❣Strong girl's❣ @strong_grlis Channel on Telegram

Strong girl's

@strong_grlis




በህይወትሽ ውስጥ ለሚፈጠር ለማንኛውም ነገር ሀላፊነት የሚሰማሽ ሴት ሁኚ..ነገሮችን ሁሉ ስታደርጊ ልክ ባትሆኚ እንኳን ሁለት ጊዜ አስቢበት እና ደሞ ነገሮችን ለመቻልም ቻይ....!!


@strong_grlis

For any
comment &
cross
@tsi_ad0

❣Strong girl's❣ (Amharic)

ማንበብሽ ነገር የሁሉም ሴት ሀላፊነትን ሲያስታወቅ ማድረግና ለሚፈጠር ነገር በህይወትሽ ውስጥ እንደሚሆን የስታደርጊ ልክን እና ሁኚ አስቢበተው ሲሆን ሁለት ጊዜ ውላትን አጽናንቶ ማድረግም ስለሚያደርግ እና ደሞ ቻይን ለመቻል ወደ @strong_grlis ላይ ያለውን መረጃ በነገራችን ማከታተል ቻይኑን ለመረጋጋ በማድረግ ነው። ይህ ስለሆነ፣ ሁልጊዜ አዲሱን ነገርን ያቀረብከው እና በስልካችሁ የሚታወቀውን እና ነገሩን ለማከብር የጠቃሽ እና የተሃላ መረጃዎች ቻይኑን እንደሚገኝ እና መዝገብ የሚያስፈልግ እና መረጃሽን ወደ በለይ ተመልክቶናል። እናንተም ፍቅርን ለማከበረት አገርም አገራችሁም በሚታወቃቸው መንገዶች ላይ የተንቀሳገለ እና ተግባራችሁን ለማስገባት በማንኛውም አስተዳደር ቢያሳየም እና እናንተን ገና ባለ።

Strong girl's

25 Jan, 13:51


እባብ ብልህነቱ መደበቁ ነው!🐍
የተገለጠ ነገር ለመገመትም ለመሸነፍም ቅርብ ነው። አዳኝ የሚያድነውን ነገር ማግኘቱን ኢላማውን እስኪያረጋግጥ ድረስ ተደብቆ ድምፅ ሳያሰማ በቀስታ ነው የሚቀርበው። ልክ የሚያድነውን መቶ ሲጥለው ነው ሚገለጠው። ግን ከመምታቱ በፊት ቢወጣ ኖሮ የሚያድነው ያመልጠዋል ወይም ይበላል!!! ብልህ ያተኮረበትን ነገር ሳይጨርስ አይወጣም። ለጠላትሽ እንዴት ልታጠቂው እንዳሰብሽ አትነግሪውም። ምክንያቱም ነገርሽው ማለት ብዛ መንገድ ልታጠቃኝ ትችላለህ ማለትሽ ነው!

የኔ ቆንጆ እባብ ብልህነቱ መደበቁ ላይ ነው። በቀላሉ እራሱን ለአደጋ አያጋልጥም። እንዴት መደበቅ እንዳለበት ያውቃል። መቼ መውጣት እንዳለበትም ያውቃል። ጊዜን ጠንቅቆ ማወቁ ነው ብልህ ያስባለው። ማንነቱን ከጊዜ ጋር ማስማማቱ!

አዎ! የኔ ልባም ሴት...!አንቺም ልክ እንደ እባብ ብልህ ሁኚ። የምትፈልጊውን የምታልሚውን ነገር ለማሳካት ተደበቂ። ህልምሽን ማንም ሳያቅ ማንም ሳይሰማ ተደብቀሽ ስሪ። ስላንቺ ውጤትሽ ብቻ ይናገር። አንቺ ዝም በይ። ሁሌም ቢሆን አንድ ነገር አስታውሺ! ማንም ምን እየሰራሽ እንደሆነ ማወቅ የለበትም። ምክንያቱም ማንም እያጠናሁ ነው ወይም እየሰራሁ ነው ብትይዉ ኦ በርቺ ጀግኒት አይልሽም። ባክሽ በኋላ ትሰሪያለሽ አሁን ነይ ይሄን እንስራ፣ እዚህ እንሂድ ብሎ ሰዓትሽን ነው የሚያቃጥለው። ለዚህ ነው መደበቅ ያለብሽ! ብልጥ ካልሆንሽ የፈለግሽበት መድረስ አትችይም። ወይኔ እንደዚ ሳላደርግ ይሄንን ሳላጠና ብለው ሲሞሉሽ አትመኛያቸው። እነርሱ ለሊቱን ቁጭ ብለው አድረው ምናልባትም የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ሰርተው ጨርሰው ነው ያንቺን ጊዜ ለማቃጠል እና ለማዘናጋት እንደዛ ያሉሽ። አትሸወጂ በዚህ ምድር ላይ ማንም መበለጥ እና መሸነፍ አይፈልገ። የጌሙን አጨዋወት ካላወቅሽ ደግሞ ሁሌም ተሸናፊ ነው የምትሆኚው። አሸናፊ መሆን ከፈለግሽ አጨዋወቱን አጥኚ። የተደበቀ ነው ሁሌም የሚያሸንፈው። በዚህ ምድር ላይ ጠላትሽን እና ወዳጅሽን መለየት በጣም ከባድ ነው። ግን አንድ ነገር አስተዉዪ። ጠላትሽ ምን እያደረግሽ እንደሆነ፣ ምን እንዳቀድሽ፣ ቀጣዩ እንቅስቃሴሽ ምን እንደሆነ ካወቀ ብቻ ነው ሊያጠቃሽ እድሉን የሚያገኘው! ስላንቺ ምንም ነገር ካላወቀ ግን ግራ ይጋባል። ለዚህ ነው ሁሌም ቢሆን ስላንቺ ውጤትሽ ብቻ መናገር ያለበት። ተደበቂ እና ግራ አጋባያቸው ልክ እንደ እባብ!
በርቺልኝ!!!





@ElBethelofficial
@ElBethelofficial

Strong girl's

22 Jan, 21:56


ተማሪ ነህ ?

Strong girl's

22 Jan, 21:47


🙏🙏ወላሂ ለአዚም አላህ ሻሂዴ ነው  ይሄን ቻናል ተቀላቅዬ ከድህነት ወጥቻለው እናንተም ተጠቀሙበት betting ምትጫወቱ  الوالد لأخيم الله شهيد ، انضممت إلى هذه القناة وخرجت من الفقر واستخدمته
https://t.me/+ED9zMzdrkhliZGE0
https://t.me/+ED9zMzdrkhliZGE0
https://t.me/+ED9zMzdrkhliZGE0

Strong girl's

19 Jan, 14:48


ግልፅ የሆነ...
...የራስሽ ፍላጎት ይኑርሽ!💐
ማንም እንደፈለገ የማያደርጋት በምታየው ነገር የማትወሰድ የማይናወጥ መሰረት ያላት ታላቅ ሴት መሆን ከፈለግሽ በህይወትሽ ውስጥ ግልፅ የሆነ የራስሽ ፍላጎት ሊኖርሽ ይገባል። መጀመሪያ ማወቅ ያለብሽ <ምንድነው የምፈልገው> የሚለውን ነው።
ግልፅ የሆነ ፍላጎት ያላት ሴት ማንም መቶ እንደፈለገ ሊያደርጋት አይችልም! የምትፈልገውን፣ የምታስበውን፣ የምታልመውን፣ የምትወደውን፣ የምትጠላውን፣ የሚያስደስታትን፣ የማያስደስታትን በአጠቃላይ ሁሉንም በእራሷ ማንነት ልክ ስለምታውቅ ማንም የራሱን ነገር ሊጭንባት አይችልም። አቋም ያላት ሴት ነች። የማትፈልገውን አልፈልግም ያልወደደችውን አልወደድኩትም ማለትን ታውቃለች! የመሰላትን ለመናገርም ሆነ ለማድረግ ሼም አይዛትም። እሷ ያረገችውን ነገር እሷ እስከወደደችው ድረስ ማንም ያስጠላል አያምርም ስላለ ማድረጓን አታቆምም። ውይ ይሄኮ አያምርብሽም ስትባል እኔ ግን ወድጄዋለሁ ብላ ዝም የምታስብል እንጂ በተሰጣት comment ብቻ የወደደችውን ነገር የምትተው አይደለችም። ጠንካራ መሰረት ያላት ሴት ነች። የራስዋ style አላት። ሰው ያደረገውን copy ማድረግ አይመቻትም። ልዩ መሆን ያስደስታታል። አዲስ ነገር ፈጣሪ ነች። ይሄ ደግሞ ሌላኛው ውበትዋ ነው።

የኔ ቆንጆ የራስሽ የሆነ ግልፅ ፍላጎት ከሌለሽ ማንም እንደፈለገ የሚያሽከረክርሽ አሻንጉሊት ነው የምትሆኚው! Even if ወንድ እንኳን የላይኛው ዉበትሽን ብቻ ነው አይቶ የሚመጣው። ለስጋዊው ስሜቱ ፈልጉሽ ብቻ! ምክንያቱም ከዚህ ለበለጠ ነገር እንዲያስብሽ የሚያደርግ ማንነት አይኖርሽም። ውበትሽን በገንዘቡ ገዝቶ ያገባሻል ቆንጆ ሚስት አለው እንዲባል ከዛም ወዲያው ትወልጂያለሽ ቤቱ አሳስሮ ያስቀምጥሻል። ምክንያቱም አስተዉዪ ማንም ሰው ቤቱ ውስጥ ቆንጆ ውሻ ወይም ድመት እንዲኖረው ይፈልጋል። ሰው ቤቱ ሲመጣ ውይ ሲያምር የሚያስብል የሚያስደንቅ ነገር ይፈልጋል። አንቺም ግልፅ የሆነ የራስሽ ፍላጎት የለሽም ማለት ህይወትሽ ልክ እንደዚ የተገዛ ነው የሚሆነው። ነገር ግን በህይወትሽ የራስሽ የሆነ ግልፅ ፍላጎት አለሽ ማለት ወንድ እንኳን አንቺን አይቶ ስለ አንድ ቀን አዳር ሳይሆን ስለወደፊት አንድ ስለሚያደርጋችሁ ዓላማ እንዲያስብ ታደርጊዋለሽ። ርካሽ እቃ ነው ሲታይ ይሄንማ ገዛዋለው የሚል ስሜትን የሚፈጥረው። ውድ እቃ ግን በቂ ገንዘብ ይኖረኝ ይሆን የሚል ጥርጣሬን ነው የሚፈጥረው! አየሽ አንቺም በዛ ልክ ስትሆኚ የትኛውም ወንድ ሲያይሽ ሊያጠምድሽ ሳይሆን የሚያስበው አንቺን ለማግኘት ምን ያህል ብቁ እንደሆነ ነው የሚያስበው። እመጥናት ይሆን ብሎ እራሱን እንዲፈትሽ ታደርጊዋለሽ። ለተራ ነገር እንዳይፈልግሽ እና እንዳያስብሽ ታደርጊዋለሽ።

አዎ! የኔ ልባም ሴት...! ግልፅ የሆነ የራስሽ ፍላጎት ይኑርሽ! በፍፁም ማንም እንደፈለገ የማያደርግሽ ይሄ እኮ ያምርብሻል ካንቺ ጋር ይሄዳል ሲሉሽ እኔ ይህንን ነው የምፈልገው ብለሽ የምትፈልጊውን ለመናገር የማትፈሪ የራስሽን ማንነት፣ ውበት፣ አስተሳሰብ የምታጎዪ እንጂ የሌሎችን የማታስመስዪ ጠንካራ ማንነት ያለሽ ሴት ሁኚ። ያኔ ሁሌም ቢሆን ማሸነፍ ላንቺ ከባድ አይሆንም። እግዚአብሔር ልዩ አድርጎ የፈጠረሽ ልዩ ሆነሽ እንድትኖሪ ነው። ስለዚህ ልዩነትሽን ጠብቂው። የሌሎች ልዩነት ስላማረሽ ከእነርሱ ኮርጀሽ ለመመሳሰል የምትጥሪ ሳትሆኚ የእነርሱን አድንቀሽ አንቺም በራስሽ ልዩነት ልዩ የሆነ የሚደነቅ ማንነት የምትፈጥሪ የማይነካ ግልፅ የሆነ ፍላጎት ያለሽ ልዩ ሴት ሁኚ!
በርቺልኝ!!!





@ElBethelofficial
@ElBethelofficial

Strong girl's

15 Jan, 10:23


He is always with us. To encourage, to comfort, to support...He will not leave us alone even in difficult situations....But we, relying on our circumstances, forget Him. While a true friend is by our side, we seek another friend. But he is always with us. His love is not based on our circumstances, like humans......!
Jesus❤️❤️❤️




@ElBethelofficial

Strong girl's

11 Jan, 20:16


የኔ ቆንጆ በህይወትሽ ውስጥ ይህንን አስተዉዪ።
አንድ ነገር ሞክረሽ ከተሳካልሽ ያ የእግዚአብሔር ምሪት ነው! አንድ ነገር ሞክረሽ ካልተሳካልሽ ግን ያ የእግዚአብሔር ጥበቃ ነው! ስለሆነልሽ እና ስለተሳካልሽ እንዳመሰገንሽው ሁሉ ስላልተሳካልሽ እና ስላልሰመረልሽም ምስጋናሽ መቀነስ የለበትም። ምናልባት ከዚያ ስኬት ጀርባ ያለው መልካም ስላልሆነ ቢሆንስ እግዚአብሔር ከስኬትሽ ጋር ያልቆመው? ምክንያቱም እግዚአብሔር ላንቺ መልካም ነው ብሎ ያሰበውን ሁሉ ሊሰጥሽ የታመነ ነው!
በርቺልኝ!!!





@ElBethelofficial
@ElBethelofficial

Strong girl's

08 Jan, 21:34


Sex or Love❤️😋

Strong girl's

08 Jan, 21:03


🙏🙏ወላሂ ለአዚም አላህ ሻሂዴ ነው  ይሄን ቻናል ተቀላቅዬ ከድህነት ወጥቻለው እናንተም ተጠቀሙበት betting ምትጫወቱ  الوالد لأخيم الله شهيد ، انضممت إلى هذه القناة وخرجت من الفقر واستخدمته
https://t.me/+MMM8fJk_52gxOThk
https://t.me/+MMM8fJk_52gxOThk
https://t.me/+MMM8fJk_52gxOThk

Strong girl's

08 Jan, 20:47


😋የጠበሳ ዘዴዎች ለወንድም ለሴትም 👌🤦‍♀ሴቶች ደፍረዉ የማይናገሩት ግን ከወንዶች🤷‍♂ የሚጠብቋቸዉ 7 ነገሮች❤️❤️

Strong girl's

08 Jan, 18:35


ቃላትን ሰዎች ላይ አታባክኚ!
የኔ ቆንጆ አንዳንዴ አንዳንድ ንግግርሽ የማይገባቸው ሁለት አይነት ሰዎች አሉ። የመጀመሪያዎቹ ከእኛ በላይ አዋቂ የለም የሚሉ ናቸው። በንግግራቸውም በተግባራቸውም ሁል ጊዜ አንቺ አላዋቂ እንደሆንሽ እና ምንም እንደማታቂ ለማሳየት የሚሞክሩ ናቸው። ከእነርሱ እንደምትበልጪ እና ከእነርሱ የበለጠ ዕውቀት እንዳለሽ ስለሚያውኩ የመናገር ዕድል አይሰጡሽም። በፍፁም አላዋቂነታቸውን እንድትገልጪባቸውና እንድታርሚያቸው አይፈልጉም። የዚህን ጊዜ እነዚህን ሰዎች በዝምታ እለፊያቸው። አዋቂ እንደሆኑ እንዲሰማቸው በማድረግ ለአለማወቃቸው ተያቸው።
ሁለተኛዎቹ ደግሞ በነገሮች በሚያደርጉት ነገር እና በሚናገሩት ነገር ሁሉ አንቺ የበታች እንደሆንሽ እንዲሰማሽ ለማድረግ የሚጥሩ ናቸው። ሁል ጊዜ በሰዎች ፊት ሊያሳፍሩሽ ይፈልጋሉ። ሊሳለቁብሽ እና ሊያሸማቅቁሽ ይፈልጋሉ። ለእነዚህ ሰዎች ምንም አይነት ምላሽ አያስፈልጋቸውም። ይልቁን ሊያሸማቅቁሽ እና ሊያሳፍሩሽ በሚሞክሩ ሰዓት በተረጋጋ መንፈስ አይን አይናቸውን በዝምታ እያየሽ ፈገግ ብለሽ እለፊያቸው። በፍፁም እነርሱን በመናገር ቃላትን አታባክኚ! ይህ ለእነርሱ ትልቅ መዋከብን እና መደናገጥን ይፈጥርባቸዋል። እንዴት? የሚል ጥያቄን ያስነሳል። ለሁሉም ነገር ምላሽ ለመስጠት የምትሞክሪ ከሆነ ትርፉ እራስን ማድከም እና ጊዜን ማባከን ነው የሚሆነው። አንዳንዴ ምላሽሽ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች መለየት አለብሽ።
በርቺልኝ!!!




@ElBethelofficial
@ElBethelofficial

Strong girl's

07 Jan, 07:13


🎀ገና'ዬ🎀
ለካ ዛሬ ያለወትሮዬ ገና በጠዋቱ ፀሐይ እንኳ በቅጡ ሳትታይ የነቃሁት ያለ ምክንያት አይደለም!
ለካ ዛሬ ያለወትሮዬ ገና በጠዋቱ ደስ የሚል ስሜት የተሰማኝ ልቤን ሃሴት የሞላው ያለ ምክንያት አይደለም!
ኦ ዛሬ! ዛሬ ለካ ልዩ ቀን ነው።
ካለመኖር ወደ መኖር የተሸጋገርኩበት ህይወቴ ጣዕምን ያገኘበት
እውነተኛ ሳቅ የሳኩበት
የመኖር ጉጉት ያገኘሁበት
ተስፋን ያገኘሁበት
እውነተኛ ፍቅርን ያገኘሁበት
በህይወቴ ትልቁን ስጦታ የተቀበልኩበት
ታሪኬ የተቀየረበት በህይወቴ ገና ነው ስል አብ ገና' ነው ብሎ ገና'ዬን የህይወቴን ትልቁን ትርጉም ጣዕም የሰጠኝ ህይወትን የተቀበልኩበት ቀን ነበር ለካ!!
ዛሬ ገና' ነው እንጂ ገና አይደለም። አሁንም ገና ያ ትርጉም የለሽ ህይወት ላይ አይደለሁም ታሪኬ በገናና ብርሃንን ካገኘሁበት ቀን በኋላ ህይወቴ ተቀይሮአል!!! ብርሃን በርቶልኛል!!!

“እንግዲህ ከእነርሱ ጋር ተካፋዮች አትሁኑ፤”
— ኤፌሶን 5፥7

🎄መልካም ገና🎄

Strong girl's

04 Jan, 21:36


Sex or Love❤️😋

Strong girl's

04 Jan, 21:28


🙏🙏ወላሂ ለአዚም አላህ ሻሂዴ ነው  ይሄን ቻናል ተቀላቅዬ ከድህነት ወጥቻለው እናንተም ተጠቀሙበት betting ምትጫወቱ  الوالد لأخيم الله شهيد ، انضممت إلى هذه القناة وخرجت من الفقر واستخدمته
https://t.me/+Ko1toim86Y43NGE8
https://t.me/+Ko1toim86Y43NGE8
https://t.me/+Ko1toim86Y43NGE8

Strong girl's

04 Jan, 21:18


😀ለዩንቨርሲቲ ና  ለ ሃይስኩል  ተማሪዎች   ብቻ የተከፈተ በኢትዮጲያ የመጀመሪያው ቻናሎች ❤️

Strong girl's

03 Jan, 17:18


Sex ፍቅርን አይገዛም!🚫
ብዙ ወንዶች የሚፈልጉትን ለማግኘት በየዋህ ሴቶች ውስጥ የሚከቱት ስህተት የሆነ አስተሳሰብ ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው "ስለምንዋደድ sex ብናደርግ ችግር የለውም!" የሚለው ነው። ይህም በብዙዎች ዘንድ sex ፍቅርን መግለጫ ነው የሚልን አስተሳሰብ ፈጥሮአል። በዚህም አንዳንድ ሴቶች የሚያፈቅሩት ወንድ ካላፈቀራቸው ወይም እየራቃቸው እንደሆነ ከተሰማቸው እንደመያዣነት ይጠቀሙበታል። ምክንያቱም ወንድ የሚፈልገውን ካገኘ የትም አይሄድም ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ይሄ በጣም የተሳሳተ እና የብዙዎችን ህይወት ያጨለመ ሃሳብ ነው። መፅሃፍ ቅዱስ ስለዚህ ሃሳብ በግልፅ የሚናገረው ነገር አለ። እስኪ አንድ በአንድ እንየው።

"2ኛ ሳሙኤል 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
"¹ ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፤ ለዳዊት ልጅ ለአቤሴሎም አንዲት የተዋበች እኅት ነበረችው፥ ስምዋም ትዕማር ነበረ፤ የዳዊትም ልጅ አምኖን ወደዳት።
² አምኖንም ከእኅቱ ከትዕማር የተነሣ እጅግ ስለ ተከዘ ታመመ፤ ድንግልም ነበረችና አንዳች ያደርጋት ዘንድ በዓይኑ ፊት ጭንቅ ሆኖበት ነበር።
³ ለአምኖንም የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ኢዮናዳብ የሚባል ወዳጅ ነበረው፤ ኢዮናዳብም እጅግ ብልህ ሰው ነበረ።
⁴ እርሱም፦ የንጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለ ምን ቀን በቀን እንዲህ ከሳህ? አትነግረኝምን? አለው። አምኖንም፦ የወንድሜን የአቤሴሎምን እኅት ትዕማርን እወድዳታለሁ አለው።
⁵ ኢዮናዳብም፦ ታምሜአለሁ ብለህ በአልጋህ ላይ ተኛ፤ አባትህም ሊያይህ በመጣ ጊዜ፦ እኅቴ ትዕማር እንድትመጣና እኔ የምበላውን እንጀራ እንድትሰጠኝ፥ መብሉንም እኔ እያየሁ እንድታዘጋጅልኝ፥ ከእጅዋም እንድበላው እለምንሃለሁ በል አለው።
⁶ እንዲሁም አምኖን፦ ታምሜአለሁ ብሎ ተኛ፤ ንጉሡም ሊያየው በመጣ ጊዜ አምኖን ንጉሡን፦ እኅቴ ትዕማር እንድትመጣና እኔ እያየሁ ሁለት እንጎቻ እንድታደርግልኝ፥ ከእጅዋም እንድበላ እለምንሃለሁ አለው።
⁷ ዳዊትም፦ መብልን ታዘጋጂለት ዘንድ ወደ ወንድምሽ ወደ አምኖን ቤት ሂጂ ብሎ መልእክተኞችን ወደ ትዕማር ቤት ላከ።
⁸ ትዕማርም ወደ ወንድምዋ ወደ አምኖን ቤት ሄደች፥ ተኝቶም ነበር፤ ዱቄትም ወስዳ ለወሰች፥ እያየም እንጎቻ አደረገች፥ ጋገረችም።
⁹ ምጣዱንም ወስዳ በፊቱ ገለበጠች እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አምኖንም፦ ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስወጡ አለ፤ ሰውም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ወጣ።
¹⁰ አምኖንም ትዕማርን፦ ከእጅሽ እበላ ዘንድ መብሉን ወደ እልፍኙ አግቢው አላት፤ ትዕማርም የሠራችውን እንጎቻ ወስዳ ወንድምዋ አምኖን ወዳለበት እልፍኝ አገባችው።
¹¹ መብሉንም ባቀረበች ጊዜ ያዛትና፦ እኅቴ ሆይ፥ ነዪ ከእኔም ጋር ተኚ አላት።
¹² እርስዋ መልሳ፦ ወንድሜ ሆይ፥ አይሆንም፤ እንዲህ ያለ ነገር በእስራኤል ዘንድ አይገባምና አታሳፍረኝ፤ ይህንም ነውረኛ ሥራ አታድርግ።
¹³ እኔም ነውሬን ወዴት ልሸከም? አንተም በእስራኤል ዘንድ ከምናምንቴዎች እንደ አንዱ ትሆናለህ፤ እንግዲህስ ለንጉሡ ንገረው፥ እኔንም አይነሣህም አለችው።
¹⁴ ቃልዋን ግን አልሰማም፤ ከእርስዋም ይልቅ ብርቱ ነበረና በግድ አስነወራት፥ ከእርስዋም ጋር ተኛ።
¹⁵ ከዚያም በኋላ አምኖን ፈጽሞ ጠላት፤ አስቀድሞም ከወደዳት ውድ ይልቅ በኋላ የጠላት ጥል በለጠ። አምኖንም፦ ተነሥተሽ ሂጂ አላት።
¹⁶ እርስዋም፦ አይሆንም ቀድሞ ከሠራኸው ክፋት ይልቅ አኔን በማውጣትህ የበለጠ ክፋት ትሠራለህ አለችው እርሱ ግን አልሰማትም።
¹⁷ የሚያገለግለውንም ብላቴና ጠርቶ፦ ይህችን ሴት ከፊቴ አስወጥተህ በሩን ዝጋባት አለው።
¹⁸ ብዙ ኅብር ያለውንም ልብስ ለብሳ ነበር፥ እንዲህ ያለውን ልብስ የንጉሡ ልጆች ደናግሉ ይለብሱ ነበርና፤ አገልጋዩም አስወጥቶ በሩን ዘጋባት።..."

ይህንን ታሪክ ሙሉውን ያስቀመጥኩላችሁ በጣም አስተማሪ ከመሆኑም በላይ ለዚህ ሃሳብ ከዚህ በላይ የሚያስተምር ታሪክ ስለሌለ ነው።

ታሪኩን በጥልቀት ከተመለከትነው አምኖን ትዕማርን እንደወደዳት እንደውም ከመውደዱ ብዛት እጅግ እንደጎሰቆለ እና እንደታመመ እናያለን። ይህም የፍቅሩን ጥግ ያሳየናል። ከዛም ዝቅ ብለን ስናነብ ቁጥር 11 ላይ አብረው እንዲተኙ ይጠይቃታል። እሷም ይህ የማይገባ ነገር እንደሆነ ልትነግረው ብትሞክርም አምኖን አልሰማትም ነበር። ዝቅ ብለን በምናነብበትም ጊዜ ቁጥር 14 ላይ ከእርሷ በላይ ብርቱ ነበርና በግድ አስነወራት ይላል። ከዚያ ግን ቁጥር 15 ላይ አብሯት ከተኛ በኋላ እና የሚፈልገውን ካገኘ በኋላ "ፈፅሞ ጠላት። አስቀድሞም ከወደዳት መውደድ ይልቅ በኋላ የጠላት መጥላት በለጠ!" ይላል። ትልቁ ትምህርት ያለው እዚህ ላይ ነው። አምኖን ፍቅሩ እጅግ የበረታ እንደነበር እና ከልቡ አፍቅሯት እንደነበር መጀመሪያ ላይ ይናገራል። ታድያ ለምን በአንዴ እንዲ ሊጠላት ቻለ?
አምኖን ትዕማርን የጠላበት ዋነኛው ምክንያት የማይገባውን ነገር በማይገባው ጊዜ ሰዓት ስላገኘ ነበር። የከበረ ነገር እንኳን ቢሆን በማይገባው ቦታ ከተገኘ ርካሽ እንደሚሆን ልክ እንደዛ!

አየሽ የኔ ልባም ሴት...! Sex ፍቅርን አይገዛውም። ስለማፈቅረው ነው፣ ስለምወደው ነው ፣ እንዳይተወኝ ነው። ብለሽ sexን እንደ መያዣነት መጠቀም ማለት በራስሽ እጅ ህይወትሽን ማበላሸት ነው። Sex በፍፁም የምታፈቅሪውን ወንድ ያንቺ ሊያደርገው አይችልም። ምናልባት ለጊዜያዊ ስሜቱ ሲል እወድሻለው ሊልሽ ይችላል እንጂ በፍፁም ያንቺ ሊሆን አይችልም። አይደለም የማይወድሽን የሚወድሽን እንኳን በፍፁም ያንቺ ማድረግ አትችይም። ጥላቻን እና ንቀትን ማትረፍ ነው ውጤቱ። ስለዚህ የኔ ቆንጆ ካልወደደሽ ካልፈለገሽ አልፈለገሽም ነው። ያንቺ ካልሆነ ሰው ጋር መጋጨቱ አይጠቅምሽም። ንፅህናሽን እና ክብርሽን ጠብቂ።
በርቺልኝ!!!




@ElBethelofficial
@ElBethelofficial
@ElBethelofficial

Strong girl's

03 Jan, 15:48


ጥያቄ
አንዲት ሴት የምታፈቅረውን ወንድ በsex መያዝ ትችላለች?

ይህንን ሃሳብ 2:00 ሰዓት ላይ እለቅላችኋለው። ነገር ግን እስከዛ እስኪ የናንተን ሃሳብ በcomment አስቀምጡልኝ።

Strong girl's

01 Jan, 16:16


መፍጠን ከፈለግሽ...
...ብቻሽን ተራመጂ!
ብዙ ጊዜ ካስተዋልሽ የትም ሂጂ ቸኩዪም አትቸኩዪም ብቻሽን ስትሄጄ በፍጥነት ነው የምትራመጂው። ምክንያቱም ሙሉ ትኩረትሽ መንገድሽ ላይ እና አረማመድሽ ላይ ነው። ትኩረትሽን ምንም ስለማይከፋፍለው በማስተዋል ትራመጂያለሽ። አረማመድሽን እንኳን በማስተዋል ታደርጊዬለሽ። እግሮችሽ መንገዱን እየመረጡ ይረግጣሉ።ነገር ግን ከጎንሽ ሰው ካለ እና ከሰው ጋር ከሆነ እየሄድሽ ያለሽው ለብቻሽ እንደምትራመጂው አይደለም የምትራመጂው። ፍጥነትሽ ይቀንሳል። ትኩረትሽም መንገድሽ ላይ ሳይሆን ከጎንሽ ያለው ሰው ላይ ይሆናል። ሃሳብሽ ይከፋፈላል። ሙሉ ትኩረትሽን ሃሳብሽም መንገድሽ ላይ ስላልሆነ ብዙ ልትደናቀፊ ብዙ ልትጋጪ ትችያለሽ።

ህይወትም በዚህ ይመሰላል። ህይወት ልክ እንደመንገድ ነው። መንገድ ብዙ እንቅፋትን እንደያዘ ህይወትም በውስጡ ብዙ ፈተናዎችን ይዟል። መውደቅ፣ መነሳት፣ ማዘን፣ መደሰት፣ ህልም፣ ግብ፣ ስኬት፣ ኪሳራ...ብዙ ብዙ ይዟል። የዚህ ምድር ህይወት መንገድ ማለቂያ ሞት ነው። ይህንን መንገድ ስትጓዢ ማንም ከጎንሽ የሚሆን የለም። ህልም የራሱን መንገድ ነው የሚጓዘው። ወደ ህልምሽ የሚያደርስሽ መንገድ ላይ ስትጓዢም ብዙ ፈተናዎች አሉት። ነገር ግን ወደ ህልምሽ መፍጠን ከፈለግሽ ለብቻሽ ተጓዢ! ማንም ከጎንሽ እንዲቆም እና አይዞሽ እንዲልሽ አትፈልጊ። እግዚአብሔር አንቺን ብቻሽን አንድ ብቻ አርጎ የፈጠረሽ የሰጠሽን የህይወት መንገድ በራስሽ እና ብቻሽን መጓዝ ስለምትችይ ነው። ሰዎች ድንገት ጥለውሽ ሲሄዱ፣ ድንገት ሲቀየሩብሽ አይግረምሽ። አይክፋሽም!

አዎ! የኔ ልባም ሴት...! መፍጠን ከፈለግሽ ብቻሽን ተራመጂ። ብቻሽን ምንም ነገር ማድረግ አያስፈራሽ። ብቻ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር እንዳለ አረጋግጪ እንጂ ምንም ነገር ለብቻሽ ማድረግ አያስፈራሽ። ጓደኛዬ የለችም እኮ፣ ጥላኝ ሄደች እኮ፣ ብቻዬን እንዴት?! አትበይ። ለብቻሽ ማድረግን ተማሪ። ምክንያቱም ማንም የራሱን መንገድ ትቶ ካይቺ ጋር አይሄድም! ማንም የራሱን ስራ ትቶ ያንቺን ስራ አይሰራም። ምናልባት መንገዳችሁ አንድ ቢሆን እንኳ ለጥቂት ደቂቃ ቢቸኝሽ እንጂ ሸኚ ቤት አያደርስም!
የኔ ቆንጆ የብቸኛ መሆን ትልቁ power ፍጥነት ነው። ይህን ስልሽ ግን እረዳት አያስፈልግሽም እያልኩሽ ሳይሆን ብቻሽን መሄድ የምትችዪውን መንገድ ለብቻሽ መሄድን ልመጂ ነው።
በርቺልኝ!!!





@ElBethelofficial
@ElBethelofficial
@ElBethelofficial

Strong girl's

26 Dec, 17:30


የሞቀ አነጋገር አይውሰድሽ!🔥
እኛ ሴቶች በተፈጥሮአችን በምንሰማው ነገር እንወሰዳለን፣ እንዋጣለን። የምንሰማውን የማመን እና በርሱ የመሳብ ባህርዪ አለን። የምንሰማው ነገር ነው ልባችንን የሚያሞቀው። ምክንያቱም ከልባችን ነው የምንሰማው። ሄዋን እንኳን እባቡ ያታለላት የነገራትን ከልባ በመስማታ ነው። በሚናገራት ጊዜ ልቧ ሞቆ ነበርና ወደ ጥፋት ወሰዳት። በዚህ ጊዜም ደግሞ ብናይ ከብዙ ሴቶች ስብራት ጀርባ "እንዲህ ብሎኝ ነበርኮ!" የሚል የቁጭት ንግግር አለ። ብዙ ሴቶች የሚሰበሩት፣ህይወታቸውን የሚያበላሹት የሚሰሙትን የውሸት ቃል በማመን ነው።
ወንዶች ደግሞ በተቃራኒው የመናገር እና ሴትን በቀላሉ የማሳመን ተፈጥሮ አላቸው። የሚፈልጉትን ለማግኘት በዋናነት ምላሳቸውን ይጠቀማሉ። እንዴት መናገር እንዳለባቸው እና ምን መናገር እንዳለባቸው ያውቃሉ። ጥበበኛ ያልሆነችን ሴት ማጥመድ ለእነርሱ በጣም ቀላል ነው። ከሴት እና ከወንድ ልዩነት አንዱ ይሄ ነው። ሴት በምትሰማው ነገር ትጠመዳለች፣ ትወድቃለች። ወንድ ግን በሚያየው ነገር ይጠመዳል። even ሴት ልጅ በአይምሮዋ የምታሰላስለው እንዴት እንዲህ ይለኛል እያለች ትኩረትዋ ንግግሩ ላይ ነው። ወንድ ግን ተክለ ሰውነታ አይኗ እያለ ነው የሚያሰላስለው።

አዎ!የኔ ልባም ሴት...! የሞቀ አነጋገር እንዳይወስድሽ ተጠንቀቂ! የሞቀ ንግግር በተለይ ለሴት ልጅ ልክ እንደ ውሃ ነው አሳስቆ የሚወስደው። መጨረሻው ግን ስብራት ነው። ንግግርን የምትለዪበት እና የምትመረምሪበት ጥበብ ይኑርሽ። እግዚአብሔር ሲፈጥርሽ በምትሰሚው ነገር የምትሳቢ አርጎ ቢሆንም የምትሰሚው ሁሉ እንዳይወስድሽ ንግግርን የምትመረምሪበት ልዩ ጥበብም ሰቶሽ ነው። ስለዚህ ያንን ተጠቀሚበት። እወድሻለው ብሎኛል እኮ አፈቅርሻለው ብሎኛል እኮ ብለሽ በፍፁም ህይወትሽን እንዳታበላሺ። እወድሻለው የሚለው ቃል በኋላ ጠላሁሽን ይወልዳል። ያንቺ እምነት ግን ስብራትን ነው የሚወልደው። መቼም ቢሆን ደግሞ መውደድ በተግባር ይገለጣል። በጣም የምንወደውን ሰው መርዝ እንደማንግተው እርግጥ ነው። በአፍ በመውደድ በተግባር ግን መጥላትን የሚገልፅ ነገርን ማድረግ እንዴት አብረው መሄድ ይችላሉ? ወንድ ልጅ የሚፈልገውን ለማግኘት ልብሽን በሚያሞቅ ንግግር ይናገርሻል። ነገር ግን መርምሮ መስማት ያንቺ ድርሻ ነው!
በርቺልኝ!!!

“.....ልብዋንም ደስ በሚያሰኛት ነገር ተናገራት።”
— ዘፍጥረት 34፥3





@ElBethelofficial
@ElBethelofficial
@ElBethelofficial

Strong girl's

19 Dec, 18:55


አንዳንዴ ወደ ህይወታችን የሚመጡ ገጠመኞች ድጋሜ አናገኛቸውም። ሁልጊዜ በማስተዋል የሚኖር ይጠቀምባቸዋል። የማያስተውል ግን ሳይጠቀምባቸው ያልፋታል። አስተዋይ ሁኚ!




@ElBethelofficial
@ElBethelofficial
@ElBethelofficial

Strong girl's

18 Dec, 17:15


🦋ተሻግረሽ እለፊው!🦋
ጥንካሬሽን ትፈልጊያለሽ? እንደ ሸክላ ወደ ወደድሽው ቅርፅ መቀየር ትፈልጊያለሽ? እንገና መታነፅ፣ ዳግም መሰራትን ትመኚያለሽ? አንድ ነገር ብቻ ጨክነሽ አድርጊ። ከባዱን አጣብቂኝ አውቀሽ ተጋፈጪው፣ አሁን የሚያስፈራሽን፣ አሁን የሚረብሽሽን፣ አሁን ጫና ውስጥ የከተተሽን እርሱን ነገር ወስነሽ አድርጊው። እየታመሙ ዛሬ ነገ ማለት አይሰራም፤ ስቃይን በጉያ ይዞ ነገርን ማዘግየት አያዋጣም፤ እንቅልፍ እያጡ የነገሮችን ቅለት መጠበቅ አይቻልም። ወይ ተመችቶሽ አልተመቸሽ ወይም ከህመሙ ጋር ተስማምተሽ አልኖርሽም። ከሁሉም በላይ የሚጠቅምሽን ምረጪ፣ ለምትፈልጊው ነገር ሃላፊነት ለመውሰድ በሚገባ ተዘጋጂ። በአዕምሮሽ የፈጠርሽው ሲዖል መሳይ መኖሪያሽ አይገባሽም፤ በፍፁም አይመጥንሽም። ስብራቱ ቢመጣ ካንቺ ፍቃድ ውጪ ባንቺ ላይ ምንም ስልጣን አይኖረውም።

አዎ! ጀግኒት..! ተሻግረሽ እለፊው፤ አራግፈሽ ጣዪው፣ ወስነሽ ተለይው። የልብ ሸክም ሲበዛ ህመም ነው፤ በሆድ የተያዘ ነገር ሲቆይ ስቃይ ነው። እያደር ያልተጠበቀ ነገር ይወልዳል፤ ሲቆይ ያልታሰበ ዋጋን ያስከፍላል፤ አላስፈላጊ መዘዝ ውስጥ ይከታል። በትኩሱ መቅረፍ ያለብሽን ጉዳይ እያዘገየሽ እራስሽን አተጉጂ። ዛሬ ለሰው ልትኖሪ ትችያለሽ፣ ዛሬ የሰው ጉዳይ ሊያሳስብሽና ሊያስጨንቅሽ ይችላል ነገ ግን ዛሬ በመጨነቅሽ አንዳች የምታተርፊው ነገር አይኖርም። ውስጥሽ እየቆሰለ ሰው ስለመልካምነትሽ ቢያወራ ምን ይጠቅምሻል? እራስሽን እያሳዘንሽ ሰዎችን ብታስደስቺ፣ እራስሽን ችላ እያልሽ የሰዎችን ይሁንታ ለማግኘት በትፋጠኚ ምን ታተርፊያለሽ? የእራስ ባዳ ሆኖ በወዳጅ መከበብ እንደ ሻማ ለሌሎች እየቀለጡ ከማለቅ የተለየ ትርጉም የለውም። የፈራሽውን ነገር እየፈልግሽ በትንሹ ማድረግ ተለማመጂ፣ ለዘመናት ያሰረሽን የይሉኝታ ቀንበርም ከትከሻሽ ላይ አስወግጂ።





@ElBethelofficial
@ElBethelofficial
@ElBethelofficial

Strong girl's

08 Dec, 19:45


የረጋ ወተት ነው ቂቤ የሚወጣው!
የኔ ቆንጆ የኔ ለምን ዘገየ ለምን ቆየ አትበይ። ጥሩ እና የተሻለ ነገር ሁሌም ጊዜ ይፈልጋል። የራስሽን እና የሌሎችን ጊዜ አታስተያዪ። ምክንያቱም ያንቺ የተሻለ ስለሆነ ነው የዘገየው።ብቻ ትንሽ ትዕግስት ይኑርሽ!
በርቺልኝ!!!🥰🥰🥰





@ElBethelofficial

Strong girl's

06 Dec, 12:04


t.me/seed_coin_bot/app?startapp=5065147095
SEED App – Meme Telegram app backed by top investors.
🔥 Burning SEED for inactive users after more than 30 days.
🚀 20M users in just 1 month!
🏆 Top-tier listing this December.
Don’t miss out — now’s the perfect time to join! 🎉

Strong girl's

05 Dec, 01:57


🦋የተለጠፈብሽን ለማወቅ አትጣሪ!🦋
በአንድ ወቅት በአንድ ክፍል ውስጥ በማማሩ ተማሪዎች አንዱን ጓደኛቸውን prunk ለማድረግ አሰቡና ከጀርባው "I'm stupid" (እኔ ደደብ ነኝ) የሚል ወረቀት ለጠፉበት። ከዛም ሁሉም ተማሪዎች ይስቁበት ጀመር። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ የMaths አስተማሪ ወደ ክፍሉ ገባ እና አንድ ከባድ ጥያቄ ሰሌዳው ላይ ፅፎ እንዲሰሩለት ጠየቃቸው። ነገር ግን ከዚህያ ጀርባው ላይ ከተለጠፈበት ልጅ በስተቀር ሁሉም ጥያቄው ከብዷቸው ስለነበር ዝም አሉ። በመጨረሻም ወረቀቱን የለጠፉበት ልጅ ሁሉም "I'm Stupid" የሚለውን ፅሁፍ እያዩ እነርሱን የከበዳቸውን ጥያቄ እንደቀላል ሰራው!
መምህሩም "ከኋላህ የተለጠፈብህን ያወክ አይመስለኝም። ብታውቅ ኖሮ ከመቀመጫህም ባልተነሳህ ነበር!!!" አሉት።

የኔ ቆንጆ ሰዎች እንድትበልጫቸው ስለማይፈልጉ በብዙ ነገር አስታከው ብዙ ወደ ኋላ የሚጎትቱሽን ነገሮች ይለጥፉብሻል። ብዙ Negative ስሞችን ያወጡልሻል። ምክንያቱም ቃል ሰዉን ምን ያህል እንደሚያስር ያውቃሉ።

አዎ! የኔ ልባም ሴት...! የለጠፉብሽን ለማወቅ አትጣሪ! ጆሮሽን ሰዎች ለሚሰጡሽ posetive አስተያየቶች እና ማበረታቻውች ብቻ ክፈቺው እንጂ ለNegative ንግግራቸው በፍፁም እንዳትከፍቺ። መተው እንኳን እንትና እንዲ ብሎሽ ብለው ሊያወሩልሽ ሲመጡ ልትሰሚያቸው እንዳትዘጋጂ። አስወጥተሽ በርሽን ዝጊባቸው። አስተዉዪ ዛሬ ላይ እንኳን መሆን የምትፈልጊውን ነገር እየሞከርሽ ያለሽው እየሰራሽ እየተጓሽ ያለሽው ወሬያቸውን ስላልሰማሽ የለጠፉብሽን ስላላየሽ ነው። እንጂማ ዛሬን ባልደረሽ ከተቀምመጥሽበት ለመጓዝ ባልተነሳሽ ነበር።
ጆሮ ለራሱ ጋዳ ነው! የተባለውም ለበጎ ነው። ቃል ትልቅ ኃይል አለው። ያስራል፣ ይፈታል፣ ያድናል፣ ያሳምማል፣ያቆስላል...! ሁልጊዜም እንድትበልጫቸው ማይፈልጉ ሰዎች በትልቅ ነገር አይደለም የሚያስሩሽ። በሁሉም ተግባራቸው ያበረታቱሻል ጎበዝ በርቺ ይሉሻል ነገር ግን በአንዲት ተራ ቃል ያስሩሻል! ስለዚህ አንቺም ጥበበኛ ሁኚ። የታሰርሽላቸው ምሰዪ ግን እንዳትታሰሪላቸው። እነሱም ሊያስሩሽ የሞከሩት በማስመሰል ነውና!!!
በርቺልኝ!!!






@ElBethelofficial
@ElBethelofficial
@ElBethelofficial

Strong girl's

04 Dec, 12:41


ሰላም ሰላም ✌️

የኔ ቆንጆ ምን ተቸግረሻል ?
ለ ፀጉርሽ ወይስ ለ ቆዳሽ ?
አሚስማማሽን ማግኘት አልቻልሺም ?🤔

አታስቢ እኛጋ የተፈጥሮ ምርጥ ግብአቶች አሉ ለሁሉም የሚስማሙ ::😌😊

አንተስ የኔ ወንድም አንተንም ያካታል

ምንድን ነው ??🤔
ካላቹ 👇👇 join me 
https://t.me/herbal_cosmotics

Strong girl's

01 Dec, 10:23


Be like butterfly!
Always beautiful and hard to catch! Everyone looks at them and admires them but cannot hold them.Their beauty is that they are not easily found. They are expensive!
🦋🦋🦋

Strong girl's

01 Dec, 08:03


ሰው አይደለን! ህይወታችን ልክ እንደጤዛ ነው። አሁንን እንጂ በኋላን ማወቅ አንችልም። ሁላችንም የበኋላን ባናቅም ግን መኖራችንን ብቻ እናስባለን እና ብዙ ተስፋ፣ ትልቅ ህልም፣ ትልቅ ምኞት፣ ትልቅ ራዕይ አለን። ስለ ነገ መልካሙን እንጂ መጥፎውን አናስብም።
ከላይ የምትመለከቷት ወጣትም ፌኔት ቱሉ ትልቅ ህልም የነበራት ነገዋን በዛሬው ልፋትዋ ለማቃናት የምትጥር ነበረች። ነገር ግን ዛሬ ላይ በገጠማት የኩላሊት ህመም ምክንያት ባላሰበችበት በፅኑ ታማ ከተኛች ወራት ተቆጥረዋል። ህልሟን መሆን የምትፈልገውን የምታልመውን ሁሉ ጥላ ዛሬ ግን አልጋ ላይ ወድቃለች። ለህክምናም የተጠየቀችውም 3,500,000 ብር ሲሆን ይህም ከሷም ሆነ ከቤተሰቦችዋ አቅም በላይ ስለሆነ እርዳታ ለመጠየቅ ተገዳለች። ለወገን ደራሽ ወገን ነውና
ዛሬም ይህችን ኖራ ያልጠገበችን ነብስ ለማዳን እጃችንን በመልካምነት መዘርጋት ይኖርብናል።
ዛሬ ላይ ለእኛ ትንሽ የሆነ ለመስጠት የምንንቀው ነገር እንኳን ለእርሷ ትልቅ ነገር ነው። ጠብታ ነው ሮቶ የሚሞላውና 70 ብር ለ50,000 ሰው የሚለውን ህይወት የማትረፍ challenge በመቀላቀል እና 50,000 ሰዎች 70 ብር ብቻ በመስጠት የተጠየቀችውን ብር መሙላት እንችላለን። እኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከዛም እንልቃለንና የመልካምነት ዘራችንን በመዝራት ህይወትን እናትርፍ። አብራችሁን ስለምትቆሙ እናመሰግናለን!



Account
👇👇👇
1000611589712 CBE
Fenet Tulu Worku
1000247849185 CBE
Abel Tulu Worku
01320444559000 Awashi
Abel Tulu Worku

Strong girl's

29 Nov, 11:54


ሰው አይደለን! ህይወታችን ልክ እንደጤዛ ነው። አሁንን እንጂ በኋላን ማወቅ አንችልም። ሁላችንም የበኋላን ባናቅም ግን መኖራችንን ብቻ እናስባለን እና ብዙ ተስፋ፣ ትልቅ ህልም፣ ትልቅ ምኞት፣ ትልቅ ራዕይ አለን። ስለ ነገ መልካሙን እንጂ መጥፎውን አናስብም።
ከላይ የምትመለከቷት ወጣትም ፌኔት ቱሉ ትልቅ ህልም የነበራት ነገዋን በዛሬው ልፋትዋ ለማቃናት የምትጥር ነበረች። ነገር ግን ዛሬ ላይ በገጠማት የኩላሊት ህመም ምክንያት ባላሰበችበት በፅኑ ታማ ከተኛች ወራት ተቆጥረዋል። ህልሟን መሆን የምትፈልገውን የምታልመውን ሁሉ ጥላ ዛሬ ግን አልጋ ላይ ወድቃለች። ለህክምናም የተጠየቀችውም 3,500,000 ብር ሲሆን ይህም ከሷም ሆነ ከቤተሰቦችዋ አቅም በላይ ስለሆነ እርዳታ ለመጠየቅ ተገዳለች። ለወገን ደራሽ ወገን ነውና
ዛሬም ይህችን ኖራ ያልጠገበችን ነብስ ለማዳን እጃችንን በመልካምነት መዘርጋት ይኖርብናል።
ዛሬ ላይ ለእኛ ትንሽ የሆነ ለመስጠት የምንንቀው ነገር እንኳን ለእርሷ ትልቅ ነገር ነው። ጠብታ ነው ሮቶ የሚሞላውና 70 ብር ለ50,000 ሰው የሚለውን ህይወት የማትረፍ challenge በመቀላቀል እና 50,000 ሰዎች 70 ብር ብቻ በመስጠት የተጠየቀችውን ብር መሙላት እንችላለን። እኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከዛም እንልቃለንና የመልካምነት ዘራችንን በመዝራት ህይወትን እናትርፍ። አብራችሁን ስለምትቆሙ እናመሰግናለን!



Account
👇👇👇
1000611589712 CBE
Fenet Tulu Worku
1000247849185 CBE
Abel Tulu Worku
01320444559000 Awashi
Abel Tulu Worku

Strong girl's

23 Nov, 18:38


ስሚኝማ ጨው በምግብ ውስጥ ያን ያህል ጣዕም የሚያመጣው ያን ያህል ተፅዕኖ የሚፈጥረው እራሱን አጥፍቶ ነው። ሟሙቶ ነው። መቼም ያለ ጨው ምግብ መብላት የሚታሰብ ነገር አይደለም። ግን ጨው ያንን ያህል ልዩነት መፍጠር የቻለዉ እየታየ ነው እንዴ? አይደለም እኮ! ምግቡ ምን ያህል እንደሚጥም ስናደናንቅ እኮ ጨዉ እዚህ ጋር ነው እዛ ጋር ነው ብለን አይደለም። እንደውም የቱጋር እንዳለ እንኳን አይገመትም።

አንቺም ተፅዕኖ መፍጠር ከፈለግሽ እራስሽን አጥፊና መስራት ያለብሽን ነገር ስሪ። መገኘት ከሌለብም ቦታ ጥፊ። ሰዎች የቱጋር እንዳለሽ እንኳን እስከማያውቁ ድረስ ምን እየሰራሽ እንደሆነ እስከማይገምቱ ድረስ እራስሽን አጥፊ። የመጥፋትን የመሰወርን power የምታቂው ጨውን ስትመለከቺ ነው።
በርቺልኝ!!!🥰🥰🥰





@queen_B77
@queen_B77
@queen_B77

Strong girl's

18 Nov, 05:02


ዛሬ ለኔ ልዩ ቀን ነው ከብዙ ድካም ከብዙ ልፋት ከረጅም ዓመታት አልፊ ጉዞ በኋላ የሚፈልገውን ነገር አገኘሁ። ቀላል አልነበረም ይከብዳል ያደክማል ግን እግዚአብሔር አልጣለኝም

ባንድም በሌላ መልኩ ከእግዚአብሔር በታች ከጎኔ የነበራችሁ ቤተስቦቼ ጓደኞቼ፣ አስተማሪዎቼ ሁላችሁንም ከልብ አመሰግናለሁ።
ላሳያችሁኝ ፍቅር ለስጣችሁኝ አክብሮት እግዚአብሔር ይስጥልኝ ሌላ ምን እላለሁ
Bestemechersha haremaya university እየሄድኩ ነው።

Strong girl's

16 Nov, 13:44


🦋የሌላውን አትመኚ!🦋
ሰው የሰው የሚያየው የራሱ የጎደለ ሲመስለው ውይም የኔ በቂ አይደለም ብሎ ሲያስብ ነው። በራሱ ነገር ላይ ቅሬታ ሲኖረው ነው የሌላውን ማየት የሚጀምረው። አይኑን ከእራሱ ላይ የሚያነሳው የራሱን ነገር ሲጠላ ነው።

የኔ ቆንጆ አንቺ ደግሞ እራስሽን የምታዪበት አስተያየት ነው እንጂ አንቺ ምንም አልጎደለሽ ነገር የለም። እግዚአብሔር ሁሉንም አሟልቶ ነው የፈጠረሽ። የሌላውን ማየት አይገባሽም። የሚያስፈልግሽ እራስሽን የምታዪበትን መነፅር ማፅዳት ነው። እራስሽን የምታዪበትን አስተያየት አስተካኪ። እራስሽን ከማንም ጋር አታወዳድሪ። እግዚአብሔር ልዩ አድርጎ የፈጠረሽ እኮ እራስሽን ከማንም ጋር እንዳታስተያዪ እና እንዳታወዳድሪ ነው። ያንቺ መልክ፣ ያንቺ ቁመና፣ ያንቺ ውበት፣ ያንቺ አሳሳቅ፣ ያንቺ አስተሳሰብ፣ ያንቺ ሁሉ ነገርሽ ልዩ ነው። በፍፁም ከሌላ ጋር ሊወዳደር አይችልም። ሁሉም ነገርሽ ልዩ ነው። አንቺ ከሌሎች ጋር እራስሽን አመሳስለሽ እና አነፃፅረሽ ውበትሽን፣ ልዩነትሽ፣ ድምቀትሽን አታጥፊው።
ዞር ብለሽ አከባቢሽን ብትቃኚ ያንቺን የሚመኙ ያንቺን የሚያዩ እኮ ብዙ ናቸው። ያንቺ የሆነውን ነገር እያዩ የሚመኙ እንደ እርሷ ብሆን የሚሉ ብዙ አሉ። ስለዚህ ከማንም ጋር ሚዛን ላይ ሊወጣ የማይችል የውበትሽን እና የማንነትሽን ክብር ዝቅ አታርጊው። አንቺ በእራስሽ በቂ እና በቂ ነሽ።
በርቺልኝ!!!🥰🥰🥰





@queen_B77

Strong girl's

14 Nov, 17:03


😌ፎንቃ MOOD🥰

Strong girl's

14 Nov, 16:54


ማርያምን ዝም ብላችሁ join በሉ
😂😂😂ጥርሳችሁ እስኪሰበር ነው ምትስቁት ግን በዋላ ጥርሳቹ ተሰብሮ ክፈል የለም😁😁 ስሞትላቹ ተቀላቀሉት 🙏

Strong girl's

14 Nov, 16:39


እንደስሙ ሽንት አስጨራሽ 😁
የዚህን ቻናል ኮሜንቶች አንብበህ ሽንትህ ካላመለጠህ እመነኝ አለም ላይ ጀግና አንተ ብቻ ነህ 😂👏👏

አልሸናም ካልክ Join ብለህ ሞክረው🤪 👇

Strong girl's

12 Nov, 03:33


🚨አሁን ONLINE ላላችሁ ብቻ የ 500 ብር ካርድ ልንሸልም ነው 🚨

ቀድመው እነዚን ቻናል ለተቀላቀሉ 20 ሰዎች የ 500 ብር ካርድ ልሸልም ነው ቶሎ ይቀላቀሉ።


https://t.me/addlist/e3BXRkE7LZYyMzJk

🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵

Strong girl's

11 Nov, 21:42


Sex or Love❤️😋

Strong girl's

11 Nov, 21:34


🙏🙏ወላሂ ለአዚም አላህ ሻሂዴ ነው  ይሄን ቻናል ተቀላቅዬ ከድህነት ወጥቻለው እናንተም ተጠቀሙበት betting ምትጫወቱ  الوالد لأخيم الله شهيد ، انضممت إلى هذه القناة وخرجت من الفقر واستخدمته
https://t.me/+SMIuQZ2eh9JmNTA0
https://t.me/+SMIuQZ2eh9JmNTA0
https://t.me/+SMIuQZ2eh9JmNTA0

Strong girl's

11 Nov, 21:24


😀ለዩንቨርሲቲ ና  ለ ሃይስኩል  ተማሪዎች   ብቻ የተከፈተ በኢትዮጲያ የመጀመሪያው ቻናሎች ❤️

Strong girl's

10 Nov, 12:00


🦋Kissing!💋🦋
Kissing(መሳሳም) ምንድነው?
Kissing መቼ ነው የተፈቀደልን?
Kissing ለፍቅረኛሞች አልተፈቀደም?
መፅሀፍ ቅዱስ ስለ እነዚህ ምን ይናገር ይሆን?!


በመጀመሪያ kissing(መሳሳም) ማለት ምን ማለት ነው? Kissing ከንፈር ላይ መሳሳም❗️
Kissing ማለት የsex አንዱ አካል ማለት ነው።
kissing ማለት አእምሮአችንን ለsex የሚያዘጋጅ ነገር ማለት ነው። ይህ ማለት አንድ ወንድ እና ሴት kissing በሚያደርጉበት ጊዜ ብዙ የሚለዋወጡት ነገር አለ። ለምሳሌ ምራቅ፣ባክቴሪያ ይለዋወጣሉ። በአጠቃላይ በወንዱ ውስጥ ያለው ነገር ወደ ሴትዋ በሴትዋም ያለ ነገር በወንዱ ውስጥ ይሆናል። ይህም የsex አንዱ አካል ያደርገዋል። በቀጣይነት ደግሞ እነዚያ ሰዎች በሚሳሳሙበት ወይም kissing በሚያደርጉ ሰዓት አእምሮአቸው sex ሊመጣ እንደሆነ ያስብ እና ሰውነታቸውን ለsex የሚያዘጋጀውን ሆርሞን መልቀቅ ይጀምራል። ምክንያቱም ለሰውነታችን የkissing መልዕክት sex ልናደርግ ነው የሚል ስለሆነ ሰውነታችንን ለዛ ያዘጋጃል። ይህም Dopamine የሚባለውን ሆርሞን እንዲለቀቅ ያደርጋል። ስለዚህ ይህ ማለት ደግሞ በአጭሩ kissing ከትዳር ውጪ እንደማይፈቀድ ያሳየናል ማለት ነው።ምክንያቱም kissing ሰውነታችንን ለsex በማነሳሳት እና Dopamine Hormone እንዲለቀቅ በማድረግ በእኛ ዘንድ መመኘት እንዲሆን በማድረግ የልብ ንፅህናችንን የሚያቆሽሽ ስለሆነ ነው።

“ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኵሰት ሁሉ ወይም መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ፤”
— ኤፌሶን 5፥3

💋Kissing ለእነማን ነው የተፈቀደው
Kissing በቃል ኪዳን በእግዚአብሔር ፊት በቅድስና ለተጋቡ እና በትዳር ውስጥ ላሉ ባል እና ሚስት ብቻ ነው የተፈቀደው።ይህ ለፍቅረኛሞች የተሰጠ ወይም የተፈቀደ ነገር አይደለም! ይህ ልክ እንደ sex በትዳር ውስጥ ብቻ የተፈቀደ ነው። ነገር ግን ከትዳር በፊት ከንፈር ላይ መሳሳም ፍቅርን መግለጫ መንገድ ሳይሆን ለውድቀት እራስን መግፊያ መንገድ ነው የሚሆነው።

🚫ስለዚህ የወሲባዊ ቅድስናችሁን ትጠብቁ ዘንድ እጮኛሞች ተረጋጉ‼️ ዛሬ እጮኛሞች ስለሆናችሁ መሳሳም ይፈቀዳል ማለት አይደለም። ምክንያቱም kissing ለመጋባታችሁ ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም። እናንተ በእግዚአብሔር ፊት ዛሬም እህት እና ወንድም ናችሁ!

<ነገ እኮ እንጋባለን ምን ችግር አለው?>
በፍፁም! ይህ ማለት አሁን እንቆሽሽ በኋላ እንታጠባለን ማለት ነው። ስለዚህ ማንን ነው የምታታልሉት? እግዚአብሔርን ማታለል አይቻልም። በንፅህና እና በቅድስና ባልተሰራ ትዳር ደግሞ እግዚአብሔር አይከብርም! የወሲባዊ ኃጢአት ደግሞ ውሲባዊ ንፅህናን ያጠፋል።

“... ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።”
— ዕብራውያን 12፥14





@queen_B77
@queen_B77
@queen_B77

Strong girl's

07 Nov, 20:53


😆የቀድሞው የዙንባቤ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ የቀለዳቸውን አዝናኝ አስተማሪ እና ቁም ነገር አዘል ቀልዶች ለማግኘት ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ 🙏 😅🤣

እኔ በበኩሌ በጣም ያዝናናናኛል  ለናንተ ጋብዣችኋለው 🙏

Strong girl's

07 Nov, 20:32


በ ONLINE ገንዘብ መስራት ይፈልጋሉ ?

Strong girl's

07 Nov, 20:21


ከነዚህ ዉስጥ የማን ደጋፊ ኖት?

Strong girl's

07 Nov, 18:24


የኔ ቆንጆ...
ሰዎች ሲሰድቦሽ አንቺም መልሰሽ እንዳትሰድቢያቸው። ይልቁንም ፈገግ ብለሽ እለፊያቸው!
ሰዎች አትችይም ሲሉሽ ኧረ እችላለው ብለሽ መቻልሽን ለማሳየት አትሞክሪ። ይልቁንም ልክ ናችሁ ብለሽ እለፊያቸው!
እራስሽን በአፍሽ ወይም በንግግርሽ ለመግለፅ እንዳትሞክሪ። አንድ ነገር እወቂ። ማንም ምንም ሊናገር ይችላል። የተናገረውን ግን ሊያደርግሽ አይችልም። ሰዎች ስለ አንቺ ያላቸውን የተሳሳተ አስተሳሰብ በንግግርሽ ሳይሆን ጊዜው ሲደርስ አይደለሽም ያሉሽን ሆነሽ አሳያቸው። ያኔ እራሳቸውን በራሳቸው ያርማሉ። ስለ አንቺ ያላቸውን የተሳሳተ አስተሳሰብ በራሳቸው ያስተካክላሉ። አመለካከታቸው ይቀየራል!
በርቺልኝ!!!🥰🥰🥰





@queen_B77

Strong girl's

04 Nov, 16:50


🦋ድንግልና!🦋
በብዛት በማህበረሰባችን እንዲሁም በአከባቢያችን ሲባል እንደሰማነው ድንግልና ማለት ክብር ማለት ነው። አዎ ልክ ነው። ክብር ማለት ነው፣ በይበልጥ ደግሞ ምልክት የሚለው ቃል በደንብ ያብራራልናል። እንዴት? እስኪ ይህንን ቃል እንመልከት።
“በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤”
— 2ኛ ቆሮ 11፥2
በዚህ ቃል ውስጥ እንደምንመለከተው "እንደ ንጽሕት ድንግል" የሚለው ቃል ድንግልና የንጽሕና ምልክት እንደሆነ ያሳያል። ይህም ማለት እግዚአብሔር ወንድንም ሴትንም ሲፈጥር ድንግል አድርጎ ነው። ያም ደግሞ እግዚአብሔር ከትዳር በፊት የትኛውንም ፆታዊ ግንኙነት አጥብቆ እንደሚከለክል ያስረዳናል።

አንዲት ሴት ወይም አንድ ወንድ ድንግል ናቸው ስንል ምንም ዓይነት ፆታዊ ግንኙነት አርገው አያውቁም እያልን ነው። ይህም ማለት አንድ ባል ሚስቱ ድንግል ሆና ሲያገኛት ክብራን ስለመጠበቁዋ እና ንጹህ ስለመሆኗ ምልክት ነው ማለት ነው።

ድንግልና በሁለት ይከፈላል።
1. የስጋ ድንግልና
የስጋ ድንግልና ማለት የሚታይ ማለት ምልክት ማለት ነው። ወይም የሚታወቅ ምልክት ማለት ነው። ይህም ሴት ለመጀመሪያ ጊዜ ግንኙነት ስታደርግ ደም ሊፈሳት ይችላል። ይህንን የስጋ ድንግልና እንለዋለን።

ዘዳግም 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ እነሆም፦ በልጅህ ድንግልና አላገኘሁባትም ብሎ የነውር ነገር አወራባት፤ የልጄም ምልክት ይኸው ይላቸዋል። በከተማም ሽማግሌዎች ፊት ልብሱን ይዘረጋሉ።

“.... እኔ ይህችን ሴት ሚስት አድርጌ አገባኋት፥ በደርስሁባትም ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁባትም.....”
— ዘዳግም 22፥14

2.የልብ (የመንፈስ) ድንግልና
የልብ(የመንፈስ) ድንግልና ማለት በስውር ያለ ወይም የማይታይ ንፅህና ማለት ነው። ሁልጊዜ ኃጢአት ኃጢአት ከመሆኑ በፊት ምኞት ነበር። ምኞትም ምኞት ከመሆኑ በፊት ሀሳብ ነበር። ምክንያቱም ሀሳብ ምኞትን ይወልዳል! ምኞት ኃጢአትን ይወልዳል! ኃጢአትም ሞትን ይወልዳል! ሁልጊዜ አንድን ነገር ከማድረጋችን በፊት ስለዚያ ነገር አስበን ነበር። imagine አርገን ነበር። ከዛም ነው ወደ ተግባር የገባነው። የልብ(የመንፈስ) ድንግልና ማለትም ይህ ነው። የልብ ምኞት ማለት ነው። ድንግልና ማለት የንፅህና ምልክት ነው። መጽሀፍ ቅዱስ ላይ

“እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።”
— ማቴዎስ 5፥28

የሚለው ቃል ስለዚህ በደንብ ያስረዳናል ብዬ አምናለው። በልቡ የተመኘ ሁሉ በዚያኑ ሰዓት ደግሞ ከተመኘው ሰው ጋር አመንዝሮአል። ይህ ማለት ደግሞ የልቡን ድንግልና አቷል ማለት ነው።

“..... ድንግልናውንም በልቡ ይጠብቅ ዘንድ ቢጸና፥ መልካም አደረገ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 7፥37

ልባም ሴት ደግሞ ክብራን የምትጠብቅም ነች። ንጹህ ነች። ስለዚህ የኔ ቆንጆ ክብርሽን ንጽህናሽን ጠብቂ! ታማኝ ሁኚ። እግዚአብሔር የሰጠሽን ንፅህና በታማኝነት ጠብቂ!!!
በርቺልኝ!!!🥰🥰🥰





ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት
👇👇👇
@queen_B77
@queen_B77
@queen_B77

Strong girl's

04 Nov, 15:05


🛑ጥያቄ🛑
👉ድንግልና ምን ማለት ነው?

እስኪ ሃሳባችሁን comment ላይ አስቀምጡልኝ።

Strong girl's

03 Nov, 09:11


አንድ NOT Coin እና Dogs ይተካል ሚባል ምርጥ Airdrop መቷል 😉😉

ከተለመደው ለየት ባለ መልኩ እስካሁን በ Telegram ዋና ከሚባሉት Airdrop Claim ያረጋቹትን የToken ብዛት ቆጥሮ ነው በመጀመሪያ Point ሚሰጣቹ 🔼🔼

ሌላውን በደንብ አጣርቼ ነገራቹሀለው 📣📣

አንድ NOT Coin እና Dogs ይተካል ሚባል ምርጥ Airdrop መቷል 😉😉

ከተለመደው ለየት ባለ መልኩ እስካሁን በ Telegram ዋና ከሚባሉት Airdrop Claim ያረጋቹትን የToken ብዛት ቆጥሮ ነው በመጀመሪያ Point ሚሰጣቹ 🔼🔼

ሌላውን በደንብ አጣርቼ ነገራቹሀለው 📣📣

LFG!
PAWS is the new top dog! 🐾

https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=mjzzLs9r

Strong girl's

02 Nov, 12:43


“.....በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።”
— ዮሐንስ 15፥5

Strong girl's

02 Nov, 12:25


🦋ለብቻሽ መቆምን ልምጂ!🦋
ማንም ሰው በህይወት መንገዱ ማንንም ተሸክሞ አይሄድም። ምናልባት መንገዳችሁ አንድ ከሆነ እነርሱ እስከሚሄዱበት ቦታ ድረስ አብረውሽ ይሄዱ ይሆናል እንጂ ማንም ሰው የእራሱን መንገድ ትቶ ካንቺ ጋር አይሄድም። ሁሉም የራሱን መንገድ ነው የሚጓዘው። ሁሉም ወደ እራሱ ህልም ነው የሚሮጠዉ። ሁሉም በራሱ plan ነው የሚንቀሳቀሰው።

አዎ! በእራስሽ መቆምን ልምጂ! ምንም ነገር ለማድረግ ሰውን የምትጠብቂ አትሁኚ። አንቺ አንቺ ነሽ! ብቻሽን ምንም ነገር ማድረግ ትችያለሽ። የራስሽን plan ከሌሎች ጋር much አርገሽ ከእነርሱ ጋር ለመስራት አትሞክሪ። ከእግዚአብሔር ውጪ ማንም ለይ ጥገኛ አትሁኚ። አንቺ ብቻሽን ማድረግ የምትችይውን ነገር ከእከሌ ጋር ባደርግ ብለሽ plan አታውጪ። ማንም አብሮሽ የሚዘልቅ የለም። በእያንዳንዱ ጉዞሽ ላይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር እንደሆነ እርግጠኛ ሁኚ እንጂ ምንም ነገር አያስፈራሽ! ማንም እስከመጨረሻው ካንቺ ጋር የሚሆን የለም። ከእግዚአብሔር ውጪ! አንቺ እና እግዚአብሔር ካለሽ እመኚ ምንም ነገር ማድረግ ትችያለሽ። በእያንዳንዱ እርምጃሽ ላይ የሰውን እጅ ሳይሆን የእግዚአብሔርን እጅ ፈልጊ። እያንዳንዱን እርምጃሽን ከእግዚአብሔር ጋር አድርጊ። በእያንዳንዱ plan በምታደርጊው ነገር ላይ እግዚአብሔር ይኑርበት! እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ይሁን እንጂ ስለሌላው አትጨነቂ።
በርቺልኝ!!!🥰🥰🥰





ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት
👇👇👇
@queen_B77
@queen_B77
@queen_B77

Strong girl's

02 Nov, 05:50


https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=mjzzLs9r

LFG!
PAWS is the new top dog! 🐾

Strong girl's

30 Oct, 07:23


ከ60 ሴኮንዶች በኋላ ሰለሚጠፋ አሁኑኑ JOIN በማድረግ ተቀላቀሉ በቴሌግራም ምርጥ ከተባሉ ቻናሎች አንዱ ነው በእርግጠኝነት ይወዱታል።
ይቀላቀሉ

Strong girl's

29 Oct, 16:20


አንድ NOT Coin እና Dogs ይተካል ሚባል ምርጥ Airdrop መቷል 😉😉

ከተለመደው ለየት ባለ መልኩ እስካሁን በ Telegram ዋና ከሚባሉት Airdrop Claim ያረጋቹትን የToken ብዛት ቆጥሮ ነው በመጀመሪያ Point ሚሰጣቹ 🔼🔼

ሌላውን በደንብ አጣርቼ ነገራቹሀለው 📣📣

አንድ NOT Coin እና Dogs ይተካል ሚባል ምርጥ Airdrop መቷል 😉😉

ከተለመደው ለየት ባለ መልኩ እስካሁን በ Telegram ዋና ከሚባሉት Airdrop Claim ያረጋቹትን የToken ብዛት ቆጥሮ ነው በመጀመሪያ Point ሚሰጣቹ 🔼🔼

ሌላውን በደንብ አጣርቼ ነገራቹሀለው 📣📣

LFG!
PAWS is the new top dog! 🐾

https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=mjzzLs9r

Strong girl's

27 Oct, 18:41


ይነበብ

ሰላም 11ኛ ክፋል ነው ያቆሙክት ዘንድሮ አሁን የምገባው 12 ነው ግን በ ቤተሰብ እና በብር ማጣት  ምክንያት ትምህርቴን እየተከታለኩ  አደለም እና  እንኳን ሌላው ለመብላት እንኳን እየተቸገረኩ ነው አሁን ላይ ለምን ስራም ብፈልግ ማግኘት አልቻልኩም በቃ እኔ ስራ መስራት ላይበጣም ፍላጎት አለኝ ግን እንዴት እድሉን እንደማገኝ ግራ ገብቶኛል ። እኔ ብሩክ ከተማ ነኝ 0923475800 ደውሉልኝ እናንተ ናችሁ ተስፋዎቼ ለኔ እባካችሁን ችላ አትበሉኝ ደውሉና ቅጠሩኝ እባካችሁ  እኔ ሰርቼ መለወጥ እና ሀገሬንም ማገልገል እፈልጋለሁ

ቤተሰብስ ካላችሁ ልትሉኝ ትችላላችሁ እኔ ከአባቴ ጋር ነው የምኖረው ግን ለማደር እንኳን በግድ ነው የሚፈቅድልኝ ከበፊት ጀምሮ አይንህን ለአፈር ብሉኛል ምን እንደማደረግ ጨንቆኝ ነው

+251923475800 +251929142684
@Best1me በ ቴሌግራም አናግሩኝ ብሩክ

134200178 Abissniya

እናንተ ናችሁ ተስፋዎቼ አድራሻ አዲስ አበባ

Strong girl's

27 Oct, 18:39


እባካችሁ እርዱት


Inbox የተላከልኝ

Strong girl's

26 Oct, 17:16


አንድ አዛወንት በረንዳ ላይ ተቀምጦ ሳለ የቤት ሰራተኛዋ ፊት ለፊታቸው ያለውን መስታወት እየወለወለች ነበር። ከዛም ወልውላ ጨርሳ ልትሄድ ስትል "ማነሽ? ኧረ ቆሻሻውን አስለቅቂው! እዚያ ጋር ጭቃ አለ።" ብለው ይቆጣሉ። ሰራተኛዋም ተመልሳ በተሰጣት ትዕዛዝ መሰረት መስታወቱን አፀዳች። ጨርሳ ልትሄድ ስትል ግን አሁንም በድጋሜ " ኧረ በደንብ አፅጂው እዚያ ጋር ጭቃ አለ። አይታይሽም እንዴ?" ብለው ተቆጡ። ሰራተኛዋም መስታወቱን መለስ ብላ ስትመለከት ጭቃው ስላልታያት በመደናገጥ ምናልባት እኔ አልታየኝም ይሆናል! ብላ እንደ አዲስ ማፅዳት ጀመረች። ከዛም በደንብ እንደፀዳ እርግጠኛ ሆና ልትሄድ ስትል አሁንም ግን "እንዴ አንቺ ልጅ ምን ሆኔሻል ዛሬ? ጭቃውን ለምንድነው የማታነሺው?" ብለው ተቆጡ። ሰራተኛዋም ደንግጣ "ኧረ ጋሼ እስቲ በደንብ እዪት ምንም የለውም እኮ!" ብላ ግራ በመጋባት አየቻቸው። አባትየዉም "እኔ ታድያ ምንድነው የሚታየኝ እስኪ ነይ እዚህ ጋር ሆነሽ እዪው።" አላት። ሰራተኛዋም ግራ በመጋባት አዛወንቱ ጋር ሄዳ በድጋሜ ተመለከተችው። ነገር ግን አሁንም ምንም ባለመኖሩ ደንግጣ ወደ አዛወንቱ ስትዞር ያደረጉት መነፅር ላይ ጭቃ እንዳለ ተመለከተች እና በእነርሱ በኩል ልክ እንደሆኑ ተገነዘበች። ከዚያም " አባባ መስታወቱ ላይ ምንም የለም። እርሶን የሚታዮት መነፅሮ ላይ ያለው ጭቃ ነው። አምጡ ላፅዳልዎት እና ደግመው ያዩታል።" ብላ መነፅሩን አፅድታ መለሰችላቸው። አዛወንቱም ድጋሜ ሲያዩት መስታወቱ ንፁህ ሆኖ አገኙት። ከዛም " አይ ልጄ ለካ ጭቃው ያለው መስታወቱ ላይ ሳይሆን መነፅሬ ላይ ነበር! በይ እንግዲህ ይቅር በይኝ። " አሉ።

የኔ ቆንጆ ስለ አንድ ችግር ከመናገርሽ በፊት መጀመሪያ ችግሩ ከየት እንደሆነ ለዪ!!!




🦋@queen_B77🦋

Strong girl's

25 Oct, 16:25


You are your own queen! 👑 Think like a queen!
Walk like a queen!
Do everything like a queen!

Strong girl's

24 Oct, 18:29


#MoE

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity

Strong girl's

24 Oct, 15:50


🦋አንድ አይነት ሁኚ!🦋
አንዳንዴ ወዳጆቼ ናቸው ያልሻቸው ከልብሽ ያቀረብሻቸው ሰዎች ሲከዱሽ እና ትላንት ይወዱኛል እኔም እወዳችኋለሁ ያልሻቸው ዛሬ ጠልተውሽ አንቺ ብቻሽን ስትወጃቸው እራስሽን ታገኛለሽ። ህይወት ተገላቢጦሽ ነው። አንዳንዴ ሳያቸው ገና ጠላኋቸው ጥሩ ሰዎች አይመስሉም ያልሻቸው ድንገት ስትቀርቢያቸው ያልጠበቅሽውን መልካምነት እና የሚያምር ማንነታቸው ያስደነግጥሻል። አንዳንዴ በሩቁ አስተያየታቸውን ብቻ አይተሽ የሚጠሉሽ የመሰሉሽ ሰዎች ስትቀርቢያቸው ላንቺ ያላቸው ፍቅር እና አክብሮት ያስገርምሻል። አንዳንዴ እኮ ህይወት እንደዚህ ነች። እንዲህ ይሆናል ያልሽውን ባልጠበቅሽው መንገድ ታገኚዋለሽ። አንቺ ግን ማንም ስለተቀየረብሽ ማንም ላይ አትቀየሪ! ሰውን በሰውነቱ ውደጂው እንጂ ስለወደዱሽ ወደሽ ስለጠሉሽ አትጥዪ! አንድ አይነት ማንነት ይኑርሽ። ያ ነው ልባምነት!!!
በርቺልኝ!!!🥰🥰🥰





🦋@queen_B77🦋

Strong girl's

24 Oct, 10:40


ሻማን ማን አቃጠለሽ ቢሏት ከተሎኮሰብኝ ክብሪት ይበልጥ አቅፌ የያዝኳት ክር ናት!

Strong girl's

24 Oct, 10:40


የሆነ እድሜ ላይ ሁላችንም ሳቂቶች ነበርን!

Strong girl's

22 Oct, 18:32


🦋ተነሺ!🦋
ማነው ስለሚፈልገው ነገር ዓልሞ የሆነለት? ማነው መሆን ስለሚፈልገው ነገር ስላሰበ እና በአይምሮው imagine ስላረገ የፈለገበት የደረሰው?
ሁልጊዜ በዓይምሮሽ የምታስቢው ነገር አለ፣የምትስዪው ነገር አለ። እንደዚ ሆኜ ፣እንደዚህ አድርጌ፣ በዚህ ወጥቼ ፣ያንን አሳክቼ፣እዚህ ደርሼ፣ ያንን መኪና ገዝቼ፣ እንደዚህ ለብሼ፣ እዚህ አገር ነው የምኖረው፣ ይሄን ያህል ውጤት አምጥቼ፣.....እና ብዙ ብዙ!
Even አንድ ቀን እገዛቸዋለው ብለሽ screenshot ያደረግሻቸውን ልብሶች እና እቃዎች አስቢ። መቼ ልትገዢያቸው ነው ያስቀመጥሻቸው? በአይምሮሽ imagine የምታደርጊውን life መቼ ይሆን የምትኖሪው?

አዎ! የኔ ልባም ሴት...! ተነሺ! ካንቀላፋሽበት የምኞት እና የቅዠት አለም ንቂ እና በእውነቱ አለም ላይ የምትፈልጊውን ህይወት ስሪ! ደኅ <በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ፣
እከክ ይጨርሰው ነበር ።> እንደተባለ በማይመች ህይወት ውስጥ እየኖርሽ የሚመቸውን ህይወት በአይምሮሽ እየሳልሽ እራስሽን አታታልዪ! በስራ እንጂ በማለም ምናልባት እገዛዋለው ያልሽውን መኪና በህልምሽ ትነጂው ይሆናል እንጂ መቼም በእውንሽ መሪውን አትይዢም!
ተማሪ ነሽ? በአይምሮሽ ጥሩ ውጤት ስታመጪ መሳሉን ተይና ተነሽ አንብቢ!
ሰራተኛ ነሽ? በአይምሮሽ ጥሩ ህይወት ስትኖሪ፣ መኪና ስትገዢ፣ ቤት ስትገዢ ማለሙን ተይና ተነሺ ስሪ!
የቤት እመቤት ነሽ? አንቺም ባሌ እንዲ ቢያደርግ ይሄን ቢገዛልኝ፣ እኔማ ቀጣይ አመት ስራ ጀምራለው፣ ማለትሽን ትተሽ ተነሺ እና ከማይመቸው ህይወት ለማምለጥ ስሪ! አንቺ ቤት መሆንሽ እና ቢሮ መሆንሽ ሳይሆን ልዩነት የሚፈጥረው ልጅ እያሳደግሽም ቢሆን ሁኔታዎችን እንዴት ወደ Business መቀየር እንደምትችይ ማሰብሽ ነው። ልዩነት መፍጠር የሚችለው አስተሳሰብሽ ነው። ካሰብሽ ቤትሽንም ቢሆን ቢሮ ማድረግ ትችያለሽ! ስለዚህ ተነሺ ሁኔታሽ እንዲይዝሽ እና እንዲገድብሽ አትፍቀጂለት። ምክንያቱም ትችያለሽ! የፈለግሽበት፣ ያሰብሽውን፣ ያለምሽውን ህይወት መኖር ትችያለሽ!
በርቺልኝ!!!🥰🥰🥰





🦋queen_B77🦋

Strong girl's

22 Oct, 16:13


Betty እባላለሁ እድሜ  23 ነው በጣም ቆንጆ  እና ለ kiss የሚገፋፋ ከንፈር አለኝ ስራዬ የ ሆቴል  አስተናጋጅ ነኝ
በምሰራበት ሆቴል በጣም ብዙ ደምበኞች ነበሩኝ  ቀኑን ባላስታውስም ወደ 2:30 አካባቢ ይሆናል ከደንበኞቼ አንዱ መኝታ ቤቱ ድረስ ቢራ እንዳመጣለት ይጠይቀኛል እኔም ቢራዉን ወሰድኩለት ክፍሉ ስገባ ግን ያልጠበኩት
see more....

Strong girl's

22 Oct, 15:51


ከ30 ደቂቃ በዋላ ይጠፋል

የ100 ብር ካርድ የሚያሸንፍ ጥያቄ?

10+10*0+10=???

Strong girl's

20 Oct, 20:03


በሰዎች ሰበብ የተፈጠሩ ሕመሞች...
እግዚአብሔር በፈጠራቸው ውብ ጥርሶች ይሸፈናሉ

𝑠𝑜 𝑗𝑢𝑠𝑡 ...

Strong girl's

19 Oct, 09:11


ቆንጂዬ ጨው ውሃ ልትቀዳ ሄዳ በዛው ሟምታ ቀርች ይባላል መለወጥ ከማትችይው ጋር ስትታግዪ ራስሽን እንዳታጪ ተጠንቀቂ!

Strong girl's

18 Oct, 16:41


🦋ደከመኝ?🦋

አቃተኝ? ዛልኩኝ ነው ያልሽው...?በቃ ተስፋ ልቆርጥ ነው ያልሽው የኔ ልባም ሴት?

ቆይ!
ቆይ አንዴ ስሚኝማ! ተስፋ ከመቁረጥሽ በፊት አንዴ ስሚኝ!
የት ነበር እደርሳለሁ ብለሽ መንገድ የጀመርሽው? የቱ ጋር ነበር ህልምሽ? ምን እሆናለው ብለሽ ነበር ትምህርት የጀመርሽው? አስታወሽው ያኔ ድካምና ዝለትን በማታውቂበት ጊዜ አስተማሪሽ፣እናትሽ፣አባትሽ
<ምንድነው መሆንየምትፈልጊው >ስልሽ ምን እንዳልሽ አስታወሽ? ያኔ እራሴ አደርገዋለው ብለሽ እንጂ በማንም ላይ ታምነሽ አልነበረም መሆን ምትፈልጊውን የተናገርሽው።በልጅ አእምሮሽ ቀላል እንደሆነ አስበሽ አይምሰልሽ!ምክንያቱም ብዙዎቹ መሆን የሚፈልጉትን የሆኑት እንደ ህፃንነታቸው ጊዜ ቀላል ነው እያሉ ነው።ምክንያቱም ከባድ ነው ብለው ለአእምሮአችን ከነገርሽው ልክ ልንሰራ ስንል እሱ በተራው ከባድ ነው አትችይም ይልሻል። ለዚህ ነው ህፃንነትሽን ልጅነትሽን አስታውሺ ያልኩሽ። ልጅ ሆነሽ ለመሄድ ስትሞክሪ ስንት ጊዜ ወድቀሽ ነበር? ብዙ ጊዜ አይደል! ግን እኮ ወደኩ ብለሽ አልተሸማቀቅሽም፣አላፈርሽም። እንደውም ልክ እንደጫወታ ድጋሜ ለመሞከር ተነስተሽ ነበር አይደል?አዎ! አየሽ ህፃንነት ማለት ማድረግ የሚፈልገው ህልሙ እንጂ ስራመድ ወደኩ ብሎ የሚመለስ አይደለም! ማፈርን አያቅም። እስቲ ልጠይቅሽ ያኔ አፍሽን ልትፈቺ ስትዪ ለማውራት ስትሞክሪ ስትንተባተቢ ሰዎች ሰምተውሽ ሲስቁ ለምን ሳትሳቀቂ? ለምን ማውራትሽን ሳታቆሚ?

አዎ! የኔ ልባም ሴት...!አንዴ ያንን ጊዜ አስታውሺው! አሁንም ተስፋ አለ! በአንድ ወቅት ላይ እየፃፍሽ ቢበላሽብሽ ወረቀት ትቀይሪአለሽ አይደል? ልክ እንደዛ አሁንም መንገድሽን መቀየር ትችያለሽ። መንገድሽን ቀይሪ እና እዪው።አስተሳሰብሽን፣አሰራርሽን መቀየር አለበት ያልሽውን በሙሉ ቀይሪ።መሆን ለምትፈልጊውን ነገር መገኘት ለምትፈልጊው ቦታ ዛሬ መክፈል ያለብሽን ዋጋ ክፈዪና ማድረግ ያለብሽን ነገር አድርጊና ነገ በትላንትናሽ ኩሪ!
በርቺልኝ!!!🥰🥰🥰





🦋@queen_B77🦋

Strong girl's

15 Oct, 16:12


ዛሬ የቻናላችን ኦነር እና በልዩ ፁሁፎቿ ምናቃት ፂዮን ልደት ነው እንኳን ተወለድሽልን ምኞታችሁን ግለፁላት
@tsi_ad0

Strong girl's

15 Oct, 04:26


እንካ እድሜዬን ተጠቀምበት
በልብህ እንዳለው አከናውንበት

Hbd to me🙏

Strong girl's

12 Oct, 21:56


እግዚአብሔርን ስትይዢ ሴትነትሽ ሞገስ አለው!

Strong girl's

12 Oct, 09:56


If have you dream
Always you are winner

Strong girl's

11 Oct, 23:49


ምን ይታይሻል?
አሁን ካለሽበት ቦታ ሆነሽ ምንድነው የሚታይሽ ? ምን ማድረግስ ትፈልጊያለሽ ? ሁሌ አደርገዋለሁ ብለሽ ቃል እየገባሽ የተውሽው ነገር ምንድነው ?
የመረጥሽውን ሁሌ ለማድረግ የምትመኚውን ከማድረግ ጀምሪ የግድ መጨረሻውን አውቀን መጀመር አይጠበቅብንም እሱ የኛ ስራ ሳይሆን የፈጣሪ ስራ ነው !
ከምን ለመጀመር አሰብሽ ?

Strong girl's

11 Oct, 20:59


ታገሺና አሸንፊ!

Strong girl's

11 Oct, 18:38


ላንቺ ብሎ የሚወጣ ላንቺ ብሎ የሚጠልቅም ፀሀይ የለም በመምሸት በመንጋት ውስጥ ግን የራስሽን ታሪክ መስራት ጀግንነት ነው ።

የዘመንሽ ጀግና ለመሆን ሞክሪ!

Strong girl's

09 Oct, 18:09


" በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ ሁሌም ጥፋተኛዋ አንቺ ነሽ " 🙃🥺
ጥፋታቸውንና በደላቸውን ሆነ ብለሽ አውቀሽ እንዳላወቀ ስታልፊ😔 ሞኝ አድርገው ያስቡሻል ፣ መሳሳታቸውን ስትነግሪያቸው ደግሞ ተጨቃጫቂ ያደርጉሻል 👩‍🦯 አብረሻቸው መሆንን በፈለግሽበት ሰአት ቢዚ እንደሆኑ ነግረውሽ ለራስሽ ጊዜ መስጠት ስትጀምሪ ተለውጠሻል ምን አግኝተሽ ነው ይሉሻል😏እነርሱው እንድትርቂ ምክኒያት ሁነው ከአይናቸው ዘወር ስትይ ተውሽን ብለው ሊወቅሱሽ ይዳዳሉ 🤔 በቃ ምንም አይጨበጡም እነሱው አስለቅሰውሽ እነሱው ካላባበልንሽ ይላሉ 🤷‍♂ እነሱው ሳቅሽን ሰርቀው እነሱው አኩራፊ ይሉሻል ፣ እነሱ ያሻቸውን ተናግረውሽ ቆየት ብለው አፌ ነው እንጂ ሆዴኮ ባዶ ነው ብለው ይሸነግሉሻል😖😖 አንቺ ተስቶሽ የተናገርሻትን አንድ ቃል ግን ሁሌ እያነሱ ሊያሸማቅቁሽ ይሞክራሉ🥺ይኼን ፈርተሽ አዉቀሽ እንዳላወቀ ሆነሽ ዝም ስትዪ ዝምታ አልወድም ዝምታሽ ይጨንቀኛል ይሉሻል .....😒 በቃ በአንዳንዶች ዘንድ አንቺ መቼም ልክ አትሆኚም ዛሬም ጥፋተኛዋ እኔ ነኝ🏃‍♀🏃‍♀
@strong_grlis

Strong girl's

05 Oct, 16:35


😢ነገሮች በፈለከሽው መንገድ ላይሄዱ ይችላሉ፣ ሰዎች ጀርባቸውን ሊያዞሩብሽ ይችላሉ፣ በዚች አለም ለመኖር የሚያጓጉህሽ ነገሮች ሁሉ ልታጪ ትችያለህ፤ ግን ሁላችንም በዚህ ስሜት ውስጥ አልፈናል ወደፊትም እናልፍ ይሆናል።

ታላቅነት ግን በዚህ ከባድ ጊዜ መቼም ተሰፋ ቆርጠሽ ጥረትሽን እንደማታቆም ለራስሽ ቃል መግባት ነው!💪

@Strong_Grlis
@Strong_Grlis

ለማንኛውም ሃሳብ፣ አስተያየት፣ጥያቄ፡-@tsi_ad0

Strong girl's

04 Oct, 15:24


🦋በራስሽ ሲሆን ያሳመመሽን...
...በሌሎች አታድርጊ!🦋
አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን ውስጥ ትልቅ ቦታ የሰጠናቸው እና ከልባችን ወደናቸው እና አክብረናቸው ከቀረብናቸው በኋላ ድንገት ሲቀየሩብን እና ከሰጠናቸው፣ካሰብናቸው ልክ እና በአይምሮአችን ከሳልናቸው የማንነት ደረጃ ድንገት ወርደው ስናገኛቸው በጣም ይከብዳል አይደል?
ውስጣችን ይያዝባቸዋል።የለመድነው ፍቅር ሲቀርብን የለመድነው አክብሮት ወደ መናቅ ሲቀየርብን ይከፋናል።እናዝናለን።

አዎ! የኔ ልባም ሴት...!በራስሽ ሲሆን ያሳመመሽን በሌሎች በፍፁም አታድርጊ። አስታወሽ ያንን ጊዜ የኔ ያልሻቸው ሰዎች በከዱሽ ጊዜ በተቀየሩብሽ ጊዜ ምን ያህል እንደከፋሽ! ምን ያህል እንዳዘንሽ! ምን ያህል እንዳለቀሽ! ምናልባትም ከልብሽ ይቅር ማለት ከብዶሽ የተቸገርሽበትን ያንን ጊዜ አስታወሽው? በጣም ይከብድ ነበር አይደል?
አዎ!በጣም ያማል።ስለዚህ ባንቺ ላይ ሲሆን ያሳመመሽን ነገር በሌሎች ላይ በፍፁም እንዳታደርጊ። አንቺ በእነዛ ሰዎች እንደተከፋሽ ሌሎች በአንቺ እንዲከፉ አታድርጊ!ምክንያቱም ልባምነት የሚጀምረው በመልካምነት ነው!!!
በርቺልኝ!!!🥰🥰🥰





🦋@queen_B77🦋