የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe) @yetemsrecipe Channel on Telegram

የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe)

@yetemsrecipe


ስለምግብ መማማሪያ ገፅ

የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe) (Amharic)

የየትም የምግብ አሰራር (Yetem's Recipe) የትም መምሪያ እና ምግብ መማማሪያ እንቋዕ አሰራር ነው። የየትም የምግብ አሰራር በየትም ትምህርት እና የምግብ ቃላት መማማሪያዎችን ይዘቱ እና መስራታቸውን እንዲሁም ሌሎች ተክሌዎችን ይጠቀሙን። የምግብ አሰራር በቅርብ ውስጥ የግምት መምሪያዎችን በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ከባድ ገፅ እንዲሁም በሰላም ለጥንት መማማሪያዎችን ይፈታል። በትም የምግብ አሰራር በማናመልከት በፊት የምግብ የመምርያ 'አትለዓለም' እና 'ምድባድ' ለመብራት እንደገና ለአንድነት አሟም። ብትም የምግብ አሰራር በማንም አገልግሎት ላይ እንላይ።

የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe)

18 Aug, 02:29


ሰላም የምወዳችሁ የዚህ ግሩፕ አባላት እንደምን አላችሁ እስካሁን በፌስ ቡክም በቴሌግራምም የአቅሜን ያህል ስንማማር ነበር ይሁን እና በሁኔታዎች አለመመቻቸት በመጥፋቴ ይቅርታ እየጠየቅኩ አሁን ደሞ በTikTok ethio_food_በሚል ስለ ጀመርኩ አጋርነታችሁን እንድታሳዩኝ ከታላቅ ፍቅር ጋር እጠይቃችኋለሁ
አመሰግናለሁ የትም ነኝ።

የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe)

20 Aug, 18:05


ሰላም የምወዳችሁ የዚህ ግሩፕ ተከታዬች አሁን ባለሁበት ሁኔታ ምንም ጊዜ ስላጣሁ ነው የጠፋሁት
ሌላው የሃገራችን የሰላም ሁኔታ የኑሮው መናር ተደማምሮ አሁን እኔ ባለሁበት ሃገር የሚሰሩትን የምግብ ዓይነቶች ስሩ ማለት የማይሞከር ነው ስለዚህ ይሄ ቀን እስኪያልፍ አልፎ አልፎ አስተማሪና ጠቃሚ የሆኑ መልእክቶችን እያረኩ ሊንኩ እንዳይዘጋ እንቆይና ሃገራችን ሰላም ሲሆን መማማራችንን እንቀጥላለን!!
እግዚአብሔር አምላክ ሃገራችንን ሰላም ያድርግልን በጣም ነው የምወዳችሁ
የትም።

የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe)

04 Aug, 15:56


The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 28 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.

የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe)

13 Jun, 15:37


   
የፆም ፓስታ አልፍርኖ
👉 የሚያስፈልገን:-
🔸ስፓጌቲ(ፓስታ ወይም መኮረኒ) እንደተመጋቢው ብዛት
🔸️የቲማቲም ስጎ
🔸️ነጭ ሶስ
👉አዘገጃጀት:-
🔹️ውሃ መጣድ እና ፓስታውን(መኮረኒውን) በጣም ሳይበስል ቀቅሎ ማውጣት
🔹️ስጎው ልክ ለፓስታ ለመኮረኒ እንደምንሰራው ቆንጆ አድርጎ መስራት
🔹️በመቀጠል ነጭ ሶስ ለመስራት ዘይት መጣድ እና ትንሽ ፍርኖ ዱቄት በማድረግ እያማሰልን ወፈር ሲል የፈላ ውሃ መጨመር እና ትንሽ ቁንዶ በርበሬና ትንሽ ጨው በማድረግ አንተክትከን ማውጣት
🔹️የቀቀልነውን ፓስታ ሁለት ቦታ ከፍለን አንደኛውን ክፋይ በነጩ ሶስ መቀላቀል ሌላውን በሰራነው ስጎ እንቀላቅላለን ግን ከስጎው በደንብ ማስተረፍ አለብን ከላይ ለምናደርገው
🔹️በመቀጠል መጋገሪያውን ዘይት በደንብ ቀብተን ነጭ ሶስ ከተቀባው ግማሹን አድርገን በመቀጠል በስጎ ከተለወሰው ደሞ እናደርግ እና  በመቀጠል በነጭ ሶስ የተለወሰውን እናደርግና  የመጨረሻውን በስጎ የተለወሰውን እናደርግና ስጎውን በደንብ ከላይ ማድረግ መጨረሻ  በ180° ሙቀት ለ30 ደቂቃ አብስሎ ማውጣት።
🔶️ ትንሽ ቀዝቀዝ ሲል አስተካክሎ ቆርሶ ማቅረብ።

የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe)

26 May, 16:03


"የፍርኖ ዱቄትና የቡላ ገንፎ"
👉 አሰራር:-
የምትፈልጉትን ያህል ፍርኖ ዱቄት(ነጩ የዳቦ ዱቄት ማለት ነው)
በመጥበሻ ላይ በትንሽ እሳት ማመስ
📍ውሃ ለክተን በድስት መጣድ
📍ጨው ማድረግ
📍ውሃው ሲፈላ የተወሰነ ቀንሰን በእቃ ማስቀመጥ
📍ዱቄቱን መጨመርና በደንብ መላግ(ማማሰል)
📍የቀነስነውን ውሃ ጠብ እያደረግን እየላግን ማብሰል
📍ሲበስልልን ቡላውን በጎድጓዳ ሳህን ላይ በጥብጦ መጨመር እና ቶሎ ቶሎ መላግ እንዳይጓጉልብን
📍በደንብ ከተያያዘልን በኋላ ማውጣትና ሳህናችን ላይ አስተካክለን በርበሬ ቅቤ ትንሽ ሚጥሚጣ አድርጎ መመገብ👌
📍ሚጥሚጣውን ካልፈለጋችሁ በበርበሬ ብቻ ማድረግ ይቻላል
🔺የቡላውን ልኬት ለማወቅ
ለምሳሌ ዱቄቱ አንድ ኩባያ ከሆነ
ቡላው የኩባያውን ¼ መሆን አለበት
📍ሌላው ብዙ ሰው ቡላ አልወድም ስለሚል እንደዚህ ሞክሩት ትወዱታላችሁ ከገብስ የገንፎ እህል ጋርም እንደዚህ ብታገነፉት ልዩ ነው
❤️ ተደስታችሁ ዋሉልኝ!!

የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe)

25 Feb, 14:03


አዚፋ
👉 የሚያስፈልገን:-
🔶️ ድፍን ምስር አንድ ኩባያ
🔶️ ቀይ ሽንኩርት 2 ራስ
🔶️ ቃሪያ 4 ፍሬ
🔶️ 4 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
🔶️ 1የሾርባ ማንኪያ ሰናፍጭ
🔶️ ½ የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት
🔶️ 1 ድፍን ሎሚ
🔶️ ጨው እንደ አስፈላጎነቱ
👉 አሰራር:-
ምስሩን ለቅሞ እና አጥቦ መቀቀል ሲበስል ማውጣትና ውሃውን አጠንፍፎ በጭልፋ ዳጥ ዳጥ ማድረግ በመቀጠል ሽንኩርቱንና ቃሪያውን ድቅቅ አድርጎ መክተፍ
👉 ምስሩን ዘይቱን ነጭ ሽንኩርቱን ጨውን ሰናፍጩን በጎድጓዳ ሳህን ላይ ማድረግ እና የከተፍነውን ሽንኩርት እና ቃሪያውን ከቶ ሎሚውን ከላይ መጭመቅ እና በደንብ ማዋሃድ ሁሉንም ቀላቅሎ ጨውን አስተካክሎ ማቅረብ
👉 ምስሩ ከተቀቀለ በኋላ ሌላው በሙሉ እንደሰላጣ ይቀላቀላል እንጂ እሳት ላይ አይጣድም!!
🔶️ በብዛት መስራት ከፈለጋችሁ እኔ የፃፍኩትን እያባዛችሁ መሄድ ነው።

የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe)

07 Oct, 19:23


🍕 ምርጥ ፒዛ 🍕
👉 የሚያስፈልገን :-
ለሊጡ
🍕 1. 300g (1 ኩባያ ከግማሽ) ዱቄት
🍕 2. 1 የሻይ ማንኪያ እርሾ
🍕 3. ትንሽ ጨው
🍕 4.አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት

👉 ከላይ ለሚደረገው
🍕 ፍሬሽ ቲማቲም 3 ራስ
🍕 የቲማቲም ድልህ 2 የሾርባ ማንኪያ
🍕 ቀይ ሽንኩርት ሁለት ራስ ተለቅ ያለ
🍕 ነጭ ሽንኩርት 1 የሻይ ማንኪያ
🍕 ዘይት ሁለት የሾርባ ማንኪያ
🍕 ጨው እንደ አስፈላጊነቱ
🍕 የበሬ ስጋ ሶሴጅ
🍕 ጦስኝ አንድ የሻይ ማንኪያ
🍕 ቺዝ 100g(እንደምትፈልጉት መጠን)
👉 አሰራር:-
🔷️ እርሾውን ዱቄቱን ጨውን እና ዘይቱን በመጨመር ወፈር አድርጎ ማቡካት እና ኩፍ እንዲል ሸፍኖ ማስቀመጥ
👉ሽንኩርቱን ከትፎ በዘይት ማቁላላት የቲማቲም ድልሁን መጨመር ትንሽ አቁላልቶ ፍሬሹን ቲማቲም ፈጭቶ ወይም በደቃቁ ከትፎ መጨመር ነጭ ሽንኩርቱንና ጨውን አስማምቶ ማውጣት ውሃ ማውጣት የለበትም
👉 ሶሴጁን በክብ በክብ መክተፍና ማዘጋጀት
👉 የፒዛውን ሊጥ ከ40-60 ደቂቃ ካቆየነው በኃላ ኩፍ ስለሚል በስሱ መዳመጥ በመቀጠል ፖትራችን ላይ ቤኪንግ ፔፐር ማድረግ ከሌለን የዳቦ ቅቤ ወይም ዘይት ቀብተን መጀመሪያ የዳመጥነውን ሊጥ ፖትራው ላይ ማድረግ ከዚያም የቲማቲም ስጎውን መቀባት ትንሽ ጦስኝ መነስነስ ከዚያም ያዘጋጀነውን ሶሴጅ ከላይ ሁሉም ቦታ ላይ ማዳረስ እና መደርደር በመቀጠል ቺዙን አድርጎ ወደ ማብሰያው መክተት
በ 180°ç ለ 30 ደቂቃ ማብሰል
ውጭ ሃገር ከሆናችሁ በ450° ለ15 ደቂቃ ማብሰል እና ከበሰለ በኋላ አውጥቶ በቅርፅ መቁረጥና ማቅረብ።
👉 ማሳሰቢያ:-ኦቭን ከሌለን በእንጀራ ምጣድ መጋገር እንችላለን ሊጡን ሳሳ አድርገን ከዳመጥን አሪፍ ይሆናል በመጥበሻም ትንንሽ ፒዛ መስራት ይቻላል
👉 ሌላው እኛ በምንወደው ግብዓት መስራት እንችላለን።

የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe)

08 Feb, 09:44


Recipe 8⃣7⃣
ጎመን በስጋ
👉 የሚያስፈልገን
🟣 ሲማሮ ጎመን
🟣 የጎድን አጥንትና ስጋ
🟣 ቀይ ሽንኩርት
🟣 ነጭ ሽንኩርት
🟣 ዘይት
🟣 ጨው
🟣 ቅቤ
🟣 ቃሪያ
👉 አሰራር:-
♦️ጎመኑን በደንብ አራግፎ መቀነጣጠስ እንጨቱን መላጥ እና ማዘጋጀት
♦️የጎድን አጥንቱን አነስ አነስ አድርገን መቀረጣጠፍ እና ስጋውን ተለቅ ተለቅ አድርጎ መክተፍ እና በደንብ አጥቦ ማዘጋጀት
ተለቅ ያለ ድስት አዘጋጅቶ ስጋውን መጨመር እና መጣድ የራሱን ውሃ እስኪጨርስ ክድን አድርጎ ማብሰል ልክ የስጋውን ውሃ ሲጨርስ መጠነኛ ዘይት አድርጎ ጥብስ ማድረግ እንዳያርብን ትንሽ ውሃ ጠብ እያደረግን በደንብ መጥበስ
♦️ከጠበስነው በኋላ ጎመኑን እና ቀይ ሽንኩርቱን መጨመር
አብረን መጥበስ
♦️በመቀጠል ነጭ ሽንኩርቱን ከተን ትንሽ ካበሰልነው በኋላ መጠነኛ ውሃ ከልሶ በደንብ መብሰሉን አረጋግጠን ቅቤና ቃሪያ ጨው ጨምሮ አስተካክሎ ማውጣት እና በትኩሱ ማቅረብ
👉 ጥብስ ብሎ በደረቁ ከፈለግን ውሃ አለመከለስ
👉 መረቅ ያለው ከፈለግን ግን በመጠኑ መከለስ
👉 ሌላው ቅቤያችን የበሰለ ከሆነ ጎመኑ ሲገባ አብሮ መጨመር
👉 ትንሽ ቅባት ያለው ስጋ ቢሆን የበለጠ ይጣፍጣል
ልኬት እንደተመጋቢው ብዛት ሞክሩት ትወዱታላችሁ።

የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe)

08 Feb, 09:42


Recipe 8⃣6⃣
የቫኒላ እስፖንጅ ኬክ
👉 የሚያስፈልገን:-
💥 500gግማሽ ኪሎ) ዱቄት
💥 አንድ ኩባያ ስኳር
💥 1 ኩባያ ዘይት
💥 6 እንቁላል
💥 2 የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
💥 1 የሾርባ ማንኪያ ቫኒላ
💥 ትንሽ ጨው
💥 ግማሽ ሊትር ወተት
👉 አሰራር:- ዘይት እና ስኳሩን እንቁላሉን በጎድጓዳ ቦል(ሳህን) አብረን በደንብ መምታት በመቀጠል ወተቱን ለብ አድርጎ መጨመር ቫኒላውን መክተት ጨውን
ከቶ ማቀላቀል በመቀጠል ዱቄቱንና ቤኪንግ ፓውደሩን መጨመር እና መቀላቀል ሊጡ በጣም መወፈር የለበትም በመቀጠል
👉 ፓትራችን ዘይት መቀባት እና ያዘጋጀነውን ሊጥ ማድረግ በመቀጠል በ180° ለ35 ደቂቃ ማብሰል እና ማውጣት ሲቀዘቅዝ መቁረስ
👉 ሞክሩት ለበዓሉም ቆንጆ ነው።

የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe)

07 Feb, 17:40


Recipe 8⃣5⃣
Meet ball(ሚት ቦል)
👉የሚያስፈልገን:-
🔷️የተፈጨ ቀይ ስጋ
🔷️የተፈጨ የዳቦ ዱቄት
🔷️ፐርስሊ በደቃቁ የተከተፈ
🔷️ነጭ ሽንኩርት
🔷️ቁንዶ በርበሬ
🔷️ጨው
🔷️ቀይ ሽንኩርት በደቃቁ የተከተፈ
🔷️አንድ እንቁላል
ሌላ እናንተ የምትፈልጉትን ቅመሞች መጨመር ትችላላችሁ
👉አሰራር :-
ሁሉንም በጎድጓዳ ሳህን አድርጎ አንድ ላይ በደንብ እንዲዋሃድ ማሸት
👉 በመቀጠል ትንሽ ትንሽ እየቀነሱ በክብ ማድቦልቦል
ዘይት ማጋልና መጥበስ ዘይቱ ማነስ የለበትም
👉በሌላ መንገድ በኦቭንም ማብሰል ይቻላል የኦቭኑ ግን በዘይት እንደሚጠበሰው ደረቅ ያለ አይሆንም በእንፋሎት እንደበሰለ ነው የሚሆነው ደረቅ እንዲል ከፈለጋችሁ ማቆየት እያያችሁት
👉 በኦቭን የምታበስሉት እና ውስጡ ልስልስ እንዲል ከፈለጋችሁ ትንሽ ወተት አድርጉበት።

የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe)

05 Feb, 18:51


ለቤተዘመድ ዝግጅት ቤት ውስጥ የተሰራ።

የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe)

04 Feb, 06:38


Recipe 8️⃣5️⃣
ጎመን በቆጮ
👉 አሰራር:- ጎመኑን ቀነጣጥሶ እና አጥቦ መቀቀል ከዛ በደቃቁ መክተፍ በመቀጠል በድስት መጣድና ትንሽ ዘይት አድርጎ ጥብስ ማድረግ እና ሚጥሚጣ ኮረሪማ ጨው አድርጎ ማውጣትና በቆጮ መመገብ
🟢 ለፍስክ በዘይቱ ፋንታ ቅቤ መጠቀም
🟢 ዘይቱን በኮረሪማ በኮሰረት ቀዝቀዝ ባለ እሳት ማንጠር ልዩ ነው ቅቤ ቅቤ ነው የሚለው የተነጠረው ዘይት ለብዙ የፆም ምግቦች መጠቀሚያ ይሆናል
👉 ሌላው ሽንኩርት ድቅቅ አድርጋችሁ ከትፋችሁ ሽንኩርቱን ጥብስ ታደርጉና ሌላው ከላይ በተፃፈው መሰረት ብትሰሩትም በጣም አሪፍ ነው ።

የየትም የምግብ አሰራር(Yetem's Recipe)

04 Feb, 06:32


Recipe8️⃣4️⃣
የኔን የተጋቢኖ አሰራር
👉 ሽንኩርት በቁመቱ በቀጫጭኑ መክተፍ እና በመጥበሻ ላይ በዘይት ጥብስ ማድረግ
👉 ከዛ ነጭ ሽንኩርት መጨመር
♦️ቁሌቱ ላይ ምጥን ሽሮ እየነሰነሱ ማቁላላት
♦️የሞቀ ውሃ ጠብ እያደረጉ በደንብ ከተጠበሰ(ከበሰለ) በኋላ ትንሽ ውሃ አድርጎ ተንተክትኮ ውፍር ሲል ጨውን አስተካክሎ ማውጣት እና ከላይ ቃሪያ ከትፎ መነስነስ እና ለገበታ ማቅረብ
👉 እኔ ቲማቲም አልጨመርኩም የምትፈልጉ ግን መጨመር ትችላላችሁ
👉 ልዩ ነው ሞክሩት።