ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media @weldwahid Channel on Telegram

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

@weldwahid


ይህ የኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤተክርስቲያን ወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤት ቻናል ነው

👉👉ለጠቅላላ @weldwahid

👉👉ለአብነት እና ግእዝ ቋንቋ ትምህርት
@weldwahidabinet

👉👉 ለቤተ መጻሕፍት አገልግሎት @Abaiyesuslib
👉👉ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት
@mels_asteyayet

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media (Amharic)

ክፍልና እናት ፣ ሚዲያ ጥያቄዎች እና እናት ፣ ማናንተ ናቸው? አሁንም በዚህ አይነት ለማንኛውም ፣ ማና ነው? ክፍልው የዚህ ክፍለ መጽሐፍ ናቸው። ይህ ወልድ ዋሕድ ሚዲያ፦ welid wahid media የሚባል ነገር ሆኖ፣ ራእይ መጠለያዎችን ይጠብቃሉ። ክልፍን በመጠቀም የኢትዮጵያውያንን ስብስብ ስነጥበባችንን በመላኩ የሚያሟሉ፣ ወጎችንና ዓረቦችን በትምህርት ከፍ እንዳያገኙ እና አንድ በትምህርትነቱ ለአገልግሎትን ይደረጉት። ከዚህም ላይ የሚኖሩበት ሰው ሰላም! በማብራሪያ እና አስተዳየት ቋንቋችሁን እና አዲሱ ብቃትን ወደ ትምህርትም ይመለከታል። ምሳሌንና መልስን ከአንድ በላይ እና ዝርዝር ሰጥተን ወደ ክፍለ ምግብ ከመጠቀም እና ምንም ግላዊ አጭር፤ ልናቸው።

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

27 Jan, 08:31


#እኔ አልቀርም
#ሰው እጋብዛለሁ
#ለወዳጆቼ አጋራለው🙏

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

27 Jan, 08:18


2 ቀን ቀረው

"እኛ ግን ይህን እንቃወም ከኃጢያት በቀር ምንም ክፉ ከበጎ ሥራ በቀርም ምንም በጎ እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኘው ነገር እንዴሌለ ለይተን ልናውቅ ይገባናል። ደስታን የሚያመጣው መንፈሳዊ ጸሎት እንጂ ጽኑ መጠጥ አይደለም ደስታን የሚያመጣው ቃለ እግዚአብሔር እንጂ ወይን አይደለም..ወይን የነፍስ መታወክ ያመጣል ፡ቃለ እግዚአብሔር ግን ጸጥታን ያመጣል።ወይን የነፍስ ሁከትን ያመጣል፡ ቃለ እግዚአብሔር ግን ሁካታን ያርቃል። ወይን ዓይነ ልቡናን ያጨልማል ፡ ቃለ እግዚአብሔር ግን የጨለመውን ዓይነ ልቡና ያበራል። ወይን (ስካር) ቀድሞ ያልነበሩትን ኀዘናት ያመጣል፣ ቃለ እግዚአብሔር ግን ቀድሞ የነበሩትንም ሳይቀር ያርቃል።

ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

27 Jan, 04:07


“አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።”
  ማቴዎስ 6፥6

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

26 Jan, 18:23


"3-5፤ ሁልጊዜ በጸሎቴ ሁሉ ስለ እናንተ ሁሉ በደስታ እየጸለይሁ፥ ከፊተኛው ቀን እስከ ዛሬ ድረስ ወንጌልን በመስበክ አብራችሁ ስለ ሠራችሁ፥ ባሰብኋችሁ ጊዜ ሁሉ አምላኬን አመሰግናለሁ።"

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:3-5፤


"1፤ በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፥ የመንፈስ ኅብረት ቢሆን፥ ምሕረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፥ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤"

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:1፤

"10፤ ነገር ግን አሁን ከጊዜ በኋላ ስለ እኔ እንደ ገና ልታስቡ ስለ ጀመራችሁ፥ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤ ጊዜ አጣችሁ እንጂ፥ ማሰብስ ታስቡ ነበር።"

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:10፤

"1፤ ስለዚህ፥ የምወዳችሁና የምናፍቃችሁ፥ ደስታዬና አክሊሌ የምትሆኑ ወንድሞቼ ሆይ፥ እንዲሁ በጌታ ቁሙ፥ ወዳጆች ሆይ።"

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:1፤

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

26 Jan, 18:22


የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ ‹‹እግዚእ ወገብር፤ አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ›› ማለት ነው።
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
የቅዱስ ገብርኤል ልመናውና አማላጅነቱ  በኹላችን ላይ ይኹን!

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

26 Jan, 18:02


ወንድሞች ሆይ ሁላችን እንሞታለን። በዚህ ዓለም ሳለን እርስ በርሳችን የማንዋደድ ከሆነ ከባድ ይሆንብናል። ከጠላቶቻችን ጋር ፈጥነን  የማንታረቅ ከሆነ ያስቀየምናቸውንም ወገኖች ይቅርታቸውን የማናገኝ ከሆነ አንዱ ሌላውን የሚኮንን ከሆነ ይቅርም ካላልነው ችግር ይፈጠርብናል። በሚመጣውም ዓለም ዘላለማዊ ሕይወትን አናገኝም። ሰማያዊው አባታችን ኃጢአታችንን ይቅር አይለንም።
   "ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ"
        @weldwahid

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

26 Jan, 17:23


የተሳትፎ ጥያቄ

ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጉም .....ማለት ነው።

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

26 Jan, 09:44


" ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ፤ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። "
       (ትንቢተ ኤርምያስ 15:16)


ሳምንታዊው የረቡዕ ጉባኤ
3 ቀን  ቀረው
📆ጥር 21      🕰12:00
አይቀርም

#እኔ አልቀርም

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

26 Jan, 01:11


ዕለተ ሰንበትን መጽሐፍ ቅዱስ በማንበብ ይሳልፉ

ባለ አራት ምዕራፉ የፊልጵስዩስ መልእክት የደስታ መልእክት ይባላል::


እባክዎን ከመልእክቱ ውስጥ ደስታን የሚመለከቱ ጥቅሶች ፈልገው ይጻፋልን

መልካም ዕለተ ሰንበት

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

25 Jan, 17:50


"እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን::"

     ሥርዓተ ቅዳሴ

እንኳን አደረሳችሁ
ጥር 18
ዝርወተ አጽሙ
ለቅዱስ ጊዮርጊስ

የቅዱስ ጊዮርጊስ አማላጅነት አይለየን🙏

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

25 Jan, 17:20


የተሳትፎ ጥያቄ

በነገው ዕለት የሚከበረው በዓል ................ነው?

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

25 Jan, 17:08


ዕለተ ሰንበት በማስቀድስ እናሳልፍ

ቅዳሴ ማስቀደስ ማለት ከክርስቶስ ቁስል አጠገብ መቆም ነው

መጋቢ ኃይማኖት ተስፋዬ ሞሲሳ

#እንዳላስቀድስ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

25 Jan, 16:03


የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፭

፩.ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤

፪አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ።

፫በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።

፬የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።

፭የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።

፮.ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።

፯.የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።

፰.ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና።

፱.የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።

፲.ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።

፲፩ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።

፲፪.ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

25 Jan, 13:55


1ኛ ሳሙ 2÷1-10

(ልቤ በእግዚአብሔር ጸና)

የሳሙኤል እናት ሐና  የጸለየችው ጸሎት።

ጸሎቱን አንብበው ሲጨርሱ አንዱን ቃል ይጻፋልን

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

25 Jan, 12:03


የተማሪዎች ጉባኤ
ኦርቶዶክሳዊ የጾታ ትምህርት ዙሪያ የተዘጋጀው የመጀመሪያ ክፍል የሆነው  ውይይት   በዲያቆን ሰሎሞን ኢያሱ እየተመራ  ተካሄደ ።

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

25 Jan, 12:02


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
"በድህነት እና በረሃብ የሚሰቃዩ ሰዎች እንደ ሠለስቱ ደቂቅ ናቸው።ከድህነት የበለጠ ምን እሳት አለ? ከረሃብስ የሚበልጥ ምን ነበልባል አለ? ሥስቱ ወጣቶች እሳት ውስጥ ሆነው እንደዘመሩ በመከራ ውስጥ ሆኖ ፈጣሪን የሚያመሰግን ሰው የመከራው እሳት ውኃ ይሆንለታል ።ለድሆች ምጽዋትን የሚሰጥ ሰው ደግሞ ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት የታደገውን የእግዘብሔር መልአክን ይመስለዋል"

   🌹 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  🌹

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

19 Jan, 18:30


የተሳትፎ ጥያቄ 2

💠ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ከሐዋርያት ጋር የተገኘበት ሰርግ ቤት ................. ነው።

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

19 Jan, 18:11


የተሳትፎ ጥያቄ

💠 ጥር 12 የሚከበረው በዓል የምን በዓል ነው?

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

19 Jan, 16:32


"አጠገብኽ  ስለሌለው  ሰው  ድክመት በተናገርክ ቁጥር፤ ሰይጣን  ይዘፍንበት  ዘንድ  ምላስኽን  በገና  አድርገኽ እንደሰጠኽ ይቆጠራል።"

ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

19 Jan, 05:28


🌹ሳምንታዊው የተማሪዎች ጉባኤ🌹

     ኦርቶዶክሳዊ የጾታ ትምህርት
                      ልዩ
            ተከታታይ ትምህርት

📆ከአርብ ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም  ጀምሮ

በመምህር ቀሲስ ብሩ ተስፋ
         
  ⌚️ ከ 9:30 ሰዓት ጀምሮ
     ⛪️ በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ


               🔔🔔🔔🔔🔔
             🔔  6 ቀን ቀረው🔔
                🔔🔔🔔🔔🔔

#እንዳልማር የሚከለክለኝ ማን ነው?
#በዕለቱ  እገኛለሁ
#አንድ ኦርቶዶክሳዊ ይዤ እገኛለሁ
#የተማሪዎች ጉባኤ

#share

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

19 Jan, 03:31


"ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጠመቁ ምክንያት ከብሉይ ወደ ሐዲስ፥ ከኦሪት ወደ ወንጌል አሻገረን፤ የመንግሥተ ሰማያትን ደጅ ከፈተልን፤ ወደ ሀገራችን (ወደ ሰማይ) ይጠራን ዘንድ ብቻ ሳይኾን ሊነገር በማይችል ክብር ያከብረን ዘንድም ቅዱስ መንፈሱን ላከልን፡፡"

  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

18 Jan, 16:21


"ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል"

              ቅዱስ ሚናስ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

18 Jan, 11:28


💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦
“ስንጠመቅ በጲላጦስ ዘመን ከተሰቀለው ከክርስቶስ፣ በነብያት አንደበት ስለ ክርስቶስ ከተናገረው ከመንፈስ ቅዱስ፣ በዮርዳኖስ የምወደው የምወልደው ልጄ እርሱ ነው ካለው ከአብ ዳግመኛ እንወለዳለን”
 
      ሰማዕቱ ዮስጢኖስም

እንኳን ለከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
መልካም በዓል

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

18 Jan, 01:50


"ፍቅረ ንዋይ ክፉ ነው፡፡ ፍቅረ ንዋይ ዓይነ ልቡናን ያሳውራል፤ እዝነ ልቡናንም ያደነቁራል፡፡

ሰዎችን ከሰውነት አስወጥቶ እንደ አውሬ እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል፡፡

በዚኽ በፍቅረ ንዋይ ደዌ የተያዘ ሰው ሰማይ ወርቅን ታዘንብለት ዘንድ፣ ምድርም የብር ጋኖችን ታፈራለት ዘንድ፣ ጳዝዮን የተባለውንም ጥሩ ዕንቁ ታመነጭለት ዘንድ፣ ተራሮችም ወደ ወርቅ ይለወጡ ዘንድ ይወድዳል፡፡

ገንዘባቸውን ይሰበስብ ዘንድ ባለጠጎችን ይጠላል፡፡ ወንድሞቹንና ዘመዶቹን፣ ወዳጆቹንና ወገኖቹንም ይክዳል፡፡"
             
               ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

17 Jan, 18:46


"አምላኬና ጌታዬ ኾይ 👏
አንተ ከኔ ከራቅኽ እኔ አንተን ካልተቀበልኹ ሌላ ሕይወት አይገባኝምና አቤቱ እንዴት ባለ ገደል እወድቃለኹ ይኾን?

እንደምንስ ባለ መከራ ተይዤ እጨነቃለኹ ይኾን?

የልቤን ክፋት - የልቤን ወስላታነት የሚያጠፋ መድኃኒት ካንተ ካላመጣኹ ከማን አመጣለኹ?

ከጠላቶቼ የማመልጥበት መማጠኛ ካንተ በቀር ማን አለኝ? የሰጠኸኝንስ ጸጋ በልቤ የሚያኖርልኝ ሌላ ማን አለ? አንተ አይደለኽምን?"

                           ውዳሴ አምላክ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

17 Jan, 09:54


❤️አባ ጥጦስ❤️

አንድ ወንድም አባ ጥጦስን "እንዴት ልቤን መጠበቅ እችላለኹ?" ሲል ጠየቀው ።

አባ ጥጦስም "አፋችንና ሆዳችን ክፍት ከኾነ እንዴት ልባችንን መጠበቅ ይቻለናል?" ሲል መለሰለት።

💡💡💡💡💡💡💡💡💡💡💡💡

ኹለት ከመናገር አንድ ማድመጥ ይላሉ አበው። አንደበታችንን ሳንገታ ቅድስና የለም!

     🌹@weldwahid🌹
         መልካም ቀን

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

16 Jan, 13:08


"ሚስትህ ተጣልታህ ከቤት እቃዋን ሰብስባ ስትወጣ ዝም ብለህ አትያት "የቀረሽ እቃ አለ" በላት "ምንድን ነው?" ስትልህ እኔምኮ ያንቺ እቃ ነኝ ይዘሺኝ ሒጂ በላት"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

16 Jan, 04:49


“የእግዚአብሔር መንገድ በየዕለቱ የሚኾን መስቀል ነው፡፡ ያለ ውጣ ውረድና ተጋድሎ፣ እንዲኹ ተዘልሎ የሚኖር ማንም ሰው ወደ መንግሥተ ሰማያት ሊወጣ አይችልም፡፡ እንዲኽ ያለው ተዘልሎ የመቀመጥ ሕይወት መንገድ የት እንደሚያደርስ እናውቃለን፡፡ ይኽም ራሱ ጌታችን ፍጻሜው ጥፋት ነው ብሎናልና፡፡”  
                
       ማር ይስሐቅ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

15 Jan, 12:05


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

የአበው ምክር!

👉 ፀሐይ በረዶን እንደሚያቀልጥ ምጽዋት ኃጢኣትን ታቀልጣለች።

👉 ጌታ ኾይ የኃጢኣቴን ብዛት የሰውነቴን ክፋት ታገስ 🙏 ባለመድኃኒት የቁስልን ክፉ መዓዛውን እንዲታገስ።

👉 አንዳንዱ ሰው ኃጢኣት  ከመሥራት ይልቅ የሠራውን ኃጢኣት መናዘዝ ይከብደዋል።

👉 በትንሽ ቀዳዳ የሚገባ ብርድ ሰውነትን እንደሚጎዳ ኹሉ በትንሽ ድክመት የሚገባ ኃጢኣትም ለሞት ይዳርጋል።

👉 ኃጢኣት በእግዚአብሔር ላይ ማመጽ ፍቅሩንም ማጣት ነው።

👉 ኃጥኣንን ውደዳቸው በሥራቸው ግን አትምሰላቸው ☝️ እነሱ በተያዙበት ፍዳ እንዳትያዝ!

👉 በኅሊናኽ ኃጢኣት ሲፈትንኽ ስለአንተ መከራ የተቀበለልኽን አምላክ አስብ።

👉 መከራ እንዳይመጣብኽ ከፈለክ  ኃጢኣት ከመሥራት ተቆጠብ።
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

15 Jan, 05:03


ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ ውእቱ አምላክ ፍጹም አሐዱ ውእቱ 🙏🙏🙏

ኵሉ ይሰግድ ለሥላሴ ፤ ወይትቀነይ ኵሉ ለመንግሥተ ሥላሴ፤
እስመ ኮነ ዘይነብር ዲበ ኪሩቤል፤
ወበዓይኑ ይኔጽር ቀላያተ፡፡

🌹እንኳን ሥሉስ ቅዱስ የባቢሎንን ግንብ ላፈረሱበት ዕለት እና ለቅዳሴ ቤታቸው ለከበረበት ዕለት በሰላም  አደረሳችኹ!🌹

ቅድስት ሥላሴ የእኛንም መለያየት እና የከበበንን መከራ እንደባቢሎን ግንብ አፍርሰው ለሕይወት ያብቁን 🤲🤲🤲 አሜን በእውነት!

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

11 Jan, 17:42


"እግዚአብሔርን "ለምን ትረሳኛለህ?" አትበለው "ጌታ ሆይ የረሳሁህን እኔን ይቅርበለኝ፤ ፍቅርህን ዘንግቻለሁና በመከራዬ ጊዜም አስበኝ" በለው እንጂ።"
#አቡነ_ሽኖዳ_ሣልሳዊ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

11 Jan, 10:53


የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም!!

   ✝️  የበደሉንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሳይሆን ፍቅርን ማስተማር ነው። ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህን ኃጢአት አትግለጥ፡፡
የባልጀራህን ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡

✝️ ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱ ልክ በእሳት ፊት እንደ ወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

✝️ ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹሕ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደ ተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ቃላቶችህ የተመጠኑና ጤናማዎች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅና ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

አምላክ ያነበብንውን ለፍሬ ያርግልን አሜን🙏

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

11 Jan, 01:58


#"ጋብቻ የቤተ ክርስቲያንና የክርስቶስ ምሳሌ ነው ፤ እንዲህ በከበረ ምሥጢር ላይ ዳንኪረኞችን በመጋበዝ ዝሙትን ታስተዋውቁበታላችሁን ? ነገር ግን ከእናንተ መካከል አንዱ እኔን እንዲህ ስትል ደናግል ወይም ያገቡት አይጨፍሩ እያልክ ነው ፤ እንግዲያ እነርሱ በዚህ ሰርግ ላይ ካልጨፈሩ ማን ሊጨፍር ነው ? ብሎ ሊጠይቅ ይችላል ፡፡ ማንም አይጨፍር ነው መልሴ ፡፡በአሕዛብ ዘንድ ይህን በመሰሉ ሥርዐቶቻቸው ዳንኪረኞች ዳንኪራቸውን ያቀርባሉ፡፡ በእኛ ግን ማንኛውም ምሥጢራት ሲከናወኑ በጸጥታ፣ በትሕትናና በጥሩ ሥነምግባር እንዲሁም በመልካም ሥርዐት ነው፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

10 Jan, 17:23


ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው?!
ቅዱስ ጳውሎስ > እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን። 2ቆሮ 3:18

➥ጎርጎርዮስ ሲያብራራው፣
የአምላክ ሰው መኾን በእግዚአብሔር አርአያ የተፈጠርንበት ክብር በትቢያ ተሸፍኖ ከነበረበትና በኀጢአት መልካችን ከተቀየረበት ወጥተን ዐይናችን አጥርቶ መመልከት የጀመረበት ነው፣
ይህም መስተዋትን በማጽዳት በሚገባ ተውቦ እንዲያንጸባርቅ ማድረግ ነው።
መስተዋቱ በእኛ ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር መልክ ሲኾን የሚንጸባረቀው ደግሞ የአምላካችን መለኮታዊ ክብር ነው።
ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

10 Jan, 00:38


✨️️️️✨️️️️✨️️️️💐💐💐✨️️️️✨️️️️✨️️️️💐💐💐✨️️️️✨️️️️✨️️️️

✨️️️️💐💐የፍቅር ሥራ ይህች ናት✨️️️️💐💐
፧፧፧፧፧፧፧፧፧

✨️️️️✨️️️️💐
ባልንጀራውን የሚረዳውን ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ይረዳዋል፡፡ ለወንድሙ የሚነቀፍበትን ስም የሚያወጣውን ፈታሒ በርትዕ እግዚአብሔር እንዲሰደብ ያደርገዋል፡፡ ክፉ ስለ ሠራ ወንድሙን በቤቱ ለብቻው ሆኖ የሚመክረው ሰው ግን በምክሩ ዐዋቂ ይሆናል፡፡ ወንድሙን በዐደባባይ የነቀፈ ግን ኀዘን ያጸናበታል፡፡ ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ብዛት ያስረዳል፤ በባልንጀሮቹ ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል፣ የምቀኝነቱን ጽናት አስረዳ፡፡ 

✨️️️️✨️️️️💐
ወዳጁን ተሠውሮ የሚመክር ሰው ብልህ ባለመድኃኒት ነው:: ያ እንዳዳነው መክሮ አስተምሮ ያድነዋልና፡፡ ወንድሙን በብዙ ሰው ፊት የሚያመሰግነው ሰው እሱ እውነተኛ ጠላቱ ነው፣ በውዳሴ ከንቱ ይጎዳ ብሎ ነውና።

✨️️️️✨️️️️💐
ኀዘን ያለበት የርሕራሄ ምልክቱ የበደሉትን ሁሉ ይቅር ማለት ነው። የጠማማ ምልክቱ ጸብ ክርክር ነው፡፡ ወደ ክብር የሚያደርስ ረብህ ጥቅም ያግኝ ብሎ የሚመክር፣ የሚያስተምር በፍቅር ይመክረዋል፣ ያስተምረዋል፡፡ ቂም በቀል የሚሻ ሰው ፍቅር የለውም፡፡ አንድም እበቀለዋለሁ ብሎ የሚመክር ከፍቅር የተለየ ነው፡፡

✨️️️️✨️️️️💐
ስሙ ይክበርና እግዚአብሔር በፍቅር ይመክራል፣ ያስተምራል፣ እበቀላለሁ ብሎ ያይደል፡፡ እሱስ በምሳሌው የተፈጠረው ሰውን ለማዳን ይገሥጻል፡፡ አንድ ጊዜስ እንኳን ቂም አይዝም፣ መዓትን አያዘጋጅም፡፡ የፍቅር ሥራ ይህች ናት፣ በቅንነት ትገኛለች፡፡ ቂም ለመያዝ እበቀላለሁ አትልም፣ በፍቅር ሰውን መናገር ነው።

✨️️️️✨️️️️💐
ብልህ የሚሆን ቅን ሰው ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ይመስለዋል፡፡ ሰውን ክፉ ስላደረገ እበቀለዋለሁ ብሎ አይገሥጸውም፣ ሊመክረው ወዶ ነው እንጂ ሌሎችንም ለማስፈራት ነው እንጂ። ተግሣጽስ በፍቅር ካልሆነ ተግሣጽ አይባልም፡፡ በጎ ነገር ያደርግልኛል ብሎ በጎ የሚሠራ ኋላ ፈጥኖ ይተዋል፡፡


✨️️️️✨️️️️💐
ምክር ወተግሣጽ ዘማር ይስሐቅ

✨️️️️✨️️️️✨️️️️💐💐💐✨️️️️✨️️️️✨️️️️💐💐💐✨️️️️✨️️️️✨️️️️

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

09 Jan, 18:35


📚📚📚📚📚📚

📚
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል።
                   ኤር. 12፥5

📚
የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል።
                     ዘፍ. 29፥27

📚
በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል።
                 1ኛ ቆሮ 2፥9

📚

(አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ -
መንፈሳዊው_መንገድ መጽሐፍ
አያሌው_ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)

📚📚📚📚📚📚

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

09 Jan, 11:14


ተአምር መስራት

አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበለት "ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ፣ እንዴት ላድርግ?" ቅዱሱ አባት መለሰለት፦
"አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው፤  ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰሃል፤ ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው።  በል ሒድና ተአምር ሥራ!"

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

09 Jan, 03:57


🙏🙏🙏🙏

"ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወነአብየኪ፥ እስመ ወለድኪ ለነ መብልዓ ጽድቅ ዘበአማን፥ ወስቴ ሕይወት ዘበአማን ..."

ትርጉም፦" ማርያም ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን እናፈቅርሽማለን፥ እውነተኛውን የጽድቅ መብል  እግዚአብሔር ወልድን ወልደሽልናልና፥ ይኸውም ልጅሽ እውነተኛ የሕይወት መጠጥ ነውና።"
                ቅዳሴ ማርያም ዘአባ ሕርያቆስ


🌾🌾🌾🌾

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

08 Jan, 18:05


“ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።”
  — ገላትያ 6፥1

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

08 Jan, 11:56


🌼🌺🌼🌺🌼🌺🌼🌺🌼🌺🌼🌺
ሰው ሆይ የሚጎዳህ ሀብትህ አይደለም ድህነትህም አይደለም።ሰውን የሚጎዳው ክፉ ልብ ነው።ክፉ ልብ ደሞ በሀብትም ሀብት በማጣትም የሚመጣ አይደለም።
       ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

          

ሌቦች ባዶ ቤትን ለመበርበር አይመጡም፣ወርቅና ብር ወዳለበት ቤት እንጂ።ዲያቢሎስም ልክ እንደዚህ ነው።ሊፈትናቸው የሚመጣው መንፈሳዊ ሀብታትን ወዳከማቹት ነው።
   
         ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
             💐@weldwahid💐

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

08 Jan, 04:32


ሳትጸልይየትም አትሂድ  ምንም አትስራ
✥✥መዝሙረ ዳዊት ፲፮:፩-፫✥✥
   ✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥

አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና #ጠብቀኝ።

እግዚአብሔርን። አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ፤ ከአንተ_በቀር_በጎነት_የለኝም።

ፈቃድህ_ሁሉ በምድር ባሉት ቅዱሳንና_ክቡራን_ላይ_ነው።

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

07 Jan, 19:00


🎙🎚🎙🎚🎙🎚🎙🎚🎙🎚🎙🎚
''......ደስታ.....''ገላ 5:-22
💿💿💿💿💿💿💿💿💿💿💿



🌹ሳምንታዊ ረቡዕ ጉባኤ በዚህ ሳምንት በቤታችን🌹

ሳምንታዊው የረቡዕ ጉባኤ በዚህ ሳምንት አይኖረንም ከዚህ በፊት በረቡዕ ጉባኤ መምህር ዲ/ን አንተነህ ያስተማሩት ትምህርት ልናስታውሳችሁ ወደድን።


በ15/2/2015 ዓ/ም በ #ረቡዕ_ጉባኤ በወልድ ዋሕድ አዳራሽ የተላለፈ ቃለ እግዚአብሔር


🎙6ሜጋ ባይት (MB) ብቻ

@weldwahid

#share

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

07 Jan, 18:21


"በድንግል ማሕፀን ሳለ በባሕርይ የማይወሰን እርሱ ሕፃን ሆኖ ተወለደ ከንጽሕት ድንግል ማርያም ጡት ወተትን ጠባ።"
      ሃይማኖት አበው 28፥17

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

07 Jan, 13:16


"በፈቃደ አቡሁ ወረደ፣ ኀበ ማርያም ተአንገደ፤ በድንግልናሃ ንጹሕ እግዚአብሔር ተወልደ። በጎለ እንስሳ ተወድየ፣ አምኃ ንግሡ ተወፈየ፤ ወከመ ሕጻናት በከየ፣ እንዘ ይስእል እምአጥባተ እሙ ሲሳየ።

➦በአባቱ ፈቃድ ወረደ፣ በማርያም ዘንድ፣ እንግዳ ሆነ፣ እግዚአብሔር በንጹሕ ድንግልናዋ ተወለደ። በእንስሳት በረት ተጨመረ፣ የንግሡንም እጅ መንሻ ተቀበለ፣ ከእናቱ ጡቶች ምግብን እየለመነ እንደ ሕጻናት አለቀሰ።"
    ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

07 Jan, 05:40


✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️ 👑👑👑✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️ 👑👑👑✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️

እንኳን ለክብር ባለቤት ለአምላካችን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ  ከእመቤታች ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ለተወለደበት የበዓላት ሁሉ ራስ ለሆነች ️️️️ለብርሃነ ልደቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። ✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️

✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️ 👑👑👑✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️ 👑👑👑✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

06 Jan, 20:59


አእላፋት የተሳተፉበት የዝማሬ መርሐ ግብር ታህሳስ 28 2017 ዓ.ም

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

06 Jan, 12:14


+  የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ +

ጌታችን በቤተልሔም ለመወለዱ ምክንያት የሆነው ለሕዝብ ቆጠራ ሲሉ ወደ ይሁዳ አውራጃ በመምጣታቸው ነበር:: ለቆጠራ መጥተው ከመቆጠራቸው በፊት ጌታችን ተወለደ:: ወደ ናዝሬት ከመመለሳቸው በፊት ግን ሁለት ሆነው ሊቆጠሩ የመጡበትን የሕዝብ ቆጠራ ሦስት ሆነው አድርገው ተቆጥረዋል::

እባካችሁ ያንን የቆጠራ መዝገብ ያለበትን ቦታ የምታውቁ  የሮማውያን ታሪክ መርማሪዎች ካላችሁ ብትነግሩኝ ደስ ይለኛል::  ደግሞ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ምን ያደርግልሃል? ካላችሁ መዝገቡ ይገኝ እንጂ እኔ ግን የምፈልገው አንድ ስም አለ:: ከብዙ የይሁዳ ተወላጆች ስም መካከል ሰሎሜ ዮሴፍ ማርያም ከሚሉ ስሞች አጠገብ አንድ  ዓለም የዳነበት ስም በሕዝብ ቆጠራው መዝገብ ሥር ተጽፎአል::

ጉልበት ሁሉ የሚሰግድለት ስም : ከሰማይ በታች እንድንበት ዘንድ የተሠጠን ስም : ከስም በላይ የሆነ ስም : ቅዱስ ገብርኤል በክብር ይዞት የወረደና ለድንግሊቱ የነገራት ስም : አጋንንት ሲሰሙት የሚንቀጠቀጡለት ስም : ሙታንን የሚያስነሣ ድውያንን የሚፈውስ ስም በዚያ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ላይ እንደዋዛ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል::

       ኢየሱስ ✍🏽

አንተ የሕዝብ ቆጠራ ሠራተኛ ሆይ ይህንን ስም እዚያ መዝገብ ላይ ስትጽፈው ብዕርህ አልተሰበረም ወይ? ቀለሙስ አልሸሸም ወይ? እጆችህስ አልተንቀጠቀጡም ወይ?

ጌታችን በዚያ መዝገብ ላይ ተጻፈ:: በዚያ መዝገብ ከጌታ ጋር የተጻፉት ንጽሕት ድንግልና ጻድቁ ዮሴፍ ብቻ አልነበሩም:: በዚያች ግዛት ያሉ ሰዎች ሁሉ አብረው ተጽፈዋል:: ጥሩ ሰዎች ክፉ ሰዎች ወንጀለኞች ነፍሰ ገዳዮች ሰካራሞች አመንዝሮች በዚያ መዝገብ ላይ ስማቸው ተጽፎአል::

ክርስቶስም ገና ከመወለዱ ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: በሕይወት ዘመኑ የኃጢአተኞች ወዳጅ የሚል ቅጽል ስም የወጣለት ጌታ በዕለተ አርብም በግራና ቀኙ ከወንበዴዎች ጋር አብሮ የተሰቀለው ጌታ አሁንም በልደቱ ጊዜ "ከዓመፀኞች ጋር ተቆጠረ" (ኢሳ 53:12)

እኛን ከቅዱሳን ጋር ሊደምረን እሱ ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: እኛን "ስማችሁ በሰማይ ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ" ለማለት እርሱ በምድር መዝገብ ላይ ተጻፈ::

ወዳጄ ክርስቶስ ስለ አንተ ሲል ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: አንተ ስለ እርሱ ከንጹሐን ጋር ተቆጠርለት:: በተወለደበት ጊዜ ከሰካራሞችና ዘራፊዎች ስም ዝርዝር ጋር ለአንተ ሲል አብሮ ተቆጠረ:: እስቲ አንተ ልደቱን አስበህ ከሚሰክሩት ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ውጣ:: ከዘራፊዎችም መካከል ተለይ:: ክርስቶስ ወደ አንድ ነገር የሚገባው የሚገቡትን ሊያወጣ ነው:: ወደ ሞት የገባው ሙታንን ሊያወጣ ነው:: ወደ ሲኦል የወረደው ነፍሳትን ከሲኦል ሊያወጣ ነው:: ወደ ሮማውያን የሕዝብ ቆጠራ የኃጢአተኞች መዝገብ ስሙ የገባውም የሁላችንን በደል ተሸክሞ እኛን ከዚያ መዝገብ ሊያስወጣን ነው::

"ስማችሁ ግን በሰማያት ሰለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ"
ሉቃ 10:20

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 28 2013 ዓ ም

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

06 Jan, 04:32


በገነት ያሉ ሦስት አስደናቂ ነገሮች

አንድ አባት ወደ ገነት ከገባ በሁዋላ ለሌላ አባት በሕልም እንዲህ ሲል ነገረው

ወደ ገነት በገባሁ ጊዜ ሦስት ነገሮች አስደነቁኝ
የመጀመሪያው ገነት ውስጥ ይገኛሉ ብዬ ፈጽሞ የማልጠብቃቸውን በእኔ ዓይን ኃጢአተኞች የሆኑ ሰዎችን በገነት ውስጥ ማግኘቴ ነው::
ሁለተኛው በገነት እንደሚኖሩ በእርግጠኝነት የምገምታቸውን ጻድቃን መስለው የታዩኝን ሰዎች በገነት ውስጥ አለማግኘቴ ነው::

ከሁሉም በላይ ያስደነቀኝ ግን እንደ እኔ ዓይነቱን እጅግ ኃጢአተኛ ሰው በገነት ውስጥ ማግኘቴ ነው" አለ::

"ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፡— እውነት እላችኋለሁ፥ ቀራጮችና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል" ማቴ 21:31

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

05 Jan, 19:10


ማገልገል ማለት ምንድን ነው?

አንድ አባት ሁሌ በቅዳሴ በኪዳን ሁሌ ቤተ መቅደስ ያገለግሉ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን በምሥጋና እንዳሉ በተመስጦ ቁጭ ብለው ያለቅሱ ጀመረ እንባቸው መሬት ጠብ ጠብ ጠብ አለም
ምዕመናን ጨነቃቸው ምን ሁነው ይሆን ብለው አዘኑ። መምህሩ ባፋቸው የሚሉት ነገር አላቸው። ጠጋ ብለው አደመጧቸው
ጌታዬ ሆይ እባክህ ለቅዱስ ሥጋህና ለክብር ደምህ አብቃኝ ነበር የሚሉት። ምዕመናኑ ተገርመው አባ ምነው ምን እያሉ ነው ብለው አፋጠው ያዟቸው። እርሳቸውም አንተን ለማገልገል ለሥጋና ለደምህ አብቃኝ እያልኩ ነው። አሏቸው
ምዕመናኖቹም አባታችን ይህን ያክል ዘመን እያገለገሉ እንኳን ለርስዎ እኛን እያቆረቡ እንደት እንድህ ይላሉ አሏቸው። እርሳቸውም የመስቀሉ ፍቅር ገብቶኝ ለሰው ሳይሆን ለራሴ ብየ የማገለገግልበት የስጋና ደሙም ፍቅሩ ገብቶኝ የምቀበልበት ቀን ነው የምለምነው ብለው መለሡ።

ወዳጆቼ ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ክርስትና በየሰፈሩ አለ።
ለሰው የምንሠራው ወይም ግዴታ ተጥሎብን የምናገለግል ብዙ ነን። አገልግሎት ማለት የፈቃደኝነት ባርነት ነው እንዲሉ በእንዲህ መልኩ መጓዝ ሲገባን ሰው ዓይተን ጀምረን በሰው አገልግሎት ያቆምን ብዙ ነን። አንዳንዶቻችን ቤተ ክርስቲያን መሄድ ፣ መፆም ፣ መስገድ ፣ መጸለይ ፣ መቀደስ ፣ መዘመር ፣ መስበክ ፣ ነጠላ መልበስ ፣ ግደታ አልያም ሕግ ነው ብለን የምንተገብር ብዙ ነን። መቼ ነው ግን ፍቅሩ ገብቶን ስለፍቅሩ እነዚህን የምንተገብራቸው። ሰው ያየናል ይደርስብናል ብለን ኃጢአትን ከመስራት የምንከለከል ብዘ ነን። አምላክን ፈረተን ሲዖል እንገባለን ብለን ክፉ ነገርን እንተወዋለን። ግን ስለፍቅሩ ብለን ፍቅሩ ገብቶን ኃጢአት የሆነውን ሁሉ የምንተወው መቼ ይሆን??

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

05 Jan, 11:55


በኤፍራታ መንደር
ልዩ የኪነ ጥበብ
የዝማሬ ምሽት በከፊል በፎቶ
📆ታህሳስ 25

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

02 Jan, 17:36


🎲 Quiz 'የምሽቱ ጥያቄ ታህሣሥ 24/2017 ዓ.ም'
"Start this quiz" የሚለውን ይጫኑ ፈተናውን ይጀምራል ። ጥያቄዎችን ሲመልሱ የቴሌግራም ቦት ሲስተም ይመዘግባል።
🖊 5 questions · 1 min

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

02 Jan, 17:21


«ወንድምህን አትናቀው»

ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው። እህትህን አትናቃት። ምንም ይሁን ምን ሰው አትናቅ። ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብከዉ እንደሆን አስተውል።

"እንዴት?"  ያልከኝ እንደሆንም ይህ የምትንቀው ወንድምህ የከደርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል። የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እሱን ናቅኸው ማለት ክርቶስን ናቅኸው ማለት ነው።

ወንድምህን የምትንቅ ከሆነም በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ እራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞትንና ከርቤን ቀላቅለው ከሰጡት፣ በፊቱ ላይም ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም። ስለዘህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

02 Jan, 11:43




የቱ ይሻላል?🤔

👉የሌሎችን ስህተት መዳኘቱ ቀላል ሲሆን፣ የራሳችንን ድካም ማስተዋሉ ደግሞ ከባድ ነው፡፡

👉ቀላሉ ሳያገናዝቡ ማውራት ሲሆን፣ ከባዱ ደግሞ ምላስን መግታት ነው፡፡

👉የሚወደንን ሰው መጉዳት ቀላል ሲሆን፣ የሚከብደው ደግሞ ያንን ቁስል ማዳኑ ነው፡፡

👉ሌሎችን ይቅር ማለት ቀላል ሲሆን፣ ይቅርታን መጠየቅ ግን ከባድ ነገር ነው፡፡

👉ሕግጋትን ማውጣት ቀላል ሲሆን፣ እነርሱን መከተሉ ደግሞ ከባድ ነገር ነው፡፡

👉ቀላሉ በእያንዳንዱ ምሽት ማለሙ ሲሆን፣ ከባዱ ደግሞ ለስኬታማነቱ መዋጋት ነው፡፡

👉ሙሉ ጨረቃን ማድነቁ ቀላል ሲሆን፣ ሌላኛውን ጎን ማየቱ ግን ከባድ ነገር ነው፡፡

👉ቀላል የሆነው ለአንድ ሰው የሆነ ቃል ኪዳን መግባቱ ሲሆን፣ የሚከብደው ደግሞ ያንን ቃል መፈጸሙ ላይ ነው፡፡

👉"እወዳችኋለሁ" ማለት ቀላል ሲሆን፣ ከባዱ ደግሞ ያንን በሕይወት ማሳየቱ ነው፡፡

👉ሌሎችን መተቸት ቀላል ሲሆን፣ ራስን ማሻሻል ደግሞ ከባድ ነው፡፡

👉ስህተት መሥራት ቀላል ሲሆን፣ ከዚያ መማሩ ደግሞ ብርታትን ይጠይቃል፡፡

👉ስላጣነው ፍቅር ማንባቱ ቀላል ሲሆን፣ ላለማጣት መንከባከቡ ግን ይከብደናል፡፡

👉መቀበል እጅግ ቀላል ሲሆን፣ መስጠት ደግሞ ልባዊ ርኅራኄን ይጠይቃል፡፡

👉ስለ መሻሻል ማሰብ ቀላል ሲሆን፣ ከባዱ ግን ወደ ተግባር መቀየሩ ላይ ነው፡፡

👉ወዳጅነትን በቃላት መጠበቁ ቀላል ሲሆን፣ ትርጉማቸውን መጠበቁ ግን ከባድ ነገር ነው፡፡

👉ልጅ እያለን ከሰማናቸው ነገሮች መካከል አንዱ በአካባቢያችን ውሻ ሲያላዝን (የተለየ ድምጽ ሲያሰማ) 'ሰው ሊሞት ነው' የሚለው አባባል ነው፤ እጅግ በሚገርም ሁኔታ ግን "እኔ ልሞት ነው" የሚል ያለመኖሩ ጉዳይ ነው፤ በተለይ አልጋ የያዙ ካሉ የሰዉ ሁሉ ትኩረት መጠቋቆሚያ የመኾናቸው ጉዳይ አጠያያቂ አይሆንም፡፡

ግን የቱ ይሻላል?🤔
ሰውን ማስተካከል ወይስ ራስን ማስተካከል፤ እነርሱ ልክ አይደሉም ማለት ወይስ እኔ ልክ አይደለሁም ማለት፤ የሌሎችን ስህተት መዳኘት ወይስ የራስን ድካም መታገል፤  የቱ ይሻላል?

ተወዳጆች ሆይ ለሚከብደውና ለሚበልጠው እንትጋ!🙏

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

02 Jan, 02:12


🍁🍀🍁🍀🍁🍀🍁🍀🍁🍀🍁🍀🍁🍀🍁🍁

           ልደቱ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት

እንኳን ለጻድቁ  አቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችኹ🙏

''ሰላም ለልደትከ ተክለሃይማኖት ሐዋርያ፤
ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ፤
ሞገሰ ልደትከ አባ በአዕይንቲሃ ርእያ፤
ነፍስየ ትባርኮሙ ወታስተበጽኦሙ ነያ፤
ለጸጋ ዘአብ ወለክግዚእ ኃረያ።''

ትርጉም:-

''ለኢትዮጵያ እና ለግብጽ ሰዎች ሐዋርያ የኾንክ ተክለ ሃይማኖት ለልደትኽ ሰላምታ ይገባል፤ የልደትኽን ክብር በዐይኖቿ ዐይታ ሰውነቴ አባትኽ ጸጋ ዘአብንና እናትኽ እግዚእ ኀረያን እነሆ ታመሰግናቸዋለች ከፍ ከፍም ታደርገዋለች''

አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን!

🍁🍀🍁🍀🍁🍀🍁🍀🍁🍀🍁🍀🍁🍀🍁🍀

"የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯

    

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

01 Jan, 18:03


ሰላም የተወደዳችሁ የወልድ ዋህድ ሚዲያ ተከታታዮች ዛሬ የቅዱስ ዳዊት የዕረፍቱ በዓል የሚከበርበት ቀን ነው ከመዝሙረ ዳዊት የምትወዱትን ክፍል ከታች ባለው የአስተያየት መስጫ ላይ ይፅፉልን።
ከቅዱስ ዳዊት ረድኤት በረከት ያሳትፈን🙏

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

01 Jan, 17:54


''እውነተኛ ጿሚ ራሱን ከክፉ ምግባራት የከለከለ፤ ከንቱ የሆኑ ንግግሮችን ከመናገር የተቆጠበ፣ ሐሰትን የማይናገር፣ ሐሜተኛ ያልሆነ፣ በማንም ላይ የማይፈርድ፣ሽንገላን የማይወድና እኒህንም ከመሰሉ ነገሮች ራሱን የተጠበቀ ፣የማይቆጣ፣ የማይበሳጭ ፣ተንኮለኛ ያልሆነ ፣ ቂመኛ ያልሆነና፣ እነዚህን ከመሳሰሉ ክፋቶች ሁሉ የራቀ ሰው ነው፡፡

ሕሊናህ ኃጢአትን ከማሰብ ይጡም፡ አእምሮህም ኃጢአትን ከማስታወስ ይከልከል፡፡ ክፉን ከመመኘት ሁሉ ጡም፡፡ ዐይኖችህ ከንቱ የሆኑ ነገሮችን ከመመልከት፣ ጆሮህም ከንቱ ከሆኑ ዘፈኖችና ከሐሜተኞች ሹክሹክታዎች ጠብቅ፡፡ አንደበትህ ከሐሜት፣ በሌላው ላይ ከመፍረድ ፣ ከስድብ፣ ከውሸት ፣ከማታለል፣ከሽንገላ ንግግሮች እንዲሁም ከማይጠቅሙና አጸያፊ ከሆኑ ቃላት ይጡሙ፡፡ እጆችህም ሰውን ከመግደልና የሌላውን ንብረት ከመዝረፍ ይጡሙ፡፡ እግሮችህም ኃጢአትን ለመፈጸም ከመሄድ ይጡሙ፡፡ ከክፉ ተመለስ መልካምንም ፈጽም፡፡''

ቅዱስ_ኤፍሬም

እኛስ እውነተኛ ጿሚ ልንባል ይገባን ይሆን?

መልካም ምሽት

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

01 Jan, 12:02


"እግዚአብሔርን እንደ ባልንጀራችሁ ቁጠሩት"
.
(ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ)

።።።።።።።።።።።።።።።።
እግዚአብሔርን ለመውደድ ከፈለጋችሁ እንደ ባልንጀራችሁ ኣድርጋችሁ ቁጠሩት።

ይልቁንም እርሱ የመጀመሪያ ባልንጀራችሁ ይሁን፤

ወደ ማንም ከመጣደፋችሁ በፊትም ወደ እርሱ ተጣደፉ።

ምስጢራችሁን ለእርሱ ግለጡለት፤
ሁሉንም ነገር ንገሩት፣
ከእርሱ ጋር መሆናችሁ የሚሰማችሁ የመደላደል ስሜት ጥልቀትም ይታወቃችሁ።

ኣሳቦቻችሁንም በሙሉ ንገሩት፣
የውስጣችሁንም ውስጥ ግለጡለት፤
ይህንንም በግልፅነት፣በምሉ እውነት፣በመተማመን እና ክፍት በሆነ ልብ ኣሳዩት።
ከእርሱ ጋር በመነጋገራችሁም ስልቹ ኣትሁኑ።

ይልቁንም""ጌታዬ ሆይ፦የምነግርህ ብዙ ነገር ኣለኝ""በሉት።

ለእኔ ያለህን ፍቅር ኣምናለሁ፣ኣንተ ለእኔ መልካም የሆነውን ነገር እንደምታደርግልኝም እርግጠኛ ነኝ።ኣንተ ይህን ለማድረግ በቂ ኃይል ኣለህ።ኣንተ ይህ ኃይል ካለህ እኔ ለምወዳቸው ሰዎች የምነግራቸውን ነገር ለኣንተ የማልነግርህ ለምንድር ነው"?።
.
.
.
"እግዚአብሔር በማንኛውም ስራችሁ ውስጥ ከእናንተ ጋር የስራ ባልደረባችሁ እንዲሆን ሞክሩ"።

እርሱ ከምናምናቸው ሰዎች በላይ ለቃሉ ታማኝና ሁሉን የሚችል ኤልሻዳይ ስለሆነ።

አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

01 Jan, 05:26


       
      
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን         
   
🔔 የረቡዕ ጉባኤ 🔔         
   
      
ዛሬ ረቡዕ ታህሳስ 23 ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ በምዕራፈ ጻድቃን ሰንበቴ አዳራሽ         
         
ሁላችኹም ከዚህ መልካም መዓድ ከቀኑ ከ12:00 ጀምሮ እንድትቋደሱ ተጋብዛችኋል!        
         

                                 
🌿🌿🌿🌿🌿

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

01 Jan, 04:10


እንኳን አደረሳችሁ፥ አደረሰን!

❀ታኅሣሥ ➋➌ በዓለ ዕረፍቱ ለቅዱስ ዳዊት (ነቢየ ጽድቅ፥ ወልበ አምላክ)❀

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

31 Dec, 16:40


ክፋትን_ከአንተ_አርቃት

"ሰይጣን ክርስቶስ በልብህ ውስጥ ያለ መሆን አለመሆኑን ያውቃል፡፡ ይኸውም ስትቆጣ ወይም ስትጮህ ወይም የማይረቡ ከንቱ ነገሮችን ስትናገር ሲያይህ ጠላት በአንተ ዘንድ እግዚአብሔር እንደሌለ ያውቃል ያን ጊዜ በውስጥህም በውጭህም ያለውን ሳይቀር ይገዛል ፤ መዝጊያ እንደሌለው ቤት እንደ ክፉ ሌባ ይገባና ውስጥህን ይበረብረዋል፡፡"

ቅዱስ_ባስልዮስ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

31 Dec, 04:38


💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

ታኅሣሥ ፳፪ ቅዱስ ገብርኤል ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ምሥጢር ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተላከ የደስታ መገኛ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው አንቺም ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ብሎ አበሠራት፡፡

💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

30 Dec, 16:31


🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁


ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህችን ዕለት "ኖላዊ ሔር" ብላ ታከብራለች:: ይሕንንም ለሳምንት ያህል ታዘክራለች:: መሠረታዊ መነሻዋም (ዮሐ. 10:1) ነው:: "ኖላዊ" ማለት በቁሙ "እረኛ" ማለት ሲሆን "ሔር" ደግሞ "ቸር-ርሕሩሕ-አዛኝ" እንደ ማለት ነው::

ገጥመን ብንተረጉመው ደግሞ "ቸር እረኛ" የሚል ትርጉምን ይሰጠናል:: ከአባታችን አዳም ስህተት በሁዋላ ተፈጥረው ከነበሩ ችግሮች አንዱ ቸር እረኛ ማጣት ነው:: እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ: ቸር እረኛ ሆኖ በገነት አሰማርቶት ነበር::

ኤዶም ገነት የለመለመች: ፈሳሾች የሞሉባት መልካም መስክ ናትና:: አባታችን ቅዱስ አዳም ደግሞ እንደ አቅሙ የጸጋ እረኝነት ተሰጥቶት ነበር:: ድቀት ካገኘው በሁዋላ ግን ከነፍስ እረኛው ጋር ተጣልቶ ከመልካሟ መስክ ገነት ወጣ::

እርሷንና የነፍሱን እረኛ ሲሻም አለቀሰ:: ተስፋ ድኅነት ሲሰጠውም ለልጆቹ ነገራቸው:: ከዚያም በመንጋው ላይ በአዳም ሴት ተተካ:: ከሴት ኄኖስ: ከኄኖስ: ቃይናን . . . እያለ ከኖኅ ደረሰ::

ከኖኅም በሴም ከአብርሃም: ከአብርሃምም በይስሐቅና በያዕቆብ ወርዶ ከሙሴ ደረሰ:: ከሙሴም በኢያሱ አልፎ ከነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ደረሰ:: እነዚህ ሁሉ እረኞች ምንም እንኩዋ ለእግዚአብሔር ሕዝብ በትጋት ቢሠሩም ሕዝቡን ከሲዖል ማዳን አልቻሉም::

ከሲዖል የሚያድን የነፍስ እረኛ ነውና ያን ጊዜ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት የራሱን: የአባቶቹንና የልጆቹን ጩኸት ባንድ አድርጐ ጮኸላቸው:: "ኖላዊሆሙ ለእሥራኤል አጽምዕ - የእሥራኤል እረኛ ሆይ ስማን!" አለ:: (መዝ. 79:1)

ጩኸቱም ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰ:: ይህንን የሰማ ጌታም በጊዜው ከድንግል ማርያም ተወለደ:: በየጥቂቱ አድጐ ቸር እረኝነቱን ገለጠ:: መድኃኒታችን እንዳስተማረን እርሱ ቸር እረኛ ነው::

ከእርሱ በፊት የተነሱት ቴዎዳስ ዘግብጽና ይሁዳ ዘገሊላ (ሐዋ. 5:36, ዮሐ. 10:8) ሐሰተኛ እረኞች ነበሩ:: እርሱ ግን እውነተኛው የበጐች በር ነውና (ዮሐ. 10:7) በእርሱ የሚገቡ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን ያገኛሉ::

እርሱ እውነተኛ እረኛ ነውና (ዮሐ. 10:11) ለመንጋው ራሱን አሳልፎ ይሰጣል:: በእሥራኤል ባሕል እረኞች ከፊት: መንጋው (በጐቹ) ከሁዋላ ሆነው ይሔዳሉና ገዳይ ቢመጣ መጀመሪያ የሚገድለው እረኛውን ነው::

መድኃኒታችን ክርስቶስ በሞቱ ሕይወትን: በመራቆቱ የጸጋ ልብስን: በውርደቱ ክብርን: በድካሙ ኃይልን ይሰጠን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ:: የማይሞት ንጉሥ ስለ መንጋው ሞተ:: ሰማይን ከነግሡ ምድርንም ከነልብሱ የፈጠረ ጌታ (ዘፍ. 1:1, ዮሐ. 1:2) ስለ በጐቹ ይህንን ሁሉ ታግሦ ከሲዖል አዳነን::

በሚያርግ ጊዜም በእርሱ ፈንታ ባለ ሙሉ ስልጣን እረኞችን: ሐዋርያትን (ዮሐ. 21:15) ሊቃነ ዻዻሳትን (ሐዋ. 20:28) ካህናትን (ማቴ. 18:18) ሾመልን:: እነርሱን እረኞች አሰኝቶ እርሱ "ሊቀ ኖሎት-የእረኞች አለቃ" ተባለ:: እነርሱም እስከ ዓለም ፍጻም የክርስቶስን መንጋ ሊጠብቁ ስልጣኑም: ኃላፊነቱም አለባቸው:: (ማቴ. 28:19)

🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

30 Dec, 12:03


በኤፍራታ መንደር
ልዩ የኪነ ጥበብ
የዝማሬ ምሽት
📆ታህሳስ 25
🕰ከ10:30 ጀምሮ
📍በወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤት

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

30 Dec, 12:01


🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿

"ወንድሞቻችን ኾይ ☝️እምነት አለኝ ምግባር ግን የለኝም የሚል ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል?

በውኑ እምነቱ ልታድነው ትችላለችን?

ከወንድሞቻችን÷ ወይም ከእኅቶቻችን÷ የታረዙ ወይም የዕለት ምግብ ያጡ ቢኖሩ÷ ከእናንተም አንዱ÷ “በሰላም ኺዱ÷ እሳት ሙቁ÷ ትጠግባላችኹም” ቢላቸው÷ ለችግራቸውም የሚሹትን ባይሰጣቸው ምን ይጠቅማቸዋል?

እንዲኹም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው፡፡

                      ያዕ. ፪÷፲፬-ፍጻ

🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

30 Dec, 04:40


"ልቦናዬ በጎ ነገርን አወጣ ።ልቦናዬ በጎ ነገርን አወጣ ። ልቦናዬ በጎ ነገርን አወጣ ። እኔም የማርያምን ቅዳሴ እናገራለሁ ። በማብዛት አይደለም በማሳነስ ነው እንጂ ። እኔም የድንግልን ውዳሴ እናገራለሁ ። መዘንጋት ባለበት ቃል በማስረዘም አይደለም ። በማሳጠር ነው እንጂ እኔም የድንግልን ገናንነትዋን እናገራለሁ ።"
       ቅዳሴ ማርያም

           🌿@weldwahid🌿

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

29 Dec, 07:26


ዝግጅታችንን ጨርሰናል
#ገናን በሜቄዶንያ
በሰዓታችን እንገናኝ🙏

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

29 Dec, 06:40


"እግዚአብሔር አምላክ እንዳዘዘኽ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አክብረው፡፡" ዘዳ ፭:፲፪

መልካም ዕለተ ሰንበት

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

07 Dec, 18:04


"ክርስቶስ መሥዋዕቱን ስለ ሁላችንም ኾኖ አቀረበ፡፡ ከመጀመሪያው ጥፋት ተጠያቂነት ሁላችንም ነጻ ያደርገን ዘንድ መቅደስ ሰውነቱን ስለ ሁላችን ሲል ለሞት አሳልፎ ሰጠ፡፡"

    ቅዱስ አትናቴዎስ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

07 Dec, 03:31


🌿🌿🌿🌿

🌿ተግሣፅ ዘቅዱስ ኤፍሬም🌿

ሕይወትህን በአግባቡ መምራት ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ ትሕትናን ተለማመድ፤ ያለ ትሕትና ተገቢውን ሕይወት መምራት አይቻልም፡፡ ሥራህን ሁሉ በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጀምር፡፡ ያን ጊዜ ፍሬዎችህ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይደርሳሉ።

ሰው ከትሕትና ከራቀ ከትክክለኛው መንገድ ርቋል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የተወ ሰውን ርኵስ መንፈስ እንደ ሳውል ያስጨንቀዋል። የጠላት ወጥመድ በማር የተቀባ ነው፡፡ በማር ጣዕም የሚማረክ ሰው ሐዘንን ሁሉ በያዘ ወጥመድ ይያዛል። ትሕትናን ውደዱ፤ ያን ጊዜ ከሰይጣን ወጥመድ ውስጥ አትወድቁም፡፡ በትሕትና ክንፍ በበረራችሁ ቁጥር ሁል ጊዜ ከጠላት ወጥመድ በላይ ትሆናላችሁ።

🌿
ግልፍተኝነት እንደ በሰበሰ ረጅም ዛፍ ነው፤ ቅርጫፎቹ ሁሉ በቀላሉ የሚሰበሩ ናቸው᎓᎓ አንድ ሰው በወጣባቸው ጊዜ ከወጣበት ከፍታ ወዲያውኑ ይወድቃል፡፡ በመልካም ሐሳብ ልቡናው የበራ ሰው ግን ምስጉን ነው፤ ክብሩም ታላቅና ዘላለማዊ ነው።

እንግዲህ ራሳችንን ለመቆጣጠር እንጣር ያን ጊዜ ኃጢአታችንን እንረዳለን፡፡ ያን ጊዜም ሁል ጊዜ ራሳችንን ዝቅ እናደርጋለን፤ እንደ እባብ በእብሪት መወጠርን እና ራሳችንን ከፍ ከፍ ከማድረግ እንቆጠባለን፡፡ እንግዲህ ራሳችንን ዝቅ ዝቅ ማድረግን እንውደድ፤ በንጹሕ ልቡና ሆነን ምናልባት የተሰጠንን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኃጢአት ከማቆሸሽ እንታደግ ይሆናል።

🌿
መልካም ጸሎት በሳግ እና በዕንባ የታጀበ ነው፤ በተለይ ደግሞ በምሥጢር የሚፈስ ዕንባ፣ በልቡናው ከፍታ ሆኖ የሚጸልይ ጌታውን በፊቱ ያያል። እኛ የምንኖረውና የምንሔደው በእርሱ ፈቃድ ነውና። ልቡናችሁ ከጠነከረ በጌታችን ፊት አልቅሱ እርሱ የዕውቀትን ብርሃን ይገልጥላችኋል፤ ወደ እርሱ የሚወስዳችሁ አዲስ ልብንም ይሰጣችኋል።

ንስሓ የገቡና ምሕረት የለመኑ ሰዎች ዕዳቸው ተሰረዘላቸው፤ ነገር ግን ለሠራኸው በደል ምሕረት ስትለምን ወንጀልን እና በደልን፤ በወንድምህም ላይ ቂም መያዝን መተው ይገባሃል። ፍቅር ሳይኖርህ ወደ እግዚአብሔር የምታደርገው ልመና ከተዘጋው በር ውጭ ይቀራል፡፡ የጸሎትን በር የሚከፍት ፍቅር ብቻ ነው፡፡

ወንድምህን ብታስቀይም እግዚአብሐርን ታሳዝናለህ፤ ካንተ ጋር ካለው ከወንድምህ ጋር ሰላምን ከፈጠርህ ግን በሰማይ ካለው ከእግዚአብሔር ጋር ትታረቃለህ፡፡ ወንድምህን በፍቅር ብትቀበለው፣ በደሉንም ይቅር ካልከው እግዚአብሔርን ተቀበልክ፡፡

🌿
ስለዚህ በተናደዱ ሰዎች በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ታረቅ፤ እንግዲህ የተበሳጩትን በማስደሰት እግዚአብሔርን አስደስተው፣ በታሰሩት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን ጎብኘው፣ በተራቡት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አብላው፤ በታረዙ ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አልብሰው፣ መንገደኛን በመቀበል እግዚአብሔርን በአልጋህ ላይ አስተኛው፤ እግሮቹንም እጠበው፣ በማዕድህም አስቀምጠው፣ እንጀራህንም ከእርሱ ጋር ተካፈል፤ ጽዋህንም ስጠው᎓᎓ እርሱ ታላቅ ፍቅሩን አሳይቶሃልና፤ እርሱ ስለ አንተ ብሎ ትበላው ዘንድ ሥጋውን ቆርሶልሃል፣ ትጠጣው ዘንድም ደሙን አፍስሷል።

📚ድርሳነ ቅዱስ ኤፍሬም ፤ ገጽ 334 - 336
📝በዲ/ን መዝገቡ ከፍያለው የተተረጎመ

🌿🌿🌿🌿

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

06 Dec, 19:05


🏆🏆🏆🥇🥈🥉🏆🏆🏆
ጥያቄ ከነ ምላሹ  |ሕዳር 26  /2017 ዓ.ም

1.ወላዲነት፣ተወላዲነት እና ሠራፂነት ምን በመባል ይታወቃል
ሀ.ግብር አምላካዊ
ለ.ፈቃድ አምላካዊ
ሐ.ኩነት አምላካዊ
መ.ልዮ አንድነት


2.አዳም ከገነት የተባረረበት (የወደቀበት)ምክንያት
ሀ.የሰይጣን ምክር በመስማቱ
ለ.ሕገ እግዚአብሔርን በመጣሱ
ሐ.አምላክ ለመሆን በመፈለጉ
መ.ሁሉም


3ከብሉይ ኪዳን ቁርባን ይመደባል
ሀ.የአብርሃም መስዋዕት
ለ.የመልከጼድቅ መስዋዕት
ሐ.የእሥራኤል በግ/ፋሲካ/ሁሉም
መ.ሁሉም


4ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ ስለ ጌታችን ሞትና ትንሳኤ ምሳሌ ነው
ሀ.ዮናስ ሥስት ቀን እና ሥስት ለሊት በዓሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ማደሩ
ለ.በዮርዳኖስ ባህር ውስጥ መጠመቁና ከባህር መውጣቱ
ሐ. ሀ እና ለ
መ .መልስ  የለም


የሰው ልጆች ቤተክርስቲያንና የቤተክርስቲያን አባል(ልጅ)ለመባል የሚያስፈልጋቸው ምንድን ነው?
ሀንስሐ መግባት
ለ.በተክሊል ማግባት
ሐመጠመቅ
መ.ሁሉም


👏👏👏 መልሶቻቸውን የላኩልን ተሳታፊዎች እናመሰግናለን🙏🙏🙏

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

06 Dec, 18:44


ተጀመረ

የተማሪዎች ጉባኤ የመክፈቻ መርሐ ግብር በድምቀት ተካሔደ::

ኀዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ : ወልድ ዋህድ ሚዲያ

በመካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤተክርስቲያን ወልድ ዋሕድ ሰንበት ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀው በአጥቢያች የሚገኙ ከ9ኛ-12ኛ ላሉ የደጃዝማች ወንድይራድ ፣ የሚኒሊየም እና የርግብ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ሌሎች ትምህርት ቤቶች  የሚማሩ ኦርቶዶክሳዊ ወጣቶች የተዘጋጀው መርሐ ግብር ተሳታፊ ሆነዋል ።


ጉባኤው በመርሐ ግብሩ መሪ በዲያቆን ሰለሞን ኢያሱ   እየተመራ በጸሎት ተጀምሯል። የጉባኤውን የመጀመሪያ ክፍል የነበረው የጸሎት መርሐ ግብር ነበር። በዚህም መሠረት በሰንበት ትምህርት ቤታች  ዲያቆናት በፀሎት ተከፍቷል ። በመቀጠልም በዕለቱ መምህር በመጋቢ ኃይማኖት ግሩም ከበደ  ታዳሚን በሚማርክ አቀራረብ  በወጣትነት እድሜ ስለሚገጥሙን ፈተናዎች እና  መሰናክል እንዴት መላፍ እንደሚገባ አስተምረዋል።


ለመሆኑ በዚህ መርሐ ግብር እንዳልሳተፍ የሚከለክለኝ ምንድር ነው?

#ዘወትር አርብ
#9:30-11:00
#በወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤት


https://t.me/hanastudent

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

06 Dec, 04:43


ዛሬ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

06 Dec, 04:28


🔔🔔🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🔔🔔
  መድኀኔዓለም ክርስቶስ  ሆይ
ክቡዱንና ግዙፉን ዕፀ መስቀል በመሸከም ምንኛ ድካምንና መከራን ልትታገስ ቻልክ። ለዚህ ረቂቅ ትህትናህ አንክሮ ይገባል።

    
መልክዐ መድኃኔዓለም

🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔

ሳምንታዊው የአርብ ጸሎት መርሀ ግብር

👉መሐረነ አብ
👉ስንክሳር

አርብ ህዳር 27 2017*ዓ.ም
ከ( 12 ፡ 30 ) ጀምሮ

በወልድ ዋህድ ሰንበት ት / ቤት አዳራሽ


"ኑ እና እግዚአብሔርን እያነጋገርን ዲያብሎስን ድል እንንሳው።"

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

05 Dec, 17:39


🎲 Quiz 'ጥያቄ   |ሕዳር 26  /2017 ዓ.ም'
"Start this quiz" የሚለውን ይጫኑ ፈተናውን ይጀምራል ። ጥያቄዎችን ሲመልሱ የቴሌግራም ቦት ሲስተም ይመዘግባል።
🖊 5 questions · 45 sec

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

05 Dec, 12:13


አባ ኢየሱስ ሞዐ

📖እግዚአብሔር በ13ኛው መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው::

📖እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው አገራችን በወንጌል ትምህርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ  ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ::📖
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
📖አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር: የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል::📖

📖ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምህርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን (ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው) ይህቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ::📖
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
📖አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምህርት: የምናኔ ማእከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ።
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
📖አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ: ሲፈጩ: ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ::📖
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
📖በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ: ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው::

📖በአንዴም ከዳሞ (ትግራይ) ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ (ወሎ) አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ: በስብከተ ወንጌል: በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ::📖
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
📖ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:📖

📖ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት አገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ (ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው) ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ::📖
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
በአገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምህርት አብስለው አመነኮሱና "ሂዱ! አገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው::📖

📖ከእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትንአቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የኋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ::📖
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
📖ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለአገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በኋላ አቅንተዋል::

📖እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ: በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም::
"እንዘ የሃሊ ዘበሰማያት ዐስቦ::
መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል::📖
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
📖ከዚህ በኋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው ህዳር 26 (በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ) በ1292 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: <<ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው!!>>

ሰንበት ትምህርት ቤታችን ይህን ውለታ በማሰብ እንዲሁም ከጻድቁ ረድኤት በረከት ለመሳተፍ   ቤተመጽሐፍቱን በፃድቁ አባ ኢየሱስ ስም ሰይማ ምዕመናንን የእግዚአብሔር ቃል እንዲያነቡ እያደረገች ያለችሁ።

አባ ኢየሱስ ሞዐ ቤተመጽሐፍት
የአገልግሎት ሰዓት
ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ
ከቀኑ11:30-1:30
እንዲሁም ቅዳሜ 3:00-1:30

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

05 Dec, 06:02


የናግራን ሰማዕታት

በ፮ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ናግራን [የአሁኗ የመን] የክርስቲያኖች ሃገር ነበረች:: የሳባ ግዛትን የእኛ ነገሥታት ሲተዋት የተተካው ፊንሐስ ደግሞ ጨካኝ አይሁዳዊ ነበርና ናግራንን ሊያጠፋት ተመኘ:: ቀጥሎም "ሃገራችሁን ልጐብኝ" ብሎ በማታለል ገባ::

ወዲያውም ሕዝቡንና ካህናትን ሰብስቦ "ክርስቶስን ካዱ" አላቸው:: ጽኑ ክርስቲያኖች ግን "አይደረግም" አሉት:: እርሱም ሊያስፈራራቸው አስቦ ፬ ሺህ ያህል ካህናት: ዲያቆናትና ምሑራንን ጨፈጨፋቸው::

ይሕንን አድርጐ "አሁንሳ?" አላቸው:: ሕዝቡ ግን አሁንም "ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን የለም" አሉት:: [ሮሜ.፰፥፭] ጨካኙ ፊንሐስም እንደ ገና ከሕዝቡ መካከል ከ፬ ሺህ ፩ መቶ በላይ የሚሆኑትን ጨፈጨፈ::

ታላቁን ቅዱስ ሒሩትንም [የሕዝቡ መሪ ነው] ብዙ አሰቃይቶ ሰየፈው:: ሚስቱን ቅድስት ድማሕንም ፪ ሴት ልጆቿን ሰይፈው የልጆቿን ደም አጠጧት:: ከዚያም ሰየፏት:: ይሕንን የተመለከቱ የናግራን ክርስቲያኖች ግን ስለ መፍራት ፈንታ በፈቃዳቸው እየተሯሯጡ ወደ እሳትና ሰይፍ ተሽቀዳደሙ::

ከተማዋም እየነደደችና ደም እየፈሰሰባት ለ፵ ቀናት ቆየች:: ይሕንን የሰማው ቅዱሱ አፄ ካሌብም ደርሶ የተረፉትን ሲታደግ ፊንሐስን ከነ ወታደሮቹ አጥፍቶታል::

አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን::

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

05 Dec, 04:54


#እንዲስፋፋ እንፈልጋለን

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

04 Dec, 18:36


ሳምንታዊው የረቡዕ ጉባኤ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

04 Dec, 12:01


“ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው እህትህን አትናቃት ምንም ይሁን ምን ሰውን አትናቅ ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብከው እንደሆነ በለው (አስተውል) እንዴት? ያልከኝ እንደሆነ ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ሆኗል የክርስቶስ ሕዋስ ከሆነ ደግሞ እርሱን ናቅከው ማለት ክርስቶስን ናቅከው ማለት ነውና ወንድምህን የምትንቅ ከሆነ በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣እራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞትን ቀላቅለው እንዳጠጡት፣ በፊቱ ላይ ከተፉበት፣.. ሰዎች በምንም አትተናነሥም ። ስለዚህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

04 Dec, 06:20


🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ አሜን።
     ደስ ሲል😊 ረቡዕ ነው ዛሬ
         💚 የረቡዕ ጉባኤ💚
       💛   12:00-1:30 💛
      ❤️  ይምጡ ይታደሙ❤️
በመንፈሳዊ ህይወት ራስዎን ያጠናክሩ
       መቅረት ያስቆጫል
       💐@weldwahid💐

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

04 Dec, 04:10


🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷
“ሰላም ለከ መርቆሬዎስ ዘሮም፥
መስተጽዕነ ፈረስ ጸሊም፥
አመ አንደዱ ታሕቴከ ውሉደ መርገም፥
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም፥
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍሕም”

ትርጉም
"በጥቊር ፈረስ ላይ የተቀመጥኽ የሮም ሰው ለኾንኸው ለመርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባኻል፤ የመርገም ልጆች ከሥርኽ እሳትን ባነደዱ ጊዜ ከተገረፈው ሰውነትኽ በብዙ ዝናብ አምሳል የፈሰሰው ደም ፍሙን አጠፋው።"

                    አርኬ ዘቅዱስ አርከ ሥሉስ



"ሮማዊ ግሩም፥ በመንፈስ ቅዱስ ሕቱም፥
መዐዛ ቅዳሴከ ጥዑም፥ ከመ ጽጌ ገዳም፥ ነዓ ነዓ ማዕከሌነ ቁም፥ በበዓልከ ትባርከነ ዮም።"

ትርጉም

"ግሩም ሮማዊ በመንፈስ ቅዱስ የታተምክ፤ እንደ ምድረበዳ አበባ የምስጋናህ መዐዛ የጣፈጠ መርቆሬዎስ በበዓልህ ዛሬ ትባርከን ዘንድ ና ና በመካከላችንም ቁም።"
                               ኢትዮጵያዊ ሊቅ



“ሰላም ለመርቆሬዎስ ሰማዕት ንጹሕ ድንግል፥ ፈጻሜ ቃለ ወንጌል።”

ትርጉም
"የወንጌል ቃል የፈጸመ ለኾነ ለንጹሕ ድንግል ሰማዕት መርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባል"
                             ተአምኆ ቅዱሳን 
                        በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ



እንኳን ለእግዚአብሔር አገልጋይ ለሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🙏

የቅዱስ መርቆሬዎስ አማላጅነት አይለየን🤲 አሜን!

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

03 Dec, 15:44


"እንደበትህን 'ይቅር በለኝ ( ይቅር በሉኝ)'
ማለትን አስለምድ ፤ እውነተኛ የኾነ ትሕትና ይሰጥሃልና።"

ባሕታዊው አባ ኢሳይያስ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

03 Dec, 13:17


"የፈጸምኸው ኃጢአት ሀብት አድርገህ አታስቀምጠው፤ ሰው ገንዘቡ ሊያደርገው  የሚገባው ምርጥ ነገር ቢኖር ኃጢአቶቹን  ለእግዚአብሔር በመናዘዝ ራሱን መውቀስ መቻሉ ነውና።"
            ቅዱስ እንጦንስ
            @weldwahid

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

03 Dec, 05:10


ምሥጢረ ሥጋዌ እሁድ ሕዳር 29  ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት  መደበኛ ትምህርታችን ይቀጥል።

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

02 Dec, 17:06


«ወዳጄ ሆይ! እግዚአብሔር ነዳያንን የሚልክልህ መስጠትን እንድትለማመድ ነው፡፡ ዛሬ በነዳያኑ አድሮ የሚለምንህ ለኋለኛይቱ ቀን ስንቅ እንዲያስቀምጥልህ ወድዶ ነው፡፡ ታድያ ንጉሥ ወደ ቤቱ መጥቶ የሚያባርር ሰው እንደምን ያለ ጎስቋላ ሰው ነው? እንግዲያውስ ነዳያንን ስታይ ወደ አንተ የመጣው ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስ እንጂ ሰው አይደለምና አትግፋው፡፡ በረከትህንም ከቤትህ አውጥተህ አትሸኘው፡፡»

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

02 Dec, 11:51


“በቃል ብዛት ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።”

  — ምሳሌ 10፥19

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

02 Dec, 04:22


አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ቆመና "ጌታ ሆይ ተመልከት እጆቼ  🤲ንፁሃን ናቸው። ደም አላፈሰሱም የሰው ገንዘብ አልቀሙም" አለ   መለሰለት "ልጄ ሆይ! አዎ እጆችህ ንፁሃን 🤲 ናቸው ግን ባዶዎች ናቸው" አለው ይባላል።

ያልገደለ እጅ ግን ያላዳነ፣ ያልሰረቀ አጅ ግን ያልመፀወተ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ የለውም። እውነተኛው መልካምነት ክፋ አለማድረግ ብቻ ሳይሆን መልካም ማድረግም ነው። የሚጎዳንን መተው ብቻ ሳይሆን ስለ ሌሎች ጥቅም መድከምም ነው።
  
        መልካም ቀን

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

01 Dec, 17:48


“ልጆቼ ፦ እግዚአብሄርን በእምነት በፀሎት እንሻው ከእኛ የጠፋ ገንዘባችንን ነቅተን ተግተን በብዙ ድካም እንድንሻው እንዲሁ ሃሳባችንን ወደ እግዚአብሄር ልናቀርብ ይገባናል ፤ ልጃችን ቢጠፋብን ፈልገን በቅርብ ያላገኘነው እንደሆነ ሃይላችንን በድካም ድካማችንን በሃይል የምንለውጥ አይደለንምን? የጠፋውን ልጃችንን ስለመፈለግስ እናገኘው ዘንድ የብሱን በእግር ባህሩን በመርከብ የምንዞር አይደለንምን? ፈልገንም ያገኘነው እንደሆነ ዳግመኛ እንዳይጠፋብን ለመጠበቅ እንተጋ የለምን? እንዲህ ከሆነ መሓሪ እግዚአብሄርን በእምነትና በፀሎት እንሻው ዘንድ ምን ያህል ይገባን ይሆን? እግዚአብሄርን ፈልጉት ነጋዴ ወርቅ ቢጠፋበት ወርቁን ያገኘው እንደሆነ ሁሉን ቦታ እንደሚፈልግ እንዲሁ እግዚአብሄርን ፈልጉት፤ እናት ልጇ ቢጠፋባት እስክታገኘው ድረስ አርፋ እንደማትቀመጥ እንዲሁ እግዚአብሄርን ፈልጉት እግዚአብሄርን እሹት ፈልጉት እስክታገኙት ድረስ በእምነት በፀሎት እሹት፡፡”

(ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ)

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

01 Dec, 01:44


#ዛሬ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

01 Dec, 01:41


ዕለተ ሰንበት የእረፍት ቀን ነው ሲባል በደዌ እንደተያዘ ሰው ከአልጋ ተጣብቀህ ተኝተህ አትዋል  መልካም ስራ ስራባት እንጂ።
     ቅዱስ አትናቴዎስ
       
@weldwahid

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

30 Nov, 06:46


🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷
ኅዳር ፳፩ ቀን የሚከበረው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል

👉ኅዳር ፳፩  በተለየ መልኩ የምናከብረው:-

1.በብሉይ ኪዳን ታቦተ ጽዮን የፈጸመችውን ልዩ ልዩ ገቢረ ተአምራትን ለማሰብ

2.ቀዳማዊ ምኒልክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛርያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበት ዕለት በመሆኑ

3.በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ ምሕረት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ይሁን ተብሎ ዐዋጅ የታወጀበት

4.ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ምሳሌ ራእይ ያየበት

5.ነቢዩ ሕዝቅኤል በተቆለፈች ቤተ መቅደስ ምሳሌዋን ራዕይ ያየበት

6.ዕዝራ በቅድስት ሀገር ምሳሌ ራእይ ያየበት

7.አብርሃና አጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያናትን ስታቃጥል ታቦተ ጸዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሐይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ

እግዚአብሔር አምላክ በእናቱ በእመቤታችን አማላጅነት ሰላሙን  ይስጠን፡፡ አሜን!
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
"እግዚአብሔርን ስለምትወድ ስለ አገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጣት ዘንድ ጸልዩ"🤲🤲🤲

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

29 Nov, 18:39


ኃጢአት ጸሎት የማቋረጥ ውጤት ነው። እውነተኛ ጸሎት ኃጢአትን የማቆም ምልክት ነው። ሰው ኃጢአትን ልምዱ ካላደረገ በቀር እየጸለየ የሚበድል፣ ከአምላኩ ጋር እየተነጋገረ የሚያምጽ የለም። አዳም እጸ በለስን የቆረጠው ከአምላኩ ጋር የነበረውን ንግግር (ጸሎቱን) በማቋረጡ ነው። ይኸውም አዳምን ጠርቶ "ወዴት ነህ?" ባለው በፈላጊው ድምጽ ተረጋግጧል።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

29 Nov, 10:47


🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸
የተወደዳችኹ የኦርቶዶክስ ቤተሰቦች!  ህዳር 27 ከ9ኛ-12ኛ ላሉ ኦርቶዶክሳዊያን ለሚጀመረው የተማሪዎች ጉባኤ  ለማስፋት እንችል ዘንድ ይኽንን መስፈንጠርያ (Link) ለ 11 እህትና ወንድሞች  ተማሪዎች ሼር እናድርግ፡፡
               ለመቀላቀል
       👇👇👇👇👇👇

    🌸🌸🌺🌺🌺🌸🌸
    🌼  @hanastudent🌼
          🌺@hanastudent🌺
              🌸@hanastudent 🌼
                  🌺@hanastudent🌸   
🌸 🌹🌸🌹እናመሰግናለን🌸🌹🌸🌺

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

29 Nov, 10:34


1, የተማሪዎች ጉባኤ  ምንድን ነው?

፨ ሰንበት ትምህርት ቤታችን  በየሳምንቱ የሚያካሂዳቸው መደበኛ ጉባኤ እና ኮርስ አንዲሁም የርቀት ትምህርት መርሐ ግብር አሉት ።የተማሪዎች ጉባኤ መንፈሳዊ ትምህርት በማስተማር በሁለት በኩሉ የተሳለ ሰይፎች በማድረግ ለቤተክርስቲያን
ብሎም  ለሀገር ብቁ ዜጋዎችን ማፍራት ነው፡፡እንዲሁም  ኦርቶዶክሳዊያን
ተማሪዎችን ከዘመናዊነት ጫና፤ ከአቻ ግፊት፤ ከሃይማኖታዊ ክህደት እና ከሌሎች  ዓለማዊ
ፈተናዎች ተጠብቀው እንዱሁም ቅድስናቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ ለማድረግ የሚያግዙ ትምህርቶች የሚሰጡበት ጉባኤ ነው

https://t.me/hanastudent

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

29 Nov, 10:24


🏆🏆🏆🥇🥈🥉🏆🏆🏆
የምሽቱ_ጥያቄ ከነ ምላሹ  |ኅዳር 19/2017 ዓ.ም 
1. በአስቆሮቱ ይሁዳ ምትክ የተተካው ሐዋርያ ማን ይባላል?
 
ሀ. ቅዱስ ማቴዎስ  
ለ. ቅዱስ ፊልጶስ  
ሐ. ቅዱስ ማትያስ  
መ. ቅዱስ ያዕቆብ 



2. ሐዋርያው ናትናኤልን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ጌታ የጠራው ሐዋርያ ማን ነው? 

ሀ. ቅዱስ ፊልጶስ  
ለ. ቅዱስ ማትያስ 
ሐ. ቅዱስ ዮሐንስ  
መ. ቅዱስ እንድርያስ 



3. ከ12ቱ ሐዋርያት ውስጥ አይመደብም፤ 
ሀ. ቅዱስ ታዴዎስ  
ለ. ቅዱስ በርተሎሜዎስ 
ሐ. ቅዱስ ማቴዎስ  
መ. ቅዱስ ማርቆስ 



4.  ከ12ቱ ሐዋርያት መካከል የመጀመሪያው ሰማዕት ነው፤
 
ሀ. ቅዱስ ጴጥሮስ  
ለ. ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ 
ሐ. ቅዱስ እስጢፋኖስ  
መ. ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ



5. ጽዮን የሚለውን ስም ይወክላል፤
 
ሀ. ታቦተ ጽዮን  
ለ. የዳዊት መናገሻ ከተማ 
ሐ. ሕዝበ አሥራኤል 
መ. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ሠ. መልስ የለም  
ረ . ሁሉም



👏👏👏 መልሶቻቸውን የላኩልን ተሳታፊዎች እናመሰግናለን🙏🙏🙏

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

29 Nov, 05:56


2 ቀን ቀረው

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

29 Nov, 04:15


🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿
መንፈሳዊ ሰው
"አንድ ሰው ከልቡ ሆኖ ያቀረበውን ጥልቅ ፀሎት እንዴት መለየት እንችላለን ? ይህን ፀሎት ከእግዚአብሔር ጋ ግንኙነት እንዳለህ የሚያሳይ ነው ።ጸሎት የሚቀርበው በኃዘን ፣በመረዳት፣በተመስጦ ፣በትኩረት፣በፍቅር፣ በትህትና ፣በጸጸት፣በእምነት በመተማመን በተስፋ የሚቀርብ ጸሎት ነው።
እንዲ ያለው ፀሎት ክብደት የሌላቸው ቃላት ስብስብ ሳይሆን በመንፈስ የቀረበ ጸሎት ነው።"

            አቡነ ሺኖዳ
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
"እግዚአብሔርን ስለምትወድ ስለ አገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጣት ዘንድ ጸልዩ"🤲🤲🤲

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

28 Nov, 17:29


🎲 Quiz 'የምሽቱ_ጥያቄ|ኅዳር 19/2017 ዓ.ም '
"Start this quiz" የሚለውን ይጫኑ ፈተናውን ይጀምራል ። ጥያቄዎችን ሲመልሱ የቴሌግራም ቦት ሲስተም ይመዘግባል።
🖊 5 questions · 45 sec

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

28 Nov, 12:06


ጥያቄ እና መልስ
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ሰላም እንዴት አላችሁ ?!

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
ሳምንታዊው የጥያቄ እና መልሳችን በተለመደው ሰዓት ምሽት 2:30 ይጀምራል ጥያቄ እና መልሱን በመሳተፍ መንፈሳዊ እውቀቱን ያዳብሩ።

ዘወትር ሐሙስ ከምሽቱ 2:30
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

አርብ የአሸናፊዎች ስም ዝርዝር ይለቀቃል👏

@weldwahid

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

28 Nov, 11:43


"እግዚአብሔር ለአንተ ሲል ራሱን ዝቅ አደረገ:: አንተ ግን ለራስህ እንኳን ስትል ራስህን ዝቅ ማድረግ እንዴት ያቅትሃል?"
         ቅዱስ መቃርዮስ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

28 Nov, 05:35


ገብርኤል ሆይ፤ ከሰው ወገን ጠዋትና ማታ ከቶ እንደ እኔ ኀዘንና ትካዜ የሚበዛበት የለም፣
ከመላእክትም ወገን እንደ አንተ ያዘኑትን የሚያረጋጋ የለም፣
ገብርኤል ሆይ፤ ስለዚህ እኔም አውቄና አንተን አምኜ ያቀረብኩትን ይህን ጸሎት እንደ ትልቅ ዋጋ ቆጥረህ የሚያረጋጋ ቃልህን አሰማኝ።

   🌹 መልክአ ገብርኤል🌹

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

28 Nov, 04:59


" ጸሎት የጭንቀት ሁሉ መሸሸጊያ ስፍራ የደስታ መሰረት፣ የቋሚ ደስታ ምንጭ ፣ ከኀዘን መከላከያ ነው።"
         /ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

27 Nov, 04:44


🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿
"ወንድሞቻችን ኾይ እምነት አለኝ ምግባር ግን የለኝም የሚል ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል?

በውኑ እምነቱ ልታድነው ትችላለችን?

ከወንድሞቻችን÷ ወይም ከእኅቶቻችን÷ የታረዙ ወይም የዕለት ምግብ ያጡ ቢኖሩ÷ ከእናንተም አንዱ÷ “በሰላም ኺዱ÷ እሳት ሙቁ÷ ትጠግባላችኹም” ቢላቸው÷ ለችግራቸውም የሚሹትን ባይሰጣቸው ምን ይጠቅማቸዋል?

እንዲኹም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው፡፡

                      ያዕ. ፪÷፲፬-ፍጻ
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
"እግዚአብሔርን ስለምትወድ ስለ አገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጣት ዘንድ ጸልዩ"🤲🤲🤲

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

26 Nov, 16:39


"እግዚአብሔር ከኃጢአተኛ ይርቃል ብሎ ማሰብ ፀሐይ ከዓይነ ሥውር [ስላላያት] ትርቀዋለች ብሎ እንደማሰብ ነው"
         ቅዱስ እንጦንስ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

26 Nov, 11:48


" የንስሐ አባት ማለት ! እርሱን ስትመለከት እግዚአብሔርን እና ትዕዛዛቱን የምታስታውስበት ሰው ማለት ነው  "
     
   ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ሣልሳዊ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

26 Nov, 04:10


🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿
"ጾም - ለጸሎት እናቱ፣ ለአርምሞ እኅቱ ፣ ለዕንባ ምንጩ እና ለመልካም ምግባራት ኹሉ ቀዳሚ ናት”
            የወንጌል ትርጓሜ

⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
"እግዚአብሔርን ስለምትወድ ስለ አገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጣት ዘንድ ጸልዩ"🤲🤲🤲

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

25 Nov, 17:43


ካነበብ ነው ሽራፊ ሀሳብ
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 
"[የራሔል ዕንባ እስከ ራማ ተሰማ ሲባል ስሰማ የድንግል ማርያም ዕንባ የት ድረስ ይሰማ ይሆን? እላለሁ:: "እመቤታችን ሆይ ስለ እኛ ስለልጆችሽ እባክሽን አልቅሺ:: የራሔል ዕንባ ራማ ከደረሰ የአንቺ ዕንባ የት ሊደርስ ነው? በየበረሃ እየወደቀ ስላለው ልጅሽ ስለሞተለት ወንድም እባክሽን ለምኚ:: ሙሴ በወንድሙ አሮን በትር ባሕርን ከፈለ:: ሳይተክሏት የለመለመችው የአሮን በትር  ድንግል ሆይ የኃጢአታችን ባሕርስ የተከፈለው ባንቺ አይደለምን? አሁንም የመከራችን ባሕር የማትከፍይልን ለምንድን ነው? ያሰኘኛል]"

ምንጭ  ከጃንደረባው የፌስቡክ ፔጅ
ዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ  "ሙሴና ሚካኤል ፍለጋ"  ከሚለው ፅሁፍ የተወሰደ
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
"እግዚአብሔርን ስለምትወድ ስለ አገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጣት ዘንድ ጸልዩ"🤲🤲🤲

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

21 Nov, 06:40


#በዓለ_ቅድስት ሐና ፲፩ ህዳር ፳፻፲፯
ፎቶ ስብስብ

ያብጽአነ አመ ከመ ዮም
እንደዛሬው ለዓመቱ ያድርሰን

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

21 Nov, 04:53


⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
"የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ ሆይ፤ የተቸገሩትን የተጨነቁትን ዘወትር እንደምትረዳቸው ሁሉ እኔንም ለመርዳት ክንፍህን ዘርግተህ ፈጥነህ ድረስልኝ ።"

  🌹    መልክዐ ሚካኤል     🌹

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

20 Nov, 06:42



"በስጋ ተዋህዶ በዚህ ዓለም ከመኖር በየክፍሉ ወደተዘጋጀው (ተሠራ) ተስፋ ህይወት ለነፍስሽ መውጣት ሰላም እላለሁ ።ቅድስት ሐና ሆይ ነፍስ ከስጋዬ በተለየች ጊዜ ማርታ ለክርስቶስ ማዕድን በቤቷ እንዳዘጋጀች ለእኔም በአማላጅነትሽ ዋጋዬን አዘጋጂልኝ።"

         🌹 መልክዐ ሐና 🌹

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

19 Nov, 17:31


🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌹🌷🌹
🌹🌹🌹🌹እንኳን አደረሳችሁ🌹🌹🌹🌹

"በድቅድቅ ጨለማ መካከል ብርሃንን በፈጠረ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ባለ በእግዚአብሔር ስም አንቺን ላምሰግን  ስጀምር ቅድስት ሐና ሆይ የምስጋናሽን (የውዳሴሽን) ነገር እስከ ፍፃሜ እንናገር ዘንድ ሐዲስ ልሳንን ስጪን።"

       🌹🌹🌹 መልክዐ ሐና 🌹🌹🌹

                    @weldwahid

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

19 Nov, 09:16


አድርሺኝ🙏

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

08 Nov, 12:10


ድንግል ማርያም በ3 ዓመት ከ3ወር (1275 ቀናት) ስደቷ ብዙ መከራዎች ተቀበለች 🤲                                                                                                             
የአምላክ እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች - ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች - የሕይወትን ውኃ ተሸክማ ተጠማች - የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች - የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች 🤲

እመ አምላክ ተራበች፣ ተጠማች፣ ታረዘች፣ ደከመች፣ አዘነች፣ አለቀሰች፣ እግሯ ደማ፣ ተንገላታች!
                                                          ስለዚኽ እንደ አባ ሕርያቆስ እንዲኽ እንበላት።                                                                                                                                        
ድንግል ኾይ ስለዚኽ እንወድሻለን ፥ እናከብርሻለን🙏 ስምሽንም ከፍ ከፍ አድርገን ለልጅ ልጅ እንጠራዋለን።

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

07 Nov, 17:33


🎲 Quiz 'የምሽቱ ጥያቄ   | ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም'
"Start this quiz" የሚለውን ይጫኑ ፈተናውን ይጀምራል ። ጥያቄዎችን ሲመልሱ የቴሌግራም ቦት ሲስተም ይመዘግባል።
🖊 5 questions · 45 sec

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

07 Nov, 03:44


ጥያቄ እና መልስ
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ሰላም እንዴት አላችሁ ?!

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
ሳምንታዊው የጥያቄ እና መልሳችን በተለመደው ሰዓት ምሽት 2:30 ይጀምራል ጥያቄ እና መልሱን በመሳተፍ መንፈሳዊ እውቀቱን ያዳብሩ።

ዘወትር ሐሙስ ከምሽቱ 2:30
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

አርብ የአሸናፊዎች ስም ዝርዝር ይለቀቃል👏

❄️መልካም ቀን❄️

@weldwahid

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

07 Nov, 03:33


‹‹በከመ ይቤ እግዚእነ በነቢይ ጊሥዋ ለቤተ ክርስቲያን እስመ ኵሉ ዘጌሠ ኀቤሃ ተአሥዮ ፍሥሐ።››

"ጌታችን በነቢዩ አድሮ እንደተናገረው ቤተ ክርስቲያንን ገሥግሡባት፤ ማልዱባት ወደ እርሷ የገሠገሠውን ደስታ ትሰጠዋለችና"
       ቅዱስ ያሬድ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

06 Nov, 18:42


"እንግዲህ ከሀሜት፣ ከሀሰት ጓደኝነት፣ የጌታን ሥም በግብዝነት ከሚጠሩ፣ ምንም የማያውቁትን ከሚያታልሉ በመራቅ ለጥሩ ነገር እንቅና። ማንም ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ የማያምን ፀረ ክርስቶስ ነው። ማንኛውም በመስቀል ላይ መከራ መቀበሉን የማያምን ዲያብሎስ ነው። ማንም የክርስቶስን ትምህርት ለራሱ እንደሚመቸው የሚያጣምም እና ትንሳኤና የመጨረሻ ፍርድ የለም የሚል ይህም የሰይጣን የበኩር ልጅ ነው።"

ቅዱስ ፖሊካርፐስ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

06 Nov, 11:51


አንድ ሌባ በተደጋጋሚ በጨለማ ወደ አንድ ግቢ ይገባል አንድ ቀን የግቢው ባለቤት ከግቢው ውስጥ ከሚገኘው ዛፍ ላይ ወጥቶ ሌባውን ይከታተለዋል ሌባው እየሮጠ መጥቶ ዛፉ ሥር ቆመ ከዛ ሌባው ዛፉ ሥር እንደቆመ ቅኝት ይጀምራል ወደ ፊት፣ ወደ ኋላ፣ ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ እየተዟዟረ አየ የቤቱ ባለቤት ዛፉ ላይ ሆኖ አንዲት የዛፍ ፍሬ ወደታች ጣለበት ፍሬዋም የሌባውን አናት መታችና ወደቀች ሌባው ቀና ብሎ ወደ ላይ አየ ከቤቱ ባለቤት ጋርም ተፋጠጠ የቤቱ ባለቤትም “ይህን ያደረኩት ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? ልትሰርቅ ባሰብክ ጊዜ ሰዉ እንዳያየኝ ብለህ ወደ ቀኝና ወደ ግራ ብቻ ሳይሆን ወደ ላይም ማየት እንዳለብህ ላስታውስህ ፈልጌ ነው” አለው ሰለዚህ ክፉ ነገር አንስራ : ሰው እንዳያየን ብለን ግራ እና ቀኝ ማየት ሳይሆን ያለብን የፈጠረን እግዝአብሔር አምላክ እንዳያዝንብን እንጠንቀቅ፤ ከክፉ ነገር እንታቀብ ሰዉን ሳይሆን ፈጣሪን እንፍራ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

06 Nov, 04:10


"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

05 Nov, 16:53


‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም››

ቅዱስ አርሳንዮስ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

05 Nov, 02:53


‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም፡፡ የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል››

ቅዱስ ሚናስ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

04 Nov, 17:28


“ዐይነ ኵሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ
የሁሉ ዐይን አንተን ተስፋ ያደርጋልና”


   ማቴ. ፮፦ ፲፬—፲፭

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

04 Nov, 09:46


የምሥጢረ ሥላሴ ጉባኤያችንን እንዴት አገኛችሁት ?

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

04 Nov, 09:38


“ተወዳጆች ሆይ! ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት ብቻ የምትሰሙ አትሁኑ፡፡ እነርሱን ለመምሰልም ተጣጣሩ እንጂ፡፡ ለጊዜው ብቻ የምታደንቋቸው አትሁኑ፡፡ ወደ ቤታችሁ ብቻ ሳይሆን ወደ ልቡናችሁ ውሳጤም ዘልቀው እንዲገቡ አድርጉ፡፡ ዘወትር አስቧቸው፡፡ በልቡናችሁ ጓዳ እንዲገቡ አድርጓቸው፡፡ እናንተን ትተው ይሔዱ ዘንድ አትፍቀዱላቸው፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ዘወትር እያያችኋቸው ትበረታላችሁ፡፡ በእምነት ትጸናላችሁ፡፡ የለበሱትን የጽድቅ ጥሩር፣ የያዙትን ምግባረ ወንጌል፣ የእምነት ጋሻ፣ የመዳን ራስ ቁር፣ የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ እየተመለከታችሁ ትበረታላችሁ፡፡”

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ )

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

02 Nov, 18:04


#ዕለተ ሰንበትን
#በመካነ ቅዱሳን

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

02 Nov, 10:31


ልጅሽ ደጅ ላይ ቆሟል

ከመስከረም 26-እስከ ሕዳር 6 ባሉ አንድ ቅዳሜ ማታ ከ3 ሰዓት በኋላ ማሕሌተ ጽጌን ለመቆም ወደየካ ደብረ ሳሕል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እየሄድኩ ነው . . . መንገዱ ጭር ብሏል፤ አንድ ሱቅ ላይ ግን ደምበኛ (ገዢ) ቆሟል፤ እኔ መንገዴን እየቀጠልኩ ነው፡፡ ደንበኛው ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣ እና ‹‹አባ ይበርኩኝ?›› አለኝ። ‹‹ካህን አይደለሁም›› አልኩት፣ በለበስኩት ነጠላ ጋቢና በእጄ የያዝኩት የጸሎት መጽሐፍ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደምሄድ አውቆ ነው፡፡ ‹‹አውቃለሁ›› አለኝ እና ‹‹ወደየትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው የምትሄደው?›› ጠየቀ መለስኩለት፤ ‹‹እባክህን ልሸኝህ?›› አለኝ አዲስ ቪ 8 መኪና እያሳየኝ፣ ‹‹ብዙም ሩቅ ስላልሆነ በእግሬ ነው የምሄደው›› አልኩት . . .
🌿🌿🍁🌿🌿
ግለሰቡ የጠጣ ይመስላል፣ በእርግጥም የመጠጥ ሽታ ሸትቶኛል፤ በእጁ ፓኬት ሲጋራ ይዟል፣ ከሱቁ ሲመጣ ከፓኬቱ ውስጥ አንዱን አውጥቶ ከንፈሩ ላይ አድርጎ ነበር ሲቀርበኝ በጣቶቹ መሃል ያዘው፣ ምልከታዬን አስተውሎ ነው መሰለኝ የያዘውን ሲጋራ በሙሉ ጣለና በእግሩ ረጋገጠው፡፡ ‹‹አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ ልትል ነው አይደል?›› አለኝ
🌿🌿🍁🌿🌿
ከዚህ ንግግር በኋላ ስካሩ ሙሉ ለሙሉ ሲጠፋ በግልጽ ይታያል፡፡ ሁሉንም የመኪናውን በሮች ከፈተና ‹‹እንዲናፈስ ፈልጌ ነው . . . በሲጋራና በመጠጥ ሽታ  የታጠነ መኪና ውስጥ እንዳትገባ›› አለኝ፤ በግርምት ቆምሁ፤
🌿🌿🍁🌿🌿
‹‹እባክህ አሁን እንሂድ?›› የጋቢናውን በር ብቻ ትቶ ሌሎቹን ዘጋጋና መኪናውን ለመንዳት ተዘጋጀ፤ በእምነት ገባሁና ተቀመጥኩ። መንገድ ስንጀምር በጣም ባዘነ ድምጸት
🌿🌿🍁🌿🌿
‹‹ሽሮ ሜዳ ነው ያደግሁት . . . ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን . . . ጽጌን በፍቅር ቆሜ ነው ያደግኩት  . . . ለረጅም ዓመታት . . . አክሊለ ጽጌ ብዬ . . . ክበበ ጌራ ወርቅ ብዬ ›› ዓይኖቼን ከመንገዱ ነቅዬ ወደርሱ ሳዞር መንታ መንታ ሆነው የሚወርዱ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም መስማት ብቻ
🌿🌿🍁🌿🌿
‹‹ዲግሪዬን ከያዝኩ በኋላ አንድ ዓለም አቀፍ ኤን ጂ ኦ ገባሁ . . . በከፍተኛ ደመወዝ በቃ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ተለያየሁ. . . አልሳለም፣ ኪዳን አላደርስ፣ አላስቀድስ፣ አላድር፣ አላነግስ ከሀገር ሀገር መዞር ከጓደኞቼ ጋር መጠጣት፣  ሲጋራ ማጨስ . . . ይኸውልህ ሚስትና ልጆች እያሉኝ ነው እዚህ ያገኘኸኝ፣ የመጠጥና የሲጋራ ጓደኞቼ በልጠውብኝ ነው ያገኘሁህ. . . ውስኪአቸውን ይዘው እየጠበቁኝ ነው ›› ያለቅሳል፣ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ግን በሥርዓት ረጋ ብሎ ይነዳል፤ መናገሩን ይቀጥላል
🌿🌿🍁🌿🌿
‹‹ተረጋግቼ ማሰብ አልፈልግም  . . . ምክንያቱም ከተረጋጋሁ ልጅነቴን ማሰብ እጀምራለሁ . . . ልጅነቴን ማሰብ ከጀመርሁ ቤተ ክርስቲያንን ማሰብ እጀምራለሁ . . . ደጀ ሰላሟን ማሰብ እጀምራለሁ. . . መቅደሷን ማሰብ እጀምራለሁ፣  . . . የዕጣኑን ሽታ ማሰብ እጀምራለሁ . . . ማልቀስ እጀምራለሁ . . . ፍቅሯን አስባለሁ  . . . የጸናጽሉ፣ የከበሮው ድምጽ ይሰማኛል፣ በመሃል ሰይጣኔ ይመጣና እውነቴን ነው ስጠራው ነዋ የሚመጣው. . . ለጓደኞችህ ደውል ይለኛል . . . በመጠጥ ራስህን ደብቅ ይለኛል እታዘዘዋለሁ ልጆቼንና ሚስቴን ጥዬ እወጣለሁ›› 
🌿🌿🍁🌿🌿
አሁን ወደ ቤተክርስቲያን ታጥፈናል፤ ወደ ግቢው የሚያስገባ በር ጋር ስንደርስ ቆመ፣ ወደውስጥ ለመግባት በሮቹ የተከፈቱ ቢሆንም አልገባም፤
‹‹ወደውስጥ ገብተህ ትንሽ ቆይተህ አትሄድም?›› አልኩ ሀዘኑ ተጋብቶብኝ ‹‹አልገባም ግን ድሮ የሚወድሽ ልጅሽ ደጅ ቆሟል በላት›› አለና ሳግ ተናንቆት መሪውን ተደግፎ ድምጽ አሰምቶ አለቀሰ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ለምን እንዳለቀሰ፣ እንዴት እንዳለቀሰ በዓይኔ ያየሁ መሰለኝ፤
‹‹እባክህን ግባና አልቅስ›› አልኩ፣ የቻለውን ያህል አልቅሶ እንዲወጣለት ፈለግሁ፣
🌿🌿🍁🌿🌿
‹‹ማን . . . እኔ? አልገባም ግን ንገርልኝ አሁንም ይወድሻል በልልኝ . . . እዚህ በር ላይ ቆሟል በልልኝ›› አለኝ፣ እያለቀሰ ወረድሁ
ቅዱስ ዳዊት ‹‹በኃጥአን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ›› መዝ 84፣10 ያለው ለምን እንደሆነ ይበልጥ ገባኝ። ሳላውቀው የእኔም እንባ መንገዱን ጀምሯል፤ ‹‹ማን ስለሆንኩ ነው እንዲህ በፍቅርህ የተሸከምከኝ››አልኩ አምላኬን፣     
በላዔ ሰብዕ ትዝ አለኝ በልጅነቱ የሚያስታውሳትን የድንግልን ድንቅ ስሟን ሲሰማ ከክህደት እንደተመለሰና ለመዳን ምክንያት እንደሆነችው፡፡ እናም ‹‹በልጅነቱ ይወድሽ የነበረውን ልጅሽን አስቢው ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢለት›› አልኳት

📝ዲያቆን ዶ/ር ቢኒያም ዘክርስቶስ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

02 Nov, 04:03


"ገድሉ የበዛ የተትረፈረፈ ኃያል፤ ተጋዳይ ብርቱ ሰው፤ በተዘረጋ ዙፋን ላይ ኃይልን ያሳየ በሰማይና በምድር መካከል ያለ የማይቆጠር የክብር ኮከብ፤ ተዓምሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ የኾነ፤ የፀሐየ ጽድቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕት ለኾነ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰላምታ ይገባል።"
 
              አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

02 Nov, 03:54


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
    🌹🌹🌹ሥርዓተ ማኅሌት🌹🌹🌹
        🌹🌹ዘማኅሌተ ፅጌ🌹🌹
         🌹የአምስተኛ   ሳምንት🌹

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

29 Oct, 04:27


(ወደ ሮሜ ሰዎች 12 )
------------
17፤ ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።

18፤ ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።

19፤ ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።

20፤ ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።

21፤ ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

28 Oct, 16:45


በፈተና ጊዜ፥ ደካማው ሰው "እንደዚህ የደረሰብኝ'ኮ" እያለ የሚያመካኝበት ሌላ ሰውን ይፈልጋል፤ ብርቱው ሰው ግን በፈተናው ይጸና ዘንድ እግዚአብሔርን ይፈልጋል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

28 Oct, 11:58


🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

"ድንግል ኾይ!

በእውነቱ አንቺ ከታላላቆች ይልቅ ታላቅ ነሽ 🤲 ማኅደረ ቃለ አብ ኾይ! ከፍጡራን ወገን አንቺን ሊተካከል የሚችል ታላቅ ማን ነው?

ድንግል ኾይ! ከየትኛው ፍጥረት ጋር አወዳድርሻለኹ? አንቺ ቀድሞ በወርቅ ካጌጠችው የሕጉ ታቦት ይልቅ በንጽሕና ያጌጥሽ ታላቅ ነሽ!

እውነተኛውን መና የተሸከምሽ የወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ መና የተባለውም ሥግው ቃል ነው፡፡"
    
         ታላቁ ሊቅ ቅዱስ አትናቴዎስ


🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

28 Oct, 04:08


🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲

ጌታዬ ኾይ!
ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን አትንሳኝ! ከመረረ ገሃነምም አድነኝ!

አቤቱ ጉልበቴ ኾይ! በኃልዮ ወይም በነቢብ ወይም በገቢር ብበድልኽ ይቅር በለኝ!

ከድንቁርና፣ ከዝንጋዔ፤ ልል ዘሊል ከመኾን፤ ክሳደ ልቡናዬንም በትዕቢት እና በክፉ ነገር ኹሉ ከማደንደን ጠብቀኝ!

ጌታዬ ኾይ! ወደፈተና አታግባኝ! ክፉውን በመሻት የታወረ ዓይነ ልቡናዬን አብራልኝ!

አቤቱ መድኃኒቴ ኾይ፡ ሰው ነኝና በድያለኹ!
አንተ ግን ምሕረትኽ የበዛ፤ መዓትኽ የራቀ ጻድቅ እና ቸር ነኽና የነፍሴን ደካማነት ተመልክተኽ አድነኝ!

ቅዱሱን ስምኽን ከፍ ከፍ አደርገው ዘንድም ረዳት የሚኾነኝን ጸጋኽን ላክልኝ!

ጌታዬ እና መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ኾይ!
በመዝገበ ሕይወት ስሜን ጻፍልኝ! መጨረሻዬንም አሳምርልኝ!

አቤቱ አባቴ እግዚአብሔር ኾይ! እስከዛሬ ድረስ በፊትኽ ያደረግኩት ምግባር ትሩፋት የለኝም!

ነገር ግን አኹን መጀመር እችል ዘንድ በርኅራኄ እርዳኝ!
የቸርነትኽን ጠል በልቡናዬ ጨምርልኝ!

ንጉሠ ሰማይ ወምድር የኾንክ እግዚአብሔር ኾይ!
ኃጥእና ርኩስ የኾንኩትን እኔን ባርያኽን በመንግሥትኽ በመጣኽ ጊዜ አስበኝ!

አሜን በእውነት እንበለ ሐሰት!

(የቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ ጸሎት)

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

27 Oct, 17:31




"ሰይጣንም የአንቺን ምስጋና ወሬ ሲሰማ በብስጭት ጥርሱን ያፏጫል።

የምስጋናሽ ወሬ በእርሱ ዘንድ መራጃ ነውና እራሱን ይቆርጠዋል፡፡

ከስምሽ አጠራር የተነሣ መብረቅ በኃይል ሲጮኽ እንደ ሰማ ኹሉ ይደነግጣል፡፡

አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ ፈጽሞ ዕረፍት አላገኘም፡፡ ባንቺ ታመመ በልጅሽም ተጨነቀ በአንድ ልጅሽ መስቀል ሥቃይ አገኘው፡፡ ከፍጡራን ወገኖች ኹሉ ይልቅ ሰይጣን አንቺን ይጠላል፡፡"

         አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ


ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

27 Oct, 12:12


መንፈሳዊ መጻሕፍት ደሰሳ
📚📖📚📖📚📖📚📖📚📖📚📖

6ኛ  ዙር የመጽሐፍ ዳሰሳችን እሁድ ጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ.ም.  "የብርሃን እናት" የተሰኘው  መጽሐፍ በስፋትና በጥልቀት ይዳሰሳል።

እርሶም በዚህ መንፈሳዊ የመጻሕፍት ዳሰሳ እና ውይይት ላይ ከ #09:30 ሰዓት ጀምሮ በምዕራፈ ጻድቃን ሰንበቴ አዳራሽ በመገኘት የመርሐ ግብራችን ተካፋይ ይሁኑ።

📚📖📚📖📚📖📚📖📚📖📚📖

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

27 Oct, 10:28


🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

"አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ኾይ!

የብርሃን እናት ነሽና አንቺን ብቻሽን በክብር በምስጋና እናገንሻለን።

የተባረክሽ አንቺ ከመላእክት ትበልጪያለሽ ከደቂቀ አዳምም ትበልጪያለሽ  ከአሳቦች ኹሉ ትበልጪያለሽ ገናንነትሽን መናገር የሚቻለው ማን ነው? አንቺን የሚመስል የለምና።

ማርያም ኾይ መላእክት ያገኑሻል ሱራፌልም ያመሰግኑሻል።

በኪሩቤልና በሱራፌል ላይ አድሮ የሚኖር ጌታ መጥቶ በማኅፀንሽ አድሯልና። ሰውን የሚወድ ወደ እርሱ አቀረበን ክብር ምስጋና ያለው እርሱ የኛን ሞት ተቀብሎ የእርሱን ሕይወት ለኛ ሰጠን ። ቅድስት ኾይ ለምኝልን።…"

🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

27 Oct, 08:43


🌹  የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት  🌹
     🌹    ሰባት ቀናት ቀሩት        🌹
        🌹  ጥቅምት 24/2017🌹
           🌹    4:00-6:00    🌹
              🌹መካነ ቅዱሳን🌹

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

27 Oct, 02:47


🌿🌿🌿🌿🌿🌿

የተወደዳችኹ🙏

የዛሬዋ ዕለት ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲመተ  ድቁናውን የተቀበለባት ንዕድ ዕለት ናት!

አምላከ ቅዱሳን ከቀዳሚ ሰማዕት ረድኤት በረከት ይክፈለን 🙏 እኛንም ሀገራችንንም በቅዱሳኑ ጸሎት እና ቃልኪዳን ይማረን! አሜን በእውነት 🤲🤲🤲

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

26 Oct, 18:13


ማኅሌተ ጽጌ

ክፍል ፪

👉"ክበበ ጌራ ወርቅ" ሲባል መዞሩ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስን ስለሚያነሣ ነው፤

ቅዱስ ጊዮርጊስ በኢትዮጵያ ጉዳይ እመቤታችንን ይጋራታልና፤ ይኸውም ኢትዮጵያን ከእመቤታችን ቀጥሎ በዐሥራትነት ተቀብሏታል፡፡ ይኸውም የኢትዮጵያ ገበዝ እስከ መባል አድርሶታል።

ይሀን በሚያስተባብር መልኩ #ሊቁ_እንዲህ_ብሏል

"ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየሐቱ፥
ዘተጽሐፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፥
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፥
አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፥
ወለኪሰ ይሰግድ ውእቱ::"

"የስሙ ምልክትና የሞቱ መታሰቢያ የተጻፈብሽ ከሚያበራ ወርቅ ይልቅ እንደ ዕንቍ የጠራ ንጽሕና ያለሽ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለእርሱ ሁሉን ታሰግጂለታለሽ፣ እርሱም ለአንቺ ይሰግዳል:: " በማለት ዘምሯል።

ሊቃውንቱ ይህን እየወረቡ ቀሳውስቱ የእመቤታችንን ሥዕልና የቅዱስ ጊዮርጊስን ሥዕል ይዘው ይዞራሉ፤

ይኸውም ስደቷን ለማዘከር እንዲሁም የኢትዮጵያን መልክአ ምድር ዞራ መጎብኘቷንና ሀገሪቱን በቃል ኪዳን መረከቧን ለማሰብ ነው፤

የጊዮርጊስ ሥዕል አብሮ መዞሩ ስለሦስት ምክንያት ነው

#የመጀመሪያው-ምክንያት

ከላይ ለመግለጥ እንደተሞከረው እመቤታችን በስደቷ ወራት የኢትዮጵያ ባለአደራ ሆና እንደተሰጠች ቅዱስ ጊዮርጊስም የኢትዮጵያ ጠባቂ ሆኖ ተሰጥቷል፡፡ ስለዚህ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ጥምር ምሥጢር ለማዘከር የጊዮርጊስን ሥዕል ከእመቤታችን ሥዕል ጋር ይዛ ሥርዓተ ዑደት ታከናውናለች።

#ሁለተኛው_ምክንያት

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት ሲኾን ሰማዕትነት ደግሞ እሳትና ስለት ብቻ አይደለም፤ ስደትም ሰማዕትነት ነው እሞሙ ለሰማዕት›› የተባለች እመቤታችን ሰማዕትነትን ባርካ ለሰማዕታት አለቃ ለቅዱስ ጊዮርጊስ እንደሰጠችው ለማስረዳት ነው፡፡

#ሦስተኛው_ምክንያት

ቅዱስ ጊዮርጊስ ለእመቤታችን ካለው ልዩ ፍቅርና አክብሮት የተነሣ
‹ደምርኒ ፍልሰትየ ምስለ ፍልሰትኪ ፍልስቴን ከፍስስትሽ ጋር ደምሪልኝ::› ብሎ ተማፅኗት ነበርና፤

ይኸውም አልቀረም የቅዱስ ጊዮርጊስ ፍልሰተ ዐፅሙ እመቤታችን ከሞት ተነሥታ ከመቃብር በፈለሰችበት በነሐሴ ፲፮ ቀን አብሮ ይከበራል፡፡

ይህ ከሥዕሉ ጋር ምን ያገናኘዋል ያልን እንደኾነ

ፍልሰት የሚለው ቃል ብዙ ትርጉም ያለው ቃል ነው፤ ፈለሰ ተሰደደ ተንከራተተ ሀገር ጥሎ ቁርበት ጠቅልሎ ሄደ ማለት ነው ፍልሰቴን ከፍልስትሽ ጋር ደምሪልኝ ማለቱ ስደቴን ከስደትሽ መከራዬን ከመከራሽ ጋር ደምሪልኝ ማለቱ ነው፤

ይህን ምሥጢር የተረዳች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዘመነ ጽጌ የሰማዕቱን መከራና ስደት ከእመቤታችን መከራና ስደት ጋር ታስባለች።

#ባሕረ_ጥበባት_ቅዱስ_ያሬድ -

"አእሚረ ጊዮርጊስ ንጽሐ ሥጋሃ ሊቀ ሰማዕታት ሰገደ ላቲ ወአምኃ ለንግሥተ ሰማይ፤ ወይቤላ ጊዮርጊስ ለማርያም ደምርኒ እም ከመ ኅቡረ ንባዕ ሠናየ ገድለ ተጋደሉ፡፡ "

"የሰማዕታት አለቃ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለሰማይ ንግሥት ለእመቤታችን ንጽሕናዋን አውቆ እጅ በመንሣት ሰገደላት ጊዮርጊስ ማርያምን እንዲህ አላት እናት ሆይ በአንድነት እንገባ ዘንድ ከገድል ከትሩፋትሽ አንድ አድርጊኝ አላት፥ መልካም ገድልንም ተጋደለ።»

በማለት ከላይ የተገለጠውን ኀይለ ቃል ይበልጥ አጉልቶ አምልቶ ይነግረናል።

ይቆየን.....

💐💐💐💐

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

26 Oct, 16:20


ማኅሌተ ጽጌ

ክፍል ፩

እንዘ ተሐቅፊዮና ክበበ ጌራ ወርቅ ሲባል

መዞሩ ምሥጢሩ ምንድ ነው?

ማኅሌተ ጽጌ በሚቆምበት ጊዜ “እንዘ ተሐቅፊዮና ክዘበ ጌራ ወርቅ ሲባል የሚዞርበት ምሥጢሩ በጽጌ ማሕሌት ጊዜ የሚባሉ ብዙ ወረቦች ነበሩ ለሥርዓተ ዑደቱ እነዚህ ወረቦች ለምን ተመረጡ ስንል በመጀመሪያ እነዚህ ሁለት ወረቦች ሁሉንም ምሥጢር ያስተባበረ መልእክት ስላላቸው ነው፤

ይኸውም "እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፥ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፥ ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ፥ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፥ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ፡፡"

🌹🌸🌹🌸🌹🌸🌹🌸🌹🌸🌹🌸🌹🌸🌹🌸

ነጭና ቀይ መልክ ያለው አበባ ልጅሽን ይዘሽ ወደ ቤተ መቅደስ #ዕለተ_ንጽሕ ተብሎ በሙሴ እንደተጻፈው በወለድሽ በ፵ ቀን ወደ ቤተ መቅደስ እንደ ገባሽ ርግቤ ሆይ ከኀዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነዪ፤ አዛኝቱ ድንግል ሆይ! ደስተኛ ከሆነው ከገብርኤልና እንደ አንቺ ሩኅሩኅ ከሆነው ከቅዱስ ሚካኤል ጋር ነዪ።»

በማለት ፀዓዳ በመለኮቱ ወቀይሕ በትስብእቱ የሚባል ልጇን ታቅፋ ወደ ቤተ መቅደስ እንደገባች ወደ ልቡናዬ ግቢ ከኀዘኔም አረጋጊኝ ብሎ ይማፀናል።

ሊቁ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤

ነጭና ቀይ የኾነ አበባ ልጅሽን ታቅፈሽ ሲል

መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ይዞ ነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነጭና በቀይ ይመሰላል፡፡ መፍቀሬ ጥበብ ሰሎሞን ከመዝሙራት በሚበልጥ መዝሙሩ ላይ "ወልድ እኁየ ጸዐዳ ወቀይሕ፤ ውዴ ነጭና ቀይ ነው... ከእልፍ የተመረጠ ነው" መሐ 5÷10 ብሎ ከዘመረው መዝሙር ወስዶ ነው፡፡

ይኸውም ነጭ የድል አድራጊነት ምልክት ሲሆን ቀይ የመሥዋዕትነት ምሳሌ ነው፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በከፈለው መሥዋዕትነት አዳምንና ልጆቹን ከሞት ባርነት አድኗል፤ ዲያብሎስንና ሠራዊቱን ድል አድርጓልና፡፡ ነጭ የመለኮቱ ቀይ የትስብእቱ ምሳሌ ነው፡፡ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተለየ አካሉ ሰው ሆኗልና፡፡

ደስተኛ ከሆነው ከገብርኤል ጋር ነዪ››

ማለቱ ገብርኤል ደስተኛ የሆነው በምን ምክንያት ነው? ያሉ እንደሆነ እርሷን ያበሥር ዘንድ በተላከ ጊዜ ራሱን ከመላአክት መካከል እንደ ዕድለኛ በመቁጠር እጅግ ተደስቶ ነበርና፡፡

ይህንን #ሊቁ_ቅዱስ_ኤፍሬም

"ዐቢይ ውእቱ ክብር ዘተውኅበ ለከ ኦ ገብርኤል መልአክ ዜናዊ ፍሡሐ ገጽ ሰበከ ለነ ልደተ እግዚእ ዘመጽእ ኀቤነ፤ ወአብሠርካ ለማርያም ድንግል ዘእንበለ ርስሐት ወትቤላ ተፈስሒ ኦ ምልዕተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ::"

ደስተኛ ሆነህ የምሥራችን የተናገርክ መልአኩ ገብርኤል ሆይ ለአንተ የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው፤ ወደ እኛ የመጣ የጌታን ልደቱን ነገርከን ለድንግል ማርያም ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ናውና ደስ ይበልሽ ብለህ አበሠርካት።››   ብሎ ገልጾታል።

ቅዱስ ገብርኤል መጋቤ ብሥራቷ መሆኑ ለእርሱ ትልቅ ክብር ነውና፡፡

እንደ_አንቺ_ርኅሩኅ ከሆነው ከሚካኤል ጋር ነዪ ማለቱ ደግሞ ቅዱስ ሚካኤል #ለሰው_ልጅ_በመራራት ይመስላታልና ነው፡፡

ይቆየን...

ክፍል ፪ን ማታ ከ፫ ሰዓት በኋላ የምንለቅ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን።

💐💐💐💐

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

26 Oct, 08:52


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
    🌹🌹🌹ሥርዓተ ማኅሌት🌹🌹🌹
        🌹🌹ዘማኅሌተ ፅጌ🌹🌹
         🌹የአራተኛ   ሳምንት🌹

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

26 Oct, 06:49


🌹🌿🌹🌿🌿🌹🌹🌿🌹🌿🌿🌹🌹
"ከገነት በተሰደደ ጊዜ ለአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ ። በግፍ የተገደለ የአቤል የውሃቱ አንቺ ነሽ ። የሴት ቸርነት አንቺ ነሽ ። የሄኖክም ሥራዎቹ ከክፉ ጥፋት የዳነባት ። የኖህ መርከብ ፣ የሴም ቡራኬ ዕድል ፈንታውም አንቺ ነሽ ።የአብርሃም እንግድነት የያዕቆብ መሰላል አንቺ ነሽ ። ዮሴፍን የምታረጋጊው አንቺ ነሽ ።፤ የሙሴ ጽላት ጳጦስ የተባለች የሲና ዕፅ በካህን አሮን ልብስ የነበረች ጸናጽል ዳግመኛም የበቀለችና ያበበች ያፈራችም በትር አንቺ ነሽ ። ፤ የእያሱ የምስክሩ ሐውልት ፣ የጌድዮን ፀምር ፣ የሳሙኤል የሽቱ ሙዳይና የዘይት ቀንድ አንቺ ነሽ ። የተመካባት የዕሴይ ሥር የአሚናባድም ሠረገላ የዳዊት መሰንቆ የሰለሞንም አክሊል አንቺ ነሽ ። የታጠረች ተክል የተዘረጋች የውኃ ጉድጓድ አንቺ ነሽ ።"
     ቅዳሴ ማርያም

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ወርሐዊ መታሰቢያ አደረሰን!