የፍጥረትን ጅማሬ የሚነግረን የዘፍጥረት መጽሐፍ የእግዚአብሔር ፍቅር የተገለጠበትም ነው።ፍቅሩን የጀመረው በአምስቱ ቀን ውስጥ ለሰው ልጆች የሚያስፈልጉትን ነገሮች በመፍጠር አሳይቷል።ሰው የሚኖርበትን ምድር ፣ የሚበላውን ፍራፍሬ እና አትክልት እንዲሁም የሚስማማውን የአየር ሁኔታና የሚጠጣውን ውኃ አዘጋጅቶለት በስድስተኛው ቀን ሰውን ፈጠረው።#እግዚአብሔር_ባለቀ_ጉዳይ_ላይ_ሰውን_አምጥቶ_አስቀመጠው።በተጨረሰ ገነት እንዲቀመጥ ያለምንም ተሳትፎ አስገባው።ሥራውን የጨረሰው እግዚአብሔር ሰውን አሥጥቶ በገነት አኖረው።በተጨረሰ ሥራ ሰው ገባ።እንዲሁም እግዚአብሔር ሰውን በክርስቶስ አማካኝነት በጨረሰው የጽድቅ ሥራ ውስጥ አስገብቶታል።
#በእርግጥ_አዳም_ገነት_ለመግባት_ነጻ_ፈቃዱን_ባይጠቀምም_ለመውጣት_ግን_ነጻ_ፈቃዱን_ተጠቅሟል።በአዲሱ ኪዳንም በክርስቶስ የተሠራውን በማመን ወደዚህ ወደተጨረሠው ሥራ መግባት ሆኖልናል።መውጣት ከፈለግንም ደግሞ መብታችን እንደተጠበቀ ነው።እረኛውን ሳይወድዱ በግ መሆን አይቻልምና።የተወደድንበትን ፍቅር ማራከስም አክብሮ ምላሽ መስጠትም በነጻ ፈቃድ ውስጥ የተካተተ ነው።እግዚአብሔር እዚያው ዘፍጥረት ላይ ለሰው የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን ጨርሶ ገነት ሲያኖረውም ፤ ከገነት መውጫም ሆነ እዚያው መቆያ ውሳኔውን እንዲወስን የእውቀት ዛፍንም ሲፈጥርለት ፍቅሩን እያሳየው ነው።የፍቅሩ ብዛት ተገደን ሳይሆን ወደን እንድንወደው መርጠንም እንድንከተለው መፈለጉ ነው።