ዓረብ ሀገር በስደት የምትኖሪው እህቴ ሆይ❕ በመጀመሪያ የአሏህ የከበረ ሰላምታ ባ'ንቺ ላይ ይሁን❕አሰላሙ ዓለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ በመቀጠል ይህ የፅሁፍ መልዕክት ከወንድምሽ የሆነ ወንድማዊ ምክር ነው።
🛑 በመጀመሪያ ስደት የሄድሽበት ዓላማ እና አስገዳጅ ጉዳይ እንዳለ ይታወቃል። እርሱም እንዳ'ብዛሃኛው ሲታይ ዱኒያዊ ችግርን ከ'ራስሽም ከቤተሰብም ለማንሳት'ና የተሻለን ህይወት ለመመስረት ነው። ይህ ይሁኑ'ና ግን ብዙ እህቶች ከሄዱ በኋላ የተነሱበትን ዓላማ በመርሳት ወይም ችላ በማለት'ና የደወለላቸውን ወንድ ሁሉ በማመን ወዳ'ልጠበቁት ዉጥንቅጥ ህይወት ይገባሉ።
🛑 እየውልሽ እህቴ❕ ከመሄድሽ በፊት አንድም ቀን ሰላም ብሎሽ የማያቅ'ና ያን ሁሉ ችግር ከእናትሽ ጋር ስትጋፈጭ አንድም ቀን አይዞሽ ብሎሽ የማያቅ ወንድ ከሄድሽ በኋላ
📎"ሃይ ዉዴ ያገሬ ልጅ በጣም'ኮ ነው የማፈቅርሽ ከዛሬ ነገ እነግርሻለሁ ስል አመለጥሽኝ እንጅ...."&
📎"አሰላሙ ዓለይኩም... ደህና ነሽ ዉዴ ....." &
📎"ሰላም ሰላም መተዋወቅ ይቻላል ?...."
እያለ ሲጠጋሽ ሲያታልልሽ እንዴት ታምኚዋለሽ !? እንዴት'ስ በዚህ ቅፅበት ለተዋወቀሽ አካል ሙሉ እምነት አሳድረሽ ገንዝብሽን ትልኪያለሽ !? ቢያንስ ቢያንስ ይህን ስታደርጊ ያን የሰው ፊት ተገርፎ ብር ተብድሮ የላከሽን አባት ለምን አታማክሪም!? ትንሽ እንኳ አታስተነትኚም!?
🔴 ስሚኝማ ዉዷ እህቴ❕ ያ "የኔ ፍቅር! ብር ላኪልኝና ቤት እንስራ እኔም ስራ ልጀምርና ከዛ መጥተሽ የደስታ ህይወት እንኖራለን" የሚልሽ ወንድ እውነቱን ለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አለሽ❔ እሱ በምትልኪው ብር ምን እንደሚያደርግ ፤ የት እንደሚውል እና ከማን'ጋ እንደሚያድር ምን አሳወቀሽ❔
🔄 ከመቶ 90% ፐረሰንቱ ምን እንደሚያደርጉ ልንገርሽማ❗️
📎የሚውለው ጫት ቤት እና ቁማር ቤት፤
📎የሚያድረው እንዳንቺ በውሸት ካጠመዳት ሴት ጋር፤
📎ስራው እጁን ታጥቦ ጥብስ መብላት ፤ ጫት መቃም ፤ ከሴቶች ጋር መዝናናት... ወዘተ ነው።
ይህን ሁሉ ግን ሚስኪኗ እህቴ አታቂም❕ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ሰዎች ሲያስጠነቀቁሽ እንኳ አለመንቃትሽ ነው።
🔴 በመጨረሻ ቤቴ ተሰርቷል ብለሽ የቤት እቃዎችሽን እረትበሽ ትደውይና ናፍቀሺኛል ሲልሽ የነበረው እውነት መስሎሽ " ሰ ር ፕ ራ ይ ዝ... ማሬ በዚህ ወር ውስጥ እመጣልሃለሁ" ስትይው ምን እንደሚያደርግ ልንገርሽ ከሰማሽኝ፦
↪️ ደህና ሰው ከሆነ ስልኩን ዘግቶ ይጠፋል።
↪️ አሊያ ግን የለመደ ዉሸቱን ቀምሮ ቤቱ እንዳልተሰራ ወይም እንደተሸጠ ያስረዳሻል።
↪️ ወይም ከሴት ጋር ሁኖ ከሆነ የደወልሽበት ሊሰድብሽ እና መቸም ከአዕምሮሽ የማይወጣ ክፉ ቃል ሊናገርሽ ሁሉ ይችላል። ከዚያም የአዕምሮ ህመምተኛ ይመስል ብቻሽን ማውራት ትጀምሪያለሽ።
🔀በጣም የምታሳዝኚው ደግሞ አሁንም ዉሸቱን አምነሽ በድጋሜ ለሱ ብር ስትልኪ ወይም በሌላ ወንድ በድጋሜ ስትታለይና ስትነደፊ ነው።
🔴 በመጨረሻም ዉዷ እህቴ ❕ አደራ አደራ አደራ የምልሽ በበረሃ ሙቀት እየተቃጠልሽ የሰበሰብሽውን ገንዘብ ገና ትዳር ይሆነኛል በሚል አጉል ምኞት ለማንም ቦዘኔ አትበትኚ❕ ላ'ንቺ ከእናትና ከአባትሽ ከቤሰቦችሽ በላይ የቀረበ የለምና ማንኛውንም ነገር ስታደርጊ አማክሪያቸው❕ ስርዓትሽን ይዘሽ ስራሽን ስሪ ፤ ዒልምሽን ተማሪ ፤ መፅሃፍ አንብቢ ሰላም ታገኛለሽ። ከዚያም አላማሽን ካሳካሽ በኋላ በደስታ ወደ ቤትሽ ትመለሽ'ና ቤተሰብ'ጋ በአደብ ተቀመጭ አሏህ ትዳርሽን ይሰራልሻል።
ነገር ግን አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው'ና አሏህ ብሎ ሷሊሕ ወንድ ጋር ከተዋወቅሽ ደግሞ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ቤተሰቦችሽን በክብር ይጠይቅና ኒካሓቹህን ታደርጋላቹህ። ገንዘብሽን ግን አደራ አጭበርባሪዎች በዝተዋልና በቤተሰብ ወይም በ'ራስሽ አካውንት አስቀምጭ❕ እውነተኛ ባል ከሆነ አንቺን እንጅ ካንቺ ምንም ነገር አይፈልግምና። ማገዝ ካለብሽም ቤተሰብ አውቀው በመጠኑ መሆን ይኖርበታል።
ስደተኛዋ እህቴ ባ'ለሽበት አሏህ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቅሽ❕
✍ በድጋሜ የተለጠፈ
✒️ ወንድምሽ አቡ ዒምራን
https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy