4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

@sport_433et


ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!

➮የሃገር ቤት ትኩስ ትኩስ መረጃዎች
➮የአፍሪካ መረጃዎችን በሙሉ
➮የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ሙሉ መረጃ
➮ቁጥራዊ መረጃዎች እና ዳሰሳዎች
➮ጨዋታዎችን በቀጥታ ከየስታዲየሙ

➮በስልክ ጥሪ ምንም አይንት የማስታወቂያ ስራ አንቀበልም!

ለማስታወቂያ ስራ @Promotion_4_3_3_Bot

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10

⓸-⓷-⓷ስፖርት በኢትዮጵያ| 2017

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ™ (Amharic)

የምስጋና በኢትዮጵያ! የስፖርት 4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ™ በምንጻወት ነው? ለማለት ማን ነው? ይህ ቡድን ወይም ኮምፒውተር እና የምኞት 4-3-3 ውድ አጋር ላይ ያለ የስፖርት ቡድን ነው። ሰላም ፊልድ። ውሽጣዊ የአፍሪካ ቆይታዎችን ለመስበር እና የአውሮፓ ታላላቅ እና ሁኔታዊ መረጃዎች ሊጎች ለመስበር እና። ዝግጁ ጨዋታዎችን በቀጥታ ከየስታዲየሙ። ያገኙ ለመስበር ምንም አይነት ማስታወቂያ ስራ በቀጣይ ስልክ ጥሪ እስከ @Promotion_4_3_3_Bot ፡፡ የቡድን ፕሮማሽን ሊመሰል እንደሚችል ውሽጣዊ ጠቃሚ @Simera10። በኢትዮጵያ በትኩስ 2017 ቦቅደው።

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 12:03


ኤሪክ ቴን ሃግ ፦

" ሞሪኒዮን መግጠም ያዝናኛኛል ምክንያቱም እሱ ታላቅ እና ብዙ ዋንጫዎችን ያሸነፈ አሰልጣኝ ነው ፤ በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት ዋንጫ አሸንፎ አልፏል ፤ ስለዚህ ከእንደዚህ አሰልጣኝ ጋር መፋለም ትልቅ ክብር ነው ።" ሲል ተናግሯል ።

@Sport_433Et @Sport_433Et

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 11:44


ቶኒ አዳምስ አርሰናል ዕድል ከቀናው በዋንጫ ይከብራል ሲል ተናግሯል ፡

"አርሰናል የፕሪሚየር ሊግ እና የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ ይችላል።"

"ይህን ያልኩት ከመሬት ተንስቼ አየደለም እንደምናስታውሰው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ቶተንሃም ለቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ መድረስ ችሎ ነበር ታዲያ ቶተንሃም ለፍፃሜ መድረስ ከቻለ ሁሉም ክለብ ለፍፃሜ መደረስ ይችላል ማለት ነው ከሱ አልፎም እንደ 2005ቱ ሊቨርፑል ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን የማንሳት ቁመና ላይ ሳይሆኑ በዕድል ማሸነፍ ይችላል።"

"አርሰናል ከቶተንሃም ፍፃሜ መድረስ እና እንደ ሊቨርፑል ቻምፒየንስ ሊግ ለመብላት የጎደለው ቡድን ሳይሆን ትንሽ ዕድል ነው።"

@SPORT_433ET @SPORT_433ET

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 11:34


የዛሬ ጨዋታዎች ግምት - 🗞

@SPORT_433ET @SPORT_433ET

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 10:42


ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ካፍ የኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ ጥያቄ ተቀብሎ እንዲያጸድቅ ጥሪ አቀረቡ !

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) የኢትዮጵያን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ ጥያቄ እንዲቀበል እና እንዲያጸድቅ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ጥሪ አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ትላንት ለፊፋ ፕሬዚዳንቶችና ለካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከፍተኛ አመራሮች በታላቁ ቤተ-መንግስት ባደረጉት የእራት ግብዣ ወቅት ኢትዮጵያ በ2029 የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ የማዘጋጀት አቅም አላት ማለታቸው ይታወሳል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል እየተካሔደ ባለው 46ኛው የካፍ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አፍሪካውያን ቤታችሁ ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ እግር ኳስ ትልቅ አሻራ እንዳላትና እ.አ.አ በ1957 ካፍ ሲመሰረትም መስራች ከነበሩ አገራት መካከል አንዷ መሆኗን ገልጸዋል።

የካፍ ፕሬዝዳንት የነበሩት ይድነቃቸው ተሰማ የአፍሪካ እግር ኳስ በዓለም መድረክ የሚገባውን ቦታ እንዲያገኝ የበኩላቸውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እግር ኳስ ወዳዶች ያሉባት አገር ናት ብለዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ እግር ኳስ ያላትን ታሪካዊ ድርሻ ከግምት በማስገባት እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ጥያቄ ማቅረቧን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫውን ተጠቅማ የአፍሪካን እግር ኳስ ለማሳደግና በስፖርቱ አገር ለመገንባት እንደምትሰራ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ስታዲየሞች እየገነባች ናት ያሉት ላይ ማሻሻያ እያደረገች እንደምትገኝ አመልክተዋል።

ካፍ የኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ ጥያቄ ተቀብሎ እንዲያጸድቅም ፕሬዝዳንት ታዬ ጠይቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ምንጭ:- የኢ ፕ ድ

@SPORT_433ET @SPORT_433ET

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 09:45


#OFFICIAL

አንቶኒ ቴይለር በመጪው እሁድ በግዙፉ ኤምሬትስ አርሰናል ከሊቨርፑል የሚያደርጉትን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመራሉ።

@SPORT_433ET @SPORT_433ET

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 09:37


የስፔን ላሊጋ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን !

[WHO SCORED]

@SPORT_433ET @SPORT_433ET

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 09:00


🚨 ባየር ሙኒክ እና ማርሴ ከማንቸስተር ዩናይትድ ማርከስ ራሽፎርድን ለማስፈረም በሚደረገው ፉክክር ፒኤስጂ ተቀላቅለዋል።

[TEAMtalk]

@SPORT_433ET @SPORT_433ET

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 08:53


ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ በአውሮፓ በሚኖረው የአየር ፀባይ ለውጥ ምክንያት የሚደረጉ ጨዋታዎች በሙሉ ለ1 ሰዓታት ያክል ወደ ፊት ይገፋሉ።

ፕሪምየር ሊግ ከቅዳሜ ጀምሮ ሌሎቹ ሊጎች ከእሁድ ጀምሮ የሰዓት ሽግሽግ ያደርጋሉ!

😴 የማታ 5 ሰዓት ጨዋታዎች ሊመለሱ ነው

@SPORT_433ET @SPORT_433ET

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 08:35


በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በስምንት የፕሪምየር ሊግ ሳምንታቶች ውስጥ አራት ክለቦች ምንም አይነት ድል ማስመዝገብ አልቻሉም።

[OPTA]

@SPORT_433ET @SPORT_433ET

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 08:31


ፍራንቺስኮ ቶቲ በ48 አመቱ ወደ ሜዳ ሊመለስ?

ጣልያናዊው የአለም እግር ኳስ ዋንጫ አሸናፊ በጡረታ ከተገለለ ከሰባት አመታት በኋላ ወደ ጨዋታ ሊመለስ መሆኑን አስታውቋል።

የቀድሞ ጣልያናዊ ኮከብ ወደ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ህይወቱ በሁለት እና ሶስት ወራት ውስጥ ለመመለስ መወሰኑን አስታውቋል።

የሮማ እግር ኳስ ክለብ የምንግዜውም ኮከብ ተጫዋች በድጋሚ በሴሪአው ለመጫወት አንዳንድ ክለቦች እንዳነጋገሩት አስታውቋል። የ48 አመቱ ጎልማሳ ከ25 አመታት የሮማ እግር ኳስ ክለብ ቆይታ በኋላ በ2017 በይፋ ጫማውን መስቀሉን ማስታወቁ አይዘነጋም።

በቆይታው አንድ የሴሪአ ዋንጫን ማሳካት የቻለ ሲሆን የምንግዜውም የክለቡ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ከመሆኑ በተጨማሪ ብዙ ጨዋታዎችን ለዋና ከተማው ክለብ ማድረግ የቻለ ነው።

ፍሬንቺስኮ ቶቲ በ2006 ከጣልያን ብሄራዊ ቡድን ጋር የአለም እግር ኳስ ዋንጫን በማርቼሎ ሊፒ ስርም ማንሳት ችሏል።በወቅቱ ከውድድሩ በፊት ጉዳት አስተናግዶ ከህመሙ ጋር እየታገለ በመድረኩ ሁሉም ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሎ ነበር።

ዝላታን ኢብራሂሞቪች በአንጋፋ እድሜው በድጋሚ ወደ ሴሪአው ክለብ ኤሲ ሚላን ተመልሶ ከተጫወተ በኋላ ቶቲ የሚሳካላት ከሆነ በአንጋፋ እድሜ ላይ ሆኖ በሴሪአው ከግብ ጠባቂ ውጭ የተጫወተ ተጫዋች በመሆን ሪከርዱን ይይዛል።[ሳምሶን አበበ]

@SPORT_433ET @SPORT_433ET

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 08:31


🇺🇸 በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ሚመጣ እድል ነው ባሉበት ቦታ ሆናችሁ መምላት ትችላላችሁ ፈጥነው እድሎን ይሞክሩ🔥

እና ምን ይጠብቃሉ?

📥 TELEGRAM: @dv2025et

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 08:31


ሜልቤት በውርርድ ዓለም ውስጥ ታማኝ አጋርዎ ነው! በእያንዳንዱ በከፍተኛ ውርርድ ዕድሎች እና ጨዋታዎች
ይደሰቱ ይቀላቀሉ እና ለመጀመሪያ ተቀማጭ ገንዘብ ጉርሻ ይቀበሉ! የማስተዋወቂያ ኮድ “QUICKCASH" ይጠቀሙ እና በመጀመሪያ ተቀማጭ ገንዘብ 100% ጉርሻ ያግኙ፡- https://refpakrtsb.top/L?tag=d_3755584m_45415c_&site=3755584&ad=45415

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 08:31


🚨አዲስ ነገር ስለ ተመላሽ ገንዘብ🚨
በ 10 ጨዋታዎች ላይ ውርርድ አድርገዋል ነገር ግን አንዷ ጨዋታ ሁሉንም እንዲያጡ ሊያደርጎት ነው?
አያስቡ!!!
በላሊቤት የቆረጡበትን ብር እስከ 10 ጊዜ ተመላሽ ማድረግ ይችላሉ።

https://help.lalibet.et/promotions/refund-stake/
👉🏻አሁን ደንበኞቻችን ካሉበት ቦታ ሆነው ቻፓ💱💲💷 እና ሌሎች አማራጭ ባንኮችን ገንዘብ ለመውጣትና ተቀማጭ ለማድረግ ለመጫወት መጠቀም እንደሚችሉ ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው!

𝗪𝗘𝗕𝗦𝗜𝗧𝗘👉🏻 https://copartners.lalibet.et/visit/?bta=35071&brand=lalibet
𝗧𝗘𝗟𝗘𝗚𝗥𝗔𝗠👉🏻 https://t.me/lalibet_et
𝗙𝗔𝗖𝗘𝗕𝗢𝗢𝗞👉🏻 https://www.facebook.com/LalibetET
አሁኑኑ ይጫወቱ እና ብዙ ብር ያሸንፉ!
LALIBET- WE PAY MORE!!!
Contact Us on 👉- +251978051653

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 07:40


📊 የአታላንታዉ ተጫዋች ማሪዮ ፓሳሊች በጣሊያን ሴሪያ ታሪክ ብዙ ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ክሮሽያዊ ተጫዋች ሆኗል።

@SPORT_433ET @SPORT_433ET

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 06:40


ከስምንተኛ ሳምነት መጠናቀቀ ቡኋላ የሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ !

@SPORT_433ET @SPORT_433ET

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 06:28


የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት ውጤቶች

@SPORT_433ET @SPORT_433ET

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 06:20


በዚህ የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን የኖቲንግሃም ፎረስት ውጤት !

1-1 vs. በርንማውዝ
✔️1-0 vs. ሳውዝሃምፕተን
1-1 vs, ዎልቭስ
✔️1-0 vs. ሊቨርፑል
2-2 vs. ብራይተን
1-0 vs. ፉልሃም
1-1 vs. ቼልሲ
✔️1-0 vs, ክርስቲያል ፓላስ

አንድ ሽንፈት ብቻ ነው ያስተናገዱት እሱንም በፉልሃሙ ጨዋታ !👏

@SPORT_433ET @SPORT_433ET

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 06:13


ከኖቲንግሃም ፎረስት ያለፉት 10 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ውስጥ 7ቱ ጎሎች የተቆጠሩት በክሪስ ውድ ነው።

@SPORT_433ET @SPORT_433ET

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 06:07


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)በመድረኩ

" ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እግር ኳስ መሰረት የጣለች ሀገር ብትሆንም በነበሩ የተለያዩ ችግሮች ስፖርቱ በሚገባው ደረጃ አለማደጉን ተናግረዋል፡፡

ሀገሪቱ የተለያዩ የኢኮኖሚ እና ፖለቲካዊ ሪፎርሞች እያካሄደች መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አሁን ላይ በስፖርቱ በተለይም በእግር ኳስ ዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የመሰረተ-ልማት መሻሻያ እና ተያያዥ የለውጥ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

የካፍ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሙትሴፔ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የ2029ኙን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ካፍ ከኮሚቴው ጋር እንደሚመክርበት ተናግረዋል።

@SPORT_433ET @SPORT_433ET

4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ

22 Oct, 06:01


“የአዲስ አበባ ስታድየም ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ለማስተናገድ ዝግጁ ይሆናል።” - የባህልና ስፖርት ሚኒስትር የነበሩት አቶ ቀጄላ መርዳሳ ሐምሌ 16 / 2015 ዓ/ም የተናገሩት

"የተጀመሩ ስታዲየሞችን የማጠናቀቅ ብቃትም ተነሳሽነትም አለን" - የወቅቱ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ ትላንት ጥቅምት 11 / 2017 ዓ/ም የተናገሩት

don't tell them show them እንዳለው የፈረንጅ አበው ወሬ በቅቶናል 🤙

@SPORT_433ET @SPORT_433ET