመለየት ራሳችንን መፈተሽ አለብን ብለዋል፡፡

#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

18 Nov, 11:49


በባለስልጣኑ የሰራተኞች የሰኞ ማለዳ መነቃቂያ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

(ህዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዘወትር ሰኞ ማለዳ የሚያደርገው የማነቃቂያና ትምህርታዊ የውይይት መርሃ-ግብር የባለስልጣኑ ሰራተኞችና አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

"እጅግ ወሳኝ የሆኑ ተግባራትን ምርታማ በሆንበት ወቅት ማከናወን በርካታ ውጤት ለማግኘት ወሳኝ ነው" በሚል የመወያያ ሀሳብ ያቀረቡት አቶ አየን ደርሰህ ሲሆኑ በመቀጠል እንዳስረዱት /Pareto Principle/ በመተግበር ለትልቅ ውጤት (80%)ለሚሆነው መገኘት በቁጥር አነስተኛ እጅግ ወሳኝ ልዩ ትኩረት ለሚያስፈልጋቸው እና ጠቀሜታ ላላቸው(20%)ተግባራት ላይ በማተኮር ይህንንም ምርታማ በሆንበት ወቅት አልሞ በርብርብ በመተግበር ውጤታማ መሆንና የታለመለትን ግብ ማሳካት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡