በአለም በድህነት ከሚታወቁ ሃገራት ሶስተኛዋ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ናት የሚገርመው ... በአለም በከፍተኛ ደረጃ አልማዝ ከሚያመርቱ ሃገራትም ሶስተኛዋ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ናት
...........
ነዳጅ አላት ፡ በዱባይ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቆች ተደርድረው የሚታዩት የወርቅ ጌጣጌጦች በአብዛኛው የሚሄዱት ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ሲሆን በአለም ከሚታወቁ ወርቅ አምራች ሃገራት መሃከልም አንዷ ነች ።
ዛሬ ፡ በኒውዮርክ ፡ ፓሪስ ፡ ለንደን እና ቶኪዮ በሚገኙ ትላልቅ የዳይመንድ መሸጫ ሱቆች ላይ ሚሊየን ዶላሮች የሚጠራባቸው የአልማዝ ጌጣጌጦች .. ተዝቀው የሚወሰዱት. . ከዚች ካልታደለች ደሃ ሃገር ነው ።እንደውም በአለም ላይ በአልማዝ ክምችታቸው ዲሞክራቲክ ኮንጎን የሚበልጡት ሩሲያና ቦትስዋና ብቻ ናቸው ።
ይሄ ብቻ አይደለም ፡ በአለም ደረጃ ለሚመረቱ ለአውሮፕላን ፡ ለመኪና ለሴራሚክስና ለኤሌትሪክ እቃዎች መስሪያ የሚያገለግለው 60% የኮባልት ምርት የሚሄደው ከዚችው ሃገር ነው ።
ከላይ ያወራነው በመመረት ላይ ያለ ማእድኗን ነው ፡ ግን ይህ ብቻ አይደለም. ......
ዲሞክራቲክ ኮንጎ. . ገና ያልተነካ ከ 23 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን ማእድን ያላትም ሃገር ነች ። በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ አመት ብቻ 26 ሚሊዮን ህዝቦቿ ለምግብ ዋስትና ችግር ተጋልጠዋል ። 3.4 ሚሊዮን ህጻናት ደግሞ ለከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በመዳረጋቸው የምእራባውያንን እርዳታ ይሻሉ ።
..........
ፈጣሪ በአልማዝና በወርቅ ቀላቅሎ በሰራው በዚች ሃገር ምድር ከሚኖሩ ዜጎቿ መሃል ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያገኙት ግማሽ ያህሉ ብቻ ናቸው ። ምድሯ በጣም በማእድን ከመበልፀጉ የተነሳ አንድ ሰው በባዶ እጁ ቆፍሮ ማእድን ማውጣት ይችላል የሚባልባት ኮንጎ ፡ ወደ መዋእለ ህጻናት ሄደው የሚማሩት ህጻናት አንድ ፐርሰንቱ ብቻ ናቸው ፡ ለአለም የሚበቃ ሃብት ይዛ መቶ ሚሊየን የማይሞሉ ህዝቦቿን ማኖር ባቃታት ዲሞክራቲክ ኮንጎ ፡ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ሰላሟን የሚነሷት ከአንድ መቶ ሃያ በላይ የሚሆኑ ፡ ታጣቂ ቡድኖች ግን በችግር ምክንያት አንድም ቀን የሚተኩሱት ጥይት አጥተው አያውቁም ።
.............
በአለም በወባ በሽታ በሚሞቱ ዜጎች ቁጥር ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሁለተኛውን ደረጃ ይዛለች ፡ በዚህም ከአምስት አመት በታች የሆኑ 19 በመቶ ህጻናት በየአመቱ ለሞት ይዳረጋሉ ፡ የኮንጎ ህዝብ የሚበላና የሚጠጣ ብቻ አይደለም ችግሩ ፡ የጤና ጉዳይም ብቻ አይደለም ፡ በነጻ የሚገኝ ሰላሙን እንኳን አጥቷል ። መሬቷ ላይ ወርቅ ቢታጣ አልማዝ በሞላበት በዚች ምድር ፡ በየቦታው የሚንቀሳቀሱት ከ 120 በላይ ታጣቂ ሀይሎች ማእድኑን እያወጡ ፡ከሀያላኑ ሀገራት መሳሪያ ይገዙበታል ።
.............
እነሱም እሳቱ እንዲቀጣጠል ሰርጎገብ እስከመላክ በሚደርስ ጣልቃ ገብነት ይሳተፋሉ ። ከአመት አመት ለውጥ የለም ፡ አልማዙ ይወጣል ፡ ወርቁ ይሸጣል ፡ ማእድናቶቿ እንደጉድ ይጋዛሉ ፡ በምትኩ መሳሪያ ይጫንላቸዋል ። ስንዴ በርዳታ ይላካል ።
አፍሪካ ፡ ከእርስ በርስ ጦርነት ወጥታ በሰላም መኖር እስካልጀመረችና ፡ ህዝቧ እስካልነቃ ድረስ ፡ ወደፊትም ፡ በአውሮፓውያን ሲዘረፍና ቅኝ ሲገዛ ይኖራል ።
ይህች በምስሉ ላይ የምናያትም የዲሞክራቲክ ኯንጎ ቦክሰኛ ናት ። እና ከጥቂት ጊዜያቶች በፊት በተጠናቀቀው የፓሪሱ ኦሎምፒክ ላይ በተካፈለችበት ወቅት ፡ በዚህ በሚያሳዝን ሁኔታ ፡ የቦክስ መድረክ ላይ ሆና ፡ አለም የኮንጎ ሁኔታ ላይ ዝምታን መምረጡ እንዳሳዘናት በምልክት በመግለፅ በሀገሯ ሰላም እንዲሰፍን በቻሉት ሁሉ እንዲያግዟቸው ጠይቃ ነበር ።
Via- Wasihun Tesfaye