Ministry Of Education @tmhrt_minister Channel on Telegram

Ministry Of Education

@tmhrt_minister


📚ይህ ትክክለኛው የትምህርት ሚኒስትር የተማሪዎች መረጃ ማቀበያ ገፅ ነው

🔵ከ1-12 መፅሃፍት ለማግኘት: @STBookbot

🔴ለFreshman : @Freshman_Robot

«Buy Ads» https://telega.io/c/Tmhrt_minister or @MoeAds_bot

Ministry Of Education (Amharic)

የትምህርት ሚኒስትር ሁለት ቁጥሮችን እና ኮሌጃችን በመጠቀም ይህ ትክክለኛው የትምህርት ሚኒስትር የተማሪዎች መረጃ ማቀበያ ገፅ ነው። የተማሯችንን ለማስተዋወቅ ለመጠቀም እና ራስን እናመለከት በተጨማሪበት ልዩ አካባቢ እንደማይሆን እናመሰግናለን። በእይታም እንቀውጣለን።nnበዚህ መረጃ ከ1-12 መፅሃፍት ለማግኘት ላይ እና ተመናዘሩበት በሉ የአካባቢ እና የትምህርት ሚኒስትሮችን በታላቅ እቅድ እና በዋጋ ለማቆም መድረስ እና ለራሱ የግምት ምልክት ማቆም እና ምርጫ እንደሚቀሰብ እናስጠቅም።nnሲሆንም ለFreshman ሚኒስትሮች እና ላይ እና በአለም የተመረጡ የምልከወኞች ለማግኘት ይህን ሲገልጽ ለFreshman : @Freshman_Robot ብለን ለመቀነስ እና ለመሳሪያ በማስተላለፍ እና ለማከናወን በሚፈልጋቸው ጉዳዮች ለማሳያ እና ለሚሳሳት ማከናወን የአካባቢ ሴራቸውን ማስተላለፍ እና ማከናወን እና ማቆም እና ማምረት እና መልስ እንደሚፈልጉ ማጠቃለያ እና የአካባቢ መድረስን በፕሮፌሰንና በአዝቃሩ ቅጅፍ እና አሁንስ በ@STBookbot ላይ ተፈጥሯል።nnለተጨማሪ በምስጋና በትክክለኛው የትምህርት ሚኒስትረች ላይ ለማውጣት ከሚገባ ተግባር እና የምርጫ እና አጋሱሚናል እና ሌሎች ተጠቃሚነት እመለከታለን። የትምህርት ሚኒስትሮች እና ተማሯችን በመኖሩ በኔትዎሮክ እና በፈርኩንስ የምርጫ እና መሳሪያ በማስቀመጥ ለሆነው ቦታ ስማቸውን በካርታ ይመልከቱ።nnበመመዝገብ በመዋቅር እግዚያብሔር እና በእኛ ለመገናኘት በስጦታ ለማያሳክ እና ከእኛ የተሸሻሽ ጉዳዮች በርካታ እሱም በተማሪ ቁጥሮች ይሆናል። በዚህ መረጃ የተማሪዎች ይህችን ኢንፎሪምህሲኖን ሴራቸውን ሆኖ በፕሮፌሰንና በአዝቃሩ ያስረዳሉ።nnከዚህም በመጠቀም እንዲህ እና ሰነዱን ከታች የተቀበረ የመረጃ እና የህጻን ገፅ መረጃዎችን እናስብል። የትምህርት እና መረጃ በግመት ከሆነው ለማግኘት መረጃ እና ህጻን ለማስቀመጥ እንቆማለን።nnየትምህርት ሚኒስትር በዚህ መረጃ ሳይንሳዊ አሰፋ እና በጠቅላላ እና ሌሎች የተማሯችን የህጻን በዚህ መረጃ እናስብል። ይህም የያዘ መረጃ ለዚህ ነው።nnበዚህ ከሆድ እንዲህ ከሚኖሩ ለማረጋጋት የታሪካዊ ህይወቶች እና የምርጫ እና እንግሊዘኛ ለሆነው። መረጃና ሳይንሳዊ ፍልፍል መገኛ ቀላል በሚለው ነገር ሰንበታቱ ለማቀናበለ።

Ministry Of Education

21 Nov, 04:46


40 ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ጠርተዋል

ለ2017 የመጀመርያ ዓመት የፍሬሽማን እና በ2016 በሪሜዲያል ማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎቻቸውን የጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች


👉1. Addis Ababa University - ገብተዋል
👉2. Adama ST University - ገብተዋል
👉3. Addis Ababa ST University - ገብተዋል
👉4. Salale University - ጥቅምት 21 እና 22/2017 - ገብተዋል
👉5. Kebri dehar University - ጥቅምት 25,26/2017 - ገብተዋል
👉6. Mizan Tepi University - ህዳር 2 እና 3/2017 - ገብተዋል
........................................................................
👉7. Hawassa University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉8. Haramaya University - ህዳር 9,10,11/2017
👉9. Raya University - ህዳር 2 እና 3/2017
👉10. Oda Bultum University - ህዳር 4,5/2017
👉11. Jigjiga University - ህዳር 7-9/03/2017
👉12. Dire Dawa University - 16 እና 17/2017
👉13. Kotebe University - ህዳር 4 እና 5 /2017
👉14. Ambo University - ህዳር 09 እና 10/2017
👉15. Wollega University -  ህዳር 4 እና 5/2017
👉16. Aksum University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉17. Borana University - ህዳር 12 እና 13/2017
👉 18. Woldia University - ህዳር 18 እና 19/2017
👉 19. Dambi Dollo University - ህዳር 11 እና 12/2017
👉 20. Wolaita Sodo University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉21. Dilla University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉22. University of Gonder - ህዳር 12 እና 13/ 2017
👉23. Arba Minch University - ህዳር 7 እና 8/2017
👉24. Wollo University - ህዳር 13 እና 14/2017
👉25. Debark University - ህዳር 18 እና 19/2017
👉26. Jinka University - ህዳር 11 እና 12/2017
👉27. Debre Tabor University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉28. Assosa University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉29. MizanTepiUniversity - ህዳር 11 እና 12/2017
👉30. Werabe University - ህዳር 19 እና 20/2017
👉31. Injibara University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉32. Madda Walabu University - ህዳር 09 እና 10/2017
👉33. Mattu University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉34. Jinka University - ህዳር 11 እና 12/2017
👉35. Assosa University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉36. Bule Hora University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉37. Gondar University - ህዳር 12 እና 13 2017
👉38. Bahir Dar University - ህዳር 16 እና 18/2017
👉39. Samara University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉40. Wachemo University - ህዳር 19 እና 20/2017
..................................................................................
🎯Federal Technical and Vocational Training Institute  - ህዳር 3 እና 4/2017 ዓ.ም

N.B: ራያ ዩኒቨርሲቲ አራዝሟል - ቀኑ ህዳር 9 እና 10/2017

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

20 Nov, 13:40


#MekdelaAmbaUniversity

በ2017 ዓ.ም መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች፣ በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት በ2016 ዓ.ም Freshman ፕሮግራም መቀጠል ያልቻላችሁ እንዲሁም በ2016 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስቴር ያልተማራችሁ (ዊዝድሮዋል ሞልታችሁ የወጣችሁ) ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 19 እና 20/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በሁለቱም ግቢ (ቱሉ አውሊያ እና መካነ ሰላም) የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው በዋናው ግቢ (ቱሉ አውሊያ ካምፓስ) መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

በ2017 ዓ.ም መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ ጥደረጋል ተብሏል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

20 Nov, 12:02


ጅማ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ተመደበለት፡፡

በዚህም ከህዳር 5/2017 ዓ.ም ጀምሮ የፍትህ ሚኒስትር ሀና አርዓያስላሴ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እንዲሰሩ መመደባቸውን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን ህዳር 4/2017 ዓ.ም ተፈርሞ የወጣ የምደባ ደብዳቤ ያሳያል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በሚያዝያ 2014 ዓ.ም ገቢራዊ ባደረገው አዲስ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ምደባ መሰረት፣ የቀድሞዋ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሠ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እና ጥላሁን ተሾመ (ፕ/ር) ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

20 Nov, 08:32


ለ2017 ፍሬሽማን ተማሪዎች የተከፈተ ምርጥ ቻናል እነሆ ! 😊

Freshman Journey 🛣

📁በመጀመሪያ አመት የሚወስዷቸውን ኮርሶችንና ኖቶችን በPDF ፣ PPT & DOCX
📁Mid & Final Exam ከነመልሳቸዉ
📁 University Tips
📁 ስለ እያንዳንዱ Department ማብራሪያ
📁የጊቢ ትኩስ መረጃዎችንና ሌሎችም ጨምሮ በነፃ የምታገኙበት! ☺️

የፍሬሽ ተማሪዎች ጉዞ | Join Now

https://t.me/Freshman_Journey

Ministry Of Education

19 Nov, 19:19


#JimmaUniversity

በ2017ዓ.ም የት/ት ዘመን በጅማ ዩኒቨርስቲ

· ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ ምዝገባችሁ በመጪው ህዳር 19 20/20179.9 - በዩኒቨርስቲው በተመደባችሁባቸው ካምፓሶች ማለትም የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (ከሴክሽን 1-26) እና ግብርና እና እንስሳት ሕክምና ኮሌጅ (ከሴክሽን 27- 31) እንዲሁም የሶሻል ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ደግሞ በዋናው ግቢ እንደሚካሄድ ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።

👉ማሳሰቢያ

1. በ2017ዓ.ም የት/ት ዘመን በጅማ ዩኒቨርስቲ በRemedial ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ግዜያችሁ በቀጣይ ማስታወቂያ የሚገለጽ መሆኑን አውቃችሁ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳስባለን፡፡

2. በ2016ዓ.ም የት/ት ዘመን በጅማ ዩኒቨርስቲ የRemedial ፕሮግራም ትምህርታችሁን የተከታተላችሁ ተማሪዎች በመጪው ቅርብ ቀናት https://portal.ju.edu.et ላይ የመለያ ቁጥራችሁን በማስገባት አጠቃላይ ውጤታችሁን ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ላለፋችሁ ተማሪዎች ምዝገባችሁ ከላይ በተጠቀሰው ቀናት በተመሳሳይ የሚፈጸም መሆኑን እንገልጻለን፡፡

3. አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ሴክሽን እና ካምፓስ ከተወሰኑ ቀናት በ3.4 https://portal.ju.edu.et ላይ ስለሚለቀቅ የአድሚሽን ቁጥራችሁን በማስገባት ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ነባር የሬሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ደግሞ ይህንን መረጃ የመለያ ቁጥራችሁን (ID No) በማስገባት ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

19 Nov, 17:57


የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ፈተና ሊፈተኑ መሆኑ ተሰማ።

ትምህርት ሚኒስቴር፤ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራንን ብቃት ለመመዘን ፈተና ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

በሚኒስቴሩ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት እዮብ አየነው(ዶ/ር ) ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ በሰጡት ቃል ፥ " የመምህራን ፈተና ከዚህ በፊት በአንደኛ ደረጃ በሚያስተምሩት ላይ ተሞክሮ ነበረ በመሆኑም አልተጀመረም ማለት አይቻልም " ብለዋል።

አሁን ግን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንን ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።

ዝግጅቱ እንዳለቀ በዚህ ዓመት ወይም በቀጣዩ 2018 ዓመት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መመህራን ፈተና መሰጠት ይጀምራል ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ገልጸዋል።

  ምንጭ፡ ሸገር ሬድዮ
ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

19 Nov, 08:30


በተያዘው የትምህርት ዘመን ለመመዝገብ ከታቀደው የተማሪ ቁጥር የተመዘገበው በአስር ሚሊዮን ያነሰ እንደሆነ ተገለፀ።

በመላ ሀገሪቱ ከቅድመ መደበኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ባሉ ትምህርት ቤቶች ከ32 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ለመመዝገብ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም የተመዘገቡት ግን 21.7 ሚሊዮን ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።

የተመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከዕቅድ በታች የሆነው በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተቋማቸውን የሦስት ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት ገልፀዋል።

ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ ይህን ለማስተካከል የመምህራን ባንክ ማቋቋምን ጨምሮ የተለያዩ የማትጊያ ስርዓቶች ይዘረጋሉ ብለዋል።

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

18 Nov, 12:09


📣 Gambella University

በ2017 ጋምቤላ ዩንቨርስቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የመግብያ ጊዜ ህዳር 23 እና 24/2017 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ያስታዉቃል::

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

18 Nov, 09:21


#Fake #Jimma

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ የተመደቡለትን ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል በሚል እየተሰራጨ ያለው ደብዳቤ የተሳሳተ መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለን።

ተማሪዎች መሰል መረጃዎችን ከማሰራጨታቹህ በፊት የዩንቨርሲቲያችሁን ትክክለኛ የማህበራዊ ገፆች በማየት ማረጋገጥ ይኖርባቸሃል።


ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

16 Nov, 12:04


#WachemoUniversity

በ2017 ዓ.ም ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 19 እና 20/2017 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡

(አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምትመዘገቡበት ካምፓስ እና ከተማ ከላይ ተያይዟል።)

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

16 Nov, 09:03


#DebreBerhanUniversity

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው በመደበኛ መርሐግብር የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም አንደኛ ዓመት ትምህርት የምዝገባ ጊዜ ህዳር 18 እና 19/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- የ12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

15 Nov, 08:15


#DebreMarkosUniversity

በ2017 የትምህርት ዘመን በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የአቅም ማሻሻያ መርሐ-ግብር (Remedial Program) ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ህዳር 12 እና 13/2017 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ!

1. ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት፤ ከ9-12ኛ ትራንስክሪፕት፤ የ8ኛ ክፍል ስርተፊኬት ዋናውን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር እንዲሁም 3x4 የሆነ 4 ጉርድ ፎቶ በመያዝ እንድትገኙ እናሳውቃለን።

2. የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ አሟልታችሁ እንድትገኙ ዩኒቨርሲቲው ያስታውቃል።

3. በ2016 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ስትከታተሉ የቆያችሁ ተማሪዎች በነበራችሁበት ካምፓስ ብቻ የምትስተናገዱ ይሆናል፡፡

4. ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡

5. በ2017 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

15 Nov, 06:35


#AksumUniversity

በ2017 ዓ.ም አክሱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንሰክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- ስድስት 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ

በ2017 ዓ.ም አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል ተብሏል።

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

14 Nov, 17:05


#SamaraUniversity

በ2017 ዓ.ም ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 16 እና 17/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- የ8ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንሰክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- ስምንት 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ትራስ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅ

በ2017 ዓ.ም ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል ተብሏል።

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

14 Nov, 14:07


በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም መደበኛ ተማሪዎች እና 2016 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ተምራችሁ ያለፋችሁ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ፦

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች መግቢያ ጊዜ ህዳር 19 እና 20/2017 ዓ.ም መሆኑን እያሳወቅን ፤ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ፡

• የ12ኛ ክፍል ሰርትፊኬት ፣ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣ 8ኛ ክፍል ሰርትፊኬት ዋና እና ፎቶ ኮፒ እንድሁም 4 3በ4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣

• ብርድ-ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ፣ የስፖርት ትጥቅ እና ሌሎች የግል መገልገያ ቁሳቁሶች መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

● በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የቅድመ- ምረቃ ፕሮግራም መደበኛ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ካምፓስ (Main campus and Durame campus) በዩኒቨርሲቲ ዌብሳይት፣ በፌስቡክ ገጽ እና በቴሌግራም

• በ2016 ዓ.ም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ የአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial) ተምራችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ በዋና ግቢ የሚትመዘገቡ ስሆን በዱራሜ ካምፓስ የተከታተላችሁ በዱራሜ ካምፓስ የሚትመዘገቡ ይሆናል

ከተጠቀሰው ቀናት ቀድመውም ሆነ ዘግይተው የሚመጣ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ፡

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአቅም ማሻሻያ መርሀ-ግብር (Remedial Program) አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ወደ ፊት የምናሳውቅ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት

ትምህርት ሚኒስቴር

https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

14 Nov, 14:07


#BahirDarUniversity

በ2017 ዓ.ም ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች እና በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ ወደ Freshman Program የመግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከህዳር 16-18/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦

- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሰላም ግቢ
- የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በፔዳ ግቢ

በተለያየ ምክንያት አንደኛ ዓመት አንደኛ ሴሚስቴር ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ለመልሶ ቅበላ ህዳር 19 እና 20/2017 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

በ2017 ዓ.ም ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ወደፊት ይገለፃል ተብሏል።

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

14 Nov, 07:30


#MizanTepiUniversity

በ2017 ዓ.ም በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው ህዳር 11 እና 12/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
- የማኅበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ሚዛን አማን ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ፣
- የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ12ኛ ብሄራዊ ፈተና ውጤት
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- ዘጠኝ የቅርብ ጊዜ 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Ministry Of Education

14 Nov, 04:44


ራስ ገዝ የሚሆኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚተመነው ክፍያ ማህበረሰቡ ላይ ጫናን በማይፈጥር መልኩ ሊሆን እንደሚገባው ተጠቆመ

በኢትዮጵያ በቅርቡ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ እንዲሆኑ መወሰኑን ተከትሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቀዳሚውን የራስ ገዝነት ደረጃ በመያዝ በዘንድሮ ዓመት የመማር ማስተማሩን ስራ መጀመሩ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ለትምህርት መርሃ ግብሮቹ ያወጣውን ገንዘብ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ሃሳባቸውን ለመናኸሪያ ሬዲዮ የሰጡ የትምህርት እና የህግ ባለሙያዎች ምንም እንኳን ተቋሙ ራሱን በራሱ ቢያስተዳድርም ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያማከለ አሰራር ሊኖረው እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

መነሻውን ከሌሎች ሀገራት ያደረገው ይህ የራስ ገዝነት አካሄድ ብዙ ውዝግቦች የነበሩበት መሆኑን የገለፁት የትምህርት ባለሙያው ዶ/ር መክብብ ጣሰው ነገር ግን ከሃይማኖቱም ሆነ ከፖለቲካ ጫና በመላቀቅ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ያስችላል ብለዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ አቅም የሌላቸውን ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ባሻገር ድርጅቶች እና ባላሃብቶች እንደሚደግፉ በመግለፅ በኢትዮጵያም ዩኒቨርሲቲዎች ራስገዝ መሆናቸው የሚበረታታ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ ነገር ግን በክፍያው  ከሌሎች ሀገራት ያለውን ተሞክሮ መውሰድ ካልተቻለ በትምህርት ስርዓቱ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ይገልጻሉ፡፡
               
ይህንኑ ሀሳብ የሚጋሩት የህግ ባለሙያው አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ትምህርት ማህበራዊ አገልግሎት ከሚባሉት ውስጥ እንደመሆኑ ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ መንገድ ሊቀርብ ይገባል ባይ ናቸው፡፡ ትምህርት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሊቀርብ ይገባል ያሉት አቶ ጥጋቡ   አግላይ እንዳይሆኑ በህግ ማዕቀፍም ሊኖራቸው እንደሚገባ ይጠቁማሉ፡፡

አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች ትምህርት በነፃ በመንግስት በኩል ሊቀርብ የሚገባ መሰረታዊ ጉዳይ ነው ሲሉ ሃሳባቸውን የገለፁልን ደግሞ የህግ ባለሙያው አቶ አይናለም ጌታሁን ናቸው፡፡ 

በዩኒቨርሲቲ ደረጃም ወጪ መጋራት(ኮስት ሼሪንግ) የማስተማር አግባብ እንዳለ በመጥቀስ አሁን ላይ በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው የተቀመጠው የገንዘብ ተመን ምናልባትም ከሚያወጣቸው ወጪዎች ጋር ተያይዞ ሊሆን ይችላል የሚል ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው እስኪቸገር ድረስ የማስከፈል ሂደት ካለ እና ሌሎችም ነገ ላይ ራስ ገዝ ሲሆኑ በዚሁ የሚቀጥሉ ከሆነ  ትምህርቱ ወደ ንግድነት የሚቀየር ይሆናል ሲሉ ያላቸውን ስጋት አቶ አይናለም ያስቀምጣሉ፡፡
                         
ትምህርትን በጥራት ማድረስ በሚል ብቻ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያላማከሉ እርምጃዎች እንዳይወሰዱ በመንግስት በኩል ቁጥጥር ሊደረግባቸው እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡ (መናኸሪያ ሬዲዮ)

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister