ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

@ethio_real_madrid_15


El Real Madrid Es Mi Corazon ⚪️⚪️

ይህ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ እና ትልቁ የሪያል ማድሪድ የቴሌግራም ቻናል ነው። ስለ ሪያል ማድሪድ አዳዲስና ትኩስ መረጃዎች የዝውውር ዜናዎች ፣ ኃይላይቶች ፣ ቪዲዮች ፣ ትንታኔ በቀጥታ ያገኛሉ !

⚪️HALA MADRID Y NADA MAS⚪️
________________________________

📢 ለማስታወቂያ ስራ @LeulaRamos

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ (Amharic)

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ በኢትዮጵያ ሪያል ማድሪድ እና ቴሌግራም የቻናሉ ነው። ይህ በአንድ እና አዳዲስ መረጃዎችን የሚመልከው ዜናዎች፣ ኃይሉትና ቪዲዮችን ለመቀነስ እና ትንታኔ አገኛለሁ። የእኔ ብሎ ምያሉ እያየሁ የኢትዮ ሪያሚዉን መጀመሪያ አስተሳሰቢ ታሪኩን ግሚዳችሁ የሚያገኙ ሥራ ተጠቃሚዎችን እና የሚሰራ ሹእ ታሪኩን ጠቃሚዎችን እንዴት ለትኩሳችን አስተካክል እንችላለን? ስለ ሪያል ማድሪድ ቴሌግራም የሚባለውን ስኬት ብቻ መረጃዎች ያገኛሉ ።

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

22 Oct, 14:40


የምባፔ መምጣት በሪያል ማድሪድ ኮከቦች የተሞላውን የመልበሻ ክፍል ሊነካ ይችላል?

ጥሩ ተጫዋቾች ሲኖሩ ለአሰልጣኙ ጥሩ ነው፤ ነገር ግን አንዳንድ ተጫዋቾች ምቾት አይሰማቸውም እና በመልበሻ ክፍል ውስጥ ጠብ ሊፈጠር ይችላል።

የባሎንዶር ሽልማትን ማን ማሸነፍ አለበት ብለህ ታስባለህ?

ቪኒሲየስ ባለፈው የውድድር ዘመን በሻምፒዮንስ ሊግ እና በላሊጋው ሻምፒዮንነቱ ሽልማቱ የተገባው ተጫዋች ነው ብዬ አስባለሁ፤ ባለፈው ሲዝን ላደረገው ነገር ሁሉ እሱ ይገባዋል ብዬ አስባለሁ።

ሪቫልዶ (የቀድሞ ባርሲሎና እና ብራዚል ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች)

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

22 Oct, 13:58


የኮርትዋ የቅርብ ጊዜ ንግግሮችን በተመለከተ?

“እሱ ያገኘው ቦታ ይገባዋል፤ እሱ በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ ግብ ጠባቂዎች አንዱ ነው። በነገሮች ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ሊኖረን ይችላል ግን እዚህ እያለ ስላደረገው እና ​​ለሰጠን ነገር ሁሉ በጣም አመስጋኝ ነኝ።”

“አንድ ላይ ሆነን በአትሌቲኮ ማድሪድ የስፔን ላሊጋን አሸንፈን በሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ተጫውተናል፤ እሱ በወቅቱ በጣም አስፈላጊ ተጫዋቻችን ነበር።”

ዲያጎ ሲሞኔ

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

22 Oct, 12:20


ሄሱስ ፎርቲያ ዛሬ ከጉዳቱ መልስ በJuvenile A ቡድን በዩዝ ሊግ ይጫወታል፤ ከዚያም ደግሞ አንቼሎቲ ጥሪ አቅርቦለት ከዋናው ቡድን ጋር ወደ ልምምድ የሚመለስ ይሆናል።

[ Marca ]

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

22 Oct, 11:40


ጋብሪ ቬጋ ወደ ሳውዲ ሲያመራ ''አሳፋሪ'' ብለክ ፖስተክ ግን ናቾ እና ሆሴሉ ሲሄዱ ለምን ዝም አልክ?

" ከእርሱ አንፃር እነሱ በጣም ትልቅ ልዩነት አላቸው ፤ ሁለት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን እና ሌሎች ትላልቅ ዋንጫዎችን ያሳኩ እንዲሁም የእግር ኳስ ዘመናቸውን ለማጠናቀቅ ከጫፍ የደርሱ ተጫዋቾች መቼም ቢሆን ከአንድ ተስፋ ከጣለበት የ21 አመት ታዳጊ እና ወደፊት ዋንጫዎችን ማሳካት ከሚኖርበት ተጫዋች ጋር ስሙን በአንድ ላይ ማንሳት አይጠበቅብህም።

ልዩነታቸው እዚህ ጋር ነው ፤ እኔ ወደ ሳውዲ የሚሄዱ ሰዎችን አልደግፍም ግን ናቾ ኢግሌሲያስም ሆነ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ሳውዲ ሀገር ያቀኑት በአውሮፓ ብዙ የሻምፒዮንስ ሊግ እና ሌሎች ትላልቅ ዋንጫዎችን አሳክተው ነው ፤ አየህ እነሱ ወደዛ ሲያቀኑ ሁሉንም ዋንጫዎችን አሳክተው ፣ የክለባቸው እና የአውሮፓ ግዛት ሌጀንድ ተብለው እግርኳስን ሊያገባዱ ስለሆነ ነው። "

ቶኒ ክሩስ

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

22 Oct, 11:00


በሮድሪጎ ዙሪያ ያሉ ሰዎች  ስለ አንቾሎቲ ቋሚ አሰላለፍ ምርጫ አይጨነቁም፤ ይልቁንስ ከሴልታ ጋር በተደረገው ጨዋታ ሮድሪጎ ያልተሰለፈው በብራዚል ጨዋታዎች ላይ ብዙ ደቂቃ በማሳለፉ እንደሆነም ተረድተዋል።

ሮድሪጎ ቅድሚያ የሚሰጠው ጤናማ እና ሁል ጊዜም ብቃት ያለው መሆንን ነው፤ ይህ ሲዝን ቀላል አይሆንም ምክንያቱም ሪያል ማድሪድ እስከ 72 ጨዋታዎች ድረስ መጫወት ይችላል።

[Diario AS] 🥈

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

22 Oct, 10:19


“ከትንሽነቴ ጀምሮ ሁል ጊዜ ሉካ ሞድሪችን እወደው ነበር፤ ቶኒ ክሩስንም እንደዛው እወደዋለሁ። ሁልጊዜም ቢሆን ክሩስ እና ሞድሪች የሰጡኝን ምክሮች በሚገባ አስታውሳቸዋለሁ።”

“ሮድሪጎ ካየኋቸው ተጫዋቾች ሁሉ ብዙ የእግር ኳስ ኳሊቲዎች ያሉት ምርጥ ተጫዋች ነው።”

ኒኮ ፓዝ

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

22 Oct, 09:36


ቶኒ ሩዲገር የእግርኳስ ዘመኑን ከማጠናቀቁ በፊት በሳውዲ እግሩን ቢያቀዘቅዝ ምንም አይመስለውም ፤ እንደውም በክለባችን እስከ 2026 ያለው ውል ካልታደሰለት እንደ አማራጭ ይቆጥረዋል።

Rodra

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

22 Oct, 08:39


የሁለቱም ቡድን ግምታዊ አሰላለፍ

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

22 Oct, 05:31


የቀጠለ ...

የውጤት ግምቶች ...

አብዛኞቹ ሚዲያዎችና አቋማሪ ድርጅቶች ጨዋታው በክለባችን ውጤት ይጠናቀቃል በማለት ገምተዋል።

ክለባችን የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ በመሆኑ የተጋጣሚውም ክብደት አንፃርም ጨዋታው በክለባችን 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸናፊነት ይጠናቀቃል ስል ግምቴን አስቀምጫለሁ።

ቀጥታ ስርጭት ...

ሁለቱ የዩዝበኪስታን ሚድያዎቹ ቲቪ ቫርዚሽ እና ፉትቦል ኤችዲ ሊያስተላልፉ ይችላል። ምንም ቢሆን ዝም ብላችሁ ጠብቁት። እንዲሁም በዲኤስቲቪ፣ አሞስ እንዲሁም 24H SPORT ላይ መከታተል ትችላላችሁ።

ጨዋታው በስልክ ከማንኛውም ቦታ በቀጥታ ስርጭት መከታተል ለምትፈልጉ በሙሉ ዳግሞ በCRICFy Tv፣ ያሲን ቲቪ መሰል... መተግበሪያ አፖቹን መከታተል ትችላላችሁ።

እንደተለመደው ዳግሞ ጨዋታውን በቴሌግራም ምሽት 4 ሰዓት ጀምሮ በተወዳጇ ቻናላችን ኢትዮ ሪያል ማድሪድ ባማረ፣ በውብ፣ ጥርት ባለ አቀራረብ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ እናደርሳለን።

ቅድመ ዳሰሳውን በአሪፍ እና በውብ አቀራረብ አዘጋጅቼ ያቀረብኩት አብዱልከሪም (አብዱ) ነበርኩ!

ድል ለሃያሉና ታላቁ ክለብ ሪያል ማድሪድ ይሁን!
ቤተሰቦች መልካም የጨዋታ ቀን ይሁንላችሁ! 🤍

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

22 Oct, 05:00


የቀጠለ ...

ግምታዊ አሰላለፍ

አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ባለፉት ጨዋታዎች ከተጠቀሙበት አሰላለፍ በተለያ መልኩ በዛሬው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ላይ በርካታ ለውጦችን እና ቅያሪዎችን እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። በዚህም መሰረት በዛሬው ጨዋታ ላይ ካርሊቶ ምን አይነት አሰላለፍ ይዘው ይገባሉ የሚለውን ለመመልከት ያክል ይህንን ግምታዊ አሰላለፍ የምናይ ይሆናል።

የክለባች ግምታዊ አሰላለፍ (4-3-3) ...
           
                      ኮርቱዋ

ቫዝኬዝ  |  ሚሊታኦ  |  ሩዲጋር   |  ሜንዲ

ቫልቬርዴ      |    ቹአሚኒ   |      ቤሊንግሀም

ሮድሪጎ         |     ምባፔ    |      ቪኒ ጁኒዮር


የዶርትሙንድ ግምታዊ አሰላለፍ (4-2-3-1) ...

                        ኮቤል

ሬይርሰን | አንቶን | ሽሎቴርቤክ | ቤንሴብይኒ

                 ካን | ሳቢትዘር

ማለን    |     ብራንድት |   ጊቴንስ

                 ጉራሲ

ይቀጥላል ...

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

22 Oct, 04:30


የቀጠለ ...

የቡድን ዜና ...

የክለባችን ቡድን ዜና ...

በክለባችን በኩል ታዳጊው የመሀል ተከላከይ ጃኮብ ራሞን፣ ኦስትሪያዊው የመሀል ተከላከይ ዴቪድ አላባ፣ ሞሮካዊው አማካኝ ብራሂም ዲያዝና ስፔናዊው ቀኝ ተመላላሽ ዳኒ ካርቨሀል በጉዳት ላይ የሚገኙ ወሳኝና ምርጥ ተጨዋቾቻችን ናቸው።

ራሞን ጃኮብ - ጉዳት

ዳኒ ካርቨሀል - ጉዳት

ብራሂም ዲያዝ - ጉዳት

ዴቪድ አላባ - ጉዳት

የተጋጣሚ የቡድን ዜና ...

በተጋጣሚው ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በኩል ሱሌ፣ ሬይና፣ ኩቶ፣ አዴዬሚ እና ዱራንቪሌ በጉዳት የሚገኙ ወሳኝና ምርጥ የቡድኑ ተጨዋቾች መሆናቸው በይፋ ተረጋግጧል።

ኩቶ - ጉዳት

አዴዬሚ - ጉዳት

ዱራንቪሌ - ጉዳት

ሬይና - ጉዳት

ሱሌ - ጉዳት

ይቀጥላል ...

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

22 Oct, 04:00


የቀጠለ ...

የእርስ በርስ ግንኙነት

ሁለቱ ክለቦች በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊጉ 14 ጊዜ ሲገናኙ 7ቱ በሎስ ብላንኮቹ አሸነፊነት ሲጠናቀቅ 3ቱ ዳግሞ በቢጫዎቹ አሸነፊነት ተጠናቋል። አራት በአቻ ተጠናቋል።

ቢጫዎቹ በሜዳችን ሳንቲያጎ በርናቦ ሰባት ጨዋታቸውን ሲያደርጉ ሰባቱንም ያለድል ወጥተዋል። ይህም በሜዳው ያላቸው ቁጥር ደካማ መሆኑን ማሳያዎች ናቸው።

ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ሪያል ማድሪድን ለመጨረሻ ጊዜ ማሸነፍ የቻለው 2014 ኤፕሪል ወር ነበር። በሜዳው ዳግሞ የተሸነፉት 3ለ2 በሆነ ውጤት በ2017 ነበር።

ክለባችን ሪያል ማድሪድ በሁሉም ውድድሮች ባደረጓቸው 5 ጨዋታዎች 3 ድሎች፣ 1 አቻና 1 ሽንፈት ሲያስተናግድ ቢጫዎቹ ዳግሞ 3 ድሎችና 2 ሽንፈቶችን አስተናግዷል።

ባለፉት ሪያል ማድሪድና ቦሩሲያ ዶርትሙንድ እርስ በርስ አምስት ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ ሶስት ጨዋታዎች ሲያሸንፍ ሁለት ጨዋታዎች አቻዎች ወጥተዋል።

ይቀጥላል ...

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

22 Oct, 03:30


| ጨዋታ ቀን | MATCH DAY ...

👉 | የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨዋታ መርሐግብር!

⚪️ ሪያል ማድሪድ ከ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ 🟡

📆 ቀን፡ ዛሬ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 12 (October 22)
ሰዓት፡ ምሽት 4:00 ሰዓት
🏟 ስታድየም፡ ሳንቲያጎ በርናቦው

ቅድመ ዳሰሳ

ክለባችን በዛሬው ዕለት የአምና የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ተጋጣሚውን በዘንድሮ ሲዝን በውድድሩ አሁን ግን በምድብ ጨዋታ ምሽት 4:00 ሲል የሚገጥም ይሆናል።

ሎስ ብላንኮቹ ባለፈው ሲዝን በውድድሩ ቢጫዎቹን በፍፃሜ ጨዋታ ሲገጥሙ 2ለ0 በሆነ ጣፋጭ ድል ውጤት አሸንፈው ዋንጫውን ከፍ አድርጓል።

ቢጫዎቹ የመጨረሻ ጨዋታቻውን በሊጉ አርብ ዕለት ጨዋታቸው ከአዲስ አዳጊውን ሴት ፓውሊ ማድረጋቸው የሚታወቅ ሲሆን 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

በአንፃሩ ባለሜዳው ክለባችን የመጨረሻ ጨዋታውን ቅዳሜ እለት ከሜዳው ውጪ ከሴልታ ቪጎ ጋር የተጫወተ ሲሆን በምባፔና ቪኒ ጎሎች 2ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

ጀርመኑ ክለብ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በቡንደስሊጋው 7 ጨዋታዎች ሲያደርግ 4 አሸንፎ፣ 1 አቻ ወጥቶና 2 ተሸንፎ በአጠቃላይ 13 ነጥብ ሰብስቦ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

እንዲሁም በዚህ የአውሮፓ መድረክ ዳግሞ 2 ጨዋታዎች ሲያደርገሰ ሁለቱንም በድል በመወጣት በአጠቃላይ 6 ነጥብ በመሰብሰብ ሊጉን በመምራት ላይ ይገኛል።

ክለባችን ሪያል ማድሪድ ዳግሞ ዳግሞ በላሊጋው 10 ጨዋታዎች ሲያደርግ 7 ድሎችና 3 አቻዎችን በማስመዝገብ 24 ነጥቦችን መሰብሰብ ችሏል።

በአውሮፓ መድረኩ በፈረንሳዩ ክለብ ሊል ያልተጠበቀ የ1ለ0 ሽንፈት አስደናግዶ ወደዚህ ጨዋታ የሚመጣው ክለባችን 3 ነጥብ ሰብስቦ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ይቀጥላል ...

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

22 Oct, 03:00


| ጨዋታ ቀን | MATCH DAY ...

👉 | የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨዋታ መርሐግብር!

⚪️ ሪያል ማድሪድ ከ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ 🟡

📆 ቀን፡ ዛሬ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 12 (October 22)
ሰዓት፡ ምሽት 4:00 ሰዓት
🏟 ስታድየም፡ ሳንቲያጎ በርናቦው

ድል ለክለባችን ሪያል ማድሪድ ይሁን! 🤍

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

22 Oct, 02:30


እንዴት አደራችሁ ማድሪዲስታስ ?

መልካም የጨዋታ ቀን ይሁንላችሁ! 🤍

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

21 Oct, 20:29


መልካም አዳር ማድሪዲስታስ 🤍

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

21 Oct, 18:42


አርዳ ጉለር ከዶርትሙንድ እና ከባርሴሎና ጋር በሚደረጉት ጨዋታዎች የጨዋታ ደቂቃዎችን የማግኘቱ ነገር ከባድ ነው።

[Diario AS] 🥈

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

21 Oct, 18:20


“ ነገ ከሪያል ማድሪድ ጋር የምናደርገው ጨዋታ ለቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜው የበቀል ግጥሚያ አይሆንም።”

“አርዳ ጉለር የተለየ ነው፤ በጣም ስኬታማ እንዲሆን እመኝለታለሁ። ኢንሻ አላህ ምናልባት አንድ ቀን የእሱ አሰልጣኝ እንደምሆን ተስፋ አደርጋለሁ።”

“ከአርዳ ጉለር ጋር በየቀኑ እናገራለሁ እሱ እንደ ታናሽ ወንድሜ ነው፤ ከሪያል ማድሪድ እና ከቱርክ ብሄራዊ ቡድን ጋር ብዙ ዋንጫዎችን እንደሚያሸንፍ ተስፋ አደርጋለሁ።”

ኑሪ ሻሂን፡ (የቦርሲያ ዶርትሙንድ አሰልጣኝ)

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15

ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

21 Oct, 18:09


የጣልያኑ ክለብ የዩቬንቱስ ኦፊሻል የቲውተር አካውንት ተጠልፎ ከላይ የተያያዘው ልጥፍ ተለቆበት ነበር። 😁

@ETHIO_REAL_MADRID_15
@ETHIO_REAL_MADRID_15