ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ @smu_gibi_gubae Channel on Telegram

ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ

@smu_gibi_gubae


ይህ ማኅበረ ቅዱሳን አዲስአበባ ማዕከል የቅ/ማ/ዩ/ግ/ጉባዔ የቴሌግራም ቻናል ነው።
#በዚህ_ቻናል
👉ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ወቅታዊ መረጃዎችን ፣መዝሙሮችን ፣ትምህርታዊ ጽሁፎችን እንዲሁም ስለ ግቢጉባዔያችን መረጃዎች እና ማስታወቂያዎች ይደርሳችኋል።
ይህንን ሊንክ በመጫን ለወዳጅዎ ያጋሩ!!
👉 @smu_gibi_gubae

ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ (Amharic)

ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ ቴሌግራም ቻናል ቅ/ማ/ዩ/ግ/ጉባዔ የቴሌግራም ቻናል አዲስአበባ ማዕከል ነው። ይህንን ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያን ወቅታዊ መረጃዎችን፣ መዝሙሮችን፣ ትምህርታዊ ጽሁፎችን እንዲሁም ግቢጉባዔያችን መረጃዎችን እና ማስታወቂያዎች ይደርሳችኋል። በመጫን ለወዳጅዎ በቅድስት ቤተክርስቲያን መረጃዎች ማንበብ እና ልናደርስ ያደርጋሉ። በማንኛውም ጊዜ ላይ እና ከብዙ ምርጥ ቻናል ገልጸዋል። ከዚያ በታች በ @smu_gibi_gubae ለመከታተል ይህንን ቻናል እንደገና ይምረጡ።

ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ

30 Jan, 19:00


ሰላም 2013 ባች የሆናችሁ የመውጫ ፈተና የምትፈተኑ ተማሪዎች የክርስትና ስማችሁን ላኩልን @ab_1994

ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ

29 Jan, 14:56


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል በዓለ ሲመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

ጥር ፳፪ በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላዕክት


ኢዮር፣ ራማ እና ኤረር የተባሉ ሦስት የመላእክት ከተሞች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክት ከፈጠራቸው በኋላ በነገድ 100 በአለቃ 10 አድርጎ በሦስቱ ሰማያት አስፍሯቸዋል፡፡ ኢዮርን በ4፣ ራማን በ3፣ ኤረርንም በ3 ከፍሎ ነው በዐሥሩ ከተማ ያሰፈራቸው፡፡

በዚህም መሠረት ኢዮርን ላይና ታች አድርጎ በ4 ከተማ ከፍሏታል፡፡ በእርሷ ያሉትን መላእክትን በ40 ነገድ 4 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያው ነገድ ‹‹አጋእዝት›› ይባላሉ፡፡ አለቃቸው ሣጥናኤል ነበር፤ እርሱም የመላእክትን ሁሉ ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርግ ነበር፡፡ ከክብሩ ሲዋረድ ቅዱስ ሚካኤል በምትኩ ተሹሞበታል፡፡ ሁለተኛው ነገድ ‹‹ኪሩቤል›› ይባላሉ፡፡ እነርሱም መንበረ ሥላሴን ይሸከማሉ፡፡ የቀሳውስት አምሳል ናቸው፡፡ አለቆቻቸው ገጸ ሰብና ገጸ አንበስ ናቸው፡፡ በሦስተኛው ከተማ በኢዮር ያሉት ሱራፌል ይባላሉ፡፡ የዲያቆናት አምሳል ናቸው፡፡ በትንቢተ ኢሳያስ በምዕራፍ 6 ላይ የተገለጹትና ኢሳያስን ከለምጹ እንዲፈወስ ያደረጉት ናቸው፡፡ አለቆቻቸው ገጸ ላህምና ገጸ ንስር ናቸው፡፡ (በነገራችን ላይ ‹‹ከሩቤል›› ወይም ‹‹ሱራፌል›› የሚባሉ የግለሰብ መጠሪያ ስሞች ስህተት ናቸው፡፡ አንደኛ እነዚህ ስሞች የብዙ መላእክት መጠሪያን የሚወክሉ ናቸው፡፡ ለአንዱ ሲሆን ‹‹ኪሩብ፣ ሱራፊ›› ይባላል፡፡ ‹ኪሩቤል› ወይም ‹ሱራፌል› ማለት ግን የብዙ ቁጥራቸው መጠሪያ ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ የቅዱሳን መላእክትን ስም እንዳለ በቁሙ ወስዶ ለግል መጠሪያ ስም ማዋል ተገቢ አይደለም፡፡ ‹‹ወለተ ሚካኤል፣ ክንፈ ገብርኤል….›› እየተባሉ ይሰየማሉ እንጂ ቀጥታ ‹ሚካኤል›፣ ‹ገብርኤል› እያሉ ሰዎችን መሰየም ስህተት ነው፡፡ 4ኛው ከተማ በኢዮር ያሉት ኃይላት ይባላሉ፡፡ የእሳት ሰይፍ ይዘው በሥሉስ ቅዱስ ፊት የሚቆሙ ናቸው፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወት የዛሉና የደከሙ ክርስቲያኖችን የሚያበረታቱ ናቸው፡፡ አለቃቸውም ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡)

ዳግመኛም እግዚአብሔር በራማ ያሉትን መላእክት በ30 ነገድ በ3 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ‹‹አርባብ›› ይባላሉ፡፡ የሥላሴ እልፍኝ አስከልካዮች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔርን መንበር በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ሁለተኞቹ በራማ ከተማ ያሉት ‹‹መናብርት›› ይባላሉ፡፡ ለእግዚአብሔርን እጅግ ቅርብ የሆኑ ናቸው፡፡ የመብረቅ ጋሻቸውን የእሳት ጦራቸውን ይዘው የሥላሴ ጋሻ ጃግሬዎች ሆነው በተጠንቀቅ ይቆማሉ፡፡ የሰውን ችግር ለእግዚአብሔር ያቀርባሉ፡፡ መዝ. 88፡6፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሦስተኞቹ በራማ ከተማ ያሉት ‹‹ሥልጣናት›› ይባላሉ፡፡ መላውን ፍጥረት ለመጠበቅ ሥልጣን የተሰጣቸውና የምጽአት ዕለት አዋጅ ነጋሪዎች ናቸው፡፡ ዳን. 12፡1፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ሱርያል ነው፡፡

ዳግመኛም እግዚአብሔር በኤረር ያሉትን መላእክት በ30 ነገድ በ3 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ‹‹መኳንንት›› ይባላሉ፡፡ የስላሴ የእሳት ባለ ቀስት ናቸው፡፡ የሰው ልጅ ልዩ ጠባቂዎች ናቸው፤ በተለይ በአደጋ ጊዜ ሎጥን እንዳዳኑት ፈጥነው ይደርሳሉ፡፡ በዕለተ ምጽዓት የሰውን ሁሉ ዐፅም ሰብስበው ለትንሣኤ ዘጉባኤ ያበቃሉ፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ሰዳካኤል ነው፡፡ ሁለተኛዎቹ ‹‹ሊቃናት›› ይላሉ፡፡ የሥላሴ የእሳት ፈረሶች ናቸው፡፡ በእሳት ፈረስ ይመላለሳሉ፡፡ እነዚህም 24ቱ ካህናተ ሰማይ ሲሆኑ አለቃቸው ቅዱስ ሰላታኤል ነው፡፡ በኤረር ከተማ የሰፈሩት ሦስተኛዎቹ ‹‹መላእክት›› ይባላሉ፡፡ ፍጥረትን ሁሉ የሚጠብቁ ናቸው፡፡ አለቃቸው ቅዱስ አናንኤል ነው፡፡ በእነዚህ የማይጠበቅ ፍጥረት የለም፡፡ ከአዝርእት ጀምሮ ሁሉን ይጠብቃሉ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ 7 መላእክትን አየሁ›› (ራዕ. 8፡2) እንዳለ ሊቃነ መላእክት በቁጥር 7 ናቸው፡፡ እነርሱም፡- ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ሩፋኤል፣ ቅዱስ ራጉኤል፣ ቅዱስ ዑራኤል፣ ቅዱስ ፋኑኤል እና ቅዱስ አፍኒን ናቸው፡፡ ‹‹ዑራኤል›› የሚለው ስም ‹ዑር› እና ‹ኤል› ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው፡፡ ‹‹ዑራኤል›› ማለት ትርጉሙ ‹‹የብርሃን ጌታ፣ የአምላክ ብርሃን›› ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው፡፡ በመሆኑም መጽሐፈ ሄኖክ እንደሚገልጸው መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል፡፡ ምሥጢረ ሰማይንና ሰማያዊውን ዕውቀት ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራው ይኸው ገናና መልአክ ነው፡፡ መጽሐፈ ሄኖክ 28፡13፡፡

መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨው ይኸው ገናና መልአክ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡

ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምሥጢር የገለጠለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ ዕውቀት ተሠውሮበት ለነበረው ለኢትዮጵያዊው ሊቅ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በእመቤታችን ትእዛዝ ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምሥጢር የገለጠለት ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ ‹‹ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ፡፡›› መጽሐፈ ዕዝራ 2፡1፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር የሕይወትና የይቅርታ ዝናም በምድራችን ላይ ያዘንብ ዘንድ እንዲሁም የእርሻችንን አዝመራ በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ ለምግብነት እንዲበቃ ከፈጣሪ ዘንድ ምሕረትን የሚለምን መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡

ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በመልአኩ አማላጂነት እጅግ ብዙ ድርሰቶችን የደረሱት መልአኩ ጽዋ ሕይወትን ካጠጣቸው በኋላ ነው፡፡ በመጀመሪያም አባ ጊዮርጊስ የተወለዱት በቅዱስ ዑራኤል አብሳሪነት ነው፡፡ በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሠረቱ አብዛኞቹ ቅዱሳት ገዳማት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው፡፡ ድርሳኑ ላይ የማይጠቅሳቸው የሀገራችን የከበሩ ቅዱሳት ገዳማትና ቅዱሳን ነገሥታት የሉም፡፡

የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክን ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ስትሰደድ መንገድ እየመራ ወደ ግብጽ እና ወደ አገራችንን ኢትዮጵያ ያመጣቸው ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ እመቤታችንን ከተወደደ ልጇ ጋር በደመና ጭኖ መላ ኢትዮጵያን ካስጎበኛት በኋላ ቅድስት አገራችንን ለእመቤታችን የዓሥራት አገር እንድትሆን ያደረገው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡

መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል በዓመት 3 ዓበይት በዓላት አሉት፡፡ ጥር 22 በዓለ ሲመቱ ነው፡፡ መጋቢት 27 የጌታችንን ክቡር የሆነ ወርቀ ደሙን ለዓለም የረጨበት ነው፡፡ ሐምሌ 22 ቀን ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትና ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የዕውቀትን ጽዋ ያጠጣበት ዕለት ነው።
የሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ምልጃና ፀሎት ከሁላችን ጋር ይሁን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ

29 Jan, 11:28


"ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው። በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው። በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው። በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ። አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [የተለያየ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ።"
ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ

ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ

28 Jan, 13:12


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
✝️ እንኳን ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከ፴፫ቱ በዓላት አንዱ ለሆነው አስተርእዮ ማርያም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን ✝️

      🌸 ጥር ፳፩ የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት 🌸
                (አስተርእዮ ማርያም)
‹‹ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ›› (ነግስ ዘቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ)
    ማርያም ማለት ልዕልት ማለት ነው፤ ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ናትና፡፡ አንድም የብዙኃን እናት፣ ጸጋ ወሀብት ማለት ነው፤ ለጊዜው ለእናት አባቷ ተሰጥታለች፤ ፍጻሜው ለዓለም ተሰጥታለችና ፍጽምት ማለት ነው፡፡ አንድም ለጊዜው መልክ ከደም ግባት አስተባብራ ተገኝታለችና ፍጻሜው ግን ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ ይዛ ተገኝታለችና፡፡ አንድም መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት ማለት ነው፤ በአማላጅነቷ ምእመናንን መርታ መንግሥተ ሰማት ታስገባለችና፡፡
   የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት (የአስተርእዮ ማርያም በዓል) ከ33ቱ የእመቤታችን በዓላት መካከል አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከመከራና ከሐዘን ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ታላቅ ዕለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ታላቁ የቤተ ክርቲያናችን አባት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ‹‹ሞት ለማናቸውም ሥጋን ለለበሰ ሰው ሁሉ የተገባ ነው የቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሞት ግን ሁሉን እጅግ ያስደንቃል ያስገርማል›› በማለት ያደነቀው።

ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ የኖረችባቸው 64 ዓመታት እንደሚከተለው ተገልጸዋል።
   ❖ ከእናት ከአባቷ ጋር 3 ዓመት
   ❖ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት
   ❖ ጌታን በጸነሰች ጊዜ በአረጋዊው ዮሴፍ ቤት 9 ወር ከ 5 ቀን
   ❖ ከልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር
   ❖ ከጌታ ዕርገት በኋላ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር 15 ዓመት በድምሩ 64 ዓመት በዚህ በኃላፊው ዓለም ኖራ ጥር 21 ቀን በ49 ዓ.ም በክብር ዐርፋለች።
   ይህንንም አበው ‹‹ሞትኪሰ ማርያም ይመስል ከብካበ›› ‹‹ማርያም ሆይ ሞትሽስ ሰርግ /ከብካብ/ ይመስላል›› በማለት ይናገራሉ፤ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ‹‹ጊዜ ዕረፍታ ለማርያም ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና በልሳነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና›› በማለት በዜማ ድርሰቱ ተናግሯል፡፡ የእመቤታችን ዕረፍት እንባ መራጨት፣ ጠጉር መንጨት፣ ደረት መድቃት እንዳለበት የሰነፍ ሰው ሞት አልነበረም፤ ይልቁንም እንደ ሠርግ ቤት መላእክት በውዳሴ፣ በማኅሌት፣ በዝማሬ፣ በምስጋና ወደ ሰማይ ሸኟት እንጂ፡፡ ይህንን ታላቅ ምሥጢር ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦት›› (መዝ 131፥8) ፣ ‹‹በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች›› (መዝ 44፥9) ሲል የተናገረው ቃለ ትንቢት በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ፣ በንጽሐ ልቡና የጸናች የእመቤታችንን ዕረፍት፣ ትንሣኤ፣ ፍልሰት/ዕርገት/ የሚያስገነዝብ የትንቢት ቃል ነው፤ (ራእ 11፥19)፡፡
   ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ‹‹የሰማይ ንግሥት›› (ራእ 12፥1) በማለት እንደገለጻት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም የእመቤታችንን ክብርና ልዕልና አምልተውና አስፍተው ገልጸውታል፡፡ ‹‹…በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዐን ናቸው፤ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ሥራቸውም ይከተላቸዋል›› ራእ 14፥13) እንዲል እመቤታችን ከዕረፍቷና ዕርገቷ በኋላ የመጨረሻ ወደ ሆነው ክብር መሸጋገሯን ያስረዳል።

◆ የዕረፍቷ ነገር
   64 ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር 21 ቀን ጌታ እልፍ አእላፋት መላእክትን አስከትሎ መጥቶ ‹‹እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ›› ባላት ጊዜ ‹‹ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህን አንተን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማሕፀኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን?›› አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ ‹‹እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል›› አላት፤ አነኚህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው፤ በዚህ ጊዜ ቅድስት ሥጋዋ ከቅድስት ነፍሷ ተለይቷል፡፡ ዕረፍቷ ጥር 21 ሲሆን የሥጋዋ በክብር ማረፍና ዕርገቷ በወርሃ ነሐሴ ነው፡፡ በዚህም ብዙ ተአምራትና አስደናቂ ምሥጢር የተገለጠበት በመሆኑ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› ተባለ።
   አስቀድመው 12ቱ ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሁሉ ተበትነው ነበርና በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ሁሉም ደመናን ጠቅሰው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ መንፈስ ቅዱስ መርቶ አመጣቸው እንጂ ለምን እንደመጡ አያውቁም ነበር፡፡ ይህም የሆነው እንዲህ ነው፡- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍቷ ሲቀርብ በጸሎቷ ሐዋርያትን እንዲያመጣላት ወደ ጌታ በመጸለይዋ ነው፡፡ ጌታም ዮሐንስን ከኤፌሶን፣ የሞቱትን አስነስቶ ያሉትን በደመና ጭኖ አመጣላት፡፡ እነርሱም መጥተው ሰገዱላት፤ በደብረ ዘይት ያሉ ደናግልም ተሰበሰቡ፤ ጌታም እልፍ አእላፋት መላእክትን አስከትሎ መጣ፡፡ በዚህ ጊዜ ዕውራን በሩ፤ ለምጻሞች ነጹ፤ አጋንንት ከሰዎች ወጡ፤ የተለያዩ በሽታ ያለባቸው ሁሉ ተፈወሱ፡፡ ከዚህ በኋላ በዝማሬ መላእክት በቃለ አቅርንት መልአከ ሞት ሳይቀርባት ነፍሷን ከሥጋዋ ለይቶ ሥጋዋን ቅበሩ ብሎ አሳረጋት።

   ቅዱሳን ሐዋርያት የእመቤታችንን የከበረ ሥጋዋን ገንዘውና ከፍነው ለማሳረፍ ወደ ጌቴሴማኒ መካነ ዕረፍት (የመቃብር ቦታ) ይዘው ሲሔዱ አይሁድ በቅንአት መንፈስ ተነሳስተው ‹‹ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሳ፤ በዐርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ እንደገናም ተመልሶ ይህን ዓለም ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ፤ አሁን ደግሞ እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች፣ ዐረገች እያሉ ሲያውኩን ሊኖሩ አይደለምን? ኑ ተሰብሰቡና ሥጋዋን በእሳት እናቃጥል›› ብለው ተማክረው መጡ፡፡ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊም የከበረ ሥጋዋን የተሸከሙበትን የአልጋ ሸንኮር በድፍረት ሲይዝ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁለት እጆቹን ቆረጣቸው፡፡ እጆቹ ተንጠልጥለው ከቆዩ በኋላ ‹‹በእውነት የአምላክ እናት ናት›› በማለት ስለ አመነ እጆቹ ተመልሰው እንደነበሩ ሆነውለታል፡፡ ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ነጥቆ ወስዶ በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ሐዋርያት ሲመጣ የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ በገነት መኖሩን ለቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፤ ሐዋርያትም የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ በገነት አግኝተው ለመቅበር በነበራቸው ምኞትና ጉጉት የተነሣ ‹‹እኛ እንዴት ሳናይ እንቀራለን ብንጠየቅስ ምን እንመልሳለን?›› በማለት በነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ጀምረው ሲጾሙና ሲጸልዩ ሰንብተው በሁለተኛው ሱባኤ መጨረሻ ነሐሴ 14 ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ የከበረ ሥጋ አምጥቶ ስለሰጣቸው በታላቅ ዝማሬና ውዳሴ ወስደው ቀድሞ በተዘጋጀላት መካነ ዕረፍት በጌቴሴማኒ ቀበሩዋት፡፡ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› የተባለበት ዐቢይ ምክንያትም ይህ ነው፡፡ እርሷም በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 ቀን ማክሰኞ ተነስታለች፤ ትንሣኤዋም ‹‹ከመ ትንሣኤ ወልዳ ፥ እንደ ልጇ ትንሣኤ›› ያሰኘው ይህ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይታ የመነሣቷ እውነታና ምሥጢር ነው፡፡

ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ

28 Jan, 13:12


◆ ለምን አስተርእዮ ማርያም ተባለ?
    በዓለ አስተርእዮ (አስተርእዮ ማርያም) የተባለበት ዐቢይ ምክንያት እግዚአብሔር ወልድ በተነገረው ትንቢት በተቆጠረው ሱባኤ መሠረት ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተልሔም ተወልዶና ማንነቱ በይፋ ታውቆ፣ ረቂቁ ገዝፎ፣ የማይታየው ታይቶ፣ የማይዳሰሰው ተዳስሶና በዮርዳኖስ ወንዝ በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ተጠምቆ የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ኅቡዕ ምሥጢር በተገለጠበትና በታየበት ዘመን ዘመነ አስተርእዮ ውስጥ የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍትዋ በዓል ስለሚከበር ነው፡፡
የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ እናትነት፣ በረከትና ቃል ኪዳን አይለየን፡፡ አሜን!
            ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ስንክሳር ዘጥር 21 ፣ ነገረ ማርያም

ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ

28 Jan, 06:46


ተጋብኡ በቅጽበት ለግንዘተ እሙ ቅድስት፨ ብፁዓን ሐዋርያት ቦኡ ኀቤሃ፨ በሰላም አምኁ ኪያሃ፨ በስብሐት ገነዙ ሥጋሃ።

++++++++++++ ተፈጸመ +++++++++++++

ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ተወዳጁ ልጅሽ ወዳጅሽ ፤ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን !!! ለዘለዓለሙ አሜን!!!

ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ

28 Jan, 06:46


#ሥርዓተ_ማኅሌት_ዘአስተርእዮ_ማርያም

እንኳን ለአስተርእዮ ማርያም በሰላም አደረሳችሁ!!! የሌሊቱን ሥርዓተ ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋራ ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል ።

፩. ነግሥ

ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፣
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ፦

ሃሌ ሉያ ለአብ ፨ ሃሌ ሉያ ለወልድ ፨ ለመንፈስ ቅዱስ ሥላሴ ዋህድ፨ እፎኑመ እመ አምላክ በከየት ደንጊፃ ፨ከመ ኲሉ ሰብእ ሞት ሶበ ሐወጻ ፨ ዮሐንስ በልብሱ ከደነ ገጻ።

ወረብ፦

እፎኑመ እመ አምላክ በከየት ደንጊፃ በከየት እመ አምላክ፤
ከመ ኲሉ ሰብእ ሞት ሶበ ሐወጻ በከየት።

፪. ነግሥ
ለምንት ይዜኃር ኃያል በኃይሉ፤
ወባዕል በብዝኃ ብዕሉ፤
ኢያድለወ ሞተ ክርስቶስ ለሥጋ አባሉ፤
ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ፤
ሞታ ለማርያም የአፅብ ለኲሉ።

ዚቅ፦

እንበይነዝ አእምሩ በውስተ ፍትሕ ከመ ኢያደሉ፨ ትጥዓም ሞተ እሙ ወእመ ኲሉ፨ አዘዘ ወልድ በርቱዕ ቃሉ።

፫. ለዝክረ ስምኪ /መልክአ ማርያም/

ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤
እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤
ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤
ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤
ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።

ዚቅ፦

ለዛቲ ድንግል ሠረቀ ላዕሌሃ ፨ብዕለ ጸጋሁ ለአብ፨ ወአግአዛ እምእኩይ ውስተ ሠናይ፨ እሞት ውስተ ሕይወት ፨ ወረሰየ ይዝክሩ ስማ ውስተ ኲሉ ዓለም።

ወረብ፦

ለዛቲ ድንግል ሠረቀ ላዕሌሃ ብዕለ ጸጋሁ ለአብ፤
ወአግአዛ እምእኩይ ውስት ሠናይ እሞት ውስተ ሕይወት፤

፬. ለእስትንፋስኪ / መልክአ ማርያም /

ሰላም ለእስትንፋስኪ ዘመዓዛሁ ሕይወት፤
ከመ መዓዛ ዕፅ ኅሩይ ዘውስተ ገነት፤
ማርያም ድንግል ቤተ ቅድሳት፤
ጽንሕኒ ውስተ ሠናይ ወሰውርኒ እሞት፤
በአክናፍኪ ርግብየ ኅሪት።

ዚቅ፦

አንጺሖ ሥጋሃ ቀዲሶ ኪያሃ፨ ኀደረ ቃል ላዕሌሃ፨ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፨ ወይቤላ ለድንግል፨ ሃሌ ሃሌ ሉያ፨ ሰሎሞን ይቤላ እኅትየ መርዓት፨ ርግብየ ሠናይት፨ ፍናወ ዚአኪ ገነት፨ እስመ ኪያኪ ኀረየ ለታዕካሁ፨ ከመ ትኩኒዮ ማኅደረ ለልዑል።

ወረብ፦

አንጺሖ ሥጋሃ አንጺሖ ሥጋሃ ላዕሌሃ ኀደረ፤
ቀዲሶ ኪያሃ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ይቤላ ለድንግል።

፭. ለገቦኪ / መልክአ ማርያም /

ሰላም ለገቦኪ ዘሐመልማለ ወርቅ ክዳኑ፤
በከመ ዳዊት ይዜኑ፤
ማርያም ድንግል ለያዕቆብ ሞገሰ ስኑ፤
በልኒ እግዝእትየ አፈቅረከ አኮኑ፤
እንዘ ረዳኢትከ አነ ዘይክለከ መኑ።

ዚቅ፦

እምሰማያት ወረደ ፨ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር፨ ኖላዊ ኄር ኖላዊሆሙ ለእሥራኤል ፨ ወረደ ስኖ ለያዕቆብ ዘአፍቀረ፨ ወስኑሰ ለያዕቆብ ዘይቤ ይእቲ ሥጋ እንተ ነሥአ፨ መድኅን እማርያም።

ወረብ፦

ወስኑሰ ለያዕቆብ ዘይቤ ዘይቤ ያዕቆብ፤
ይእቲ ሥጋ ይእቲ ሥጋ እማርያም እንተ ነሥአ መድኅን።

፮. ለፀዓተ ነፍስኪ / መልክአ ማርያም /

ሰላም ለፀዓተ ነፍስኪ እንበለ ፃዕር ወፃማ፤
ለነቢር ዘልፈ በየማነ ወልድኪ ፌማ፤
ማርያም ድንግል ለባሲተ ሞገስ ወግርማ፤
አጽንዒ በረድኤትኪ ለሕይወትየ ድካማ፤
እምሕይወተ ኄራን አበው ኢታሕጽጺ ዐቅማ።

ዚቅ፥

ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና ፨ ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና፨ ጠሊላነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና።

ወረብ፦

ጊዜ ዕረፍታ ለማርያም ጊዜ ጊዜ ጊዜ ዕረፍታ ለማርያም፤
ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ።

፯. ለበድነ ሥጋኪ / መልክአ ማርያም /

ሰላም እብል በድነ ሥጋኪ ጽሩየ፤
ዘተመሰለ ባሕርየ፤
ማርያም ድንግል ዐጸደ ወይንየ፤
ንስቲተ ለዕበየኪ እንተ አቅረብኩ ግናየ፤
ኢይትኃደግ ዲበ ምድር ምሥጢ ሰማየ።

ዚቅ፦

ኦ ትቤ ማርያም ፨እወጽእ እምዝንቱ ሥጋየ፨ ወአሐውር ውስተ ሕይወት ዘለዓለም፨ ኦ ተዘከርኬ ዮሐንስ ዘይቤለከ ሊቅ አመ ትረፍቅ ዲበ እንግድዓሁ።

፰. ለግንዘተ ሥጋኪ / መልክአ ማርያም /

ሰላም ለግንዘተ ሥጋኪ በእደ ሐዋርያት አርጋብ፤.በአፈወ ዕፍረት ቅድው ዘሐሳበ ሤጡ ዕፁብ፤
ማርያም ድንግል ወለተ ኅሩያን ሕዝብ፤
ረሰይኩኪ እግዝእትየ ህየንተ እም ወአብ፤
ይሕፅነኒ ከመ ጥብ ፍቅርኪ ሐሊብ።

ዚቅ፦
ተጋብኡ በቅጽበት ለግንዘተ እሙ ቅድስት፨ ብፁዓን ሐዋርያት ቦኡ ኀቤሃ፨ በሰላም አምኁ ኪያሃ፨ በስብሐት ገነዙ ሥጋሃ።

፱. ለመቃብርኪ / መልክአ ማርያም /

ሰላም ለመቃብርኪ ለጌቴሴማኒ በመርኅባ፤
እንተ ይእቲ ለኢየሩሳሌም ቅሩባ፤
ማርያም ድንግል ለሀገረ መንግሥት ርግባ፤
ትትሜጦ ወረቀ እምአፌር ወጸበለ አፈው እምሳባ፤
ጌቴሴማኒ ለሥጋኪ ምስካባ።

ዚቅ፦

ሃሌ ሃሌ ሉያ፨ ዓውዳኒ ዘጽድቅ ወመርኅባኒ ዘዕንቊ፨ አንቀጸ አድኅኖ ሐዳስ ንጽቅ።

፲. ለመቃብርኪ / መልክአ ማርያም /

ሰላም ለመቃብርኪ ለኢየሩሳሌም በአድያማ፤
እንተ ይእቲ ጌቴሴማኒ ስማ፤
ማርያም ሰንበት ዕረፍተ ጽዑራን እምፃማ፤
አመ ኀደረ ላዕሌኪ ፀሐየ ቅዱሳን ዘራማ፤
ኃይለ ልዑል ጸለለኪ በመንክር ግርማ።

ዚቅ፦

ኢይሜንንዋ ኪያሃኒ ወአድያሚሃኒ ነያ ጽዮን ፨ ቅድስት ሀገረ እግዚአብሔር።

፲፩. እግዚአብሔር ጽጌ ትንቢት / ማኅሌተ ጽጌ /

እግዚአብሔር ጽጌ ትንቢት ለቢሶ ሥጋኪ ሥጋ ዚአነ፤
አመ አስተርአየ በምድር ወተአምረ ለነ፤
ንዌድሰኪ እንዘ ንብል ምክሃ ዘመድነ፤
ዮም በፍሥሃ ለማርያም እምነ፤ አስተርእዮ በሰማይ ኮነ።

ዚቅ፦

አስተርአየ ዘኢያስተርኢ፨ ኮነ እሙነ አስተርእዮቱ ለመድኃኒነ ክርስቶስ፨ እሙነ ኮነ አስተርእዮቱ፨ እምድንግል ተወልደ፨ እሙነ ኮነ አስተርእዮቱ፨ በሥጋ ረቂቅ፨ እሙነ ኮነ አስተርእዮቱ፨ በ፴ ክረምት በዮርዳኖስ ተጠምቀ፨ በበሕቅ ልሕቀ።

++++++++++ አንገርጋሪ ++++++++++

ኢኮነ ነግደ ወፈላሴ ሀገሪቶሙ ለቅዱሳን፤
ንሕነ ሰብአ ቤቱ ለእግዚአብሔር ኲልነ፤
አምላክ ኀደረ ውስተ ሥጋ ተአቊረ፤
እንዘ ኢይትጋባዕ በሙላድ፤
ዘድንግል መናሥግተ ኢያርኂዎ ዘኪሩቤል ኢርእዮ።

++++++++++አመላለስ+++++++

ዘድንግል መናሥግተ ኢያርኂዎ፤
ኢያርኂዎ ዘኪሩቤል ኢርእዮ ኢያርኂዎ ኢርእዮ ዘኪሩቤል።

++++++++++ እስመ ለዓለም ++++++++++

እግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ፨ ቃል ቅዱስ፨ መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፨ ዘመንበሩ ዓቢይ ውእቱ፨ ያቀድም አእምሮ ኅሊና ሰብእ፨ መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፨ ግሩም እምግሩማን፨ ዘመጽአ ውስተ ዓለም፨ መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፨ ስብሐት ዘኢየኃልቅ ወስን ዘኢያንጸበርቅ፨ መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፨ ዘይሥዕሎሙ ለሕፃናት፨ ወይነግሥ ለመላእክት መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፨ እስመ ንጉሥ ውእቱ ሰከበ በጎል፨ ሰገዱ ሎቱ ሰብአ ሰገል፨ መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፨ እምግርማሁ ትርዕድ ምድር፨ ዜናዊ ስቡሕ ዘለዓለም፨ ወእስከ ለዓለም ንጉሥ ውእቱ።

++++++++++ አመላለስ ++++++++++

ዘመንበሩ ዓቢይ መንበሩ ውእቱ መንበሩ ዘኪሩቤል፤
ያቀድም አእምሮ አእምሮ ኅሊና ሰብእ።

++++++++++++ አቡን ++++++++++++

አቡን ሃሌ ሉያ ወበውእቱ መዋዕል ወጽአ ትእዛዝ እምኀበ ቄሣር ንጉሥ፨ ከመ ይጸሐፍ ኵሉ ዓለም ፨ ማርያምሰ ወለደት ወልደ ዘበኵራ ፨ ቤዛነ ዓቃቤ ነፍሳቲነ ፨ እስመ እምዘርዓ ዳዊት ዘመጽአ በቤተልሔም ዘይሁዳ።

++++++++++ ሰላም ++++++++++

ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ

25 Jan, 09:35


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
   ጥር 18🕯 ዝርወተ ዐፅሙ ለቅዱስ ጊዮርጊስ

ጊዮርጊስ ማለት ኮከበ ጽባሕ፣ ፀሐይ፣ ሐረገ ወይን ማለት ነው፡፡ የተወለደው ጥር 2 ቀን በታናሿ እስያ በቀበዶቅያ ሲሆን አባቱ ዘረንቶስ (በቅብጥ ቋንቋ አንስጣስዮስ) እናቱ ቴዎብስታ (በቅብጥ ቋንቋ አቅሌስያ) ይባላሉ፡፡ ማርታና እስያ የሚባሉ ሁለት እህቶች ያሉት ሲሆን አባቱ የቀበዶቅያ መስፍን ነበር፡፡
  ዐሥር ዓመት ሲሞላው አባቱ ስለሞተ በምትኩ ሌላ ደግ መስፍን ተሾመና በቤቱ እያስተማረ አሳደገው፡፡ እርሱም ፈረስ ግልቢያና ቀስት ውርወራ ለምዶ ጦር ሜዳ ወጣ፤ በዚያም በጠላቶቹ መካከል ገብቶ ‹‹እኔ የክርስቶስ ወታደር በክርስቶስ ስም እመጣባችኋለሁ›› ሲል ጠላቶቹ ደንግጠው ይበተኑና ይሸሹ ነበር፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ 20 ዓመት በሞላው ጊዜ ይህ መስፍን ሞተ፤ ከዚህ በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኀዘኑን ጨርሶ ወደ ቤሩት ሔደ፡፡ በቤሩት ደራጎንን ያመልኩና ሴት ልጃቸውን ይገብሩለት ስለነበር ደራጎኑን በኃይለ መስቀል ድል ነስቶት ሕዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መልሷቸዋል፡፡ በዚያም ቤሩታዊቷን ከደራጎን አስጥሏታል፡፡
   በፋርስ የነበረ ጣዖት አምላኪ የነበረው ንጉሥ ዱድያኖስ በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ብዙ መከራን አድርሶበታል፤ ጥር 18 ቀን ሥጋውን በመንኮራኩር ፈጭተው አጥንቱን በደብረ ይድራስ ላይ ዘሩት፡፡ ሥጋው ያረፈበት ሳር፣ ቅጠሉ፣ ደንጊያው፣ እንጨቱ ሁሉ ‹‹ጊዮርጊስ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር፣ ጊዮርጊስ ሰማዕቱ ለእግዚአብሔር›› እያሉ አመስግነዋል፡፡ ጌታችን ከሞት አስነስቶት ሥጋውን ፈጭተው ወደ ተራራ ላይ በትነው ወደ ንጉሡ የሚመለሱትን ወታደሮች ከኋላቸው ደርሶ ‹‹ቆዩኝ ጠብቁኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም እጅግ ደንግጠው ይህ እንዴት እንደሆነ ሲጠይቁት ‹‹አምላኬ ከሞት አዳነኝ›› አላቸው፡፡ ጭፍሮቹም እጅግ ደንግጠው ከእግሩ ሥር ወድቀው ይቅር በለን ብለው በአምላኩ እንደሚያምኑ መሰከሩለት፤ ቅዱስ ጊዮርጊስም ከመሬት ላይ ውኃ አመንጭቶ በጸሎት ጌታችንን ቢጠይቅ ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ አጥምቋቸዋል፡፡ እነርሱም በንጉሡ ፊት ሔደው ስለ ጌታችን በመመስከር በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዐፅሙ ተቃጥሎ አጥንቱ ተፈጭቶ በደብረ ይድራስ ላይ የተበተነበት ጥር 18 ቀን ስለሆነ መታሰቢያውም በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ (የቅዱስ ጊዮርጊስን ሰፋ ያለ ታሪክ ሚያዚያ 23 ቀን ይመልከቱ)፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን አሜን!
             ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ስንክሳር ዘጥር 18 ፣ መድበለ ታሪክ ፣ ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ
       •════•🍃🌹🍃•════•

ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ

24 Jan, 16:31


ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን የሚለውን ዩቲዩብ ቻናል እዚህ ግሩፕ ውስጥ ያላችሁ ሰብስክራይብ እንድታደርጉ እና ያሬዳዊ መዝሙራት እና ኪነጥበባዊ ዝግጅቶችን እንድትከታተሉ ፣ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ሼር ላይክ በማስደረግ በየ social midia እንድናስተዋውቅ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ።
 
https://youtube.com/@-zemawetibebzmk7905?si=iRlgwFiTrsXJWG9b

1,345

subscribers

2,403

photos

28

videos