Tikvah-University

@tikvahuniversity


Tikvah-University (English)

Welcome to Tikvah-University, a Telegram channel dedicated to providing valuable educational content for individuals seeking to expand their knowledge and skills. Whether you are a student looking to enhance your learning experience, a professional aiming to develop new competencies, or simply someone who loves to learn, Tikvah-University is the perfect platform for you. Our channel features a wide range of topics, including science, technology, business, arts, and more, presented in an engaging and informative manner. Join our community of learners and gain access to exclusive resources, study materials, webinars, and discussions that will help you reach your academic and personal goals. With Tikvah-University, the possibilities for learning are endless. Start your educational journey with us today and unlock your full potential!

Tikvah-University

22 Oct, 12:47


ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በተቋሙ የሪሚዲያል ተማሪዎች የነበራችሁና የማለፊያ ነጥብ ያሰመዘገባችሁ እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳችሁ በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ጥቅምት 21 እና 22/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ መያዝ የሚኖርባችሁ፦
▪️ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ
▪️ አራት 3x 4 ጉርድ ፎቶግራፍ

የምዝገባ ቦታ፦
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጀኔራል ታደሰ ብሩ ከምፓስ

@tikvahuniversity

Tikvah-University

22 Oct, 07:16


#ጥቆማ

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለ2017 ትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ሰልጣኞችን መመዝገብ ጀምሯል፡፡

መስፈርቶች
▪️የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆነ/የሆነች፣
▪️በ2015/16 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የማለፊያ ውጤት (50%) ያለው/ያላት፣
▪️በ2014/15 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትለው ያጠናቀቁ

ስልጠናው በአዲስ አበባ ላምበረት መናኸሪያ አካባቢ በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ግቢ የሚሰጥ ሲሆን፤ በተጨማሪም የቻይንኛ እና ኮሪያኛ ስልጠናዎች ይሰጣሉ፡፡ ኢንስቲትዩቱ የምግብ እና የዶርም አገልግሎቶች ያቀርባል፡፡

የምዝገባ ጊዜ፦
ጥቅምት 11-15/2017 ዓ.ም
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ፦
ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም
ትምህርት የሚጀምረው፦
ኅዳር 2/2017 ዓ.ም

አስፈላጊ ሰነዶች
▪️ የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
▪️ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሰርተፊኬት
▪️ የሪሚዲያል ፕሮግራም ሰርተፊኬት

@tikvahuniversity

Tikvah-University

22 Oct, 07:04


#DebreTaborUniversity

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡

በዚህም በ2016 ዓ.ም አንደኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የነበራችሁ የደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ትምህርት የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 25 እና 26/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በ2016 ዓ.ም በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተቋሙ መሔድ ያልቻለችሁና ዊዝድሮዋል መሙላት ሳትችሉ የቀራችሁ ተማሪዎች በዚህ ዓመት ትምህርታችሁን ከቀጣይ ባች ጋር መቀጠል እንድትችሉ ዩኒቨርሲቲው ስለፈቀደ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

በ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ዓመት የምትቀላቀሉ (2016 ዓ.ም ሪሚዲያል የነበራችሁ እና አዲስ የምትመደቡ) ተማሪዎች በሌላ ማስታዎቂያ ጥሪ ይደረግላችኋል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity

Tikvah-University

22 Oct, 07:03


💫 ከዳር እስከ ዳር በፈጣኑ የሳፋሪኮም ኢንተርኔት! እንገናኝ! የተመቸንን ሼር እናድርግ! 👍 ከወደድነው ጋር እንደልብ እንገናኝ!

አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!

የቴሌግራም ቦታችንን https://t.me/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether

Tikvah-University

22 Oct, 07:03


የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም 14ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Principles and Practices of Accounting) የአምስት ወር የቅዳሜ እና እሑድ ስልጠና  ይጀምራል።  

👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ የአካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Tikvah-University

21 Oct, 16:49


#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

➤ የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የሙያ መስኮች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 71
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ከ2ኛ ዲግሪ ጀምሮ
➤ የሥራ ልምድ፦ አይጠይቅም
➤ የሥራ ቦታ፦ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ
➤ የማመልከቻ ጊዜ፦ ከጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሰባት (7) ተከታታይ የሥራ ቀናት

የምዝገባ ቦታ፦
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ (በሁሉም ግቢዎች) የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ

ለበለጠ መረጃ፦ 0471350151 / 0473360159

(ዩኒቨርሲቲው ያወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity

Tikvah-University

21 Oct, 13:12


#MoE

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ እንደሚገለፅ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች፣ ምደባው ይፋ እስከሚደረግ በትዕግስት እንዲጠብቁ ሚኒስቴሩ ጠይቋል፡፡

@tikvahuniversity

Tikvah-University

21 Oct, 12:12


የ2017 ስልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና የመቁረጫ ነጥብ:

የተፈጥሮ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት

የስልጠና ደረጃ 1 እና 2
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 141 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 137 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 138 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 134 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 124 እና ከዚያ በታች፡፡

የስልጠና ደረጀ 3 እና 4
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 142 ከዚያ በላይ፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 138 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 139 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 135 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 125 እና ከዚያ በላይ፡፡

የስልጠና ደረጀ 5
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 179 ከዚያ በላይ፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 167 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 170 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 162 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 154 እና ከዚያ በላይ፡፡


የማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት

የስልጠና ደረጃ 1 እና 2
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 ከዚያ በታች፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 135 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 134 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 124 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 124 እና ከዚያ በታች፡፡

የስልጠና ደረጀ 3 እና 4
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 140 ከዚያ በላይ፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 136 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 135 እና እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 125 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 125 እና ከዚያ በላይ፡፡

የስልጠና ደረጀ 5
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 172 ከዚያ በላይ፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 164 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 165 እና እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 160 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 154 እና ከዚያ በላይ፡፡

@tikvahuniversity

Tikvah-University

21 Oct, 09:59


የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ዛሬ ይፋ ተደርጓል።

የመቁረጫ ነጥቡ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia

Tikvah-University

21 Oct, 08:03


#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለነባር አንደኛ፣ ሦስተኛ እና አራተኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡

በዚህም የነባር አንደኛ፣ ሦስተኛ እና አራተኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ጥቅምት 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በቅጣት ምዝገባ ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም ብቻ ሲሆን፤ ትምህርት ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2016 ዓ.ም አዲስ አንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል ፕሮግራም በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity