ከ ሸዕባን ወር ጋር የተያያዙ አንዳንድ ምክሮች📜
أولا : يجـب قضـاء الصـــــوم لمن أفطر أياما من رمضان الماضي قبـل أن يدخل رمضان القادم.
አንደኛ፦ ከዚህ በፊት የረመዳን ቀዷዕ ያለበት አካል በዚሁ በሸዕባን ወር ውስጥ መጪው ረመዳን ሳይገባበት ቀዷዕ ሊያወጣ ግድ ይለዋል።
ثانيا : يجب تعلم أحكام الصيـــــــام قـبـل دخـــــــول رمـضـــــــان القـــــــادم.
ሁለተኛ፦ መጪው ረመዳን ከመግባቱ በፊት የፆም ህግጋቶችን መማር ግድ ይላል።
ثالثا : مـن السنة الإكثـار مـــن الصيــــام فـي شـعبـــــــان
ሶስተኛ፦ በሸዕባን ወር ፆምን አብዝቶ መፆም ከነብያችን ሱና ይመደባል።
رابعا: من هدي السلف الإكثار من قـــراءة القرآن في شعبــان.
አራተኛ፦ ከቀደምት ሰለፎች ተግባር ውስጥ ቁርዓንን በዚህ በሸዕባን ወር ውስጥ አብዝቶ ማንበብ ነው።
خامسا : لايجـوز تخصيـص يوم أو ليلة النصف من شعبان بعبــادة خاصـة
አምስተኛ፦ በሸዕባን አጋማሽ ላይ የዚያን ቀንንም ሆነ ሌሊትን ለየት ባለ ኢባዳ መለየት አይቻልም።
سادسا: لايـجــوز صيــام يــــوم الشـــــــك وهـو يـــــوم الثـلاثين من شعبان
ስድስተኛ፦ አጠራጣሪ ቀን የሸዕባን 30ኛ ቀንን መፆም አይቻልም።
👉(አንዳንድ ምክንያቶች ካሉ ግን የሚበቃ ይሆናል)
سابعا : الدعـاء بأن يبلغك الله رمضـــــــان وان يوفـقـك فيـه للعمـل الصالـح.
ሰባተኛ፦ አላህን ረመዳንን እንዲያደርስህ በረመዳን ውስጥም መልካም ስራ መስራትን እንዲያስችልክ መለመን።
ثامنا : ينبغي إنهاء الأشغال الدنيوية قبل رمضان للتفـرغ للعـبـــادة في رمضــــــــــان
ስምንተኛ፦ በረመዳን ውስጥ በዒባዳ ለማሳለፍ ከረመዳን በፊት በዱንያ መወጠርን መተው ይገባል።
تاسعا : من عادة السلف إخـراج الزكاة في شعبان.
ዘጠነኛ፦ ከቀደምት ሰለፎች ልማድ: በዚህ በሸዕባን ወር ውስጥ ዘካን ማውጣት ነበር።
✍ ጦለሃ አህመድ
https://t.me/tolehaahmed
https://t.me/tolehaahmed