ኑ እናንብብ @nuenanbib Channel on Telegram

ኑ እናንብብ

@nuenanbib


ኑ እናንብብ (Amharic)

ኑ እናንብብ የቴሌግራም እናንብብ ነው እናንብብ በአማርኛ አዳዲስ ንግግርን ሳይጠቅም እና በሐዚብ እና ርዕሰ ሃገር የሚመለከተውን መረጃውን ጠብቀን በኮምፒውተር በሔኖክ ቴሌግራም ብቻ ማግኘት ይችላል። ኑ እናንብብ የቴሌግራም እናንብብ ናት፣ በተለያዩ ዝርዝሮችና ታሪኮች ውስጥ ንግግርን ከተስማማች በኋላ እንደገና ያለን አገናኝ ማንበብ ያስፈልጋል። ከዚህ በታች ኑ እናንብብ የኮምፒውተሩን እናንብብ ከሚፈልጉ ግዜ ለገላገል የሚለዋወጥ ሰው ሆነ፣ የፔሽንት አፕሊኬሽንን ለመሙላት እና ሌላው ስምን በመጠቀም የከብትና ኑ እናንብብን በማዘጋጀት እንክፈልናለን። እናንብብን ለመሀብቱ እና ለመስራት እናንብብ ከሌሎች ሰዎች የሚፈልጉበት በእጅጉ አለ። ከዚህ በታች እናንብብን እንደገና መገኘት በጀርባ እንደሚኖር ኮምፒውተሩን በሔኖክ ስለሚሰሩት መረጃ አግኝታለሁ።

ኑ እናንብብ

08 Feb, 09:23


ዶናልድ ትራምፕ የአፍሪካ መሪዎች ሰው መሆናቸውን እጠራጠራለሁ አሉ‼️

👉🏿 ከ50 ዓመታት የአህጉሪቷ የነጻነት ጉዞ በኋላ፣ ለህዝባችው አስፈላጊውን መሠረተ ልማት ካላሟላችው ሰው ነን ብላችው ታስባላችው?


👉🏿በወርቅ፣ በአልማዝ፣ በነዳጅ፣ በዩራኒየም፣ በብረት፣ በማዕድን፣ በብር፣ በማግኒዥየም፣ በነሐስ፣ በጋዝ የተፈጥሮ ሃብቶቻችው ላይ ተቀምጣችው፣ ህዝባችው በረሃብ፣ በትምህርት አለመዳረስ፣ በጤና አገልግሎት እጦት፣ ቢሞት፣ ሰው ነን ብላችው ታምናላችው?

👉🏿በስልጣን ላይ ቆይታችው፣የራሳችሁን  ዜጎች ለመግደል ከውጭ የጦር መሣሪያዎችን ስታስገቡ፣ ሰው ነን ብላችው ታስባላችው?

👉🏿የገዛ ዜጎቻችሁን እንደውሻ ስታንገላቱና ስትገድሉ፣ ማን ዜጎቻችሁን እንዲያከብር  ትጠብቃላችው?

👉🏿በራሳችው  አገር ላይ ቀማኛና ሌባ በመሆናችው ፣ የሃገራችሁን  ሀብቶች ሁሉ በመስረቅ፣ አብዛኞቹ ዜጋዎቻችው በስደትና በድህነት ውስጥ እንዲያልፉ ስታረጉ፣ የሰው ልጆ ነን ብላችው ታስባላችው?
ትራምፕ ይሄን የተናገሩት ሰሞኑን በዋሽንግተን ዋይት ሀውስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መሆኑን ተመልክቻለሁ።
[አዩዘሀበሻ]
===================

ኑ እናንብብ

04 Feb, 10:18


አንዳንዴ . . . ያለ ነው!

አንዳንድ ጊዜ ማመንታት ያለ ነው - በፍጹም ግን ወደ ኋላ አንመለስም!

አንዳንድ ጊዜ መፍራት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንንበረከክም!

አንዳንድ ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ያለ ነው - በፍጹም ግን አናቆምም!

አንዳንድ ጊዜ መሸነፍ ያለ ነው - በፍጹም ግን ሕይወት ከሚያቀብለን የየእለት ጦርነት አንሸሽም!

አንዳንድ ጊዜ መድከም ያለ ነው - በፍጹም ግን ዝለን አንወድቅም!

አንዳንድ ጊዜ ግራ መጋባት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንቅበዘበዘም!

አንዳንድ ጊዜ በሰው መገፋት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከዚያ ሰው ውጪ መኖር አየቅተንም!

አንዳንድ ጊዜ ድብርት ያለ ነው - በፍጹም ግን ደንዝዘን አንቀርም!

አንዳንድ ጊዜ ለጥያቄ መልስ ያለማግኘት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከመጠየቅ አናርፍም!

አንዳንድ ጊዜ ክፋት ያሸነፈ መምሰሉ ያለ ነው - በፍጹም ግን መልካምነትን አንጥልም!

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence

ኑ እናንብብ

01 Feb, 18:53


ኑሮ አያሻግርም!

እኮ ማነው!
የሰውነት ድልድይ እንዲህ እየፈረሰ፣
የሰውነት መንገድ እንዲህ እየሻከረ፣
መንገዱን ሊያስውብ  እንዲህ ያሳመረ?
ይልቅ ንገሩልኝ!!
ለእንደኔ ዓይነቱ ሰው፤
በግርግር ደቦ ትልሙ ለፈረሰ፤
የአበባ ዘመኑን በነጠላ መንገድ ሲጓዝ ለጨረሰ፡፡
በቁስ መደራረብ፣
            በዜና ጋጋታ ተስፋ አይሰፈርም፤
“አስፓልት” እግር እንጂ ኑሮ አያሻግርም!

በረከት በላይነህ
የመንፈስ ከፍታ

@Zephilosophy

ኑ እናንብብ

01 Feb, 07:58


በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ባህሪህን ይወስናል

ባህሪይህን ተመልከተውና በራስህ ላይ ያለህን አመለካከት በግለጽ ይጠቁምሃል፡፡ ከሰዎች ጋር ስትሆን የምትገልጠው ባህሪይ በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ነጸብራቅ ነው፡፡ ብቻህን ስትሆን፣ ስለራስህ ስታስብ፣ ራስህን በመስታወት ስትመለከተው ስለራስህ የምታስበውን ትክክለኛውን ሃሳብ አግኘውና ከሰዎች ጋር ስትሆን የምታንጸባርቀውን የባህሪህን ፍቺ ይነግርሃል፡፡

ለምሳሌ፣ ጤናማ የሆነ በራስ መተማመን አመለካከት ያለው ሰው የሚገልጠው ባህሪይና የዝቅተኝነት ስሜት ያለው የሚገልጠው ባህሪይ አንድ አይደለም፡፡

እንደተገፋና እንደተናቀ፣ ዝቅተኛ እንደሆነ የሚያስብ ሰው ማንም ሳይነካው ሰውን የሚነካና የሚተናኮስ ባህሪይ ያዳብራል፡፡ ማንም ገፋው አልገፋው ምንም ለውጥ እንደማያመጣበት የሚያስብ ሰው የተረጋጋና አላማው ላይ የሚያተኩር ባህሪይ ይታይበታል፡፡

ለምንም ነገር ያለመመጠን ስሜት ያለበት ሰው የፍርሃትና የአይን አፋርነት ባህሪ ይወርሰዋል፡፡ የሚመጥን ማንነትና አመለካከት እንዳለው የሚያስብ ሰው ደፋርነትና ተግባቢነት ይኖረዋል፡፡

ሰዎች አይፈልጉኝም የሚል ስሜት ያለበት ሰው ለሁሉም ሰውና ለሁሉም ነገር እሺ ባይነት ያጠቃዋል፡፡ ተፈለገም አልተፈለገም ተረጋግቶ የሚኖር ሰው ያመነበትንና ያላመነበትን በመለየት ሃሳቡን መግለጽ ችግር የለበትም፡፡

ተወዳድሮ ለማሸነፍ እንደማይበቃ የሚያስብ ሰው አታላይና አጭበርባሪ ባህሪይን ያዳብራል፡፡ ምንም ነገር ቢሆን ራሱን አሰልጥኖ መወዳደር እንደሚችል የሚያምን ሰው ደግሞ ቀጥተኛና እውነተኛ ይሆናል፡፡
በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ጤናማ ሲሆን ማሕበራዊ ግንኙነትህም እንደዚያው ጤናማ ይሆናል፡፡

ስለዚህ ማሕበራዊ ሕይወትህ እንዲስተካከል ከፈለክ በቅድሚያ በራስህ ላይ ያለህን ምልከታ አስተካክለው፡፡

ዶክተር ኢዮብ ማሞ

የስብዕና ልህቀት

ኑ እናንብብ

24 Jan, 07:51


"ብሔርተኛነት ጨቅላ ሕፃናትን እንደሚያጠቃ አደገኛ በሽታ ነው።"

በብሔርተኛነት ላይ ትችት በማቅረብ የሚታወቁት ኤሪክ ሆብስቦውንን /Eric Hobsbawn/፣ እና ፍራንዝ ፋነንን /Franz Fanon/ የመሳሰሉ ምሁራን እንደሚሉት “ብሔርተኛነት የተካረረ ልዩነትንና ቅራኔን በመፍጠር አንድን ሕዝብ በሌላ ሕዝብ ላይ አነሳስቶ ስልጣንና ሀብትን ለመቆጣጠር በመሳሪያነት ጥቅም ላይ የሚውል ርዕዮት ነው። የውጪ ጥራዝ- ነጠቅ ርዕዮት ሰለባ በመሆን ጤናማ የሆነውን የባሕልና የቋንቋ ወይም የብሔር ማንነታችንን አውዳሚ ወደሆነ የፖለቲካ መሳሪያነት በመቀየር አስተሳሳሪ ማንነታችንን በጣጥሰን ጥለነዋል። አሁን በእጃችን ላይ የቀረችው ስጋና ደሟ የሆነውን ኢትዮጵያዊነትን ተነጥቃ በአፅመ-ቅሪቷ ብቻ በመኖርና ባለመኖር መካከል እየተንገዳገደች የምትገኘው አገረ-ኢትዮጵያ ነች። አገረ-ኢትዮጵያም የግንባታ ሂደቷ ከመቆምም አልፎ በመቀልበሱ ምክንያትም አሁን የምትገኝበት ደረጃ በከፍተኛ የህልውና የአደጋ ቋፍ ላይ ነው። ዓለም-አቀፍ እውቅና ኖሯት በስምና በካርታ ላይ ከመኖሯ በቀር ለህልውናዋ ዋስትና የሚሰጡ እጅግ ብዙ አስተሳሳሪ እሴቶቿን አጥታለች።

ብሔርተኛነትን በርዕዮትነት እንደማራመድ ለአገር አንድነትና ሰላም ብቻ ሳይሆን ለብሔር-ብሔረሰቦች የእኩልነት መብት መከበርም ፀር የሆነ የፖለቲካ አመለካከት የለም። አንድ ኃይል ራሱን በአንድ ብሔር ስም አደራጅቶ ለፖለቲካ ስልጣን ከታገለና ስልጣን ከያዘ በኋላ የሁሉንም የአገሪቱን ሕዝብ ጥቅምና ፍላጐት የሚያስጠብቅ የእኩልነት ስርዓት ሊመሰርት አይችልም። ብሔር የመሬት ወይም የግዛት ባለቤት ከሆነም ከዚያ ብሔር ውጪ ያሉ ዜጐች መጤና ሁለተኛ ዜጐች ተደርገው ከመታየት ሊድኑ አይችሉም።

በአገራችን በተግባር እየሆነ ያለውም ይኸው ነው። አልበርት አንስታይን /Albert Einstein/ በጥሩ አባባል እንደገለፀው ብሔርተኛነት “ጨቅላ ሕፃናትን እንደሚያጠቃ አደገኛ በሽታ” /Infantile Disease/ ነው።

የኢትዮጵያዊነትን መሸነፍ እንደ ጥሩ ውጤትና ድል በመቁጠር የሚኩራሩ የዘመናችን ብሔርተኞች ብዙዎች ሆነዋል። ይህ መኩራራታቸው የሚመነጨው ግን ብሔርተኛነት ሄዶ ሄዶ የአጥፍቶ-ጠፊነት ውጤት እንደሚያስከትል ካለመረዳት ነው። ጆን ግሬይ /John Gray/፣ በርትራንድ ረስል /Bertrand Russell/፣ ሃናህ አረንት /Hannah Arendt/ እና መሰል ፀሐፍት እንደሚሉት “የብሔርተኝነት ትግል ሲጀመር በፍጥነት የሚያድግና የሚጠናከር ሲሆን፣ በሒደት ግን በውስጡ በሚፈጥረው የጥላቻና የመከፋፈል አዙሪት ባልተቋረጠ ሁኔታ እየተበተነና እየተዳከመ የሚሄድ ነው። ብሔርተኛነት በቆየና የበለጠ በተጠናከረ ቁጥር ሁሉጊዜ የሚፈጥረው ሌላ ከሱ የባሰ ጠባብና አክራሪ ብሔርተኛነትን ነው። ከዚህ የተለየ ሌላ የእድገት ዑደት የለውም። እድገቱ ቁልቁል ነጓጅ /Degenerative/ ሒደት ነው።

አንድ ጊዜ የጋራ መተሳሰሪያችን ከሆነው ከኢትዮጵያዊነት ወይም ከዜግነት ማንነታችን መነቀል ከጀመርን በኋላ አሁን ላይ ንዑስ-ብሔርተኞች ሲሉ እንደሚሰማው ከብሔር ማንነታችን አውርዳችሁ አድዋና ተንቤን፣ ወለጋና አርሲ፣ ወይም ጎንደርና ጎጃም ወዘተ... ብላችሁ አትከፋፍሉን ብሎ ሌሎችን ማማረር ትርጉም የለውም። እንዲህ ዓይነቱ አባባል የብሔር ፖለቲካን መነሻ እንጂ መድረሻን አስቀድሞ ካለማወቅ የሚመነጭ ድክመት ነው። በዜግነት ደረጃ ያልጠበቅነውን መተሳሰር ወደ ብሔር ደረጃ ከወረድን በኋላ አስጠብቀን የማስቀጠል ዋስትና ሊኖረን አይችልም። አንድ ጊዜ የብሔርተኛነት ፖለቲካን የተለማመደ ሕዝብም የራሴ የሚለውን አገር ከመመስረት ባነሰ በሌላ ማናቸውም ዓይነት ውጤት የመርካት ዕድል የለውም። ሁልጊዜም ብሶተኛ፣ ነጭናጫና ጠባጫሪ ሆኖ የሚኖር ነው።

ተዋቂው ፀሀፊ ኤሪክ ሆፈር /Eric Hoffer/ እንደሚለው፣ “ማንኛውም የግለሰቦችን መብት ለቡድን ጥያቄ አሳልፎ የሚሰጥ የቡድን እንቅስቃሴ ሕዝብን ለጊዜው በብሶት፣ በስሜትና በጥላቻ ከማነሳሳት ባለፈ አገርንና ስርዓትን በጋራ የመገንባትና የማስቀጠል ሚና የለውም”። ባለፉት 33 ዓመታት በአገራችንም ሆነ በአካባቢያችን ሲሆን እንደታየው የብሔር “ነፃ አውጪ” ድርጅቶች ዕጣ-ፈንታ እየተበተኑ ከመሄድ የተለየ አልሆነም። የራሳቸውንም ሆነ “ነፃ እናወጣሀለን” የሚሉትን ሕዝብ ሕይወት ከመኖር ወደ አለመኖር ሲቀይሩት እንጂ ችግሩን ሲፈቱለት አልታዬም። የኦነግ፣ የብአዴን፣ የኦህዴድም ሆነ የ50 ዓመታቱ የሕወሓት የብሄርተኛነት ጉዞ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ይመስለኛል። ኢትዮጵያዊያን ብሔርተኛነትን በአገር ደረጃ በፖለቲካ ርዕዮትነት ማራመድ ከጀመርን በኋላ በታሪካችን ታይቶ በማይታወቅ መጠን በሚሊየኖች ስንፈናቀልና በጭካኔ ስንጨፈጨፍ በገሃድ እያየንም ዛሬም በሚያሳዝን ሁኔታ የተለየና አዲስ መፍትሄ ማሰብ አልቻልንም። በመረረ ጥላቻ፣ በአጉል እልህና ፉክክር ሕሊናችን ስለተጋረደ “የጅል ዘዬ ሁሌ አበባዬ”እንዲሉ ዛሬም “ብሔርተኝነት ወይም ሞት!” በማለት የጥፋቱን መንገድ የበለጠ አጠናክረን ቀጥለንበታል።

ከልደቱ አያሌው ገፅ የተወሰደ

@zephilosophy
@zephilosophy

ኑ እናንብብ

23 Jan, 08:47


----
የሕላዌ ውበት … የኑባሬ አክሊል … የጥበባት ሁልቆ
ራስን መውለድ ነው … ከራስ ውስጥ ፈልቅቆ!!!
----
https://t.me/bridgethoughts

ኑ እናንብብ

19 Jan, 12:18


‹‹የጥምቀት ወግ››
++++++


እንደ ጥምቀት የምወደው በዓል የለም፡፡

ነፍሴ ነው፡፡

ገና ጥር ከመግባቱ ያቁነጠንጠኛል፤ ደረሰ ደረሰ እያልኩ፡፡


ዋነኛው መንፈሳዊና ሐይማኖታዊ ፋይዳው እንዳለ ሆኖ ጥምቀት ለእኔ ህዝባዊ ፌስቲቫል፣ ገፋ ሲልም የካርኒቫል ቀለምና ስሜት ያለው ወደር የለሽ የአደባባይ ነጻ የህዝብ በዓል ነው፡፡

ጥምቀት ባለህብረ ቀለም የባህል አውደ ርእይ፣
የውበት አውድማ፣

ግዙፍ የህዝብ ቡፌ ነው፡፡


ልብ ላለው፤ ከከተራ ጀምሮ ያለው መንፈሳዊ፣ ሐይማኖታዊ፣ ህዝባዊና ባህላዊ ትእይንት ልብን ይሰውራል፡፡
እንኳንም ኢትዮጵያዊ ያደረገኝ ያሰኛል፡፡
በደስታ ያፍነከንካል፡፡፡፡


‹‹እነሆ ጥምቀት ደረሰ
ነጭ ነጩን እየለበሰ
ህዝቡ ወደ ባሕር ገሰገሰ
ታቦቱን እያነገሰ››

እየተባለለት መምጣቱ የሚበሰርለት የጥምቀት በዓል ለወንዱም ለሴቱም፣ በተለይ ደግሞ ለአፍላዎቹ የመታያ፣ የመዋቢያና፣ የመፍኪያ ወቅት ነው፡፡

ወንዶች ሌላ ጊዜ ችላ የሚሉትን በመፈተል ብዛት የተቆጣጠረ ፀጉራቸውን ብን አድርገው ያበጥራሉ፣ እንደ ኪሳቸው ውዱን ይለብሳሉ፡፡

ሴቶች ሹሩባቸው በዘመኑ ፋሽን ይቆነደዳሉ፤ የቻሉ ሂውማን ሄራቸውን ልቅም ተደርገው ይሰፋሉ፣ ታጥበውና ታጥነው፣ እንሾሽላ ሞቀው፣ ሳውና ባዝ ውለው፣ ተቀሽረውና አስደንጋጭ ውበታቸውን ይዘው እንደ ኪሳቸው ባማረው ቀሚስ ተውበው ብቅ ብቅ ይላሉ፡፡


‹‹ይሄ ሁሉ ቆነጃጅት የት ተደብቆ ነው›› እስኪባል…

ቀይ ቢባል፣ ጠይም ቢባል፣ ጥቁር ቢባል…ውበት…ሃበሻዊ ውበት ሁሉም በየአይነቱ
… ከባለ ግቢ ትልቅ ብረት በር፣ ከቀበሌ ቤት ደጃፍ፣ ከየኮንዶሚኒየሙ ቤት ያለማቋረጥ ይፈሳል፡፡

ከብዛቱ የተነሳ ያፈዛል፣ ያደነዝዛል፡፡


እንደው ለመሆኑ ለጥምቀት የማያምርባት ሴት የትኛዋ ናት?


ከቤት ሰራተኛ እስከ የሃብታም ሚስት..
ከአጎጠጎጤ ኮረዳ እስከ ቀብራራ እመቤት..
ከቫዝሊን እስከ ውድ ሜክአፕ የተቀቡ ፊቶች እንደ ፀሃይ እያበሩ በጃንጥላ ተከልለው መንገዱን ሲያጥለቀልቁት ማየት እውነትም ጥምቀት የእኩልነት በአል ነው አያሰኝም?

በዓመት አንዴ የሚያገኙትን ብስኩት፣ ለስላሳና ሎሊፖፕ አከታትለውና ደራርበው የሚያላምጡና የሚጠጡ ከደሃና ባለጸጋ ማህጸን የወጡ ህጻናት በደስታ ሲቦርቁ ሰታይ ልብን ደስ አይልም?

ዶሮ ግዙልኝ፣ ሰንጋ እረዱልኝ፣ ዳቦ ድፉልኝ፣ ቶርታ ሸምቱልኝ ሳያስብል ሁሉንም እንዳቅሙ አስውቦና አስጊጦ በአደባባይ እኩል የሚያደርግ የሁሉም በዓል ነው ጥምቀት!



ታቦት አንግሶ ሲያበቃ፤

ለጥምቀት በዓል አደባባይ ወጥቶ ያልዘፈነ፣ ሆ ብሎ ያላስባለ ጎረምሳ፣
ግጥም ተቀብላ በስሜት ያልደገመች፣ ያላጨበጨበችና እስክስታ ያልወረደች ኮረዳ፣
በሃርሞኒካ ግጥምና ዜማው ስሜት የማይሰጥ ግን በስሜት የተሞላ ‹‹ሲሲ..ፓራራ›› ሙዚቃ ያልተናጠ ወጣት ምኑን ወጣት ሆነ?


ይሄ ሁሉ ሲሆን በክቡ ጥግ ቆመው ወጣቶቹን በግብረገብ ሚዛን ላይ የሚያስቀምጡ ተቆጪ አዛውንትና በአለፈብኝ ቁጭት የሚወዘወዙ ጎልማሶች ካልታዩበት ምኑን ጥምቀት ሆነ!


እንዲህ ያለውን ምስቅልቅል ግን ውብ ስእል እንካችሁ የሚል ሌላ በአል የለም፡፡
ጥምቀትን የሚመስል አንዳችም ነገር የለም፡፡

የሚገርመኝ ለወትሮው የሚያንገሸግሸኝ ጩኸትና ሁካታ፣ የድምፅ መጋጨትና መሳከር፣ የብዙ ነገር መደበላለቅ ለጥምቀት ሲሆን የሚጥመኝ ነገር ነው ፡፡ ጭራሽ ድምጽ ካልተማታብኝ፣ ነገር ካልተሳከረብኝ፣ ቀለም ካልተደባለቀብኝ ቅር ይለኛል፡፡


አለ አይደል…


እዚያ ማዶ ….

‹‹ነይ ነይ እምዬ ማርያም
ነይ ነይ ቤዛዊት ዓለም ››

ወይ ደግሞ

‹‹እጣን እጣን ይሸታል መሬቱ
አባቴ ገብርኤል ያደረበቱ ››

እያሉ በመዝሙር የህዝቡን ስሜት የሚገዙ ዘማሪዎችን ስሰማ…

ከወዲህ ደግሞ

››አሞራ በሰማይ ሲያይሽ ዋለ
የአንገትሽ ንቅሳት ውበትሽን እያየ ››

እያሉ እየጨፈሩ ልጃገረዶችን የሚባብሉ ጎረምሶችን ዘፈን ስሰማ ደስ ይለኛል እንጂ አልረበሽም፡፡
ምድሪቱ ላይ ያለ ምግብን አንዱን ባንዱ ላይ እየደራረብኩ ስበላ አሁንም ደስ ይለኛል እንጂ አይጣላኝም፡፡


ጥምቀት ነዋ! ካልተደባለቀ ምኑን ጥምቀት ሆነው!


ስለዚህ ዛሬ በከተራ

ድብልቅልቅ፣ ሽብርቅ፣ ድምቅና ፍልቅልቅ ያለ የጥምቀት በዓል ስመኝላችሁ ከደስታ በቀር የሚሰማኝ አንዳችም ስሜት የለም፡፡

ኑ እናንብብ

15 Jan, 15:07


ተቀጣሪ ወይም ነጋዴ ሆነህ ቤት ብትገነባ
- ከገቢህ 35% የገቢ ግብር
- የመሬቱ ሊዝ
- የጣራና ግድግዳ ግብር
- ለግንባታው የባንክ ብድር ወለድ
- በምትከፍለው እያንዳንዱ ትራንዛክሽን ባንክ ቻርጅና ቫት
- አሁን የንብረት ግብር
- በሁሉም ክፍያ ላይ ቫት
- ከሆነ ባለሥልጣን ጋር ከተነጃጀስክ ውርስ
- 30% ግሽበት
- ያለምክንያት መዋጮ
- ያለዕድሜህ ሽበት
- የማይቆም ጦርነት

=> መፍትሔ:- ባገኘኸው የትኛውንም safe መንገድ ስደት

Via Abdulkadir Hajj Nureddin

@EliasMeseret

ኑ እናንብብ

13 Jan, 15:10


ኤለን መስክ እንዲህ ይላል፦

“ከቀድሞዬ ፍቅረኛዬ አምበር ሄርድ ጋር በተለያየንበት ጊዜ ላደረኩላት ነገር ሁሉ ሒሳብ ጠየቅኳት እና ሁሉንም ነገር ሙሉ በሙሉ ከፍላለች:: በሴቶች ላይ በጣም ስስታመ ነኝ 💸::

አምበር ሄርድ የእኔ ገንዘብ እስከሆነ ድረስ በግዴለሽነት ገንዘብ ማውጣት ትወድ ነበር። በዚህም ለብዙ የበጎ አድራጎት ስራ የሚውል ገንዘብ እያለችኝ መቀበል ታዘወትር ነበር።

ትዊተርን የገዛሁት ለፖለቲካዊ ወይም ለንግድ ዓላማ ሳይሆን ለአምበር ነው። እንደ ቫለንታይን ቀን ስጦታ ልሰጣት ፈልጌ ነበር። ነገር ግን ከቫላንታይን አንድ ቀን በፊት በትዊተር ላይ አዲስ የወንድ ጓደኛ ስታገኝ ከእኔ ጋር ተለያየች።

ከእኔ ጋር ከተለያየች በኋላ ከትዊተር አገድኳትና ስሙን ወደ
X ቀየርኩት። ነገር ግን አዲሱ ፍቅረኛዋን በቴስላ ድርጅት ውስጥ ቀጠረችው። እና ከጥቂት ቆይታ በኋላ እኔ  አለቃው ላይ እንዲህ ማድረግ ስላልፈለገ ተለያት።

ከዚያም በግንኙነታችን ወቅት ለምታጠፋው ለእያንዳንዱ ሳንቲም ደረሰኝ ሰጠኋት። እና ሙሉውን ገንዘብ መልሳ ከፈለችኝ። ምክንያቱም ግንኙነታችንን ከመጀመራችን በፊት አብረን ካልሆንን ትከፍለኛለች የሚል ሰነድ እንድትፈርም አድርጊያለሁ። በሴቶች ጋር በጣም ንፉግ ነኝ እና ለዚህም ይመስለኛል እስካሁን ያላገባሁት”
✌🏼😌

ኑ እናንብብ

10 Jan, 07:59


እሱ፤ አንድ ሚልዮን ብር ብሰጥሽ ከኔ ጋር ትተኛለሽ?

እሷ፤ አንድ ሚልዮን ብር? ዋው! ይመስለኛል አዎ፡፡

እሱ፤ በመቶ ብርስ?

እሷ ፤ ጥፋ ከዚህ፡፡ ምን መስዬህ ነው? ሴተኛ አዳሪ?

እሱ፤ ሴት አዳሪነትሽን መጀመሪያውኑ ተስማምተናል፡፡ አሁን በገንዘቡ ላይ እንደራደር።

ልክነት መቼ እና እንዴት ነው
የሚኖረው? መቼ ነው ይህቺን ሴት ሴተኛ አዳሪ የምንላት? መቼ ነው ይህቺን ሴት ክብሯን የጠበቀችው? መቶ ብር ወይስ መቶ ሺ ብር ላይ? ወይስ አንድ ሚሊዮን ላይ? መቼ ነው ክብሯን ያጣችው?

የገነባነው ክብር እና ፅድቅ  በየትኛው የብር መጠን ላይ እንሽረዋለን? ከሻርነውስ የእውነት መልካም ሰው ነን ማለት እንችላለን?
ምናልባት ምግባራችን እንደ ሴቷ በገንዘብ ስላልተፈተነ ይሁን ጥሩ ሰው የመሰልነው ?

@zephilosophy

ኑ እናንብብ

05 Jan, 16:14


የሴትልጅ ቁንጅና ምንድነው?
_______

(ውበትና ደም-ግባትስ?)

"ቁንጅና ምንድነው ሰዎች አስረዱኝ
እኔ እሷን ወድጄ ታምሜያለሁኝ...
ውበትና ቁንጅናሺ፣ ይማርካል ለሚያይሺ.."

- ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ

በየዘመኑ "የሴት ልጅ ውበት" የሚባለውን አስተሳሰብና መስፈርት ማን ፈጠረው? "ቆንጆ" ሴት ከቆንጆ ሰው በምን ትለያለች? ሴቶች በ"ሽንጥና ዳሌሽ ሲታዩ..." ዓይነት መስፈርቶች እንዲለኩ የበየነላቸው ማነው?

ወንዶች ሴቶችን የሚስሉበት መንገድ ከስሜት ጋር የተያያዘ ለምን ሆነ? ከወሲባዊ መስህብ አሊያም ከመራባትና ከእናትነት አስተሳሰቦች ውጭ ሊታሰብ የሚችል የሴት ልጅ ሰብዓዊና ማኅበራዊ ፋይዳ ከየማኅበረሰቡ አንጎል የተነነው በምን ምክንያት ነው?

ውበት ምንድነው? ደርባባነትን ከሴት ልጅ ለምን እንድንጠብቅ ሆንን? በዘመናት ውስጥ የተቸራቸውን ማኅበራዊ ተክለሰብዕናና የተሰጣቸውን ሚና ለመጫወት እምቢ ያሉ ሴቶች ዕጣፈንታ ምንድን ነበር? አሁንስ ምንድነው?

ወንዶች በጥቅሉ ለሴቶች ያለን ዝንባሌ በጎችንና ፍየሎችን ሽንጣቸውን ለክተን፣ ጥርሳቸውን ፈልቅቀን፣ ሸሆናቸውን መትረን ለመግዛት ከምንሄድበት መንገድ ብዙም ያልተለየ ሆኖ የሚገኘው በምን የተነሳ ነው? ተፈጥሯዊ ነው? ወይስ ማኅበራዊ?

የሴቶች ተፈጥሯዊ ሰዋዊ አገልግሎት ምንድነው? ብለን ነው የምናስበው? ለምን?

የሴትን ልጅ አካላት ዕርቃን እያወጡ የተሳሉ አያሌ ክላሲካልና ሞደርን የጥበብ ሥራዎች (ሥዕሎች፣ ቅርፃቅርፆች፣ ስነፅሑፎች፣ ሙዚቃዎች፣ ወዘተ.) ለምን በየዓለሙ በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ሆኑ?

የሰውልጅ ሴትን ልጅ ከsensual pleasure ውጭ ለማሰብ ያልቻለበት አብይ ምክንያቱ ምንድነው? ሴቶችስ ራሳቸውን ከመኳኳልና ከማጊያጌጥ፣ ሽንጥና ዳሌያቸውን ከማጉላት፣ ፀጉራቸውን ከመሾረብና በአልባሳት ከመሸለም ውጭ ያለውን ጥልቅ የራስ ማንነታቸውን ለመፈለግ ብዙ ዝንባሌ የማያሳዩት ለምንድነው?

በሴትነት ውስጥ ከማኅበራዊው መስፈሪያ ሚዛን የማፈንገጥ ዋጋው ምን ያህል ነው? ይህች ዓለም የማን ዓለም ነች?

እውን It's a man's man's world እንደሚባለው.. ዓለማችን የወንዶች ብቻ ዓለም ነች? ከሆነች ሴቶች የተነጠቀ ሙሉ የሰውነት ክብራቸውንና ዋጋቸውን ለማስመለስ ምን ያድርጉ?

የፆታ አስተሳሰባችን በምን በምን ነገሮቻችን ውስጥ ሥር እንደሰደደ፣ እስከ ምን ከፍታ እንዳሻቀበና እንዴትስ ተብሎ እንደተድበሰበሰና እንደተሸነገለ ልብ ብለን አስተውለነዋል?

ሴትነት ምንድነው? ወንድነትስ? ውበትስ? የሴት ልጅ ውበት ምንድነው? ሴትን ልጅ ያለ ጭንና ባቷ ለማሰብ ፈቃደኝነቱ ያለው ወንድ ከመቶ ስንት ፐርሰንት ነው? ራሷን ከቀሚሷ ውጭ አድርጋ ማሰብ የምትችልስ ሴት ከመቶ መሐል ስንት ትገኛለች?

የነዳጅ ዘይትን የሚተኩ በርከት ያሉ የኃይል አማራጭ ቴክኖሎጂ ተገኝተዋል በዘመናዊዋ ዓለማችን። ግን የዔለም ኢንዱስትሪ ሁሉ ከነዳጅ ጋር የተያያዘ ነው። ዲዛይኑ፣ ሸቀጡ፣ ንግዱ፣ ኢኮኖሚው፣ ቴክኖሎጂው፣ መኪናው፣ መርከቡ፣ አውሮፕላኑ... ሁሉ ከነዳጅ ጋር የተሳሰረ ነው። በዚህ የተነሳ ዓለም የሚያውቀውንና ህልውናውን የመሠረተበትን ኋላቀሩን ነዳጅ ዘይት መተው አይፈልግም። የሴት ልጅ ውበትስ ተመሣሣይ ነገር ይኖረው ይሆን?

በዓለም ሁሉ "የሴቶችን ውበት" መሠረት አድርገው የሚመረቱ ምርቶች፣ ዲዛይኖች፣ ፅሑፎች፣ ሳይንሶች፣ ፊልሞች፣ ኢንደስትሪዎችና ማኅበራዊ አወቃቀሮች... ባንዴ ተንደው እውነተኛ የሴቶችን ሙሉ ሰውነትና ክብር ወዳረጋገጠ ዘመናዊ አስተሳሰብ መሻገር ይችላሉ? የሚቻል ነው? ሴቶች ቂጥና ፊታቸው እየታየ የሚመዘኑበት ዘመን እስኪያበቃስ ስንት ዓመት ይፈጃል?

ይህ የናዖሚ ዎልፍ መፅሐፍ ላለፉት 3ሺህ ዓመታት የተቀነቀኑ የስነውበት ፍልስፍናዎችን፣ ሳይንሶችንና አስተሳሰቦችን እጅግ ጥልቅ በሆነ መንገድ ይቃኛል። አጥብቆ ይሄሳል። እና የውበትን ትርጉም እንድንፈትሽ ያስገድዳል።

ሴቶች ከወንዶች የውበት መስፈርት ራሳቸውን ማላቀቅ አለባቸው፣ ነፃ መውጣት አለባቸው ትለናለች።

በምጥን ፈገግታዋና በመርገፍ ቀሚሷ ዓለምን የምታማልለው ሞናሊዛ የኋላቀሩ ዘመን ማስረጃ ሆና ተቀድዳ የምትጣልበት፣ የፒካሶና የሌሎች በዓለም የተደነቁ የእርቃን ሴቶች ሥዕሎችና ኃውልቶች ተጠራርገው ወደ ቆሻሻ ቅርጫት የሚጣሉበት፣ የሴት ልጅን ሉዓላዊነት ያከበረ፣ ኮርማዊውን የወንዶች ዓለም የገረሰሰ፣ አዲስ የሴቶች ነፃነት ዘመን መበሠር አለበት ትላለች።

ከዚህ በፊት "ዘ ሴክስ ኦፍ ቲንግስ" የሚል አስገራሚ መሠል ይዘት ያለው በአንዲት ጀርመናዊት-እንግሊዛዊት ሪሰርቸር ዶክተር የተፃፈ አንድ ዳጎስ ያለ መፅሐፍ አግኝቼ ስገረምና የያዝኳቸውን ሁሉ የሴትልጅ አስተሳሰቦች ስሞግት ቆይቼ ነበር።

ይህን መፅሐፍ ካነበብኩ በኋላ ደግሞ ብርቱካን ከንፈርሽ፣ ብርንዶ ትንፋሽሽ፣ የዘንባባ ማር ይመስላል ፍቅርሽ፣ ፅጌረዳ ስላንቺ ልጎዳ፣ ሐር ይመስላል ፀጉርሽ፣ ሎሚ ተረከዝሽ፣ ስልታዊ ውዝዋዜሽ፣ ዓይናፋርነትሽ፣ ችቦ አይሞላም ወገብሽ፣ ካንቺ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት፣ እና አንቺን ያለውን በቴስታ ጥርሱን🤩... የመሣሰሉትን የምወዳቸውን የሙዚቃ ስንኞች ከአዕምሮዬ ለማጥፋት ምን ዓይነት ላጲስ መጠቀም እንዳለብኝ በማሰላሰል ላይ ነኝ🤓!!!

ይህች ደራሲና ተመራማሪ፣ ሶስተኛው የፌሚኒዝም አብዮት ተብሎ የሚጠራውን አስተሳሰብ ያፈለቀችና ለዓለም ያስተዋወቀች ጉምቱ ምሁር ስለመሆኗ ከተለያዩ ዜና መወድሶች ለመረዳት ችዬአለሁ።

ለማንኛውም ሃሳቦቿ የያዝካቸውን የሴት ልጅ ውበት ኮተቶች ሁሉ ያስጥሉሃል። ግን ፍራቻዬ ያለንን አስጥላን... በምትኩ የምትሰጠን ውበት ምን ዓይነት እንደሆነ ደራሲዋም ራሷ በትክክል ያወቀችው አልመሠለኝም።

ሽንጥና ዳሌሽ ሲታዩን ትተን... ወደ ምን እንሻገር? ውብ የምንላትን ሴት ከየት እናግኛት? ከስንደዶ አፍንጫና ከማር ከንፈር ውጭ ያለችዋ ቆንጆ ሴት ማነች? ከወዴትስ ትገኛለች? እውን አለችስ ወይ በዓለም ላይ? ሴቶቹ ራሳቸውስ ይቀበሏታል?

ደራሲዋ የምትሰብከን ሴቶች ከሙክትነትና ከጌጥነት አሊያም ከስሜት ማስተንፈሻነት የወረደ የወንዶች አስተሳሰብ ነፃ የሚወጡባት ዓለምስ እውን በዚህ የቅርብ ዘመን ትውልድ እውን ሆና እናያት ይሆን? ...

የወንዶች አሽኮርማሚነት፣ እና የሴቶች ተሽኮርማሚነት አብቅቶ፣ ማንም ማንንም የማያሽኮረምምባትን ዓለም የምናየው መቼ ነው? መቼ ነው ያቺ የፍፃሜ (ዋንጫ) ቀን መምጫዋ? ምን ምልክትስ እንጠብቅ?

ወንድሜ (እና እህቴ🤩)... በበኩሌ ጥይቴን ጨርሼያለሁ!

አሰፋ ሀይሉ

ኑ እናንብብ

05 Jan, 05:21


በሌላው ጫማ መሆን

አንድን ሰው በትክክል ለመረዳት በሱ ቦታ ብሆን ኖሮ ምን ይሰማኝ ነበር ብለህ ማሰብ አለብህ። አንዳንድ ነገሮችን በሌሎች ጫማ ውስጥ ሆነህ እስካለየሀቸው ድረስ ልትረዳቸው አትችልም። እናም በሌሎች ጫማ ሆነህ የሰዎችን ስሜት ለመረዳት ሞክር። በሕይወት ውስጥ ባሉ ጠቃሚ ግንኙነቶችህ ውስጥ ሁሉ ተጠቀምበት፡፡ ከቤተሰቦችህ ጋር፣ ከሰራተኞችህ ጋር ወይም ከመራጮችህ ጋር ሊሆን ይችላል፡፡ የሚና መቀያየር (role reversa) የጋራ መግባባትን ለመፍጠር የሚሆን ቀላልና ፈጣን ስልት ነው። አንደ ለማኝ ለብሶ የሚያስተዳድረው ህዝብ ውስጥ በመግባት ችግራቸውን ለመረዳት እንደጣረው ንጉስ ሁን።

የስብዕና ልህቀት
#share
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence

ኑ እናንብብ

02 Jan, 05:15


ሀሳዊ-ካፒታል እንደ ካርል ማርክስ፦

በአንዲት ትንሽና ደሃ የገጠር መንደር ውስጥ ሁሉም ሰው በብድር እዳ ተዘፍቆ ይኖራል። በድንገት አንድ ሀብታም ቱሪስት ወደ መንደሩ ይመጣል። ከዛ ወደ አንድ ሆቴል ይገባል። እንግዳ መቀበያ ላይ 100 ዶላር ያስቀምጣል። እና ምቹ ክፍል ለመምረጥ ወደ ላይ ይወጣል። በዚህ መሃል የሆቴሉ ባለቤት መቶ ዶላሩን በመውሰድ ስጋ ቤቱ ጋር ተሯሩጦ እዳውን ይከፍላል። ስጋ ቆራጩ በነዚህ ዶላር ተደስቶ ወደ ከብት ነጋዴው ተሯሩጦ የቀረውን ዋጋ ከፍሎ ያካክሳል። ከብት ነጋዴው በተራው መቶ ዶላሩን ወስዶ እዳውን ሊከፍል ወደ ምግብ ሚመገብበት ነጋዴ ጋር ይሄዳል።

የምግብ ነጋዴውም ከሩቅ ሀገር ምግብ ይዞ የሚመላለሰው የከባድ መኪና ሹፌር ጋር ይሄዳል። የከባድ መኪና ሹፌሩም መኖውን ለማድረስ በፍጥነት ወደ መንደሩ ያቀናል። በዚህም ከዚህ በፊት የበረበትን እዳ በማሰብ ለሆቴሉም ባለቤት  መቶ ዶላር ይሰጠዋል። ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ባለ ሀብቱ ቱሪስት ከመምጣቱ በፊት የሆቴሉ ባለቤት ተመልሶ መቶ ዶላሩን ቅድም በነበረበት የእንግዳ መቀበያ ቦታ ላይ ያስቀምጠዋል። የክፍሎቹ ስታንዳርድ ያልተመቸው ቱሪስት ወርዶ መቶ ዶላሩን ወስዶ ከተማውን ለቆ ለመውጣት ይወስናል።

ከከተማዋ ነዋሪዎች ውስጥ አንዳቸውም ያተረፉት ነገር የለም። ነገር ግን ሁሉም እዳውን ከፍሎ ጨርሷል!።
🤝🏼

ኑ እናንብብ

02 Jan, 05:10



ትንሽ ደግሞ ከቁም ነገር ያልተኛ ያላናቀላፋ እውነት እንማር።


አንድ ገበሬ ሊሸጠው የሚፈልገው በግ ስለነበረው ወደ ገበያ ወሰደው ይባላል። አራት ወንበዴዎች አይተውት በጎቹን በብልሃት ሊሰርቁት ተስማምተው ወደ ገበያ በሚወስደው መንገድ ጥግ ጥግ ያዙ። የበጎቹ ባለቤት ወደ ገበያ የሚያልፍበት መንገድ ላይ አንደኛው ሌባ ተቀምጧል። ሁለተኛው ከመጀመሪያው ሌባ ራቅ ብሎ ተቀምጧል። ሶስተኛው ከግማሽ እርቀት በኋላ ተቀመጠ። አራተኛው መንገዱ ከማለቁ ጥቂት እርምጃ የሚቀረው ቦታ ላይ ተቀመጠ። እናም የበጎቹ ባለቤት በመጀመሪያው ሌባ በኩል አለፍ ብሎ ሰላምታ ሰጠው። ሌባው ወደ ገበሬው ዘወር ብሎ እንዲህ አለው፦ “ውሻውን ለምን አሰርከው?”

ገበሬው “ይህ ውሻ ሳይሆን በግ ነው ወደ ገበያ ልሸጠው ነው”

ትንሽ እራቅ ካለ በኋላ ሁለተኛውን ሌባ አገኘውና እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ “ለምን ይህን ውሻ ከኋላ አስረ ትመራዋለህ?!”

ገበሬውም ሌባውን አይቶ እንዲህ አለው፦ “ይህ በግ ነው ገበያ ልሸጠው ነው።” ነገር ግን ጥርጣሬ በልቡ ውስጥ ዘልቆ መግባት ስለጀመረ ከሁለቱ ሰዎች እንደ ሰማው ውሻ መሆኑን ለማረጋገጥ በጉን መመልከት ጀመረ። ከተወሰነ ርቀት በኋላ ሶስተኛውን ሌባ አገኘውና እንደ ቀድሞው ጥያቄ ጠየቀው፦ “ውሻውን ለምን ከኋላ አስርከው?”

የበጎቹ ባለቤት ግራ መጋባቱ በጣም እየጨመረ መጣ። ወደ ሌባው ዞር ብሎ ተመለከተ። ግን ለጥያቄው መልስ አልሰጠም ምክንያቱም ውሻ እንጂ በግ እንዳልሆነ ተገንዝቧል። ከተወሰነ እርቀት በኋላ አራተኛውን ሌባ አገኘውና ሰላምታ እየሰጠው የፈጠነ እንዲህ አለው፦ “ሰውዬ ውሻውን አስረ ከኋላህ እየመራህ የመትሄደው ምን ችግር ቢገጥምህ ነው!?” እዚህ ላይ የበጉ ባለቤት ውሻ እንጂ በግ እንዳልሆነ አረጋግጧል። ግን አራቱንም ውሸታም ናቸው ማለት ምክንያታዊ አይደለም። ከዚያም ወደ ሌባው ዘወር ብሎ እንዲህ አለው፦
“በችኮላ ይኼ ውሻ በግ ነው ብዬ አስሬው ወደ ገበያ ወስጄ ልሸጠው ነበር። እስከ አሁን ድረስ ውሻ እንደሆነ ግልጽ አልሆነልኝም። ሳስበው ዛሬ ልክ አይደለው መሰለኝ” አለና በጉን ፈትቶ ወደ ቤቱ በችኮላ በጉን ፍለጋ ወደ ቤት አቀና። በዚህም ሌቦቹ በጉን ይዘው በደስታና በጭፈራ ወደመጡበት ሄዱ!።


አስተምሮቱ፡-

በዚህ መልኩ ነው የህዝብ አስተያየት በጥቂት ባለስልጣኖች ይፈጠራል። እና የሚያታልሉትም በአለም አቀፍ ሚዲያዎች አማካኝነት ተጠቅመው ነው። ለዚህም የተቻለውን ሁሉ በማድረግ እውነታውን በማጭበርበር፣ በማጣመም፣ የቅዠት ትዕይንቶችን ፈጥረው በማሳሳት እና በማታለል በአእምሮ መጫወት ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሁሉም ሚድያዎች ውሸት እየመገቡን ውሸቱን እውነት ያደርጉታል። በአዕምሮ ይጫወታሉ አዕምሮአችንን ያስቱናል። አንድ መታወቅ ያለበት ሀቅ በጉ በአዕምሮአችን ውስጥ ሳይሆን በእውነታው አለም ነው። በዋቴ የተፈጠረ የህልም ውሻ መጨረሻው እኛን ቀረጣጥፎ መብላት ነው። ስለዚህ እምነታችንን፣ ባህላችንን እና እውቀታችንን በሌቦች እጅ መተው የለብንም በተለይም በአዕምሮ ሌቦች!።

ኑ እናንብብ

02 Jan, 05:09


"What lies behind us and what lies before us are tiny matters compared to what lies within us." – Ralph Waldo Emerson


___

ተፈጥሮን 'የማረም' አባዜ አለብን... መሆንን አንቀበልም - መሆንን አናደንቅም... ይልቁን 'እንዲሆን በምንፈልገው' ውስጥ እንጠፋለን... 'እንዲህ መሆን' ነበረበት እያልን እንቆጫለን... 

___

በዙሪያችን ያሉ ዕጽዋት፣ ወንዞች፣ ተራራ፣ መንገዶች፣ ሰዎች ሳይቀር 'እንዲሆኑ በምንፈልገው' ሁኔታ ግዴታ ውስጥ ወድቀው ተፈጥሮአዊነት ተሰልበዋል...


አንድ የ Landscape Architect ወዳጄ እንደነገረኝ የወንዞችን ውበት በመጠበቅ ስም የወንዙን ውሃ ከከባቢው ጋር የሚኖረውን መስተጋብር የሚቀንሱ ግንባታዎችን መስራት፣ ለወንዙ መጥፋት የመጀመሪያው እርከን ነው... የሲሚንቶ ግድግዳ ሰርተህ ውሃውን ከአፈሩ ስትነጥለው ወንዙ መድረቅ ይጀምራል... 


የወንዙ ውሃ ከአፈሩ ጋር መስተጋብር አለው፣ በዙሪያው ከሚበቅሉ ዛፎች፣ በውስጡ ካሉ ነፍሳት፣ ከሚቀላቀሉት ኬሚካሎች... ወዘተ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው...


"Look deep into nature, and then you will understand everything better." – Albert Einstein


ሌላ ወዳጄ ደግሞ አንድ ከተማ በአስፓልት ብቻ እየተሸፈነች የምትሄድ ከሆነ የከርሰ ምድር ውሃ እጥረት እንደሚገጥማት አውግቶኛል... የክረምት ዝናብ ወደ አፈር ውስጥ መስረግ አለበት... ይህ ካልሆነ ሁለት ጉዳት አለው... ከተማዋ - ክረምት በጎርፍ ትጠቃለች፣ በበጋ ከፍተኛ የውሃ እጥረት ያሰቃያታል... 


የተፈጥሮን መስተጋብራዊ ዑደት መረዳት ተፈጥሮን ለመቅረብ የመጀመሪያው መስፈርት ነው... እርስ በእርሱ በተሳሰረ ዓለም ውስጥ የትም ቦታ የሚሆን አንድ ነገር ለሌላኛው የሚያተርፈው ጉዳትና ጥቅም አለ... 


ሁሌም ቢሆን ተፈጥሮን እንዲሆን በምትፈልገው እሳቤህ ውስጥ ከመጨቆንህ በፊት ሊሆን የሚገባውን ለማሰብ ጊዜ መውሰድና ጠቢባኑን ማድመጥ ግዴታህ ነው... 


"Nature does not hurry, yet everything is accomplished." – Lao Tzu


ይህን ሃሳብ ይዘን ወድ ሰው እንምጣ...


መልክ የሌለው የፍጹማዊነት ህመም አለብን... እንከን የለሽ ሆነን ለመታየት እንሻለን... ይህ እንዴት ይሆናል? ኑረት - ፍጹማዊነት የሚል ቃል ከመዝገበ ቃላቷ ውስጥ የለም... እኛ ነን ይህን የፈጠርነው... ሕይወት ሕብራዊት ናት... [Yin እና Yang] ወይም ነገሩን ገልብጠን በሌላ አውድ ብንረዳው ተፈጥሮ እንደወረደች ውብ ናት፤ ጉድለትን የፈጠርነው እኛ ነን...


"Nature knows no indecencies; man invents them." – Mark Twain


ሴቲቱ መልኳ 'እንዲሆን በሚፈለገው' ግዴታ ውስጥ ወድቆ ወርቅ ቅብ ሆናለች... አለባበሰዋ በማሕበረሰብ ድንጋጌ ተመትሮ ከላይ እስከ ታች ብልጭልጭ ብላለች... ገላዋ በዘመን የውበት ሚዛን ተሸልቶ በአርተፊሻል ገላ ተለብጣ ትውላለች... ተፈጥሮአዊ ሴት ማየት ሲያምርህ ይቀራል... ራሷን የተቀበለች ሴት ማግኘት ልዩ ጸሎት ይጠይቃል...


"To be beautiful means to be yourself. You don’t need to be accepted by others. You need to accept yourself." – Thich Nhat Hanh


ዝነኞች፣ መሪዎች፣ አርቲስቶች... ወዘተ 'እንደሚጠበቅባቸው' እንጂ እንደ ወረደ ተፈጥሮአቸው Act ስለማያደርጉ የማይጋባ ሳቅ ይስቃሉ፣ ለልብ የማይጥም ቃል ይደረድራሉ፣ ዘመን መላቅጡን ባሳጣው አለባበስ ተጨቁነው ይቀርባሉ...


"To be yourself in a world that is constantly trying to make you something else is the greatest accomplishment." – Ralph Waldo Emerson


____

የሆነን እንደመሆኑ ካልተቀበሉት የዕድሜ ልክ ሕመምን፣ ብሎም የመጥፊያ ቅመምን ያዘጋጃል... 

ፊትህ ላይ የወጣብህን ማድያት መቀበል የየዕለት ሕመምህን ያስቀረዋል... አለመቀበል ግን በራስ የመተማመን አቅምህን ከመስለብ በዘለለ ማጥፊያ የመሰለህን ሁሉ ከፊትህ እየዶልክ ዥንጉርጉር ገጽ እንድትላበስ ያደርግሃል...

የሰውነትሽን 'እንከን' አለመቀበል በአደባባይ እንዳትቆሚ ማድረጉ ብቻ አይደለም ችግር... አቅምሽን፣ ጸጋሽን፣ መቻልሽን ሁሉ ነጥቆ ተሰባብረሽ በተደበቅሽበት ለሌላ ሕመም ምንጭ ሆኖ ይቀጭሻል...


"You are imperfect, permanently and inevitably flawed. And you are beautiful." – Amy Bloom
___

የሆነን መቀበል የአድናቆት ድርቅ እንዳይመታን ብቻ አይደለም - ከሆነው በላይ እንዳይሆንብንም ዋስትና ነው... 
____

'Acceptance' በሚል ርዕስ የጫርኳት ማስታወሻ ላይ የተጋራሁዋችሁን የገጣሚት ሰናይት አበራ “በየፈርጁ” የምትል ጥልቅ ግጥም እዚህም ልድገም...

____

".. ለምን እንጨነቅ
ለምን እንሳቀቅ
የእርጥብ ቅል ክብደቱ – ነውና እስከሚደርቅ
ለምን እንሳቀቅ

.. ሁሉም በየፈርጁ
ሁሉም በያይነቱ

የፊቱን ፈንጣጣ – በፈርጥ ቢመስለው
ያንገቱን ስር እንቅርት – በውቅርት ቢያስጌጠው

ሁሉን ተቀብሎ…

እንደ አዶከበሬ – አሜን አሜን ቢለው
ለተመልካች እንጂ – ለያዘው ቀላል ነው።"

[እኛ - 1988]
____

ይህ ጽሑፍ የሚነበብ ፊርማ አለው... 

እነሆ: 


"There is no need to be perfect to inspire others. Let people get inspired by how you deal with your imperfections." – Anonymous

____

@bridgethoughts

ኑ እናንብብ

01 Jan, 14:37


የሙላ ናስሩዲን ቀልዶችና ጨዋታዎች
በግሩም ተበጀ
@Zephilosophy

ኑ እናንብብ

01 Jan, 13:21


የማስተካከል ድንቅ ጥበብ

በመጀመሪያ ለሕይወታችን እቅድ እንሰራለታለን፡፡ አንደኛ እቅድ ትምህርት፣ ስራ፣ የፍቅር ሕይወት፣ ቤተሰብ እያልን እናድጋለን፡፡ ከዚያም ወደ ሕይወት ግቦቻችን እንደርሳለን። በእርግጥ እንደዚያ እንደማይሰራ እንደምታውቅ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ሕይወታችን ማባሪያ በሌለው ብጥብጥና ግርግር ውስጥ ታልፋለች፡፡ የሕይወታችን አብዛኛውን ጊዜያችንን የምናጠፋውም ባላየናቸው የሕይወት ውጣ ውረዶች የሚመጡብንን ፈተናዎች በመታገል ነው፡፡

በህይወት ውስጥ ወሳኙ ነገር መነሻው ሳይሆን ከመነሻው በኋላ የሚመጡት የማስተካከያ ጥበቦች መሆናቸውን ተምሬያለሁ። ከብዙ ቢሊዮን ዓመታት በኋላ ተፈጥሮም ይህን - የተማረች ትመስላለች። ህዋሳት በተከፈሉ ቁጥር የመቅዳት ሂደት ስህተቶች (copying errors) ቀጣይነት ባለው መልኩ በዘረመላዊ ቁሶች ውስጥ እየተፈጠሩ ይሄዳሉ፡፡ ስለሆነም በእያንዳንዱ ህዋስ ውስጥ እነዚህን ስህተቶች ወደኋላ ተመልሰው የሚያስተካክሉ ሞለኪዮሎች አሉ። የዲ ኤን ኤ ጥገና ባይኖር ኖሮ ልክ እንደተወለድን በሰዓታት ውስጥ በካንሰር አማካይነት መሞታችን አይቀርም ነበር፡፡ የበሽታ መቋቋም ሥርዓታችን የሚሰራውም በተመሳሳይ መልኩ ነው። ችግሮች ቀድመው የማይታዩ በመሆናቸው ምክንያት ቀድሞ የተዘጋጀ ማስተር ፕላን የለም፡፡ ቫይረሶችና ባክቴሪያዎች በየጊዜው እየመጡ ሰውነታችንን ያጠቃሉ። የመከላከል ሥርዓታችንም ሁልጊዜ ይሄንን በማስተካከል ይሰራል።

ስለዚህ ወደፊት ሁለት በጣም የማይጣጣሙ ጥንዶች መካከል የሰመረ ትዳር መመስረቱን ስትሰማ ብዙ አትደነቅ፡፡ ይህ የስሪትን (set up) አጋኖ የማየት አይነተኛ ምሳሌ ነው፡፡ በግልጽ ካወራን የትኛውም ሰው ለትንሽ ሰዓት በግንኙነት ውስጥ ከቆየ ያለማስተካከያና ያለማሻሻያ ግንኙነቱ መቀጠል የማይችል መሆኑን ይረዳል። የትኞቹም ጓደኝነቶች ማደግ አለባቸው፡፡

ብዙውን ጊዜ ከማያቸው የተሳሳቱ አረዳዶች መካከል አንዱ ‹ጥሩ ሕይወት ማለት የተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ መኖር ማለት ነው› የሚለው ድምዳሜ ነው፡፡ ይህ ስህተት ነው፡፡ ጥሩ ሕይወት . የሚመጣው ቀጣይነት ባላቸው የዘወትር ማሻሻያዎች ውስጥ በማለፍ ነው፡፡

እና እኛ ለማስተካከልና ለመሻሻል የምናቅማማው ለምንድን ነው? ምክንያቱም እያንዳንዷን የማስተካከያ ስራ የምንረዳት በመስመራችን ላይ እንደተገኘ ድክመት ስለሆነ ነው፡፡ በእርግጠኝነት እቅዳችን እየሰራ አለመሆኑን እንናገራለን፡፡ በዚህም የውርደት ስሜት ይሰማናል፡፡ እውነታው ግን ሌላ ነው፡፡ እቅድ እንደወረደ ሰርቶ አያውቅም፡፡ ድንገት ያለምንም እንከን ሰርቶ የሚያውቅ ከሆነም እንኳን ሁኔታው ፍፁም አጋጣሚ ነው፡፡

ታዋቂው የአሜሪካ ጀኔራልና በኋላም ፕሬዝደንት) ዋይት ኤዘንሃወር እንዳለው “እቅዶች ምንም አይደሉም፧ ማቀድ ግን ሁሉ ነገር ነው፡፡” ነገሩ ወጥ የሆነ ፅኑ እቅድ ስለመያዝ አይደለም፤ በተደጋጋሚ እና ሁልጊዜ የሚኖር የማቀድና የማሻሻል ሂደት እንጂ።

“ወታደሮችህ ልክ የጠላትን ጦር ሲያገኙ” ይላል ኤዘንሃወር “የትኛውም እቅድ ጥቅም አልባ ይሆናል፡፡

ህገ መንግስታት ሁሉም ህጎች የሚያርፉባቸውን መሰረቶች የሚጥሉ የበላይ ሰነዶች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ሁሉም ህገ መንግስታት በመሻሻል ሂደት ውስጥ ያልፋሉ። ለምሳሌ በ1787 የፀደቀው የአሜሪካ ህገ መንግስት እስካሁን ባለው ዘመኑ 27 ጊዜ ተሻሽሏል። የስዊዘርላንድ ህገ መንግስትም ከ1848 በኋላ ሁለት ትልልቅ ማሻሻያዎችን (revisions) እና በርካታ ጥቃቅን ማስተካከያዎችን አስተናግዷል፡፡ የጀርመኑ የ1949 ህገ መንግስት በበኩሉ 60 ያህል ማሻሻያዎች አይቷል፡፡

ይህ ውርደት ወይም ድክመት አይደለም፡፡ ትርጉም የሚሰጥ ሂደት እንጂ። የማስተካከል አቅም የየትኛውም
ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ መሰረት ነው፡፡  ዴሞክራሲ የሚገነባው በማስተካከያ ስርዓቶች ውስጥ ነው፡፡ በወጉ የሚስራው ብቸኛው የመንግስት አይነትም ይሄ ነው፡፡

እንዳለመታደል ሆኖ በሌሎች ሁኔታዎች ላይ ያላን የማስተካከል ፍላጎት ደግሞ ዝቅ ያለ ነው፡፡ የትምህርት ስርዓታችንን
መጥቀስ ይቻላል። የትምህርት ስርዓታችን በእውነታ እውቀት እና በሰርተፍኬት (ስሪት) ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በዲግሪ እና በስራ ቦታ ውጤታማነት መካከል ያለው ክፍተት ግን ብዙ ነው። ይሄንን እያስተካከልን አይደለም፡፡

በባህሪ እድገታችንም ውስጥ ተመሳሳይ ነገር አለ፡፡ አንድ ብልህና አስተዋይ የምትለው ሰው እንደሚኖርህ እርግጠኛ ነኝ፡፡ የዚህ ሰው አስተዋይ መሆን ዋና ምክንያቱ ምን ይመስልሃል? ስሪቱ? .
(ትክክለኛ ዘር፣ ጥሩ አስተዳደግ፣ ጥራት ያለው ትምህርት) ወይስ የማስተካከል ልምዱ? (በሕይወቱ የሚያያቸውን ክፍተቶችን በየጊዜው እያስተካከለ የመሄድ ችሎታው?)


ሲጠቃለል; ለማስተካከል ያለንን መጥፎ አተያይ ማስወገድ አለብን። ትክክለኛውን - ህግ እንከተላለን ብለው እየታገሉ እድሜያቸውን ከሚያቃጥሉ ሰዎች ይልቅ በጊዜ ራሳቸውን ማስተካከል የጀመሩ ሰዎች የበለጠ ተጠቃሚ ናቸው። ፍፁም የሚባል ልምምድ እና ህግ የለም። የሕይወት ግቦችም ከአንድ በላይ ናቸው። ፍፁም የቢዝነስ ስትራቴጂ የሚባል ነገርም የለም። ትክክለኛ የሚባል አንድ ስራ ብቻም እንዲሁ።
ሁሉም ተረቶች ናቸው። እውነታው ይሄ ነው። በአንድ እርምጃ ትጀምራለህ፤ በየደረጃው እያስተካከልክ ትጓዛለህ፡፡ አለም የበለጠ ውስብስብ እየሆነች በሄደች ቁጥር መነሻ ነጥብህ ጠቃሚነቱን እያጣ ይሄዳል። ስለዚህ “በፍፁም ስሪትህ” ላይ ኃይልህን አታባክን፤ በስራም ቢሆን፣ በግል ሕይወትም ቢሆን፡፡ ከዚያ ይልቅ በአግባቡ እየሰሩ ያልሆኑ ነገሮችን ማስተካከልን ተማር፤ ተለማመድ። ይህንንም በፍጥነት እና ያለ ምንም የጥፋተኝነት ስሜት አድርገው፡፡

✍️ሮልፍ ዶብሊ
📚The art of clearly thinking
#share
@Human_intelligence

ኑ እናንብብ

31 Dec, 05:38


"የምሁራን ሚና በዘመናዊት ኢትዮጵያ"!!
_
__

(በሙሉዓለም ገብረመድኅን)

አይቴ፤ We Let Africa Down Badly በሚለው ዝነኛ መጣጥፉ ላይ አፍሪካውያን ምሁራን ላይ በከረሩ ቃላት ይገስፃቸዋል። ቅሬታውንም ይገልጻል፡፡

በጆርጅ አይቴ ምሁራዊ ግሳጼ የደረሰባቸው ምሁራንን በግብር የሚወክሉ፣ ፊደል የቆጠሩ አሽከሮችን ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ታሪኳ ደጋግማ አስተናግዳለች፡፡ ከሃምሳ ዓመት ወዲህ ባለው ሀገራዊ ጉዟችን ውስጥ በቂ አብነቶችን መጥቀስ ይቻላል።

ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ፕ/ር መሳይ ከበደ ለዚህ ሙግት ዋቢ የሚሆን መጣጥፍ አለው፡፡ Beyond Ideology: The Betrayed Task of Ethiopian Intellectuals በሚል ርዕስ መሳይ፣ የኢትዮጵያ ምሁራንን ገቢራዊ ማንነት በተጠየቅ ሞግቷል፡፡

‹‹ለኢትዮጵያ ሕዝቦች መበደልና በፍትሕ አልባ
ሥርዓት ውስጥ መሰቃየት ምሁራን የሚያሳዩት
ደንታ ቢስነት ሳያንስ ለአምባገነናዊው መንግሥት
የየብሔራቸውን ጥግ ይዘው በመቆም የሚሰጡት
ድጋፍ እጅግ አሳዛኝ ተግባር መሆኑ ግልጽ
ሊሆን ይገባል፡፡ ዛሬ የደረስንበት ሁኔታ የሚያሳየን
ኢትዮጵያ ግድየለሽና አድርባይ ብቻ ሳይሆኑ
ንጉሠ ነገሥታዊው ሥርዓት ከወደቀበት ጊዜ
ጀምሮ አምባገነንነት በጥልቀት እንዲሰፍን
በማድረግ ረገድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ
ኃላፊነት ወይም ተጠያቂነት ያለባቸው መርዘኛና
ሥር ነቀል የሆኑ ምሁራንን አፍርታለች፡፡››

የሚለው መሳይ፤ አውቶክራሲያዊ የነበረው ንጉሠ ነገሥታዊው ሥርዓት በጣም አደገኛና ይበልጥ አፍራሽ በሆነ አምባገነናዊ አገዛዝ እንደተተካ በጽሁፉ ላይ ይሞግታል፡፡

የዛሬን አያርገውና ፕ/ር ዓለማየሁ ገ/ማርያም በተመሳሳይ ተጠየቅ Ethiopia: The Irresponsibility of the Privileged? በሚለው ጽሁፋቸው ፥ የኢትዮጵያ ምሁራንን ኃላፊነታቸውን የዘነጉ ግድ የለሽ ስለመሆናቸው ሞግተዋል፡፡

ፕ/ሩ የምሁራኑን ቀሰስተኝነት ሲገልጹ የሞራል ግዴታውን በመርሳት፤ ደስታውን ከማሳደድ ባሻገር፤ ከራስ ለማትረፍ ከመሯሯጥ ባለፈ፤ በፕሮግራም ታስሮና ተለጉሞ ከዚያ ውጪ የማይንቀሳቀስ የከፍተኛ ትምህርት ምሩቅ ግኡዝ ሮቦት ከመባል ውጪ ሌላ ሊባል አይችልም፤ ሲሉ ኮንነዋል፡፡ (ራሳቸው ግን ዙረው ተዘፍቀውበታል)

የሆነው ሆኖ በየትኛውም ሀገር ያሉ ምሁራን የማህበራዊ፤ ፖለቲካዊና የሳይንሳዊ ለውጥ ግንባር ቀደም ኃላፊ መሆን እንዳለባቸው አጠያያቂ አይደለም፡፡ ይሁንና ለምሁራኑ ሚና የሀገራቱ ሥርዓታት ባህሪ ይወስነዋል፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ባለች ተፈራራቂ አምባገነናዊ ሥርዓታት ስታስተናግድ በኖረች ሀገር የምሁራን ሚና ማህበረ-ፖለቲካዊ ለውጥ ላይ ቢያተኩር ይመረጣል፡፡ የማህበራዊ ኀይሎች ሚና ንቃተ ህሊናቸው በነሆለለበት ሁኔታ የፖለቲካ ነጻነት ተሟጋችና አምራች ኀይል መገንባት የማይታሰብ ነው።

ይህን መንገድ የመረጡ፣ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ በእጅጉ ያሳሰባቸው የትናንትም ሆነ የዛሬ ቄሳራውያን የሴራ ፖለቲካን በተጠየቃዊ አጀንዳዎች የሞገቱ፣ ከአካዳሚያዊ የልሂቅነት ክፍተቶችን ከመድፈን ጎን ለጎን አገዛዙ ያነበረውን ብሔራዊ ድንዛዜ በመግፈፍ የአደባባይ ምክንያተኝነትና የሃሳብ ልዕልና ዜጎች እንዲያገኙ የታገሉ ጥቂትም ቢሆኑ የአደባባይ ምሁራን ነበሩን!

በአጭር ጊዜ ተተኪ ስለማግኘታቸው ግን አጠራጣሪ ሆኗል። ኢትዮጵያ በአደባባይ ምሁራን ድርቅ የተመታች አገር ሆናለች። ህመሟንም እዚህ ግድም ፈልገው።

የዘንድሮ ምሁር አንድም ምንግዴለሽ ነው፤ አልያም ለሥልጣን እውነትን ከመናገር ይልቅ ፥ በሥልጣን ያደረ ደላላ ሆኖ ነው የሚታየው። በዝምታ አልያም በሚና የአገር አፍራሾቹ አጋዥ ካልሆነም የግለሰብ ሥልጣን አስቀጣይነት የኢትዮጵያ ምሁራን መገለጫ ሆኗል።

በርግጥም የኢትዮጵያ አንዱ ደዌ ከዳተኛ ምሁራን ውርሳቸው መቀጠሉ ነው። ይህ ደዌ ማርከሻ መድኀኒት እስካልተገኘለት ድረስ ኢትዮጵያ ከአዙሪቱ መውጣት አይቻላትም። ከዳተኛ ምሁር የሀገሪቱ ህመም ነው!

በተረፈ ግን ያለፈው ሃምሳ ዓመት "የኢትዮጵያ አዕምሮ" የታወከ ነው። የግዕዝ ስልጣኔን የሚሽረው የደደቢቱ ትርክት ምንጩ ነቀልተኝነት ሆኖ የሚታየው በምድረዳ በዳ የበቀለ ይመስል የነበረው የግራ ጭንቅላት ደዌ ይመስለኛል።

ኑ እናንብብ

29 Dec, 17:26


መሞትን መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው። ሰው የሚያውቀው ሁሉ መሞት ተራ የስጋ መበስበስ ነው። ሞክራችሁ ታውቃላችሁ¿ ከማወቅ ነፃ መሆን፣ ከትዝታችሁ ነፃ መሆን፣ ያለ ምንም ክርክር እና ፍርሃት እራሳችሁን በማስደሰት ነፃ መሆን።

በቤተሰባችሁ፣ በቤት፣ በማንነታችሁ ላይ መሞት። ሙሉ በሙሉ ስም-አልባ መሆን። ሙሉ በሙሉ የማይታወቅ ብቸኛው ሰውነትን መላበስ። ሁከት በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ናችሁ እና ምንም ዓይነት ጥቃት እዚህ የለም። ስለዚህ በየቀኑ ይሞቱ፤ እንደ ሀሳብ ሳይሆን በእውነቱ የራስ ለውጥ መጀመርያ ነው።

ሰው በአዕምሮ የሰበሰበውን መጽሃፍ፣ ቤቱን፣ የባንክ ሂሳብ የሚባሉትን ብቻ አይደለም በውስጡ ብዙ ነገሮችን አጭቋል!። የስድብ ቃላቶች፣ የሽንገላ ባህሪዎች፣ የእራሳችሁን ልዩ ልምዶችና ትዝታዎች በጠቅላላ የስነ-ልቦና ስኬቶችን በማሳየት እናንተን እንደሆነ እንዲሰማችሁ አድርጓል። ለዚህ ሁሉ መፍትሔው መሞት ነው፤ ሳይከራከሩ፣ ሳይነጋገሩ፣ ሳይፈሩ፣ ዝም ብለው መተውና መልቀቅ። ይህንን ለትንሽ ጊዜ ያድርጉ ከአዕምሮ ነፃ በመሆን ትመለከታላችሁ። ሚስታችሁ፣ ልብሳችሁን፣ ባለቤታችሁን፣ ልጆቻችሁን ወይም ቤታችሁን "በእኔ" ነው ወይም "የእኔ" ነው በሚል ሃሳብ ስሜታችሁን አሳልፋችሁ ለውስጣችሁ አትስጡ። ዝም ረጭ ከምንም ጋር አለመጣበቅ ነፃ የሆነ ባዶ ስፍራ ነገር ግን በሰላም የተሞላ። በዚህ ሞት ውስጥ ትልቅ ውበት አለ፤  ያ ውበት የማያቋርጥ ዘላለማዊ ፍቅር ይሰጣችኋል።



    
Osho-zen silence 📖

ኑ እናንብብ

29 Dec, 09:32


✅️“በጦርነት ሺህዎችን ከማረከ በላይ ራሱን የገዛ ሰው ታላቅ ነው። ከሌሎች በተሻለ እራሳችንን ብናሽንፍ ምንኛ ታላቅ በሆንን። 

✅️ ምኞትን ተቆጣጥረን በማያቋርጥ ራስን መግዛት ባህል ውስጥ መኖር። ዴቫም ሆነ ጋንዳባ ወይም ከብራህማስ ጋር የተጣበቀች ማራ ይህን ድል ሊለውጠው አይችልም። አሁን ወደ ሽንፈት ለመመስ ጊዜው ረፍዷልና ራስን ማሸነፍ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው!።”


             ―ሲድሃርታ ጓተማ

ኑ እናንብብ

26 Dec, 13:26


‹‹ይመስገን በደሌ››

÷÷÷÷÷÷÷÷÷


ምሽት አስራ ሁለት ሰአት፡፡

‹‹ሰለቸኸኝ›› ብላ በድላኝም የሚያዳላላት ልቤ ላይ ተረማምዳ በሄደች በዓመቱ ተመልሳ መጣች፡፡


‹‹ናፈቅኸኝ- እንዳንተ የሚወደኝ አጣሁ›› ብላ፡፡


ያኔ እንደዋዛ ትተውኝ የሄዱ እግሮቿን እንደዋዛ ወደእኔ ስትመለስባቸው…



ካለ እሷ ያሳለፍኩትን ገሃነምን ገነት የሚያስመስል አመት አውቃ አይደለም፡፡

ምን ነካው እስክባል አብራኝ ሳትሆን ስሟን የጠራሁበትን፣
በየጎዳናውና በየአደባባዩ ያለምክንያት ስንጠራወዝ ሳላያት የተከተልኳትን፣
በናፍቆትዋ ብዛት ለለየለት እብደት አምስት ጉዳይ የደረስኩበትን ጊዜ አታውቀውም፡፡

የእሷን ጠረን ያጣሁበት አመት አስራሁለቱም ወር ክረምት ሆኖ መውጣቱን አታውቅም፡፡


የጉዳቴን ጥልቀት ሳትጠይቅ፣ የስብራቴን ልክ ሳትረዳ…


ዛሬ፣በምሽት ልክ ላንሰራራ ስንጠራራ፣ ልድን ዳር ዳር ስል ‹‹ናፈቅከኝ›› ብላ መጣች እንጂ ለዚህ ሁሉ ግድ የላትም፡፡



ይሄው በሬ ላይ ቆማ ስትቅለሰለስ፣ በሽታዬ አገርሽቶብኝ፣ ጨክኜ ልመልሳት ጉልበት ሳጣ፣ ያለ ይሉኝታ ገፍተር አድርጋኝ ቤቴ ከመግባቷ፣



የገረጣ ፊቴን አይታ ሳትደነግጥ፣ የከሳ ገላዬን ተመልክታ ሳትሳቀቅ፣

‹‹እንዴት ከርምህ?›› እንኳን ሳትለኝ፣


አልጋው ላይ እንደ ኳስ ወርውራኝ ከተጠመጠመችብኝ በኋላ፣
እንክትክት አድርጋው ሄዳ ወጌሻ አጥቶ የከረመ ልቤን ትንፋሽ ባሸነፋቸው ቃላቶችዋ ታባብለዋለች፤
በእጦቷ የተጎዳ ሰውነቴን ተጠግታ ክፉኛ ፣ በአደገኛ ሁኔታ ትተሻሸኛለች፡፡




ካልበረታሁ፣ በዚህ ሰበበኛ ገላዋ ጎትታ ለአንድ አመት ወደነበርኩበት ሲኦል ልትመልሰኝ ነው፡፡
እምቢ ካላልኩ፣ የዚህች ሴት ገላዋ ረጅም ገመድ ነው፡፡

የምወደው፤ የምሞትለት ግን ደግሞ ወደ መቀመቅ የሚያወርደኝ ረጅም ገመድ፡፡


‹‹በናትሽ ተይ›› አልኳት ጉልበቴን ሰብስቤ- ስማኝ ትንፋሽ ሊያጥረኝ ሲቃጣ፡፡
‹‹ለምን….አልናፈቅኩህም?›› አለችኝ መሳምና መተሻሸቷን ጨምራ፡፡


ከአልጋው ላይ ተስፈንጥሬ ተነሳሁና ብቸኛዋ የቤቴ ወንበር- በርጩማ ላይ- ቁጭ አልኩና ዝም ብዬ እያየኋት፣
‹‹ለዚህ አይደለም የናፈቅሽኝ›› አልኳት፡፡


ያልኳት እንዳልገባት የገባኝ ግን ቸኩላ እንዲህ ስትለኝ ነበር፡፡

‹‹እሺ ምንም አናደርግም…ና ወደ አልጋው…ስለናፈቅከኝ ብቻ አንተ ጋ…እዚህ ልደር››

ጠባቡና ያልተነጠፈ አልጋዬ ላይ በደልዳላና የሚያስጎመጅ ግማሽ እርቃን ሰውነቷ ስትቅበጠበጥበት አንደበትዋ ብቻ ሳይሆን መላ ሰውነቷ የሚለማመጠኝ መሰለኝ፡፡


ና…ና….

ዲ-ያ-ቢ-ሎ-ስ፡፡

‹‹አይሆንም…እደሪ ብልስ የት ትተኛለሽ?›› አልኩ የገዛ ቤቴን እንደ አዲስ እየቃኘሁ፡፡


ከአልጋዬ በስተቀር የሚተኛበት ነገር የለም፡፡


ከሷ ጋር አልጋዬን መጋራት ደግሞ ገደል አፋፍ ላይ እንደመቆም ነው፡፡
ጫፌን ነካ ካደረገችኝ ተምዘግዝጌ መውደቄ ነው፡፡
እንደዚያ ለማድረግ ምኔን መንካት እንዳለባት ደግሞ አሳምራ ታውቃለች፡፡

‹‹በመሃል ትራስ እናደርጋለን…ብዙ ትራስ›› አለችኝ አሁንም ቅብጥብጥ ሰውነቷን መቆጣጠር ባቃታት መልኩ እየሰራት፡፡

በእኔና እሷ የተነፋፈቀ ገላ መሃከል እንኳን የትራስ ክምር ቀይባህር ቢዘረጋም ለውጥ የለውም፡፡
ዋናው ቁምነገር ግን እሱ አይደለም፡፡



ለአንድ አመት የከፈልኩት ከባድ ዋጋ በአፍታ ደስታ እንዲሰረዝ አልፈልግም፡፡
ያ ሁሉ እሷን የመርሳት ስቃዬን እሷን በማግኘት ድል እንዲመታ አልፈቅድም፡፡


ለእኔ ይሄንን ገላ አቅፎ መተኛት ማለት….


በስንት መከራ ሲጋራ አቁሞ ከሱስ የተላቀቀ ሰው ከሲጋራ ሱስ መላቀቁን በማስመልከት ሲጋራ ቢያጨስ ማለት ነው፡፡ ምን አይነት እብደት ነው…?


ልክ ይሄን ሳስብ…
ነቃሁ፡፡ በረታሁ፡፡

ከበርጩማዬ ሳልነሳ እንድትሄድ ጠየቅኳት፡፡
በአፏ ሳይሆን አይኖቿ፣ በዳሌዋ፣ በጭኖቿ፣ በጡቶቿ እምቢ አለችኝ፡፡


ያን ጊዜ የናፍቆቷ አይነት ተለይቶ ተገለጠልኝ፡፡


መክሳት መጎሳቆሌን እያየች አንዴት ነህ ሳትለኝ የእሷው ገመምተኛ የሆነ ገላዬን ማቀፍ የፈለገችው ናፍቆትዋ ምን አይነት ቢሆን እንደሆነ ገባኝ፡፡

ጭካኔዋ፡፡ ራስ ወዳድነቷ፡፡



ይሄን ሳውቅ …
ቅድም ያባበለኝ መቅበጥበጥዋ፣ ቅድም ያማለለኝ ገላዋ ወጥመድ ሆኖ ታየኝ፡፡

ያኔ ይበልጥ በረታሁና ከመጠየቅ አልፌ እንድትሄድ አዘዝኳት፡፡
እምቢ ብላ ስትሞላፈጥ ገፍትሬ ማስወጣት ሲቀረኝ ገፍቼ አስወጣኋትና በሬን ቆለፍኩ፡፡

ልክ ያኔ …

ከሄደች በሃዘን ጭጋግ ታፍኖ የከረመው ቤቴ በምሽት ከየት መጣ ባልኩት ብርሃን ሲጥለቀለቅ ፣
አመት ሙሉ ተርበው ሲጠብቋት የነበሩት አይኖቼ በማገገሜ የደስታ እምባ ሲያቀርሩ ተሰማኝና


‹‹አሁን አገገምኩ፡፡ እንኳንም ተመልሳ ምንም እንዳልጎደለብኝ አሳየችኝ…›› አልኩ፡፡


አሁን…


‹‹እንዳንተ የሚወደኝ ሰው አጣሁ›› ብላ የምትመለስ ሴት ሳትሆን፣
‹‹እንዳንተ የምወደው ሰው የለም›› ብላ አብራኝ የምቆይ ሴት እንደምትገባኝ ስለገባኝ፡፡


‹‹ለመቁረጥ በመታደሌ- ይመስገን በደሌ›› እያለ የዘፈነው ማን ነበር!?

ኑ እናንብብ

25 Dec, 08:00


"መውደቅን መፍራት የሚመጣው የማይረቡ እሴቶችን ከመምረጥ ነው።"

✍️ ማርክ ማንሶን

መራመድ እየተማረ ስላለ ህፃን ልጅ ስታስብ፣ ያ ልጅ ለመቶዎች ጊዜ እየወደቀ ራሱን ይጎዳ ነበር፡፡ ነገር ግን የትኛውም ነጥብ ያንን ልጅ ቆም ብሎ “አይ ይቅር ሳስበው መራመድ ለእኔ አይሆንም እዚህ ላይ ጥሩ አይደለሁም” ብሎ እንዲያስብ አያደርገውም፡፡

መውደቅን መሸሽ በህይወታችን በኋላ ላይ የምንማረው ነገር ነው፡፡ እርግጠኛ ነኝ አብዛኛው የትምህርት ስርዓታችን ነው፡፡ ሌላው ትልቁ ድርሻ የሚመጣው ደግሞ ሁልጊዜ ለማዘዝ በሚሞክሩ ሀሳብን በሚያናንቁ ልጆቻቸው እየወደቁም በማይፈቅዱ ቢሆን በራሳቸው እንዲማሩ እንዲያውም የትኛውንም ያልታታዙትን ነገሮች በመሞከራቸው ልጆቻቸውን ከሚቀጡ ጥብቅ ወላጆች ነው፡፡ ከዚያ ደግሞ ያለማቋረጥ የከዋክብትን በስኬት ላይ ስኬት ማግኘት የሚነግሩን መገናኛ ብዙሃን አሉ፡፡ እነዚህ መገናኛ ብዙሃን ስኬቱን ሲነግሩን ያንን ስኬት ለማግኘት የሚያስፈልጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ከባድና አሰልቺ ልምምዶችን አያሳዩንም፡፡

በሆነ ነጥብ ላይ አብዛኞቻችን መውደቅ የምንፈራበት ቦታ ላይ እንደርሳለን፡፡ የዚያን ጊዜ በደመነፍስ ውድቀትን እንሸሽና ፊት ለፊታችን ባለው ነገር ላይ ወይም በለመድነው ነገር ላይ ብቻ ተጣብቀን እንቀራለን፡፡

ይህ ደግሞ ያስረናል፡፡ አፍኖ ይይዘናል፡፡ በእውነት ስኬታማ የምንሆነው ለመውደቅ በመረጥንበት የሆነ ነገር ላይ ብቻ ነው፡፡ ለመውደቅ ፈቃደኛ ካልሆንን ስኬት ለማግኘት ፈቃደኛ አይደለንም ማለት ነው፡፡

አብዛኛው መውደቅን መፍራት የሚመጣው የማይረቡ እሴቶችን ከመምረጥ ነው፡፡ ለምሳሌ ራሴን የምለካበት ደረጃ “የማገኘው ሰው ሁሉ እንዲወደኝ ማድረግ” በሚል ቢሆን መውደቄ የሚወሰነው በራሴ ድርጊቶች ሳይሆን መቶ በመቶ በሌሎች ድርጊቶች ላይ በመሆኑ ጭንቀታም እሆናለሁ፡፡ እኔ ልቆጣጠረው የምችለው ነገር ባለመሆኑ ለራሴ ያለኝ ዋጋ በሌሎች ፍርድና ምህረት ስር ይወድቃል ማለት ነው፡፡

ነገር ግን በዚያ ፈንታ መለኪያዬን “ማህበራዊ ህይወቴን ማሻሻል” ላይ ባደርገው ሌሎች ሰዎች ምንም አይነት ምላሽ ቢኖራቸው እኔ ግን “ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት መኖር” በሚለው እሴት መሰረት መኖር እችላለሁ፡፡ ለራሴ ያለኝ ዋጋ የተመሰረተው በራሴ ባህርያትና ደስታ ላይ ይሆናል ማለት ነው፡፡

የማይረቡ እሴቶች ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ የሚጨበጡ ውጫዊ ግብ የያዙ ናቸው፡፡ እነዚህን ግቦች መከተል ጭንቀት ያመጣል፤ ልናገኛቸው ብንችል እንኳን ባዶነትና ሕይወት አልባነት እንዲሰማን ያደርጉናል፡፡ ምክንያቱም አንድ ጊዜ ካገኘናቸው የምንፈታቸው ሌሎች ችግሮች አይኖሩንም፡፡የተሻሉ እሴቶች እንደተመለከትነው ሂደት ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡

“በአለማዊ ደረጃ ስኬታማ መሆን ለሚለው እሴት መለኪያህ “ቤትና አሪፍ መኪና መግዛት” ቢሆን፣ ያንን ለማግኘት ሀያ አመታት ወጥረህ በመስራት ታሳልፋለህ፡፡ ከዚያ አንድ ጊዜ መለኪያህን ካገኘኸው የሚቀርህ ነገር አይኖርም፡፡ ከዚያ መላውን እድሜህን ሲያሽከረክርህ የኖረው ችግርህ ስለተወገደ የጉልምስና ዘመን ቀውስን መቀበል ትጀምራለህ፡፡ማደግን ለመቀጠልና ለመሻሻል ሌሎች አጋጣሚዎች የሉም፡፡ እናም ደስታን የሚፈጥረው ደግሞ እድገት እንጂ በዘፈቀደ የመጡ ረጅም ዝርዝር ያላቸው ክንውኖች አይደሉም፡፡

ፒካሶ መላውን ህይወቱን ብዙ የሰራ ነው፡፡ እስከ ዘጠናዎቹ እድሜው ድረስ የኖረና እስከ መጨረሻዎቹ ቀናት ድረስ ስዕል ይሰራ ነበር፡፡ መለኪያው “ዝነኛ መሆን” ወይም “በጥበቡ አለም ብዙ ገንዘብ መስራት” ወይም “አንድ ሺ ስእሎች መሳል” ቢሆን ኖሮ ከረጅም ጊዜ በፊት አንድ ቦታ ላይ ቆሞ ይቀር ነበር፡፡ ከዚያ በጭንቀት ወይም ራስን በመጠራጠር ይሸነፍ ነበር፡፡ ስራዎቹን እንዲህ ከአመት ወደ አመት እንዲሻሻሉና እንዲፈጠሩ ማድረግ አይችልም ነበር፡፡ሽማግሌ ሆኖም ካፌ ውስጥ ቁጭ ባለበት ብቻውን በወረቀት ላይ በመሳሉ ደስተኛ ነው፡፡ የተመሰረተበት እሴት ትጉህ እና ፈጣሪ መሆን ነበር፡፡ የእነዚህ እሴት መለኪያ  የማያልቅ ቀጣይነት ያለው የሕይወት ዘመን ሂደት ነው።

#share
የስብዕና ልህቀት
@Human_intelligence

ኑ እናንብብ

21 Dec, 16:53


____

Being a man, in the sense of maturity and character, goes beyond biological definitions. It involves personal growth, responsibility, and integrity. Here are some qualities often associated with this concept:

1. Responsibility: Taking accountability for your actions and decisions, and fulfilling your commitments.


2. Integrity: Being honest and having strong moral principles, even when it's difficult.


3. Emotional Maturity: Recognizing, understanding, and managing your emotions while being empathetic toward others.


4. Respect: Treating others with dignity, regardless of their background, beliefs, or status.


5. Strength and Vulnerability: Balancing inner strength with the courage to show vulnerability when needed.


6. Purpose: Striving to contribute meaningfully to your community, family, or personal goals.


7. Adaptability: Facing challenges with resilience and a willingness to grow and learn.


8. Leadership: Leading by example, inspiring others, and being dependable in times of need.

____

Ultimately, being a man—or simply a mature, responsible person—is a lifelong journey of growth, self-awareness, and building meaningful relationships.
_

@bridgethoughts

ኑ እናንብብ

17 Dec, 09:38


ግቦችን እርሳቸውና በሂደቱ ላይ አተኩር

የተለመደው አረዳድ በሕይወታችን ውስጥ የምንፈልጋቸውን ነገሮች ለማሳካት፣ ብዙ ጭንቀት የሌለበት ዘና ያለ ሕይወትን ለመኖር እና ውጤታማ ሕይወትን ለመምራት ቁልፉ ነገር ሊተገበሩ የሚችሉ ግቦችን ማስቀመጥ ነው” የሚለው ነው፡፡

እኔም ለብዙ ዓመታት ልማዶችን የምቃኝበት መንገድ ይህ ነበር። እያንዳንዳቸው ሊደረስባቸው የሚቻሉ ግቦች ናቸው፡፡ ለምሳሌ በትምሀርት ቤት ውስጥ ማምጣት ስላለብኝ ውጤት ግብ አስቀምጣለሁ። በቢዝነሱ ውስጥ ላገኘው ስለምፈልገው ትርፍ፣ በጂም ቤት ላነሳው ስለምፈልገው ክብደት ወዘተም እንደዚያው፡፡ በተወሰኑት ውጤታማ መሆን የቻልኩ ቢሆንም በአብዛኞቹ ግን አልተሳካልኝም፡፡ በሂደት ያገኘሁት ውጤት ካስቀመጥኩት ግብ ጋር ያለው ግንኙነት ውስን መሆኑን ተረዳሁ፡ ከዚያ ይልቅ ያመጣኋቸውን ውጤቶች ጨምሮ ሁሉም ነገሮች ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ከሂደቱ (system) ጋር እንደሆነ አወቅሁ፡፡

በስርዓታዊ ሂደት (system) እና በግቦች (goals) መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? ይህንን ልዩነት ለመጀመሪያ ጊዜ የተማርኩት ከ “ዲልበርት ኮሚክ” ጀርባ ካለው ካርቶኒስት ከስኮት አዳምስ ነው፡፡ ግቦች ልታሳካቸው የምትፈልጋቸው ውጤቶች ናቸው፡፡ ስርዓታዊ ሂደቱ ግን ወደእነዚህ ውጤቶች የሚመራህ ሂደት ነው፡፡

👉አሰልጣኝ ከሆንክ ምናልባት ግብህ ውድድሩን ማሸነፍ ሊሆን ይችላል። ሂደትህ ደግሞ ተጨዋቾችን የምትመለምልበት መንገድ፣ ልምምድ የምታሰራበት መንገድ፣ ምክትል አሰልጣኞችህን የምትጠቀምበት መንገድ ወዘተ... ናቸው፡፡

👉ሥራ ፈጣሪ ከሆንክ ግብህ ባለ ብዙ ሚሊዮን ዶላር ቢዝነስ መገንባት ሊሆን ይችላል። የምርትን ሀሳቦች የምትፈትንበት መንገድ፣ ሰራተኞችን የምትቀጥርበት ሁኔታ፣ የማርኬቲንግ ስራውን የምትመራበት መንገድ ወዘተ ደግሞ የሂደቱ አካል ይሆናሉ፡፡

👉ሙዚቀኛ ከሆንክ ደግሞ ግብህ አዲስ ሙዚቃ መስራት ሊሆን ይችላል፡፡ የምትሰራቸው _ ልምምዶች ብዛት፣ አስተያየቶችንና ምክሮችን ተቀብለህ የምትተገብርበት ሁኔታ ወዘተ... ግን ሂደቶቹ ናቸው፡፡

አንድ ጥያቄ ደግሞ እናንሳ፡፡ ግቦችህን ሙሉ በሙሉ በመተው ሂደቱ ላይ ብቻ ብታተኩር ውጤታማ መሆን ትችላለህ? ለምሳሌ አንተ የቅርጫት ኳስ አሰልጣኝ ብትሆንና ውድድሩን የማሸነፍ ግብህን ሙሉ በሙሉ ረስተህ ቡድንህ በየቀኑ የሚሰራው ተግባራዊ ሥራ ላይ ብቻ ብታተኩር ውጤት ልታመጣ ትችላለህ?
እኔ ልታመጣ እንደምትችል አስባለሁ።

በየትኛውም ስፖርት ውስጥ ግቡ የተሻለ ውጤት ይዞ ማጠናቀቅ ነው፡፡ የውጤት ሰንጠረዥን እያዩ ሙሉ የጨዋታን ጊዜዎችን ማሳለፍ ግን ትርጉም የለሽ ነው፡፡ እውነተኛው መንገድ ለውጤታማነት በየቀኑ ለመሻሻል መጣርና ልዩነት ማሳየት ነው፡፡ የ3 ጊዜ የሱፐር ቦል አሸናፊው ቢል ዋሽ እንዳለው “ውጤት ለራሱ ይጨነቃል፡፡” ለሌሎች የሕይወት ዘርፎችም እውነታው ይሄው ነው፡፡ የተሻለ ውጤት ማምጣት ከፈለግክ ግቦችን መደርደርን ችላ በልና ሂደቱ ላይ አተኩር፡፡

ምን ማለቴ ነው? ግቦች ምንም ጥቅም የላቸውም እያልኩ ነው? በፍፁም! ግቦች አቅጣጫን ለማስቀመጥ በጣም ጠቃሚ ነገሮች ናቸው፡፡

ለውጥ ለማምጣት በጣም የሚጠቅመን ግን ሂደት ነው፡፡ በቂ ስርዓት ሳትቀርዕ ያስቀመጥካቸው ግቦች ላይ ብቻ በማውጠንጠን ጊዜ ማሳለፍ ብዙ ችግሮች ይፈጥራል፡፡
ከችግሮቹ ውስጥ አራቱን እንመልከት
ይቀጥላል...

Atomic habit
ጄምስ ኬለር

የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence

ኑ እናንብብ

17 Dec, 06:04


ባባ ቫንጋ በቀጣዩ የፈረንጆች አመት 2025 ምን ይከሰታል ብለው ተነበዩ?
ታዋቂዋ የቡልጋሪያ ጠንቋይ "ሶሪያ በአሸናፊዎች እጅ ትገባለች፤ በምስራቁ ምዕራባውያንን የሚያጠፋ ሶስተኛው የአለም ጦርነት ይጀመራል" ብለዋል‼️
ከ28 አመት በፊት ህይወታቸው ያለፈው ባባ ቫንጋ እስከ 2030 ድረስ አለማችን የምታስተናግዳቸውን አበይት ክስተቶች ተንብየዋል
ቫንገሊያ ፓንዴቫ ጉሽቴሮቫ ወይም በተለምዶ ባባ ቫንጋ እየተባሉ የሚጠሩት ቡልጋሪያዊት ጠንቋይ አዲስ አመት ሲቃረብ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ይስባሉ።
አይነስውሯ ባባ ቫንጋ በ85 አመታቸው በፈረንጆቹ 1996 ህይወታቸው ቢያልፍም እስከ 2030 አለማችን የምታስተናግዳቸውን አበይት ክስተት ተንብየዋልና አሁንም ድረስ ይነሳሉ።
በ12 አመታቸው የአይን ብርሃናቸው ካጡ በኋላ የወደፊቱን የመተንበይ ብቃት እንዳዳበሩ የሚናገሩት ባባ ቫንጋ የመስከረም 11ዱን የኒውዮርክ መንትያ ህንጻዎች ጥቃት፤ የሶቪየት ህብረት መፈራረስና ካንሰር የተባለ በሽታ ቀጣይ ስጋትነትን አስቀድመው ተንብየዋል።
ከ16 ቀናት በኋላ በሚገባው 2025ም በአለማችን የሚከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮችን ከህልፈታቸው በፊት ተንብየዋል ብሏል ዴይሊ ታር በዘገባው።
የአውሮፓ ጥፋት
ባባ ቫንጋ የፈረንጆቹ 2025 ምዕራባውያንን ክፉኛ የሚጎዳ አስከፊ ጦርነት የሚከሰትበት መሆኑን ተንብየዋል። በሶሪያ ጉዳይ አስቀድመው ተናገሩት የተባለውም የቡልጋሪያዊቷን እንስት የመተንበይ ችሎታ በጉልህ አሳይቷል። "ሶሪያ በመጨረሻ በአሸናፊዎች እጅ ትወድቃለች፤ አሸናፊው ግን አንድ አይሆንም" ያሉት ባባ ቫንጋ፥ "በምስራቁ ምዕራባውያንን የሚያጠፋ ሶስተኛ የአለም ጦርነት ይጀመራል" ሲሉ ተንብየዋል።
ከዮፎ ጋር ግንኙነት
ባባ ቫንጋ "በ2025 የሰው ልጆች ምንነታቸው ከማይታወቁ በራሪዎች (ዮፎ) ጋር ግንኙነት ይጀምራሉ፤ ይህም ምናልባትም አለማቀፍ ቀውስ ያስከትላል" ይላሉ።
የአሜሪካዋ ኒው ጀርሲ ከአንድ ወር በላይ ዩፎ ይሁኑ ድሮኖች እስካሁን በውል ያልተለዩ በረሪ አካላት በሰማይ እያንዣበቡባት ነው።
ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ካሸነፉ የአሜሪካ መንግስት በዩፎዎች ዙሪያ ያለውን ዝርዝር መረጃ ይፋ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸው ይታወሳል። የትራምፕ መመረጥም የባባ ቫንጋ ትንበያ እውን ሊሆን እንደሚችል አመላካች ነው ተብሏል።
#Alain #Vanga
=====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇⬇️⬇️
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s

ኑ እናንብብ

16 Dec, 05:21


Oneness

__

መቁጠሪያ የሌላቸው ዓለማት የተሰሩበትና የተሳሰሩበት ክር (the fabric of the cosmos) 'አንድ' ነው ይላል Quantum Physics... ታላላቆቹ መንፈሳዊ መምህራን ደግሞ ትስስሩ የተለያዩ 'ነገሮች' ሕብረት አይደለም፤ ግላዊ (subjective) መገለጦች (manifestations) ያሉት አሃድ፣ ከሁልቆ በማይናጸር አንድነት የቆመ አንዳዊነት (Oneness) ነው ይላሉ... 
 

አንዳዊ ነው ስንል ቁጥራዊ (Numerical) ነው እያልን አይደለም... ብቸኛ፣ ተገዳዳሪ የሌለው፣ ተቃራኒ አልባ ማለታችን እንጂ... All that is!!


ይህን አንዳዊነት ሂንዱ 'ብራህማን'፣ ታኦይስት 'ዳዎ'፣ ፊዚስት 'ኢነርጂ' (Unified field)፣ ሱፊ 'Wahdat al-Wujud' ይለዋል...


አንዳዊነት የዩኒቨርሱ እንቆቅልሽ ማጠንጠኛ ነው... የሁለንታ ጠቅላላ ምስጢር ማጎሪያ ነው... የምልዓተ ዓለሙ ትብትብ ውል መፍቻ ነው... ዓለሚቱ ከዚህ የሚበልጥ ዕውቀት የላትም!!...


ይህን እውነት መቀበል ለቅርፃዊው ሰው ከባድ ነው... ብድግ ብሎ የተቃርኖ (duality) መልኮችን በሙሉ እንደሌሉ መቀበል አስቸጋሪ ይመስላል... ምክንያቱም የዕለት ተለት ልምምዶቻችን ይህንን አያሳዩምና... 


ነገሩን በተለያዩ መነጽሮች ውስጥ መመልከቱ ግን አንዳች ቅርጽ ያበጅ ይሆናል... ለምሳሌ ፍልስፍና፣ ሐይማኖትና ሳይንስ ውስጥ እሳቤው ያለውን ቦታ መፈተሽ የመብሰልሰያ ፈር ለማበጀት መነሻ ይሆናል... ከፍልስፍና እንጀምር...
__

@bridgethoughts

ኑ እናንብብ

13 Dec, 05:59


The phrase "If you see the Buddha, kill him" is a well-known Zen koan, often attributed to the 9th-century Chinese Zen master Linji (Rinzai in Japanese). This provocative statement is not meant to be taken literally. Instead, it carries profound spiritual and philosophical meaning in the context of Buddhist practice. Here's an explanation:

1. Letting Go of Attachments:
The statement suggests that clinging to any fixed image or idea of the Buddha (or enlightenment) is a hindrance to true understanding. Enlightenment cannot be confined to an external figure or a specific concept—it is something to be directly experienced.


2. Avoiding Idolatry:
Zen teachings emphasize direct experience and self-discovery. If you encounter an idea of the Buddha, it’s likely a projection of your own mind. The phrase urges you to transcend these projections and seek the ultimate truth beyond external forms.


3. Non-Duality and Liberation:
The koan challenges the dualistic mindset that separates "the Buddha" from "you." It encourages practitioners to realize their own innate Buddha-nature, rather than seeing enlightenment as something outside or separate from themselves.


4. Spiritual Independence:
It also warns against overly relying on teachers, doctrines, or symbols. True awakening comes from within, not from worshipping or blindly following others.



In essence, the phrase is a radical invitation to go beyond superficial understanding and experience the profound, boundless truth for oneself.
___
@bridgethoughts

ኑ እናንብብ

12 Dec, 14:24


የትኩረት መዛባት

በዚህ ማህረሰብ ውስጥ  “ተመልከት የእኔ ሕይወት ከአንተ ሕይወት የበለጠ ያማረ ነው” በሚሉ በማህበራዊ ድረ- ገፆች በሚተላለፉ መልዕክቶች በኩል ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ የጥፋተኝነት ስሜት ወዘተ... የመሳሰሉት አሉታዊ ልምዶች ያሉት ትውልድ እየፈራ ነው፡፡

ሰዎችም ሆነ የቲቪ ማስታወቂያዎች የመልካም ሕይወት ቁልፉ አሪፍ ስራ ማግኘት፣ ወይም ዘናጭ መኪና ወይም ቆንጆ ሴት ጓደኛ ያለህ መሆን እንደሆነ እንድታምን ይፈልጋሉ፡፡ አለም ያለማቋረጥ የሚነግርህ ነገር፣ የተሻለ የሕይወት መንገድ የሚባለው ብዙ መግዛት፣ ብዙ ማግኘት ፣ ብዙ መዋብ እንደሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜ በተደጋጋሚ ስለሁሉም ነገር ግድ እንዲኖርህ በሚነገሩ መልዕክቶች ስለምትጨናነቅ ያለማቋረጥ አዲስ ቅንጡ ነገሮችን ስለመግዛት፤ የእረፍት ጊዜህን ውድ በሆኑ ቦታዎች ስለማሳለፍ የምታስብ ትሆናለህ ወይም ፋሽን ልብሶች እና ኮስሞቲክሶችን ስለመግዛት የምታስቢ ትሆኛለሽ።

  እነዚህ ነገሮች ከባድ የበታችነት እና የጭንቀት ስሜት ከመፍጠራቸውም በላይ በማይገባ አይነት የማይረቡና የውሸት ከሆኑ ነገሮች ጋር የተጣበቅክ እንድትሆንና ሕይወትህን ሙሉ የማይጨበጥ ደስታና እርካታ ስታሳድድ እንድትኖር ያደርግሃል፡፡ የመልካም ሕይወት ቁልፍ ስለ ብዙ ነገሮች መጨነቅ ሳይሆን፣ ስለ ትንሽ ለዚያውም እውነት፣ አስቸኳይና አስፈላጊ ስለሆነው ነገር ብቻ መጨነቅ ነው፡፡

Mark Manson

@zephilosophy

ኑ እናንብብ

12 Dec, 09:56


"ዝምታን የተማርኩት ከለፍላፊ፤ ትግስትን የተማርኩት ደግሞ ትግስት ከሌለው እንዲሁም ደግሞ ደግነትን የተማርኩት ከክፉ ቢሆንም በጣም የሚገርመዉ ነገር ለነዚህ መምህሮቼ ምስጋና ቢስ መሆኔ ነዉ።"
ካህሊል ጅብራን

@zephilosophy

ኑ እናንብብ

10 Dec, 19:43


አንድ የሃይማኖት አባት ጋር 3 ሰዎች ኑዛዜ እየሰጡ ነው።

የሃማኖት መምህሩ ወደ መጀመርያው ሰውዬ በመሄድ "ምን ኃጢአት ሠራህ?" የመጀመርያው ሰውዬ “ቦክሰኛ ነኝ እና ስራ ላይ በተፈጠረ ሰህተት አንድ ሰው ገድያለሁ” ሲል መለሰ። ካህኑም ከወንዙ እጨለፈ “ይህን የተቀደሰ ውሃ ጠጣና ኃጢአትህ ይሻርልሃል” ሲል መለሰ። ቦከሰኛውም እንደተባለው አደረገ።

ካህኑ ወደ ሁለተኛው በመሄድ ጠየቀ "ምን ኃጢአት ሠርተሃል?" ሁለተኛው ሰውዬ፡- “ሜካፕ ሰሪ ነኝ እና እኔ ጋር ሊሰሩ ከሚመጡ ሴቶች ጋር ተኝቻለሁ። በዚህም ባለቤቴ ላይ ማግጫለሁ” ካህኑም በድጋሚ ከወንዙ በመጨለፍ "ይህን የተቀደሰ ውሃ ጠጣና ኃጢአትህ ይሻራል" ሲል መለሰ። ሜካፒሰቱም እንደተባለው አደረገ።

ካህኑ ወደ ሶሰተኛው ሰውዬ ጋር በመሄድ "ምን ኃጢአት ሠራህ?" ሲል ጠየቀው። ሰውዬው ግን ምንም ሳይናገር ካህኑ ከሚጨልፍበት ወንዝ ውስጥ ዘሎ ገባ። ካህኑም በድንጋጤ ጠየቀው "ምን ሆነሃል? የዚህን ያህል ምን አይነት አጥያት ብትሰራ ነው?"

ሶስተኛው ሰውዬ ቁና ቁና እየተነፈሰ መለሰ “እ… ደህና እኔ የቀበሌ ሰራተኛ ነኝ” ሲል ካህኑ አቋረጡትና ከኪሳቸው ብልቃጥ እያወጡ "ተለቅልቀህ ስትጨርስ ይህን ብልቃጥ ጠጣ! እውነት እልሃለሁ በወንዙ ኃጢአትህ ሁሉ ይሻራል፤ ይህን ስትጎነጭ ደግሞ ከዚህ በኋላም አንዳችም አጥያት አትሰራም"

የቀበሌ ሰራተኛው የተሰጠውን ብልቃጥ ግጥም አድርጎ ከጠጣ በኋላ፦“አሁን ቀለለኝ አባ እንዴት ነው ግን ከዚህ በኋላ አጥያት መስራት የማቆመው?”

ካህኑ ተረጋግተው መለሱ፦ "ስለምትሞት!"
🤞🏽😌

ኑ እናንብብ

10 Dec, 19:10


ጥቂት ስለ ሚዲያ ነፃነት
(ተስፋአብ ተሾመ)
* * *

አምባገነኖች ከጥንት እስከዛሬ ማፈን መለያቸው ነው። መረጃ ወደ ህዝብ በአግባቡ እንዳይደርስ መትጋት መታወቂያቸው ነው።

ጋዜጠኞች እና ሚዲያዎች ለህዝብ ድምፅ እንዳይሆኑ ፥ መረጃም እንዳያጋሩ በገዢዎች ሲታፈኑ ማየት ብርቅ ባይሆንም ሁሌም እንደ አዲስ ሀዘንን ይፈጥራል።

ጋዜጠኞች ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ መሆን ይገባቸው ነበር። ነገር ግን ዛሬ ላይ ጋዜጠኞች ራሱ ድምፅ የሚሆንላቸው ይፈልጋሉ። ብዙሃን መገናኛዎች ከተፈጠሩለት አላማ ጋር መተባበር የማይችሉባት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። ይህ ግን ለጨቋኞች የማያዋጣ መንገድ ነው።

ከዚህ ቀደም የመረጃ ምንጮች ዋናዎቹ የመገናኛ ብዙሃን ነበሩ። ጋዜጦች ፥ ቴሌቪዥኖች ፥ ራዲዮኖች ዋነኛ የመረጃ ምንጭ ሆነው ያገለግሉ ነበር። ያኔ እኚህን ብዙሃን መገናኛዎች ማፈን ለጨቋኞች የሚሰጠው አንዳች ጥቅም ይኖራል። እውነትን ለመሰውር ፥ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ለመንዛት ይረዳ ነበር።

ዛሬ ግን እንደዛ አይደለም።

ዛሬ ላይ ማህበራዊ ትስስር ገፆች የመረጃ ምንጭ ሆኗል። መንግስታት ጋዜጦችን ቢያፍኑ ጦማሪያን ፌስቡክ አሊያም ቴሌግራም ላይ ይፅፋሉ። ራዲዮኖች የደበቁትን ሚስጥር ዩቲዩቦች ያጋልጡታል። ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ያልተናገሩትን ቲክቶከሮች ያወሩታል።

ዛሬ ላይ መረጃ ማፈን ቀላል አይደለም።

መንግስታት ጋዜጠኞችን ባፈኑ ቁጥር ማህበራዊ ገፆች ላይ ያሉ ሰዎች ጉልበታቸው እየበረታ ይሄዳል። ተደማጭነታቸው ይጨምራል።

በዚህ ዘመን መንግስታት ሚዲያ በማፈን ጉልበትና የህዝብ ሃብት ከሚያባክኑ ዴሞክራሲን ለማስፈን ቢጥሩ ያዋጣቸው ነበር።


@Tfanos

ኑ እናንብብ

10 Dec, 18:49


ትግልህን ምረጥ!!

“ከሕይወት የምትፈልገው ምንድነው?” ብዬ ብጠይቅህና “ደስተኛ መሆን፣ ታላቅ ቤተሰብ መመስረትና የምወደው ስራ እንዲኖረኝ፡፡” ብለህ ብትመልስልኝ፣ መልስህ የተለመደና የሚጠበቅ ከመሆኑ የተነሳ ምንም ትርጉም የሌለው ይሆናል፡፡

ሁሉም ሰው ጥሩ በሆነው ይደሰታል፡፡ ሁሉም ሰው ጭንቀት የሌለበት፣ ደስተኛና ቀላል ሕይወት መኖር፤ በፍቅር መውደቅ፣ በጣም ደስ የሚል ወሲባዊ ግንኙነትና የፍቅር ጓደኝነት፣ ዘናጭ መሆንና ገንዘብ መስራት፣ ታዋቂና የተከበረ መሆን፣ በጣም የተደነቀ ከመሆን የተነሳ ወደ አንድ ቦታ ሲራመድ ሰዎች እንደ ቀይ ባህር የሚከፈሉለት ቢሆን ይፈልጋል፡፡

ሁሉም ሰው ያንን ይፈልጋል፤ ያንን መፈለግ ቀላል ነው፡፡

በጣም ደስ የሚለውና ብዙ ሰዎች በጭራሽ የማያስተውሉት መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ግን “በሕይወትህ ውስጥ ምን አይነት ስቃይ ትፈልጋለህ? ልትታገል የምትፈልገው ምንድነው?” የሚል ነው፡፡ምክንያቱም ህይወታችን እንዴት እንደሚሆን የሚወስነው ትልቁ ነገር ያ ነውና፡፡

ለምሳሌ ብዙ ስዎች አሪፍ ቢሮ እንዲኖራቸውና ብዙ ገንዘብ መስራት እንዲችሉ ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን በሳምንት ስልሳ ሰዓት በመስራት፣ በረጅም ጉዞዎችና አሰልቺ በሆኑ የወረቀት ስራዎች መሰቃየት የሚፈልጉ ሰዎች ብዙ አይደሉም፡፡

ብዙ ሰዎች አሪፍ ወሲብ፣ ጥሩ የፍቅር ግንኙነት እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ሰው ወደዚያ ለመድረስ አስቸጋሪ የሆኑ ንግግሮችን፣ አሳፋሪ ሁኔታዎችንና የስሜት መጎዳቶችን ለማለፍ ፈቃደኛ አይደለም፡፡ ከዚያ ይረጋጉና፣ ጥያቄው ከ “ቢሆንስ?” ወደ “ከዛስ?” እስኪለወጥ ድረስ ለአመታት ያስባሉ፡፡

ደስታ ትግል የሚጠይቅ በመሆኑ የሚነሳው ከችግር እንጂ ልክ እንደ አበባና ቀስተደመና ከመሬት የሚነሳ አይደለም፡፡ እውነተኛ የእድሜ ልክ እርካታና ትርጉም የሚገኘው ትግሎቻችንን በመምረጥና ማስተዳደር በኩል ነው፡፡

አሪፍ የሰውነት አቋም እንዲኖርህ ትፈልጋለህ እንበል፡፡ ነገር ግን ለብዙ ሰዓታት ጂም ውስጥ በመስራት የሚያጋጥምህን ህመምና አካላዊ ጭንቀት በፅናትና በደስታ ካልተቋቋምክ፣ የምትመገበውን ምግብ መመጠን እና ማስተካከል ካልወደድክ፣ የምትፈልገውን በስፖርት የተገነባ ሰውነት አታገኝም፡፡

ሰዎች የራሳቸውን ስራ መስራት ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን ያንን ለማድረግ በሚደረግ ሙከራ የሚያጋጥማቸውን አደጋ፣ እርግጠኛ ያለመሆን፣ ተደጋጋሚ ውድቀት ካልተቋቋሙ፣ ምንም ነገር ጠብ ለማይል ነገር ያጠፏቸውን ጊዜያት በደስታ ካልተቀበሉ፣ስኬታማ ስራ ፈጣሪ መሆን አይችሉም፡፡

ሰዎች የትዳር አጋር፣ ወይም የፍቅር ጓደኛ ይፈልጋሉ። ነገር ግን ከሚያጋጥሙህ ተደጋጋሚ አለመፈለጎች የተነሳ የሚመጣብህን የስሜት መዋዠቅ በትዕግስት  ካላለፍክ፣ ማስተንፈስ የማትችለውን ወሲባዊ ውጥረት ካልተቋቋምክና የማይደወል ስልክ ላይ ማፍጠጥን ካልተጋፈጥክ ማራኪ አጋር ማግኘት አትችልም፡፡ ይህ የፍቅር ጨዋታ ክፍል ነው፡፡ ካልተጫወትክ ማሸነፍ አትችልም፡፡

ያንተን ስኬት የሚወስነው “በምን መደሰት ትፈልጋለህ?” በሚለው ጥያቄ አይደለም፡፡ ወደ ደስታ የሚወስደው መንገድ በሚያንሸራትቱ ነገሮችና በእፍረት የተሞላ በመሆኑ ተገቢ የሚሆነው ጥያቄ “ምን አይነት ስቃይን መቋቋም ትፈልጋለህ? የሚል ነው፡፡
ሕይወት ሁልጊዜ በፅጌረዳ ያሸበረቀ ሊሆን አይችልም፡፡ ስቃይ አልባ ሕይወት ሊኖርህ የማይችል ከሆነ ደግሞ የሆነ ነገር መምረጥ አለብህ፡፡

በጣም አስፈላጊውና ከባዱ ጥያቄ፣ “መቋቋም የምትፈልገው ምን አይነት ስቃይ ነው?” የሚለው ነው፡፡ የሆነ ቦታ የሚያደርስህና ለሕይወት ያለህን እይታ ሊለውጥ የሚችለውም ጥያቄ ይህ ነው፡፡ እኔን እኔ፣ አንተን አንተ ያደረገን እንዲሁም እኛን የሚገልፀንና የሚለያየን በመጨረሻም አንድ ላይ የሚያደርገን ጥያቄ ይህ ነው፡፡

በአብዛኛው በጉርምስናና በወጣትነት ዘመኔ ሙዚቀኛ በተለይም የሮክ ሙዚቃ ኮከብ ስለመሆን አልም ነበር።የትኛውንም በጊታር የታጀበ ሙዚቃ ስሰማ አይኖቼን ጨፍኜ በምናቤ ራሴን መድረክ ላይ በአድናቆት
ለሚጮኹ ብዙ ሰዎች ጊታር ስጫወት፣ ሰዎች በእኔ ጊታር አጨዋወት ተማርከው ራሳቸውን ሲስቱ እመለከት ነበር፡፡ ሀሳቡ ለእኔ ቢሆንስ? የሚል ጥያቄ ስላልነበረ ይህ ህልም ለሰአታት ይዞኝ ይቆይ ነበር፡፡ በአድናቆት በሚጮኹ ተመልካቾች ፊት እንደምጫወት እርግጠኛ ነበርኩ፤ ግን መቼ? ሁሉንም ማቀድ ነበረብኝ፡፡ እዚያ ደርሼ አሻራዬን ለማሳረፍ፣ እንዲሁም አስፈላጊውን ኃይልና ጥረት መስጠት ከመቻሌ በፊት ጊዜዬን መጠበቅ ነበረብኝ፡፡ በመጀመሪያ ትምህርቴን መጨረስ፣ ከዚያ ጊታር ለመግዛት ተጨማሪ ገንዘብ መስራት፣ ከዚያ ደግሞ ለመለማመድ በቂ ነፃ ጊዜ ማግኘት፣ ቀጥሎ የመጀመሪያ ፕሮጀክቴን ማቀድ ያስፈልገኝ ነበር፡፡ ከዚያ... ከዚያ. . . በቃ፡፡

ይህንን ነገር የእድሜዬን ግማሽ ያህል ሳልመው የኖርኩ ቢሆንም ምኞቴ ግን ለፍሬ አልበቃም፡፡ በመጨረሻ ለምን ለፍሬ እንዳልበቃ እስክረዳ ድረስ ረጅም ጊዜና ረጅም ትግል ወስዶብኛል፡፡ ለካ ለፍሬ ያልበቃው ከልቤ ስላልፈለግኩት ነበር፡፡

በምናቤ ራሴን መድረክ ላይ ሆኖ ሳየው፣ ሰዎች በአድናቆት ሲጮሁ፣ እኔ ፍፁም ከልቤ ሆኜ ጊታር ስጫወት ሳልም ፍቅር የወደቅኩት ከውጤቱ ጋር እንጂ ከሂደቱ ጋር አልነበረም፡፡

ያልተሳካልኝም በዚያ ምክንያት ነበር፡፡ በተደጋጋሚ ወድቄያለሁ፡፡ በበቂ ሁኔታ አለመሞከር ብቻ ሳይሆን እንዲያውም አልሞከርኩም ማለት ይቻላል፡፡ የየእለቱ አሰልቺ ልምምድ፣ የሙዚቃ ቡድን መፈለጉና አብሮ መለማመዱ፣ ሰዎችን የመጠበቁ ስቃይ፣ የጊታሬ ክሮች መበጠስ፣ እቃዎቼን ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ የመኪና አለመኖር ህልሜን ተራራ የሚያክል አድርጎብኝ ነበር፡፡ እዚያ ላይ ለመድረስ ደግሞ ተራራውን መውጣት ያስፈልግ ነበር፡፡ እኔ ደግሞ የወደድኩት ውጤቱን በምናቤ ማየት ብቻ ስለነበር፣ ብዙም ተራራ መውጣት እንደማልወድ ለመረዳት ብዙ ጊዜ ወስዶብኝ ነበር፡፡

የተለመደው ባህላዊ ትረካ ያቋረጥኩ ወይም ተሸናፊ መሆኔ፣ “ያላገኘሁ” መሆኔ፣ ህልሜን በመተው እና ምናልባትም በህብረተሰቡ ጫናዎች እንድሸነፍ በማድረግ በሆነ መንገድ ራሴን እንድወድቅ ያደረግኩ እንደሆንኩ ይነግረኛል፡፡

እውነቱ ግን ከእነዚህ ገለፃዎች በተሻለ ደስ የሚል አለመሆኑ ነው፡፡ እውነቱ የሆነ ነገር እንደምፈልግ አስቤ ነበር፡፡ ግን አልፈለግኩም ነበር፡፡ አለቀ፡፡ የፈለግኩት ሽልማቱን እንጂ ትግሉን አልነበረም፤ የፈለግኩት ውጤቱን እንጂ ሂደቱን አልነበረም፡፡ ፍቅር የያዘኝ ከድሉ እንጂ ከትግሉ አልነበረም፡፡

ሕይወት ደግሞ በዚያ መንገድ አይመራም፡፡ማንነትህ የሚታወቀው ልትታገልለት ፈቃደኛ በሆንከው ነገር ነው፡፡ ስፖርት የመስራትን ትግል በደስታ የሚቀበሉ ሰዎች የሚፈልጉትን ስፖርታዊ አቋም ያገኛሉ፡፡ ረጅም የስራ ሳምንትንና ቢሮክራሲ መቋቋም የሚችሉ ሰዎች የአመራር መሰላል ጫፍ ላይ መድረስ የሚችሉ ሰዎች ናቸው፡፡

ይህ ስለ ቆራጥነት ወይም ጥርስን ስለመንከስ አይደለም፡፡ ይህ “ህመም ከሌለ ማግኘት የለም” የሚለው አይነት ሌላ ግሳፄ አይደለም፡፡ ይህ ትግላችን ስኬታችንን ይወስናል፡፡  ችግሮቻችን የደስታዎቻችን መፈጠሪያ ናቸው የሚል የሕይወት በጣም ቀላሉና መሰረታዊ አካል ነው፡፡

አየህ ይህ መጨረሻ የሌለው ቀጥ ብሎ የቆመ ጠመዝማዛ ብረት ነው፡፡ የሆነ ነጥብ ላይ መውጣት ማቆም እንደሚፈቅድልህ ካሰብክ፣ ነጥቡን ስተሃል ብዬ እፈራለሁ፡፡ ምክንያቱም ደስታው ያለው በራሱ በመውጣቱ ላይ ነውና!!

📚The subtle art of not giving a fuck
✍️Mark Manson

የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence

ኑ እናንብብ

10 Dec, 13:35


ቤተል አደባባይ ላይ ተሽከርካሪዎች በግድ እንዲቆሙ እየተደረጉ ሰዎች እየታገቱ መሆኑ ታወቀ

(መሠረት ሚድያ)- ከቅርብ ወራት ወዲህ ቤተል አደባባይ ላይ በተለይ ዘመናዊ የሚባሉ መኪናዎችን የሚያሽከረክሩ ሰዎች በሁለት ሌሎች መኪናዎች መንገድ ተዘግቶባቸው በጠራራ ፀሀይ እየታገቱ እንደሆነ ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

እነዚህ ግለሰቦች በዚህ መልኩ ታግተው ከተወሰዱ በኋላ እስከ 5 ሚልዮን ብር እየተጠየቀባቸው እንደሆነ ለመሠረት ሚድያ የሚደርሰው ጥቆማ ያሳያል።

አንድ የጉዳዩ ሰለባ የሆኑ ግለሰብ ድርጊቱን ለማንም እንዳይናገሩ ማስፈራርያ ስለሚደርሳቸው እንጂ በዚህ መልኩ በርካታ ዜጎች ታፍነው እየተወሰዱ ገንዘብ ከፍለው እየተለቀቁ እንደሆነ ተናግረዋል።

ሁለት ሚልየን ብር ከፍለው እንደወጡ የሚናገሩት ግለሰቡ ያገቷቸው ሰዎች የፀጥታ አካላት እንደሆኑ እንደደረሱበት ጨምረው ተናግረዋል።

"ህዝብን ይጠብቃሉ ተብለው የሚመደቡ አካላት ህዝብ ላይ እንዲህ በደል ሲያደርሱ ማየት እጅግ ያሳዝናል" ያሉን ግለሰቡ በዚህ ምክንያት ከሀገር ለመውጣት እንደተገደዱ ተናግረዋል።

በተያያዘ ዜና ከውጭ ሀገራት ወደ ሀገር ቤት ለዘመድ ጥየቃ፣ ለመዝናናት እና ለስራ የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የእገታ ሰለባ እየሆኑ እንደሆነ ታውቋል።

ሰዎች ከውጭ እንደመጡ ሲታወቅ በክትትል ኢላማ ውስጥ እንዲገቡ እንደሚደረጉ የተጠቆመ ሲሆን በተለይ ሀብትና ንብረት እንዳላቸው የሚታወቁ የዲያስፖራ ኮሚኒቲ አባላት እገታ እንደተፈፀመባቸው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

አንዳንዶች ካረፉበት ሆቴል እና አፓርትመንት ጭምር "ትፈለጋለህ" በሚል ምክንያት እንደሚወሰዱ እና በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ግን የገንዘብ ድርድር እንደሚጀመር ታውቋል።

በዚህም እስከ 2 ሚልየን ብር ከፍለው የተለቀቁ የዲያስፖራ ኮሚኒቲ አባላት እንዳሉ እና ይህም በኤምባሲዎች እና በፖሊስ ተቋማት በኩል ጭምር እንደሚታወቅ ጨምሮ ተገልጿል።

በክፍላተ ሀገራት ይፈፀሙ የነበሩ የእገታ ወንጀሎች አሁን አሁን በጠራራ ፀሀይ በመሀል አዲስ አበባ እየተፈፀመ መሆኑ በብዙዎች የሚታወቅ ቢሆንም መረጃው እንዳይወጣ በሚፈፀም ማስፈራራት ወደ ሚድያ እንደማይወጣ ታውቋል።

መረጃን ከመሠረት!

@MeseretMedia

ኑ እናንብብ

09 Dec, 13:09


`` በክረምት ጥልቀት ውስጥ የማይጠፋ በጋ በራሴ ላይ አገኘሁ። አእምሮ በውጥረት ልባችንን በህመም የሚሞላ መከራ እስካልገጠመን ድረስ ምን ያህል ጠንካራ እና ኃያል እንደሆንን አናስተውልም። በሁላችንም ውስጥ ታላቁን ተራራ የመቋቋም ድፍረት እና ችሎታ እንዳለን ስንገነዘብ፤ በመንገዳችን ላይ ያለው ከባድ ጊዜ ለጥንካሬ የተዘጋጀ ግብዣ አድርገን እንወስደዋለን። ያለደም ስርየት የለም!፤ የምንነጻው ስንጨማለቅ ነው.. ``

  አልበርት ካሙስ

የስብዕና ልህቀት
@human_intelligence

ኑ እናንብብ

30 Nov, 06:14


በዚህ ቻናል
ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#join በማድረግ የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ ይሁኑ
👇👇👇
የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence

ኑ እናንብብ

30 Nov, 05:41


ፍቅር እንዳማረበት እንዲዘልቅ የሚያደርጉ 10 መንገዶች
#Share (ላገባም ላላገባም የሚሰራ ነው።)
__
የፍቅር ተፈጥሮአዊ አካሄድ አልጋ በአልጋ እ
ንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ የፍቅር ግንኙነቱ ሲጀመር የነበረው ፍቅር በሂደት እየቀነሰ የነበረው እንዳልነበረ ሊሆን ሁሉ ይችላል፡፡ በመሰረቱ ካልታረመ፣ ካልተኮተኮተ፣ በጥቅሉ አስፈላጊው እንክብካቤ ካልተደረገለት ዝም ብሎ ማበቡን እና መልካም ፍሬ ማፍራቱን የሚቀጥል ምንም ነገር የለም፡፡ ያልተሰራበት ግንኙነት እጣ ፈንታው ደስታ አልባ መሆን ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ እጅግ በጣም ጥሩ የሚባሉ፣ ለብዙዎች ምሳሌ ሆነው የሚቀርቡ የፍቅር ግንኙነቶች እንኳን ፍፃሜያቸው የማታ ማታ መራራቅ አልፎ ተርፎም መለያየት ሊሆን ይችላል፡፡ ትልቁ የፍቅር ሕይወት ፈተና ሲጀመር የነበረው ፍቅር እንዳማረበት እንዲዘልቅ ማድረግ ነው፡፡

ምንም እንኳን ፍቅርን ለመመስረት ሁለት ሰዎች አስፈላጊ ቢሆኑም እንዲፀና እና ይበልጥ አስደሳች እንዲሆን ለማድረግ ግን አንድ ሰውም በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ ኃላፊነቱን ግን አስቀድሞ መውሰድ ይጠይቃል፡፡ የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ነው የሚያድረው፡፡ ክፍቱን የተተወ ቤት ውስጥ ብዙ ነገር ገብቶ ይወጣል፤ ብዙ ነገር እንዳልነበረ ይሆናል፡፡ ያለመጠባበቅ የቻልነውን ያህል ለማድረግ ጥረት ማድረግ አስፈላጊ የሚሆነው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ውጤቱ ላይ ትኩረት ማድረግ ጥሩ ነው፡፡ ዋናው ነገር ከእሷ ወይንም ደግሞ ከእሱ መምጣቱ ሳይሆን ዞሮ ዘሮ የሁለቱ የፍቅር ግንኙነት ጣፋጭ እና ፅኑ መሆኑ ነው፡፡ ፍቅራችሁ የሚፀናበት ይበልጥ የፈካ እና የደመቀ፣ ዘመናትን የተሻገረ መሆን የሚችለው ያለመጠባበቅ ኃላፊነት ወስዳችሁ መስራት ያለባችሁን መስራት ስትችሉ ነው፡፡ ምንም ተባለ ምንም አንድ ሰው ሁልጊዜም ኃላፊነቱን መወጣት መጀመር አለበት፡፡ በራሱ ሊንቀሳቀስ እና ሊለወጥ የሚችል ምንም ነገር የለም፡፡ የትዳር ግንኙነት ሲሆን ደግሞ ለማደስ ጥረት ካልተደረገ ወደ መፍረሱም ሊያቀና ይችላል፡፡

ቀጥሎ የትዳር ህጎች ከሚል መጽሐፍ ውስጥ ያገኘናቸውን 10 ፍቅር እንዳማረበት እንዲዘልቅ ያደርጋሉ የሚባሉ ህጎችን አለፍ አለፍ ብለን እናስቃኛችሁ፡፡ እነዚህ ተግባራት ላገቡ ብቻ ሳይሆን ላላገቡና በፍቅር ግንኙነት ላሉም የሚጠቅሙ ተግባራት ናቸው ፡፡

1ስሜትን የሚያነቃቁ ነገሮችን ማድረግ

መቼም አብሮ ሲኖር የሚያጋጭ፣ የሚያቀያይም፣ ቅሬታ የሚፈጥር ወዘተ ብዙ ነገር ይኖራል፡፡ ስሜት ይህንን ተከትሎ ይቀዘቅዛል፡፡ ፍቅር ስሜትም ነው በአንድ ጎኑ፡፡ በመሆኑም ስሜትን የሚያነቃቃ ደስታ የሚፈጥር ነገር ማድረግ የአድናቆት አስተያየት መስጠት ለአብነት ያህል አስፈላጊ ነው፡፡ ስራዬ ብላችሁ ማድነቅን ተለማመዱ፡፡ “ትላንት ማታ ጓደኛዬ ቤት በጣም ተጫዋች ሆነህ ነበር ያመሸኸው፤ ደስ ብሎኛል”፣ “አምሮብሻል” ወዘተ ዓይነት አድናቆት ሊሆን ይችላል፡፡ ከትችታችን ይልቅ አድናቆታችን በጣም መብለጥ ይኖርበታል፡፡

2ትችትን መቀነስና አድናቆት መጨመር

በአንፃሩ ትችት ትዳር ሲመሰረት አካባቢ አስፈላጊ ነው ይላሉ ብዙ ሰዎች፡፡ ጊዜ በነጎደ ቁጥር ግን ሰዎች ለትችት አለርጂክ መሆን ይጀምራሉ፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ትችትን መቀነስ አንድ አንድ ነገሮችን አይቶ እንዳላዩ ማለፍም ያስፈልጋል፡፡ መነገር አለበት የምንለው ነገር ካለም ከሁለት እና ሶስት አረፍተ ነገር ባልበለጠ እርዝማኔ መገልፅ ይመከራል፡፡ እርግጥ ነው ለትዳርና ፍቅር መጽናት አስፈላጊ የሆኑ መስተካከል ያለባቸው ነገሮች ከሆኑ፤ ግንኝነቱን በማይጎዳ መልኩ መነጋገሩ አስፈላጊ ነው፤ ምክኒያቱም አለባብሰው ቢያርሱ በአፈር ይመለሱ እንዳይሆን፡፡ ስለዚህ ትችቱ ለፍቅር ግንኝነቱ ሲባል እንጂ እጸጽን ነቅሶ ለማውጣትና የእራስን ትክክለኝነት ለማጉላት መሆን የለበትም፡፡ ትችት በምንሰጥበት ጊዜ ከጥሩ ጀምረን መሀል ላይ ትችታችንን ገልጸን ከዛም በአድናቆት ወይም በበጎ ነገር መደምደም ይመከራል (ሳንድዊች እስታይል እንደሚባለው)፡፡

3አዳማጭ ሁኑ

ማደመጥ ለፍቅረኛችን ወይንም ለትዳር አጋራችን የምንሰጠው ትልቁ ስጦታ ነው፡፡ ትርጉም መስጠታችሁን፣ ተሳሳተ የምትሉትን መረጃ ማስተካከላችሁን ጥላችሁ በሙሉ ልባችሁ ማዳመጥ ጠቃሚ ነው፡፡

4ራሳችሁ ላይ ትኩረት አድርጉ

ለራሳችሁ፣ ጓደኞቻችሁ፣ ቤተሰባችሁ ወዘተ ከትዳራችሁ በተጨማሪ ጊዜ መስጠት ጥሩ ነው፡፡ የግላችሁ ጊዜ ማሳለፊያ ልምድ ይኑራችሁ፡፡ በራሳችሁ እና በራሳችሁ ጉዳይ ላይ ምንም ትኩረት የማታደርጉ ይልቁንም ሙሉ ትኩረታችሁ የትዳር አጋራችሁ ላይ ከሆነ ተቺዎች ወይንም ደግሞ ጭንቀታሞች ትሆናላችሁ፡፡ እያንዳንዷን እዚህ ግባም የማትባል ጉዳይ እያነሳችሁ ስትጥሉ አሰልቺ እና አፋኝ ዓይነት ግንኙነት እንዲኖራችሁ ታደርጋላችሁ፡፡

5ይቅርታ ጠይቁ

ምንም እንኳን ለተፈጠረው ችግር የእናንተ እጅ ድርሻ ትንሽ እንደሆነ ብታስቡም “እኔ ይኼ ችግር እንዲፈጠር ለተጫወትኩት ሚና ይቅርታ ይደረግልኝ” ማለትን ተለማመዱ፡፡

6ይቅርታ ካልተጠየኩኝ ሞቼ እገኛለሁ አትበሉ

አንድ አንድ ጊዜ ይቅርታ ሳይጠይቁ ሰዎች መተዋቸውን፣ ለውጥ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው በተለያየ መንገድ ሊገልፁ ይችላሉ፡፡ይቅርታ ካልተጠየኩ ሞቼ እገኛለሁ ማለት ግን አላስፈላጊ ተደራራቢ ችግር ይፈጥራል፡፡ ዋናው ቁም ነገር ተፈላጊው ለውጥ መምጣቱ ነው፡፡

7ዘወትር ፈላጊዎች አትሁኑ

በስሜት የራቀ የሚመስል ሰው ጫና ሲደረግበት ይበልጥ ይርቃል፡፡ መተንፈሻ አየር መስጠት፣ ራስ ላይ ትኩረት ማድረግ በአንፃሩ የራቀንም ያቀርባል፡፡ የት ወጣች የት ገባች ውጤታማ አይደለም፡፡

8ሀሳባችሁን አጭር እና ለስላስ በሆነ መንገድ ግለፁ

ደጅ ደጁን የሚል ሰው አንድ አንድ ጊዜ ህመም የሚፍጥረበትን የቃላት ልውውጥ ሽሽት ውስጥ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሀሳብን አጠር አድርጎ፣ በተለሳለሰ መንገድ መግለፅ ጥሩ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ድምፅንም ጭምር ዝቅ አድርጎ መናገር ተገቢ ነው፡፡ ከጣራ በላይ ድምፅን ከፍ አድርጎ መናገር ቁጣ ይመስላል፤ ከሆነም በዛ መልኩ መግለፁ አስፈላጊ አይደለም፤ ከመፍትሄነት ይልቅ የባሰ ችግር ፈጣሪነቱ ይጎላል፡፡

9ሁሉን መስዋዕት አታድርጉ

ተለዋወጭ ሰው መሆን አስፈላጊ ባይሆንም ሁሉንም ነገር ለእርስ በእርስ ግንኙነቱ ሲባል መስዋዕት ማድረግ ግን አይመከርም፡፡ ጫና እየተደረገባችሁ ሁሉንም እምነታችሁን፣ ምርጫችሁን እና መንገዳችሁን ገደል አትክተቱ፡፡

10በመጠኑም ቢሆን ሁለታችሁም የግልጊዜ ይኑራችሁ

ሰዎች በባህሪያቸው የሚሳቡት ከእርስ በእርስ ግንኙነቱ ውጪ ሌሎች ተጨማሪ የሚወዳቸው የራሱ ነገሮች ወዳሉት ሰው ነው፡፡ የመጽሐፍት ክበብ፣ በጎ ፍቃድ፣ ዋና ወዘተ ሊሆን ይችላል ባላችሁ ትርፍ ጊዜያችሁ መሞከሩ ይመከራል፡፡ ለብቻችሁ የሚኖራችሁ ጊዜ በጋራ ለሚኖራችሁ ጥሩ ቆይታ አስተዋፅዖ ያደርጋል፡፡ሁሌ አብሮ መሆን መዛዛግና መሰለቻቸት ሊፈጥር ይችላል ፡፡

በነጋሽ አበበ

የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence

ኑ እናንብብ

29 Nov, 09:59


"መስሪያ ቤታችንን ግን ምን ነካው?" አለ የመብራት ሃይል ሰራተኛ 😂

ኑ እናንብብ

21 Nov, 15:49


ኢትዮጵያን የሚወክለን ክፋ.ት ነው
(ተስፋአብ ተሾመ)
* * *

አንድ ወጣት መታረ.ዱን ሰማን። ሰው እንደ እንደእንስሳ ተጋድሞ በአንገቱ ስለት አለፈበት ተባለ። ቪዲዮውን አላየሁትም። ማየትም አልፈልግም።

ከጥቂት አመታት በፊት Is is ኢትዮጲያውያንን አንበርክኮ ሲያ.ርዳቸው ሁላችንም ተደናግጠን ነበር። "የሰው ልጅ በዚህ ልክ እንዴት ይከፋል?" ተባባልን። የ አይ ኤስ ድርጊት የፈጠረብን ድንጋጤ ሳይለቀን በደቡብ አፍሪካ ሰዎች በህይወት ሳሉ እሳት ተለቀቀባቸው። ያኔ እኛ እንዲህ ያለ ክፋት የማንፈፅም እንደሆንን ይሰማን ነበር።

ሩቅ የሚመስለው ቀርቦ ለማየት ጥቂት እድሜ ብቻ በቃን። በገዛ ሐገራችን ሰው ተዘቅዝቆ ተሰቀለ። ወንድም ወንድም ላይ ጨከነ።
"እንዲህ ያለ ነውር እኛን አይወክለንም" ብለን እያሰብን ሳለ ነውር ተደጋገመ። ሰዎች በእሳት ሲቃጠሉ ተመለከትን ፥ ነብሰ-ጡሮች የጭካኔ ሰለባ ሆኑ፥ ህፃናት አንገታቸው ላይ ሰይፍ ገባ፥ ወጣቶች በድንጋይ ተወ.ግረው ተገ.ደሉ፥ ሴቶች ማህፀናቸው የጦር ሜዳ ሆነ ፥ አዛውንቶች በመደዳ ተረ.ሸኑ፥ ጭካኔ መደበኛ ሆነ።

ከመቀሌ እስከ ሞያሌ፥ ከአሶሳ እስከ ሀዋሳ ፥ ከወላይታ እስከ ሰበታ.... የክፋት አይነት ታየ። በአራቱም መአዘን ሁሉም አይነት ነውር ተደረገ።

ባለፉት ጥቂት አመታት ብቻ እምነት ተቋማት እሳት በልቷቸዋል፥ አዛውንቶች ተዋርደዋል ፥ ከተሞች ወድመዋል ፥ እርስ በእርስ ተጠቃቅተናል።

"አንድ ነን" እያልን ስንመፃደቅ የከረምን ቢሆንም እርስ በእርስ ምን ያህል እንደምንጠላላ እና ለመጠፋፋት አጋጣሚዎችን ስንጠብቅ እንደኖርን ያለፉት አመታት ምስክሮች ናቸው። ኦርቶዶክሳዊያን ሲጠቁ ጮቤ ይረግጡ የነበሩቱ ጥቂት አልነበሩም። ሙስሊሞች ሲበደሉ ሀሴት ያደርጉ የነበሩቱ ቀላል ቁጥር የላቸውም። አማራ ሲታ*ረድ የሚፈነደቁቱ ተቆጥረው አያልቁም። በትግራዋይ ሞ.ት የተሳለቁቱ ቀላል ቁጥር የላቸውም። ለኦሮሞ ሞ.ት ደንታ ቢስ የሆኑቱ እልፍ ናቸው። ከሶስቱ ብሔር ውጭ ለሆኑቱ ደግሞ ማንም ግድ የለውም።

በሐገራችን ከእለት ወደ እለት ብዙ ጥፋት እንሰማለን። አጋንንት የሰው ገላ ለብሰው ይንቀሳቀሱ ይመስል ጨካኞች ሆነናል። ነገር ግን መመፃደቃችን ዛሬም ከእኛ ጋር ነው።

ብዙ ፀያፍ ነገር ከተፈፀመ በኋላ "ይሄ ድርጊት አይወክለንም" እንላለን። ታዲያ የሚወክለን ምንድነው? መራራውን እውነት መቀበል አለብን። የእስከዛሬው ጥፋት ይወክለናል።

ዘረ.ኛ መሆናችንን ማመን አለብን። ጨካኝ እና ፅንፈኛ መሆናችንን መካድ አይጠቅመንም። አለአዋቂነት እንዳስገበረን መቀበል ይኖርብናል። እኛን የሚወክለን ክፋት ነው። ይህን ካላመንን አንድንም።

በሽታችንን ካላመንን ልንፈወስ አንችልም። እውነቱን እንቀበለው። እርስ በእርስ እንጠላላለን፥ አለአዋቂ ነን ፥ ፅንፈኛም ነን... ይህ ነው የሚወክለን


@Tfanos

ኑ እናንብብ

20 Nov, 15:19


'የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጎምጀትም ሁሉ ተጠበቁ '

#Ethiolia | በ40 ዓመቷ በጨጓራ ካንሰር ከመሞቷ በፊት በዓለም ታዋቂው ዲዛይነር እና ደራሲ “ክሪስዳ ሮድሪጌዝ” እንዲህ ስትል ፅፋለች።

1. ጋራዥ ውስጥ የአለማችን ውድ መኪና ነበረኝ፣ አሁን ግን በዊልቸር መንቀሳቀስ አለብኝ።

2. ቤቴ ሁሉንም አይነት ብራንድ ያላቸው ልብሶች፣ ጫማዎች እና ውድ እቃዎች ይሸጣል፣ አሁን ግን ሰውነቴ በሆስፒታሉ በተዘጋጀ ትንሽ ጨርቅ ተጠቅልሏል።

3. በባንክ ውስጥ ብዙ ገንዘብ አለኝ።  አሁን ግን ከዚህ መጠን ምንም አልጠቀመኝም።

4. ቤቴ እንደ ቤተ መንግስት ነበር አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ በሁለት አልጋዎች ተኝቻለሁ።

5. ከባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ወደ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል.  አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ ከአንድ ላብራቶሪ ወደ ሌላ በመንቀሳቀስ ጊዜዬን አሳልፋለሁ

6. በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ፊርማ ሰጥቻለሁ ነገርግን በዚህ ጊዜ የሕክምና መዝገቦች የእኔ ፊርማ ናቸው።

7. ፀጉሬን ለመስራት ሰባት ፀጉር አስተካካዮች ነበሩኝ ፣ አሁን ግን - በራሴ ላይ አንድ ፀጉር የለኝም።

8 .በግል ጄት ላይ፣ የትኛውም ቦታ መብረር እችላለሁ፣ አሁን ግን ወደ ሆስፒታል በር ለመራመድ ሁለት እርዳታዎች ያስፈልጉኛል።

9. ምንም እንኳን ብዙ ምግቦች ቢኖሩም, አሁን የእኔ አመጋገብ በቀን ሁለት ክኒን እና ምሽት ላይ ጥቂት የጨው ውሃ ጠብታዎች ናቸው::

10. ይህ ቤት፣ ይህ መኪና፣ ይህ አውሮፕላን፣ ይህ የቤት ዕቃ፣ ይህ ባንክ፣ ብዙ ዝናና ዝና፣ አንዳቸውም አይመጥኑኝምነበር። አሁን ግን ከእነዚህ ውስጥ አንዳቸውም ሊደርሱልኝ እና ሊጠቅሙኝ አልቻሉም፡፡ 

“የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ ..🤔

ኑ እናንብብ

20 Nov, 13:03


#አፈሳ

🔵 “ ወጣቶች እየታፈሱ ነው። የሚታፈሱትም ያለ ፍላጎታቸው ወደ ግዳጅ ሊላኩ ነው ” - የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች

🔴 “ ያገኘናቸው በጣም በርካታ ግኝቶች አሉ ” - ኢሰመኮ


በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ወጣቶች “ በመንግስት ፀጥታ አካላት ” እየታፈሱ መሆኑን፣ በዚህም እንዲህ አይነት ድርጊት በሚፈጸምባቸው ቦታዎች ወጣቶች በነጻነት የመንቀሳቀስ መብታቸው እንደተገደበ ነዋሪዎች በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አቤት ብለዋል።

ነዋሪዎቹ እየተፈጸመ ነው በሚል የተማረሩበት የአፈሳ ድርጊት በይበልጥ እየተካሄደ ያለው በባሌ ሮቤ፣ በሻሽመኔ፣ በአርሲ ነገሌ፣ ባቱ፣ ወንጂ፣ በአዳማ ከተሞችና በዙሪያ ገባው መሆኑም ተመላክቷል።

ነዋሪዎቹ፣ “ ወጣቶች እየታፈሱ ነው። የሚታፈሱትም ያለ ፍላጎታቸው ወደ ግዳጅ ሊላኩ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ ወጣቶቹ ለመዝናናትም ሆነ ለሥራ ሰብሰብ ብለው መንገድ ላይ ሲገኙ ያለምንም ጥያቄ ታፍሰው በመኪና እየተጫኑ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየተወሰዱ ነው ” በማለት ሁነቱን አስረድተዋል።

“ ከዚች ቀደምም አፈሳ ወጣቶች በሚሰበሰቡበት ቦታ ለምሳሌ ዴኤስቲቪ ፣ ፑል ቤት ነበር አሁኑ ግን መንገድ ላይ የሚገኙት ጭምር በገፍ እየተወሰዱ ነው ” ብለዋል።

አንዳንድ ከ15 እስከ 18 ዓመት እድሜ ያላቸው ታዳጊዎችም የተወሰዱበት ሁኔታ አለ ሲሉ ገልጸዋል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ የክልሉ ነዋሪ “ ከሻሸመኔ አንድ የምናውቀው የቤተሰብ ልጅ ተወስዷል። ከሻሸመኔ ተጭነው ወደ ወላይታ ሶዶ አካባቢ መሄዳቸውን ለቤተሰቦቹ ተናግሯል ” ብለዋል።

አንድ የአዳማ ከተማ ነዋሪ ደግሞ ፥ “ ሰው በተለይ ወጣቱ ፈርቷል። ያለውን ወቅታዊ ነገር በመፍራት ስራውን ትቶ በጊዜ ቤት የሚመለስ አለ። ከወጣው እታፈሳለሁ በሚል ስጋት ከቤት የማወጡም አሉ። የጊዜ ገደብ የተቀመጠ ይመስል ውጭ ያለው ሰው 12:00 ስሆን ወደ ቤቱ ለመግባት ይጣደፋል ” ሲል ገልጿል።

“ ሰዎችን ያለምክንያት ይዘው ያስራሉ ሰው ካለው እና 20,000-30,000 መክፈል ከቻለ ይለቃሉ። ያልቻለ ደግሞ ተወስዶ ይሄዳል ” ሲልም አክሏል።

ሰሞኑን አንድ ጓደኛቸው ተይዞ የባንክ ሰራተኛ ነኝ ብሎ ማስረጃ አሳይቶ መለቀቁን ጠቁሟል።

ድርጊቱ በሚፈጸምባቸው አካባቢዎችም ሰዎች ከቤት ለመውጣት፣ ሥራ ለመስራት ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸው አስረድተው፣ “ የሰው ልጅ መብት ግን ለይስሙላ ነው እንዴ የተጻፈው ? መቼ ነው ይህ መብታችን እንኳ የሚከበረው ? ከዚህ ቀደምም አፈሳ ነበር። ያሁኑ ግን ብሷል ” ሲሉ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በርካታ እናቶች ልጆቻቸው ከሚኖሩበት ሰፈር ሳይቀር ተወስደውባቸው በስንት ልመና ከተያዙበት ቦታ ያስወጧቸው አሉ።

በተለይ ወጣቶች ከተያዙ በኃላ የሚወሰዱት ወደ ማቆያ ቦታዎች ነው።

ለቀረበው ቅሬታ ምላሽ ለማግኘት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ ኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ሙከራ ቢያደርግም፣ ስልክ ሆነ የፅሑፍ መልዕክት ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነም።

ከቀናት በፊት የክልሉ መንግሥት “ በክልሉ የጅምላ አፈሳ አለ በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው ” ሲል በፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት በኩል ገልጾ ነበር።

እየተፈጸመ ነው የተባለውን የአፈሳ ድርጊት ሰምቶ እንደሆን በሚል የጠየቅነው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ግን አፈሳ እየተፈጸመ ነው የሚለው ቅሬታው ትክክል መሆኑን ነግሮናል።

ወጣቶችን ወደ ‘ግዳጅ ትሄዳላችሁ’ በሚል በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸመ ነው የተባለውን አፈሰ ኮሚሽኑ ሰምቶ ነበር ? ስንል የጠየቅነው ኢሰመኮ በምላሹ፣ “ አፈሳውን በተመለከተ የሰራነው ብዙ ሥራ አለ።  ፐብሊክ ስቴትመንት ይሰጣል ” ብሏል።

“ ምንድን ነው የሚለውን በሂደት የምናቸው ይሆናል። ግን ጉዳዩ ኦረዲ ብዙ ሥራ ተሰርቶበታል። መግለጫው ሲወጣ ይደርሳችኋል ” ነው ያለው።

አፈሳው ትክክል ነው ? እንዲህ አይነት ድርጊት እየተፈጸመ ነው? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ ኮሚሽኑ፣ “ በጣም ብዙ የኦሮሚያ አካባቢዎች ላይ ገብተን የሰዎች ማቆያዎችን አይተናል ” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

“ ስለዚህ የማኀበራዊ ሚዲያው አሊጌሽን ምንድን ነው? የሚለው እንዳለ ሆኖ በእኛ በኩል ግን ያገኘናቸው በጣም በርካታ ግኝቶች አሉ ” ሲል አረጋግጧል።

ከክልሉ ጋር የተየጋገርንባቸው፣ እያደረገረግን ያለናቸው ጉዳዮችም አሉ” ሲል ኮሚሽኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

ኑ እናንብብ

19 Nov, 14:51


አዲስ አበባ ገና ፓሪስን አልመሰለችም፣ ወደፊት ግን ልትመስልም... ልትበልጥም ትችላለች!

ግን ኢቢሲ ህዝብ በሚሊዮኖች በሚራብበት፣ በሚገደልበት፣ በሚፈናቀልበት እና በሚሰደድበት ወቅት የቁንጅና ውድድር ይመስል ከተማ ለከተማ መልክ ሲያወዳድር የሚውል ሚድያ ሆኖ አረፈው?

ይህ ነው የኢቢሲ 'አዲሱ አቀራረብ' ተብሎ በስፋት ሲተዋወቅ የከረመው?

#ሙያውንአታርክሱት

@EliasMeseret

ኑ እናንብብ

17 Nov, 20:51


ችግር መኖሩን አምኖ "ለማስተካከል እየሰራን ነው" የሚል ሳይሆን በዚህ መልኩ ፈጦ የሚታየውን እውነታ የሚክድ አካሄድ መኖሩ መጪው ግዜ ከባድ የመሆኑ አንድ ማሳያ ነው

ለመሆኑ ፋና ብሮድካስቲንግ ትናንት የህዝብ አፈሳ መረጃ "ሀሰት ነው፣ ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመለሳለን" ብሎ ምነው በዛው ቀረ? 🤔

@EliasMeseret

ኑ እናንብብ

17 Nov, 12:11


ሶስቱ የነፃነት መንገዶች
(ግመል፣አንበሳ፣ህፃን)
ኒቼ

አንተ ታላቅ ነህ ራስህንስ ስለምን ከመንጋዎች መሃል ትፈልገዋለህ? ሰዎች ባሰመሩልህ መስመር ላይስ ስለምን ትኖራለህ? ከልጅነትህ እስካሁን የተነገሩህ እና የተጻፉልህን ትርጓሜዎችን መርመራቸው ፤  አውላላ ሜዳ ላይ የታሰሩ መስሏቸው ከቆሙ በጎች ጋርስ ምን ታደርጋለህ?
መንጋዎች መነጠልን አይፈልጉም፤ በራሳቸውም የሚወስኑት ውሳኔ የለም - እንዲሁ ከመንጋው ጋር በመጓዝ ደህንነታቸውን (ምቾታቸውን)ማስጠበቅ ብቻ ይፈልጋሉ፡፡

መንጋዎች አብረው አንድ ላይ ይሰበሰባሉ፤ ለእነሱ መልካም የሆነውን እንዲያሳያቸውም እረኛውን ይከተሉታል፡ ከመንጋው ተነጥለህ ነጻነትህን ማወጅ ከፈለግኽ መንገድህ ይህ ነው - ግመል - አንበሳ - ህጻን


ግመል - (እውቀትን፣ እውነት እና ጥበብን ፍለጋ)

አንዳንድ ሰዎች እንደ በግ መንጋው ውስጥ አይወሸቁም፤ ሃላፊነትንም ከመሸከም አይሸሹም፤ በሃሩር በረሃ ውስጥ ከባድ ሸክምን ተሸክመው ያልፋሉ፡፡ በመንጋ ቢጓዙም፣ ሸክሙ የየግላቸው ነው፡፡ ማንም ግመል የሌላኛውን ሃላፊነት ሸክም አይጋራም፡፡ የመጀመሪያው የነጻነት መንገድ “ግመል" መሆን ነው፡፡
ግመል መሆን የምንጀምረው እውነታውን ከመጋፈጥ ነው። እውቀትን እና ጥበብን ከእያንዳንዱ ጥጋት መለቃቀም  ጀምር፤ እውነታውንም እወቅ፡፡ ግመል እንዲህ ይጠይቃል፡-

“ምን ያህል ይከብዳል፣ ከባዱና ሊያስደስተኝ የሚችለው ሸክምስ የትኛው ነው?

ታላቁን ሸክም መሸከም ይኖርብናል፤ የግመል መንፈስ ደስታውን የሚያገኘው በጥንካሬው ውስጥ ነው፡፡ ከባዱን ሸክም እንደተሸከመ ወደ በረሃው ይጣደፋል፡፡ ከባድ ሃላፊነቶች ታላቅ እና መልካም ናቸው። ሸክማችን በበዛ ቁጥር ማወቃችን ይጨምራል ግመል- ሕይወት ከእርሱ ላይ የምትወረውራቸውን ነገሮች (ፍርሃት፤ አስፈሪ እውነት፤ ፍቅር ወዘተ) መቻል ይኖርበታል።


አንበሳ - (ማድረግ እችላለሁ)

አዲሱ ማንነት በረሃውን መቆጣጠር እና መምራት ይኖርበታል፤ ነገር ግን ይህን ለማድረግ ከግዙፍ እና አስፈሪ ድራጎን ጋር መጋፈጥ አለበት፡፡ የድራገኑም ስም “ይህን አድርግ/አታድርግ” ይባላል። ድራገኑ እውነተኛ ነጻነትን እንዳታገኝ ይጋርድሃል።

“ይህን አድርግ/አታድርግ” ማህበረሰቡ ያስቀመጠልህ መስመሮች ናቸው፡፡ እንዴትም መሆን እና ምን ማድረግ እንዳለብህም ይነግሩሃል። ይህ ዋናው ጠላትህ ነው፤ ድራጎኑንም ልትገድለውም ይገባሃል።

አንበሳው በድራገኑ ፊት በቀረበ ጊዜ “እችላለሁ፤ አደርገዋለሁም” አለው። ድራገኑም መልሶ “ማንም እንደዚህ አድርጎ አያውቅም፤ አንተ ማነህና ነው?
አንበሳው ነጻነቱን ለማግኘት የበረሃውን ድራጎን ማሸነፍ ይኖርበታል።
አጓራ “እኔ ማንም አይደለሁም፤ እንዲሁ ያለፍቃዴ የተጫነብኝን ስርዓት አልቀበልም”

ኒቼ ይህንን The Sacred No' (ቅዱስ አይ) ይለዋል፡፡ አይነኬ ተብለው በማህበረሰቡ ውስጥ የተቀመጡ ህግ፣ ደንብ ወግ እና ባህሎችን ይቃወማል።ማንም ቢሆን የሚመሩትን የራሱን ስርዓት እና ደንቦች ለራሱ ማውጣት ይኖርበታል፡፡ አይሆንም እያሉ ድራጎኑን በመፋለም ሂደት ውስጥ ደስታ
የለም፤ ሆኖም ነጻነትን የፈለገ የግድ ይህን ማድረግ ይኖርበታል::

ህጻን - (አዲስ ጅማሮ)

አሁን ፍቃድህ ባንተ እጅ ነው᎓᎓ ድራጎኑ ሞቷል፡፡
አንዲት ከተማን አስብ - በዚህች ከተማ ውስጥ ህግ፣ ስርዓት፣ ደንብ እና ወግ የሚባሉ ማሰሪያዎች የሉም፡፡ ሁሉም እንደየራሱ ይኖራል:: ይህቺ ከተማ ማንን ትወክላለች? ምንስ የሚሆንባት ይመስልሃል?
ከተማዋ የህጻናት ከተማ ናት፤ ህግን የማያውቁ ህጻናት እንዲሁ ተፈጥሮ እንዳዘዘቻቸው የሚኖሩ ህጻናት ሞልተውባታል፡፡

ኒቼ ይህንን The Sacred Yes” (ቅዱስ አዎ) ይለዋል፡፡
“ህጻናት ንጹህ እና ዝንጉ ናቸው፡፡ አዲስ ጅማሮ፣ አዲስ ጨዋታ በራሱ የሚሽከረከር ጎማ፣ የተቀደሰ አዎ”

እውነተኛ ነጻነት ያለው በጫወታ ውስጥ ባሉ ህጻናት ላይ ነው ይለናል ኒቼ። ህጻናት ዓለምን ከማንም አልተረከቧትም፡፡ በአግራሞት እና አዲስ ነገርን በመፈለግ ውስጥም ይኖራሉ፡፡ ህጻን በሚያደርጋቸው ተግባራት ውስጥ ትርጉሞችን በራሳቸው ፍቃድ ይፈልጋሉ፡፡ ማንም ሕይወት እንዲህ ናት፣ ዓለም ይህቺ ናት ብሎም የተረጎመላቸው የለም፡፡
ሰው-ማህበረሰቡ የሰጠውን ሁሉንም
ትርጓሜዎች አልቀበልም (The
Sacred No) ካለ በኋላ፣ ሕይወት የምትሰጠውን ትርጉም ይቀበላል (The Sacred Yes) የራሱን ህግ እና ደንቦች ያረቃል፤ የራሱን እሴቶች ይገነባል᎓᎓ ተፈጥሯዊ የሆነውን ማንነቱንም ይኖራል፡፡

በኒቼ ፍልስፍና ሰው ነፃነቱን ከፈለገ ከግመልነት ጀምሮ ህፃን እስኪሆን ድረስ መጓዝ ይኖርበታል።


መፅሀፍ-የፍልስፍና ማዕድ
ደራሲ -ጥበበኛው ሰለሞን

@Zephilosophy
@Zephilosophy

ኑ እናንብብ

20 Oct, 14:25


ነፃ ፍቃድ

ነጻ ፍቃድ የሚለውን ሃረግ በአጭሩ ስንፈታው የመምረጥ ነጻነት ማለት ይሆናል፡፡ የሰው ልጅ ነጻ ኾኖ ምርጫዎቹን ይመርጣል የሚለው ሃሳብ ለዘመናት የሰው ልጆችን ሲያከራክር ቆይቷል። ኃይማኖተኛው ፈላስፋ ቅዱስ አውግስቲን የፈለግነውን የመምረጥ ነጻ ፍቃድ አለን፤ ኾኖም ለምርጫዎቻችን ዋጋ እንከፍላለን ይለናል፡፡ አለማትን የፈጠረው እግዚአብሔር ከፊትህ ማር እና ሬት፣ ጽድቅን እና ኩነኔን አስቀምጦልሃል፤ መርጦም የመብላት ነጻነቱ ያንተ ነው᎓᎓ ነገር ግን የኃጢአትህንም፣ የጽድቅህንም ዋጋ ከሰማይ ቤት ትቀበላለህ። አንዳንዶች የኃይማኖተኞችን የነጻ ፍቃድ አስተምህሮ ምኑን ነጻ ፍቃድ ሆነ? ይላሉ፡፡ ሰው ይህን ካደረግክ በእሳት ትቃጠላለህ እያሉ ማስፈራራት እንዴትስ ነጻነት ተሰጥቶናል ለማለት ያስችለናል? ሆኖም እኔም አንተም ለምርጫዎቻችን ሰማይ ቤት ሳንሄድም ዋጋ እንደምንከፍል እናውቃለን፡፡ ሁሌም ቢሆን የቀን ተቀን ውሎህ ላይ  መልካም ውሳኔዎችን ባለመወሰንህ፣ ስቃይህን በምድር ላይ እንድትቀበል  ትሆናለህ፡፡ ወንጀል ከሰራህ የሚያስርህ አካል አለ። ሰውነትህን ካልተንከባከብከው የእርጅና እና የበሽታ መጫወቻ ትሆናለህ፤ ዛሬ ላይ ነጻ ሆነህ የወስንካቸው ውሳኔዎች ነገን ሊያጨልሙት ወይንም ሊያፈኩት ይችላሉ፡፡

ሌላኛው ከነጻ ፍቃድ የለንም ባዮች የሚነሳው ሃሳብ- እድል እና እጣ ፈንታ ናቸው። የሰው ልጅ እጣፈንታው ቀድሞውኑ በአምላኩ የተጻፈ እና የታወቀ ከሆነ እንዴት ነጻ ነው ሊባል ይቻላል? ሁሉን አዋቂ አምላክ ቀድሞ ያወቀውን ዓለም የምንኖር ከሆነ፣ የኛ ኑሮ ከአንድ ድራማ ውስጥ ካለ ገጸ ባህሪ በምን ይለያል? እኛም እርሱም የድራማውን መጨረሻ መቀየር አንችልም፤ የቱስ ጋ ነው ነጻ የመምረጥ ፍቃድ ያለን? የክርስቲያን ፈላስፋው ቻርለስ ሃርትሾረን እኔ እና አንተ የእጣፈንታችን ጸሐፊ ነን፤ ሁሉን አዋቂ የሆነው አምላክ ለኛው ብሎ ከካኽሊነቱ ዝቅ አለ፤ ነጋችንንም እንዳያውቅ ኾነ የሚለውን ሃሳብ ያራምዳል። እንዲህ ከኾነ እና እጣፈንታችንንም ሁሉን አዋቂ የሆነው አንድ አምላክ ካላወቀው፣ ነጻ ፍቃዳችን በእጣፈንታ ይወሰናል የሚለው ሃሳብ ውድቅ ይሆናል፡፡ እናም እኔ እና አንተ የሰማንያም፣ የአርባም ቀን እድል የለንም፡፡ እጣፈንታችንንም ራሳችን መጻፍ እንችላለን ወደሚል መደምደሚያ ያደርሰናል፡፡

እድልስ? እድል ውስጥ የፈጣሪ እጅ የለበትም እኔ እና አንተ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ በመኪና ያልተገጨነው በእድል ምክንያት ነው፡፡(ምናልባትም የመኪና አደጋ ደርሶብህም ሊሆን ይችላል) እናም ብዙ ነገሮቻችን ላይ እድል እጁን ያስገባል፡፡ እዚህ ላይ የምናነሳው ሌላኛው መሟገቻ ሃሳብ እሳተ ጎመራ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ድርቅ እና ሌሎች አደጋዎች መነሻቸው ተፈጥሮ መሆኑን ነው፤ እናስ የተፈጥሮ ክፋት ከእኔ ውሳኔዎች እና ነጻ ፍቃድ ጋር ምን ያገናኘዋል? እኔ የምመርጣቸው ወይም የምተዋቸው አይነት የስህተት አልያም የልክነት ጠባያት አይደሉም፡፡ ውሸታም መሆንን ልመርጥ እችላለሁ፤ ሆኖም በመብረቅ መመታት የእኔ ምርጫ አይደለም፤ ከነጻ ፍቃዴም ጋር አይገናኝም።

የስነ መለኮት የጥናት ዘርፍ ውስጥ የሚካተተው ቲዮዲስ የሚባል ክፍል አለ።ቲዮዶስ በምድር ላይ ስለምን ክፋቶች ተፈጠሩ የሚለውን ያብራራልናል ሰዎች ሲፈጠሩ የተሰጠቻቸው ነፍስ ሙሉ አይደለችም፤  የዘላለሙን ዓለም ፍጽምናም ለመቀላቀል እንደ ወርቅ ተፈትና ማለፍ ይጠበቅባታል፡፡ እናም መጥፎ ከፊቷ ይቀርብላታል፡፡ መልካሙን መልካም እና ከመረጠች የዘላለም ሕይወትን ታገኛለች፤ አይ ካለችም ዘላለማዊ ሞት ያገኛታል፡፡ እናም ፈጣሪያችን ነፍስያችንን ይፈትን ዘንድ ክፋትን እና መልካምነትን መሳ ለመሳ አድርጎ ፈጠረ። ሆኖም ይሄ ሃሳብ የእንስሳትን መታመም እና መጥፎ ሁኔታ ውስጥ መግባትን አያብራራልንም፤ እነሱስ ዘላለማዊ ያልሆነች ነፍስን ይዘው ስለምን ይሰቃያሉ? እዚህ ላይ ሌላ ጥያቄ ልናነሳ የምንችለው፣ ህጻናትስ ምንም ነፍስ ያላወቁ እና ክፉ እና ደግን የማይለዩ ብላቴናዎችስ ለምን ይሰቃያሉ? ሌላ ሃሳብ ለመጨመር ያህል፣ አንዳንዶች በስቃይ ውስጥ አልፈው ለፈጣሪያቸውም ታማኝ ሆነው ያልፋሉ፤ ሌሎች በምቾትም ውስጥ ሆነው በመልካምነት ውስጥ ለፈጣሪያቸው ታማኝ ሆነው ያልፋሉ፤ የማንኛቸውስ ነፍስ የበለጠ ዋጋ አላት? ሁለቱም መልካምሰዎች፣ ሁለቱም ለዘላለማዊ ሽልማት የተገቡ ቢሆንም፤ አንደኛው በስቃይ ሲያልፍ ሌላኛው በምቾት ውስጥ አልፏል፡፡

ዛሬ ጠዋት ላይ አምስት ደቂቃን አርፍደህ መነሳትህ አዋዋልህን በእጅጉ ይለውጠዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ምርጫህ፣ የጓደኛ ምርጫህ፣ የምግብ ምርጫህ፣ የትዳር አጋር ምርጫህ እና ሌሎቹም ነጻ ሆነህ የመረጥካቸው ምርጫዎችህ ሕይወትህን እንዳሻቸው ይጠመዝዙታል። የኔ ምርጫ ልክ ይኹን አይኹን ካላወቅኹኝ እንዴት ነጻ ሁኜ እና ፈቅጄ መረጥኩት እላለኹ? ማንስ የእድሉን መጨረሻ እያወቀ መጥፎን መንገድ ይመርጣል? ሕይወቴ መጨረሻቸውን ሳላውቅ በመረጥኳቸው ምርጫዎቼ እና ከኔ ቁጥጥር ውጪ በሆኑ ሁነቶች ይመራል። እና እኔ በፍቃዴ ወደ ምፈልገው መዳረሻ እሾፍራለው ለማለት እችላለሁን?

መፅሀፍ - የፍልስፍና ማዕድ
ፀሀፊ- ጥበበኛው ሰለሞን

@Zephilosophy
@Zephilosophy

ኑ እናንብብ

08 Oct, 17:31


አምባገነኖች ጉልበት አላቸው። የጉልበታቸው ምንጭ ህዝብ እንዴት መተባበር እንዳለበት አለማወቁ ነው።

ህዝብ መተባበር ሲችል ጉልበተኝነታቸው ያበቃል።


@Tfanos

ኑ እናንብብ

08 Oct, 07:46


ለፍልስፍና አፍቃሪዎች ድንቅ ቻናል
👇👇👇
@Zephilosophy
ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ

በዚህ ቻናል ከተለያዪ የአለም ዳርቻዎች የተነሱ የታላላቅ ፈላስፋዎች አስተሳሰቦች እና ፍልስፍናዎች ይቀርባሉ።ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ፤ ከሰሜን እሰከ ደቡብ የአለምን የአስተሳሰብ ኮምፓስ የቀየሩ ፈላስፋዎች እና ሃሳቦቻቸው ከየመፅሀፉ እየተጨለፉ ለናንተ ይቀርባሉ። ከሶቅራጥስ እስከ ኒቼ ፤ ከቡድሃ እስከ ኦሾ ፤ ከማርክስ እስከ ሌኒን አለም ላይ የማይፋቅ አሻራዎቻቸውን ያሳረፋ ሰዎች ፤ ከክርስትና እስከ ቡዲሂዝም ፣ከእስልምና እስከ ሂንዲይዝም ፣ከሶሻሊስት እስከ ካፒታሊስት በዘመናት ውስጥ የተፈጠሩ ሀይማኖቶች ፣ስርዓቶች ርዕዮተ ዓለሞች ሁሉ ይዳሰሳሉ። ለዓለም ያስገኙት ሞራላዊና መንፈሳዊ ትሩፋቶች ይወዳሳሉ። ታሪካዊ ህፀፆቻው ደግሞ ያለምህረት ይተቻሉ ፣ይወቀሳሉ።

ማህበረሰቡ የሚሳሳላቸው ባህሎቹ እና እምነቶቹ በነፃነት ይጠየቃሉ ፣ይመረመራሉ ይፈተናሉ። እንደ ጣት ቁስል የተፈሩ እውነቶች መሀረባቸው ይገለጣል። እንደ ማህበረሰብ በጉያችን የጋረድናቸው እባጮች የግንባር ስጋ ይሆናሉ።ከግለሰብ እስከ ቡድን ፤ከሀይማኖት እስከ ርዕዮተ -ዓለም
፤ ከኋለቀር ባህሎች እስከ ዘመናዊ ስልጣኔዎች ያለምንም ፍርሃት በግላጭ ይሞገታሉ፣ ይመረመራሉ፣ይጠየቃሉ ውስጣቸው የተደበቀው እውነት እስኪገለጥ ድረስ በአውድማው ላይ መንሽ እየተፈለገ ፍሬው ከገለባ ይለያል።
መንሻችን የሰላ አምክንዮዊ አእምሮ፣ የሰከነ የሞራል ልዕልና እና ንፁህ ሰዋዊ ህሊና ናቸው።

Join
👇👇👇👇
@Zephilosophy

ኑ እናንብብ

04 Oct, 10:22


Dirty minded always see...

ኑ እናንብብ

30 Sep, 11:49


(አሁን Sarcastic የሩሲያ ስነ-ጽሑፍ ታሪክ አገኘውና ወደእኛ አመጣውት  በእንግሊዘኛው ደግሞ ይበልጥ ይጥማል)


አንድ ሩሲያዊ አዛውንትን እንዲህ ብዬ ጠየቅኳቸው፦"መንግስት ለምን ሶስቴ አሰረህ?"

ሽማግሌው፡- ፓርቲውን ስቀላቀል ወጣት ነበርኩና ከፓርቲው ኮሚሽነር ጋር አብሬ ስለ ፓርቲው ታሪክና መርሆዎች እየተረዳው ነበር። ነገር ግን በክሬምሊን በኩል ስናልፍ ጥያቄ የፈጠረብኝን ነገር ጠየቁኩት፦ "የክሬምሊን ግንብ ከፍ ያለ ነው፤ ለምንድነው እንዲህ ከፍ ያለው?"

ኮሚሽነሩም፦ "አህያዎች ዘለው እንዳይገቡ የተሰራ ግንብ ነው" ብሎ መለሰልኝ። ስለታጠረው ግንብ ስላልገባኝ ደግሜ ጠየቅኩት "ከውጭ የሚኖሩት አህዮች ወደ ውስጥ እንዳይገቡ ነው ወይስ ከውስጥ ያሉት ወደ ውጭ እንዳይወጡ?" በዚህ ድፍረቴ  አሰሩኝ እስታሊን እስኪሞት ድረስ አልተፈታውም ነበር።

ከእስር ሲለቁኝ መንግስት በመቀየሩ ደስ ብሎኝ የአዲሱን ጠቅላይ ሚነስተር የክሩሺቭን ፎቶ ጎን የእስታሊንን ፎቶ አስቀምጥኩ። የፓርቲው ኮሚሽነር የስታሊንን ፎቶ ሲመለከቱ በዚህ ድርጊት ተገርመው ጠየቁኝ፦
"አሁንም የዛን አህያ ፎቶ እንደ ጀብዱ ትሰቅላላችሁ?"

ኮሚሽነሩ ስለየትኛው አህያ እንደሚያወሩ ግራ ስለገባኝ ወደ ሁለቱም ፎቶግራፍ እያፈጠጥኩ መልሼ ጠየቀኳቸው "ሁለት ነው የሚታዩኝ ስለየትኛው እንደሚያወሩ አልገባኝም?" በዚህ ቃሌም በድጋሚ ወደ ዘብጥያ ወረድኩ። አዲስ የተባለው ጠ/ሚኒስተር ክሮትሾቭም እስኪሞት ድረስ አልተፈታውም።

በቀደም የልጅ ልጄን ልደት እያከበርኩ ነበር። የፓርቲው ኮሚሽነር ደውሎ እንዲህ አሉኝ፦ "የባለፈው ፓርቲ የመጨረሻ ስብሰባ ላይ ለምን አልመጣህም?"

እኔም በመገረም፦
"የመጨረሻችሁ እንደሆነ ባውቅ ኖሮ ከነሙሉ ቤተሰቤ መጥቼ አከበር ነበር!" አልኩት። ለሶስተኛ ጊዜ አሰሩኝ
😕

ኑ እናንብብ

24 Sep, 17:11


The best spritual books

ኑ እናንብብ

23 Sep, 10:32


The power of descpline
@nuenanbib

ኑ እናንብብ

22 Sep, 06:23


ሁሌ እንደማደርገው አይቼ ላልፈው ነበር...!

"በነፃነት ያሻን ቦታ መሄድ" የሚለውን ሳይ ግን...

አሁን ላይ ስንቱ ወገን ነው ጠግቦ በልቶ እያደረ ያለው? ስንቱ ነው በነፃነት እያሰበ እና እየተናገረ ያለው? ማነው ከአዲስ አበባ ውጪ ንቅንቅ ብሎ ያሻው ቦታ የሚሄድ? ስንቱ ነው ለፍቶ ጥሮ ያገኘውን ጥሪት በልማት ስም እየተቀማ እና እየፈረሰበት ያለ?

ይሄ አላማ ከስንት አመት በኋላ ይሳካ ይሆን?

መሬት ላይ ካለው ችግር ይልቅ እንዲህ አይነት የተስፈኛ አካሄድ እጅጉን ያስፈራል፣ የባሰው ችግር ገና ወደፊት እንደሆነም ያመላክታል።

#Ethiopia

@EliasMeseret

ኑ እናንብብ

21 Sep, 17:13


የብቸኝነትና የባዶነትን ስሜት መጋፈጥ

በውስጣቸው ከራሳቸው ጋር ብቻቸውን የሆኑ፣ አዕምሮና ልባቸው ከብቸኝነት ስቃይ የፀዱ ሰዎች እውነተኞች ናቸው

አዝናኝና አስከፊ ነገር በሞላበት ዓለም ሁሉም ሰው ተሳታፊ ከመሆን ይልቅ ተመልካች መሆኑ አያስገርምምን? አብዛኞቻችን ትንሽ ነፃ ጊዜ ስናገኝ አንድ የሚያስደስተን ነገር እንፈልጋለን፡፡ ከተማ ውስጥ ከሆንን  ቴሌቪዥን ወይም ሞባይል እንከፍታለን ወይም ወሬ እንጀምራለን፤ አለዚያም መፅሀፍ ወይ መፅሄት እናነሳለን፡፡ የመደነቅ የመዝናናት፣ ራሳችንን የመርሳት የማያቋርጥ ፍላጐት አለን፣ ብቸኝነትን፣ ጓደኛ ማጣትን፣ ሳይረበሹ መቆየትን እንፈራለን፡፡ ሳናወራ ወይም ሳንዘፍን በፀጥታ በመስክ ወይም በጫካ ውስጥ እየተራመድን ስለ ራሳችንና በውስጣችን ስላለው ነገር የምናስተውል ጥቂቶቻችን ነን፡፡ አብዛኞቻችን እንዲህ ማድረግ የሚሳነን ስልቹዎች ስለሆንን ነው፤ በመማር ወይም በማስተማር፣ በቤት ጣጣ ወይም በስራ ተጠምደናል፡፡ ስለዚህም ነፃ ጊዜ ስናገኝ በቀላሉ ወይም በከባዱ መደነቅን እንፈልጋለን፡፡ እናወራለን ወይም ወደፊልም ቤት እንሄዳለን - ወይ ወደ አንዱ ሃይማኖት እንዞራለን። ሃይማኖትም አንደኛው ዓይነት ከስልቹነት የማምለጫ መንገድ ሆኗል፡፡

ይህን ሁሉ ተገንዝባችሁ እንደሆነ አላውቅም:: አብዛኞቹ ሰዎች በአንድ ነገር ተጠምደዋል - የተወሰኑ ቃላትን በመደጋገም፣ በዚህ ወይም በዚያ ጉዳይ በመስጋት - ምክንያቱም ከራሳቸው ጋር ብቻቸው መሆንን ስለፈሩ። የሚረብሻችሁ ነገር ሳይኖር ብቻችሁን ለመሆን ብትሞክሩ ምን ያህል ከራሳችሁ መውጣት እንደምትፈልጉና ማንነታችሁን ለመርሳት እንደምትሹ ትገነዘባላችሁ። ለዛም ነው ይህ ግዙፍ የደስታ መዋቅር፣ ፈጣን ረብሻ ስልጣኔ የምንለው ነገር አካል የሆነው:: አስተዋዮች ከሆናችሁ የዓለም ህዝቦች ይበልጥ እየተረበሹ እንደመጡ፣ ውስብስብና ዓለማዊ እየሆኑ እንደሄዱ ትመለከታላችሁ። የደስታው መብዛት፣ አዲስ የሚወጡ ፊልሞች መብዛት፣ የጋዜጦች በስፖርታዊ ጉዳዮች መሙላት - እነዚህ ሁሉ ያለማቋረጥ መደሰትን እንደምንፈልግ ያመለክታሉ፡፡ ውስጣዊ ባዶነት ስላለብን ግንኙነቶቻችንና ማህበራዊ ለውጦቻችን ከገዛ ራሳችን ለማምለጥ እንደ መሳሪያ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ብቸኝነት የወረራቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ አስተውላችኋልን? ከብቸኝነታቸን ለማምለጥ ተሽቀርቅረን ፣ ግብዣ ወዳለበት እንሔዳለን፣ ቴሌቪዥን እናያለን፣ ሞባይል እንነካካለን፤ እናወራለን ወዘተ፡፡

ብቸኝነት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? አንዳንዶቻችሁ ቃሉን ባታውቁም ስሜቱን በደንብ ታውቁት ይሆናል። ብቻችሁን ሽርሽር ስትወጡ ወይም ከሞባይል ስትላቀቁ ወይ ከሰው ጋር መነጋገር ስታቆሙ ይህ ሁሉ ነገር እንዴት አሰልችቷችሁ እንደነበር ትገነዘባላችሁ፡፡ ይህን ስሜት በደንብ ታውቁታላችሁ፣ ነገር ግን ለምን እንደሰለቻችሁ አታውቁም፤ ምን ብላችሁ ጠይቃችሁም አታውቁም:: ያን ስልቹነት በጥቂቱ ብትመረምሩት መንስኤው ብቸኝነት እንደሆነ ትገነዘባላችሁ፡፡ አብረን መሆን የምንፈልገው፣ መዝናናት የምንፈልገው፣ የሚረብሹንን መምህራን ወይም ምርጥ ፊልሞች የምንሻው ከብቸኝነታችን ለማምለጥ በማሰብ ነው፡፡ ውስጣዊ ብቸኝነት ሲሰማን የህይወት ተመልካች እንሆናለን ፤ ይህን ብቸኝነታችንን ተገንዝበን አልፈነው ስንሄድ ብቻ ተሳታፊዎች መሆን እንችላለን፡፡

ብዙ ሰዎች እንዴት በብቸኝነት መኖር እንደሚችሉ ስለማያውቁ ትዳር ይይዙና ሌላ አይነት ማህበራዊ ግንኙነት ይመሰርታሉ፡፡ ይህ ሲባል ግን አንድ ሰው ብቻውን መኖር አለበት አይደለም። መወደድ ስለፈለጋችሁ ብቻ የምታገቡ ከሆነ ወይም ሰልችቷችሁ ስራችሁን ራሳችሁን እንደ መርሻ ከተጠቀማችሁበት መላ ህይወታችሁ ረብሻን ፈላጊ እንደሆነ ትገነዘባላችሁ፡፡ ከዚህ ልዩ የብቸኝነት ፍርሃት በላይ የሚሆኑ ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ ነገር ግን ከዚህ ፍርሃት በላይ ሲኮን እውነተኛው ሀብት ይገኛልና ሁሉም ሰው ፍርሃቱን መብለጥ አለበት፡፡

በብቸኝነትና ብቻን በመሆን መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ፡፡ አንዳንድ ወጣት ተማሪዎች ብቸኝነት ምን እንደሆነ አያውቁ ይሆናል፤ በዕድሜ የገፉት ግን ይህን ጠንቅቀው ያውቃሉ። ብቸንነት ጨርሶ  የመቆረጥ፣ ያለምንም ምክንያት በድንገት የመፍራት ስሜት ነው። አእምሮ የሚጠጋው ነገር ሲያጣ፤ የባዶነቱን ስሜት የሚያስወግድለት ነገር ሲያጣ ይህ ፍርሃት ይሰማዋል። ይህ ብቸኝነት ነው፡፡

ብቻን መሆን - ግን ፍፁም የተለየ ነገር ነው፤ በብቸኝነት ውስጥ አልፋችሁ ስትገነዘቡት የሚመጣ የነፃነት ሁኔታ ነው። በዚያ የብቻ መሆን ሁኔታ ውስጥ ስትሆኑ በስነ - ልቡና ረገድ የማንም ጥገኛ አትሆኑም፡፡ ምክንያቱም ደስታን፣ ምቾትን መፈለጋችሁ ያቆማል፡፡ ይህን ጊዜ ብቻ አዕምሮ ሙሉ በሙሉ ብቻውን ይሆናል፤ ፈጣሪ ይሆናል፡፡

የብቸኝነትን፣ የባዶነትን ልዩ ስሜት የመጋፈጡን፣ ያለ መፍራቱን፣ ስሜቱ ሲመጣ ሞባይል ያለመጠቀሙን፤ በስራ ያለመጠመዱን ወይ ወደሲኒማ ቤት ያለመሮጡን፤ ከዚህ ይልቅ ስሜቱን የመመልከቱን፣ የመገንዘቡን ነገር መፍጠር ያለበት ትምህርት ነው:: ስጋትን የማያውቅ ወይም ያላወቀ ሰው የለም፡፡ ይህንን ስሜት በወሲብ፣ በሀይማኖት፣ በስራ፣ በመጠጥ፣ ግጥሞች በመፃፍ ወይም በልባችን የተማርናቸውን ጥቂት ቃላት በመደጋገም ወዘተ ለማምለጥ ስለምንሞክር ፈፅሞ አንገነዘበውም።

ስለዚህም የብቸኝነት ህመም ሲመጣባችሁ ትታችሁት ከመሮጥ ይልቅ ተጋፈጡት፡፡ ትታችሁት ከሮጣችሁ ፈፅሞ አትገነዘቡትም፤ ሁልጊዜ በየጥጋጥጉ ቆሞ ይጠብቃችኋል። ስሜቱን ተገንዝባችሁ አልፋችሁት ብትሄዱ ግን ማምለጡ፣ መዝናናቱ አስፈላጊ እንዳልሆነ - ትረዳላችሁ፤ አዕምሯችሁ የማይበላሽ፣ የማይነጥፍ ብልፅግናን ይጎናፀፋል፡፡ 

ይህ ሁሉ የትምህርት አካል ነው፡፡ በትምህርት ቤት ፈተና ለማለፍ ብቻ የተወሰኑ ትምህርቶችን የምትማሩ ከሆነ ትምህርት ራሱ ፣ ከብቸኝነት የማምለጫ መንገድ ይሆናል፡፡ ትንሽ ብታስቡበት ይገባችኋል።

በውስጣቸው ከራሳቸው ጋር ብቻቸውን የሆኑ፣ አዕምሮና ልባቸው ከብቸኝነት ስቃይ የፀዳ ሰዎች እውነተኞች ናቸው- ምክንያቱም እውነታውን ከራሳቸው ይረዳሉ፣ ጊዜ የማይወስነውን መቀበል ይችላሉ፡፡

ክሪሽና ሙርቲ

@Zephilosophy
@Zephilosophy

ኑ እናንብብ

16 Sep, 15:07


መላውን ዓለም ከመጨበጥ ይልቅ ራስን መጨበጥ የተሻለ ነው
ኦሾ

ሰው ሲወለድ እንደ ዘር ሆኖ ነው - እንደ አንድ እምቅ አቅም፡፡ ሲወለድ ልከኛ ሆኖ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ልዩ ነው - ምክንያቱም በመላው ህልውና ውስጥ ሰው ብቻ ነው አንድ አቅም ሆኖ የሚወለደው፤ ሌሎች እንስሳት ልከኛ ሆነው ነው የሚወለዱት፡፡

አንድ ውሻ ሲወለድ ውሻ ሆኖ ነውና መላ ህይወቱንም እንዲያ ሆኖ ይኖራል። አንድ አንበሳ ሲወለድ አንበሳ ሆኖ ነው፡፡ ሰው ሲወለድ ግን ሰው ሆኖ አይደለም፡፡ ሰው ሲወለድ እንደ ዘር ሆኖ ነው። ሰው ሊሆንም ላይሆንም ይችላል። ሰው የወደፊት ተስፋ አለው! ሌሎች እንስሳት ግን ተስፋ የላቸውም፡፡ ሁሉም እንስሳት ሲወለዱ በደመነፍስ ፍፁም ሆነው ነው፡፡ ሰው ብቸኛው ፍፁም ያልሆነ እንስሳ ነው። ስለዚህም በሰው ላይ እድገት፣ ዝግመተ - ለውጥ ይቻላል።

ትምህርት በእቅምና በልከኝነት መካከል ያለ ድልድይ ነው። ትምህርት በዘር መልክ ራሳችሁን እንድትሆኑ ያግዛችኋል፡፡ በተራ ትምህርት ቤቶች፣ በኮሌጆችና በዩኒቨርስቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው ትምህርት አይደለም። በእነዚህ ተቋማት የምታገኙት ትምህርት ጥሩ ስራ፣ ጥሩ ገንዘብ እንድታገኙ የሚያደርጋችሁ ብቻ ነው:: እውነተኛ ትምህርት አይደለም፤ ህይወትን አይሰጣችሁም። በቃ የኑሮዋችሁን ደረጃ ከፍ ቢያደርገው ነው፤ ነገር ግን የተሻለ ኑሮ የተሻለ ህይወት አይደለም፤ ሁለቱ አንድ አይደሉም።

በዓለም የሚሰጠው ትምህርት ተብዬ ነገር ዳቦ እንድታገኙ ብቻ የሚያዘጋጃችሁ ነው። ኢየሱስ እንዳለው «ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም::>> ዩኒቨርሲቲዎቻችሁ ደግሞ ይህን ነው እያደረጉ ያሉት - በተሻለ፣ በቀለለ፣ በተመቸ፣ ጥረት፣ ድካም በሌለበት መንገድ ዳቦ እንድታገኙ ያግዛችኋል። ስራቸው በሙሉ እናንተን ዳቦና ቅቤ እንድታገኙ ማዘጋጀት ነው፡፡ ይህ አይነቱ ትምህርት በጣም፣ በጣም ኋላቀር ነው:: ለህይወት አያዘጋጃችሁም፡፡

ስለዚህም ብዙ ሮቦቶች ሲረማመዱ ታያላችሁ:: እንደ ተላላኪዎች፣ የጣቢያ ተቆጣጣሪዎች፣ ዋና ሰብሳቢዎች ብቃት አላቸው:: ፍፁማን ናቸው፣ ጥበበኞች ናቸው:: በጥልቀት ብትመለከቷቸው ግን ለማኞች እንጂ ሌላ ምንም እንዳልሆኑ ትረዳላችሁ፡፡ የህይወትን እንዲት ቅንጣት እንኳን አልቀመሱም፡፡ ህይወት ምን እንደሆነ፣ ፍቅር ምን እንደሆነ፣ ብርሃን ምን እንደሆነ አያውቁም፡፡ ስለ እግዚአብሄር ምንም አያውቁም፣ ህልውናን አልቀመሱም፣ እንዴት መዝፈን፣ መደነስ፣ መደሰት እንዳለባቸው አያውቁም:: የህይወትን ሰዋሰው የማያውቁ መሀይማን ናቸው። አዎ፣ ከሌሎች የበለጠ ያገኛሉ፤ ከሌሎች የበለጠ ብልጣ ብልጦች ናቸው፤ በስኬት መሰላል ከፍ ብለው ይወጣሉ - በውስጣቸው ግን ባዶ፣ ምስኪኖች ናቸው፡፡

ትምህርት ውስጣዊ ብልፅግናን ያጐናፅፋል፡፡ የበለጠ መረዳ መስጠት በጣም ኋላቀር የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ነው። ኋላ ቀር ነው ያልኩት በፍርሃት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው፤ ካልተማርኩ በህይወት መቆየት አልችልም፣ በሚለው አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው። ሗላቀር ነው ያልኩት በውስጡ ነውጥን ስላዘለ ነው፤ ውድድርን ያስተምራችሗል፣ ምኞታም ያደርጋችኋል። ሌላ ምንም ሳይሆን ሰዎች እርስ በርስ የሚጠላሉበት የውድድር ዓለም ለመፍጠር የሚደረግ ዝግጅት ነው።

ስለዚህም ዓለም የእብዶች መኖሪያ ሆናለች። በዚህ ሁኔታ ፍቅር ሊወጣ አልቻለም። አንዱ  የሌላኛውን ጉሮሮ በሚበጥስበት በዚህ ነውጠኛ፣ ምኞታም የውድድር ዓለም ውስጥ እንዴት ፍቅር ሊታይ ይችላል? ሗላ ቀር ነው ያልኩት «በደንብ ካልተማርኩ፣ በቂ ከለላ ካላገኘው፣ ደህና መረጃ ካልያዝኩ በህይወት ፈተና ውስጥ አሸናፊ አልሆን ይሆናል>> በሚል ፍራቻ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው። ህይወትን እንደ ትግል ብቻ ነው የሚመለከታት፡፡

እኔ ትምህርትን የማየው ህይወትን እንደ ትግል ሳይሆን እንደ ደስታ ሲቀርፅ ነው፡፡ ህይወት ውድድር ብቻ መሆን የለባትም፣ ደስታ ጭምር እንጂ፡፡ ትምህርት በዓለም ላይ ከሚገኙ ዘፈን፣ ዳንስ፣ ቅኔ፣ ሙዚቃ፣ ስዕል፤ ዛፎች፣ አዕዋፋት፣ ሰማይ፤ ፀሃይ፣ ጨረቃ እና ሌሎች ነገሮች በሙሉ ሊያዋህዳችሁ ይገባል፡፡

ትምህርት ራሳችሁን እንድትሆኑ ሊያዘጋጃችሁ ይገባል። አሁን ግን አስመሳዮች እንድትሆኑ እያዘጋጃችሁ ነው፤ ሌሎችን እንዴት መምሰል እንዳለባችሁ እያስተማራችሁ ነው፡፡ ይህ ትምህርት ማሳት ነው፡፡ ትክክለኛ ትምህርት ራሳችሁን በእውነተኛ መንገድ እንዴት እንደምትሆኑ ያስተምራችኋል። እናንተ የተለያችሁ ናችሁ። እናተን የሚመስል ማንም የለም ፡ ወደፊትም አይኖርም። ይህ እግዚአብሄር ያጐናፀፋችሁ ታላቅ በረከት ነው። ይህ የእናንተ ክብር ነው! ልዩ መሆን ነው፡፡ አስመሳይ አትሁኑ፤ የካርቦን ቅጂዎች አትሁኑ።

እናንተ ትምህርት የምትሉት ነገር ግን ይህን እያደረገ ነው፡፡ የካርቦን ቅጂዎችን ይፈጥራል፤ እውነተኛ መልካችሁን ያጠፋል። <<ትምህርት>> የሚለው ቃል ሁለት ትርጉሞች አሉት፤ ሁለቱም ደግሞ ውብ ናቸው። አንደኛው ትርጉሙ ተግባር ላይ ባይውልም በደንብ ይታወቃል- አንድ ነገር ከውስጣችሁ ማውጣት። <<ትምህርት» ማለት በውስጥ ያለን ማውጣት፣ ውሀን ከጉድጓድ እንደ ማውጣት አቅምን በተግባር ማውጣት ነው።

ይህ ግን አልተተገበረም፡፡ ከዚህ ይልቅ ነገሮች ወደ ውስጥ እንዲገቡ እንጂ እንዲወጡ አልተደረገም። ህብረተሰብ እና ታሪክ፣ ሳይንስ እና ሂሳብ ወደ ውስጣችሁ ያንቆረቁርላችኋል። እናም ፓሮቶች ትሆናላችሁ። ልክ እንደ ኮምፒዩተር ይጉሰጉሱባችኋል:: የእናንተ የትምህርት ተቋማት ነገሮች በጭንቅላቶቻችሁ ውስጥ የሚታጨቁባቸው ስፍራዎች ናቸው፡፡

እውነተኛ ትምህርት በውስጣችሁ የተደበቀውን (እግዚአብሔር በውስጣችሁ እንደ ሃብት ያስቀመጠውን) አውጥቶ፣ ገልጦ አንፀባራቂ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል፡፡

ትምህርት ሌላም ትርጉም አለው:: ትምህርት (Education) የሚለው ቃል የመጣው Educare ከሚለው ቃል ነው:: ትርጉሙም ከጨለማ ወደ ብርሃን ማምጣት እንደማለት ነው፡፡ ከጨለማ ወደ ብርሃን ማምጣት በጣም አስፈላጊ ትርጉም አለው፡፡ ዮፓኒሻዶች እንዲህ ይላሉ «ጌታችን ሆይ፣ ከሃሰት ወደ እውነት ምራን፡፡ ጌታችን ሆይ፣ ከሞት ወደ ህይወት ምራን፡፡ ጌታችን ሆይ ከጨለማ ወደ ብርሃን ምራን፡፡» ይህ ነው «የትምህርት» ትክክለኛ ትርጉም፡- ከጨለማ ወደ ብርሃን።

ሰው ግን በጨለማ፣ ባለመንቃት ውስጥ እየኖረ ነው:: ሆኖም በብርሃን ምሉዕ መሆን ይቻላል፡፡ ነበልባሉ እዚያ አለ፡፡ ይሁንና መንበልበል፣ ወደ ውጭ መውጣት አለበት፡፡ ንቃት እዚያ አለ፤ ይሁን እንጂ መቀስቀስ አለበት:: ሁሉም ነገር ተሰጥቷችኋል! ስትወለዱ ይዛችሁት መጥታችኋል፡፡ ሰብአዊ አካል ስላለን ብቻ ሰው ነን ማለቱ ስህተት ነው፡፡ ለዘመናት ለብዙ መሳሳቶች መንስኤ የሆነው ይህ አስተሳሰብ ነው፡፡

ሰው ሲወለድ እንደ አንድ እድል፣ ሁኔታ ሆኖ ነው። ይህን የተጠቀሙበት ደግሞ እጅግ ጥቂቶች ብቻ ናቸው - ኢየሱስ፣ ቡድሀ፣ መሐመድ፣ ባሃውዲን። እውን ሰው የሆኑት እጅግ ጥቂቶች ናቸው- በብርሀን ሲመሉ የቀረ ጨለማ አይኖርም፣ በነፍስ ውስጥ የሚተርፍ አለመንቃት አይኖርም- ሁሉም ነገር ብርሃን ሲሆን፣ እናንተ ንቃትን ስትሆኑ...

ንቃት፣ ንቃት ብቻ፣ ንፁህ ንቃት... ይህ ያለው ብቻ ምሉዕ ይሆናል። ይሄን ጊዜ ህይወት ቡራኬ ትሆናለች።

ትምህርት ከጨለማ ወደ ብርሃን ይወስዳችኋል።

@Zephilosophy
@Zephilosophy