ታህሳስ 15/2017 ዓ ም
የከተማ አስተዳደሩ የሥራ እድል ፈጠራ እና የሌማት ቱሩፋት የንቅናቄ ሥራዎች የ42 ቀናት አፈፃፀምን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።
በከተማ ግብርና ዘርፍም ሆነ በሥራ ዕድል ፈጠራ የንቅናቄ ሥራዎች የተሻለ አፈፃፀም መመዝገቡ ከመድረክ ተገልጿል።
መድረኩን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ክቡር አቶ አለማየሁ እጅጉ በጋራ መርተውቷል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡት ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ በቀጣይ የሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ከቅጥር ባሻገር ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
አቶ ጥራቱ አያይዘውም ከሌማት ቱሩፋት ስራ ጋር ተያይዞ ነባር ተቋማትን ማስቀጠል እና አዳዲስ የፋሚሊ ቢዝነሶችን አጠናክሮ ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ምክትል ኃላፊ በሰጡት ሀሳብ በሥራ እድል ፈጠራ እና በሌማት ቱሩፋት ስራዎች ውጤት ማስመዝገብ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ዕሴት የሆነውን ሰው ተኮርነት ማስፈፀም መሆኑን ገልፀው ከዚህም በላይ የላቀ አፈፃፀም ለማስመዝገብ አመራሩ ስራውን ከመቼውም ጊዜ በላይ በጥብቅ ዲሲፒሊን ሊመራ ይገባል ብለዋል።