በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ በጎሮ ወረዳ አሎሼ ኤልቶኬ ቀበሌ የለማ ሃያ ሄክታር ኩታ ገጠም የስንዴ እርሻ እንዲሁም በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ውስጥ የሚገኘው የተቀናጀ የምርመር ማእከል ውስጥ የሚገኙ ስንዴ ዝርያዎች ላይ የሚሠሩ የምርምር ስራዎች በተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት እና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተጎበኙ፡፡
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር ፣በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራት ወደ አካባቢው ህብረተሰብ በመግባት መጠነ ሰፊ አገልግሎት ለማህበረሰቡ በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡
በመስክ ጉብኝቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር አህመድ ከሊል እንዳሉት መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከሶስት እና አራት አመታት በፊት ወደ በኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴን ወደ አርሶ አደሩ ወርዶ መስራት በጀመረበት ወቅት አስር አስር ሄክታር በሶስት ወረዳዎች በማልማት ነበር የጀመረው፡፡ሆኖም ዩኒቨርሲቲው ጠንካራ አቋም በመያዝ በባሌ፤ ምስራቅ ባሌ እና ምእራብ አርሲ ዞኖች ዘጠኝ ወረዳዎች አሁን ላይ መቶ ሰማኒያ/180/ ያህል ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም አስተራረስ ዘዴ እንዲለማ ማስቻሉን ተናገረዋል፡፡
አክለውም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አላማው ለአርሶ አደር የእህል ዘር ማቅረብ ሳይሆን ለአርሶ አደሩ የሞያ እገዛ ማድረግ፣ ተሞክሮ ማጋራት ብሎም በምርምር ያገኛቸውን የምርምር ውጤቶች ማድረስ መሆኑን በመግለፅ ወደ ፊትም ቢሆን ዩኒቨርሲቲው ከወረዳው ጋር በቅንጅት በመስራት ለላቀ ውጤት እንደሚተጋ በመግለፅ ለተገኘው ውጤት ተሳትፎ ለነበራቸው አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ ፕሮፌሰር በላይ ሰማነህ በበኩላቸው በመስክ ጉብኝቱ የተመለከትኩት ነገር ትልቅ ተስፋ ሰጭ ጅምር ነው ፡፡ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መስመሩን አግኝቶታል ይህንን መስመር መከተል ይኖርበታል በለዋል፡፡ኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴ የተበጣጠሳ ነበረውን የአስተራረስ ዘዴን በመቀየር በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በማድረግ ረገድም ጠቀሜታው የላቀ በመሆን ዩኒቨርሲቲ በሌሎች አርሶ አደሮች ዘንድ ግንዛቤን በመፍጠር የአመለካከት ለውጥ ላይም በስፋት መስራት እንዳለበት አመላክተዋል፡፡
በወረዳው የኩታ ገጠም አሰተራረስ ዘዴው ተጠቃሚ የሆኑት አርሶ አደሮችም በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አስተምሮ በማስመረቅ ብቻ የማይቆም መሆኑን በሰጠን ድጋፍ እና ክትትል ተመልክተናል፡፡ አስራ ስድስት አባ ወራዎች እና እማ ወራዎች ሃያ ሄክታር መሬት ከማረስ ጀምሮ ለዘር 30 ኩንታል ምርጥ ዘር እና መድሀኒት በማስረጨት እና ሙያዊ እገዛም ጭምር በመስጠት አግዞናል ሲሉ ተናገረው መጀመሪያ ላይ ስለ ኩታ ገጠም አስተራረስ ዘዴ ግንዛቤው ስላልነበረን ፍቃደኖች አልነበርንም አሁን ላይ ግንዛቤ አግኝተን ጥቅሙን ተረድተነዋል፡፡በመሆኑም ልሎች አርሶ አደሮችም ይህንን ዘዴ ሊወስዱ እና ሊጠቀሙበት ይገባል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ልህቀት በብዝሃነት !
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ
የውጭ እና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ባሌ ሮቤ
ለተጨማሪ መረጃ
ስልክ 0222441361/0228902110