FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ @fm94_7 Channel on Telegram

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

@fm94_7


የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ (Amharic)

አብረን የሚታወቀው FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ በየትምህርት እና ትምህርት የሚከታተሉትን ሬዲዮ እና ኢንፋሻሊክ የሚያቀርበውን ምርጫ ነው። fm94_7 ከሰው ሆነ እና ሰዎች ከተማ አካልና ሌሎች እንዲሁም በአገራችን አገሪቱ ላይ የምንገኝበት የትምህርት ድህረ ገጽ ነው። ይህ ድህረ ገጽ በዓለም አቀፍ በኤሌክትሪክ በራስዋርት እና በየማህበር ስህተትን ለመገበር ለማደናግ እና ለሌላ ሰው ማዳረግ ያስፈልገዋል። ስለዚህ ሰላምና ውድ ማህበረሰብን ማወቅ ብቻ ነው! ምንም እናስብ በመላክ እና ያሰናዳን።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

13 Jan, 08:16


የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ነገ ይጠናቀቃል
*****
05/05/2015 ዓ.ም

የ2017 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (የ12ኛ ክፍል) ፈተና ምዝገባ በመጪው ማክሰኞ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቋል።

በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ካሉ በቀጣዮቹ ዛሬ እና ነገ እንዲመዘገቡ ያሳሰበው አገልግሎቱ፤ ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ፈተናውን እንደማይፈተኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መልዕክት አስጠንቅቋል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

11 Jan, 13:17


ለትራፊክ አደጋ ተጋላጭ ከሆኑ 84 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ  550 በጎ ፈቃደኛ ረዳት የተማሪ ትራፊክ አስተባባሪዎች ተመረቁ።


ጥር 3/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የትራንስፖርት ዘርፍ ልምድ ልውውጥ ለማድረግ በመዲናችን የተገኙ የክልል ትራንሰፖርት የሥራ ሃላፊዎች ቡድን አባላት በተገኙበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ያሰለጠናቸው 550 ረዳት የተማሪ ትራፊክ ፖሊሶች በዛሬው እለት ተመርቀዋል።


ባለስልጣን መ/ቤቱ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በከተማዋ ለትራፊክ አደጋ ተጋላጭ ከሆኑ 84 ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች በመንገድ ደህንነት እና መሠረታዊ የመንገድ ትራፊክ ፍሰት ማስተናበር ዙሪያ የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር ስልጠና ወስደው በተግበረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቅጥር ጊቢ ተመርቀዋል።


ተመራቂ ተማሪዎቹ በትምህርት መግቢያ እና መዉጫ ሰዓት የትራፊክ ማስተናበር ስራን፣ በየትምህርት ቤቶቻቸው ባሉ የመንገድ ደህንነት ክበባት የግንዛቤ ማስጨበጫን የሚሰሩ ሲሆን በበዓላት ቀናት እና በዕረፍት ቀናቸው በሚኖሩበት አካባቢ የትራፊክ ፍሰቱን የማስተናበር ስራ ያከናውናሉ።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

11 Jan, 09:16


ርዕደ መሬቱ በ37 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ።

በአፋር ክልል ጋቢ ዞን እየተከሰተ ባለው ተከታታይ ርዕደ መሬት በሶስት ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 37 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት ማድረሱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሃላፊ አቶ አብዱ ሀሰን ያዮ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለፁት÷ በጉዳቱ ሙሉ በሙሉ የወደሙ እና በከፊል ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች መኖራቸውንም አክለው ገልፀዋል፡፡

16 ትምህርተ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ጉዳት ሲደርስባቸው 21 ትምህርት ቤቶች ደግም ከፊል ጉዳት እንደረሰባቸው ሃላፊው ገልፀዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዳይርቁ በክልል ደረጃ ኮሚቴ በማቋቋም ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

ጉዳቱ የደረሰው በአዋሽ-ፋንታሌ፣ ዱላሳ እና ሓንሩካ ወረዳዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

11 Jan, 09:08


በመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት የደረሰበት በገቢ ረሱ ዞን ዱለሳ ወረዳ የሚገኘው ሳጋንቶ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

11 Jan, 08:26


ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስስተዳደር የ5 ሚሊዮን ኮርስ ኢኒሼቲቭ የቅዳሜና እሁድ የስልጠና ፕሮግራም በይፋ አስጀመረ።

ጥር 3/2017 ዓ.ም

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በዛሬው ዕለት የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ የቅዳሜና እሁድ የስልጠና መርሃ ግብር አስጀመረ።
ስልጠናዉ በይፋ ያስጀመረዉ ኢመደአ በ2016 ዓም በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የሰመር ካምፕ ፕሮግራም ያሰለጠናቸዉን 237 ተማሪዎች በሚያስመርቅበት ቀን ነዉ።

ስልጠናዉ በተቋሙ የሳይበር ልሕቀት ማዕከል ውስጥ የሚሰጥ ሲሆን ይህም በመዲናችን አዲስ አበባ የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች ስልጠናውን ለመውሰድ የሚያስችላቸውን ምቹ ሁኔታ (የስልጠና ቦታ፣ ኮምፒውተር እና የኢንተርኔት አቅርቦት) በነጻ እንዲያገኙና ስልጠናውን በቀላሉ ለመውሰድ የሚያስችላቸው ነው፡፡

የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ስልጠናዉን ለመዉሰድ ከ8ሺ በላይ ሰልጣኞች ተመዝግበዋል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

08 Jan, 10:55


ማስታወቂያ!

(ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም ለሚያዘጋጀው ልዩ የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና የቅድመ ዝግጅት ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡

ስልጠናው የመምህራንን የስልጠና ፍላጐት መሰረት ያደረገ እንዲሆን በተለያዩ የሀገራችን ክፍል ከሚገኙ መምህራን መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል የበይነ መረብ መጠይቅ ተዘጋጅቷል።

በመሆኑም በማንኛውም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጂኦግራፊ፣ የታሪክ፣ የኢኮኖሚክስ፣ የስነዜጋ እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የትምህርት ዓይነቶች የምታስተምሩ መምህራን ከዚህ መልእክት ጋር ተያይዞ በተቀመጠው ሊንክ በመግባት የተዘጋጀውን መጠይቅ እንድትሞሉና ለሚዘጋጀው ስልጠና የበኩልዎን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቅርባል። https://forms.gle/NTMzLQK6pohUpvkq6 https://forms.gle/NTMzLQK6pohUpvkq6

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

06 Jan, 16:50


በተጨማሪ የልደት በዓሉ የሚያስተምረን ቁም ነገር ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ _ የበደለውን የሰው ልጅ ይቅር ካለውና የመዳን ተስፋ ከሰጠው እኛም ይህንን በዓል ስናከብር የበደሉንን ይቅር በማለት ፣ ያጠፋነውን በማስተካከልና በማረም ፣ ጥላቻን በማስወገድ ፣ ፍቅርን ለሰው ልጆች በመስጠት ሊሆን ይገባል ሲል የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሳስቧል፡፡

ያለንን ማካፈል ፤ የታረዙትን ማልበስ እና የታመሙትን መጠየቅ ዘመናትን ተሻግሮ የመጣ አብሮ የመኖር ኢትዮጵያውያን እሴቶቻችን መሆናቸውን የገለጸው ጉባኤው  እነዚህን እሴቶች  ተጠብቀውና ተጠናክረው ለትውልዱ እንዲተላለፉ ካለን በማካፈል እና እርስ በርስ በመደጋገፍ የአብሮነትና የወንድማማችነት ባህላችን ሆኖ እንዲቀጥል ልንሰራ ይገባል ብሏል፡፡

ክርስቶስ ሕይወት እና አስተምህሮ አገልጋይነት በመሆኑ ይህንን ከጌታ የተማርነውን እራስን ለሌሎች መስጠትን፣ ትህትና እና የአገልጋይነት ባህሪይ በመላበስ የማገልግል ምሳሌነትን ባለንበት የሃላፊነት ቦታ ሁሉ ልንተገብረው እንደሚገባ ይህ በዓል በአንክሮ ያሳስበናልም ነው ያለው ጉባዔው፡፡

ጉባኤው ከዚህ ቀደም በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ሰበዓዊ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን በማስታወስ  ወደ ፊትም ይህንን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል፡፡

በዚህ በዓልም በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮዓዊ ችግሮች ምክንያት በተለያዩ መጠለያ ውስጥም ይሁን በየአከባቢያችን የሚገኙ አቅመ ደካሞችን እና አረጋውያንን ልናግዛቸው ልንደግፋቸው ይገባል ሲል ጉባዔው መልዕክት አስተላልፏል፡፡

በዓሉ የሰላም፤ የፍቅር ፣ የመከባበር ፣ የወንድማማችነት እንዲሁም ኢትዮጵያ ወደ ዘላቂ ሰላም የምትሸጋገርበት ጊዜ እንዲሆን የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

06 Jan, 16:49


በዓሉን ስናከብር ያለንን በማካፈል ፤ የታረዙትን በማልበስ እና የታመሙትን በመጠየቅ ሊሆን ይገባል-የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ

ታኀሣሥ 28/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ጉባዔው በመልዕክቱ በመላው ዓለም ለሚገኙ የክርስትና ዕምነት ተከታይ ኢትዮጵያዉያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

“የጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ለሰው ልጆች ሁሉ “ታላቅ የምስራች” ተብሎ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሲበሰር በዋናነት ሁለት ታላላቅ ጉዳዮች ተከናውነዋል” ያለው ጉባዔው “የመጀመሪያው በጌታ መወለድ ምክንያት ሰዎችን ሁሉ ከሃጢያትና ከሞት የሚያድን መድሃኒት መገኘቱን ሲሆን ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም በበረት ውስጥ ሲወለድ እሱ የዓለም ፈጣሪ እና ጌታ ሆኖ ሰውን ዝቅ ብሎ የማገልገልን ምሳሌነት የተወልን መሆኑን ያስታውሰናል” ሲል ገልጿል፡፡

ይህን በዓል ስናከብር ክርስቶስ ከሃጢያትና ከሞት የሚያድነን መሆኑን በውል በመገንዘብና በሰዎች መከካል ስንኖርና ስናገለግል በትህትናና ለሰዎች ክብር በመስጠት መሆኑን መዘንጋት የለብንም ነው ያለው ጉባዔው በመግለጫው፡፡

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

06 Jan, 16:44


https://m.youtube.com/watch?v=Ud69mhCjE10

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

06 Jan, 13:56


የልደት በዓልን በገና ዛፍ የማድመቅ ልምድ በእጅጉ እየተስፋፋ የመጣው ቪክቶሪያ ኢራ (ከ1837 እስከ 1901) ተብሎ በሚጠራው የእንግሊዝ ዘመነ መንግሥት ነው። በአሁኑ ወቅት በዓለማችን በየዓመቱ ከ350 ሚሊዮን በላይ አርቴፊሻል የገና ዛፎች እንደሚሸጡ መረጃዎች ያመላክታሉ። በኢትዮጵያ የገና መምጣትን ተከትሎ “የገና ጨዋታ” በስፋት ይዘወተራል። በገና ጨዋታ ወቅት ግጥሞችን መደርደር የተለመደ ነው። “በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ”፤ በገና ጨዋታ የለም ሎሌ ጌታ” እየተባለም ይገጠማል።
በተለይ ከበዓሉ ጋር በተያያዘ በየዓመቱ የባህል ስፖርት የሚከናወን ሲሆን ከተለያዩ ቦታዎች የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን በጃንሜዳ ተሰብስበው የገና ጨዋታ ውድድር ያካሂዳሉ። የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በዓሉን የማኅበራዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ይጠቀሙበታል። በበዓሉ ወዳጅ ዘመድ ይጠያየቃል፤ ዕለቱን በአብሮነት ያሳልፋል። የገና አባት መነሻ ታሪክ በ4ኛው ክፍለ ዘመን ኔዘርላንድስ ውስጥ የነበሩ ቅዱስ ኒኮላስ የተባሉ ጳጳስ ናቸው። እኚህ አባት በልግስናቸው ስመ-ጥር እንደነበሩ የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

ይህንኑ ምሳሌ በማድረግ የገና አባቶች (ሳንታ ክላውስ) የሚባሉ ሙሉ ቀይ እና ነጭ ልብስ በመልበስ እና ረጅም አርቴፊሻል ነጭ ፂም በማድረግ ለልጆች ከረሜላ ያድላሉ። በኢትዮጵያ የገና አባት የሚባሉት የገና ጨዋታን የሚመሩ አባቶች ናቸው፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን በከተማዎች አካባቢ የፈረንጆቹን የገና አባት (ሳንታ ክላውስ) መመልክቱ የተለመደ ሆኗል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

06 Jan, 13:55


የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አከባበር ከጥንት እስከ ዛሬ
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በአብዛኛው የዓለም ሀገራት በጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ታኅሣሥ 25 ይከበራል። የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች በብዛት በሚገኙባቸው እንደ ሩሲያ፣ ግሪክ፣ ዩክሬን እና ሮማኒያ ባሉ ሀገራት ደግሞ በዕሉ በጎርጎሮሳዊያኑ ጥር 7 ላይ ያርፋል። በሀገራችን የልደት በዓል በየዓመቱ ታኅሣሥ 29 (በየአራት ዓመቱ /በዘመነ ዮሐንስ/ ደግሞ ታኅሣሥ 28) ላይ በተለያዩ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥርዓቶች ተከብሮ ይውላል። የልደት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ፈጣሪ የሰውን ልጅ ለማዳን አንድያ ልጁን ለቤዛነት የሰጠበት (አምላክ ሰው የሆነበት) መሆኑ ስለሚታመን የሥጦታ በዓል ተደርጎ ይታሰባል።
ይህን መነሻ በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች በዕለቱ የተለያዩ ስጦታዎችን ይሰጣጣሉ። በሀገራችንም በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለክርስቶስ ልደት በዓል (ለገና) ፖስት ካርድን ጨምሮ ሌሎች ስጦታዎችን መለዋወጥ እየተለመደ መጥቷል። የገና ዛፍን (ክሪስማስ ትሪ) በቀለማት እና በተለያዩ ጌጣጌጦች አስውቦ መስቀል የተጀመረው በ16ኛው ክፍለ ዘመን ጀርመን ውስጥ መሆኑ ይነገራል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

06 Jan, 13:32


ከ30 ዓመታት በፊት የፊዚክስ ሊቁ የ2025 ትንበያዎች
ስመ ጥሩ እንግሊዛዊ ሳይንቲስት ስቴቨን ሃውኪንግ እ.አ.አ በ1995 ዓለም ከ30 ዓመታት በኋላ ምን ልትመስል ትችላለች የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር፡፡ የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት 2025 መግባቱን አስመልክቶ የፊዚክስ ሊቁን ትንበያዎች ከ30 ዓመት በኃላ በምልሰት ተቃኝተዋል፡፡ ሊቁ በ30 ዓመታት ውስጥ የሚጠበቁ ግዙፍ ለውጦች ብሎ ካነሳቸው ጉዳዮች በየዘርፉ የቴክኖሎጂው መፍላት ነው፡፡ ሃውኪንግ የበይነ መረብ ጥቃት፣ የኮምፒዩተር ቫይረስና የመረጃ ምንተፋዎች እንደሚስፋፉ የተናገራቸው ትንበያዎች ባለ ጥቁር ምላስ አስብለውታል፡፡
ሌላኛው ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የርቀት ህክምና አገልግሎት ትንበያው ሲሆን ሊቁ ስልጡን ሮቦት ሀኪሞችን የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ብሎ ነበር፡፡ ይህ የሃውኪንግ ትንበያ ሙሉ በሙሉ ባይሳካም በተለያዩ የዓለም ሀገራት ጅማሮዎች ግን ተስተውለዋል፡፡
የሰው ልጅ ከህዋ ላይ ውድ ማዕድናትን ወደ ምድር ማጋዝ እንደሚጀምር በፊዚክስ ሊቁ የተሰጠው ትንበያ፤ ናሳን ጨምሮ የተለያዩ የጠፈር ምርምር ማዕከላት ከጨረቃ መጡ የተባሉ ድንጋዮችን በሙዚየም እስከማሳየት ቢደርሱም እስከ ማዕድን ቁፋሮ ስለመድረሳቸው ግን መረጃ ማግኘት አይቻልም፡፡ በህዋ ላይ ማዕድናት ያማውጣት ስራ ባይጀመርም፤ እድሉ ግን አሁንም እንዳለና በህዋ ላይ ያሉ ሰው ሰራሽ ቁሳቁሶች ለጠፈርተኞች እንቅስቃሴ እክል መሆናቸው ይገለጻል፡፡
ሳይንቲስቱ በትንበያው ከ30 ዓመታት በፊት ሊከሰት ይችላል ያለው ጉዳይ በዲጂታል የባንክ አገልግሎት ገንዘብ ከባንክ መክፈያ ማሽን ማውጣት የሚቻልበት ቴክኖሎጂ በወደፊቱ የባንክ ዘርፍ ተግባራዊ እንደሚሆን ነበር፡፡ የሳይንቲስቱ ግምቶች እውን ሆነዋል፡፡ ዲጂታል የባንክ አገልግሎት ደንበኞች ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ የሚችሉበት ዘመን እውን ሆኗል፡፡

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

06 Jan, 12:13


እንኳን ለ2017 የገና በዓል አደረሳችሁ!

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

06 Jan, 12:11


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም

የገና ፆም ከቤተ ክርስቲያን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የሚፆሙት ታላቅ ፆም ነው። ዛሬም ክርስቲያኖች ይህንን ፈለግ ተከትለው በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የሚያስቡበት ነው።

ይህንንም ታላቅ የፆም ወቅት በማጠናቀቅ ለዛሬ ው የገና በዓል ዋዜማና በነገው እለት ለሚከበረው የገና በዓል ላደረሳችሁ ላደረሰን ለፈጣሪ ክብር ምስጋና ይድረሰው።

በዓሉን ስናከብር ያለንን ተካፍለን ፣ አቅመ ደካምችንና አረጋዊያንን አግዘን እንዲሁም ለሌሎች ብርሀን በመሆን፣ ወንድማማችነትን በማጎልበት ፣ ፍቅርን በማብዛት እና እርስ በእርስ በመደጋገፍ ሊሆን ይገባል።

በመጨረሻም ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን ! እያልኩ በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የመረዳዳት፣ የሰላም ፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆን ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

አመሰግናለሁ!

ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደሙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

06 Jan, 10:13


በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት ምን አይነት ጥንቃቄ ልናድርግ ይገባል?
የዘርፉ ባለሙያዎች የመሬት መንቀጥቀጥ አሊያም ከፍተኛ ንዝረት ሲከሰት "ቤት ውስጥ ከሆናችሁ በፍጥነት ከለላ ፈልጉ" ይላሉ። በቀላሉ የማይሰበር ጠረጴዛ ካለ መንቀጥቀጡ እስኪያባራ እዚያ ሥር መከለል , ካልሆነ ደግሞ ጭንቅላታችሁን በክርናችሁ ሸፍናችሁ ያላችሁበት ቤት ጥግ ላይ መሸሸግ ፣ ጋዝ ካለበት፣ ከመስታወት፣ ከበር እና ከግድግዳ ውጭኛው ክፍል በአጠቃላይ ሊወድቁ ከሚችሉ ቁሶች አካባቢ መራቅ ። ለምሳሌ ጣራ ላይ ከተሰቀለ አምፖል ራቅ ማለት ይመከራል። አልጋ ካሉ ደግሞ እዚያው እንዲሆኑ ይመከራል። ጭንቅላትዎን በትራስ ይከላከሉ። ነገር ግን ከአልጋው በላይ ከበድ ያለ መብራት ካለና ከወደቅ አደጋ ሊፈጥር የሚችል ከሆነ ቀረብ ወዳለና ከለላ ወዳለው ቦታ በፍጥነት ይሻገሩ። አሳንሰር የተገጠመለት ሕንፃ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ በፍፁም እንዳይጠቀሙት።

በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት ውጭ ካሉ ከሕንፃዎች፣ የኤሌክትሪክና ስልክ ገመዶች እንዲሁም ከመንገድ መብራቶች ይራቁ።
ገላጣ ሥፍራ ላይ ካሉ መንቀጥቀጡ እስኪያባራ እዚያው ይሁኑ። ትልቅ አደጋ ሊኖር የሚችለው ሕንፃዎች አካባቢ ነው። በተለይ በሕንፃ መውጫና እና መግቢያ አካባቢ መሆን አይመከርም። እየተንቀሳቀሰ ያለ ተሽከርካሪ ውስጥ ከሆኑ በተቻለ ፍጥነት አቁመው እዚያው ተሽከርካሪ ውስጥ ይሁኑ። ቢቻል ሕንፃዎች አካባቢ፣ ዛፎች አጠገብ እና የኤሌትሪክና ሌሎች ገመዶች ባለቡት ሥፍራ ባያቆሙ ይመረጣል። የመሬት መንቀጥቀጡ ካባራ በኋላ ክብሪት መለኮስ አይመከርም። ምክንያቱም መንቀጠቀጡ ጋዝ ላይ አደጋ አድርሶ ከሆነ እሳት ሊፈጥር ይችላል። መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ከሆነ እና ፍርስራሽ ካለ አፍና አፍንጫን በመሀረብ መሸፈን ፣ አደጋ ባለባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ለአደጋ ጊዜ የሚሆን ምግብና መጠጥ ቢያዘጋጁ ይመረጣል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

06 Jan, 09:49


ርዕደ መሬት የሚለካው እንዴት ነው?
ርዕደ መሬት የሚለካው የአፍታ መጠን መለኪያ በሚባል መስፈርት ነው።

2.5 ወይም ከዚያ ያነሰ መንቀጥቀጥ ሊሰማን አይችልም። ነገር ግን በመሳሪያዎች እገዛ ሊታወቅ ይችላል።

እስከ አምስት የሚደርሱ መንቀጥቀጦች የሚታወቁ ቢሆንም የሚያደርሱት አነስተኛ ጉዳት ነው። በቱርክ የደረሰው ርዕደ መሬት 7.8 ሲሆን፣ ትልቅ በሚባለው ደረጃ ውስጥ ተካቷል።

በዚህም ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ሕንጻዎችን ወደ ፍርስራሽነት በመቀየር፣ አስካሁን ከ10 ሺህ በላይ ነገር ግን ቁጥሩ በየደቂቃው የሚጨምር ሕይወትን በመቅጠፍ አሁን እንደተፈጠረው ዓይነት ከፍተኛ ጉዳትን ያስከትላል።

በርዕደ መሬት መለኪያ ከ8 በላይ የሚመዘገብ ነውጥ አስከፊ ጉዳት ያስከትላል። በዚህም የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተበት ማዕከላዊው ስፍራ እና በአቅራቢያው የሚገኙ ግንባታዎችን እና ሰዎችን ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋ ይችላል።

እአአ በ2011 በጃፓን የባሕር ዳርቻ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 9 ሆኖ ተመዝግቧል። ምድር ላይ ሰፊ ውድመት ከማስከተሉም በላይ ተከታታይ ግዙፍ ሱናሚዎችንም ፈጥሯል።

አንደኛው ሱናሚም በባሕህር ዳርቻው የኒውክሌር ጣቢያ ላይ ትልቅ አደጋ አስከትሏል።

አስካሁን ከተመዘገቡት ሁሉ ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ 9.5 ሲሆን በ1960 በደቡብ አሜሪካዊቷ አገር ቺሊ ውስጥ የተከሰተው ነበር።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

05 Jan, 14:33


(ታህሳስ 27/2017 ዓ.ም) ማስታወቂያ!

1 :- የ 1 2ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጥር 6 /2017 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል። ስለሆነም ምዝገባ ያላጠናቀቃችሁ ከቀነ ገደቡ አስቀድማችሁ እንዲታጠናቅቁ እናሳስባለን።


2:- የ2017 የትምህርት ዘመን ፈተናዎች ይዘት የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ሁኔታ ከ 9 - 12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ 8 ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7- 8ኛ ክፍሎች የሚሸፍን ይሆናል።


3:- እያንዳንዱ ተማሪ በተማረበት የክፍል ደረጀ የተማረውን የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርጐ ሊዘጋጅ ይገባል። ፈተናዎቹ ተማሪዎቹ የተማሩትን መሠረት አድርገው የሚዘጋጁ ይሆናል።


የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል ።


የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

04 Jan, 14:18


ቻርልስ ሬክተር የሬክተር ስኬል ፈጣሪ
-------
ከሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ ጋር ተያያዥነት ያላትን ይህችን እንካችሁ ፤

የእንቅጥቅጡን መለኪያ የፈጠሩት እኚህ ሰው እንደሆኑ ታውላችሁ ፥ ቻርልስ ሬክተር ይባላሉ።

ዜግነታቸው አሜሪካዊ ነው ፥ አንቱታን ያገኙ የስነ ምድር ተመራማሪ ነበሩ።

ከሙያ አጋራቸው ቤቶ ጉተንበርግ ጋር በመሆን የመሬት እቅስቃሴ እና ንዝረት የሚለካበትን መሳሪያ ፈጥረዋል።

መለኪያው የእርሳቸውን ስም ወስዶ ሬክተር ( Rechter Scale ) ተብሏል።

ቻርልስ ግኝቱን መፍጠር የጀመሩት እአአ በ1932 ሲሆን ያጠናቀቁት ደግሞ በ1935 ነው።

ሰሞኑን ከዚህ ስም ጋር ያው ወዳጅ ሆነንም የለ፥ ላለፉት ሶስት ሳምንታት ገደማ ቢያስ በቀን ሶስቴ ስማቸው በሃገራችን ሚዲያዎች ይጠራል ።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

04 Jan, 14:14


ክብርት ወ/ሮ አበበች ነጋሽ አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ያስተላለፉት መልዕክት

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

04 Jan, 13:58


በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች!

አዋሽ ፈንታሌን ጨምሮ በስምጥ ሸለቆ አካባቢ የተለያዩ ሬክተር ስኬል የተመዘገበበት ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ማድረግ የሚገቡ ጥንቃቄዎች በተመለከተ ተከታዩን ምክር ለግሷል።

ከቤት ውጭ ከሆኑ፦ ከዛፎች፣ ከሕንፃዎች ፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።

በቤት ውስጥ ከሆኑ፦ በበር መቃኖች፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ ይገባል። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ ፦ ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም፣ ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።

መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ፦ የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም እንደሚገባ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

04 Jan, 12:32


የመሬት መንቀጥቀጥ እንዴት ይከሰታል?
መሬት የተዋቀረችው በሦስት ንብርብሮች ነው። የመሬት ማዕከላዊው ክፍል 'ኮር' ይባላል። ቀጥሎ የሚገኘው 'ማንትል' ነው። በመቀጠል 'ክረስት' ይመጣል። ይህ በዓይናችን የምናየው የመሬት ክፍል ነው።
ክረስት እና የማንትል የላይኛው አካል ቴክቶኒክ ፕሌትስ ከተባለው ድንጋይ የተሠሩ ናቸው። 'ቴክቶኒክ ፕሌትስ' ዝግ ባለ መልኩ ሁሌም ይጓዛሉ። በዚህ መካከል ግጭት እና መተፋፈግ ይፈጠራል። ይህ ነው የመሬት መንቀጥቀጥ ሆኖ በመሬት ገጽ ላይ ያሉ አካላትን የሚነቀንቀው እና የሚያፈራርሰው።
በቀላል አገላለጽ በዓይናችን ከምናየው መሬት በታች ያሉት ንብርብር አለቶች በተቃራኒ አቅጣጫ እየተጓዙ እርስ በርስ ሲተፋፈጉ አሊያም ሲፋጩ መሬት ትንቀጠቀጣለች ማለት ነው። 'ቴክቶኒክ ፕሌትስ' በየዓመቱ በጥቂት ሴ.ሜ እንቀስቃሴ ያደርጋሉ። እነዚህ መሬት የተዋቀረችባቸው አለቶች በተለያየ አቅጣጫ ነው የሚንቀሳቀሱት። ፍጥነታቸውም የተለያየ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ አለቶች እርስ በርስ ተፋፍገው ሊያልፉ ይችላሉ። ሌላ ጊዜ ደግሞ አንዱ ክፍል ከሌላኛው እየራቀ ሊሄድ ይችላል። እርስ በርስም የሚጋጩ አሉ። በተለያየ አቅጣጫ የሚጓዙ ድንጋዮች ሲተፋፈጉ ርዕደ መሬት ያስከትላሉ። በመተፋፈጉ መካከል የሚከሰተው ኃይል ከፍተኛ ስለሆነ የመሬት ማዕበል ይፈጥራል። የመሬት መንቀጥቀጥ የባሕር ጠለል ላይ ሲከሰት ደግሞ ከፍተኛ ማዕበል ይፈጠራል። ሱናሚ የሚባለውም ይህ ነው።

በዓለማችን በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ የመሬት ነውጦች ይመዘገባሉ። አብዛኛዎቹ ዝቅተኛ የሚባሉ እና በተለየ ቴክኖሎጂ የሚለዩ ናቸው። በጣም ከፍተኛ የሚባሉት ደግሞ ከተሞችን የማፈራረስ አቅም አላቸው። ይህ የመሬት ውስጥ ንቅናቄና መንቀጥቀጥ ጥንካሬ የሚለካበት መሳሪያ ሬክተር ስኬል ይባላል። ይህ መለኪያ ርዕደ መሬቱ የፈጠረውን ማግኒቲዩድ ይመዝናል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

04 Jan, 12:18


በአጠቃላይ ባለፉት 24 ሰዓታ ውስጥ በኢትዮጵያ ከ5 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች የተከሰቱ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ሦስቱ በሬከተር ስኬል ከ5 በላይ ሆነው ተመዝግበዋል። መንግሥት ክሥተቶቹን በዘርፉ ባለሙያዎች በቅርብ እየተከታተለ ይገኛል ያለው መግለጫው፤ በተለይ የርዕደ መሬቱ ማዕከል የሆኑት አካባቢዎችን በመለየት በ12 ቀበሌዎች ላይ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቦታው በማሰማራት የጉዳቱን መጠን አሠሣ እያደረገ ይገኛል ሲል ገልጿል። በእነዚህ ቀበሌዎች ከሚኖሩ 80 ሺህ ዜጎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማራቅ ለማሥፈር ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ነው በማለትም አስታውቋል። በማኅበራዊ አግልግሎት ሰጭ ተቋማት፣ በኢኮኖሚ ተቋማት እና በመሠረተ ልማት ላይ ሊኖረው የሚችለው ተጽዕኖ ላይ ክትትል እየተደረገ መሆኑንም አመልክቷል።

ርዕደ መሬቱ እስካሁን ባለው ሁኔታ በዋና ዋና ከተሞች የጎላ ተጽዕኖ አላደረሰም ያለው መግለጫው፣ ቢሆንም ዜጎች በባለሙያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ መልእክቶችን እንዲከታተሉና በጥብቅ እንዲተገብሩ አሳስቧል። የዘርፉ ባለሞያዎች በተለይም ወርሃ መስከረም እና ጥቅምት ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች የነበሩባቸው ወራቶች እንደሆኑ ገልጸዋል። በኅዳር ወር ጋብ ብሎ የነበረው ርዕደ መሬት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ሲሆን፤ ከእስካሁኑ በሬክተር ስኬል ከፍተኛው ርዕደ መሬት የታየውም ባለፉት ቀናት ነው።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

04 Jan, 12:18


መንግሥት የርዕደ መሬት በታየባቸው አካባቢዎች የጉዳቱን መጠን አሠሳ የሚያደርግ ቡድን ማሰማራቱን ገለፀ
26/04/2017 ዓ.ም
መንግሥት የርዕደ መሬት በታየባቸው አካባቢዎች ከተለያየ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ ባለሙያዎች ማሰማራቱን ገለፀ።

የመንግሥት ጉዳዮች ኮሙኒኬሽን ቅዳሜ፣ ታህሳስ 26/ 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ርዕደ መሬቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ 80 ሺህ ዜጎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማራቅ ለማሥፈር ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
መግለጫው አክሎም ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ርዕደ መሬቱ በታየባቸው አካባቢዎች ተሰማርተው የጉዳቱን መጠን አሠሣ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጿል።

በኢትዮጵያ ከ2017 አዲስ ዓመት ጀምሮ በአፋር፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች እየተደጋገሙ እና ንዝረታቸውም እስከ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ ድረስ እየተሰማ ይገኛል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ክሥተቶቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጠን እና በድግግሞሽ እያደጉ መሆናቸውን አስታውቋል።

በተለይም በዚህ ሳምንት በርዕደ መሬት መለኪያ እስከ 5 ነጥብ 8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ መንቀጥቀጥ መከሠቱን መረጃዎች ያሳያሉ ሲልም ገልጿል። በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ትናንት ለሊት 9:52 ሰዓት ገደማ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍ ያለ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ትናንት ሌሊት የነበረው የመሬት መንቀጥቀጡም በሬክተር ስኬል 5.8 ሆኖ መመዝገቡን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ አስታውቋል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

04 Jan, 10:18


የመምህራን እና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ለምክትል ርዕሳነ መምህራን ስልጠና ሰጠ።

ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም

ስልጠናው በተከታታይ የሙያ ማሻሻያ(ተሙማ) መርሀ ግብር አተገባበርን መሰረት አድርጎ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመምህራን ልማት ምክትል ርዕሳነ መምህራን መሰጠቱን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራን እና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበራ ስልጠናው በዋናነት በትምህርት ቤቶች ወጥ የሆነ ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ (ተሙማ) መርሀ ግብር ተግባራዊ እንዲሆን ዘርፉን የሚመሩ ምክትል ርዕሳነ መምህራን በቂ ግንዛቤ ፈጥረው መርሀ ግብሩን በአግባቡ ተግባራዊ እንዲያደርጉ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም በስልጠናው ከተከታታይ የሙያ ማሻሻያ መርሀ ግብር ባሻገር ከአዲስ ጀማሪ መምህራን (አጀመ) ጋር በተገናኘም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው መሰጠቱን ጠቁመው የስልጠናው ተሳታፊዎች ከመርሀ ግብሮቹ አተገባበር ጋር በተገናኘ ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት በማድረግ የተማሪዎች ውጤትና ስነ ምግባር እንዲሻሻል የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

ስልጠናውን የቢሮው የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ቀናሳ እንዲሁም የክፍለ ከተማ ሱፐርቫይዘር የሆኑት አቶ ታምሩ ሁጂሶ መስጠታቸውን የመምህራን እና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

04 Jan, 01:03


#ማስታወቂያ
ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምርት ተቋማት
   ባሉበት

ጉዳዩ ፦ በጥር  ወር 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው  የመዉጫ ፈተና  ውይይት ስለሚኖር እንድትሳተፉ ስለማሳወቅ፤

በ2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የተፈታኞችን ምዝገባ ለማካሄድ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተማሪዎችን መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል የሶፍት ዌር ቴምፕሌት በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ታህሳስ 28/2017ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ላይ የሚጀምር ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የሶፍት ዌር ቴምፕሌት አጠቃቀም ዙርያ ላይ በzoom meeting  ማብራሪያና ገለፃ ስለሚደረግ እንድትሳተፉ እያሳሰብን የzoom meeting  link ቀደም ብሎ የሚለቀቅ ይሆናል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

02 Jan, 18:15


ክፍት የሥራ ማስታወቂያ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ባለሙያዎችን አወዳድሮ በዝውውር መቅጠር ይፈልጋል፡፡

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

02 Jan, 15:59


የ2017 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የሪፎርም ተግባራት አፈጻጸም ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ ባለሙያዎች ገለጻ ተደረገ፡፡

ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የግማሽ ዓመት የሪፎርም ተግባራት አፈጻጸምን በሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ሊደረግ መሆኑ ተገጿል ፡፡ ድጋፍና ክትትሉ በነገው ዕለት በሁሉም ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች የሚካሄድ መሆኑን በሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት የተገለጸ ሲሆን በድጋፍና ክትትል መስፈርት ዙሪያ ለባለሙያዎች ገለጻ ተደርጓል፡፡

ቀደም ሲል ከቢሮው እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸምን እና የተግባር ምዕራፍ አጀማመርን መሰረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል መካሄዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀፍቱ ብርሀኑ ገልጸው አሁን የሚደረገው ድጋፍና ክትትል ቀደም ሲል በተካሄደ ተመሳሳይ ተግባር ትምህርት ጽህፈት ቤቶቹ የተሰጡ ግብረ መልሶችን የጋራ አድርገው ምን ያህል የማስተካከያ ስራ እንደሰሩ ለማየት የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አያይዘውም እንደገለጹት የሚደረገው የድጋፍና ክትትል ስራ ሲጠናቀቅ በቀጣይ ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የአንደኛ መንፈቅ ዓመት አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ ምዘና የሚካሄድ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የስራ ክፍሉም ምዘናውን ለማካሄድ በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስገንዝበዋል፡፡

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

27 Dec, 13:36


በማጠናከሪያ ትምህርት ስትራቴጂ ዙሪያ የቀረበ የሬድዮ ዝግጅት

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

27 Dec, 05:54


የመጀመሪያው የሱፐርቪዥን ክላስተር ማዕከላት የ6 ወር የስራ አፈጻጸም ምዘናን አስመልክቶ የተሰራ የሬድዮ ዝግጅት

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

25 Dec, 19:36


ፓርከር ሶላር ወደ ፀሐይ የተጠጋችው 6.2 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር (3.8 ሚሊዮን ማይል) ርቀት ላይ ነው።

ኒኮላ ፎክስ እንደሚሉት ይህ ርቀት በጣም የበዛ ቢመስልም በንፅፅር እጅግ ቅርብ ነው።

"እኛ ከፀሐይ 93 ሚሊዮን ማይል ርቀት ላይ ነው የምንገኘው።ለምሳሌ ፀሐይ እና መሬት አንድ ሜትር ርቀት ላይ ቢሆኑ ፓርከር ሶላር ከፀሐይ 4 ሴንቲ ሜትር ርቀት ላይ ነው ማለት ነው። ይህን ያህል ቅርብ ነው" ይላሉ።

መንኩራኩሯ ወደ ፀሐይ ስትጠጋ 1400 ዲ.ሴ ሙቀት ተቋቁማ ነው። የፀሐይ ሙቀት የመንኩራኩሯን ክፍሎች የማቅለጥ ኃይል አለው።

ፓርከር ሶላር 11.5 ሴንቲሜትር ስፋት ባለው ካርበን-ኮምፖሲት የተሸፈነች ቢሆንም ዓላማዋ ቶሎ ገብቶ መውጣት ነው።

መንኩራኩሯ የሰው ልጆች ከሠሯቸው ቁሶች እጅግ ፈጣን ስትሆን በሰዓት 430 ሺህ ማይል ትጓዛለች። ይህ ማለት ከለንደን ኒው ዮርክ በ30 ሰከንድ እንደመጓዝ ነው። ሲል ቢቢሲ ዘግቧል

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

25 Dec, 19:35


የአሜሪካው የሕዋ ምርምር ተቋም መንኩራኩር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ፀሐይ የመጠጋት ሙከራ እያደረገች ነው። ቢቢሲ

16/2017 ዓ.ም

ፓርከር ሶላር ፕሮብ የተባለችው መንኩራኩር እጅግ ከፍተኛ ሙቀት እና ላቅ ያለ ጨረር ተቋቁማ ወደ ፀሐይ የመጠጋት ሙከራ ታደርጋለች።
መንኩራኩሯ ለበርካታ ቀናት ከግንኙት ውጭ ስትሆን ሳይንቲስቶች የፀሐይን ቃጠሎ ተቋቁማ ይሆን ወይ የሚለውን በጉጉት እየተጠባበቁ ነው።

መንኩራኩሯ መትረፍ አለመትረፏን እ.አ.አ ታኅሣሥ 27 ይታወቃል ተብሏል።
ፓርከር ሶላር ይህን ሙከራ የምታደርገው ፀሐይ እንዴት እንደምትሠራ ለመረዳት ነው ተብሏል ።

የናሳ የሳይንስ ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ኒኮላ ፎክስ "ላለፉት መቶ ዓመታት ሰዎች ፀሐይን ሲመረምሯት ቆይተዋል። ነገር ግን የአንድ ሥፍራ ከባቢያዊ ሁኔታ ለማወቅ ተጠግቶ ማየት ያስፈልጋል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

"ስለዚህ የኮከባችንን ከባቢያዊ ሁኔታ ለማወቅ በአቅራቢያዋ መብረር አለብን ማለት ነው"
ፓርከር ሶላር ፕሮብ በአውሮፓውያኑ 2018 ነው ወደ ሶላር ሲስተም ማዕከላዊ ክፍል ያቀናችው።

መንኩራኩሯ እስካሁን 21 ጊዜ ፀሐይን ዞራለች በየወቅቱም ወደ ፀሐይ እየተጠጋች ትገኛለች። በአውሮፓውያኑ ገና ዋዜማ ግን ከምን ጊዜውም በላይ ወደ ፀሐይ ተጠግታለች።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

25 Dec, 13:13


የዩኒቨርሲቲዎች በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ እንደሚመደብ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017
ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብላቸው በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለፁ።
በትምህርት ዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በተቀናጀ መልኩ ማሻሻል የሚያስችል ስምምነት ተፈርሟል።
ስምምነቱን በትምህርት ሚኒስቴርና 47 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የቦርድ ሰብሳቢዎችና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ተፈራርመዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት፥ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በመሰረታዊነት ለመቀየር የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ወሳኝ ነው ብለዋል።
በተለይም ብቃት ያለው የሰው ሃይል ለማፍራትና ፋይዳቸው የጎላ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን ለማውጣት ጥራት ላይ መስራት ግዴታ መሆኑ በስምምነቱ ተካቷል ብለዋል።
ስምምነቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትክክለኛ መንገድ የሚሰሩና ተጠያቂነት ያለባቸው እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ሀገር የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በሳይንሳዊ ምርምር የሚያግዙ መሆን እንዳለባቸውም ነው የተናገሩት።
በሀገር የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑና የዜጎችን ሕይወት እንዲቀይሩ ሁሉም ተቋም ሃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት አለበት ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብላቸው በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ ይሆናል ያሉት ሚኒስትሩ፥ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያስመዘገቡ እኩል በጀት የሚመደብበት አሰራር ይቀራል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች የተጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃትና በጥራት እንዲፈፅሙ በተለይም ሙስናን ማጥፋት ግዴታ መሆኑንም አንስተዋል።
ሙስና የትውልድ ጸር በመሆኑ ለትውልዱ አርዓያ የሚሆን ዩኒቨርሲቲ መፍጠር እንደሚገባ ማስገንዘባቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

25 Dec, 12:57


የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎትዎን ለማዳበር መፅሐፍትን ያንብቡ

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

25 Dec, 11:03


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው ክትባቱ በሁሉም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች እንደሚሰጥ ጠቁመው በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮችም ሆኑ ሌሎች ባለድርሻ አካላት በትምህርት ተቋማት ተገኝተው ክትባቱን ለሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የክትባት ሂደቱ በተቀመጠው የጊዜ መርሀ ግብር እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው  አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው ክትባቱ በሁሉም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች እንደሚሰጥ ጠቁመው በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮችም ሆኑ ሌሎች ባለድርሻ አካላት በትምህርት ተቋማት ተገኝተው ክትባቱን ለሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የክትባት ሂደቱ በተቀመጠው የጊዜ መርሀ ግብር እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው  አስገንዝበዋል ።

ክትባቱ የሚሰጣቸው ዕድሜያቸው ከ9 እስከ 12 ሴት ተማሪዎች ሲሆን ክትባቱ ከታህሳስ 21 ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቆይ መሆኑ በመግለጫው ተጠቅሷል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

25 Dec, 10:40


ዕድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ለሆኑ ሴት ተማሪዎች የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ሊሰጥ መሆኑ ተገለጸ።

ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም

ክትባቱን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ ጋር በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የማህጸን በር ካንሰር ክትባት እድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ሆኖ ከዚህ በፊት ክትባቱን ላልወሰዱ ታዳጊ ሴት ተማሪዎች እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ ገልጸው ዘንድሮ በከተማ አስተዳደሩ ክትባቱን እንዲወስዱ በዕቅድ ከተያዙ 177,000 በላይ ታዳጊ ሴቶች ውስጥ 90% የሚሆኑት በትምህርት ተቋማት እንደመገኘታቸው በትምህርት ቤት ለሚሰጠው ክትባት ከፍተኛ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል።

የማህጸን በር ካንሰር በሀገራችን ኢትዮጵያ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በገዳይነቱ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ በሽታ እንደሆነ በተለያዩ ጥናቶች መረጋገጡን ዶክተር ዮሀንስ ጫላ ጠቁመው ክትባቱ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ መቆየቱን በመጥቀስ የዘንድሮ መርሀ ግብር ስኬታማ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

24 Dec, 16:28


ዩኒቨርሲቲው ለ5 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ለአምስት የዩኒቨርሲቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታውቋል፡፡



በዚህም መሰረት፡-

ዶ/ር አለማየሁ ተ/ማሪያም……. በስፔሻል ኒድስ ኤጁኬሽን
ዶ/ር አስራት ወርቁ ……………. በጂኦቴክኒክስ ኢንጂነሪንግ
ዶ/ር መኮንን እሸቴ ……………. በፕላስቲክ ሰርጀሪ
ዶ/ር ሚርጊሳ ካባ ……………… በፐብሊክ ሄልዝ
ዶ/ር ተባረክ ልካ ………………. በዴቨሎፕመንት ጂኦግራፊ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝተዋል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

24 Dec, 10:14


በ1ኛ ሩብ አመት በተካሄደ ድጋፍና ክትትል የተሻለ አፈጻጸም ካስመዘገቡ የትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ በሆነው ነጻነት ጮራ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ልምድ ልውውጥ ተካሄደ።

ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም

በልምድ ልውውጡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱን ጨምሮ የቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እና የሪፎርም አስተባባሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመርሀ ግብሩ የነጻነት ጮራ ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ላይን በሪሁን ትምህርት ቤቱ በ2017 ዓ.ም 1,289 ተማሪዎችን ተቀብሎ በ133 መምህራን የመማር ማስተማር ስራውን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው ትምህርት ቤቱ ወላጆችን ጨምሮ የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብ በማስተባበር ባከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል።

ትምህርት ቤቱ በ2017 ዓ.ም ከሪፎርም ስራዎች ባሻገር ቢሮው ያወረደውን የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ስትራቴጂ ውጤታማ ለማድረግ መምህራንን የስራው ባለቤት በማድረግ እያከናወነ የሚገኘው ተግባር ለሌሎች ተቋማት ተሞክሮ መሆን የሚችል ተግባር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸው የትምህርት ቤቱ አመራሮች በቅንጅት መስራታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ያበረከተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ማረጋገጣቸውንም አስታውቀዋል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በላይ ነጋሽ በበኩላቸው ነጻነት ጮራ ትምህርት ቤት በክፍለ ከተማው በአፈጻጸማቸው የተሻሉ ከሆኑ ተቋማት መካከል አንዱ መሆኑን በመግለጽ ትምህርት ቤቱ ውጤታማ የሆነበትን አሰራር ወደሌሎች የማስፋት ስራ እንደሚሰራ አመላክተዋል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

07 Dec, 03:32


ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
ባሉበት

ጉዳዩ፦ አዲስ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ
እንድትልኩ ስለማሳሰብ ይሆናል፤

የፌዴራል መንግስት አስፈፃሚ አካላት ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ 1263/2014 ዓ.ም እና የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ለማቋቋም በሚኒስትሮች ምክርቤት በወጣ ደንብ ቁጥር 515/2014 ዓ.ም መሰረት በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠበቅ እና ለመከታተል ያስችለው ዘንድ በመመሪያ 987/2016 ዓ.ም አንቀፅ 17 ንኡስ አንቀፅ 2 መሰረት አዲስ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ ወቅቱን ጠብቆ ለባለስልጣኑ መላክ እንዳለባችሁ ተደንግጓል፡፡
በመሆኑም በተቋማችሁ ፈቃድ በተሰጣችሁ ትምህርት መስኮች፣ ትምህርት ደረጃ፣ መርሃ ግብር እና ካምፓስ በ2017 ዓ.ም የመዘገባቸውን አዲስ ተማሪዎች ብቻ ከዚህ በፊት በተላከው ቅጽ መሰረት ዝርዝር መረጃውን ከታህሳስ 1/2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 15/ 2017 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡ 

ሲል የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በማህበራዊ ገፁ አሳስቧል ።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

07 Dec, 03:17


በትምህርት ቤቶች ዙሪያ አዋኪ ድርጊቶችን የፈፀሙ 879 ተቋማት እርምጃ ተወሰደባቸዉው

የአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ፤ በትምህርት ቤቶች ዙሪያ አዋኪ ድርጊቶችን ሲፈፅሙ የተገኙ 879 ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጉዳዩን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በዚህም እርምጃ የተወሰደባቸዉ 184 ጫት ቤቶች፣ 48 መጠጥ ቤቶች፣ 12 ፔንሲዮኖች፣ 112 ጠላና መሰል አልኮል የሚሸጥባቸዉ ግሮሰሪዎች፣ የድምፅ ብክለትን ያስከተሉ 122 እንድሁም 220 የቆሻሻ እና መሰል አዋኪ ድርጊቶች የሚፈፀምባቸዉ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡

ኦፕሬሽኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ እና የአዲስ አበባ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በቅንጅት አከናዉነዉታል፡፡

በቀጣይም በትምህርት ተቋማቶች ዙሪያ ያሉ አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈፅሙ ተቋማት
ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ተገልጿል፡፡

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

03 Dec, 12:51


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በትምህርት ተቋማት የመስክ ምልከታ አካሄዱ።

ህዳር 24/2017 ዓ.ም
የመስክ ምልከታውን ከየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከአቶ ፈይሳ ወዳጆ ጋር በመሆን በክፍለ ከተማው ወረዳ 1 በሚገኙት ህዝባዊ ሰራዊት እና ቅዱስ ማርቆስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ነው ያካሄዱት።

ዶክተር ዘላለም በህዝባዊ ሰራዊት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየተገነባ የሚገኘውን የG+4 ህንጻ ያለበትን ደረጃ ከተመለከቱ በኋላ በትምህርት ቤቱ በመማሪያ ክፍል እጥረት ምክንያት እየሰጠ የሚገኘውን የፈረቃ ትምህርት ለማስቀረት እየተገነባ የሚገኝ ህንጻ በመሆኑ ግንባታውን እያከናወኑ የሚገኙ አካላት በፍጥነት ህንጻውን በማጠናቀቅ ትምህርት ቤቱ ከፈረቃ ትምህርት እንዲወጣ ሌት ከቀን መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

በተመሳሳይ ቅዱስ ማርቆስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በርካታ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ እንደመገኘቱ በትምህርት ቤቱ ለማስፋፊያ ግንባታ የተለየውን ቦታ በመመልከት ግንባታው ባስቸኩዋይ እንዲጀመር አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ እንዲሰራ ኃላፊው የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

02 Dec, 14:22


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የጉዋንጉዋን አለም አቀፍ የትምህርት ተቋም ቡድን በሃገራችን በመገኘት የትምህርት ስርዓቱን ለማየት በመቻሉና በቀጣይም የትምህርት ስርዓቱን ለማየት የተማሪዎች የልምድ ልውውጥ እቅድ በማቀዱ በራሳቸውና በትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የጉብኝት ቡድኑ ጉብኝት ባደረገባቸው ትምህርት ቤቶች 12 የእግር ኳሶች ፤ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል አንድ ላፕቶፕ ኮምፒውተርና የመዝለያ ገመዶች በስጦታ አበርክተዋል፡፡

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

02 Dec, 14:19


ተቋም የመጡ ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር የሚገኙ ሶስት ትምህርት ቤቶች ላይ ጉብኝት አደረጉ፡፡

(ህዳር 23/2017 ዓ.ም) የኮርያው ጉዋንጉዋን አለም አቀፍ የትምህርት ተቋም ተወካዮች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኘውን የቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፤ ጠመንጃ ያዥ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና መሪ ህዳሴ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የጉብኝቱ አባላት በቀጣይ የኮሪያን ተማሪዎች ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት እንዲሁም የኢትዮጵያን ተማሪዎች ወደኮርያ በመውሰድ የትምህርት ስርዓትና ባህል ልውውጥ ለማድረግ ማቀዳቸዉ ተገልጻል፡፡

የጉብኝት ቡድኑ አባላት በትምህር ቤቶቹ የተመለከታቸውን አንኳር ጉዳዮች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በመገኘት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የቢሮው ማኔጅመንት አባላትና ዳይሬክተሮች በተገኙበት ውይይት ያደረጉ ሲሆን፤ በትምህርት ቤቶቹ ለተደረገላቸው አቀባበልም ምስጋና አቅርበዋል

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

28 Nov, 06:31


19ኛውን የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በአል አስመልክቶ በተማሪዎች መካከል ሲካሄድ የቆየው የጥያቄና መልስ ውድድር ማጠናቀቂያ ስነስርአት

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

28 Nov, 03:27


ፕሬስ ሪሊዝ

(ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በስራና ክህሎት ቢሮ የተደረገ የክትትልና ቁጥጥር ሪፖርት፣የእውቅና ፍቃድ፣የድንገተኛ ኢንስፔክሽን ግኝት እና የሙያ ብቃት ምዘና ሪፖርት የሚቀርብበት መርሃ-ግብር አዘጋጅቷል፡፡

በመርሃ-ግብሩ ላይ ከስራና ክህሎት ቢሮ የሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች፣በባለስልጣኑ እና በዘጠኙ ቅ/ጽ/ቤት የሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች፣በከተማችን ያሉ የመንግስትና የግል የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚገኙ ይሆናል፡፡ 

መርሃ-ግብሩ ህዳር 19/2017 ዓ.ም በኢሊያና ሆቴል ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ይከናወናል፡፡

ከመርሃ-ግብሩ የሚጠበቀው የማሰልጠኛ ተቋማት የተገኙትን ግኝቶች መሰረት በማድረግ ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን በመለየት የተሻለ የስልጠና ተቋም እንዲሆኑ ማስቻል፣አሰልጣኞችና ሰልጣኞች በአዲሱ የሙያ ብቃት ምዘና እንዲመዘኑና ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡ ማስቻል ነው፡፡   

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

26 Nov, 09:31


ለብርሃን ዐይነ ስዉራን ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ት/ቤት ተማሪዎች የተሰጠ የህይወት ክህሎት ስልጠና

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

26 Nov, 08:40


በት/ቤቶችና ወረዳዎች በተካሄደ ምልከታ ዙሪያ የተሰናዳ ልዩ የሬድዮ ዝግጅት

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

23 Nov, 14:13


ዓለም አቀፍ የህጻናት ቀን አከባበር በአብዮት እርምጃችን ት/ቤት

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

22 Nov, 08:46


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኤግዚቪሽን ጎበኙ።

ህዳር 13/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች የብልፅግና ፓርቲ የአምስተኛ ዓመት ምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በትላንትናው ዕለት ተመርቆ የተከፈተውን ኤግዚቪሽን ጎብኝተዋል።


በጉብኝቱ ላይ በከተማ አስተዳደሩ ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ አንኳር ስራዎች በቪአር ፣ በቪዲዮ ፣ በፎቶና በሞዴሎች ቀርበው ገለፃ
የተሰጠባቸው ሲሆን በጉብኝቱ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ
ወንድሙ ዑመር እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል ።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

21 Nov, 11:51


19ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት በተማሪዎች መካከል የተደረገ የጥያቄና መልስ ውድድር

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

21 Nov, 06:53


የ19ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በተመለከተ የተደረገ የፓናል ውይይት

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

20 Nov, 18:27


በትምህርት ተቋማት በተካሄደ የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

ህዳር 11/2017 ዓ.ም
ድጋፍና ክትትሉ የተቋማቱ የዝግጅት ምዕራፍ አጀማመር እና የተግባር ምዕራፍ አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ የተካሄደ ሲሆን በውይይቱ በድጋፍና ክትትሉ የተሳተፉ አካላት ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ዘንድሮ የቢሮው ማኔጅመንት አባላት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በሁሉም የትምህርት ተቋማት ድጋፍና ክትትሉ የሪፎርም ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ መካሄዱን ገልጸው ድጋፍና ክትትሉ በዋናነት በየተቋማቱ የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት አድርጎ እንደመካሄዱ  በቀጣይ ግብረ መልሱን መሰረት በማድረግ ተቋማቱን ወደ ተቀራረበ የአፈጻጸም ደረጃ ለማምጣት በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል።

በዛሬው ውይይት  በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች እና በወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች የተካሄደ የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ መቅረቡን የቢሮው የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋገኘሁ ለገሰ ጠቁመው በቀጣይ ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ የወረዳ እና ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት  የክትትልና ድጋፉ ግብረ መልስ ቀርቦ ውይይት የሚካሄድ መሆኑን አስገንዝበዋል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

18 Nov, 09:57


የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ተጀመረ።
    __  // ____
(ህዳር 09/2017 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የትምህርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግን አስጀምሯል።
ተማሪዎች መደበኛ የትምህርት ጊዜያቸውን ሳይጎዱ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የስፖርት ሊግ መርሃ ግብሩ ተዘጋጅቶ ወደተግባር ገብቷል።   የተማሪዎች ከመደበኛ ትምህርትቸው ጎን ለጎን በተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች መሳተፍ የተማሪዎችን አካላዊ፣ ማህበራዊ፣ ስነ ልቦናዊ ጠቀሜታው የጎላ ነው።
ከዚህ አኳያም በ2017 የትምህርት ዘመን በምስራቅ ቀጣና የተደራጀው የሀረሪ ክልል በሁሉም ትምህርት ቤቶች በቮሊቦል፣ በእግር ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ፣ በእጅ ኳስ፣ በአትሌትክስ፣ በጂምናስቲክስ፣ በጠረዼዛ ኳስ እና በባህላዊ ስፖርት አይነቶች የክልሉ አመራሮች ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የትምህርት ቤት አመራሮች በተገኙበት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀትተከፍቷል።
ስፖርታዊ ውድድሩ አመቱን ሙሉ የሚቀጥል ሲሆን ከሀረሪ ክልል በተጨማሪም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት የማስጀመሪያ መድረክ ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ገብቷል፡፡

በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ደግሞ በደቡብ ቀጣና ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በደቡብ ኢትዮጵያ በጋሞ ዞንና በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በቮሊቦልና በእግር ኳስ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በእግር ኳስ ፣ በቮሊቦል እና በአትሌትክስ ስፖርት በደመቀ ሁኔታ ተጀምሯል፡፡

በሌሎች የቀጣና አደረጃጀቶች ስር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድሮቹን በቅርቡ የሚያስጀምሩ ይሆናል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

16 Nov, 09:29


የመንግስት ት/ቤቶች እውቅና ፈቃድ አሰጣጥ

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

15 Nov, 13:35


በዚህ የውይይት መድረክ በአጠቃላይ 32 የሚሆኑ የት/ተቋማት ባለቤቶችና የት/አመራሮች ተገኝተው ውይይት ያደረጉ ሲሆን በክፍተት የተገኙባቸውን ጉዳዮች ሙሉ በሙሉ ስህተት መሆናቸውን በማመንና በመቀበል ከተደረገው ምልከታ በኋላ ባለው ጊዜ ያስተካከሉ መሆኑን ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡ በማጠቃለያውም በቀጣይ ምልከታው የሚቀጥልና ተቋማትም የጀመሩትን የእርምት እርምጃ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቅጣጫ በማስቀመጥና መተማመን ላይ በመድረስ የእለቱ ውይይት በሙሉ መግባባት ተጠናቋል፡፡
የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት ምንጭ በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በማህበራዊ ድረ ገጹ አስፍሯል፡፡

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

15 Nov, 13:35


የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤቱ በድንገተኛ ኢንስፔክሽን ምልከታ ከፍተኛ የስርዓተ ትምህርት ጥሰት ከታየባቸው የትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት አደረገ፡፡

ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ በድንገተኛ ኢንስፔክሽን ምልከታ ከፍተኛ የስርዓተ ትምህርት ጥሰት ከታየባቸው ት/ቤቶች ጋር ውይይት አደረገ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት በ2017 በጀት ዓመት በአንደኛ ሩብ ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት ድንገተኛ ኢንስፔክሽን ትግበራን በ148 ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች ቁጥጥር ማድረጉን ገልጾ፡፡
በዚህም ትግበራ የስርአተ ትምህርት ጥሰት ማለትም ያልተፈቀዱ የትምህርት አይነቶችን የሚያስተምሩ፣ከማስተማሪያው ቋንቋ በተጨማሪ የትምህርት አይነቶችን በመለየት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት የሚሰጡ እና የሌላ አካል የሆነና ያልተፈቀደ መጽሐፍ በራሳቸው ፍቃድ በማሳተም ለማስተማሪያነት የሚጠቀሙትን በመለየት መድረክ በማዘጋጀት የማወያየት ስራ መሰራቱን በመግለጽ ፤በእለቱ ተለይተው የተጠሩትን 35 የሚሆኑ ተቋማት የታየባቸውን የስርአተ ትምህርት ጥሰት ጉዳዮች በትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መስፍን ተ/ማሪያም በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱም የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሀም ምትኩ የሰርአተ ትምህርት ጥሰት በዜጎች ላይ የሚፈጸም አስጸያፊ የሆነ ተግባር እና የመንግስትን አቅጣጫ አለመከተል መሆኑን አስረግጠው አስረድተዋል፡፡

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

15 Nov, 12:25


በሀገር አቀፍ የተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ሥራዎች ውድድር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አንደኛ በመሆን አጠናቀቀ ፡፡

ህዳር 6/2017 ዓ.ም
9ኛው ሀገር አቀፍ የተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ሥራዎች ውድድርና አውደርዕይ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት በመካሄድ ላይ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፣ ስቴም ፓወር ፣ ስቴም ሲነርጂ ፣ ከጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት እና ኢጁኬሽን ፎረም ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የዓለም አቀፍ የሳይንስ ቀንን ምክንያት በማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ9ኛ ጊዜ ከህዳር 2 እስከ 6/2017 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በካሄደው የሳይንስ ዓውደ ርዕይ ላይ በተደረገ ፈጠራ ስራ ውድድር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ አንደኛ በመሆን አጠናቋል፡፡

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

13 Nov, 13:06


ስለ ፈተና ቢጋር (እቅድ) አዘገጃጀት

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

13 Nov, 13:03


ለ19ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ከሚከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መካከል…

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

13 Nov, 09:04


ስለመማሪያና ማስተማሪያ መጽሀፍ ግምገማ የተዘጋጀ የሬድዮ ዝግጅት

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

13 Nov, 02:51


9ኛው ሀገር አቀፍ የተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ሥራዎች ውድድርና አውደ ርዕይ ተጀመረ
=====================
9ኛው ሀገር አቀፍ የተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ሥራዎች ውድድርና አውደርዕይ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ተጀምሯል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት መሪ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉቀን ንጋቱ አውደርዕዩን በከፈቱበት ወቅት ተማሪዎችንና መምህራንን በማበረታታትና በማነቃቃት ለተሻለ የፈጠራ ሥራዎች ዝግጁ እንዲሆኑ የሚረዳ በመሆኑ ትምህርት ሚኒስቴርም የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።

ዶ/ር ሙሉቀን አያይዘውም መምህራንና ተማሪዎች መድረኩን ለእርስ በርስ የልምድ ልውውጥ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ጠቅሰው የፈጠራ ሥራዎችም ወቅታዊ ችግሮችን በመፍታት ሂደት የነገይቱን ሀገራችን ችግሮች ታሳቢ እንዲያደረገ አሳስበዋል፡፡

አገር አቀፍ የስቲም ፓወር ዳይሬከተር ዶ/ር ስሜነው ቀስቅስ በበኩላቸው የሳይንስ ትምህርቶችን በተግባር አስደግፎ በማስተማርና የፈጠራ ሥራዎችን የመደገፍ ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ጠቅሰዋል። የተሠሩ ሥራዎች ተስፋ ሰጪና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን ማፍራት የተቻለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ስሜነው አክለውም የበለፀጉ አገሮች እዚህ ደረጃ ሊደርሱ ያቻሉት ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው በመሥራታቸው እንደሆነ ጠቁመው የአገራችንን የፈጠራ ሥራዎች ይበልጥ ለማበረታታትና ውጤታማነቱንም ለመጨመር ከትምህርት ቤት እስከ አገር አቀፍ ደረጃ ያሉትን መሰል መድረኮች ከማጥናከር ጎን ለጎን በአህጉርና ዓለም አቀፍ ደረጃም ጭምር ለማመቻቸት እየተሠራ መሆኑንም ገልፀዋል።
የሥራ ፈጠራ ውድድሩና አውደርዕዩ ለቀጣይ ሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ መሆኑም ተመላክቷል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

13 Nov, 00:30


ወ/ሮ አበበች አያይዘው እንደገለፁት  ክትትልና ድጋፉ በቅንጅታዊ ስራዎች የተሰሩ ሥራዎችን በማየት ቀጣይ የትምህርት ስራውን ስኬታማ ለማድረግ  ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ ወደ ተግባር ምዕራፍ ለመግባት የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም በሁሉም የትምህርት ተቋማት ተቀራራቢ አፈጻጸም እንዲኖር አቅም ለመፍጠር የራሱ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አብራርተዋል::

የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋአገኘሁ ለገሰ በበኩላቸው ከማእከል እስከታች ወረዳና ትምህርት ቤቶች ድረስ ወርዶ የትምህርት አፈጻጸም ስራዎች በተመሳሳይ አሰራርና ወጥ የሆነ ስርዓት እንዲዘረጋ  የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመው፤ ከዚህ በፊት የነበሩ የክትትልና ድጋፍ ግብረመልሶች ለክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ቀርቦ ክትትል ድጋፍ ሲደረግ የቆየ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በቀጣይም በሚቀርቡ የድጋፍና ክትትል ስራ ግብረመልስ ውጤት ለወረዳ ስራ አስፈጻሚ ቀርቦ የድጋፍና ክትትል ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡ በገለፃው ላይ ለተነሱ የግልጽነት ጥያቄዎችም ማብራሪያ ሰጥተዋል ፡፡

በገለፃው ወቅት የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ሃፍቱ ብርሃኔ  የክትትልና ድጋፉን አስፈላጊነትና ዓላማ እንዲሁም ምንነትና ይዘቶች የያዘ ሰነድ በዝርዝር አቅርበዋል ፤ በሰነዱም የድጋፍና ክትትሉ ባለሙያዎች ሊከተሉት የሚገባ የግብረ መልስ አሰጣጥ ሂደቶች ላይ  ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል::

በዚህ ለሁለተኛ ጊዜ በሚደረግ ድጋፍና ክትትል ስራ ከቢሮ ፤ ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ የተውጣጡ 415 የሚሆኑ የመደገፍ አቅማቸው ከፍተኛ የሆነ ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮች የሚሳተፉ ሲሆን በ 458 በሚሆኑ 1 ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፤አዳሪ ትምህርት ቤቶችና የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች  በመገኘት ድጋፍና ክትትሉን እንደሚያደርጉ በገለፃው ተጠቁሟል።

📻📻📻📻📻📻📻📻📻📻📻

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

13 Nov, 00:15


ለተቋማት የሚደረግ ድጋፍና ክትትል በትምህርት ተቋማት መካከል ተቀራራቢና ውጤታማ አፈፃፀም በዋናነት በተማሪ ውጤትና ስነምግባር መሻሻል ከፍተኛ ሚና እንዳለዉ ተገለጸ፡፡
 
ህዳር 3/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት የ2017 በጀት ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀምና የተግባር ሥራዎች አጀማመር ዙሪያ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ስር ለሚገኙ የወረዳ ትምህርት ፅ/ቤቶች ፣1ኛ ደረጃ ፣ መካከለኛ ደረጃ እና አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና ለአዳሪ ት/ቤቶች ጨምሮ ከ458 በላይ የትምህርት ተቋማት ላይ ክትትልና ድጋፍ ለሚያደርጉ ባለሙያዎች የድጋፍና ክትትል ሂደቱን እና የሚጠበቀውን ሂደት በማስመልከ ገለፃ አደረ::

በገለፃው ወቅት የስራ አቅጣጫ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፉ ኃላፊ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የዝግጅት ምዕራፍ ለትምህርት ሴክተሩ ዋና ዋና ተግባራት የሚከናወንበት ወቅት መሆኑን ጠቅሰው በመጀመሪያ ምዕራፍ የተከናወኑ የቁልፍ አፈፃፀም አመላካች ሥራዎችን ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የታዩ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶችን ለማረም በሚያስችል መልኩ እቅድ መታቀዱንና እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የተሄደበትን ርቀት በድጋፍና ክትትሉ በሚደረግ ምልከታ እንደሚታይ አብራርተዋል ፡፡

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

09 Nov, 11:44


የአ.አ ምክር ቤት አባላት በት/ቢሮ ባደረጉት ምልከታ ዙሪያ የተሰናዳ የሬድዮ ዝግጅት

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

05 Nov, 14:11


ዶክተር ዘላለም አያይዘውም በኢ-ስኩል ሲስተም አማካይነት በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች የ2017ዓ.ም የተማሪ ቅበላ ኦን ላይን በማካሄድ ወደ መማር ማስተማር ስራ መገባቱን ገልጸው ቢሮው በያዝነው የትምህርት አመት የተማሪዎችን የሒሳብና እንግሊዘኛ ውጤት ለማላቅ ስትራቴጂ ነድፎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ በመግለጽ የተማሪዎች የምገባ አገልግሎትም ሆነ ዩኒፎርምን ጨምሮ ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶች ከመሰራጨታቸው ባሻገር በኮሪደር ልማት ምክንያት የመኖሪያ አከባቢ ለቀየሩ ነዋሪዎች በሄዱበት አከባቢ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

በመርሀ ግብሩ በኢ-ስኩል ሲስተም የተካተቱ ስድስት ሞጁሎች ዝርዝር በቢሮው የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ደረጀ ዳኜ የቀረበ ሲሆን የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ በቀረቡት የአንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን አቅርበው ምላሽ ተሰቷል።

የቋሚ ኮሚቴ አባላትም በቢሮ የተቋቋመውን የህጻናት ማቆያና ጂም ጎብኝተዋል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

05 Nov, 14:10


በትምህርት ዘርፍ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የሴቶች ወጣቶችና ህጻናት ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ገለፁ ።

ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የሴቶች ወጣቶችና ህጻናት ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አባላት የተቋሙን የአንደኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም የቢሮው የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በተገኙበት ገምግሟል።

ቢሮው በዝግጅት ምዕራፍ አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን እና የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አዘጋጅቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ በማድረግ ወደተግባር መግባቱን በመገምገም በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ ታስቦ የዛሬውን መርሀግብር ማዘጋጀት ማስፈለጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የሴቶች ወጣቶችና ህጻናት ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ዘይነባ ሽኩር አመላክተዋል።

በዝግጅት ምዕራፍ ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል የ2016 ዓ.ም አፈጻጸምን በመገምገም እና የ2017 ዓ.ም እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር መገባቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ለቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ገለጻ ባደረጉበት ወቅት አስረድተዋል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

05 Nov, 12:47


በእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ውጤት መሻሻል ዙሪያ አቶ ተክለሚካኤል አለሙ ከኤፍ ኤም 94.7 ጋር ያደረገው ቆይታ

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

05 Nov, 08:05


ስርዓተ ጾታን መሰረት ባደረገ የማስተማር ስነዘዴ ዙሪያ የተሰራ የሬድዮ ዝግጅት

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

04 Nov, 13:48


👉የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

👉በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦
➡️ በዌብሳይት :
👇👇👇👇👇 https://placement.ethernet.edu.et 
➡️ በቴሌግራም :
👇👇👇👇
https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

👉ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።

👉ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

03 Nov, 08:13


የመሰረታዊ ጎልማሶች ትምህርት መጽሐፍ ትውውቅን በተመለከተ ከጣቢያችን ጋር የተደረገ ቆይታ

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

03 Nov, 06:23


ስርዓተ ጾታን መሰረት ያደረገ የማስተማር ስነ ዘዴን (Gender responsive pedagogy) በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።


ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም
ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ትግበራ ቡድን የተሰጠ ሲሆን በመርሀ ግብሩ በየትምህርት ቤቱ የሚገኙ የስርአተ ጾታ ክበባትን የሚደግፉ ምክትል ርዕሳነ መምህራን እና የክበባቱ ተጠሪ መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል።


አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የዘርፈ ብዙ ጉዳይን ትኩረት የሰጠ በመሆኑ ተግባራዊነቱ በመማር ማስተማር ሂደቱ የስርአተ ጾታ ጉዳይን ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው መዘጋጀቱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ትግበራ ቡድን መሪ አቶ ይልማ ተሾመ አስታውቀዋል።


ቡድን መሪው አክለውም ስልጠናው በየትምህርት ቤቱ የተደራጁ የስርአተ ጾታ ክበባትን በማጠናከር ጾታን መሰረት አድርገው የሚስተዋሉ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያግዝ ግንዛቤ የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመው ስልጠናው ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች መሰጠቱን ገልጸዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው በበኩላቸው በትምህርት ፖሊሲው የተካተተው የስርዓተ ጾታ ጉዳይ በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ እንዲሆን ለትምህርት ማህበረሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አመላክተዋል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

02 Nov, 19:08


የገላን ልዩ የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤተ ተማሪው ኤባ ዓለሙ በበኩሉ፥ በትምህርት ቤቱ የከተማ ግብርና መኖሩ ሳይንስን በተግባር በማረጋገጥ ስለ ግብርና በቂ እውቀት እንዲኖራቸው ማድረጉን ጠቅሷል።
ተማሪዎቹ አክለውም ከትምህርት ቤት ውጪ በየአካባቢያቸው በጓሮ አትክልት እና በአረንጓዴ ልማት የመሳተፍ የአስተሳሰብ ለውጥ እንዳመጡበትም ገልጸዋል።
የትምህርት ቤቶቹ ርዕሰ መምህራን እንዳሉት በትምህርት ቤቶች የከተማ ግብርና መጀመሩ በርካታ ፋይዳ አለው ብለዋል።

የደጃዝማች ወንድይራድ ከፍተኛ ሁለተኛ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ካሱ ቱምሳ፥ ተማሪዎች እያንዳንዱን አዝዕርትና ፍራፍሬ ከብቅለት ጀምሮ ለፍሬ እስኪበቃ የሚያልፍበትን ስነህይወታዊ ዑደት በአግባቡ እንዲያውቁ ማስቻሉን ጠቅሰዋል።

የገላን ልዩ የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት ርዕሰ-መምህር ካሳሁን መርጋ በበኩላቸው፥ የከተማ ግብርናው በትምህርት ቤት ደረጃ የማስተማር ስነዘዴን ተግባር ተኮር ከማድረጉ ባለፈ የስራ ባህልን መቀየሩን ገልጸዋል።
ርዕሳነ መምህራኑ አክለውም የከተማ ግብርናው በተለይ በከተማ ያሉ ተማሪዎች የግብርና ሥራን እንዲያውቁ እንዲሁም እፅዋትን የመትከልና የመንከባከብ ባህል እንዲኖራቸው ማድረጉን ገልጸዋል።
በትምህርት ቤታቸው የከተማ ግብርናን እውን በማድረጋቸው ምርት ለሠራተኞችና ለገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ ማስቻሉንም አንስተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፋሩቅ ጀማል፤ ትምህርት ቤቶች በከተማ ግብርና ትግበራ ቀዳሚ መሆናቸውን አንስተዋል።
እስካሁን 650 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ወደ ልማቱ የገቡ ሲሆን፥ የምግብ ምርት ከማምረት ባለፈ ተማሪዎቻቸው ስለ እርሻ በተግባር የተደገፈ እውቀት እንዲይዙ በማድረግ እየተጠቀሙበት ነው ብለዋል።
በቀጣይም ሌሎች ትምህርት ቤቶች ተሞክሮውን ወስደው እንዲተገብሩና በመዲናዋ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲያግዙ፣ ራሳቸውም በገቢ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይሰራል ነው ያሉት።
ኮሚሽኑም ሙያዊ ስልጠና እና የግብዓት ድጋፍ ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ሲል የዘገበው ኢ ዜ አ ነው።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

02 Nov, 19:08


በአዲስ አበባ 650 ትምህርት ቤቶች የከተማ ግብርናን ለተግባር ትምህርት እያዋሉት ነው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2017

በአዲስ አበባ 650 ትምህርት ቤቶች የከተማ ግብርናን ለተግባር ትምህርት እያዋሉት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፋሩቅ ጀማል ገለጹ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በመደበኛው ከግብርና ስራ በተጨማሪ የከተማ ግብርና ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡
በአዲስ አበባም በአትክልት እና ፍራፍሬ፣ በእንስሳት፣ በዶሮ እንዲሁም በንብ ማነብ ላይ ከግለሰብ እስከ ተቋማት ተሳትፎ እያደረጉ ናቸው።
በመዲናዋ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችም በግቢያቸው የሚገኙ ክፍት ቦታዎችን በጓሮ አትክልት እያለሙ ይገኛሉ።
የደጃዝማች ወንድይራድ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የገላን የወንዶች አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የከተማ ግብርናን በመተግበር ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ተማሪ ብሌን ዓለሙ እና ተማሪ ረቂቅ ይልቃል በንድፈ-ኃሳብ የሚማሩትን የእርሻ ትምህርት በትምህርት ቤቱ የከተማ ግብርና በተግባር ሙከራ በመፈተሽ የእውቀት አድማሳቸውን እያሰፉ መሆኑን ተናግረዋል።

FM 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ

18 Oct, 13:35


የሬድዮ ዝግጅት በደጃዝማች ወንድይራድ ት/ቤት ስለተደረገው ጉብኝት

2,035

subscribers

1,133

photos

412

videos