Addis Ababa Communication Bureau @aacommu Channel on Telegram

Addis Ababa Communication Bureau

@aacommu


Addis Ababa Communication Bureau (English)

The Addis Ababa Communication Bureau, also known as @aacommu, is a Telegram channel dedicated to providing the latest news and updates from the bustling city of Addis Ababa, the capital of Ethiopia. The channel serves as a hub for communication and information, offering residents and visitors alike a convenient platform to stay informed about local government initiatives, events, and developments. Who is it for? The Addis Ababa Communication Bureau channel is designed for anyone with an interest in staying up-to-date with the latest news and information coming out of Addis Ababa. Whether you are a resident looking to learn about new city projects or an outsider curious about the vibrant culture of Ethiopia's capital, this channel is for you. What is it? The channel provides a range of content, including official announcements, press releases, event notifications, and more. Followers can expect to receive updates on important city-wide initiatives, such as infrastructure projects, public events, and community campaigns. Additionally, the channel serves as a platform for the city government to engage with the public, share important announcements, and gather feedback from residents. With the Addis Ababa Communication Bureau channel, you can stay informed about everything happening in the heart of Ethiopia. Join @aacommu today to connect with the vibrant community of Addis Ababa and be the first to know about the latest news and events in the city.

Addis Ababa Communication Bureau

27 Jan, 17:20


"ፒያሳ ትላንት እና ዛሬ"

Addis Ababa Communication Bureau

27 Jan, 05:42


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው የ4ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል ።

በዚሁም መሰረት ካቢኔው የሃገራችንን ዲፕሎማሲ ታሳቢ ያደረገ የኤምባሲዎች የመሬት ጥያቄን እና የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅቃሴ ለሚያጎለብቱ፣ ሰፊ የስራ እድል እየፈጠሩ ላሉ፣ የዉጪ ምንዛሬ እያስገኙ ላሉ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረቻ ማስፋፊያ ቦታ ጥያቄዎችን መርምሮ ውሳኔ አሳልፏል።

Addis Ababa Communication Bureau

18 Jan, 18:46


" ከተራ -ጥምቀት በአዲስ አበባ በአስደናቂ አብሮነት ተዉቦ"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Addis Ababa Communication Bureau

18 Jan, 18:44


ውብ አዲስ!!

Addis Ababa Communication Bureau

06 Jan, 12:31


እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

እየሱስ ክርስቶስ በሰው ልጆች እና በአምላክ መካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ አፍርሶ በምህረት፣ በይቅርታ እና በታላቅ ፍቅር ወደ ምድር መምጣቱ ሰላምን እና ፍቅርን ለምድር እንዲሁም አብሮነት እንዲጎለብት ምሳሌ ለመሆን ነው::
ስለዚህ በዓሉን ስናከብር የእየሱስ ክርስቶስን ምሳሌነትን በመከተል የሰላም እሴቶችን እየገነባን፣ ፍቅራችንን ይበልጥ እያጎለበትን እንዲሁም አብሮነታችንን እያጠናከርን ሊሆን ይገባል::

በዓሉን ስናከብር ያላቸው ለሌላቸው ማዕድ በማጋራት ፍቅር፣ መተሳሰብና አብሮነት በሚገለጽበት መልክ እንዲሆን ጥሪ እያቀረብኩ፣ የሰላም እና የደስታ በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

መልካም በዓል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Addis Ababa Communication Bureau

06 Jan, 10:49


በለሚ ኩራ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ከባለሃብቶች ጋር በመተባበር የገነባናቸው ቤቶች እና የስራ እድል ለተፈጠረላቸው የልማት ተነሺ የከተማችን ነዋሪዎች የመስሪያ ቦታዎችን አስተላልፈን እንኳን አደረሳችሁ ብለን ማዕድ አጋርተናል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብቻ በኮሪደር ልማትና በመንገድ ወሰን ማስከበር ለተነሱ 4ሺ 510 እማወራ እና አባወራዎች ንጹህ እና መሠረተ ልማት የተሟሉላቸው መኖሪያ ቤቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብተን ያስተላለፍን ሲሆን 1264 በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች ደግሞ የስራ እድል ፈጥረን የመስሪያ ቦታዎችን አስረክበናል::
አዳዲስ 4 ህንጻዎች በአያት ሪል ስቴት፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ጄ ኤፍ ኤም ፔትሮሊየም ዲስትሪቢዩሽን እንዲሁም በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የተገነቡ ሲሆን በተጨማሪም በላይነህ ክንዴ ግሩፕ በአቃቂ ቃሊቲ 48 ቤቶችን እንዲሁም በንፋስ ስልክ ላፍቶ 141 ቤቶችን ገንብተን ለነዋሪዎች አስተላልፈናል::

መንግስት ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን የተወጡ ባለሃብቶችን በነዋሪዎቹ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ::
መልካም በዓል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication

Addis Ababa Communication Bureau

05 Dec, 16:37


አብሮ ለመኖር አብሮ መስራት ያስፈልገናል

Addis Ababa Communication Bureau

05 Dec, 16:04


19ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ከተማ አቀፍ ማጠቃለያ " ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ በአድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ በታላቅ ድምቀት ተከበረ::

ኢፌዴሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር እንደተናገሩት ሃገራችን ብዝሃነት ካላቸዉ የአለም ሃገራት አንዷ መሆኗንና ይህንንም ከትዉልድ ትዉልድ ለማስቀጠል በዉይይትና በምክክር በመስራት የሃሳብ ልእልና ማረጋገጥ እንደሚጠበቅ ገልፀዉ ለሃገራዊ መግባባት እና ለፌደራላዊ ሃገራዊ ግንባታ ስርዓት ማደግ በጋራ መቆም አለብን ብለዋል፡፡

አክለዉም አዲስ አበባ ሁሉም ከየአቅጣጫዉ የተሰባሰቡባትና የሚኖሩባት ማሳያና አምሳያ ስትሆን ለዚህም የሁሉም አሻራ ያረፈባት፤የሁሉም ላብ የፈሰሰባት፤የሁሉም እጆች ያበጃጇት፤የወል ታሪክ የተፃፈባት ህብረብሄራዊ ትስስር ያደመቃት የልህቀት ማእከል ከተማ መሆኗን ገልጸዉ ይህም የብልፅግና ጉዞአችን እዉን አድርጎ ያስቀጠለዉ መሆኑን አዉቀን ትዉልዱ የእርስ በእርስ ትስስሩ በማስፋት ለሰላምና ለፍትሃዊ ተጠቃሚነት የጀመረዉን ጉዞ አጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ብዘሃነትን ያቀፈች በመሆኗ የማንነት የባህል የቋንቋ የእምነት እና የተለያዩ ትዉፊቶች የሚንፀባረቁባት ብዝሃነትን ያስተናገደች ድንቅ ሃገር ነች ያሉት ከንቲባዋ ይህን ብዝሃነት በወጉ አክብሮ በእኩልነት እና በፍትሃዊነት የሚነሱ ጥያቄዎችን በአግባቡ በመመለስ እና በማረጋገጥ የኢትየጵያን አንድነት በጠንካራ መሰረት ላይ መገንባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነትና ለፌደራላዊ ስርዓት ግንባታ ወሳኝ ሚና አለዉ ብለዋል፡፡

Addis Ababa Communication Bureau

05 Dec, 15:57


ከአጥር መለስ

Addis Ababa Communication Bureau

05 Dec, 04:56


"ዉብ አዲስ"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለበለጠ መረጃ
https://linktr.ee/addisababacommunication

Addis Ababa Communication Bureau

04 Dec, 16:26


የእግረኛ መንገድ በኮሪደር ልማት!!

Addis Ababa Communication Bureau

03 Dec, 15:27


መረጃ እንደየ ሰው በጎ ፈቃድ በሚተነተንበት አሁን በምንገኝበት የድህረ እውነት ዘመን ሚዛናዊነታችንን ጠብቀን መረጃዎችን ከምንጫቸው በመውሰድና ትክክለኝነታቸውን በማረጋገጥ በማረጋገጥ ለሕዝብ ተደራሽ ልናደርግ ይገባል ::"የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትአለም መለሰ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጃው የሚገኙ የኮሚኒኬሽን መዋቅ የቀጣይ የመረጃ እና የኮሙኒክሽን እስትራቴጂ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ የኮሙኒኬሽን የቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ እናትአለም መለሰ እንደተናገሩት መረጃ እንደየሰው በጎ ፈቃድ በሚተነተንበት አሁን በምንገኝበት የድህረ-እውነት ዘመን ተቋማዊ ሚዛናዊነትን ጠብቀን መረጃዎችን ከምንጫቸው በመውሰድና ትክክለኛነታቸውን በማረጋገጥም ለሕዝብ ተደራሽ በማድረግ የሕዝቡን የመንግሥት መረጃ ፍላጎት ማርካት ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል ።

ጥንካሬያችንን በማጉላት ሀገራዊ ሪፎርሙን ተዋህደን በጋራ ልንመራ ይገባልም አክለው ያሉት ቢሮ ኃላፊዋ ሌሎችንም ተቋማት ተቀናጅተን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ የመደገፍ ነባር ልማዳችንን አጠናክረን ልናስቀጥል ይገባልም ብለዋል ።

Addis Ababa Communication Bureau

02 Dec, 18:16


በሰፈር የሚያስብ ሰው ኢትዮጵያን ማየት አይችልም!!

Addis Ababa Communication Bureau

02 Dec, 12:33


ከሳር ቤት ላፍቶ አደባባይ..

Addis Ababa Communication Bureau

24 Nov, 12:49


“የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና!” በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል መድረክ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የፓን አፍሪካ አዳራሽ በመከናወን ላይ ይገኛል።

Addis Ababa Communication Bureau

12 Nov, 11:01


አዲስ አበባን ተመራጭ ያደረጋት ምንድነው!

Addis Ababa Communication Bureau

11 Nov, 17:51


በዛሬው 4ተኛ አመት 3ተኛ መደበኛ የካቢኔ ስብሰባች ሁለተኛ ኮሪደር ስራ ያለበትን በጥልቀት ገምግሟል ።

በግምገማው በዋናነት ትኩረት ያደረግነው የልማት ተነሺዎች የተስተናገዱበትን አግባብ፤ በመንግስት የሚኖሩ የነበሩ የተነሱበት አግባብ፤ መሰረተ ልማት የተሟሉላቸው መሆኑን፤ በተመሳሳይ ሁኔታ የግል ተነሺዎች ደግሞ የካሳ የ3 አመት የቤት ኪራይ እና ምትክ መሬት መውሰዳቸውን ፤የትራንስፖርት አቅርቦት እና የሞራል ካሳ በህጉ መሰረት የተከፈለ መሆኑን የተተነተነ ሪፖርት በየኮሪደሩ አስተባባሪዎች ቀርቦ ተገምግሟል።

በግምገማውም ሁሉም ህጋዊ ውል ወይም ሰነድ ኑሯቸው እንዲሁም በመጠለያ በተገኙበት ተጠልለው የሚኖሩ ነዋሪዎችን ሁሉ የቤት መስተንግዶ እና የቤት መሰረተ ልማቶች በተሟላላቸው እጅግ የተሻለ ፣ ንፁህ ፣ መሠረታዊ መገልገያዎች የተሟሉላቸው ቤቶች የተስተናገድ ሲሆን፤ ለመኖር ምቹ አካባቢ ያገኙ ስለመሆኑ እና አንዳንድ ሳይቶች ላይ የመንገድ ደረጃውን ለማሻሻል ግንባታ እየተካሄደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦ ካቢኔው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ውሳኔ አስተላልፏል።

ሌሎች ሳይት ላይ አስፈልጊው መሰረተ ልማት ተጠናቆ ነዋሪዎች የየእለት ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል ፤የማህበራዊ ኑሯቸው ሳይበታተን እድር ፤ ማህበር እና አብሮነታቸው የመሰረቱት ማህበራዊ መስተጋብር እንደተጠበቀ መስተናገዳቸው ን አቃቂ ፤ገላን ጉራ ፤ፉሪ ሃና ፤አራብሳ አምስት እና ስድስት አያት ሶስት፤ ላፍቶ ሃይሌ ጋርመንት እና ለሚኩራ አጠገብ የተሰሩት ሎኮስት ፤አየርጤና ቂርቆስ ለገሃር አካባቢ ፤አራዳ ሰባ ደረጃ አካባቢ በማሃል ከተማ የተገነቡ ቤቶች ላይም የተስተናገዳቸውን እና አፈፃፀሙም ጥሩ መሆኑን ካቢኔው ገምግሟል።
የመሠረተ ልማት ቅንጅት አካላት ከከተማ እስከ ፌደራል ተቋማት የነበራቸው ተሳትፎ በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ካቢኔው በጥንካሬ ገምግሟል ።
በተጨማሪም መሬት እና ካሳ ምትክ እስካሁን ድረስ ብቻ ከ4.6ቢሊየን በላይ መከፈሉን የሁለት አመት የቤት ኪራይ መከፈሉን እና ቀሪ ተነዴዎችም ቅድመ ዝግጅት ሂደት ካቢኔው በጥንካሬ ገምግሟል ። በሌላ በኩል በኰሙኒኬሽን ሥራዎችን በደንብ ደጋግሞ ለሕዝብ መረጃን ማድረስ ላይ ከዚህ በላይ ማድረስ እና ተደጋጋሚ የሚዲያ ሽፋን ያላቸው የመረጃ ስርጭት ለህብረተሰቡ መድረስ እንዳለበት ካቢኔው አሳስቧል። መረጃን የሚያዛቡ እና ሀገር እንዳትለማ ውዝንብር በሚፈጥሩ የተለያዩ ዝንባሌዎች የሚያሳዩ የመረጃ ምንጮችን እና አካላት ላይ ህጋዊ ርምጃ በመወሰድ እንዳለበት በአፅንኦት ኣንስተዋል ::
በ2ኛው ዙር ኮሪደር ልማት ስራ 2879 ሄክታር ስፋት ፤ 135ኪሎ ሜትር የኮሪደር ርዝመት ያለው ሲሆን ፤ 240ኪሎ ሜ የአስፋልት መንገድ፣ 237 የእግረኛ መንገድ ፣ 32 የህፃናት መጫዎች ቦታዎች ፣ 79 የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች ፣ 114የታክሲ እና አውቶቡስ መጫኛ እና ማውረጃ ፣ 58 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ቦታዎች፣ 368 ሄክታር አረንጋዴ ልማት ሽፋን ያላቸው ቦታዎች፣ የ 111 ኪ.ሜ ሳይክል መንገድ ፣ 17 የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ 106 የህዝብ መረዳጃ ቤቶች፣ 121 ኪ.ሜ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ፣ 182 ኪ.ሜ ድሬኔጅ መውረጃ መስመር ፣ 50 የተሸርካሪና እግረኛ መተላለፊያ ፣ 75 ኪ .ሜ ሪቴይኒንግ (የድጋፍ ግንብ) ስራዎችን የሚያካትት ነው ::
ይህንኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ክትትል ማሳደግ፤ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ የተተገበሩ የ አንደኛ ዙር ኮርድር ልማት ልምዶች ተቀምረው ለ2ተኛው ዙር በተሻለ ብቃት መስራት እንደሚያስፈልግ ፤ ቅንጅታዊ አሰራርም በተጠናከረ መልኩት አሳድጎ በጥንካሬ አሁን ካለው በላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ካቢኔው አሳስቧል።

Addis Ababa Communication Bureau

11 Nov, 14:29


በልማቱ ደስተኛ ነን!!

Addis Ababa Communication Bureau

11 Nov, 12:39


በአዲስ አበባ ከተማ በመርካቶ አካባቢ አንዳንድ ነጋዴዎች “ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው” የሚል መሰረት የሌለው ውዥንብር ውስጥ መግባታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ተመልክተናል፡፡

ውዥንብሩ ከየት መጣ የሚለው ሲጣራ በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች በዚህ ሂደት ውስጥ እንዲያልፉ በሚደረገው ሥራ ሲሆን በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎችን በመለየት በደረሰኝ ግብይት እንዲፈጽሙ የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ጊዜያት ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል::

ይሁን እንጂ ይህንን ጥሪ ወደ ጎን በመተው እና ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል የሚያስቡ አካላት በሚነዟቸው ውዥንብሮች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ንብረት የሚያሸሹና ሱቅ የሚዘጉ ነጋዴዎች ተገቢነት ከሌለው ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንዲሁም አምራች፣ አከፋፋይና ቸርቻሪ ነጋዴዎች ያለደረሰኝ መገበያየት ህገወጥ ተግባር መሆኑን በአግባቡ በመረዳት ወደ ህጋዊ መስመር ሊገቡ ይገባል፡፡

በመርካቶ እየተከናወነ የሚገኘው ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል እየተሰራ ያለ ስራ ሲሆን ለዚህም የንግዱ ማኅበረሰብ ተባባሪ ሊሆን ይገባል::

አንዳንድ ያለደረሰኝ በመገበያየት ሕዝብና መንግሥት ማግኘት ያለባቸውን ጥቅም እያሳጡ የራሳቸውን ኪስ የሚሞሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንዲሁም ከዚህ በፊት ያለደረሰኝ የተገዙ ዕቃዎች ካሉ ሕጉ በሚያዘው መሠረት የማስመዝገብ ሥራ ማከናወን ይጠበቅባቸዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰቡ ብልሹ አሠራርን ጨምሮ ደረሰኝ የማቆርጡ እና ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈጽሙ አካላትን በ7075 ላይ እንዲጠቁሙ ጥሪውን ያቀርባል::

Addis Ababa Communication Bureau

11 Nov, 12:34


የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ሁለት አበይት ተግባራት በተመለከተ የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

የአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት እየሰጠችበት ያለውን የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ሲስተም የሚተካ አዲስ የCRVS, e-ID and Mobile ID የተባለ ሲስተም አልምቶ ወደ ስራ ለማስገባት ቅድመ ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን ይህንኑ ፕሮጀክት የማማከር እና የመከታተል ስራ በተመለከተ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንቲትዮት እንዲሁም ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር ዛሬ ስምምነት ተፈፅሟል።

በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የፋይዳ ምዝገባ ስራ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በጋራ ለመምራት የሚያስችል ስምምነት ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ጋር በዕለቱ ተፈፅሟል። ላለፈው አንድ ወር የምዝገባ ስራን ተቋማቱ በጋራ እያስተባበሩ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በቀጣይ ግዚያት ተጠናቅሮ የሚቀጥል ይሆናል።

Addis Ababa Communication Bureau

23 Oct, 10:52


ዛሬ ጠዋት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ንግግር ያደረጉበት ''የተጠናከረ የባለብዙወገን ግንኙነት ለሚዛናዊ የአለም ልማት እና ደኅንነት'' በሚል ጭብጥ የ16ኛው የብሪክስ ጉባኤ ዝግ ስብሰባ ተካሂዷል።

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2023 ወደብሪክስ እንዲቀላቀሉ ከተጋበዙት ሀገራት መካከል መሆኗ ይታወቃል። ከጥር 2024 ጀምሮም የአባልነታችን እንቅስቃሴ በይፋ ጀምሯል።

#PMOEthiopia

Addis Ababa Communication Bureau

20 Oct, 16:41


ከጭለማ ወደ ብርሃን!

Addis Ababa Communication Bureau

20 Oct, 16:20


የኮንዶሚኒየም ቤትን በተመለከተ!

Addis Ababa Communication Bureau

20 Oct, 15:52


ኮሪደር ልማት ቅድሚያ ልንሰጠው የሚገባን ተግባር ነው!!

Addis Ababa Communication Bureau

20 Oct, 15:34


ጥናትን በተመለከተ!

Addis Ababa Communication Bureau

20 Oct, 10:58


ፈፅሞ አብሮ አይሄድም!!

Addis Ababa Communication Bureau

20 Oct, 10:57


የኑሮ ውድነትን በተመለከተ!

Addis Ababa Communication Bureau

16 Oct, 14:11


ዛሬ 6/2/2017 የሁለተኛው የኮሪደር ልማት ስራን በተመለከተ ለኮሙኒኬሽን ባለሞያዎችና ለመዋቅሩ የተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ !!