ፕሮቴስታንት መዝሙር @perotestantworship Channel on Telegram

ፕሮቴስታንት መዝሙር

@perotestantworship


እግዚአብሔር መልካም ነው በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃቸዋል

ፕሮቴስታንት መዝሙር (Amharic)

የፕሮቴስተንት መዝሙር በሚለው መረጃ እንደፕሮቴስቲንት መዝሙር በአማርኛ ለማከናወን የሚገባን በደግሞ ሁሉም የወንጌል ተይዞ በጥንቃቄ ወስኖአል። ይህ መዝሙር ከሚባለው ሆኗው በተከታታይ ማህበረሰብ እየተገኘን ነው። ፕሮቴስተንት መዝሙር፥ እንዴት እንደሚለዌው በመቀነስ የሆነውን ፕሮቴስተንት መዝሙር ማየት እንችላለን? ሰለባለም በሁሉም ውጤት ተወዳጅ መጀመሪያ በነበሩት በእኛ ምላሽ አጠገብ ላይ ነገር አሁን አብሦላል። ስለዚህ የፕሮቴስተንት መዝሙር ለማስተማር በመጨረሻ በልዩ አዘጋጅቶ ሁኔታዎችን ፈቃድ ካልሰጠ አንዱ ሊኖራቸው ይችላል። ፕሮቴስትተንት መዝሙር ስለሆነ በቻይናል መርጠኛና ብቻዊ ክምት ችግር።

ፕሮቴስታንት መዝሙር

28 Dec, 06:20


https://t.me/stelotlegeta

ፕሮቴስታንት መዝሙር

28 Dec, 06:16


እስከ መጨረሻው አንብቡት😭

ይሄ ቤተክርስቲያን በምዕራብ ጉጅ ዞን በቡሌ ሆራ ወረዳ በደጎ ሶዱ ቀበለ ውስጥ የምትገኝ የደራርቱ አጥቢያ ቃል ህይወት ስሆን ከዚህ በፊት በ2010ዓ.ም በነበረው በጉጅ እና በጌድኦ ብሄረሰብ  እርስ በርስ ጦርነት ሙሉ በሙሉ ፈርሶ፤ የቤተ ክርስቲያን ንብረት  በሙሉ ተዘርፎ ፤ ህዝቦቿ ተበትሎ፤ እንዳልነበረች ሆናለች።

ጦርነቱ አብቅቶ ዛሬ 7አመታትን ብያስቆጥርም ፤ማንም ዞር ብሎ አያላቸው ፤ የጠየቁ፤ እንዲሁም ድጋፍ ያደረጉ የመንግስት አካል አልበረም፤ ከጦርነት ጫናም ጭምር የነበራቸው አቅም ውስን ስለነበረ መልሶ የአምልኮን አደራሻ ስላልቻሉ፤ ተበታትኖ የነበሩ ምዕመናን ጥቅቶቹ ተመልሶ በውጭ ሳር ላይ ቁጭ እያመለኩ ይገኛሉ።😭  ዛሬ ላይ እንዳደገና  ከ7አመት ቆይታ በኋላ መታሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጅቶ
አባቶችና እናቶች በዕንባና በፀሎት ቆይቶ አሁን ያንን የአምልኮ አደራሽ መልሶ ለመስራት ሰዎችን እርዳታ እየጠየቁ ይገኛሉ፤  ምናልባት በልባችሁ ውስጥ  የእግዚአብሔር ትንሽ ፍቅር እንዲሁም የትውልድና የቤተክርስትያን ሸክም የምሰማችሁ ፤የቤቱ ቅናት ያላችሁ በሀገር ውስጥ እና ከአገር ውጭ የምትኖሩ ቅዱሳን
ማንም ባያያችሁም እግዚአብሔር ያያችሃል፤  ማንም ባያመሰግናችሁ እግዚአብሔር ብድራቱ እመልስላችኃል ።

1 ቆርቆሮ መግዛት ትልቅ ዋጋ አለው።
በዚህ ቤት ክርስቲያን ጎን በመቆም፤ በፀሎትና  ያቅማችሁ ያህል ድጋፍ በማድረግ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ መልካም አሻራችሁን እንድታሳርፉ፤ ለበጎ ሥራ እንድትረባረቡ፤በእግዚአብሔር ፍቅር ላሳስባችሁ እወዳለሁ፤

“ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥”
  — ቆላስይስ 3፥23

ወንድማችሁ አገልጋይ አቡካ ዶር ነኝ
ለዚህ ቤተክርስቲያን ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉት በዚህ ይደውሉ
📞 0945631515
1000226469919 CBE

ፕሮቴስታንት መዝሙር

08 Dec, 11:26


እንጸልይ ለጌታ በአንድነት

https://t.me/stelotlegeta

ፕሮቴስታንት መዝሙር

23 Nov, 10:04


" ለጥቂት ጊዜ"
ፓ/ር ታምራት ሀይሌ

ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን
ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን
በ ማላኪቲ አጃቢ በ እግዛኢያቢሀር ማላካቲ
ኢየሱስ ፡ ይመጣል ፡ ከላይ ፡ ከሰማያት
የአባቴ ፡ ብሩካን ፡ ኑ ፡ እረፉ ፡ ይለናል
እንደ ፡ ድካማችን ፡ ዋጋ ፡ ይከፍለናል
ተስፋ ፡ እንደሌላችሁ ፡ ፈጽሞ ፡ አትዘኑ
እርስ ፡ በእርሳችሁም ፡ በዚህ ፡ ቃል ፡ ተጽናኑ

ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን
ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን

በጌታ ፡ የሞቱ ፡ ቀድመው ፡ ይነሳሉ
ሰማያዊ ፡ አካል ፡ ፈጥነው ፡ ይለብሳሉ
እኛ ፡ ሕያዋን ፡ እንለወጣለን
አብረን ፡ በደመና ፡ እንነጠቃለን
ተስፋ ፡ እንደሌላችሁ ፡ ፈጽሞ ፡ አትዘኑ
እርስ ፡ በእርሳችሁም ፡ በዚህ ፡ ቃል ፡ ተጽናኑ

ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን
ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን

ዓለም ፡ በክፋቷ ፡ እየባሰች ፡ ሄደች
ሕያዋንን ፡ አልፋ ፡ በድን ፡ አሳደደች
አዲስ ፡ ነገር ፡ የለም ፡ ነው ፡ እንደተጻፈው
በክርስቶስ ፡ ትዕግስት ፡ ሁሉን ፡ እንለፈው
የሚረዳን ፡ ጸጋ ፡ ጌታ ፡ ይሰጠናል
ኋላም ፡ በመምጣቱ ፡ በክብር ፡ ይገልጠናል

ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን
ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን

ጌታ ፡ የሚዘገይ ፡ መስሎ ፡ ቢታያቸው
በዚህ ፡ ዓለም ፡ አምላክ ፡ ታውሮ ፡ ዐይናቸው
እንደ ፡ ተስፋ ፡ ቃሉ ፡ አይዘገይም ፡ በእውነት
እንደ ፡ ሌባ ፡ ሆኖ ፡ ይመጣል ፡ በድንገት
የወጉት ፡ ያዩታል ፡ በዘውድ ፡ አሸብርቆ
በግርማው ፡ ሲገለጥ ፡ ከከዋክብት ፡ ደምቆ

ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን
ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን

ነቀፋና ፡ ስድብ ፡ ስደትና ፡ ዛቻ
የጠላት ፡ ተግዳሮት ፡ የዘመድ ፡ ጥላቻ
እጦትና ፡ ህመም ፡ ሃዘንና ፡ እሮሮ
ያለው ፡ የሚመጣው ፡ ሁሉም ፡ ተደምሮ
ይገለጥ ፡ ዘንድ ፡ ካለው ፡ ሰማያዊ ፡ ክብር
ያሁን ፡ ዘመን ፡ ስቃይ ፡ አይወዳደር

ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን
ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን
 
🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
  @ye_Protestant_mezemur
  @ye_Protestant_mezemur
   ─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───

ፕሮቴስታንት መዝሙር

23 Nov, 10:04


.                  "ትወደኛለህ"
                  
               ዘማሪ ሳሙኤል ንጉሴ
             
   🎧𝑵𝒆𝒘 𝑨𝒎𝒂𝒛𝒊𝒏𝒈 𝑮𝒐𝒔𝒑𝒆𝒍 𝒔𝒐𝒏𝒈🎧

ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ
🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼

ፕሮቴስታንት መዝሙር

18 Oct, 15:42


.         "የእግዚአብሔር እጅ"
              
          ዘማሪት ራሔልአለማየሁ
     
    🎧𝑨𝒎𝒂𝒛𝒊𝒏𝒈 𝑳𝒊𝒗𝒆 𝑾𝒐𝒓𝒔𝒉𝒊𝒑🎧
   
  🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
  

ፕሮቴስታንት መዝሙር

18 Oct, 15:42


.           "የእግዚአብሔር እጅ"
              
          ዘማሪት ራሔልአለማየሁ
     
    🔸𝑨𝒎𝒂𝒛𝒊𝒏𝒈 𝑳𝒊𝒗𝒆 𝑾𝒐𝒓𝒔𝒉𝒊𝒑🔸
   
  🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
  @ye_Protestant_mezemur
  @ye_Protestant_mezemur
   ─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───

ፕሮቴስታንት መዝሙር

01 Oct, 15:09


"አትለዋወጥም"
ዘማሪት መስከረም ጌቱ

አንተ የዘመናት አምላክ ያው አንተ ነህ
አንተ አትለዋወጥም ያው አንተ ነህ
አንተ እኔ እኔ ነኝ ያልህ ያው አንተ ነህ
አንተ ትላንትናም ዛሬም ያው አንተ ነህ

የማትለዋወጥ አንተ ብቻ
ዘመን የማይሽርህ አንተ ብቻ
የነበርህ ያለህ አንተ ብቻ
ዙፋንህ የፀና አንተ ብቻ

ክበር ክበርልን ንገስ ንገስ
ሙሉ መስዋዕታችን ላንተ ይፍሰስ(2*)

ዓለም ተለዋዋጭ ሁሉ
ከፍ ያለው ዝቅ ሲል የነበረው ሲቀር
ፍሰቱን ጠብቆ ሁሉ ሲተካካ
አንተ ጸንተህ ኗሪ ምንም አትነካ

አንተ የዘመናት አምላክ ያው አንተ ነህ
አንተ አትለዋወጥም ያው አንተ ነህ
አንተ እኔ እኔ ነኝ ያልህ ያው አንተ ነህ
አንተ ትላንትናም ዛሬም ያው አንተ ነህ

ብርቱዎች ስደክሙ ደካሞች ሲገዙ
ሽማግሌው ሲያልፍ ሲያረጅ ጎበዙ
እውቀትም ሲሻሻል ስልጣኔም ሲሻል
አንተ ለዘላለም ተረጋግተህ ምትኖር

አንተ የዘመናት አምላክ ያው አንተ ነህ
አንተ አትለዋወጥም ያው አንተ ነህ
አንተ እኔ እኔ ነኝ ያልህ ያው አንተ ነህ
አንተ ትላንትናም ዛሬም ያው አንተ ነህ

የማትለዋወጥ አንተ ብቻ
ዘመን የማይሽርህ አንተ ብቻ
የነበርህ ያለህ አንተ ብቻ
ዙፋንህ የፀና አንተ ብቻ

ክበር ክበርልን ንገስ ንገስ
ሙሉ መስዋዕታችን ላንተ ይፍሰስ(6*)

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@ye_Protestant_mezemur
@ye_Protestant_mezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───

ፕሮቴስታንት መዝሙር

29 Dec, 16:11


. "ነፍሴ የምትወድህ"
ዘማሪት ፍሬህይወት አበባው


ኢየሱስ ያለህበት ሰላሜ ያለበት(4*)
አንተ የዋልክበት ደስታዬ ያለበት(2*)
አንተ የከበርክበት ስኬቴ ያለበት(2*)
የተጠራህበት መድሃኒቴ ያለበት(2*)

ነፍሴ የምትወድህ ሆይ
ሁሉም ይቅርና አንተ ዋል ከቤቴ ×፪
ነፍሴ የምትናፍቅህ ሆይ
ሌላው ይቅርና ብቻ ዋል ከቤቴ ×፪

የምፈልገው አንተን ነው
ሁሌ የምመኘው አንተን ነው
እኔ የሚመቸኝ ቤትህ ነው
የምታስፈልገኝ አንተ ነህ

ፈልጌ አይደለም ከእጅህ አንድ ጉርሻ
እንድንዘልቅ እንጂ እስከ መጨረሻ
ከአንተ ጋር አኑረኝ ይሄ ነው ፀሎቴ
ቢከፋኝ ቢደላኝ እግርህ ስር ነው ቤቴ

ነፍሴ የምትወድህ ሆይ
ሁሉም ይቅርና አንተ ዋል ከቤቴ ×፪
ነፍሴ የምትናፍቅህ ሆይ
ሌላው ይቅርና ብቻ ዋል ከቤቴ ×፪

የምፈልገው አንተን ነው
ሁሌ የምመኘው አንተን ነው
እኔ የሚመቸኝ ቤትህ ነው
የምታስፈልገኝ አንተ ነህ

በመንፈስህ ልስከር ሙላኝ በየእለቱ
ከአንተም አልነጠል ላፍቅርህ በብርቱ
በድንግዝግዝ አልኑር አይኖቼን አብራልኝ
ጌታ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን አስተምረኝ

ነፍሴ የምትወድህ ሆይ
ሁሉም ይቅርና አንተ ዋል ከቤቴ ×፪
ነፍሴ የምትናፍቅህ ሆይ
ሌላው ይቅርና ብቻ ዋል ከቤቴ ×፪

የምፈልገው አንተን ነው
ሁሌ የምመኘው አንተን ነው
እኔ የሚመቸኝ ቤትህ ነው
የምታስፈልገኝ አንተ ነህ


በምትሰራበት ቀን እንዳልሆን እንግዳ
በሩቁ አጨብጫቢ ታዛቢ እንደ ባዳ
ከእግርህ ስር ቁጭ ብዬ ልማርህ እሻለሁ
የልብህን ሃሳብ ፈቃድህን እንዳውቀው
share♻️share♻️share♻️

🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣👇 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼

ፕሮቴስታንት መዝሙር

29 Dec, 15:26


. "ተመስገን"
ዘማሪ ፓ/ር እንዳለ ወ/ጎርጊስ


ተመስገን የልቤ ፈውስ
የልቤ ጠጋኝ (፬x)

ክብር ይሁን የማጽናናትህ ደመና
ክብር ይሁን ዙራዬን ከቦታልና
ክብር ይሁን ሚያቋርጥ አይደል ደስታዬ
ክብር ይሁን ምንጩ አንተ ነህ ጌታዬ

የልቤ ጉልበት ይንበረከካል
ገብተህ ላከምከው ክብር ይሰጣል
ክብር ይሁንልህ (፪x)

ክብር ይሁንልህ (፬x)

እሩቅ ነው መንገዱ ይለቤ አድራሻ
ሰው አይደርስበትም ይቆማል ውጪው ጋር (፪x)

ልቤ ቢቆስልብኝ አካሚው አንተ ነህ
ከደጅ የማትቆም የምትገባ ዘልቀህ
ከደጅ የማትቆም የምትገባ ዘልቀህ
ክብር ይሁንልህ (፬x)

ማን አለኝ (፪x)
ከፊቴ እያለፈ የልቤን የሚረዳ
ዘልቆስ የሚጐበኝ የመንፈሴን ጓዳ
አንተ ብቻ ነህ ለልቤ መክፈቻ ያለህ
አንተ ብቻ ነህ ለውስጤ መክፈቻ ያለህ

ክብር ይሁን የማጽናናትህ ደመና
ክብር ይሁን ዙራዬን ከቦታልና
ክብር ይሁን ሚያቋርጥ አይደል ደስታዬ
ክብር ይሁን ምንጩ አንተ ነህ ጌታዬ

የልቤ ጉልበት ይንበረከካል
ገብተህ ላከምከው ክብር ይሰጣል
ክብር ይሁንልህ (፪x)

ክብር ይሁንልህ (፬x)
share♻️share♻️share♻️

🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣👇 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼

ፕሮቴስታንት መዝሙር

27 Dec, 16:28


.      "አልተስማማም ሰማይ"
        
   ዘማሪ ብርሃነመስቀል ወ/መድን
   
🔸  𝑵𝒆𝒘 𝑨𝒎𝒂𝒛𝒊𝒏𝒈 𝑮𝒐𝒔𝒑𝒆𝒍 𝒔𝒐𝒏𝒈  🔸

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼

ፕሮቴስታንት መዝሙር

25 Dec, 15:33


ሰላም ቤተሠቦቼ ለመደበሪያ ያክል የፊልም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

ፕሮቴስታንት መዝሙር

22 Dec, 17:35


ሠላም ወደ ቻናላችን ተመልሠናል እናመሠግናለን like. share. subscriber እንዳይረሳ👍👍👍

2,549

subscribers

22

photos

58

videos