አዲስ መረጃ @adissemereja Channel on Telegram

አዲስ መረጃ

@adissemereja


መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

አዲስ መረጃ (Amharic)

አዲስ መረጃ በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ ። በዚህ መረጃ የተያያዙ ስራዎችን እና እናመሰግናለን ። ይህ መረጃ የአስተያየት እና ማስታወቂያ ስራዎችን እናወያዩ ያለዎችን ለማስተላለፍ እና ለማራኪያ ሆነን እንጠቀማለን ።

አዲስ መረጃ

16 Oct, 12:34


#ኢትዮጵያ #ቻይና

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ቻይና አቅንተው በቻይና ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ናቸው።

ከጠ/ሚ ፅ/ቤት በወጣ መረጃ የቻይናው ጠ/ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ለዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ይፋዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በኃላም የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል። በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የምጣኔ ኃብት ትብብር ግንኙነት ማጠናከሪያ መንገዶች ላይ መክረዋል ተብሏል።

ከሁለትዮሽ ውይይቱ በመቀጠል ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ጠ/ሚ ሊ ኪያንግ በተገኙበት በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ መስኮች 12 ያህል የትብብር ስምምነቶች እና ሁለት የፍላጎት ሰነዶች ተፈርመዋል።

ዶ/ር ዐቢይ በቻይና ይፋዊ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ ከአራት ዓመት በኃላ ሲሆን በቀጣይ በሚካሄደው 3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ አለም አቀፍ ትብብር መድረክ ላይም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፎቶ፦ #PMOffice

አዲስ መረጃ

16 Oct, 12:32


የእህቱ ልጅ በሆነ የሰባት አመት ህፃን ላይ የግብረሰዶም ወንጀል የፈፀመ ተከሳሽ በፅኑ እስራት መቀጣቱ ተገለጸ።

ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው በሰኔ ወር 2014 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በተለምዶ ማሪያም ወንዝ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚኖርበት ቤት ውስጥ ነው።

የ37 ዓመት ዕድሜ ያለው ተከሳሹ እና የተከሳሹ እህት በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን ተከሳሹ ሰው የሌለበትን አጋጣሚ ጠብቆ የሰባት ዓመት ዕድሜ ያለው የእህቱን ልጅ በስለት በማስፈራራት የግብረ ሰዶም ወንጀል ፈፅሞበታል።

ፖሊስ በቀረበለት ጥቆማ መነሻነት ተከሳሹን ተከታትሎ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ አስፈላጊ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ በአቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰረትበት አድርጓል፡፡

የተከሳሹን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ጥፋተኝነቱን በማረጋገጥ ሰሞኑን በዋለው ችሎት በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

ወላጆች ልጆቻቸው ለእንደዚህ አይነት ወንጀል ሰለባ እንዳይሆኑ ዕድሜያቸውን መሰረት በማድረግ አስቀድመው በግልፅ መወያየት እና ተገቢውን ክትትልና ጥበቃ ማድረግ  እንደሚኖርባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን ያስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

አዲስ መረጃ

11 Oct, 19:34


#ነዳጅ

በመካከለኛው ምሥራቅ በእስራኤልና ሀማስ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ መፍጠር የጀመረው የዋጋ ጭማሪ ተጠናክሮ የሚቀጥል ከሆነ በኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የመጣው የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ የበለጠ ሰማይ ሊነካ ይችላል የሚል ሥጋት ፈጥሯል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ድረስ የነዳጅ ዋጋን ወደ ተጠቃሚው ለማስተላለፍ በወሰነው መሠረት እስሁን ድረስ በአማካይ ከአሥር በመቶ በላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረገ የመጣ በመሆኑ በእስራኤል እና ሀማስ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ሊፈጥር የሚችለው የዓለም የነዳጅ ዋጋ በቀጥታ ወደ ተጠቃሚው ማኅበረሰብ ከማስተላለፍ ሊቆጠብ እንደሚገባ የኢኮኖሚ ባለሞያው አቶ አወት ተክኤ መክረዋል።

የኢኮኖሚ ባለሞያው አቶ አወት ተክሌ ምን አሉ ?

" በመካከለኛው ምሥራቅ የሚከሰት ጦርነትና አለመረጋጋት በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድር ነው።

በቀዳሚነትም የዓለም የነዳጅ አቅርቦትና ገበያ የሚታወክ በመሆኑ፣ ይህ ሁኔታ የሚከሰት ከሆነ አሉታዊ ተፅዕኖው ለኢትዮጵያም የሚተርፍ እና የሚያሰጋ ነው።

የዓለም የነዳጅ ምርትና ገበያ ሰላምን ይፈልጋል። እንዲህ ያሉ ትልልቅ ጦርነቶች በተለይ አገሮች በፖለቲካ አመለካከታቸው ወገንተኝነታቸውን በግልጽ በሚያሳዩበት ወቅት የነዳጅ ግብይት ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል።

በተለይ አሁን በተቀሰቀሰው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ምክንያት በአካባቢው የሚገኙ የመካከለኛው ምሥራቅ ነዳጅ ባለፀጎች ለአንደኛው ወገን የሚያደላ የፖለቲካ አቋም ለመያዝ ከተገደዱ ይህንን የፖለቲካ አቋማቸውን የሚገልጹት የነዳጅ ምርትና አቅርቦታቸውን በመገደብ እንደሚሆን ቀደም ሲል የነበራቸውን ተሞክሮ ያሳያል።

ከዛሬ 50 ዓመታት በፊት በነዚሁ ወገኖች መካከል በተቀሰቀሰ ጦርነት ነዳጅ አምራች አገሮች በሁለቱ ተፋላሚዎች መካከል ጎራ ለይተው በመሠለፋቸው በዓለም የነዳጅ ምርትና አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ዕክል ፈጥረው ነበር።

አሁንም እነዚሁ ተመሳሳይ አገሮች የሚፋለሙበት ጦርነት በመከሰቱ በነዳጅ ሀብት የታደሉት የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች በዋናነትም፣ ኢራንና ሳዑዲ ዓረቢያ ያሉ አገሮች አንደኛውን ተፋላሚ ወገን ደግፈው ምዕራባዊያኑ ደግሞ ሌላኛውን ወገን ደግፈው የሚቆሙ ከሆነ የዓለም የነዳጅ ምርትና አቅርቦትን ሊያስተጓጉልና ዋጋውም ጣሪያ ሊነካ ይችላል።

ይህ ሁኔታ ከተከሰተ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች ትልቅ ፈተና ነው።

ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግሥት ከነዳጅ ድጎማ ለመውጣት ቀስ በቀስ የሚያደርገውን የዓለም የነዳጅ ዋጋን መሠረት ያደረገ ወርኃዊ የችርቻሮ ዋጋ ማስተካከያ ቆም ብሎ ሊፈትሸው ይገባል።

ያልጠበቀውን ጦርነት ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እንዳለ ኅብረተሰቡ ላይ መጫን የሚያዋጣ አይደለም።

መንግሥት ከነዳጅ ድጎማ ለመውጣት በገበያ ዋጋ እየሠራ ቢሆንም እንዲህ ባሉ ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ግን ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖው ግልጽ ከመሆኑ አንፃር በተለይም በአሁኑ ወቅት የሚታየው የዋጋ ንረት ጦርነቱ ሊያስከትል የሚችለውን የዋጋ ጭማሪ ኅብረተሰቡ ላይ እንዲጫን ማድረግ ተገቢ አይሆንም።

ይህ ካልሆነ ግን የዋጋ ንረቱን በማባባስ ማኅበረሰብን ብሎም ኢኮኖሚውን ይጎዳል።

በሌላ በኩል ግን የእስራኤልና የፍልስጤም ጦርነት ከተፋላሚ አገሮች ባሻገር አገሮችን ጎራ ለይተው ወገንተኝነታቸውን እየገለጹ መሆን ምናልባት ትላልቆቹ የነዳጅ አቅራቢዎች ነዳጅ ባያቀርቡ ዓለም ላይ ችግር እንዳይኖር በተቃራኒ ያሉ አገሮች ተጨማሪ ነዳጅ በማቅረብ ገበያውን ለማረጋጋት ሊሞክሩ የሚችሉበት ዕድል እንዳለ አለ። ይህ ሊሆን የሚችለበት ዕድል ጠባብ ቢሆንም አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ሲታይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው አይቀመስም ብዙ አገሮችን ተጎጂ ያደርጋቸዋል፡፡

በተለይ ከፍተኛ የገቢ ንግድ ያለቸው አገሮች የዋጋ ጭማሪ ሊያስከትልባቸው ይችላል። ስለዚህ በተለይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ሊያስከትል የሚችለው ተፅዕኖ በማሰብ መንግሥትም ጊዜውን የዋጀ አሠራር ያስፈልገዋል።

በአጠቃላይ ግን የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ዓለም አቀፉን ኢኮኖሚ ይፈትናል፡፡

ጦርነቱ ዛሬ ያቆማል ቢባል እንኳን በብዙ መልኩ ተፅዕኖው ቀላል አይሆንም። በተለይ ዕቃን የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ዘርፎች በሚፈጠርባቸው ሥጋት እንቅስቃሴያቸው ይገደባል፡፡ ከዚህም ሌላ መንቀሳቀስ ከቻሉም ከፍተኛ የኢንሹራንስ ሽፋን የሚጠይቁ መሆኑንና ተያያዥ ጉዳዮች የአቅርቦት ዋጋን ስለሚያስወድዱ የጦርነቱ ግልጽ የሆነ ተፅዕኖ አለው። "

(ከሪፖርተር

አዲስ መረጃ

10 Oct, 19:06


ኢሰመኮ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ተጠርጣሪዎች ለአካለ መጠን ከደረሱ ተጠርጣሪዎች ጋር ተቀላቅለው እንደሚታሰሩ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ በአንዳንድ ፖሊስ ጣቢያዎች እድሜያቸው ከ18 በታች የሆኑ ተጠርጣሪዎች ለአካለ መጠን ከደረሱ ተጠርጣሪዎች ጋር ተቀላቅለው የሚታሰሩ መሆናቸውን ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ገልጿል።

ኢሰመኮ ከሐምሌ ወር 2014 እስከ ሰኔ ወር 2015 ድረስ ያለውን የሴቶችና ሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ኹኔታን ያካተተ ዓመታዊ ባለ 46 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም አደረኩት ባለው ክትትል በሶማሌ ክልል ፖሊስ ጣቢያዎች እና ማረሚያ ቤቶች ዉስጥ ያሉ ታራሚ ሕፃናት ለአካለ መጠን ከደረሱ እስረኞች ጋር ተቀላቅለው እንደሚያዙ፤ እንዲሁም በሚቆዩባቸው ጊዜያት የሕፃናቱን ዕድሜ ያላገናዘበ የኃይል እና የእርምት እርምጃዎች እንደሚወሰድባቸው አመላክቷል።

በተመሳሳይም በጉለሌ ክፍለ ከተማ በየካቲት ወር 2015 በእንጦጦ አምባ ትምህርት ቤት በተፈጠረ የጸጥታ ችግር ምክንያት የክፍለ ከተማው ፖሊስ ሕፃናትን ጨምሮ በርካታ ተማሪዎችን በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ገልጿል፡፡

ኢሰመኮ ግንቦት 4/2015 ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ጉብኝት በወቅቱ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ 64 ሕፃናት ታስረው መገኘታቸውንና ሕፃናቱ ለ5 ቀናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በእስር እንዲቆዩ መደረጉ አሳሳቢ ሆኖ መገኘቱን አውስቷል፡፡

በወላጅ ወይም አሳዳጊ ጥበቃ ሥር የመቆየት እንዲሁም በዋስ የመለቀቅ መብቶቻቸውም በአብዛኛው የማይከበርላቸው መሆኑ፣ በሚቀርብባቸዉ ክስ ላይ መልስ ለመስጠት ዕድል የማያገኙና በተጨማሪም በቂ የሕግ ባለሙያ ድጋፍ ማግኘት እንደማይችሉም ተገልጿል።

እንዲሁም በወንጀል ተግባር ላይ ለተገኙ ሕፃናት በአገሪቱ ሕግ የተቀመጠው ጥበቃ በአብዛኛው የማይፈጸም መሆኑ ጠቁሟል።

ይህም ያለፍርድ ቤት ፈቃድ ሕፃናት ላይ የወንጀል ምርመራ መደረጉ፣ ተጠርጣሪ ሕፃናት ወዲያውኑ ፍርድ ቤት ቀርበው ቃል እንዲሰጡ የማይደረግ ከመሆኑም ባሻገር ቃል የሚሰጡት ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች በሌሉበት መሆኑን  ገልጿል።

በመጨረሻም በሚሻሻለው የወንጀል ሥነ ስርዓት እና የማስረጃ ሕግ ለሕፃናት ልዩ ጥቅም ቅድሚያ እንዲሰጥ የሚያስገድድ መርሕ እንዲካተትና በወንጀል ለተጠረጠሩ ሕፃናት ከመደበኛ የፍትሕ ሂደት ውጪ ተፈፃሚ የሚሆኑ የሥነ ሥርዓት እርምጃዎችን እንዲካተቱ ኢሰመኮ ጠይቋል።

አዲስ መረጃ

10 Oct, 19:05


" የተፈታኞቹን ውጤት በአንድ ሳምንት ውስጥ ለማሳወቅ ይሰራል ፤ የሚያልፉ ተማሪዎችም በሀገር አቀፍ ደረጃ ውጤታቸው ከተገለፁት ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ለማድረግ እንጥራለን  " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

" ፈተናው ዛሬ በአራቱም ዩኒቨርሲቲዎች በሰላም ተጀምሯል። " - የትግራይ ትምህርት ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

ፈተናው በክልሉ በሚገኙ አራቱ የፌደራል ዩኒቨርስቲዎች በተመሳሳይ ጊዜ በሰላማዊ ሁኔታ መሰጠት መጀመሩ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አረጋግጠዋል።

በቢሮው የግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሰለሞን ገ/ታትዮስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፦
- በራያ ዩኒቨርስቲ 1561
- በመቐለ ዪኒቨርስቲ 2280
- በዓዲግራት ዩኒቨርስቲ 2382
- በኣክሱም ዩኒቨርስቲ 3291 በአጠቃላይ ከዘጠኝ ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናቸውን ዛሬ ጀምረዋል።

ፈተናው ጥቅምት ሁለት ይጠናቀቃል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መስከረም 28 /2016 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት ፤ የትግራይ ተፈታኞቹን ውጤት በአንድ ሳምንት ውስጥ ለማሳወቅ ይሰራል።

የሚያልፉ ተማሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ውጤታቸው ከተገለጸ ተማሪዎች ጋር አብረው ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ለማድረግ ጥረት ይደርጋል ብለዋል።

ፎቶ፦ TIGRAY tv

አዲስ መረጃ

09 Oct, 19:29


ውጤት እንዴት መመልከት ይቻላል ?

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች መገ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

በዌብ ሳይት 👉 https://eaes.edu.et/

በአጭር የጽሑፍ መልዕክት 👉 6284

በቴሌግራም 👉 https://t.me/eaesbot

#MoE

አዲስ መረጃ

09 Oct, 10:26


#ሙሉ_መግለጫ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ የሰጠው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጥዋት 12 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ።

8,152

subscribers

4,923

photos

79

videos