TIKVAH-ETHIOPIA

@tikvahethiopia


ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

TIKVAH-ETHIOPIA (Amharic)

ቲክቫህ-ኢትዮጵያ በሚል እና በየትምክስ በሚባለው እግር እና ውስጣው ላቀማጥለን የብቻ ህዝብ ነን። ቲክቫህ-ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ስለኖርና እንባዮው ዘግናኘነት እንደሚታደግ በመሆን እናሸንፋለን። ቲክቫህ-ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ይህን ትክክለኛ መረጃን እና መልዕክቱን ስለሚሰጥ ለአዝሙድ ወይም ለተማከስን ለክፍል ቴሌግራም እንዲሁም በሌላ ስህተት ያግኙን። ለተጨባነሁት ቲክቫህ መረጋጋችንን እና ላቀማጥነትን መረጃን ለመሰረት አድርገን እናመላክምን። የሚሰሩት ለመረበን እና ያንን አገልግሎትን ከመጠበቅና ከሌላ ምስሎት ከተነሳ እናመላክም። ቲክቫህ-ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ለማንበብ በዚህ ቦታ ተከታታይ አካል መሰብሰቢያ እና መልዕክት መለዋወጫ ማንበብ እንድና ከሌላ ምስሎት መልዕክተኞችን እናከብር ቢችል፣ ዛሬ በደንብ ወኔ ምልክቱ አለ።

TIKVAH-ETHIOPIA

22 Oct, 09:46


ፎቶ ፦ ' መርካቶ ሸማ ተራ ' ከትላንት ምሽቱ ከባድ የእሳት አደጋ በኃላ ዛሬ ከላይ በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስላል።

ከቆርቆሮ እና ከኮነቴነር ቤቶች አቅራቢያ ወዳለው ' ነባር የገበያ ማዕከል (ህንጻ) ' የተዛመተው እሳት የህንጻውን አንደኛውን ክፍል ክፉኛ አውድሞታል።

እስካሁን ሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት ሪፖርት አልተደረገም።

በትላንት ምሽቱ የእሳት አደጋ ምንም እንኳን ይፋዊ የጉዳት መጠን ባይገለጽም የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው።

በርካቶች ብዙ የደከሙበት ንብረታቸው በአንድ ምሽት ወደ አመድነት ተቀይሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፥ " በአደጋው የደረሰውን የጉዳት መጠኑን የተመለከተ ዝርዝር ጥናት ተደርጎ ከባለሃብቶች እና ከህብረተሰቡም ጋር በመሆን በፍጥነት መልሶ የማቋቋም ስራ ይሰራል ፤ ቦታውንም ወደ ቀደመው የንግድ ተግባር እንዲመለስ የማድረግ ስራ እንሰራለን "  ብሏል።

@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA

22 Oct, 09:45


#AddisAbaba

በርካታ ቦታዎች በሊዝ ጨረታ እንዲሸጡ ቀረቡ።

አዲስ አበባ ውስጥ 143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ለሊዝ ጨረታ መቅረቡ ተሰምቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ 143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር መሬት ለሊዝ ጨረታ እንደቀረበ አሳውቋል።

የሊዝ ጨረታው ከጥቅምት 8 እስከ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ክፍት መደረጉ ነው የተሰማው።

ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውጭ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለጨረታ የቀረቡ መሬቶች መኖራቸው ተነግሯል።

ይህ ከ2016 ዓ.ም ወዲህ 4ኛው ዙር የሊዝ ጨረታ ነው።

143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር መሬት / ቦታ ለሊዝ ጨረታ ሲቀርብ በከተማ አስተዳደሩ ታሪክ በቁጥር ከፍተኛው እንደሆነ ቢሮው መግለፁን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ተጨማሪ መረጃ ፦

🔴 ለአንድ የጨረታ ሰነድ የሚከፈለው የማይመለስ ብር 2,300 ብር ነው ተብሏል።

🔴 የጨረታውን ሰነድ ከጥቅምት 08/2017ዓ.ም እስከ ጥቀምት 21/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ በ (
2merkato.com link :- https://addisland.2merkato.com ወይም afrotender.com link:-https://addisland.afrotender.com) ላይ ነው መግዛት የሚቻለው።

🔴 ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ እንዳለባቸው ተገልጿል።

🔴 አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም፡፡ ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኝ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል ተብሏል።

የጨረታ ቁጥር እና የቦታዎቹን ኮድ እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች በዚህ ማግኘት ይቻላል :
https://www.aalb.gov.et/blogs/detail/72

@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA

22 Oct, 09:43


🔈 #የሰራተኞችድምጽ

" የምንሰራው ስራና የሚከፈለን ወርሃዊ ደመወዝ አይመጣጠንም ፤ ድካማችንን የሚመጥን ክፍያ አናገኝም " - ሰራተኞች

በብረታ ብረትና ሞደፊክ ስራዎች የተሰማራው ከትእምት (EFORT) ግዙፍ ድርጅት አንዱ በሆነ መስፍን ኢንዳትሪያል ኢንጅነሪነንግ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የመብት ጥያቄ እንዳላቸው ገለጹ።

ሰራተኞች ዛሬ ስራ በማቆም ወደ ትእምት ( ትግራይ መልሶ ግንባታ) ዋና ቢሮ በመጓዝ " የመብት ጥያቂያችን ይመለስ " ብለዋል።

ብዛታቸው ከ150 በላይ የሆኑ ሰራተኞቹ ፦

➡️ የሚሰሩት ስራና የሚከፈላቸው ወርሃዊ ደመወዝ እንደማይመጣጠን፤

➡️ በድርጅቱ በቀን አስከ 20 ሰዓታት የሚሰሩ ሰራተኞች ቢኖሩም የሚያከፈላቸው ከፍያ እጅግ አነስተኛ መሆኑ፤

➡️ ደርጅቱ አትራፊ ቢሆንም ለሰራተኞቹ የሚከፍለው ደመወዝ እጅግ አነስተኛ እንደሆነ፤

➡️ ከጥቅማጥቅም ፣ ያልተከፈለ ውዙፍ ደመወዝና የሰራተኛ ቅጥር ጋር የተያየዘ ጥያቄ እንዳላቸው ገልጸዋል።

" ለረጅም ጊዜ የመብት ጥያቄያችንን የሚመጥን አስቸኳይ መልስና መፍትሄ እንፈልጋለን " ብለዋል።

ለሰራተኞቹ ዘግይተው መልስ የሰጡት የትእምት የሰው ሃይል አስተዳደር ተኽለወኒ ገ/መድህን ፥ " ቀጣዩ አርብ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም ከትእምት ኢንደውመንት አመራሮች በጋራ በመሆን ጥያቄያችሁ እናደምጣለን " በማለት ሸኝተዋቸዋል።

መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪነንግ በብረታ ብረትና ሞደፊክ ስራዎች የተሰማራ ከትእምት (EFORT) ግዙፍ ካምፓኒዎች አንዱ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            

TIKVAH-ETHIOPIA

22 Oct, 09:43


#Infinix_TV

አዲሱ ኢንፊኒክስ TV X5 ከጥግ እስከ ጥግ ያለምንም የስክሪን ገደብ እየተመለከቱ እስኪመስሎት ድረስ ፍሬም አልባ ወይም Bezel Less ተደርጎ ተመርቷል ይህም በቴሌቭዥኖት የሚያዩት ምስልን ከዕውነታ መለየት እሰኪያቅት ድረስ ልዩ ያደርገዋል፡፡

@Infinix_Et | @Infinixet

#InfinixTVX5 #Infinix #ElevateYourSpace #Perfectview #tvx5

TIKVAH-ETHIOPIA

22 Oct, 09:42


የአቢሲንያ ስኩል ማኔጅመንት ሲስተም ኢ-ላይብረሪ የትምህርት እና አጋዥ መጻሕፍት ዳውንሎድ በማድረግ መጠቀም ያስችላል፡፡

የአቢሲንያ ባንክ ፌስቡክ ፔጅን ሊንኩን በመጠቀም ይቀላቀሉ፡ https://www.facebook.com/BoAeth

#BoAschoolmanagement #school #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

TIKVAH-ETHIOPIA

22 Oct, 08:14


#BRICS+

16ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በሩሲያ ይጀመራል።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ለመሳተፍ ካዛን ከተማ ገብተዋል።

ከኢትዮጵያ መሪ በተጨማሪ ፥
- የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን
- የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬድራ ሞዲ
- የደቡብ አፍሪካው ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ ሩስያ፣ ካዛን ገብተዋል።

የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ እንዲሁም የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ፣ ሌሎችም መሪዎች እና የሀገራት ተወካዮች ወደ ሩስያ እያቀኑ ይገኛሉ።

Video Credit - RT

@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA

22 Oct, 07:48


ምርጫ ቦርድም የክፍያ ጭማሪ አደረገ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአገልግሎት ክፍያ ላይ ጭማሪ አድርጓል።

እስካሁን ድረስ ፦

➡️ ለሀገር አቀፍና ለክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ ሰርተፊኬት ለማግኘት 100 ብር፤

➡️ ለሙሉ ዕውቅና ለሀገር አቀፍና ክልላዊ ፓርቲ 200 ብር፤

➡️ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰረታዊ ሰነዶቻቸውን በጉባኤ አሻሽለው ሲያቀርቡ 30 ብር ይከፍሉ ነበር።

አሁን በተደረገው ጭማሪ ፦

🟢 ጊዜያዊ ዕውቅና ክፍያ 👉 15,000 ብር (አስራ አምስት ሺህ ብር)

🟡 የሙሉ ዕውቅና ክፍያ 👉 30,000 ብር (ሰላሳ ሺህ ብር)

🔴 የሰነድ ማሻሻያ ክፍያ 👉 5,000 ብር (አምስት ሺህ ብር) ገብቷል።

@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA

22 Oct, 07:47


#ሶማሌክልል

" መሳሪያ አንግበው በጫካ እየታገሉ ያሉ ሰዎች በሌሉበት ምክክሩ የተሳካ ይሆናል የሚል ግምት የለንም  "- ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በሶማሌ ክልል ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር አጀንዳ የመሰብሰብ የምክክር ምዕራፍ እያደረገ ነው።

ከባለድርሻ አካላት መካከል የፓለቲካ ፓርቲዎች ተጠቃሽ ሲሆኑ፣ በውይይት መድረኩ የተገኘው ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ከቲክቫህ ኢትዮጵያና ሌሎች ሚዲያዎች ጋር ቆይታ አድርጓል።

ስለውይይቱን ሂደት፣ የኮሚሽኑን አካታችነት፣ የታጠቁ ኃይሎች፣ የባሕር በርን በተመለከተ ጥያቄዎች የቀረቡላቸው የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ኢሴ ባናሃጂ አቡቦከር ምላሽ ሰጥተዋል።

ምን አሉ?

" የኢትዮጵያዊያን ግጭትን የምናስወግድበት የራሳችን ባህሎች አሉን። ባህሎቻችንን ባለመከተል በአገራችን ብዙ ችግሮች እየተከሰቱ ስለሆነ እነዚህን ችግሮች ይቀርፋል ተብሎ ነው መድረኩ የተዘጋጀው።

በመድረኩ የሶማሌ ህዝብን ወክለን መጠየቅ ያለብንን ነገር እየተወያዬን ነው።

(ለምሳሌ ህዝቡ ከዚህ በፊት በነበሩት መንግስታት የደረሰበት በደል፤ ቅሬታ፣ ቁስል አለው)፤ በቅድሚያ ህዝቡ ያለበት ቁስል ይታከም። ብዙ አጀንዳዎች አሉ።

ከአካታችነት አንጻር እኛ እንደ ፓለቲካ ፓርቲ አገራዊ ውይይቱ የበለጠ ውጤታማ ይሆናል ብለን የምንጠብቀው በመድረኩ ያልተካተቱ ሰዎች ቢካተቱበት ነው።

መሳሪያ አንግበው በጫካ እየታገሉ ያሉ ሰዎች በሌሉበት ምክክሩ ሰክሰስፉል ይሆናል የሚል ግምት የለንም። 

እነርሱ እንዲካተቱ ነው እንደ ፓለቲካ ፓርቲ ደጋግመን እየጠየቅን ያለነው። መድረኩ ለማንም የሚጠቅም እንጂ ማንም የሚከስርበት አይደለም። 

መሳሪያ አንግበው በጫካ እየታገሉ ያሉ አካላትም ወደ መድረኩ መጥተው ሀሳባቸውን አቅርበው በሚያግባባን ሀሳብ እንድንግባባ፣ በማያግባባ ሀሳብ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ተሰብስቦ ሪፈረንደም እንዲያደርግ ነው አስተያየት የምንሰጠው
" ብለዋል።

በመድረኩ የተዳሰሱ ጉዳዮችን በተመለከተም፣ " የፓለቲካ ፓርቲዎች እንደ ጥያቄ ያቀረቡት አጀንዳ፣ ለምላሌ የኛ ፓርቲ፣ አሁንም አገራችን እየተመራችበት ያለውን ፌደራሊዝም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ሌላው የኢትዮጵያ ባንዲራን በተመለከተ ነው። ስለኢትዮጵያ ባንዲራ የኛ ፓርቲ ያለው አመለካከት ባንዲራው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ አይወክልም የሚል ነው " ብለዋል።

" ስለዚህ አሁን ያለው ባንዲራ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉ አንድ ላይ በመሆን ሁሉንም የሚወክል ምልክት ተደርጎበት ባንዲራ ላይ ለውጥ እንዲደረግ የሚል አስተያየት ነው ያቀረብነው " ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ መንግስት ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የባሕር ወደብ በተመለከተ ተጠይቀው ባደረጉት ገለጻ፣ " እንደ ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ኢትዮጵያ የባሕር ወደብ እንድታገኝ በጣም እንፈልጋለን " ብለዋል።

" ግን እንደ ፓርቲነት ይሄን ባሕር የምንፈልገው ከዚህ በፊት የባሕር በር የሌላቸው ብዙ የአፍሪካ አገሮች ባሕር ያገኙበትን መንገድ ተከትለን ኢንተርናሽናል ሕግ በሚፈቅደው ሁኔታ እንዲሆን ነው " ሲሉ አክለዋል።

ኢትዮጵያ ከሱማሌላንድ ጋር ባደረገችው የባሕር በር ሥምምነት ክልሉ ያደረበት ስጋት አለ? ተብሎ ለቀረበላቸው በምላሻቸው፣ " አዎ። ኢትዮጵያ መንግስት ከሱማሌላንድ ጋር ያደረገው ሥምምነት እኛ ላይ አንዳንድ ስጋት ፈጥሮብናል " ነው ያሉት።

" ባሕር ያልነበራቸው አገሮች ከጎረቤት አገሮች ጋር ኢንተርናሽናል ሕግን መሠረት ባደረገ መንገድ ተፈራርመው ባሕር እየተጠቀሙ ነው። የነርሱን ልምድ በተከተለ መንገድ የባሕር በር ብናገኝ ፍላጎታችን ነው " ብለዋል።

የኦጋዴን ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ከሀገራዊ  ምክክሩ እንዳገለለ በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ያስታወቀ ሲሆን፣ ፓርቲው በዝርዝር ምላሽ እንዲሰጥ ለማድረግ ያደረግነው ጥረት ፓርቲው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለጊዜው አልተሳካም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA

21 Oct, 22:16


🔈#መርካቶ

" እኔ የመርካቶ ልጅ ነኝ፤ እዛውም ነው የምሰራው።

ዛሬ በአይኔ ያየሁት የእሳት አደጋ እጅግ አስከፊ ነው።

በጣም ብዙ ንብረት ወድሟል። የአላህ ጥበቃ ሆኖ እኔ በአካባቢዬ ላይ የሰው ህይወት አልተጎዳም።

ነገር ግን በእሳት አደጋው እጅግ በጣም አዝነን እያለ ተጨማሪ ሃዘን የፈጠረብን ብዙ አለ።

አንዱ የተለያዩ አካላት ለዝርፊያ ያደረጉት እንቅስቃሴ ነው።

አንዳንድ ሰው በዚህ የከፋ ጊዜ አብሮ ተጋግዞ እሳቱን ማጥፋት ሲገባው የራሱ ያልሆነን ንብረት ለመዝረፍ ሲሯሯጥ ማየት እጅግ ያሳዝናል።

ሌላው በየማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተከታይ ለማፍራት ሲባል ያልተባለውን በማለት፣ ያልተደረገውን ተደርጓል በማለት ' ላይክ ፣ ሼር ፣ ፎሎው ' አድርጉን እያሉ በዚህ የችግር ወቅት ያልተገባ ነገር የሚያደርጉ ሰዎችን መመልከቴ አሳስዝኖኛል።

አንዳንዶቻችን ህሊናችንን በዚህ ልክ ማጣታችን እጅግ አሳፋሪ ነው። ነገ እኛን ምን እንደሚገጥም እኮ አናውቅም።

ይህ ከባድ አደጋ እውነተኛ መንስኤው እና የጉዳቱ መጠን በፍጥነት እንዲጣራልን እንፈልጋለን።

ብዙ ለፍቶ አዳሪ ዜጋ እጅግ የደከመበት ፣ የለፋበት ንብረቱ በአንድ ምሽት ወደ አመድነት ተቀይሯል። " - ሃሚ (መርካቶ)

@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA

21 Oct, 21:12


#Update

" እዚህ ላይ ባይገታ እሳቱ ሰፊ አካባቢዎች ላይ  ደርሶ ህይወት ያጠፋ ነበር ፤ ሃብትም ይወድም ነበር " - አቶ ፍቅሬ ግዛው

በመርካቶ ሸማ ተራ የደረሰው ውድመት አሳዛኝ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው አሁናዊ ሁኔታውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኮሚሽነር ፍቅሬ ፤ " አሁን ላይ እሳቱን በቁጥጥራችን ስር አድርገናል ፤ የማጥፋትና የመልቀም ስራ ነው የሚቀረን " ብለዋል።

" እጅግ ከፍተኛ ርብርብ ተደርጎ እዚህ ላይ ባይገታ በጣም ብዙ ቦታ ፣ ሰፊ አካባቢዎች ላይ እሳቱ ደርሶ ህይወት ያጠፋ ነበር ፤ ከዚህ የበለጠ ሃብትም ይወድም ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።

" የአካባቢው አስቸጋሪትነት እሳቱን ለመቆጣጠር ረጅም ሰዓታት ወስዷል " ያሉት ኮሚሽነሩ " ከዚህ በኃላ ብዙ ጉዳት ያደርሳል ብለን አናስብም፤ ተቆጣጥረነዋል ማለት ይቻላል " ብለዋል።

" እሳቱ ዳግም እንዳይቀጥል ቦታውን አዳሩን በሙሉ ተቆጣጥሮ ቅሪት ነገሮች ካሉ እነሱን እያጠፋን እንቀጥላለን ፤ ህብረተሰቡ እሳት ሊያቀጣጥሉ የሚችሉ ነገሮችን ያስወግድ " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከስፍራው ካሉ ነዋሪዎች በደረሰው መልዕክት በእሳቱ በርካታ ንብረት መውደሙን ፣ ከቆርቆሮ ቤቶቹ ወጥቶ አጠገብ ያለ ህንጻ ተያይዞ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን፣ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ባይጠፋም ከቅድሙ አንጻር ሲታይ እሳቱ የከፋ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia