🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸 @palestine_history Channel on Telegram

🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸

@palestine_history


🇵🇸
I DREAM OF A DAY TO SEE A FREE PALESTINE
˚˚˚
ፍልስጢናውያኖች ስለ ሙስሊሙ ሁሉ ኡማ ክብር ታሪክ ንብረት እና ማንነት ሲሉ ነፍሳቸውን እየገበሩ ያሉ ጀግናና ፅኑ ህዝቦች ናቸው።ጉዳያቸው ጉዳያችን ህመማቸው ህመማችን ሊሆን እያንዳንዳችን ስለ ፍልስጢን ያገባናል ይመለከታል!እነሱ ከኛ እኛም ከነሱ ነን🤎!
˚˚˚

ስለ ፍልስጢን ብቻ😉!

🇵🇸 ፍልስጢን 🇵🇸 (Amharic)

ፍልስጢናውያኖች ስለ ሙስሊሙ ሁሉ ኡማ ክብር ታሪክ ንብረት እና ማንነት ሲሉ ነፍሳቸውን እየገበሩ ያሉ ጀግናና ፅኑ ህዝቦች ናቸው። ጉዳያቸው ጉዳያችን ህመማቸው ህመማችን ሊሆን እያንዳንዳችን ስለ ፍልስጢን ያገባናል ይመለከታል! እነሱ ከኛ እኛም ከነሱ ነን🤎! በሙስሊሙ ኡማ እንዴት እንደሚታያለን? ይህ የህዝብ ታሪኩን እና ማንነትዎን የሚገልጽ ጀግናና ፅኑ ህዝብ ናቸው። ፍልስጢን ትምህርት ከሆነ፣ ታሪኩን ማስተካከልና ምርጥ እና እንኳን አላስተዋልም! ይህን ቦታዎን ለማንኛውም ሰው የፍልስጢን ታሪኩን የሚገልጽበት ተጨማሪ ተቆጣጠር ይሆናል! ፍልስጢን የሚባለውን ነፃነቱን ስለብቻ በመጠቀም በከረመ ማድረግ ይችላል 😊!

🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸

14 Oct, 03:03


😊ስለ ፍልስጢን አዳዲስ መረጃ ከፈለጋቹ ከስር ባለው የቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ👇👇👇👇
@OUR_Palestinians
@OUR_Palestinians

🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸

05 Jan, 17:25


ከሪም ዩኑስ ለ 40 አመት በፅዮናዊያን እስር ቤት ታስሮ ከቆየ ቡሀላ በዛሬው ቀን ተፈቷል።

🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸

02 Jan, 15:42


📸በ2022 ፍልስጢን በወራሪው የፂዮናዊው መንግስት የግፍ ግድያ ያጣቻቸው ልጆቿ ምስል

🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸

02 Jan, 15:42


ባሳለፍነው የአውሮፓውያኑ 2022 አመት ውስጥ

📯56.815 የሁዶች ወደ ተከበረው መስጂደል አቅሳ ግቢ ገብተዋል (ካሳለፍናቸው አመታቶች አንፃር በ2022  የሁዶች በአቅሳ መስጂድ ላይ እጥፍ ነፃነት አግኝተዋል)

📯ከጋዛ ከተማ ብቻ 53 ህፃናት ተገለዋል

📯ከቁድስ ከተማ 18 ሰዎች ሸሂድ ሆነዋል

📯2998 የቁድስ ከተማ ነዋሪ ታስሯል

📯223 ፍልስጢናውያን ቤተሰብ መኖርያ ቤቶችን በግፍ ፈርሰው ቤት አልባ ተደርገዋል

📯222 ፍልስጢናውያን ከቤቱ እንዳይወጣ ታግዷል

📯967 ፍልስጢናውያን ከመስጂደል አቅሳ/ከቁድስ ከተማ እንዳይቆይ ተባሯል

©ፓለስታይን ፔጅ
©ኩሉና መርየም
©ሀዋሪተል አቅሳ
📮@palestine_history

🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸

01 Jan, 10:03


@palestine_history

🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸

27 Nov, 05:34


╔═══════════════╗
ኢዘዲን አልቀሳም
╚═══════════════╝

እሱ ከሶሪያ ወደ ፍልስጤም በመምጣት የራሱን የትግል እንቅስቃሴ የጀመረ ድንቅ ሙጃሂድ ነው፡፡ የመንግሥት ሠራተኛ በመምሰል በብዙ የፍልስጤም ክልሎች እየተዘዋወረ በአምስት አምስት አባላት የተደራጁ ህዋሳትን በሰፊው ያዋቀረው ኢዘዲን አልቀሳም ነው፡፡ ኢስላማዊ ህግጋት የትግሉ መመሪያ መሆን እንዳለባቸው አስተምሯል፡፡ ብቸኛው የነፃነት መንገድም ጂሃድ ፊ ሠቢሊላህ መሆኑን አስምሮበታል፡፡ አፅንዖትም አድርጎበታል፡፡
ይህ በኢዘዲን አልቀሳም የተደራጀ የህቡዕ ንቅናቄ በዓይነቱ ለየት ያለና በዓረብ ፍልስጤሞች የትግል ታሪክ ትልቁ የመስዋዕትነት ንቅናቄ ሆኖ ዘመናትን ተሻገረ፡፡ ማዘዣ ቢሮዎቹ ደሃው ህዝብ በሚበዛበት የኢያሪኮ ከተማ ነበር፡፡ በአካባቢው ላይ ተቀባይነት እያገኘ ሲመጣ አደረጃጀቱን አሰፋ፡፡ የዳዕዋ፣ የወታደራዊ ሥልጠና፣ የአቅርቦት፣ የኤሌክትሮኒክስና የውጭ ግንኙነት አካላትን በመፍጠር አቋሙን ይበልጥ አጠናከረ፡፡
እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1935 ኢዘዲን አልቀሳም የአብዮቱን መጀመር ይፋ አደረገ፡፡ ይህም የሆነው ሠላማዊ መፍትሄ የማፈላለጉ ጥረት በተደጋጋሚ ተሞክሮ ያለውጤት መቅረቱ እውን ከሆነ በኋላ ነበር፡፡ የአብዮቱን መጀመር ተከትሎ በቀሳም ታጣቂዎችና በእንግሊዝ ጦር መካከል ተከታታይ ግጭቶች ተካሄዱ፡፡ ብዙ ፍልሚያዎች ተደረጉ፡፡ አልቀሳም ማፈግፈግ ግድ ሆነበት፡፡ ከተወሰኑ የጦር ጓዶቹ ጋር አንድ ቦታ ላይ ከበባ ተደረገበት፡፡ እጁን በሰላም እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡ አልፈቀደም፡፡ በተከተለው የተኩስ ልውውጥ አቅጣጫዋ በውል ያልተለየ ጥይት አገኘችው፡፡ ተገደለ፡፡ በተቀሩት ጓዶቹና በእንግሊዝ ጦር መካከል የከረረ ውጊያ ተካሄደ የሞቱት ሞተው የተቀሩት ጠላት እጅ ላይ ወደቁ፡፡
አልቀሳም የመሰዋቱ ዜና ሲሰማ መላው ፍልስጤም ተላወሰ፡፡ የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ለፍልስጤማዊያን ሌላ የትግል ቃል ኪዳን ማሰሪያ ቀን ሁኖ ዋለ፡፡ የቀሳም ንቅናቄ በዓላማውና በተነሳሽነቱ ረገድ በዓይነቱ የመጀመሪያ፣ በአይሁዶችና በእንግሊዞች ላይ በቀጥታ ያነጣጠረ ወታደራዊ ንቅናቄ ነበር፡፡ኢዘዲን አልቀሳም ለፍልስጤም ነፃነት መዋጋትን ሊላህ ብሎ ኒያው አድርጎ ከሶሪያ ወደ ፍልስጤም በመምጣት ኑሮውን እዚያው ያደረገ አላህን ፈሪ ሰው ነበር፡፡ እሱ ባቀጣጠለው ስውራና በከፈለው መስዋዕትነት በፍልስጤሞች ዘንድ የላቀ ተነሳሽነት ተፈጠረ፡፡ ህዝቡ ተቀሰቀሰ፡፡ በእርግጥም እሱ ያመላከተው የትግል መንገድ፣ የውጊያ ስልትና የተጋፋጭነት አቋም ትምህርት ሰጪ ነበር፡፡ የአይሁድ/ እንግሊዝን ጣምራ ኃይል ጂሃድን መርሁ ባደረገ ስሌት መዋጋት እንደሚያስፈልግ በሁሉም ፍልስጤማዊ ዘንድ እየታመነበት መጣ፡፡ እስከዛሬም ድረስ ቀሳም በሚል ፅሑፍ አናታቸው ላይ በማሰር መፋለሙን ተያያዙት።
በቀሳም መሞት የፍልስጤም አብዮት አብሮ አልሞተም፡፡ ነገሮች ቤንዚን እንደተርከፈከፈበት እሣት ይበልጥ ተቀጣጠለ፡፡ የ1936ቱ የረዘመ አብዮት ፈነዳ፡፡ የሥራ ማቆም አድማ፣ ተገዳዳሪ ሠልፍ፣ ለቅኝ አገዛዝ ህጎች አልታዘዝ ባይነት፣ የዚህ አብዮት ዓይነተኛ መለያዎች ነበሩ፡፡ ህዝባዊ አመጹ ብረታዊ ድጋፍም እየታከለበት ቀጠለ፡፡
ሁኔታው በፍልስጤሞች ወገን ባጭሩ ከላይ የተወሳውን ዓይነት ገጽታ ሲኖረው በአይሁዶች በኩል ደሞ የተጀመረው አፍራሽ ድርጊት በእንግሊዝ ጦር ሽፋን ሰጪነት እንደቀጠለ ነበር፡፡ በ1940ዎቹ ይበልጥ እየተጠናከረና ዓይን እያወጣ የመጣው የጽዮናዊያን እንቅስቃሴ ጭፍን ደረጃ በመድረስ የ1948ቱን የአይሁድ መንግሥት (Jewish state) ምሥረታ እውን አደረገ፡፡
ፍልስጤሞች ይህን ፈጣጣ ድርጊት በይሁንታ አላለፉትም፡፡ በቁጥርና በትጥቅ ከፍ ብሎ ተጠናክሮ ከተጋረደባቸው የእንግሊዝ ጦርና የአይሁድ ሠፋሪ ታጣቂ ኃይል ጋር እጃቸው ላይ ባለ ነገር ሁሉ ተፋለሙ፡፡ የተቀሰቀሰው የህዝበ ፍልስጤም ቁጣ በዋዛ እንደማይበገር የተረዱት እንግሊዞችና የአይሁዶች ሠፋሪ የተነሱበትን ግዛት የማስፋት እቅድ ዳር ለማድረስ ሲሉ እስከዛሬ ድረስ ጠባሳው ያልሻረውንና በሙስሊሙ ዓለም በተለይም ዓረብ ፍልስጤም ዘንድ መሪር ትውስታ ያስከተለውን አንነክባ ተብሎ የተሰየመውን የሜይ 15/1948ቱን አስከፊ ድርጊት በፍልስጤም ሠላማዊ ህዝብ ላይ ፈፀሙ፡፡

╔═══════════╗
@palestine_history
@palestine_history
@palestine_history
╚═══════════╝

🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸

18 Nov, 18:06


ሺ ጊዜ የንግግር ጠቢብ ቢኮንም የፍልስጤሞችን ጀግንነት በሰው ልጅ ቋንቋ መግለጽ አይቻልም

┈┈❈••✦ ✾ ✦••❈┈┈

የ19 ዓመቱ መሽቀርቀር የሚወድ እና ብዙ ጊዜ ሰልፊ ፎቶ መነሳት የሚያስደስተው አዳዲስ ልብሶችና እስማርት የሞባይል ስልኮችን የሚቀያየር ዑመር አቡ ለይሊ የተባለ ወጣት ከወደ ፍልስጤም ለመስጂደል አቅሳ ክብር ህይወቱን አሳልፎ ሰጠ። የቱንም ያክል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የማረከው ወጣት ቢሆንም በኢስላም ላይ ያየውን ውርደት አይቶ ለማለፍ ዘመናዊ ቁሶቹ አባብለው እንዲታገስ ሊያደርጉት አልቻሉም። የመስጂደል አቅሳ መደፈር አንገበገበው።

ወደ አቅሷ ጉዞ ጀመረ። የመስጂዱ በር በእስራኤል ወታደሮች መዘጋቱን ተመለከተ። በሩን ክፈቱልኝ ሲልም ጠየቀ። ወታደሮቹም አንከፍትልህም ነበር መልሳቸው። መስጂዱ የእኛ ነው እናንተ ስለዚህ በርም ሆነ ስለ መስጊዱ ምን አግብቷችሁ ነው አዛዥ የሆናችሁት? በመለት ጮኸ። እንደማይከፍቱለት ነገሩትና እንቢ ካለ እርምጃ እንደሚወስዱበት አስፈራሩት።

ከመስጂዱ ትንሽ ራቅ ብሎ ከተጓዘ በኋላ አንዱን የአይሁድ ወታደር መሳሪያውን ቀምቶ አካባቢው ላይ ባሉ የእስራኤል ነፍሳት ላይ ሁሉ በራሳቸው ጥይት ገደላቸው። እሱን ለማግኘት ከ300 በላይ የእስራኤል ጦር ተሰማራ። በመጨረሻ በአንድ ከሀዲ ፍልስጤማዊ ጠቋሚነት ተደብቆ የነበረበትን ቦታ የእስራኤል ወታደሮች በከባድ መሳሪያ ሳይቀር መደብደብ ጀመሩ።

እጅ ሳይሰጥ አንድ ጥይት እስክትቀረው ድረስ ብቻውን ከመቶ በላይ የእስራኤል ወታደር ጋር ተታኩሶ ሸሂድ ሆነ። በቤቷ ደብቃው የነበረችውም የአንዲት አሮጊት ቤት በዶዞር እንዲፈርስ ተደረገ።
ዑመር አቡ ለይሊን የአይሁድ መገናኛ ብዙሃኖች ሳይቀሩ የፍልስጤም ራንቦ ብለው ሰየሙት።
ለአቅሷ የተሰውትን ጀግኖች ሁሉ አላህ ጀነተል ፊርደውስን ይሸልማቸው።

┈┈❈••✦ ✾ ✦••❈┈┈

👇👇👇👇👇
@palestine_history
@palestine_history

🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸

18 Nov, 15:14


አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ

እጅግ ውብና አስገራሚ የፍልስጢን ታሪኮችን የጀግኖቻችንን ወግ በአዲስ ወኔ በአዲስ መንፈስ ወደናንተ ልናደርስ ተዘጋጅተን ጨርሰናል ከነገ ጀምሮ ዘወትር 3 ሰዓት የምናደርሳችሁ ይሆናል ኢንሻ አላህ

🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸

25 Oct, 15:54


ሳሚያ ትባላለች የመጀመሪያዋ እና ብቸኛዋ በቁድስ ከተማ የምትገኝ ሴት የባስ ሹፌር ናት

@palestine_history

🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸

25 Oct, 12:42


📸ለናብሌስ ከተማ ሸሂዶች ሽኝት እየተደረገ

🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸

25 Oct, 07:21


#Quranic_Reflection ♡

واقصد في مشيك ... واغضض من صوتك
« በአካሄድህም መካከለኛ ኹን ፤ ከድምጽህም ዝቅ አድርግ፡፡» ٣١:١٩ 🥰

ታላቁ ሰው ሉቅማን ልጁን ከመከራቸው ምክሮች ሁሌም በህይወቴ ላይ ተግባራዊ ማድረግን ከምፈልጋቸው ምክሮች በዋነኝነት እነዚህን ሁለቱን ነው! ♡

" ወቅሲድ ፊ መሽዪክ "

በህይወት ጉዞ መንገድ ላይ በዝግታ መራመዱም በፍጥነት መራመዱም እንደማያዋጣ ያስታውሰኛል ፤ ለምንም ስራ ይሁን ሀሳብ ሰከን ያለ እርምጃ እንደሚያስፈልገው ፤ መካከለኛ የሆነው አረማመድ ፤ አንድ በአንድ መሰናክሎችን የሚያልፈው አረማመድ ፤ ኢስቲቃማ ያለው አረማመድ እንደሆነ ይታወሰኛል። 🤎

በሌላ በኩል ደግሞ 'قصد' ማለት ሌላኛው ፍቺው አላማ ማለት ከመሆኑ ጋር ጉዞዬ በአላማ የታጀበ ጉዞ ፤ ከፍ ያለው ግቡ ጋር ለመድረስ ከስር የሚጀምር ጉዞ ፤ ሁሌም አቅጣጫ አመላካቹን አል-ራህማን ፊት ለማስቀደም የሚጥር እና የረሱለላህን ሲራ እንደ ኮምፓስ የሚጠቀም ጉዞ እንደሆነ ያስረዳኛል። 🤎

" ወግዱድ ሚን ሰውቲክ "

በዚህ መካከለኛ እርምጃ ላይ ትልቁ አስኳል ድምፅን ዝቅ ማድረግ ነው ፤ ብዙ ሙፈሲሮች 'መካከለኛው ጉዞ ዝቅ ካለው ያልተንጫጫ ድምፅ ጋር ካልተጣመረ ዋጋ የለውም' ይላሉ።

ያልተንጫጫ ድምፅ ፤ የማይረብሽ አንደበት ፤ ድምፅን ዝቅ አድርጎ መስራት ፤ ጎልቶ መታየትን አለመውደድ(Attention Seeker አለመሆን) ፤ በምንሰራው እና በምንሰጠው ሀሳብ ላይ የሰዎችን Approval አለመጠበቅ ብሎም እጁጉኑ አለመውደድ ፤ ስራችን ብዙ ላይክ/ቪው ይኑረው ትንሽ ላይክ ተመሳሳይ የሆነ ስሜት መሰማት ፤ ትልቁ ነገር ሰዎች ዘንድ Shine ማድረግ ሳይሆን ጌታዬ ዘንድ Shine ማድረግ  እንደሆነ ያመላክተኛል። 😊

👤ናዲያ

📮https://t.me/palestine_history

🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸

25 Oct, 05:43


🇵🇸🗞
ትናንት ለሊቱን የወራሪው እስራኤል ወታደሮች ወደ ናብሌስ መንደር ድንገተኛ ከበባ አድርኮ ጥቃት ከፍቶ ነበር ከተቃዋሚዎችም ፍልስጢናውያን ጋር ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ አድርገዋል በዚህም ከፍልስጢን ወገን 4 ሰው ሸሂድ ሆኗል 22 ሰው ደግሞ ቆስሏል

📮https://t.me/palestine_history

🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸

24 Oct, 18:12


˚˚˚•˚˚🇵🇸

#ፍልስጢን
የአንቢያኦች አባት የሆኑት ኢብራሂል ማረፊያ ኸሊል ምትባለዋን ከተማ ይዛለች

#ፍልስጢን
የነቢዩላህ ሳሊህ መኖርያ ቤት የነበረችውን ረምላህ/ራሙላ ምትባል ከተማ ይዛለች

#ፍልስጢን
የያእቆብ የተጓዙባት ጡል ከረም ምትባል ከተማ ይዛለች


#ፍልስጢን
የነቢዩላህ ሙሳ መቃም የነበረችው አሪሀ ከተማን ይዛለች

#ፍልስጢን
የነቢዩላህ ኢሳ የተወለዱባት በይትለህም ከተማን ይዛለች

#ፍልስጢን
ኢሳ ይኖሩበት የነበረችው የ ናሲራ ከተማን ይዛለች

#ፍልስጢን
ነብያቶች ሁሉ የተሰበሰቡበት እና ረሱሉና ኢማም ሆነው ያሰገዱባት ቁድስ አለችባት

📮https://t.me/palestine_history

2,406

subscribers

807

photos

113

videos