የግዕዝ መማርያ @geez_memarya Channel on Telegram

የግዕዝ መማርያ

@geez_memarya


የግዕዝ መማርያ (Amharic)

የግዕዝ መማርያ በተቃራኒዋ እና ቀዋሪ የትም አሰራር በማስቀመጥ እንደተከተሉ እና የሚፈፅሙ ቀሚስ ደረሰና መገኘት እንዲህ መሐላ የተገለጻቸውን ሀሳብዎች በቅርብ ተልእኮ መወያያ እና የምከተሉትን ቀሪቶች ገለጸናል። ይህ እድሜበዋ ግን በአንድ ዓመት በህልሞች በመተርጊያ እንደአስተዋወን ችግረናል። የተጎበኙ መማሪያዎች እንዳልበዙ ይህ አገራችን ቦኋችንን ይወቅሳል።

የግዕዝ መማርያ

20 Jan, 03:36


የአእላፋት ዝማሬ የመሐረነ አብ ጸሎት ይዘት እነሆ! ጸሎቱን ይከታተሉበት፤ ጻሎቱን ለማጥናት ይጠቀሙበት፡፡

የግዕዝ መማርያ

20 Jan, 01:18


እንኳን አደረሳችሁ
የጥምቀት በዓል መዝሙሮች ስብስብ
ለወዳጆ ያጋሩ
https://t.me/Geez_Memarya
https://t.me/Geez_Memarya

የግዕዝ መማርያ

15 Jan, 13:49


#መጽሐፈ አርጋኖን
Share
https://t.me/Geez_Memaryahttps://t.me/Geez_Memarya

የግዕዝ መማርያ

14 Jan, 08:30


#የመጽሐፉ_ይዘት👇

ምዕራፍ ፩ - መሠረተ ግእዝ 
👉ግእዝ የሚለው ቃል ትርጓሜ
👉ፊደላተ ግእዝ
👉አኀዝ
👉መራሕያን
👉የግስ ዝርዝር በመራሕያን(የባለቤት ዝርዝር)
👉የስም ዝርዝር በመራሕያን 
👉መስተዋድዳን ቀለማት 
👉የቃላት ጥናት

ምዕራፍ ፪ - ሥርዓተ ንባብ ዘልሣነ ግእዝ
👉የንባብ ዓይነቶች
👉ተናባቢ ንባብ
👉የተጸውዖ ስሞች የንባብ ሕግጋት
👉የሆሄያት ተጽእኖ
👉መጠይቃን ቃላት
👉የቃላት ጥናት 

ምዕራፍ ፫ - ግሥ
👉የግሥ ስልት
👉መራኁት(የግሥ መነሻዎች)
👉አርእስት ግሥ 
👉ሠራዊት ግሥ
👉የአርእስተ ግሥ ገሢሦት (የግሥ     መሪዎች እርባታ)
👉ጸዋትው የግሥ እርባታ ሕግጋት
👉ንዑስ (መለስተኛ) እርባታ
👉ዝርዝር እርባታ
👉የግሥ ጥናት
https://t.me/Geez_Memarya

የግዕዝ መማርያ

14 Jan, 07:30


አውሥኦተ ቃል (Dialougue)

     ክፍል ፩

🧓ለይኩን
እፎ ኃደርከ እኁየ?
  • እንዴት አደርክ ወንድሜ?

🧔🏻አሮን
እግዚአብሔር ይሰባሕ
  • እግዚአብሔር ይመስገን።

🧓ለይኩን
መኑ ይትበሀል ስምከ?
  • ስምኸ ማን ይባላል?

🧔🏻አሮን
አሮን ይትበሀል
  • አሮን እባላው።

🧓ለይኩን
መኑ ይትበሀል ስመ አቡከ?
  • የአባትህ ስም ማን ይባላል?

🧔🏻አሮን
ስመ አቡየ ገብረ እግዚአብሔር ይትበሀል
• አባቴ ገብረ እግዚአብሔር ይባላል።


🧓ለይኩን
እስፍንቱ አኃው ሀለዉከ?
  • ስንት ወንድሞች አሉህ?

🧔🏻አሮን
ሠለስቱ አኃው ሀለዉኒ
  • ሦስት ወንድሞች አሉኝ።

🧓ለይኩን
እስፍንቱ አኃት ሀለውከ?
  • ስንት እህቶች አሉህ?

🧔🏻አሮን
ክልዔቱ አኃት ሀለዉኒ
  • ሁለት እኅቶች አሉኝ።


🧓ለይኩን
ማዕዜ ውእቱ ዘተወለድከ?
  • መቼ ነው የተወለድከው?

🧔🏻አሮን
በወርኃ መጋቢት በ፲፱፹፱ ዓ.ም ተወለድኩ
  • በመጋቢት ወር በ1989 ዓ.ም ተወለድኩ።

🧓ለይኩን
ትምህርት እፎ ውእቱ?
  • ትምህርት እንዴት ነው?

🧔🏻አሮን
ጥቀ ሠናይ ውእቱ
  • በጣም ጥሩ ነው ፡፡

🧓ለይኩን
ሠናይ መዓልት እኁየ በሰላም ያስተራክበነ
  • መልካም ቀን ወንድሜ በሰላም ያገናኘን።

🧔🏻አሮን
አሜን ለኩልነ ይኩን
  • ለሁላችን ይሁን።
https://t.me/Geez_Memarya

የግዕዝ መማርያ

14 Jan, 06:30


ተዚያንዎ - ንግግር  - Conversation

           
◦እፎ ውእቱ ጥዒናከ እኁየ ?
/ጤናህ እንዴት ነው ወንድሜ /

◦ዳኅና አነ እኅትየ ፡፡
/ደህና ነኝ እህቴ/

◦አቅርብከኑ ዘይትበላዕ ወዘይሰተይ?
/የሚበላ ወይም የሚጠጣ ነገር ላቅርብልህ/

◦ኢርኅብኩ ፡፡
/አልራበኝም/

◦ኦሆ እኁየ  ?
/እሺ ወንድሜ/

◦እፎ ውእቶሙ ወላድያኒከ?
/ወላጆችህ እንዴት ናቸው/

◦ዳኅና ውእቶሙ ፡፡
/ደህና ናቸው/

◦ንበል ወፂአ ለቃሕዋ ?
/ለቡና ወጣ እንበል/

◦ኦሆ ! ንሑር ወንስተይ ቃሕዋ ፡፡
/እሺ እንሂድ ቡና እንጠጣ/

◦ዝ መካን ሠናይ ውእቱ
/ይህ ቦታ ጥሩ ነው/

◦እወ ኅሩይ መካን ውእቱ ፡፡
/አዎ ምርጥ ቦታ ነው/

◦ኢየአምር ተፈሢሕየ ከመዝኑ በሕይወትየ ፡፡
/በሕይወቴ እንደዚህ ተደስቼ አላውቅም/

◦ግሩም ውእቱ አስተፍሥሕ ርእሰከ ፡፡
/ግሩም ነው እራስህን አዝናና/

◦አኮ ሕይወት ዐራት በዐራት ፡፡
/ሕይወት አልጋ በአልጋ አይደለችም /

◦እወ እኁየ እትመነይ ለከ ዘይኄይስ ዕፃ ፡፡
/አዎ ወንድሜ የተሻለ ዕድል እመኝልሀለሁ/

◦ፍጹመ እሴብሕ ፡፡
/በጣም አመሰግናለሁ/ 
https://t.me/Geez_Memarya

የግዕዝ መማርያ

14 Jan, 05:30


👉መስተዋድድ

መስተዋድድ ከስም እና ከግስ በተጨማሪ ከስም ላይ ወይም ከግስ ላይ እየወደቁ የንግግሩን/የጽሑፉን ሐሣብ የተሟላ እንዲሆን የሚያደርጉ ቀለማት ናቸው፡፡ እነዚህም በግእዝ ቋንቋ ሰዋስው አገባብ ይባላሉ፡፡
በግእዝ ቋንቋ የሚከተሉት መስተዋድዳን አሉ፡፡
🔴 ዲበ፣ላዕለ፣መልዕልተ ➛ በላይ
🔴 ታሕተ፣መትሕተ ➛በታች
🔴 ማዕከለ ➛መካከል/በ _ መካከል
🔴 ውስተ ➛ውስጥ/በ _ ውስጥ
🔴 ቅድመ ➛በፊት/በ _ ፊት
🔴 ድኅረ ➛በኋላ/በ _ ኋላ
🔴 እስከ(እስከነ)➛እስከ
🔴 ኀበ ➛ወደ/ዘንድ
🔴 መንገለ ➛ወደ
🔴 አምሳለ➛ እንደ
🔴 ከመ ➛እንደ
🔴 ምስለ➛ጋር
🔴 እንበለ ➛ያለ፣በቀር
🔴 እም/እምነ ➛ከ
🔴 እመ ➛ቢ፣ባ፣ብ፣ሊ፣ከ ፣ኪ
🔴 እንዘ➛እየ፣ሲ፣ሳ፣ስ
🔴 ሶበ/አመ ➛ በ _ ጊዜ
🔴 ጊዜ➛ በጊዜ/በ _ ጊዜ
🔴 ዝንቱ/ዝ➛ ይህ
🔴 ዛቲ➛ ይህች
🔴 እሉ➛እኝህ
🔴 እላ ➛እኝህ
🔴 ዘ፣እለ፣እንተ ➛የ
🔴 በይነ፣በእንተ፣እንበይነ ➛ስለ
🔴 በይነዝንቱ፣በእንተዝንቱ ➛ስለዚህ
🔴 እምድኅረዝንቱ ከዚህ ➛በኋላ
🔴 እስመ / አምጣነ / አኮኑ ➛ ና
🔴 መጠነ ➛ያህል
🔴 ዳዕሙ / ባህቱ ➛ነገር ግን
🔴 አላ ➛እንጅ
🔴 ወሚመ/አው ➛ወይም
🔴 ናሁ ➛እነሆ
🔴 እፎ ➛እንዴት
🔴 ጌሠም➛ ነገ
🔴 ዮም/ይዕዜ ➛ዛሬ
🔴 ትማልም ➛ ትላንት

👉የመስተዋድዳን ዝርዝር በአስሩ መራሕያን
መስተዋድዳን ቀለማት የሚዘረዘሩ እና የማይዘረዘሩ አሉ።ከማይዘረዘሩት ለምሳሌ እም፣እስከ
የሚዘረዘሩት መስተዋድዳን ግን በአሥሩ መራሕያን በአገናዛቢ ቅጽል አማካኝነት ይዘረዘራሉ።
በሚዘረዘሩበት ጊዜም አብዛኛዎቹ መድረሻቸውን ወደ ኀምስ ይለውጣሉ።
ምሳሌ ፦ ፩. መንገለ
🔵 መንገሌየ = ወደ እኔ
🔵 መንገሌነ = ወደ እኛ
🔵 መንገሌከ =ወደ አንተ
🔵 መንገሌኪ =ወደ አንቺ
🔵 መንገሌክሙ =ወደ እናንተ
🔵 መንገሌክን =ወደ እናንተ
🔵 መንገሌሁ =ወደ እርሱ
🔵 መንገሌሃ=ወደ እሷ
🔵 መንገሌሆሙ=ወደ እነርሱ
🔵 መንገሌሆን=ወደ እነርሱ
ምሳሌ ፦ ፪. ምስለ
🔵 ምስሌየ=ከ እኔ ጋር
🔵 ምስሌነ=ከ እኛጋር
🔵 ምስሌከ=ከ አንተ ጋር
🔵 ምስሌኪ=ከ አንቺ ጋር
🔵 ምስሌክሙ=ከ እናንተ ጋር
🔵 ምስሌክን=ከ እናንተ ጋር
🔵 ምስሌሁ=ከ እርሱ ጋር
🔵 ምስሌሃ=ከ እርሷ ጋር
🔵 ምስሌሆሙ=ከ እነርሱ ጋር
🔵 ምስሌሆን=ከ እነርሱ ጋር
ከኀምስ ውጭም መድረሻቸውን ወደ ራብዕ እና ሳልስ በመቀየር የሚዘረዘሩ አሉ።
ምሳሌ ፦ ፫. ከመ
⚪️ ከማሁ = እንደ እርሱ
⚪️ ከማከ = እንደ አንተ
⚪️ ከማየ = እንደ እኔ
⚪️ ከማሆሙ = እንደ እነርሱ
⚪️ ከማክሙ = እንደ እናንተ
⚪️ ከማነ = እንደ እኛ
⚪️ ከማሃ = እንደ እርሷ
⚪️ ከማኪ = እንደ አንቺ
⚪️ ከማሆ = እንደ እነርሱ
⚪️ ከማክን = እንደ እናንተ
ትምህርቱን እየተከታተላችሁ ያላችሁ በጣም አመሠግናለሁ
https://t.me/Geez_Memarya

የግዕዝ መማርያ

14 Jan, 04:30


📜መስተዋድድ✍🏾

መስተዋድድ ከስም እና ከግስ በተጨማሪ ከስም ላይ ወይም ከግስ ላይ እየወደቁ የንግግሩን/የጽሑፉን ሐሣብ የተሟላ እንዲሆን የሚያደርጉ ቀለማት ናቸው፡፡ እነዚህም በግእዝ ቋንቋ ሰዋስው አገባብ ይባላሉ፡፡
በግእዝ ቋንቋ የሚከተሉት መስተዋድዳን አሉ፡፡
➻ ዲበ፣ላዕለ፣መልዕልተ ➛ በላይ
➻ ታሕተ፣መትሕተ ➛በታች
➻ ማዕከለ ➛መካከል/በ  መካከል
➻ ውስተ ➛ውስጥ/በ  ውስጥ
➻ ቅድመ ➛በፊት/በ  ፊት
➻ ድኅረ ➛በኋላ/በ  ኋላ
➻ እስከ(እስከነ)➛እስከ
➻ ኀበ ➛ወደ/ዘንድ
➻ መንገለ ➛ወደ
➻ አምሳለ➛ እንደ
➻ ከመ ➛እንደ
➻ ምስለ➛ጋር
➻ እንበለ ➛ያለ፣በቀር
➻ እም/እምነ ➛ከ
➻ እመ ➛ቢ፣ባ፣ብ፣ሊ፣ከ ፣ኪ
➻ እንዘ➛እየ፣ሲ፣ሳ፣ስ
➻ ሶበ/አመ ➛ በ  ጊዜ
➻ ጊዜ➛ በጊዜ/በ  ጊዜ
➻ ዝንቱ/ዝ➛ ይህ
➻ ዛቲ➛ ይህች
➻ እሉ➛እኝህ
➻ እላ ➛እኝህ
➻ ዘ፣እለ፣እንተ ➛የ
➻ በይነ፣በእንተ፣እንበይነ ➛ስለ
➻ በይነዝንቱ፣በእንተዝንቱ ➛ስለዚህ
➻ እምድኅረዝንቱ ከዚህ ➛በኋላ
➻ እስመ / አምጣነ / አኮኑ ➛ ና
➻ መጠነ ➛ያህል
➻ ዳዕሙ / ባህቱ ➛ነገር ግን
➻ አላ ➛እንጅ
➻ ወሚመ/አው ➛ወይም
➻ ናሁ ➛እነሆ
➻ እፎ ➛እንዴት
➻ ጌሠም➛ ነገ
➻ ዮም/ይዕዜ ➛ዛሬ
➻ ትማልም ➛ ትላንት

👉የመስተዋድዳን ዝርዝር በአስሩ መራሕያን
መስተዋድዳን ቀለማት የሚዘረዘሩ እና የማይዘረዘሩ አሉ።ከማይዘረዘሩት ለምሳሌ እም፣እስከ
የሚዘረዘሩት መስተዋድዳን ግን በአሥሩ መራሕያን በአገናዛቢ ቅጽል አማካኝነት ይዘረዘራሉ።
በሚዘረዘሩበት ጊዜም አብዛኛዎቹ መድረሻቸውን ወደ ኀምስ ይለውጣሉ።
ምሳሌ ፦ ፩. መንገለ
➻ መንገሌየ = ወደ እኔ
➻ መንገሌነ = ወደ እኛ
➻ መንገሌከ =ወደ አንተ
➻ መንገሌኪ =ወደ አንቺ
➻ መንገሌክሙ =ወደ እናንተ
➻ መንገሌክን =ወደ እናንተ
➻ መንገሌሁ =ወደ እርሱ
➻ መንገሌሃ=ወደ እሷ
➻ መንገሌሆሙ=ወደ እነርሱ
➻ መንገሌሆን=ወደ እነርሱ
ምሳሌ ፦ ፪. ምስለ
➻ ምስሌየ=ከ እኔ ጋር
➼ ምስሌነ=ከ እኛጋር
➻ ምስሌከ=ከ አንተ ጋር
➻ ምስሌኪ=ከ አንቺ ጋር
➻ ምስሌክሙ=ከ እናንተ ጋር
➻ ምስሌክን=ከ እናንተ ጋር
➻ ምስሌሁ=ከ እርሱ ጋር
➻ ምስሌሃ=ከ እርሷ ጋር
➻ ምስሌሆሙ=ከ እነርሱ ጋር
➻ ምስሌሆን=ከ እነርሱ ጋር
ከኀምስ ውጭም መድረሻቸውን ወደ ራብዕ እና ሳልስ በመቀየር የሚዘረዘሩ አሉ።
ምሳሌ ፦ ፫. ከመ
➻ ከማሁ = እንደ እርሱ
➻ ከማከ = እንደ አንተ
➻ ከማየ = እንደ እኔ
➻ ከማሆሙ = እንደ እነርሱ
➻ ከማክሙ = እንደ እናንተ
➻ ከማነ = እንደ እኛ
➻ ከማሃ = እንደ እርሷ
➻ ከማኪ = እንደ አንቺ
➻ ከማሆ = እንደ እነርሱ
➻ ከማክን = እንደ እናንተ
ትምህርቱን እየተከታተላችሁ ያላችሁ በጣም አመሠግናለሁ
ለጓደኞቻችሁም ሼር አድርጉት ግእዝን እናሳድገው
https://t.me/Geez_Memarya

የግዕዝ መማርያ

14 Jan, 03:12


ለወዳጅዎ #ሸር ያድርጉ።
https://t.me/Geez_Memarya
https://t.me/Geez_Memarya
https://t.me/Geez_Memarya

የግዕዝ መማርያ

14 Jan, 03:07


ይህ ቅዱስ ላሊበላ የሚለው ተንቀሳቃሽ የሞባይል መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) በዉስጡ የአራቱን ካህናት ነገስታት ማለትም:- የቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ፣ የቅዱስ ሀርቤ (ገብረማርያም) ፣ የቅዱስ ላሊበላንና የቅዱስ ነአኵቶለአብን ታሪክ ፤ ቅዱስ ላሊበላ ያነጻቸው አስሩ ቤተ መቅደሶች ፤ መልክአ ላሊበላ ዘልሳነ ግዕዝ እንዲሁም በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ዙሪያ የሚገኙ ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትን ታሪክ የሚያስረዳ ተንቀሳቃሽ የሞባይል መተግበሪያ ነው።

ለወዳጅዎ #ሸር ያድርጉ።
https://t.me/Geez_Memarya
https://t.me/Geez_Memarya
https://t.me/Geez_Memarya

የግዕዝ መማርያ

14 Jan, 02:58


https://t.me/Geez_Memarya
share በማድረግ ይተባበሩን

የግዕዝ መማርያ

14 Jan, 02:55


https://t.me/Geez_Memarya

1,536

subscribers

17

photos

16

videos