አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀 @orthodoxzelalemawit Channel on Telegram

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

@orthodoxzelalemawit


ምሳሌ 9
⁹ ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጽድቅንም አስተምረው፥ እውቀትንም ያበዛል።
¹⁰ የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው።
¹¹ ዘመንህ በእኔ ይበዛልና፥ የሕይወትህም ዕድሜ ይጨመርልሃልና።
¹² ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥ ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ።

በዚህ ቻናል ከመፅሀፍት📖 የተቀነጨቡ ፅሁፎች ያገኛሉ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀 (Amharic)

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀 አዲስ ቤት በአባትና እናት ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጽድቅንም አስተምረው፥ እውቀትንም ያበዛል። የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው። ዘመንህ በእኔ ይበዛልና፥ የሕይወትህም ዕድሜ ይጨመርልሃልና። ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥ ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ። በዚህ ቻናል ከመፅሀፍት📖 የተቀነጨቡ ፅሁፎች ያገኛሉ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

08 Feb, 19:14


የፍቅር ጥጉ ለተፈቀረው ወዳጅ ራስን መስዋዕት አድርጎ መቅረቡ ነው   ::

ባለትዳሮች (ወደትዳር ) ምትገቡ አስቡባት ከጌታ የተቀበልናት ሕይወት ይህችኛይቱ ናት 🤗🤗🤗

በቸር እደሩልኝ🙏🙏🙏
https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

07 Feb, 06:00


አሐቲ ድንግል
ማርያም ማለት ምን ማለት ነው?

ማርያም ማለት፦
እግዝእት:- እመቤት ማለት ነው የዓለሙን ንጉስ በመውለዷ ከፈጣሪ በታች የፍጥረት ንግስት ሆናለችና፤

ጸጋ ዘተውኅበት ለኩሉ ዓለም፦ ለዓለሙ ሁሉ የተሰጠች ጸጋ ማለት ነው። ለአበው በተስፋ የሰጣቸው ሲሆን ለእኛ ደግሞ ከመስቀሉ ሥር እናት ትሁናችሁ ብሎ ሰጥቶናልና። (ዮሐ ፲፱፤፳፮) ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ንግሲቲቱ በቀኝህ ትቆማለች የሚለውን የዳዊት መዝሙር ሲተረጉም In becoming the mother of creator she become the Mistress of all creation (የፈጣሪ እናት በሆነች ጊዜ የፍጥረታት ሁሉ ንግስት እመቤት ሆናለችና በማለት ተርጉሞታል። (መዝ 44፤9)

ተስፋ ማለት ነው፦ ለአዳም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ካለው ጀምሮ መድኃኒቴን የምትወልጅልኝ ልጄ እያለ ተስፋ አድርጓት በልቦናው መዝገብነት ይዟት የኖረ ስንቁ ናት። አበውም ድንግል ማርያምን መቼ ፀሐይ ክርስቶስን ወልዳልን ከቁረ መርገም ድነን አይተነው እያሉ ተስፋ አድርገዋት ነበር። ተስፋቸው ክርስቶስም ከእርስዋ ተወልዶ ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ገብተዋል። ለዚህ ምስክር የሚሆነን አረጋዊ ስምዖን "ጌታ ሆይ አገልጋይህን ዛሬ ታሰናብተዋለህ፥ አቤቱ በሰላም እንዳዘዝክ አይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና በህዝብ ፊት ሁሉ ያዘጋጀኸውን ለአሕዛብ ብርሃንን ትገልጽ ዘንድ፥ ለእስራኤልም ክብርን" በማለት ተስፋውን አይቶ አርፏል። (ሉቃ 2፥29)

የባሕር ከርቤ (Myrrh of the sea) ማለት ነው። ይህ ከርቤ እጅግ ውድ ዋጋ ያለው ከዘይት ጋር ተጨምሮ በጠበብተ ኦሪት ተቀምሞ ለንዋያተ ቅድሳት ማክበሪያ የታዘዘ ሽቱ ነው። ሙሴ ደብተራ ኦሪቱን በኦሪት መቅደሱ ያሉትን ሁሉ በዚህ ሽቱ እንዲቀባ ታዟል። ሽቱ ያረፈባቸውን የነካ ሁሉ እንደሚቀደስ እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮታል። ባሕር የተባለ ይህ ዓለም ሲሆን እመቤታችንም ከእርስዋ ስጋን ነስቶ ክርስቶስ ተብሎ ስሙ እንደ ዘይት ተዋህዶን ክርስቲያን ተብለን እንድንጣፍጥ የድኅነት መሳሪያ የመዓዛ መንፈሳዊ ምንጭ ናትና የባህር ሽቱ ትባላለች።

ሽቱ ያረፈበትን የነካ ሁሉ እንደሚቀደስ በልጇ ስም አምነው ተጠምቀው በእምነት የሚቀርብ ሁሉ ይጣፍጣልና ይላሉ አበው!

የባሕር ኮከብ (Star of the seas) ማለት ነው። ባሕር የተባለ ይህ ዓለም ነው፥ በባሕር የሚበላም የማይበላም ደግሞ ክፉም ፍጥረት እንዳለ በዚህ ዓለምም አማኒም ከሓዲም መናፍቅም ጻድቅም ኃጥእም ይኖራልና፥ ዳግመኛም ባሕር ከሁከት አይርቅም ይች ዓለምም ከሁከት አትርቅምና፥ በባህር ላይ ሲጓዙ በመርከብ ላይ ሆነው የንጋት ኮከብን አብነት አድርገው ከተጓዙ ካሰቡት ይደረሳል። ሰብአ ሰገልን ኮከብ እየመራ ቤተልሔም እንዳደረሳቸው ማለት ነው። እንዲሁም ሁሉ እመቤታችን በዚህ ዓለም የክህደት የኃጢአት ሞገድ እንዳያጠፋን የተረፍንባት መርከባችን ናት።

ብርህት (Illuminated) ማለት ነው። ብርሃኗ ከፀሐይ ይበልጣል፤ መለወጥ የሌለባት የድኅነት በር ናት ውበቷም በፍፁም ክብርና ሞገስ የተሸለመ ነው፤ እውነት በእውነት የመና መሶብ ነች። ጽድልት መባሏ ነውርና ነቀፋ የሌለበት የእግዚአብሔር እናት በመሆኗ ነው።

አሐቲ ፍቅርት፦ ብቻዋን የምትወደድ (Beloved One) ማለት ነው። ንጉስ ውበትሽን ወዷልና ተብሎ የተዘመረላት እግዚአብሔር መዓዛ ድንግልናዋን ወዶ ከእርሷ ሰው እስኪሆን ድረስ፥ ፍጥረትን ሁሉ በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብቅሎ የሚመግብ ጌታ ጡቶቿን ጠብቶ እስከማደግ ድረስ ደርሶ ብቻዋን በእግዚአብሔር የተወደደች ናትና።

የባሕር ምንጭ (Drop of the sea) ማለት ነው። እመቤታችን በዚህ ዓለም በሦስት ዋና ዋና የድኅነት ምንጭ ሆናለችና። የጥምቀት፥ የቁርባን፥ የቅዳሴ ናቸው። ይህም ማለት ከጎኑ የፈሰሰው ውሃ፥ ከጎኑ የፈሰሰው ደም ከእርሷ ባህሪ የተገኘ ነውና ጌታ የተጠመቀውም ከእርሷ በነሳው ስጋ ነው የምንበላው ቅዱስ ስጋው የምንጠጣው ክቡር ደሙ ከእርሷ የነሳው ነውና የቁርባን ምንጭ ትባላለች።

ዳግመኛም ማርያም ማለት ልዕልት ማለት ነው።


አሐቲ ድንግል በአባ ገብረኪዳን ግርማ ገጽ 257 የተወሰደ
https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

06 Feb, 12:52


" ልቤ ያውቀዋል "

ልቤ ያውቀዋል ያደረክልኝ ነገር
የሰራህልኝን ስራ
መዳኒዓለም አወጣህኝ ከመከራ
በቃል ጉልበት አይወራ (2)


https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

05 Feb, 19:14


እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ሰው ሆኗልና ኑ ይህን ድንቅ እዩ

ስለ ተገለጠልን ምሥጢር ምስጋና አቅርቡ ሰው የማይሆን ሰው ሆኗዋልና ቃል ተዋሕዷልና ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ ዘመን የማይቆጠረለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት የማይታወቅ ተገለጠ የማይታይ ታየ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ  በርግጥ ሰው ሆነ ትላንት የነበረው ዛሬም ያለው መቼም የሚኖረው ኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግድለት እና እናመሰግነው ዘንድ አንድ ባሕርይ ነው ።

ቅድስት ሆይ ለምኝልን አዕምሮውን ጥበቡን(ማስተዋሉን) ሳይብን አሳድሪብን🤲🤲🤲


የረቡዕ ውዳሴ ማርያም

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

04 Feb, 18:46


https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

04 Feb, 18:46


https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

04 Feb, 12:15


እዚህ ላይ ጥያቄ ሃሳብ ያላቹ ካላቹ መድረኩ ክፍት ነው ኮመንቷ ላይ አስፍሩ
ከሊቃውንት አንደበት ደሞ ወደ አመሻሽ አካባቢ አንዳንድ ቪዲዮዎችን አስቀምጥላቹሃለው ቸር አምሹልኝ🤗🤗🤗

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

04 Feb, 12:07


ዛሬ ካጋጠመኝ ጥቂት ነገር ልበላችሁ!

የመድሃኒዓለም ንግስ የነበረበት ደብር ሄጄ ታቦቱ ዑደት በሚያረግበት ሰአት የመድረክ መሪው(የደብሩ መምህር) የኦሪትን ህግ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ፅላት በማንሳት እሱ ታቦት ነው ያለን ብለው አሉ !😔 በጥቂቱ አስተካክዬ ያኔ ታቦትን የሰጠ አምላክ አሁን እነዚን ጣዖት ነው ጣሉ ይላል ወይ ብለው ለማለት ፈልገው ከሆነ በሚለው ሊሉ ይሆን ብዬ አስተካክዬ ለመረዳት ፈልጌ ነበረ ከጉባኤው በሃላ ግን ወርጄ ሳናግራቸው ጭራሽ በታቦተ ፅዮንም ይሰዋል ያለን የብሉይኪዳን ታቦት ነው ሃዲስ ኪዳን ላይ መች ቀርፆ ሰጠ አላሉኝም ጌታ ይቅር ይበለን😔 🤲🤲🤲 ይሄ ትልቅ ስህተት ነው የጌታን ሞት እና ትንሳኤን አለማመን ነው ይሰመርበት

የብሉይ ኪዳን ታቦት የለንም!!!

መምህራን እዚህ ካላችሁ እባካችሁ ማይክ ስለተያዘ ልብስ ስለተለበሰ የመጣልን ሁሉ በአውደ ምህረት አይበጠረቅም ለምዕመናን ህሊና ተጠንቀቁ ተጨነቁ እንጂ እስከመቼ መምህር በሚል ስም እና ልብስ ተሸፍኖ ይኖራል መምህሬ ጌታ ሚፈልገው ልብስህን አይደለም እሱ ሚፈልገው አንተን እና የምታስተምረውን ምዕመን ነው ጌታ ሚጨነቀው ስለምትሰበስበው ገንዘብ እና ስለምታሳንፀው ህንፃ አይደለም ገንዘቡ ስለሆኑ ምዕመናን እና በደሙ ያነፃቸው ህንፃ ሥላሴ የሆኑትን ምዕመናንን እንጂ ወዴት እየሄድን ነው ጌታ አይነ ልቡናችንን ያብራልን😢


በጣም ደሞ ያናደደኝ ይሄን ጥያቄ ቁሜ ስጠይቅ መምህሩን ምን የህል የሚከተሉ ምዕመናን እዳሉ ያወኩት እኔን እደመናፍቅ አይተው ዝም ሊያስብሉ ሲሞክሩ እና የመምህሩን የተሳሳተ ትምህርት እንደነሱ ይዤ እድሄድ ግድ ሲሉ ያሳዝናል ከልብ ከልብ

ስለምዕመናን የማይጨነቅ ካህን ዲያቆን መምህር እራሱ ምዕመን የጌታ አይደለም ጌታ ይሄንን ነው ያለው 👇

“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።”
ሐዋርያት 20፥28

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

03 Feb, 19:51


እኔነታችን ጌታ ነው ❤️

“በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤" 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥19-20

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

02 Feb, 08:15


መልካም የጌታ ቀን 🤗🤗🤗

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

02 Feb, 08:13


#በቅዳሴያችን⛪️

በቅዳሴያችን የምትሰየመው
ምስጢራትን የምትፈጽመው
የክህነት ምንጭ ለሐዋርያት
አንተ እኮነህ ሊቀ ካህናት

#አዝ ===============

ካህኑ ሲቀድስ አንተን የሚማልል
በንጉሣችን ፊት ቆሞ ፅኑ የሚል
"ክርስቶስ" በተዋህዶ መቅደስ የተሰየምከው
አድርጎህ ነው አንተን የእርሱ ሊቀ ካህን (2)

#አዝ ===============

ባርክና ፈትተው አንጻና ቀድሰው
ህብስቱንም ስጋህ ወይኑን ደምህ አርገው
"አማኑኤል" እያለ የሚጠራህ በቅዳሴው ሰዓት
ተረድቶ ነው ያንተን ሊቀ ካህንነት (2)

#አዝ ===============

በመስቀል ምልክት ቄሱ ባርክ የሚልህ
በኑዛዜ እግዚአብሔር ይፍታህ የሚልልህ
"መድኃኔዓለም" ያሬድ በመዝሙሩ አጉልቶ ሚያሳይህ
ሊቀ ካህናችን ክርስቶስ አንተነህ (2)

#አዝ ===============

የሊቀ ካህንነት ግብሩን ሳይጠይቁ
መቅደስ ሳይኖራቸው መስዋዕትን ሳያውቁ
"ኢየሱስ" እኛ ጋር ነው ብለው የሚያታልሉትን
መልስልንና ይወቁት ግብርህን (2)

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

01 Feb, 20:02


እውነት ነው ያለ (በጉ)ስጋ በዓሉ በዓል አይመስልም።

“ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።” (ዮሐ 1፥29)

አቤቱ እንደ ቸርነትህ ወደ አማናዊው ሕይወትም ወደ ሆነው ማዕድህ አቅርበን አንድም አድርገን አዋህደንም።

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

29 Jan, 14:19


https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

29 Jan, 10:38


"የህይወት እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፤ እርገትሽ ሳይሆን ወደ መቃብር መውረድሽ ይገርመኛል።

የብርሃን እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትወጂኛለሽን? ብየ አልጠይቅሽም ፍቅርን የወለድሽ አንቺ ለዓለሙ ሁሉ ፍቅርሽ የበዛ ነውና፤ አትናፍቂኝምን? ብየም አልጠይቅሽም ዘወትር እኔን ለመጠበቅ ከጎኔ እንደማትለይ አውቃለሁኝና፤ ሆኖም እመቤቴ ሆይ፦ እንደ ቶማስ አይሽ ዘንድ በእጅጉ እጓጓለሁ የቶማስ ንፅህናና ቅድስና ግን የለኝም እንደ ዮሃንስ ከጎንሽ ልሆን እጓጓለሁ የዮሃንስ ንፅህና እና ፀጋ ግን የለኝም።

እናቴ ሆይ፦ እንደ ኤልሳዕ የልቦናዬ አይን በርቶ ሰማያዊ ክብርሽን ላይ አልተቻለኝምና አዝናለሁ ኤልሳዕ በፀሎት ሃይል የግያዝን አይን እንዳበራ አንቺም የልቡና አይኔን ታበሪልኝ ዘንድ የእናትነት ፍቅርሽንም አይቼ እረጋጋ ዘንድ ሃይልሽን በእኔ ላይ አበርቺ፡፡

ድንግል ሆይ፦ ይህን የምል የእምነት ማረጋገጫ ፈልጌ አይደለም በልጅሽ መሰረትነት የታነፅኩኝ በልጅሽ ስምም የተጠመቅኩኝ ነኝና፤ ነገር ግን ስለምትናፍቂኝ ይህን አልኩኝ ስለዚህም ነይ ነይ እምየ ማርያም እያልኩኝ እንደ እናቶቼም እለምንሻለሁ፡፡ የብርሃን ልብስሽን ለብሰሽ ነይ የክብር አክሊልሽን ደፍተሽ ነይ አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ነይ እናይሽ ዘንድ ነይ፡፡"🤲🏻🤲🏻


ፃድቃኔ ማርያም

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

29 Jan, 04:52


https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

29 Jan, 04:52


❖ እንኳን ለእመቤታችን ንጽሕት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

➦​  አስተርዮ _ ቃሉ የግእዝ ቃል ሲሆን
ትርጉሙም ፦ መታየት ወይም መገለጥ ማለት ነው፡፡

” አስተርእዮ ማርያም “
አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል።
ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ተንሥኢ ወንዒ”  የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መኃ ፪፥፲) ብሏታል።
ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ
ቅዱስ ዳዊት “ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር” መዝ.፹፮፥፫ እግዚአብሔር ማህጸንሽን ከተማ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የኖረብሽ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው የተደረገው ነገር ዕጹብ ድንቅ ነው እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆና ማረፏ ይደንቃል። ታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት ቅዱስ ያሬድ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን «ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት ገልጾታል።


➦​  ጥር 21 ቀን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይቶ በደመና ተነጥቃ ወደ ገነት በመግባት በሰማይና በምድር የተሰጣትን ፀጋና ክብር የገለፀችበት እለት ስለሆነ በዓሉም አስተርዮ ማሪያም ይባላል።

❖ የድንግል ማሪያም ጥበቃ ምልጃዋ አይለያችሁ።

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

28 Jan, 06:05


አቤቱ ጌታዬ ሆይ የአን† መለኮታዊ ውበት በእኔ ውጥ ይታይብኝ ዘንድ ስጠኝ አለኝ የምለው ውበቴ አንተ ነህና ለስዎች ሁሉ ወንጌል( መልካም ዜና) እሆናቸው ዘንድ ስጠኝ። በልቡናው አንተን የሚናፍቀውም ሁሉ እኔ አይቶ ደስ ይሰኝ ዘንድ አንተን መምስልን ስጠኝ ከሁሉ ግን ነብሴ ፊትህን መናፈቅ አንተን መውደድንም ስጣት አንተን መውደድ ሕይወቷ ከአንተ መራቅ ሞቷ ነውና።

በቸር ዋሉልኝ 🤗🤗
https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

27 Jan, 08:09


በህይወታችሁ አንድ የምትወዱትን ፃድቅ አባት (ሰማዕታት፣ፃድቃን) በደንብ አጥብቃችሁ ያዙዋቸው ታሪካቸውን አንብቡ ስለነሱም አስቡ እነሱንም ተከተሉ ወደክርስቶስ መርተው ይወስዷቹሃል እና

ከርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ያገኘዋት ደገኛ ምክር

እግዚአብሔር አምላክ የነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን በረከት ይስጣቸው ሚስጢሩን ጥበብን ማስተዋሉን ያድላቸው🤲🤲 ፀልዩላቸው የድካማቸውን ፍሬ እዲያገኙ🥰🥰🥰

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

27 Jan, 08:02


ህሊናዬን በፍቅሩ ከያዘኝ ሐዋርያ መሃል ቅዱስ ጳውሎስ ነው የሱን ነገር ሳስበው በጣምም ነው ምደነቀው

ቅዱስ ጳውሎስ ሆይ የሐጢአት ፍቅር ከውስጤ ተነቅሎ የክርስቶስ ፍቅር  በልቤ ላይ ይነድ ዘንድ ትዕቢቴን ጥዬ ራሴን የክርስቶስ ባሪያ አደርግ ዘንድ አትለየኝ አበርታን የሃይማኖትን መንገድ ፍፃሜ አገኝ ዘንድ እኔ ደካማውን ምራኝ 🤲🤲 አሜን🙏

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

25 Jan, 13:14


መዝሙር 73
²⁷ እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፤

²⁸ ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው


https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

25 Jan, 06:23


https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

25 Jan, 06:22


https://youtu.be/sYdNxLlRxJU?si=iNNELD46macp84Am


https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ👆

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

24 Jan, 13:18


እደዚህ 👆youtube  መልክ ምንለቃቸውን እየተከታተላችሁ ነው  ይቀጥል ? ወይስ ተቀይሮ ወደ Audio ይለቀቅ ምርጫችሁ ምንድነው በኮመንት 👇አሳውቁን ሚመቻችሁን🤗

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

24 Jan, 13:13


"ብዙ ህዝባችን የሚጠፋው እውቀት ከማጣት ነው!! "

ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

20 Jan, 09:15


“የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፦ የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው።” ዮሐንስ 2፥3

https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

19 Jan, 19:22


ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ! ሁሉ በዮርዳኖስ ቢሰበሰብ በደል አስጨንቆት ነው ፣ አንተ ግን ወደ ዮርዳኖስ የሄድኸው ጽድቅን ልትፈጽም ነው❤️

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

19 Jan, 19:06


ተወዳጆች ዛሬ በበዓለ ጥምቀቱ ያሳለፍናቸው ሚስጢራት ቢያንስ 3 ነገሮች ናቸው

፩ ሚስጢር የመገለጥ ቀን ( የሥላሴ ልዩ ሶስትነት በጎላ የተረዳንበት ) ማቴ ➌ ÷➊➏-➊➐

፪ የምስክርነት ቀን ( የወልድን በተለየ አካሉ ግብሩ ሥጋ ለብሶ በዚህች ምድር ሲመላለስ ብናየውም ሩቅ ብዕሲ ሳይሆን እውነተኛ የባሕሪይ አምላክ መሆኑን የእግዚአብሔር አብ የዘለዓለም ልጁ መሆኑን የተነገረበት ነው) ማቴ ➌ ÷ ➊➐

፫ ትሕትናን እና ፍቅርን በግልፅ ያየንበትም ዕለት ናት ማቴ ➌ ÷ ➊➊-➊➐

ታድያ ግን ከዚ ቀድሞ ትንሽ ከፍ ብሎ 👆እደፃፍኩላችሁ የቤተክርስትያን በዓላት ቀን ወቶላቸው ጉባኤ ተዘርግቶላቸው እዲከበሩ ቀኖና የሰራችው ቤተክርስትያን በዓሉን እደበዓል እድናስበው ብቻ ሳይሆን በዋናኝነት በዓሉን እንድንኖረው ነው ! አሁን ግን ዋና ጉዳዩ ጭራሽኑ እየተዘነጋ መቷል ክርስትያኖች ስለ ሚከበሩ በዓሎች ምንነት በመረዳት ያንን ወደመመስከር (ወደመተግበር) ከማደግ ይልቅ የበዓሉ ሆይሆይታ እየሳበን በዓሉን በሥጋዊ ነገሮች ብቻ ተደስቶ ከማለፍ የዘለለ ሆኖ አይታይም ተወዳጆች የጥምቀትም እለት እደመሆኑ ሚስጢር ከፍቅር ና ትህትና የታየበት እለት በመሆኑ ስብከትም (ምስክርነትም) የተሰጠ እደመሆኑ በዚህ ሚስጢር ብዙ ወንድም እህቶችን ወደክርስቶስ መርከብ ልንስብበት የሚገባ እለት ነበረ ቢቻል! ካልተቻለ ደሞ እራስን በማፅናት(በማበርታት) ክርስቶስ በሚወደው መንገድ ከክርስቶስ ጋር ማኖርን የምንኖርበት እለት ነበረች ጌታ በዓላትን አክባሪዎች ብቻ ሳይሆን የባዓሉን አክብሮ በዛ በዓል ታሪክ ውስጥ የራስን ታሪክ እየሰሩ ኗሪ ያርገን 🤲🤲🤲🤲

“ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።”
ያዕቆብ 1፥22


“ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም።”
  ዕብራውያን 4፥2

ነገም ቃና ዘገሊላ ነው ይታሰብበት 😉🤭
ስለሎሚ አላወራሁም😁

ተጨማሪ ሃሳብ ካላችሁ ኮመንቷ ላይ አስፍሩልኝ

በቸር እደሩልኝ🤗🤗🤗
https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

19 Jan, 19:06


https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

19 Jan, 04:37


"ብዙ መሠዊያዎች" ነገር ግን አንድ መሠዊያ
***
ብዙ አብያተ ክርስቲያናት (ሕንጻዎች እና የአጥቢያ ምዕመናን) ቢኖሩም የቤተ ክርስቲያን የማኅበሯ ፍጻሜ ግን አንዲት ናት። በየ አብያተ ክርስቲያናቱ 'ብዙ መሠዊዎች' ቢኖሩም ክርስቶስ ራሱን የሠዋበት ሰማያዊ መሠዊያ አንድ ነው። ብዙ ሲመስሉን አንድ ናቸው፤ በሁሉም ላይ የሚቀርበው አንዱ ክርስቶስ ነውና። ብዙ ቦታዎች ላይ በተለያዩ ጊዜያት ቅዱስ ቁርባን ይፈተታል፤ ነገር ግን በሁሉም ያለመከፋፈል የሚፈተተው ያው አንዱ የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም ነው። ይህ ራሷ ከሆነ ከክርስቶስ አካሉ ለሆነች ለቤተ ክርስቲያን የተሰጣት ከጊዜ እና ቦታ ከፍ ያለ መንፈሳዊ አንድነት ነው።
ይህን የተረዳ እና ለሰዎች ማስረዳት የቻለ እውነተኛውን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት ተረድቷል። የቅዱስ ቁርባን የአንድነት ሥርዓትም የዚህ መሠረት ነው።
***
"በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤" የሚል ድንቅ የአብ ድምፅ ለተሰማበት፣ ወልድ በለበሰው ሥጋ ተጠምቆ ውሆችን ለቀደሰበት እና መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በክርስቶስ ላይ ሲኖር ለታየበት የቅድስት ሥላሴ የመገለጥ በዓል (በዓለ አስተርእዮ) እንኳን በሠላም አደረሰን!

(በረከት አዝመራው)

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

17 Jan, 18:43


የትኛይቱ_ከተራ_ውስጥ_ናችሁ?

ጥር ዐሥር ቀን የበዓለ ጥምቀት መግቢያ በር ነው። አጽር ቅጽር ይላሏ ከተራ ነውና። ከተራ በአንድ በኩል የወራጅ ውኃን ማቆም፥ መሰብሰብ፥ በአንድ ቦታ ማድረግን የሚያመለከት ሲኾን፥ በሌላ በኩል የእግዚአብሔር ታቦታትን ካህናትና ምእመናን ከትረው (ከበው) መጓዝን ያመለክታል። ይህን ስናስብ ክርስትና አጽር ቅጽር ያለው፥ የተለካ ሕግና ሥርዓት ያለው ርቱዕ ሃይማኖት መኾኑን በከተራ በኩል ልብ ይሏል። ልክ የዓሣ መኖሪያው ውኃ እንደ ኾነ ኹሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆችም ሕይወት ውኃ በኾነው የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮና ሕግ ላይ የተመሠረተ ነው። በእርሷ ሕግና ሥርዓት ውስጥ የማይኖር ከእርሷ ከተራ ውጭ ነው የሚኾነው። የውኃ ዳር አካባቢ የእግዚአብሔር ማደሪያ የኾኑ ታቦታቱ በካህና አማካኝነት የሚጓዙት በውኃ ዳር አካባቢ እንድንተከል ለማድረግ ነው። ይኸውም በቃለ እግዚአብሔር መሠረት ላይ መተከል ነው። በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአስተምህሮ ውኃ አካባቢ እንድንጸና ሊያመላክቱን ውኃ ወዳለበት እንደሚወስዱን አድርገን ብንረዳ እንዴት ያምር! በእርግጥም እንዲያ ነውና።

በወንጌል ትምህርት ያልተከተረ ልቡና ኹል ጊዜም ቢኾን ሲነዋወጽና፥ ወጪ ገቢው ሲያቆሳስለው ይኖራልና። ወንጌል ርቱዕ ሕግ ነው። በጽኑዓን ልቡና ይከተራል። ንጹሐን ቅዱሳን በሕይወታቸው ውስጥ ወንጌልን ከትረው ከዚህ ዓለም ርካሽ አስተሳሰብ ተጠብቀው ኖረዋል። እንግዲያውስ ኹል ጊዜ በዓለ ከተራን ሳናሳልፍ ልንኖርበት ይገባናል። ይኸውም በወንጌል ከተራ ልቡናችንን ሰብስበን መኖር ነው። ሰሎሞን በመኃልየ መኃልይ "የታተመች፣ የዘጋች፣ የተቈለፈች" ገነት ብሎ የሚላት የእኛን ሰውነት ጭምር ነው። በንጽሕናና ሕግጋተ እግዚአብሔርን በመፈጸም አሸብርቃና አምራ ገነት የመሰለች ሰውነት ይሏል የእውነተኛ ክርስቲያን ሰውነት ናት። ተንቀሳቃሽ ከተራዎች ይሏል በቅድስና የቅዱሳንን ሕይወት እየጠጣች የተከተረች የክርስቲያኖች ሰውነት ናት።

ተአምራት ገድላት የእኛን ሰውነት ከተራነት የሚያጸኑ አዕማዳት እንጂ ባልተከተሩ ሰዎች (ኦርቶዶክሳዊ አረዳድ የሌላቸው) የሚፈርሱ ተራ ድርሰቶች አይደሉም። በክርስቶስ አምላክነት አምነን በቅድስና ከተራ ውስጥ ስንኾን እኛ ራሱ ገድልና ተአምር ወደ መኾን ልንሻገር የምንችል መኾናችንን ልብ ልንል ይገባናል። የተአምራትና ገድላት አንዱም ዓላማ ከውጭ ማስቀረት ሳይኾን እኛን ራሱ ማሳተፍና ማለምለም ነውና። የቅዱሳን አበው ርቱዕ የኾነ የሃይማኖት አረዳድ ሲኖረን ያኔ ተንቀሳቃሽ ተአምራትና ገድላት ይሏል እኛው ነን። ለዓሣ በየብስ መኖር ባዕድ እንደ ኾኑ ኹሉ ለክርስቲያን ከተአምራትና ከገድላት መንፈስ ውጭ ኾኖ መኖር ባዕድ ነው። ቅዱሳን አባቶቻችን የከተሩልንን የተአምራትና የገድላትን ከተራ ትተን አሳቾች በግል ስሜታቸው ወደ ሠሯት፥ "የማትከበር ከተራ" እንዳንጓዝ እንጠንቀቅ። የመቅበዝበዛችን ዋና ምክንያትስ የኃጢአትን ጣዕም በውስጣችን ጥልቅ አጣፍጠን መክተራችን አይደለምን? እንግዲህ ከክፉ የኃጢአትና ያለማስተዋል ከተራ እንውጣና ወደ እውነተኛው የከተራ አከባበር እንምጣ!

ከተራ በልቡናችን ውስጥ በንጽሕና መከተሩን የምንረዳው ከአከባበር መንፈሳችን ነው። በዓሉ የጌታችን ጥምቀት መግቢያ ኾኖ ሳለ የዘፈንና የጭፈራ መግቢያ፥ ወዲህም የስካር መግቢያ ካደረግነው ከተራችን ወዴት አለ? ጌታችን በወንጌል በበሩ የማይገባ ሌባና ወንበዴ ነው ማለቱን ልብ እንበል። ወደ ጥምቀት አበው በሠሩልን የከተራ አከባበር በር ካልገባን የጌታ ቃል በእኛ የሚፈጸም ወደ መኾን የሚመጣ መኾኑን ልብ ልንል ይገባል። ሌብነትና ውንብድና ግን በእውነቱ መግቢያ የኾነ አይመስላችሁምን? እስኪ የየሪሳችንን የከተራ አከባበር እንመርምረው! በዓሉን ስናከብረው ምንድን ነው የሚሰማን? ለምንስ ነው የምንሄደው? ምንስ ነው የሚያስደስተን? ዓለምስ በአከባበር ሂደታችን በእርግጥም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አማናዊ አከባበር እያየች ነውን? እኛ ሌላ አከባበር ፈጥረን ያሰናከልናቸውን ስንት ናቸው? ታቦታቱ ምድርን እየባረኩ ሲዞሩ ያልተነካና ያልተቀደሰ ሐሳብ ያለን ብዙ አይደለንምን? እንግዲያውስ በየግላችን ከሠራናቸው የኃጢአት ከተራዎች እንውጣ። እግዚአብሔር አብ እርሱን ስሙት ባለው ቃል መሠረት ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስን "እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ" ሲል እንስማው። በፍቅር ከተራ ውስጥ ኹሌም ጸንተን ለመኖር እንትጋ! እግዚአብሔር በከተራት አማናዊት ከተራ ውስጥ ልቡናችን ይገባ ዘንድ ኃይሉን ያድለን፤ መልካም በዓለ ከተራ🤗!

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

16 Jan, 18:25


ለባሪያህ መከናወንን አድርግለት🤲

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

16 Jan, 18:18


"የተጠራነው እንድንቀደስ ነው"

ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

15 Jan, 19:18


አጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ
( ጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም )


በዚህች ቀን ቅድስት ሥላሴ በኃጢያት የተገነባውን የሰናኦር ግንብ ያፈረሱበት ነው:: ሙሉ ታሪኩ ዘፍጥረት 11 ፤1 ላይ ይገኛል

ተወዳጆች ከዚህ ታሪክ ላይ ልናስተውለው ቢገባ ብዬ ያሰብኳትን 1 -2 ነገር ልበላችሁ

1:- እግዚአብሔርን ያሳዘነ በሰናኦር የተገነባ ህንፃ

ልክ እደታሪኩ እኛ የሥላሴ ህንፃ ሁነን ሳለ ብዙ እግዚአብሔርን የሚያሳዝኑ የሃጢአት ግንቦችን በልባችን ላይ ገንብተን ይሆን ?

2 ዘፍጥረት 11÷4 እንዲህም፦ ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስማችንን እናስጠራው አሉ።

በጣም የገረመቺኝ ነገር " ስማችንን እናስጠራው አሉ " ምትለዋ ናት ብዙዎቻችን ልክ እደዚ ነና ስማችንን ስለማስጠራት ስማችን ከፍ ከፍ እንዲል ብዙ ነገሮችን እንሰራለን እንደክማለን ግን በግልባጩ ስንቶቻችን ነን እግዚአብሔር በምሰራው ደስ ይለዋል ወይ ? የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ነው ወይ ? ብለን ምናስበው 🤔 እግዚአብሔር ስማችን ስለተጠራ ስላልተጠራ ጉዳይ የለውም ጉዳዩ ስማችንን እናስጠራ ብለን በምንሰራው ስራ ከፈቃዱ ወተናል ወይ ነው የሐጢአት ግንብን ገንብታቹሃል ወይ ነው ?

የሰናኦርን ግንብ የሰሩ ስማችን ይጠራል ያሉ ግን መጨረሻቸው እንዲህ ሆኖ ቀርቷል

ዘፍጥረት 11
⁵ እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።
⁷ ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።
⁸ እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ።
⁹ ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፥ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።


የበዓላት መከበር ራስን ለመፈተሽነው

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

15 Jan, 09:51


ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አንተን ደስ ከማያሰኝህ ሀሳብ እንለይ ዘንድ መለየትን ስጠን🤲 አሜን!🙏

ቅዳሴ እግዚዕ

“ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤” 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥8
ሰናይ ቀን🤗🤗


https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

14 Jan, 05:58


በፖለቲካው ዐውድ ብዙ የተባለለት የ66ቱ አብዮት፣ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቂ ውይይት አልተደረገበትም። ቤተ ክርስቲያን በሂደቱ ስለገጠማት ነገር ከውጪ ተነገራት እንጂ፣ በራሷ መነጽር ኵነቱንም ሆነ ታሪኩን ገምግማለች ማለት አይቻልም። ስለዚህ እንደ ኤማሁስ ቤተ ክርስቲያንም የአብዮቱን 50ኛ ዓመት በራሷ መነጽር መገምገም አለባት በሚል እምነት ሲሠሩ የቆዩ ነገሮች ነበሩ። ይኼ ውይይት የዚያ ውጤት ነው። እንደወትሮው ሙሉ ውይይቱን እንድትከታተሉ፣ አዳምጣችሁም አሳባችሁንም እንድታጋሩን እንጠይቃለን።

https://youtu.be/etaDulBBQaQ?si=0HZVEI1N8K0vXPtz


https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ተጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

13 Jan, 17:51


" እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ ትምህርት ነው ፤ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች።" [ ምሳ.፲፭፥፴፫ ]

ለክርስቶስ ለቀን አንተ ጀምረው ብለን የጀመርነው ለጌታ የሰጠነው የትኛው ሕይወታችን የትኛው ስራችን ኖሮን ይሆን?

ትዳራቹን ክርስቶስ ሆይ ተገኝበት ብላችሁታል እሱን አስቀድማችሁታል ?

ልጆቻችሁን አንተ አሳድግ ብላችሁታል ?

ትምህርታችሁን አንተ አስፈፅመን ብላችሁታል ?

የተጣላችሁትን ስለጌታ ፍቅር ብላችሁ ትታችሁለታል ?

የትኛውን ነገር ለክርስቶስ ትተንለት ይሆን
?

በአባቶች ዘንድ ያለችውን አንተን በማፍቀር የመፍራትን ጥበብ ስጠን 🤲 ስጋዊ የሆነው የማስመሰል ህይወት ጠልፎ እዳይጥለን ብርታት ሁነን🤲

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

13 Jan, 10:44


አምላኬ  አምላኬ ነፍሴ አንተን ተጠማች  ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች”
  መዝሙር 63፥1

ቸር ጌታ ሆይ ዳግም ከማያስጠማው የሕይወት ውሃ እጠጣ ዘንድ ከሕይወት ማዕድህም እቀርብ ዘንድ ብርታ ሁነኝ እኔ በባዶ በመመላለስ ደክሜያለሁ ዝያለሁ ጌታዬ ባዶነቴን ሙላው 🙏🙏🙏

ዮሐንስ 4
¹⁰ ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት። ¹⁴ እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት።
¹⁵ ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ አለችው።

ባዶነትን ሚሞላ ቸር ጌታን እያሰባችሁ ቸር ዋሉልኝ🤗🤗🤗
https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

11 Jan, 13:36


በአንድ ቤተክርስቲያን በነበረ የህብረት ጉባኤ ላይ አንድ የመፅሀፍ ቅዱስ ቃል እንዲያነቡ አንድ ወጣት እና አንድ በእድሜ ጠና ያሉ አባት ተመረጡ....በመጀመሪያም ለወጣቱ ተሰጠዉ እና መዝሙር 23 ማንበብ ጀመረ በቃሉም

1: እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
2: በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤
በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
3: ነፍሴን መለሳት፥
ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ.....እያለ ቃላትን ሳይስት ተናገረ ጉባኤ ዉስጥ የነበሩትም በጣም ተደንቀዉ አጨበጨቡለት....ከዛም አዛዉንቱ ቀጠሉ...የደከመ አይናቸዉ ላይ መነፅራቸዉን እያረጉ ለማንበብ ተዘጋጁ አነበቡ ጨረሱም ከዛ ግን ጉባኤዉ ውስጥ ያሉት በሙሉ አለቀሱ በዚህ ጉባኤ ዉስጥ አዲስ የነበረ አንድ ሰዉ ግራ ተጋብቶ ወደ አዛዉንቱ ሄዶ "አባቴ ወጣቱ ያለምንም ግድፈት በቃሉ ሲያነብ ሰዉ አጨበጨበ እርሶ ሲያነቡ ግን አለቀሱ እና አልገባኝም ለምንድነዉ" አለ አዛዉንቱም መለሱ "አየህ ልጄ እሱ የሚያዉቀዉ ጥቅሱን ነዉ እኔ ማዉቀዉ ግን እረኛዉን ነዉ"አሉ።

ከህይወታችን ቀድተን የምንሰጠዉ ነገር ሰዉን የመንካት ሀይል አለዉ እግዚአብሔር ባሰመረልን በህይወት መንገድ ላይ መሄድን አንጣ ምክንያቱም ሰዎችን የሚነካ ከህይወት ቀድተን የምንሰጠዉ በዚህ ስለሆነ።



ዮሐንስ 4
¹⁰ ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት።
… 
¹⁴ እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት።

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

10 Jan, 12:16


አቤቱ ሆይ በኔ ያደረችውን ኃጢአት ቸርነትህ ያቸንፋት፡፡ ይቅርታህም ከበደሌ ይበርታ
የምሕረትህም ዝናም የዕዳ በደሌን ደብዳቤ ይደምስሰው፡፡ የማዳንህም ቃይል በኔ ላይ ይገለጽ፡፡

ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ፡፡ አቤቱ ሆይ የውጭ ተክል አታርገኝ፡፡ የጽድቅ ተክል
አድርገኝ፡፡ የኃጢአት አይደለም፡፡ የዕውነት ተክል አድርገኝ የሐሰት አይደለም የፍቅር ተክል አድርገኝ የጽል አይደለም፡፡

የበረከት ተክል አድርገኝ የመርገም አይደለም የክብር ተክል አድርገኝ የኃሣር የጎስቁልና አይደለም ሕይወት ተክል አድርገኝ የጥፋት አይደለም፡፡ ያንተ ተክል አድርገኝ የሰይጣን አይደለም የቅዱሳን ቅድስት ተክል በነቢያት ትንቢት ካፊያ የምለመልም አድርገኝ፡፡

የመጻሕፍት መጀመሪያ የምትሆን ኦሪት ደመና
የምትጋርደኝ፡፡ ከቅዱስ ወንጌል ፈሳሽ
የምጠጣ ከጎንህ ከፈሰሰው ደም የምረካ ልሁን፡፡ በእናትህ በድንግል ጸሎት የሃይማኖት አበባ ላብብ፡፡ የጽድቅ ፍሬን ላፍራ ከቅዱሳንህ ሐዋርያትም ከቃላቸው ፍሬ የተነሣ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የተባረከ የወይን ቦታ ልባል የጽድቅን ፍሬ የሚያስቀረውንም የኃጢአት እሾህ ጠምዝዘው ከደጁም አሜከላውን አረሙንም ሙጃውንም ንቀለው፡፡ አቤቱ ከኔም አርቀው ሥርዓትህን የሚሠሩትን ያበባቸውን ፍጻሜ እንዳፈራ አድርገኝ፡፡


https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

09 Jan, 06:15


ዛሬ በዳዊት ከተማ ጌታ ተወልዶላችኋል የሚል የመላእክትን ስብከት ከመስማት፣ ቤዛ ኵሉ ዓለም ዮም ተወልደ (የዓለሙ ሁሉ ቤዛ ዛሬ ተወለደ) የሚል ዝማሬን መዘመር ከመቻል በላይ ዕጹብ ድንቅ ነገር የለም። ክርስትና ይኼንን የምሥራች ለዓለም ይዞ የመጣ ነው። በዓለ ልደትን በተመለከተ የቀረበውን ውይይት እንድትመለከቱ እንጋብዛችኋለን

https://youtu.be/NLF9VjZxcKI?si=by_Z8NPmhG-yqIX3


https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ንኳት

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

08 Jan, 19:37


ያፈቀረንን ቸር ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እናፈቅረው ዘንድ ያፈቀራቸውን እናፍቅራቸው በዚህ የፍቅር ልጆች እደሆንን እንለያለን

1ኛ ዮሐንስ 4
⁷ ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ።
⁸ ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።

በቸር እደሩልኝ🤗🤗🤗

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

08 Jan, 08:31


ያለአንተ መኖር እንዴት ተከናወነልኝ እንዴትስ ተቻለኝ፡፡ አንተን መውደድም አንተ ካልረዳኸኝ አይሆንልኝም፡፡ካደረክልኝ አንፃር ያለብኝ የፍቅርህ እዳ ያስጨንቀኛል። የአንተ የፍቅር ብድራት የሌለበት አንድስ እንኳን የለም የእኔ ግን ከሁሉ ይልቅ የእጥፍ እጥፍ ነው፡፡ ቁጣህ እንኳ ሳይሆን ፍቅርህ የከበደኝ እኔ

“ ፍቅርህን እናስባለን " መኃልየ. 1፥4

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

07 Jan, 06:54


የክብር ልብስ ሆነን
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

06 Jan, 20:40


‹‹ወልድ ተሰጠን›› (ኢሳ.፱፥፮)

እንኳን አደረሳችሁ!


ነቢየ እግዚአብሔር ልዑለ ኢሳይያስ የታነገረው ይህ ቃል ለጊዜው በምርኮ በጭንቅ ለነበሩ፣ በሰናክሬም ዛቻ፣ በብልጣሦር የግፍ አገዛዝ አስጨንቋቸው ምድራዊ ሕይወታች በመከራ አዘቅት ሰጥሞ ለነበሩት ለእስራኤላውያን ቢሆንም የመከራው ጊዜ አልፎ ከስደት እንደሚመለሱ፣ በተድላ ደስታ የሚኖሩበት መልካም ጊዜ እንደሚመጣ ሲሆንም ፍጻሜው ግን በጽመት አዘቅት ሰጥመው፣ በመከራ ፍኖት ተጉዘው ኑረውም፣ ሞተውም የዲያቢሎስ ምሮኮኞች የሲኦል ግዞተኞች ለነበሩ ለአዳምና ለልጆቹ የጽድቅ ፀሐይ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ተወልዶ፣ በሞቱ ሞትን አጥፍቶ ከዲያሎስ አገዛዝ ከጨለማ ሕይወት እንደሚያወጣቸው የተነበየው ነው:: (ኢሳ.፱፥፮ አንድምታ)

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ልዑለ ቃል ነቢየ ኢሳይያስ ‹‹ወልድ ተውህበ ለነ፤ ወልድ ተሰጠን›› በማለት እንደተናገረው ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ወልድ ሲወለድልን የጨለማው የሰው ልጆች ሕይወት በራ፤ ቤተ ልሔም አቅራቢያ መንጎቻቸውን ሲጠብቁ ለነበሩ እረኞች እስካሉበት ቦታ ድረስ ባሕረ የብርሃን ወንዝ (የብርሃን ጎርፍ) ፈሰሰላቸው፤ በአዳምና ሔዋን በደል ምክንያት በሰዎችና በቅዱሳን መላእክት መካከል የነበረው የጠብ ግድግዳ ፈርሶ፣ ሰላም ተመልሶ ፍቅር ነግሦ በአንድ ላይ ሆነው ምሥጋና የባሕርይው ገንዘቡ ለሆነ ፈጣያቸው በተፈጠሩበት ዓላማ መሠረት አዲስ ምሥጋንን አቀረቡ፡፡ ‹‹መላእክት ከኖሎት ኖሎት ከመላእክት ጋር አንድ ሆነው አመስግነዋል፡፡›› (ሉቃ ፪፥፲፬ አንድምታ)

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

06 Jan, 20:40


ብርሃናውያን መላእክት በጨለማ ላለው አዳምና ልጆቹ ከጨለማ የሚያወጣቸው ወልድ በተሰጣቸው (በተወለደላቸው) ጊዜ ተደስተው ‹‹..ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ፡፡›› (ሉቃ.፪፥፲፫)

ውድ አንባብያን! ይህን የተቀደሰ ዕለት በደስታ፣ በፍቅርና በሰላም እናከብር ዘንድ ከጥልና ከጥላቻ ርቀን፣ በንስሐ ነጽተን፣ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀን፣ በወንድማማችነት ፍቀር ተሰባስበን ይሁን!

መልካም በዓል!

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

06 Jan, 05:33


“የአእላፋት ዝማሬ በመንፈስ ቅዱስ የተሰናዳ የሰላም መዝሙር ነው" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

የአእላፋት ዝማሬ
The Melody of Myriads

የዘንድሮው የአእላፋት ዝማሬ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ በተመሳሳይ ሰዓት ይካሔዳል!

ታኅሣሥ 28 የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት በዝማሬ ለማክበር ለአእላፋት ዝማሬ እንገናኝ ።

https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

06 Jan, 05:16


የእግዚአብሔርን ጥበብ እንናገራለን" ፩ቆሮ ፪÷፯

የተወለደው (ሰው የሆነው) ማነው?

እግዚአብሔር ሰው ሆነ ስንል ምን ማለት ነው?

እግዚአብሔር ለምን ሰው መሆን አስፈለገው?
  - ሰውን በተፈረደበት የሞት ፍርድ ውስጥ መተው
  - ሰውን ማዳን

    ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

05 Jan, 08:14


https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

05 Jan, 08:13


#new🔴እግዚአብሔር እንደማስመሰል የሚጠላዉ ነገር የለም! መምህር ያረጋል አበጋዝ #kendil_media...
https://youtube.com/watch?v=E50ApnWj4iA&si=5BYor7uii0OQsjX3


https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ👆

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

04 Jan, 10:11


''የወደድኩህ በጣም ዘግይቼ ነው፡፡ ቀዳማዊ ብትሆንም ምንጊዜም አዲስ ነህ፡፡ እፈልግህ ነበር አንተ በፈጠርከውና ባሳመርከው ውስጥ ሁሉ ያለማስተዋል እባዝን ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን አንተ ከእኔ ጋር ነበርህ እኔ ግን ከአንተ ጋር አልነበርሁም፡፡''

ከዚህ በኋላ ቅዱስ አውግስጢን እግዚአብሔርን በውስጡ ሲያገኘውከጻድቃን ወገን ሆነ።ወዳጆች ሆይ! እኛም ብንሆን እግዚአብሔርን ከእኛ ውጪ ብንፈልገው መንገዱ ይጠፋብናል። ስለዚህ እናስተዉል! ወደ እኛነታችንና ወደ ውስጣችን ጠልቀን እንግባና እግዚአብሔርን እንፈልገዉ፡፡ በዚያ በጥልቁ ባለው ውሳጣዊ ማንነታችን ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ በዚያ ምንጩ የማይነጥፍና የማይደርቅ የፍቅር ውኃ ሆኖ ፊት ለፊት እናየዋለን፡፡ ያኔ ነው እጅግ በመደነቅ በዝምታ በልቅሶና🥹 የደስታ ሲቃ ተውጠን ''እግዚአብሔርን አየሁት👀'' ማለት የምንችለው፡፡

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

03 Jan, 05:55


«ወንድምህን አትናቀው»

ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው። እህትህን አትናቃት። ምንም ይሁን ምን ሰው አትናቅ። ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብከዉ እንደሆን አስተውል።

"እንዴት?"  ያልከኝ እንደሆንም ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል። የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እሱን ናቅኸው ማለት ክርቶስን ናቅኸው ማለት ነው።

ወንድምህን የምትንቅ ከሆነም በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ እራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞትንና ከርቤን ቀላቅለው ከሰጡት፣ በፊቱ ላይም ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም። ስለዘህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ያለመናናቅ ክርስቶስን በሕሊና በማሰብ በክርስቶስ ፍቅር በቸር ዋሉልኝ🤗🤗🤗

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

02 Jan, 11:59


ቤተሰቦች እስቲ ስለ ካህናት እና ስለ መምህራን ከኛ ምትጠበቀዋን ጥቂት ያላስተዋልናትን ልበላቹ

በየትኛውም ጉባኤ መምህራን ሲያስተምሩ ስለመምህራን መፀለይ ተገቢነው በመምህሩ አድሮ መንፈስ ቅዱስ እዲናገር ሚስጢር እዲገልጥ

መምህርም በየትኛውም ትምህርት ላይ ከመናገር ቀድሞ በሱ አድሮ መንፈስቅዱስ እዲናገር በሰሚውም ደሞ ሁኖ መንፈስቅዱስ ደሞ ሚጠቅማቸውን ፍሬ እዲሰጣቸው ማይጠቅማቸው ካለ እዲያስረሳቸው መፀለይ ግድ ይለዋል

እደገና መምህሩ ያጎደለው የሳተው ካለ ደሞ ስለኛ ስለሰሚዎች መፀለይ ነው መንፈስ ቅዱስ አቃንቶ ሞልቶ ሚስጢሩን እዲገልፅልን በጉባኤ ይህንን ማድረድ አንዱ ክርስትያናዊ ሕይወት መገለጫ ነው መፅሐፍ ቅዱሳዊም ነው👇👇

ሌላው ለንስሐ አባቶቻችን (ስለካህናት) መፀለይ ካህን ስናገኝ በካህኑ አድሮ ጌታ እዲናገረን በጎም እይታ እዲኖረን ስለ ካህኑ እና ስለ እኛ መፀለይ ይገባናል ይህች ልዩ ፍቅርንም ትሰጠናለች ከመምህራን እና ከካህናት እግር ስርም እዳንጠፋ ምክንያት ትሆነናለች🥰  

ብዙውን ጊዜ ግን ይህ ልማደ ክርስትና የለንም  በጥቂቷ ግን ወደጉባኤ ስንሄድ ወደካህናት ለመማር ስንቀርብ በህሊናችን ስለጉባኤው እየፀለይን እንቅረብ ጌታም ይረዳናል 🙏


ቆላስይስ 4
² ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ፤
³ በዚያን ጊዜም ስለ እርሱ ደግሞ የታሰርሁበትን የክርስቶስን ምሥጢር እንድንነግር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልን ዘንድ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ፤
⁴ ልናገር እንደሚገባኝ ያህል እገልጠው ዘንድ ጸልዩልኝ።

“ጸልዩልን፤ በነገር ሁሉ በመልካም እንድንኖር ወደን፥ መልካም ሕሊና እንዳለን ተረድተናልና።” ዕብራውያን 13፥18

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

31 Dec, 17:57


፨ doctrine እና speculation እንለይ።

ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

31 Dec, 04:12


🛑 ሊንኩን ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ

https://youtu.be/ElE7NNzNJYA?si=8pLTy7GCtScfPJCp


https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

31 Dec, 04:11


እንኳን #ለብስራት_ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

በዚህ ዕለት ታላቁ መልዐክ መጋቢ ሐዲስ የተባለ ቅዱስ ገብርኤል ለዓለም ታላቁን ዜና አበሰራት !

የሰው ዘር በሙሉ ለ 5ሺ 500 ዘመን አንድ ዜናን በጉጉት ይጠብቅ ነበር ። መጠበቅ ከባድ ነው ! ግን ደግሞ መጠበቅ ተስፋ ነውና አለመጠበቅ አይቻልም። ኅጥሁ ከ ጻድቁ በአንድነት "ፈኑ ዕዴከ እም አርያም" እጅህን  ከሰማይ ከመንበርህ ላክልን እያሉ ይማጸኑ ነበር

የለመኑትን የማይነሳ የተናገረውን የማይረሳ እግዚአብሔር አብዝተው ቢለምኑት አንድም ስራውን የሚሰራበት ጊዜ በመድረሱ መልዓኩን ወደ አንዲት የ15 ዓመት ብላቴና ላከው። ቅዱስ እና ሊቅ የሚሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለጽኑ ሸክም ጽኑ ተሸካሚ ያስፈልጋል እንዳለ መለኮት ለመቀበል በንጽህና ለተገኘች ቅድስት መልዓኩ ታላቁን ዜና አበሰራት ።

በዓለም ላይ ትልቁን ዜና ማብሰር ምን ይሆን ስሜቱ ?!

ወናሁ ትጸንሲ ወትወልዲ :- እነሆ ትጸንሻለሽ ትወልጃለሽ ብሎ የተናገረ መልአኩ ገብርኤል ድንቅ ነገር አበሰረን ። ብስራትሽ ብስራታችን ነው ። በብስራትሽ ነገረ ድኅነታችን ታወጀልን።

ድንግል ሆይ #ይኩነኒ :-ይሁንልኝ በማለትሽ የአዳም ተስፋው ፣ የአበው ልመና ፣ የነቢያት ትንቢት የአዳም ልጆች ድኅነት ተፈጽሟል።

አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ በተገባ ተገኝተሻል እና አማልጂቱ ሆይ ክብር ይገባሻል።
ቅዱስ ህርያቆስ እንዲህ እያለ እንዳመሰገነሽ እኔም አመሰግንሻለው ።

እግዚአብሔር አብ በሰማይ ሁኖ ምስራቅን እና ምዕራብን ሰሜንን እና ደቡብን ዳርቻዎችንም ሁሉ #በአማን_ነጸረ በእውነት ተመለከተ ተነፈሰም አሻተተም እንደ አንቺ ያለ አላገኘም ። የአንቺን መዓዛ ወደደ ። ደም ግባትሽንም ወደደ ። የሚወደውን ልጁንም ወደ አንቺ ሰደደ።

አንቺን የወደደ እግዚአብሔር አብ ቅዱስ ነው #በእውነት ቅዱስ ነው !
በማኅጸንሽ ያደረ ወልድ ዋሕድም ቅዱስ ነው
#በእውነት ቅዱስ ነው !
ያጸናሽ የእውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስም ቅዱስ ነው
#በእውነት ቅዱስ ነው !

መልካሙን ዜና ያበሰርክ አብሳሪው ሆይ ስለ ዛሬም መልካሙን ዜና አሰማን !



https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

29 Dec, 18:09


መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወደ እስር ቤት እንደገባ ነበር ጌታ ስብከቱን የጀመረው። ታዲያ ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ከዮሐንስ እስር በኋላ የጌታን መገለጥ የተናገረው በብርሃን መውጣት መስሎ ነው። አስቀድሞ ነቢዩ ኢሳይያስ "በጨለማ ይኖር የነበረ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን ወጣለት" ብሎ የተናገረው የጌታን መገለጥ እና በገሃድ መታየት ተከትሎ ስለመጣው ብርሃናዊ ሕይወት መሆኑን ወንጌላዊው በትርጉም ይነግረናል። ብርሃን ዘበአማን፣ ብርሃን ዘበጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመጣ በኋላ በብርሃን መኖር፣ በብርሃን መመላለስ ለሰዎች ተሰጥቷል። ቤተ ክርስቲያንም በዚህ ሳምንት ምስክርነቷ ስለዚሁ ነው። ውይይቱ እነሆ።

https://youtu.be/YV6TY0bbF0M?si=lqNSw3ckO3fAuDj2


https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

28 Dec, 12:01


https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

28 Dec, 11:27


ዳንኤል 3 ÷¹⁷ የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፥ ንጉሥ ሆይ!
¹⁸ ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ አሉት።

እምነት ሲመሰከር ተመለከታችሁ በጌታ🥰🥰🥰


እግዚአብሔርን ለቆ ከሚገኝ ክብር ከሚገኝ ገንዘብ ከሚገኝ ሹመት ይልቅ  እግዚአብሔርን ይዞ የሚገኝ እሳት ዋጋ አለው  ከመላዕክቱ ጋር እንመላለስበታለን እና


“በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ።”
  — መዝሙር 84፥10

የአናንያ የአዛርያ እና የሚሳኤል የእምነት ፅናት የጌታ ፍቅር በኛም ልብ እዲኖር እድንመሰክር እንድንኖር በረከታቸው አትለየን🤲🤲🤲 ቅዱስ ገብርኤል በዚህ ዘመን ከክርስቶስ ፍቅር ለይቶ አውጥቶ ከሚጥል እሳታዊ ፈተና ፈጥኖ ደርሶልን በእምነታችን እንድንቆም ይርዳን አይለየን🙏🙏🙏🙏

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

27 Dec, 18:46


††† እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት †††

††† በቤተ ክርስቲያን ክቡር ከሆኑ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ገብርኤል ብዙ የክብር ስሞች አሉት:: በተለይ ግን:-
*ሊቀ አርባብ:
*መጋቤ ሐዲስ:
*መልአከ ሰላም:
*ብሥራታዊ:
*ዖፍ አርያማዊ:
*ፍሡሐ ገጽ:
*ቤዛዊ መልአክ:
*ዘአልቦ ሙስና . . . እየተባለ ይጠራል::

በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ስሙ በብዛት ተጠቅሷል:: ስለ ረዳትነቱና አማላጅነቱም ቤተ ክርስቲያን በስሙ ታቦት ቀርጻ: መቅደስ አንጻ በሥርዓት ክብሩን ትገልጻለች::

ከእነዚህም አንዱ ሠለስቱ ደቂቅን እንዳዳነ የሚታሰብበት አንዱ በዓሉ ዛሬ ነው::
"ለዝንቱ ዜናዊ መልአከ ኃይል::
በዛቲ ዕለት ከመ ይትገበር በዓል::
መምሕራን አዘዙ ወሠርዑ በቃል::" እንዲል:: (አርኬ)

ንጉሡ ከምርኮ ወጣቶች ለቤተ መንግስት ሲመርጥ ሦስቱ ቅዱሳንና ዳንኤል ተመርጠው የምቾት ሕይወት ተዘጋጅቶላቸው ነበር:: ነገር ግን በምግብና በአምልኮ ከአሕዛብ ጋር መተባበርን አልፈለጉምና ምርጫቸው ጾምና ጸሎት ከቆሎ ጋር ሆነ::

ምንም እንኳ በቤተ መንግስት ውስጥ ቢኖሩ: ምንም የነገሥታት ልጆች ቢሆኑ ለእነርሱ ከእግዚአብሔር ፍቅር የተሻለ አልነበረምና በጥሬ ቆሎ ተወስነው ኖሩ::

አምላካቸው ከሃሊ ነውና በውበትም ሆነ በጥበብ በባቢሎን ምድር ከነርሱ የሚደርስ አልተገኘም:: ንጉሡም በባቢሎንና በአውራጃዋ ላይ ሾማቸው:: ስማቸውንም በአማልክቱ ስም ሲድራቅ: ሚሳቅና አብደናጐ አላቸው::

ከነገር ሁሉ በኋላ አሕዛብ ቀንተውባቸዋልና የክፋት አዋጅን አሳወጁ:: ናቡከደነጾር 60 ክንድ ቁመት ያለውን የወርቅ ምስል አቁሞ ስገዱ ቢላቸው አይሆንም በማለታቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተፈረደባቸው:: ነበልባሉ ከጉድጓዱ ወደ ላይ 49 ክንድ ቢነድም ቅንጣት ያህል ፍርሃት አልጎበኛቸውም::

ወደ እሳቱም ሲጥሏቸው መልዐከ አድኅኖ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው:: ከሆነው ነገር የተነሳ አሕዛብ አፈሩ:: ናቡከደነጾር ግን ከዙፋኑ ተነስቶ የቅዱሳኑን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ::

ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን
"አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው::
አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው:: (መልክዐ ገብርኤል)


https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

27 Dec, 18:46


https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

26 Dec, 09:56


አሁን በዚህ ዘመን ሱሪ የምትለብስ እህት ቅዱስ ቁርባን መጥታ እንዳትቀበል እንደሚል ዓይነት የግንዛቤ እጥረት ያለበት ብቻ ሳይሆን በሽታም ጭምር ያለበት ሰው ማን አለ በስመ አብ.. ለራሱ የሃጢአት ክምር ተሸክሞ በሌሎች ሰዎች ጥቃቅን ነገሮች ላይ አፉን የሚያላቅቅ ሰው..

ጌታ ስለ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ሲናገር እንዲህ ይላል:

“እናንተ ዕውሮች መሪዎች፥ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ።”
[ማቴዎስ 23: 24]

@Apostolic_Answers

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

26 Dec, 03:29


https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

26 Dec, 03:28


🛑የሚገርም ነው! እጅግ ጥልቅ የሆነው የኦርቶዶክስ የነገረ ክርስቶስ ትምህርት! ክፍል 4
https://youtube.com/watch?v=F63SwSg_x3o&si=R5zcihjWTKIjepAp



https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

24 Dec, 17:28


ስለ ክርስቶስ ማንነት ተሳስተው ለሚያሳስቱ ሰዎች እጅግ ድንቅ ትምህርት! በዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው Deacon Yoha...
https://youtube.com/watch?v=Ty91w_Xc76w&si=v4VmX2KMSJD2Iaka


https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

23 Dec, 03:16


ከእግዚአብሔር ጋር ዉለን ስናድር ለኛ ማይታየን ማይታወቀን ክርስቶስን መምሰል ይሆንልናል

ዘጸአት 34:29
እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ከሲና ተራራ በወረደ ጊዜ ሁለቱ የምስክር ጽላቶች በሙሴ እጅ ነበሩ፤ ሙሴም ከተራራው በወረደ ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ተነጋገረ የፊቱ ቁርበት እንዳንጸባረቀ አላወቀም ነበር።

ከጌታ ጋር እንዋል እንደር ከሱ ጋር እንቆይ።

ክርስቶስን በህሊና ከማሰብ ሳትቦዝኑ ቸር ዋሉልኝ 🤗🤗🤗

“የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።”ራእይ 22፥21

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

22 Dec, 14:03


#ጥንተ_አብሶ

እዚች ሃሳብ ላይ ትንሽ የተዛባ አመለካከት አንዳንዶች ዘንድ ስለምትስተዋል ግልፅ እንዲሆን ተመልከቷት🤗🤗🤗

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

21 Dec, 19:44


ዘመነ ስብከት 'ይመጣል፣ ይወለዳል' ካሉ ነቢያት ጋር በመንፈስ አንድ ሆነን የጌታን ልደት የምንሰብክበት ዘመን ነው። "ዛሬ ተወለደ" እያልን ከመዘመራችን በፊት፣ እንደ ነቢያቱ ልደቱን አስቀድመን እንሰብካለን። ከስብከት እስከ ልደት ያሉት ጊዜያት ከነቢያቱ ጋር በመንፈስ፣ ከእረኞቹ ጋር በአካል መገኘትን የሚያጠይቁ ናቸው። የስብከት ቀለማት ምሥጢር በመክፈቻነት የቀረበበት ይኼን ቪዲዮ ያድምጡ።

https://youtu.be/nC0m10v8dAk?si=c9NRl-x-Yd1Ttl-W


https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

20 Dec, 09:34


“ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።”1ኛ ጴጥሮስ 2፥2-3

እግዚአብሔር በጥበብ እና በሞገስ በቤቱ ያሳድጋት 🥹

https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

19 Dec, 19:30


"ቤተክርስትያንን መርዳት ከፈለክ ሌሎችን ለማረም ከማሰብ በፊት በቅድሚያ እራስን ማስተካከል ይበጃል። እራስህን ካስተካከልክ አንድ የቤተክርስትያን ክፍል ዳነ ወይም ተስተካከለ ማለት ነው። ሁሉም ሰው ይህን ማድረግ ከቻለ ቤተክርስትያን ጤናማ ትሆናለች። ስለዚህ ላስተዋለው ሰው ሌሎች ላይ መፍረድ እጅግ በጣም ቀላል ነው እራስን ማስተካከል ግን ጥረት ይጠይቃል።"

ቅዱስ_ፓሲዮስ

ሰናይ የያዕቆብ ለሊት🤗🤗 🌕
https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

19 Dec, 03:18


መዝሙር 67
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ፤

² በአሕዛብ ሁሉ መካከል ማዳንህን፥ መንገድህንም በምድር እናውቅ ዘንድ።


ቸር ዋሉልኝ🤗🤗🤗

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

18 Dec, 13:41


አንድ የተረዳዋትን ነገር ላካፍላችሁ🤗

ክርስትያን እደክርስትያንነቱ እነዚህን 👆 ቢያነብ እጅግ ይጠቀማል ብዬ አስባለሁ በእርግጠኝነት ስነግራችሁ 😊

ሃይማኖተ አበው :- ስለ ሃይማኖቱ ምንነት እውነት የአበውን ምስክርነት ትምህርት (አስተምሕሮ) እውቀት የሚንይዝበት የምንረዳበት ሲሆን


ስንክሳር:- ደግሞ ስለሃይማኖታቸው ብለው የተጋደሉትን አበው ህይወት (ኑሮ) እናውቅበታለን ሃይማኖትን እንዴት በኑሮ (በህይወት) መመስከር እደሚቻል እንገነዘብበታለን የቀደሙትን ቅዱሳን ህይወት እያየን ተስፋ እናረጋለን እንበረታለን እንፀናለን ማለት ነው

“የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።”ዕብራውያን 13፥7

ሳጠቃልለው:- ከላይ በጥቂቱ ለመንካት እደሞከርኩት ለህይወታችን በጣም አስፈላጊዎች ናቸው እመኑኝ ጥቂት ጥቂት አንብቡ ለውጡን ታዩበታላችሁ

እግዚአብሔር በነገሮች ሁሉ እንጠቀም ዘንድ ብርታት ይሁነን 🙏🙏🙏

“የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።”ራእይ 22፥21


https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

18 Dec, 13:26


https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

01 Dec, 19:19


ጥልቅ ማሰላሰልና ንባብ ለምን ያስፈልገናል? ከቀሲስ አባተ አሰፋ ጋር ዘለግ ያለ ውይይት አድርገናል። መልካም ቆይታ።

https://youtu.be/QKDw1LQyb6M?si=kWDw0c-DVIKlR49K


https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

30 Nov, 11:22


ጽዮንን ክበቧት
                         
Size 27.4MB
Length 1:18:41

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

https://t.me/orthodoxzelalemawit
https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

30 Nov, 05:41


https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

30 Nov, 05:36


"ከአዳም ጎን በወጣችው አጥንት ሰይጣን የአዳምን ልብ ሠረቀ። ከኹለተኛዋ አጥንት [ከድንግል ማርያም] ግን ሰይጣንን እንደ ዳጎን የቆረጠ ኅቡዕ ኃይል ወጣ በዚህችኛዋ ታቦት አሸናፊነትን የሚሰብክና የሚያውጅ መጽሐፍ ተደብቋልና። ምሥጢርም ተገለጠ ዳጎን በራሱ መማጸኛ ቦታ ወዳደቀ። ይህ ምሳሌ ነው ከድንግል የወጣው ሰይጣንን በተማመነበት ቦታ ጥሎታልና። ምሥጢሩም ተፈጸመ በእውነተኛው በግ የዋጀን አጥፊያችንን ዳጎን እንደ ጠፋ ያጠፋው የተባረከ ይኹን።” (መቅደስ ስ ኤፍሬም ሶርያዊ, Rhythm iii, On the Nativity, Morris, p.20) ((Blessed Virgin, p. 66).

ድንግልስ ከታቦተ ጽዮን ትበልጣለች በእርሷ የወደቀው በዳጎን የሚያስተው ሰይጣን ነውና! እንኳን አደረሳችሁ ለሐዲስ ኪዷኗ ታቦት በዓል አደረሳችሁ ❤️


#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

29 Nov, 08:42


አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ፤ ማረኝና አድምጠኝ።አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተውኝ።

መዝሙር 27:7-9


#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

26 Nov, 03:04


በእነዚህ የጉባኤ ቀናት ሁላችሁም ተገኝታችሁ የእግዚአብሔርን ቃል ተማሩ

https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

24 Nov, 19:23


ከአእምሮ በላይ የሆነው የክርስትናችን ምሥጢር እዚህ ቃል ውስጥ ይገኛል። ከሁሉ በላይ፣ ሁሉ የእርሱ፣ ሁሉ በእርሱ የሆነ አምላክ ራሱን ባዶ አደረገ። የፍቅር ጥጉ ይኼ ነው። ከቅዱስ ጳውሎስ ጀምሮ ብዙ ቅዱሳን ይኼ ፍቅር ውስጣቸው ዘልቆ ገብቷልና፣ ራሱን ለሰጣቸው አምላክ መልሰው ራሳቸውን ለመስጠት ሲፈቅዱ በታላቅ ደስታ ነበር። የክርስቲያናዊ ሕይወት አልፋና ኦሜጋ ይኼው ነውና።



https://youtu.be/oiPF_eQHtCc?si=qNH6uzUz_aXnClbN


https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

23 Nov, 07:14


ሕማሜን በሕማምህ አድን፤ በቁስልህም ቁስሌን ፈውስ፡፡ ደሜን ከደምህ ጨምር፤ ሕይወት የሆነ የቅዱስ ሥጋህን መዓዛም በሥጋዬ ጨምር፤ በጠላቶች /በአይሁድ/የጠጣሃው ከርቤም ክፉ ሐሞትን የጠጣች ነፍሴን ያጣፍጣት፡፡ በሰፊው መስቀል ላይ የተዘረጋው ሥጋህም ሕሊናዬን ወደ አንተ ያድርገው:: በጠላት /በዲያብሎስ ድል ተነስቻለሁና። በመስቀል ላይ የዋለው ራስህ በርኩሳን ዘንድ የተቀጠቀጠ ራሴን ከፍ ያደርገው፡፡ በከሀድያን የተቸነከሩ ቅዱሳት እጆችህም ወደ አንተ ይንጠቁኝ፡፡

በወንጀለኞች ምራቅንና ጉስቁልናን የተቀበለ ፊትህ በኃጢአት የጐሰቆለ ፊቴን ያብራልኝ፡፡ የተሰቀለች ሰውነትህም ወደ አባትህ ዐረገች:: ጸጋህም ወደ አንተ ታድርሰኝ፡፡ አቤቱ ለመማጸን ዕንባ የለኝም፡፡ ለመለመንም ያዘነ ልብ የለኝም፡፡ ልጆችህን ወደ ርስታቸው የሚሰበስብ ንስሐና ኀዘንም የለኝም። ከጥፋት ብዛት የተነሣም ሕሊናዬ ጠቆረ፡፡ በእነዚህና በመሳሰሉትም ልቡናዬ ተሸፈነ፡፡ ወደ አንተ እመለከት ዘንድም ኃይል የለኝም፡፡ ከክፋት የተነሣም አዕምሮዬ ቀዘቀዘ፡፡ በተቃጠለ ፍቅር ዕንባን ማፍሰስም ተሳነው፡፡

የመልካም ነገር ሁሉ መዝገብ ክርስቶስ ሆይ፤ አንተና ለመፈለግ በፍቅር እወጣ ዘንድ ፍጹም ንስሐንና ትጉ ልቡናን ስጠኝ፡፡ ስለ አንተም ከሁሉ የተለየሁ ሆንሁ: ቸር ሆይ፣ ከባሕርዩ የወለደህ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞም በባሕርዩ የነበርህ የአብን ጸጋ ስጠኝ፡፡ አርአያህና አምሳልህም ውስጤን ያድሰው:: እነሆ ተውሁህ፤ አንተ ግን አትተወኝ፤ ወደ አንተ መጣሁ፤ አንተም እኔን ለመፈለግ ውጣ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(ውዳሴ አምላክ ዘሐሙስ)

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

21 Nov, 13:27


https://youtu.be/i0wPuW-82U4?si=nTW6kzYov9XFdH4m



https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

21 Nov, 05:37


እነሆ ከመላእክት አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ!

እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል አደረሰን!!!

መልአኩ የእኛን መቸገር አይቶ ሊረዳን ፈጥኖ ወደ እኛ ይምጣልን!!!

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

21 Nov, 05:36


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን

ኅዳር 12-ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር ንሥረ አርያም የሚባል ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ ንዑድ ክቡር የሆነ ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ዕለት ነው፡፡

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል፡- ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ' ካ-ከመ' ኤል-አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ ‹‹መኑ ከመ አምላክ-እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው›› ማለት ነው፡፡ አንድም ለእግዚአብሔር አሸናፊ ድል አድራጊ የቸርነትና የርህራሄ መገኛ መዝገብ ማለት ነው፡፡
ገናናው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ዲያብሎስን ወደ ጥልቁ ጥሎት በእርሱ ምትክ ከሁሉ የበላይ ሆኖ በተሾመበት በዚህ ዕለት በበዓሉ መታሰቢያ በኅዳር 12 ቀን የክብር ባለቤት በሆነ በእግዚአብሔር ፈቃድ ክንፎቹን ወደ ሲኦል ያወርዳል፣ ኃጥአንንም ወደ አዲሲቱ ምድር ያወጣቸዋል ይኸውም የመላእክት አለቃ የሚካኤል ሠራዊት ይሆናሉ፡፡ ይቅርታ የተደረገላቸውና ምሕረት አግኝተው በአንድ ጊዜ በክንፉ ያወጣቸው ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በየዓመቱ በኅዳር 12 ቀን እንዲህ እያደረገ እልፍ ነፍሳትን ያወጣል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ወገኖች የሆኑትን ሁሉ እንደሥራቸው ወደ ምሕረት ቤት ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ይወስዳቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ አብ መጋረጃ ውስጥ ይገባል፣ በዚህች ዕለት ምድራዊትና ሰማያዊት ስለሆነች ምሕረቱም ከመንበሩ በታች ይሰግዳል፡፡ ስለውኃ ምንጮች፣ ስለ ወይን ቦታዎች፣ ስለ ምድር ፍሬዎች በምድርም ላይ ስለሚኖሩ ስለ ሰው ልጆች ነፍስ ሁሉ፣ ስለ እንስሳትም፣ ስለ ሰማይ ወፎችም፣ ስለ ባሕር ዓሣዎችም፣ በምድር ላይና በባሕር ውስጥ ስለሚንቀሳቀሱ ሁሉ የምሕረት ባለቤት ከሆነ ከአብ ዙፋን በታች ሁልጊዜ በማመስገን ይሰግዳል፤ ልመናውንም እስኪሰማውና የምሕረትንም ቃል እስኪያስተላልፍለት ድረስ ከእግረ መንበሩ ሥር አይነሣም፡፡
ለዚህ ዓለም ምሕረትን የሚለምኑ ቅዱሳን መላእክትም በየዓመቱ ኅዳር 12 ቀንበእግዚአብሔር የዙፋኑ ዓውደ ምሕረት ዙሪያ ተሰብስበው ስለ ሰውና ስለ እንስሳትም ሁሉ ምሕረትን የሚለምን ቅዱስ ሚካኤል ከአብ መጋረጃ ውስጥ በወጣ ጊዜ ቸርና መሐሪ አብ ለቅዱስ ሚካኤል የሰጠው ልብሱን እነዚያ መላእክት ይመለከታሉ፣ ይቅርታን የማግኘት ምልክታቸው ነውና፡፡ ስለዚህ እነዚህ ቅዱሳን መላእክት በምድር ላይ ምሕረት እንደተደረገ ሰውንም እንስሳትንም ይቅር እንዳለ በዚህ ዓለምም የሚሆነውን ሁሉ አይተው ቅዱስ ሚካኤል በለበሰው ልብስ አምሳል ያውቁታል፡፡
ስንክሳሩ እንደሚለው ይህ እጅግ የከበረ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋራ በመሆን ገድላቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ የሚያጽናናቸውና የዘወትር ጠባቂአቸው ሆኖ የሚራዳቸው እርሱ ነው፡፡›› የብዙዎቹንም ቅዱሳን ገድል ስንመለከት የዘወትር ጠባቂያቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
ቅዱሳን በሕይወት ሳሉ ይህ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ረዳትና የዘወትር ጠባቂ፣ እንደጓደኛም አማካሪ ሆኖ የተበቃቸውን ስንቱን ቅዱሳን ዘርዝረን እንቸላለን፡፡ እርሱ ያልረዳው ቅዱስ የለም፡፡ መከራውን ያላስታገሰው ሰማዕት የለም፡፡ ለቅዱሳኑ እንዲህ እንደጓደኛቸው ሆኖ ሲጠብቃቸው ይኖራል፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ሚካኤል ለኃጥአንና አምላካቸውን ለካዱ ሰዎች ደግሞ በቁጣ ለመቅሰፍት ይመጣባቸዋል፡፡ ሰናክሬም በእግዚብሔር ላይ ክፉ በመናገሩ በአንዲት ሌሊት ብቻ 185,000 (መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ) ሠራዊቱን ቅዱስ ሚካኤል በብርሃን ሰይፉ ፍጅቷቸው አድሯል፡፡ 2ኛ ነገ 19፡35፣ ኢሳ 37፡36፡፡
እግዚአብሔርን ለሚወዱና እርሱንም ለሚያከብሩት መታሰቢያውንም ለሚያደርጉለት ግን ከሚፈልጉት ነገር ከቶ አያሳጣቸውም፣ ዘወትርም ይጠብቃቸዋል፣ በኋላም በአማላጅነቱም ከሲኦል እሳት ያድናለቸዋል፡፡ እነሆ ይህ ገናና ክቡር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡- ‹‹የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ ለቅዱስ ሚካኤልም ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን እስኪያጡ ድረስ ቸገራቸው፡፡ ዱራታዎስም ሸጦ ለመልአኩ በዓል መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱንና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለትና ወደ ባለጸጎች ሄዶ በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ፣ ሁለተኛም ወደ ባለ ስንዴ ዘንድ ሄዶ በእርሱ ዋስትና ስንዴን እንዲወስድ ዳግመኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ዘንድ ሄዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ ነገር ግን ወደቤቱ ሳይርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አዘዘው፡፡ ዱራታዎስም እንደታዘዘው አደረገ፡፡ ወደቤቱም በተመለሰ ጊዜ ቤቱ ሁሉ በበረከት ተመልቶ አገኘው፡፡ እርሱም እጅግ ተደስቶ የዚህን የክበር መልአክ የመታሰቢያውን በዓል አደረገ፡፡ ጦም አዳሪዎችንና ድኆችን ጠርቶ አጠገባቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ሁለተኛ ተገለጠላቸው፡፡ ዱራታዎስንም የዓሣውን ሆድ እንድሰነጥቅ አዘው፡፡ በሰነጠቀውም ጊዜ 300 የወርቅ ዲናር በዓሣው ሆድ ውስጥ ተገኘ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ዱራታዎስንና ሚስቱን ቴዎብስታን እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ፣ ለባለ ዓሣውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ፡፡ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ እግዚአብሔር አስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን፣ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን አስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ፣ በኋለኛውም መንግሥተ ሰማያትን አጀጋጀላችሁ›› አላቸው፡፡
እነርሱም ይህን ነገር ሲሰሙ ደነገጡ፡፡ የከበረ ገናናው መልአክም ‹‹ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ፣ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ፡፡ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም›› አላቸው፡፡ ይህንንም ከነገራቸው በኋላ ወደ ሰማያት ወጣ፡፡ እነርሱም በፍርሃትና በክብር ሰገዱለት፡፡››
የመላእክት አለቃ ቅዱስ የሚካኤል ጥበቃው አይለየን! ከበዓሉ በረከት ይክፈለን!

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

20 Nov, 05:15


ለ እግዚአብሔር በሥጋ አያቱ ናት ለእመቤታችን ደግሞ እናቷ ናት ይህችው እናት ዛሬ የከበረ እረፍቷ ነው ።

የቅድስት ሐና በረከቷ ይደርብን ታላቅ በዓል ነው ከቅድስት ሐና እቅፍ እመቤታችን አለች ከእመቤታችን እቅፍ የዓለሙ መድኅን ክርስቶስ ኢየሱስ አለ! እንኳን አደረሳችሁ ተወዳጆች ! በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከእኛ ጋር ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን🙏


መልካም ቀን ይሁንልን🥰
#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

19 Nov, 09:25


"ፍቁር ክርስቶስ ሆይ ከሕዋሳትህ እንደ አንዱ አድርገኝ ... እንደ እግርህ...እንደ እጅህ...

ፍቅርህ ያዝለኛል  አንተን መዘከር ያቃጥለኛል ሁል ጊዜ ስራን ለመስራት ያነቃቃኛል አቤቱ ፍቅርህ በልቦናዬ ፈጥኖ አደረ በሰውነቴ ተሰራጨ ሕዋሳቴን ፀጥ አደረጋቸው።

አቤቱ ጌታዬ ሆይ ወዮልኝ። በፍቅርኽ መንደዴን የሚያበርድልኝ ማነው?... መወደድ ያለህ አቤቱ አንተን የሚወድኽ ንዑድ ነው እላለኁ። አንተን አይቶ የሚሰለች የለምና።"

አረጋዊ መንፈሳዊ

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

17 Nov, 18:20


የዶክተር አለማየሁ ዋሴ እመጓ መጽሐፍ በቅርብ ዘመን ከተጻፉ መጻሕፍት መሀከል በብዛት የተነበበና ከፍተኛ ተወዳጅነት ያገኘ መጽሐፍ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። የዚያኑ ያህል መጽሐፉ አወዛጋቢ ነገርም አላጣውም። መጽሐፉ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ታሪክ ነው ወይንስ ልቦለድ ከሚለው ጀምሮ መጽሐፉ ጥቆማ የሚሰጥበት የቅዱሱ ጽዋዕ በኢትዮጵያ መገኘት አሁንም ድረስ አፍላ አጀንዳ ነው። የአሁኑ ዳሰሳችን የሚመለከተው ይኼንን መጽሐፍ ነው። ተከታተሉ፤ አስተያየታችሁንም አጋሩን


https://youtu.be/Y1sFLZRDkVI?si=OUZ5QYLQsVO9fTnV



https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

16 Nov, 18:41


"ቤታቸውን ገነት ያደረጉ ቤተሰቦች ገነትንም ቤታቸው እንደምያደርጓት እሙን ነው።"

ሰባኪው ዲሜጥሮስ ፓናጎፖውሎስ

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

16 Nov, 05:43


እመቤቴ ሆይ ልጅሽን እንዴት እንደምንወደው አስተምሪን ከአንቺ በላይ እርሱን የሚወድ የለምና...

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

15 Nov, 13:23


በቅዳሴ ሰአት የግል ጸሎት ማድረግን በተመለከተ ቤተክርስቲያን ምን ትላለች?

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

14 Nov, 16:26


ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ብዛት ያስረዳል፤ በባልንጀሮቹ ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል፣ የምቀኝነቱን ጽናት አስረዳ፡፡ 

ወዳጁን ተሠውሮ የሚመክር ሰው ብልህ ባለመድኃኒት ነው:: ያ እንዳዳነው መክሮ አስተምሮ ያድነዋልና፡፡ ወንድሙን በብዙ ሰው ፊት የሚያመሰግነው ሰው እሱ እውነተኛ ጠላቱ ነው፣ በውዳሴ ከንቱ ይጎዳ ብሎ ነውና።

ኀዘን ያለበት የርሕራሄ ምልክቱ የበደሉትን ሁሉ ይቅር ማለት ነው። የጠማማ ምልክቱ ጸብ ክርክር ነው፡፡ ወደ ክብር የሚያደርስ ረብህ ጥቅም ያግኝ ብሎ የሚመክር፣ የሚያስተምር በፍቅር ይመክረዋል፣ ያስተምረዋል፡፡ ቂም በቀል የሚሻ ሰው ፍቅር የለውም፡፡ አንድም እበቀለዋለሁ ብሎ የሚመክር ከፍቅር የተለየ ነው፡፡

ስሙ ይክበርና እግዚአብሔር በፍቅር ይመክራል፣ ያስተምራል፣ እበቀላለሁ ብሎ ያይደል፡፡ እሱስ በምሳሌው የተፈጠረው ሰውን ለማዳን ይገሥጻል፡፡ አንድ ጊዜስ እንኳን ቂም አይዝም፣ መዓትን አያዘጋጅም፡፡ የፍቅር ሥራ ይህች ናት፣ በቅንነት ትገኛለች ቂም ለመያዝ እበቀላለሁ አትልም፣ በፍቅር ሰውን መናገር ነው።

ብልህ የሚሆን ቅን ሰው ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ይመስለዋል፡፡ ሰውን ክፉ ስላደረገ እበቀለዋለሁ ብሎ አይገሥጸውም፣ ሊመክረው ወዶ ነው እንጂ ሌሎችንም ለማስፈራት ነው እንጂ። ተግሣጽስ በፍቅር ካልሆነ ተግሣጽ አይባልም፡፡

#ማር_ይስሐቅ

#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ
#ዲያቆን_ሞገስ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

14 Nov, 05:22


ለጆሮ👂 ቁርስ ትሆነን ዘንድ እነሆ ተጋበዙልኝ 🤗🤗🤗

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

13 Nov, 10:50


ፈውስ እና ድኅነት

በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

13 Nov, 10:18


☝️ሃሳቡን በዚች ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ ሃሳብ እንጠቅልለው 🤗

እዚህ ጉዳይ ላይ ጥያቄ ያለው ካለ ኮመንቷ ላይ አስፍሩ👇

በቸር ዋሉልኝ🙏
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

12 Nov, 19:12


''አንዳንዶች ኢትዮጵያ ምድረ ገነት ናት ይላሉ ኢትዮጵያ ገነት ከሆነችማ መፆሙ መፀለዩ ምን አስፈለገ እየኖርንባትም አይደለ ጎበዝ 😁 ''

ምን ይባላልም ጭራሽ በመጨረሻው ዘመን ከሌሎች ሃገራት ወደኢትዮጵያ ይፈልሳሉ ይከማቻሉ ይሉናል 🤭

ኑሮ ሳይወደድ በፊት ነበረ አሁን ግን እንጃ እዚም ያለው መሮታል እንኳን እነሱ ሊመጡ ሳስበው🤔 😂😂😂😂😂

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

12 Nov, 14:23


ለአንዲት ሃገር በተሰጠን ቃልኪዳን መሰረት ሰው ሁሉ ምንም ባይሰራም ይድናል ሃገርም ይጠበቃል የሚል ሃሳብ በቀን ውሎዬ ላይ የሚያንፀባርቁ ሰዎች አጋጥመውኝ ነበረ ታድያ ይህ በጣም ከባድ እሳቤ ነው ካለንበትም ጥፋት ወጥተን ወደንፅህና ከፍ እዳንል የሚጎትተን የቃልኪዳኑ ምንነት ወደሰማያዊ ህይወት የሚያቀናን ሳይሆን ለዚሁ ምድራዊ ህይወት ብቻ እንድናስብ የሚያረገን ማነቆ የሆነ ሃሳብ ነው ይህ ሃሳብ ብዙሃኑ ዘንድ የሚታሰብ ከሆነ ጥቂት ነገሮችን እንበልበት!

በተሰጠን ቃልኪዳን ብቻ መዳን አይቻልም ያንን ቃልኪዳን አሜን ብሎ በመቀበል ውስጥ እንጂ ከሚጠቀሱት ውስጥም ምሳሌ

ኢትዮጵያ የቃልኪዳን ሃገር ናት አትጠፋም የሚሉ ይኖራሉ ! የቃልኪዳን ሃገር ብትሆንም ቃልኪዳኑን የሚፈፅሙ ህዝቦች ከሌሉ ግን አትጠፋም ብሎ መናገር አይቻልም ቃልኪዳኑ ሚኖረው ተቀብሎ በሚኖረው ምዕመን ዘንድ ስለሆነ ኢትዮጵያ የተባሉትም ህዝቦቿ ናቸው እንጂ ሳር እና ቅጠሉ ስላልሆነ ቃልኪዳኑ ሚኖረው ከሚኖረው ህዝብ ጋር ነው ማለት ነው!


ከአባቶች የተሰጠ ሃሳብ ደሞ እነሆ🤗🤗


ለቅዱሳን የተሰጠ ቃልኪዳን ለመዳናችን ያለው አስተዋጽኦ


#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

ጥያቄ ካለ ከስር ኮመንት መስጫ ላይ አስፍሩ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

12 Nov, 08:47


እንዲህ በፍቅር ያዝሁሽ በጣቶቼ አይደለም በሀይማኖት ያዝሁሽ በመዳሰስ አይደል በእደ ህሊና ያዝሁሽ በእደ ስጋ አይደል።
እደ ህሊናዬን ግን የሰው ሀይለኝነት ሊያስተወው አይችልምና።የሰይፍ ስለትም ሊቆርጠው አይችልም።

ልትደግፊኝ ያዝኩሽ ልትጥይኝ ግን አይደለም ወደላይ ከፍ ከፍ ልታደርጊኝ ያዝሁሽ ወደ ታች ልታወርጂኝ ግን አይደለም።

ለዘለዓለሙ ያዝሁሽ ለእድሜ ልክ ብቻ አይደለም።እናቴ ሆይ ነብሴ ባንቺ ዘንድ ትክበር ስለ ቸርነትሽም እመቤቴ ነሽ ስለ ፍቅርሽ የታመንሽ ስለ ልጅሽም የመድሀኒት ቀንድ ሆይ አስቢኝ እንደወደቅሁ እቀር ዘንድ አትርሺኝ።

📖አርጋኖን ዘሠሉስ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

11 Nov, 10:31


https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

11 Nov, 08:58


አንድ አንድ ሰው የሃይማኖት መርኆ የሚቀርጸው ከዕቅበተ እምነት እና መናፍቃንን ከማሳፈር ወይም ከመብለጥ አንጻር ብቻ ሲኾን ጥልቅ ለኾነው ኦርቶዶክሳዊ ነገረ መለኮት ዓለምን መፈተሽ ለሚያስችለው ኦርቶዶክሳዊ ንጻሬ ዓለም ደንታ የሌለው ይኾናል። የእንደዚኽ አይነቱ ሰው የኹል ጊዜ ፍላጎት ነገር ኮሽ በማይልበት ቤተ ክርስቲያን መኖርን መናፍቃኑን ማስቀናት ነው። ተባብሮ የውጭ ጠላት እንደማሳፈር እንደ ደላው ሰው በውስጥ ተዋስዖ ማድረግን እንደ ቅብጠት ይቆጥረዋል። ይህ ሰው ቤተ ክርስቲያን በዘመናት እንዴት እውነትን ከሀሰት እየለየች እንደተሻገረች የገባው አይመስልም። በዚህ ምክንያት በውስጥ የሚደረግን ተዋስዖ አጥብቆ ይጸየፋል።

ሌላኛው አይነት ሰው ደግሞ ስለ ትክክለኝነቱ ከመጨነቅ ይልቅ ተያያዥ ጉዳዮች ያሳስቡታል። የግል ጉዳዩ የሚወደው ሰባኬ ወንጌል ዘመዱ የኾነ ጳጳስ ወይም ያስቀጠረው ጳጳስ... ወ.ዘ.ተ ቀስፎ ስለሚይዘው የውስጥ ተዋስዖን ይጸየፋል።

ከዚህ ውጭ የኾነው እምነቱን በመጠየቁ የሚያጣው የሚመስለው የእምነቱን ጉዳይ ለተወሰኑ ሰዎች ሰጥቶ እነሱን እያመነ መኖር የሚፈልግ ሰነፍ ሰው ነው። አብዛኛው ሰው የእምነት ፍርሃት አለበት። ለዚህ ማሳያው የምንዘምራቸው መዝሙራት ሳይቀሩ "አንተ ባታውቅም ኦርቶዶክስ መልስ አላት" የሚል አሳብ ያላቸው ናቸው። ለእንደዚህ ዓይነት ሰው በውስጥ የሚደረግ ተዋስዖ ስጋት ነው።

ውስጣዊ ተዋስዖ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ አካል አይደለምን?
እንደ ተለመደው አሳብ አስተያየት ትለመናላችኹ።
ኤማሁሳውያኑ በመንገድ እንዲኽ ተወያዩበት


ኢዮብ ወንድወሠን

https://youtu.be/VYm1SakDhR8?si=lDnLABDv8OcolyqA



https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

08 Nov, 17:46


ዮሐንስ 6
⁶⁸ ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን?

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

07 Nov, 11:21


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

07 Nov, 11:20


አማኑኤል ማለት:- እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ (እግዚአብሔር ምስሌነ) ማለት ነው።
እግዚአብሔር በአካል ከፍጥረቱ ተለይቶ አያውቅም። እርሱ በአካል የሌለበት ቦታ የለምና።
👉  በረድኤትም በብሉይኪዳን ከቅዱሳን አበው፣ ከቅዱሳን ነቢያትና፣ ከቅዱሳን ነገሥታት ጋር ነበር።

🔰 ይህኛው "ምስሌነ" ግን አነጋገሩ ከረድኤት የተለየ "ምስሌነ" ነው። በረድኤት ከእኛ ጋር መኖርን ብቻ የሚገልጽ አይደለም።

🔰 የእኛን ሥጋ ተዋሕዶ ከእኛ ጋር መኖሩንም የሚገልጽ አነጋገር ነው። አማኑኤል የሚለው ስም ስመ ሥጋዌውን የሚገልጽ ስም ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን እንደ እኛሰው ሆኖ ክሦ፣ ቤዛ ሆኖ አድኖናል።

እንግዲህ ምንንም፣ ማንንም አንፈራም። የሚያስፈራን ነገር የለም። ምክንያቱም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው።💪

“እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?”
  — መዝሙር 27፥1

አማኑኤል (28)

እንኳን አደረሳችሁ ተወዳጆች🙏
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

06 Nov, 03:58


🔴 አዲስ ዝማሬ " ኢየሱስ ጥዑመ ስም " ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም መሠረተ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት @-m...
https://youtube.com/watch?v=N1jP92OAfqI&si=AjCHDTwCqzVFGxe1


https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

06 Nov, 03:58


ኢየሱስ ጥዑመ ስም

https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

05 Nov, 17:22


" ቅጥሩም ወደቀ።”
— ኢያሱ 6፥20

የኢያሪኮን ቅጥር በእግዚአብሔር ታቦት እንዳፈረሱት ሰማሁ እኔም ከኢያሪኮ ግንብ የገዘፈ ኀጢአቴን ያፈርስልኝ ዘንድ በማስተዋል ወደ አዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ወጣሁ።

🫴እንኳን ፍቅር ለሆነው ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓል በሰላም ዓደረሳችሁ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

02 Nov, 06:34


ትክክለኛው አገልግሎት እዴት ያለው ነው?

ለእግዚአብሔር መስራት ነው ወይስ ከእግዚአብሔር ጋር መስራት 🤔

ራሳችንን እንፈትሽበት ሰሚ ጆሮ አስተዋይ ልቡና ያድለን ወደትምህርቱ 🤗


#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድግ_አትዘንጉ👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

02 Nov, 06:29


🔴አዲስ ስብከት 🔴 "ከእግዚአብሔር ጋር መስራት "መ/ር ብርሀኑ አድማስ @TemroMedia
https://youtube.com/watch?v=Em-5OexgwKs&si=-dfhIbiwro_IQ2Xq


https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

01 Nov, 11:02


ሰው የገዛ ሞባይሉ ቢጠፋ ቤቱን ሙሉ በሙሉ ገለባብጦ ነው የሚፈልገው። እግዚአብሔርን ሳናገኝ ግን ውለን እናድራለን። እግዚአብሔርን በማጣታችን ነፍሳችን ደግሞ ጥያቄዋ አያርፍም። ሁልጊዜ ሰው አይረካም፤ ስለማይረካም ነው ይገላል ይቀማል፤ ተሹሞ መሾም ይፈልጋል፤ አግብቶ ማግባት ይፈልጋል፤ ይዞ መያዝ ይፈልጋል። ሰው ለምንድነው ልቡ የማያርፍለት ካላችሁኝ የልብ ማረፊያው እግዚአብሔር ስለሆነ ነው።

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

31 Oct, 20:26


በትረ ማርያም አበባው

https://t.me/orthodoxzelalemawit

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

31 Oct, 18:03


☝️ተዋሕዶ በተዓቅቦ?

#ነገረ #ክርስቶስ #ትምህርት #ላይ #መዘንጋት #የሌለባቸው #ጉዳዮች
፩. አምላክ ሰው የሆነው ሰውን ለማዳን ነው። ለሰው ልጆች ያለው ጥልቅ ፍቅሩን የገለጠበት ነው ሥጋዌ።

፪. አምላክ እንዴት ሰው ሆነ? የሚለውን አለማወቅ ይጎዳል። እንዴት ሰው ሆነ በሚለው ከብዙ ቤተ እምነቶች ጋር የምንለያይበት ስለሆነ ጠንቅቆ ማወቅ መልካም ነው። እንዴት ሰው ሆነ?
ሀ. እንበለ ውላጤ
ለ. እንበለ ሚጠት
ሐ. እንበለ ኅድረት
መ. እንበለ ምትሐት
ሠ. እንበለ ቱሳሔ
ረ. እንበለ ፍልጠት
ቀ. እንበለ ቡዓዴ
በ. እንበለ ትድምርት
ተ. እንበለ ምንታዌ
ነ. በተዋሕዶ በተዓቅቦ
ነው። እኒህን አለመለየት ከክሕደት አዘቅት ያስገባል። አምላክ ሰው ሲሆን ከአምላክነቱ ተለውጦ ወደሰውነት ተቀይሮ አይደለም። አምላክ ሰው ሲሆን ሰው አምላክ ሆኗል። ሰው አምላክ ሲሆን ከሰውነቱ ተለውጦ ወደ አምላክነቱ ተቀይሮ አይደለም። "ወኢተወለጠ ህላዌ ቃል ኀበ ህላዌ ትስብእት ወኢህላዌ ትስብእት ኀበ ህላዌ ቃል። ዳእሙ ይሄልዉ ክልኤቱ ህላዌያት በበህላዌሆሙ እንበለ ውላጤ" እንዲል (ሃይ.አበ.፵፫፣፭)። በተጨማሪም ሃይ.አበ.36 ላይ "ኢያፍለሰ ፈጣሪ መለኮቶ ለከዊነ ፍጡር። ፈጣሪ ባሕርይውን ፍጡር ወደመሆን አልለወጠውም። ወኢደምሰሰ ትስብእቶ ፍጡረ ለከዊነ ፈጣሪ። የተፈጠረ ሥጋንም ፈጣሪ ወደመሆን አልለወጠውም" ተብሎ ተገልጿል። በተዋሕዶ ሰው ወደ አምላክነት አምላክ ወደ ሰውነት አልተለወጠም። እንበለ ውላጤ መባሉ ለዚህ ነው። ሰውነት ተለውጦ አምላክ ብቻ ሆኗል፣ ክርስቶስን አምላክ ብቻ፣ ረቂቅ ብቻ፣ ምሉእ ብቻ ይባላል ካሉ መለኮት ሥጋን ውጦታል የሚል የአውጣኪ ክሕደት ነው። ክርስቶስን ሰው ብቻ፣ ግዙፍ ብቻ፣ ውስን ብቻ ይባላል ካሉ ይህ የእስልምና ክሕደት ነው። አካልን አዋሕደው ባሕርይን ካላዋሐዱ የካቶሊካውያን፣ የመለካውያን ኦርቶዶክሶች (የግሪክ፣ የሩሲያ፣ የዩክሬንና የመሳሰሉት) ክሕደት ነው። አምላክ ሰው ሲሆን ወደሰውነት ተለውጧል ካሉ የሐራ ጥቃ ክሕደት ነው። አምላክ በሥጋ አደረ የሚለውን ይዘው ኅድረት ካሉ የጳውሎስ ሳምሳጢ ክሕደት ነው። አምላክ ሰው መስሎ ታየ እንጂ ሰው አልሆነም ካሉ የማኒ ክሕደት ነው። ከተዋሕዶ በኋላ ክርስቶስ የሠራውን ሥራ እየለያዩ ይህ የሥጋ ሥራ ነው፣ ይህ የመለኮት ሥራ ነው እያሉ መለያየትም ክሕደት ነው። ከተዋሕዶ በኋላ ያለው ሥራ የተዋሕዶ ሥራ ነው። ከተዋሕዶ በኋላ ያለ አካል የተዋሕዶ አካል ነው። ከተዋሕዶ በኋላ ያለ ባሕርይ የተዋሕዶ ባሕርይ ነው። ኀደረ፣ ደመረ የሚሉት ቃላት እንደ ጊዜ ግብሩ ተዋሐደ ተብለውም ሊተረጎሙ ይችላሉ። ኩሉ መለኮቱ ኀደረ በሥጋ ሰብእ ሲል ተዋሕዶን ያመለክታል። ነአምን ከመ ተደመረ ኩለንታሁኬ ለቃል ወኩለንታሁ ለትስብእት ሲል ተዋሕዶን ያመለክታል።

የእኛ አስተምህሮ ተዋሕዶ በተዓቅቦ ነው። ፍጹም አንድነት ያለመለወጥ ነው። ተዓቅቦን የዘነጋ ተዋሕዶ ውላጤ ነው። ተዋሕዶን የዘነጋ ተዓቅቦ ምንታዌ ነው። ሥጋ አካሉን፣ ባሕርዩን፣ ግብረ ባሕርይውን እንደያዘ ሳይለውጥ የቃልን አካሉን፣ ባሕርዩን፣ ግብረ ባሕርዩን ገንዘብ አደረገ። ቃልም አካሉን፣ ባሕርይውን (ከዊኑን)፣ ግብረ ባሕርይውን ሳይለቅ ባሕርይውን እንደያዘ ሳይለውጥ የሥጋን አካሉን ባሕርይውን፣ ግብረ ባሕርይውን፣ ባሕርይውን ገንዘብ አደረገ። መምህረ ዓለም ቅዱስ ቄርሎስ እንቲኣሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ወእንቲኣሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል ያለው ይህንን ነው።


በትረ ማርያም አበባው

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

31 Oct, 14:04


👉ማታ በሌላ ትምህርት እንመለሳለን እስከዛ በነዚህ ጥያቄዎች ስለሚቀሉ ፈታበሉልኝ🤭

ያላችሁ ሃሳብ ካለ በኮመንቷ ኮምቱልን😁🤜

ተሳትፎዋችሁን በሪያክት እንየው እስቲ😉 👇👇

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

30 Oct, 09:40


የነፍሴ ጥያቄ | ኦርቶዶክስ ማለት ምን ማለት ነው? | ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ | ክፍል 1
https://youtube.com/watch?v=8_uZ3f26oEI&si=uPzXRzEi9idqIaUQ


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

29 Oct, 17:39


የቀድሞ ኒቂያ ከተማ መገኞዋ ቦታ በአሁኑ☝️☝️☝️

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

29 Oct, 17:38


ኦርቶዶክሳዊ ዕይታ (አዕምሮ) ሚለውን ለመረዳት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ማለት ምን ማለት ነው ሚለውን እንመልከት 👀

ኦርቶዶክስ  :- የግሪክ ቃል ነው በሁለት ተከፍሎ ይነገራል ይህም ''ኦርቶ'':- ማለት ቀጥተኛ ትክክለኛ ማለት ነው ። ''ዶክስ'':- ማለት ዕምነት ፣ ሃይማኖት ፣ አስተምህሮ ማለት ነው።
ኦርቶዶክስ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ለመጠሪያነት የዋለው በ 325 ዓ.ም በኒቂያ ጉባኤ በአሁኗ (ቱርክ:-ኢዝኒክ) ከተማ ነው ። የታሪኩ ዋና መነሾ የአሪዮስ የኑፋቄ ትምህርት ቤተክርስትያንን ክፉኛ አውኳት ስለነበረ 318 ቱ ሊቃውንት ቅዱሳን አበው በመንፈስ ቅዱስ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ  በመሆን አሪዮስን አውግዘው ጥያቄ በተነሳባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ለማስረዳት ቅዱስ አትናቴዎስና ሌሎቹም ቅዱሳን አባቶች የቤተክርስትያንን እምነትና አስተምህሮ የሚገልፅ የሃይማኖት አንቀፅ አዘጋጅተው አፅድቀዋል። በዚህም ትክክለኛ ዕምነት (አስተምህሮ) ያሏት ክርስትያኖች ኦርቶዶክስ ናት በማለት ጠርተዋል ማለት ነው።

ተዋሕዶ:- ከልሣነ ግዕዝ የመነጨ ቃል ነው ። ትርጉሙም 👉'' አንድ መሆን'' ማለት ነው። ምስጢራዊ ፍቹ ግን ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕሪይ አንድ ባሕሪይ የመሆን ምስጢር ነው።
👉ሁለት አካል የተባለው አካለ መለኮት እና አካለ ሥጋ ናቸው
👉 ሁለቱ ባሕሪያት የተባሉት ባሕሪየ መለኮትና ባሕርየ ሥጋ ናቸው።

ታድያ ክርስቶስ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕሪይ አንድ ባሕሪይ ተዋሕዶ በተዓቅቦ ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው ነው። ተዓቅቦ ማለት :- በመጠባበቅ ማለት ማለትም አንዱ አንዱን ሳያጠፋው ማለት ነው ለምሳሌ ሙሴ በሲና ያያትን እፀ ጳጦስ መውሰድ ይቻላል። ይህም ስያሜ የተሰጠው በ 431ዓ.ም ከካቶሊካውያን 2 ባሕሪ ትምህርት በሃላ እደተሰጠ ሊቃውንት ይናገራሉ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

28 Oct, 04:59


ነገረ አበው

ዲ/ን አቤል : ካሳሁን

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

28 Oct, 04:41


የክርስቶስ ትምህርት እና ቤተ ክርስቲያን
https://youtube.com/watch?v=zSJssv5v8eY&si=zII5Im5y-gC2ReB-

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

27 Oct, 05:15


በእሁዱ ቅዳሴ መግቢያ ላይ በህብረት የምትዜመዋ የቅዳሴ ዜማ ☝️ እዴት ያለ ምታፅናና ቃል ናት

“ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።” ያዕቆብ 5፥11

አምላከ ቅዱሳን ከሰንበት ረድኤት ይክፈለን🤲

👇ከፅጌሬዳዋም እየቀጠፋችሁ ውሰዱ ለዛሬ😁
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

26 Oct, 06:14


Bekedaseyachen | "በቅዳሴያችን" ዘማሪ ቀሲስ እስክንድር ወልደማርያም
https://youtube.com/watch?v=18k72Z8d6Sg&si=XziR6CZLJ0n8iSU5


አዳምምጡዋት የጠዋት የጆሮ ቁርስ ችያለሁ 😁🤗🤗🤗🤗🤗

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

25 Oct, 18:32


በየርእሱ የተከፋፈለ የአባቶች ትምህርት ነው

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

25 Oct, 13:51


             †             
[ ኦርቶዶክሳዊ እይታ ምልከታ ማለት !

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

25 Oct, 05:53


ልክ እንደዚህ የተለያዩ አባቶችን ሕይወት እና ትምህርት ላይ የተጻፉ መጽሐፎች አሉ ከእነዚህ ጀምሩ እና ሌሎቹንም እየገዛችሁ አንብቡ pdf እንለቃለን ሌሎች ፅሁፎችንም እናተ ለሌሎች ተደራሽ እያረጋችሁም ጠብቁ🙏

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

25 Oct, 05:45


ክርስትናን በትክክል ለመረዳት፣የክርስቶስን ቤተክርስቲያን ለማወቅ እና በዛች ቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ለመኖር እነዚህ ነገሮች ያስፈልጋሉ።

   1. Mind of the church(phranema)
   2.patristic view
   3. reading with the apostolic fathers

   4. Reading with the church

እነዚህ አገላለጾች ሁሉም አንድን ነገር ያሳያሉ እሱም "ኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ" ይሄንን ኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ ለማግኘት እና በዛ መነጽር ነገሮችን ለማየት እና ለመረዳት ደግሞ ሐዋርያዊ የሆኑ አባቶች አስተሳሰብን ማወቅ እና መረዳት የግድ ነው። አስተሳሰባችን ኦርቶዶክሳዊ ሲሆን ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን ህይወት እና ቅዱሳት መጻሕፍትን እንረዳለን መለኪያ እና ሚዛንም ይሆነናል። እውነተኛውን ከሃሰተኛው ለመለየት አንቸገርም ግራም አንጋባም በስሜትም አንመራም ስለዚህ አባቶቻችንን ማወቅ አለብን።

“የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።”
    ዕብራውያን 13፥7

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ከተገኙ ብታነቡ መፀሐፍት📖 ጥቆማ👇

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

24 Oct, 17:22


ብርና ወርቅ ሳይዙ | Birrna Werk Sayzu |@zemare_yared
https://youtube.com/watch?v=ttokrvzH8iQ&si=tC1C9vKY_yNKH7rB


ለሰጣችሁን በጎ አስተያየት እያመሰገንን ተጋበዙልን ብለናል 🤗🤗🤗

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

24 Oct, 04:44


☝️የቀጠለ.......

ለመሠረታዊ ትምህርተ ሃይማኖት "በዋናነት" የሚጠቀሱ አባቶች

1.ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ (50-117 ዓ.ም) :- የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀመዝሙር የነበረ፣ የአንጾኪያ ቤተክርስቲያን 3ተኛው ጳጳስ ነበር ከጴጥሮስ እና ከኢቮዲየስ ቀጥሎ

2.ቅዱስ ፖሊካርፐስ (69-156 ዓ.ም) የነበረ አባት ነው ከቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ዘአንበሳ ጋር ባለንጀራ ነበሩ ቅዱስ ፖሊካርፐስም የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀመዝሙር ነበር

3.ቅዱስ ሄሬኔዎስ:- የቅዱስ ፖሊካርፕ ደቀመዝሙር ነበር(130 ዓ.ም ወይም 142- 202 ዓ.ም)

4.ቅዱስ ቆጵርያኖስ ሰማዕት (St. Cyprian of carthage) ከ200 - 258 ዓ.ም

5.ቅዱስ አቡሊዲስ (170 -236 ዓ.ም )

6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ(298 - 373 ዓ.ም)

7.ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም( 315 - 386 ዓ.ም)

8.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ (330 - 379 ዓ.ም)

9.ቅዱስ ጎርጎሪዮስ ዘእንዚናዙ(329 - 390 ዓ.ም)

10.ቅዱስ ጎርጎሪዮስ ዘኑሲስ (330 - 395 ዓ.ም)

11.ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ(347 - 407 ዓ.ም)

12.ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ( 315 - 403 ዓ.ም)

13.ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ (376 - 444 ዓ.ም)

14.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ( 459 - 538 ዓ.ም)

15.ቅዱስ ያሬድ (505 - 571 ዓ.ም)

(መድሎተ ጽድቅ ፣ ቅጽ 1 ፣ ዱያቆን ያረጋል አበጋዝ )

"የከበሩ የአባቶቻችን ልጆች ልትሆኑ ከወደዳችሁስ እነርሱ የጻፉትን እንጂ ምንም ምን ሌላ አትመኑ"

       ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

23 Oct, 13:00


☝️የቀጠለ......

"የሐዋርያነ አበው" ዘመን የሚባለው ከ70 ዓ.እ(AD)-160 ዓ.እ(AD) ያለው ነው። (ዓ.እ:- ዓመተ እግዚእ)

በመስኩ ጥናት ያደረጉ ሊቃውንት እንዲሁም የቤተክርስቲያን የታሪክ መጻሕፍት እንደሚናገሩት በዚህ ዘመን ከሚመደቡት አበው ውስጥ:-

* ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም(St. Clement of Rome)

*ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ (St. Ignatius of Antioch )

*ቅዱስ ፖሊካርፐስ ዘሰርምኔስ(St. Polycarp of Smyrna)

*ፓፒያስ ሊቀ ጳጳሳት ዘሄራሊስ (Papias of Hierapolis)

*በርናባስ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ)

* ሔርማ ኖላዊ( Hermas the shepherd) ይገኙበታል።

እነዚህ ሐዋርያውያን አበው በተለያየ አገር የኖሩ ይሁኑ እንጂ በመልእክቶቻቸው ያንጸባረቁት አስተምህሮት ግን ተመሳሳይ እና ከአንድ ምንጭ የተቀዳ ነው። ይህም ነገር የቤተክርስቲያንን ኩላዊነት/Catholicity/ የሚያሳይ ቀዳማዊ ማስረጃ ነው።

📖(አባቶችህን እወቅ(ነገረ አበው) ፣ ዲያቆን አቤል ካሳሁን)

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

23 Oct, 05:58


ነገረ አበው (Patrology) 


ክፍል አንድ


"Patrology" የሚለው ቃል "pater" ከሚለው የመጣ ሲሆን "አባቶችን ማጥናት" ማለት ነው። በአጠቃላይ ይህ የሥነ መለኮት ዘርፍ የሚያጠናው ስለ አባቶች ሕይወት እና ትምህርት ነው።

  
የቤተ ክርስቲያንን አባቶች በምን እናውቃለን?

አንድ አባት የቤተ ክርስቲያን አባት ለመባል የሚከተሉትን መሥፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።

1. ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ሊኖረው ይገባል
2. የቅድስና ሕይወት ሊኖረው ይገባል
3. የቤተ ክርስቲያንን ማረጋገጫ ማግኘት ይኖርበታል

 
የቤተ ክርስቲያን ሐኪሞች

እነዚህ ከቤተ ክርስቲያን አባቶች ውስጥ በቅድስናቸው ቤተ ክርስቲያንን ከመናፍቃን በመጠበቅ አና በሌሎች ነገሮች ከሌሎች የጎሉ ናቸው። እነዚህም ቅዱስ ባስልዮስ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ፣ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ወዘተ ይጠቀሳሉ።

 
የነገረ አበው ጥቅም አና ዓላማ

ነገረ አበውን ማጥናት ዋነኛው ጥቅሙ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ለመረዳት ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ አባቶች የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ምንጭ ስለሆኑ ነው።

ዓላማው ደግሞ እነዚህን አባቶች በማጥናት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት መረዳት አና ከቅድስና ሕይወታቸው ለመማር ነው።
 
የነገረ አበው ትምህርት ክፍፍል

የመጀመርያው የነገረ አበው ትምህርት በቋንቋ ሊከፋፈል ይችላል። ይህም የጽርዕ፣ የላቲን፣ የሱርስት፣ የቅብጥ፣ የግእዝ ወዘተ እያልን መከፋፈል እንችላለን።

ሁለተኛው እከፋፈል በዘመን ሲሆን የመጀመሪያዎቹ ማለትም ፩ኛ እና ፪ኛ መቶ ክፍለ ዘመን አባቶች፣ የወርቃማው ዘመን አባቶች፣ የኋለኛው ዘመን አባቶች ተብለው ይከፈላሉ።

አስቀድመን ግን ወደ ነገረ አበው ትምህርት በደንብ ከመግባታችን በፊት ስለ ቤተ ክርስቲያን ባሕርያት ማወቅ ይኖርብናል።
• ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት፤ ማለትም ክርስቶስን ያመኑ እና በጥምቀት የተባበሩ ሁሉ አንድ ናቸው።
•  ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ናት፤ ማለትም የክርስቶስ አካል ስለሆነች ንጽሕት ቅድስት ናት።
•  ቤተ ክርስቲያን ኩላዊት ናት፥ ማለትም የመሬት አቀማመጥ፣ ቋንቋ ወይም ብሔር አይገድባትም።
•  ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት ናት፤ ማለትም ሐዋርያዊ እምነት አላት።


የቤተ ክርስቲያን መከፋፈል

ከጉባኤ ኤፌሶን በኋላ (431 ዓም) Assyrian Church of the East, The East Syrian Church እና Chaldean Church of the East የንስጥሮስን ትምህርት እንቀበላለን በማለት ከቤተ ክርስቲያን ወጡ።

ከጉባኤ ኬልቄዶን በኋላ (451 ዓም) ኬልቄዶናውያን የሆኑ እና ኬልቄዶናውያን ያልሆኑ በመባል በድጋሚ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ተከፍላለች።

በድጋሚ በ1054 ዓ.ም በኬልቄዶናውያን መካከል የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን (Eastern Orthodox) በመባል ለሁለት ተከፍለዋል። ይህም መከፋፈል "The Great Schism" በመባል ይታወቃል።


Oriental Orthodox vs Eastern Orthodox

Oriental Orthodox የምንላቸው አብያተ ክርስቲያናት የኬልቄዶንን ነገረ መለኮት (ማለትም የሁለት ባሕርይ ትምህርትን) የማይቀበሉ የቅዱስ ቄርሎስን የአንድ ባሕርይ ትምህርትን የሚቀበሉ ናቸው። እነዚህም the Coptic Orthodox Church of Alexandria፣ the Syriac Orthodox Church of Antioch፣ the Malankara Orthodox Syrian Church፣ the Armenian Apostolic Church፣ the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church እና the Eritrean Orthodox Tewahedo Church ናቸው።

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

22 Oct, 17:25


ከእርሱ ጋር ኀብረት ፍጠሩ!

እግዚአብሔርን ለማወቅ ለመውደድ ከእርሱ ጋር መተባበር አለባችሁ። ንባብ ብቻውን በቂ አይደለም። ንባብ የሚከፍትላችሁ መዝጊያውን ብቻ ነው። ከዚህ በኋላ እናንተ ትገቡና ከእግዚአብሔር ጋር ትኖራላችሁ ከዚያም ከእርሱ ጋር መኖር ጣፋጭ መሆኑን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።

ስለሆነም ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን ሕይወትን ትሞክሩታላችሁ እርሱ በሁሉም ነገር ውስጥ ተካፋይ እንዲሆንም ትፈቅዳላችሁ።

እንደ ባልጀራችሁ አድርጋችሁ ልትወዱት ሞክሩ አሳቦቻችሁንና ሚስጥሮቻችሁን ለእርሱ ንገሩት። ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ጠብቁና እርሱ ምን ያህል ከእናንተና ለእናንተ እንደሚሰራ ታያላችሁ። ከዚህ በተጨማሪ በአሳቦቻችሁና በተሰጥኦዎቻችሁ ከመተማመን የበለጠ በእርሱ ላይ መተማመንን ታውቃላችሁ።

[ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ]

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

22 Oct, 07:05


"When a bad or gloomy thought, fear or temptation threatens to afflict you, don’t fight it to try and get rid of it. Open your arms to Christ’s Love and He will embrace you, then it will vanish by itself.”

+ St Porphyrios of Kavsokalyvia

"መጥፎ ወይም ጨለምተኛ ሀሳብ፣ ፍርሃት ወይም ፈተና ሊያስጨንቅህ በሚችልበት ጊዜ፣ እሱን ለማስወገድ አትዋጋው፣ እጆቻችሁን ለክርስቶስ ፍቅር ክፈቱ እና እሱ ያቅፋችኋል፣ ያኔ በራሱ ይጠፋል።"

+ የካቭሶካሊቪያ ቅዱስ ፖርፊሪዮስ

“ ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤”2ኛ ጢሞ 2፥8
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

21 Oct, 17:40


ሰላም የችግሮች አለመኖር ሳይሆን በፈተናዎች(በችግሮች) ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር የመሆን ውጤት ነው።

እግዚአብሔር የሚሰጠውን ሰላም የትኛውም ኃይል ሊወስደው አይችልም!

ዲ/ን አቤል ካሳሁን

“ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” ዮሐንስ 14፥27
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

21 Oct, 06:52


ሕማሜን በሕማምህ አድን፤ በቁስልህም ቁስሌን ፈውስ፡፡ ደሜን ከደምህ ጨምር፤ ሕይወት የሆነ የቅዱስ ሥጋህን መዓዛም በሥጋዬ ጨምር፤ በጠላቶች /በአይሁድ/የጠጣሃው ከርቤም ክፉ ሐሞትን የጠጣች ነፍሴን ያጣፍጣት፡፡ በሰፊው መስቀል ላይ የተዘረጋው ሥጋህም ሕሊናዬን ወደ አንተ ያድርገው:: በጠላት /በዲያብሎስ ድል ተነስቻለሁና። በመስቀል ላይ የዋለው ራስህ በርኩሳን ዘንድ የተቀጠቀጠ ራሴን ከፍ ያደርገው፡፡ በከሀድያን የተቸነከሩ ቅዱሳት እጆችህም ወደ አንተ ይንጠቁኝ፡፡

በወንጀለኞች ምራቅንና ጉስቁልናን የተቀበለ ፊትህ በኃጢአት የጐሰቆለ ፊቴን ያብራልኝ፡፡ የተሰቀለች ሰውነትህም ወደ አባትህ ዐረገች:: ጸጋህም ወደ አንተ ታድርሰኝ፡፡ አቤቱ ለመማጸን ዕንባ የለኝም፡፡ ለመለመንም ያዘነ ልብ የለኝም፡፡ ልጆችህን ወደ ርስታቸው የሚሰበስብ ንስሐና ኀዘንም የለኝም። ከጥፋት ብዛት የተነሣም ሕሊናዬ ጠቆረ፡፡ በእነዚህና በመሳሰሉትም ልቡናዬ ተሸፈነ፡፡ ወደ አንተ እመለከት ዘንድም ኃይል የለኝም፡፡ ከክፋት የተነሣም አዕምሮዬ ቀዘቀዘ፡፡ በተቃጠለ ፍቅር ዕንባን ማፍሰስም ተሳነው፡፡

የመልካም ነገር ሁሉ መዝገብ ክርስቶስ ሆይ፤ አንተን ለመፈለግ በፍቅር እወጣ ዘንድ ፍጹም ንስሐንና ትጉ ልቡናን ስጠኝ፡፡ ስለ አንተም ከሁሉ የተለየሁ ሆንሁ: ቸር ሆይ፣ ከባሕርዩ የወለደህ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞም በባሕርዩ የነበርህ የአብን ጸጋ ስጠኝ፡፡ አርአያህና አምሳልህም ውስጤን ያድሰው:: እነሆ ተውሁህ፤ አንተ ግን አትተወኝ፤ ወደ አንተ መጣሁ፤ አንተም እኔን ለመፈለግ ውጣ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(ውዳሴ አምላክ ዘሐሙስ)

የክርስቶስን ፍቅር በማሰብ ቸር ዋሉልኝ🤗
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

20 Oct, 06:21


ኤጲስ ቆጶስ የሚለው ማዕረግ በጥንቱ የሮማ ቤተሰባዊ መዋቅር ውስጥ 'አንድ ሮማዊ ጌታ በሚያስተዳድረው ቤት ውስጥ የሚሠሩ አገልጋዮች አለቃ - master of slaves' የሚጠራበት ስም ነበር። ክርስቲያኖች ስሙን ከዚያ ነበር የወሰዱት። በእግዚአብሔር ቤት ካሉ አገልጋዮች መሀከል አንዱ ግን ታላቁ አገልጋይ ስም ኤጲስ ቆጶስ መባሉ የጥንቶቹ ተምኔት ምን እንደሆነ በግልጥ ያሳያል። ዛሬ ይኼ የአገልጋይነት መንፈስ የሚገኘው የት ይሆን? የሚለው የእኛ የቤት ሥራ ነው። አገልግሎትን በተመለከተ የተወያየነውን እንደ ወትሮው እንድታዳምጡ፣ አሳባችሁንም እንድታጋሩን ግብዣችን ነው።

https://youtu.be/-M_tj2UM-oE?si=45QsJ9fFkpY9620M

“እግዚአብሔር ሰንበትን እንደ ሰጣችሁ እዩ።”
— ዘጸአት 16፥29

https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

19 Oct, 18:43


https://youtu.be/DDu6pzl94eg?si=CeEWPbrekzeqKJyd


https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

19 Oct, 06:11


በሥጋ ደመና ተጭኖ መመላለስን እንማያውቅ፤
ወደ ግብጽ ምድር ሲወርድ ደክሞ አላበው፤
የአበባ  ከንፈሮቹ ውበትም በፀሐይ ሐሩር ጠወለገ፤
መከታ የሆኑ የእናቱን ጡቶች ለመጥባት በወደደ ጊዜ! ወተት አጥቶ እንደሕፃናት አለቀሰ፤
ስለወልድ እንባ መፍሰስ የእኔም እንባ ይፍሰስ፡፡
....
ያንጊዜ በስደቱ ከእሱ ጋር ብኖር፤
እሱን በጀርባዬ ማዘልን በተመኘሁ ነበር፤
የእግሩንም ትቢያ በምላሴ እልስ ዘንድ፤
በዐለት ላይ የተሳለ የእጁን ምልክትም በአፌ እስም ዘንድ፤
የዮሴፍ በትር በተተከለበትም ከእሱ ጋር አርፍ ዘንድ፤
በማርያም ልጅ የፍቅር ጦር ልቤ ቆሰለ፡፡

ሰቆቃወ ድንግል

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

18 Oct, 17:24


‹‹ ቤተክርስቲያንን ከክርስቶስ የሚለይ የለም ክርስቶስ ከቤተክርስቲያን እንደማይለይ ቃል ገብቷልና ስለዚህ ማንኛውም የጉዞ አቀበትና ቁልቁለት ቢያጋጥማትም ከክርስቶስ ጋር ያለች ቤተክርስቲያን አትደነግጥም በካታኩንቦ ብትቀድስም በወርቅ በተለበጠ በሐር በተንቆጠቆጠ ቤተመቅደስም ብትቀድስ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ናት፡፡ ››

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

በቸር ዕደሩልኝ🤗
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

18 Oct, 06:45


በዚኽ ዓለም ስንኖር በምንም ነገር እርግጠኞች መኾን አንችልም። ሐብታም ልንኾንም ላንኾንም እንችላለን። ባለሥልጣኖች ልንኾንም ላንኾንም እንችላለን። ግን በአንድ ነገር ብቻ እርግጠኛ ነን።

ሟ ቾ ች ነን!

መምህር ኢዮብ ይመኑ

ቸር ዋሉልኝ🤗
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

17 Oct, 08:20


"📖አሐቲ ድንግል"
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ከመፅሐፏ ምርቃት የተቀነጨበች ንግግር 🤗

''1 በር ነው ያለው እሱም ክርስቶስ ነው
ቅዱሳኑ ደሞ ወደክርስቶስ በር ነት መርተው የሚያደርሱ ናቸው ''

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

16 Oct, 18:33


#ክፉን_በመልካም_እንዴት_መቃወም_ይቻላል ?

የምታስፈራዋን የፍርድ ቀን እንባህን በማፍሰስ አስብ። ተስፋህ በእርሱ ዘንድ የቀና የጸና ይሆን ዘንድ የፈጣሪህን መልካም ተስፋውን ስበክና መስክር። መቀባጠር የሚያበዙትን በአርምሞህ ጸጥ አሰኛቸው ፤ ሐሜተኞችን በትዕግሥትህ ገሥጻቸው ፤ እንቅልፋሞችን በትጋትህ አንቃቸው ፤ ሀጥአንን አጽናናቸው ፤ የተዋረዱትን ራስህን በማዋረድ በትሕትና አረጋጋቸው ፤ ገንዘብ በማጠራቀም የበለጸጉትን ናቃቸው። ከዓለም የተለየህ ሁን ፤ የዓለም ፍቅሯና ትርፏ ፍርድን እደሚያመጣ እወቅ። ከዚህች ዓለም ትሸሽ ዘንድ ፍጠን ተሽቀዳደም ። ነፍስህንም ከመቀባጠር ፤ ጥቅም ከሌለው ከንቱ ጨዋታና ዋዛ ፈዛዛ አሳርፋት ።ይልቁንም የተሠወረውን ለሚያውቅ  እግዚአብሔር ምስጋና አቅርብ እንጅ። ድኽነትን እንደ ወርቅ ውደዳት።

📖መፅሐፈ ወግሪስ
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ቸር እደሩልኝ🤗
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

16 Oct, 07:26


“ ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤”2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥8

ቸር ዋሉልኝ🤗
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

15 Oct, 17:48


https://youtu.be/UJqDe2vd4N0?si=E8kJBnxk9BUpMwot

ዘመኑን የበከለ ክርስትያኑን ተዓምር ወዳጅ ከድህነት ይልቅ ጊዜያዊ (ስጋዊ) ፈውስ ላይ ብቻ ያተኮረ እዲሆን እና እረኛ እዳጣ መንጋ ከአንዱ ወደአንዱ እዲቅበዘበዝ ያደረ በሽታ ነው እጅግ ሊታሰብበት የሚገባ ትምህርት ነው ተከታተሉልኝ ታተርፉበታላችሁ🤗🤗🤗

“ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።”
— ሉቃስ 10፥20

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

15 Oct, 05:55


እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እረፍት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

#ዋኖቻችሁን_አስቡ። ዕብ 13:7

ይህን ኃይለ ቃል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለጊዜው ለዕብራውያን ሰዎች የተናገረው ሲሆን ፍጻሜው ግን በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኘን ለኛ ለምዕመናን ሁሉ ነው።

ዋኖቻችን እነማን ናቸው ቢሉ ሐዋርያው «የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁ» በማለት መልሶልናል። እነርሱም ከቀደምት አበው ጀምሮ ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ ቅዱሳን ናቸው።

ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ።በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል። “በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፥ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን።” ሮሜ 14፥8 እዳለው ቅዱስ ጳውሎስ ሕይወታቸውን ለክርስቶስ የሰጡ ወንጌልን(የእግዚአብሔርን ቃል) በቃላቸው የሰበኩት ብቻ ሳይሆን አካል አልብሰው ሚዳሰስ ሚታይ አድርገው የኖሩት የዕምነትን ፍሬ ያስመሰከሩ ታላቅ ቅዱስ የቤተክርስቲያናችን አባት ናቸው የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቀር አላቸው። ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው። በ8ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል። ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡

በመጨረሻም ሐዋርያው እንዳለን ቅዱሳኑን አስበን የነርሱን አሰረ ፍኖት ተከትለን በምግባር በሃይማኖት እንድንመስላቸው አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን። እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ሰዓሊተ ምሕረት ፍቅሯን በልባችን ጧዕሟን በአንደበታችን ታኑርልን። የጻድቁ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።

መልካም በዓል🤗!

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

14 Oct, 16:28


+++++++#በበጎነት_መጽናት#+++++++++

ማር ወግሪስ እንዲህ ይላል፦ "ዳግመኛም ስማኝ ልንገርህ! ለዘለዓለም ላንተ ይብስብሃልና ባደርክበት ኹሉ ቃልህን አትለውጥ። በሰዎች መካከል ጥልን አትዝራ፤ አነዋወርህ ኹሉ በሰላም ይኹን፤ ወደ ልቡናህም ቍጣን አታስገባ፤ ወንድምህ የበደለህን ከቶ አታስብ። የቍጡ ሰው ድካሙ ኹሉ በዐይን ጥቅሻ በከንፈር ንክሻ ፈጥኖ ያልፋልና። ቂምን በልቡናው የሚያኖር ሰው የሰይጣን ደቀ መዝሙሩ ነው፤ የዘለዓለም ሕይወትንም አያያትም። ማንንም ማንን አትማ፤ ከማንም ጋር አትከራከር፤ የባልጀራህን ንብረት አትመኝ የሌላውንም አትቀማ።

ሐሜተኛ ሰው የእግዚአብሔር ጠላቱ ነው። በጠላትህ ውድቀትና ሞት ደስ አይበልህ፤ ባዘኑት ላይ አትሣለቅ፤ ለዕውሩ መሰናክል አታኑርበት። ስትጸልይ ለመቀመጥ አትቸኩል፤ ለጸሎት ዝግጁ ኾነህ በቆምክበት ቦታ ኹሉ አትነቃነቅ፤ በመካነ ጸሎትህ ላይ አዘውትረህ ቆመህ ተገኝ። ለለመነህ ኹሉ ስጥ፤ ከሌለህ ደግሞ እግዚአብሔር ይስጥህ ካለው ያድርስህ ብለህ በለዘበ ቃል ተናገር። የምትሠራውን ሥራ ኹሉ ፊት አይተህ አድልተህ አትሥራ። የደረሰብህን ኹሉ እግዚአብሔርን አመስግነህ ተቀበል። ይህንን ያደረግህ እንደ ኾነ በእግዚአብሔር ትእዛዛትና ሕግጋት አንተ በእውነት ፍጹም ነህ። እኔስ በእውነት የእግዚአብሔርን ጥበብ አደንቃለሁ።" እንዲል። (አባ ገብረ ኪዳን ግርማ ፣ የአራቱ ጉባኤያት የምስክር መምህር)፣ መጽሐፈ ወግሪስ፣ 2013 ዓ.ም፣ ገጽ 51)።

የሕይወት መርሐችን ከላይ በተገለጸው መሠረት ቢኾን በበጎ መጽናት እንችላለን። ክፉ ነገር በሕሊናች ውስጥ በመጣ ጊዜ ወዲያው አስወግደን ብናስወጣው እና ሕሊናችን ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ኹል ጊዜ ብናስቀምጥ፥ በዚያም ቃል ብንመሰጥበት ሕይወታችን የተስተካከለ ይኾናል። ድንገት ስሜታዊ ኾነን ወደ ክፉ ልንሳብ ስንል ራሳችንን የምንቆጣጠርበት የእግዚአብሔር ቃል ውስጣችን ሊኖር ይገባል። በእርግጥም የሕይወት መርሐችንን በቃለ እግዚአብሔር እያደረግን ስንሄድ ስሜታችን በራሱ በቃለ እግዚአብሔር እየተገራ ይሄዳል። ውስጣችንም በቃለ እግዚአብሔር መመራትን እንደ ግዴታ መቀበል ይጀምራል። እንዲህ ሲኾን ብንጣላ ወዲያው ይቅር እንባባላለን፥ ቢበድሉን እንታገሳለን፥ ቢሰድቡን ስድብ የሚገባን ኃጥእ እንደ ኾን አድርገን እንቀበላለን፣ ቢንቁንም የክፉ ሥራችን ውጤት መኾኑን አምነን ያለተቃውሞ እንቀበላለን። እንዲህ በበጎ እየጸናን ስንሄድ የሚረብሸን ነገር በእኛ ላይ ኃይሉን እያጣ ይሄዳል፤ ሕይወታችንም በፍጹም ሰላምና ዕረፍት ይመላል።

እንግዲህ ምክንያታዊ ነኝ ብለን ከምናስበው አጸፋዊ መልስ ኹሉ እየራቅን እንሄዳለን። እንዲህ ያደረግኹት እንዲህ ስላደረገችኝ/ገኝ ነው እያሉ ከመናገር ኹሉ ነጻ እንወጣለን። በሕይወታችን የሚገጥሙንን ችግር የምንላቸውን ነገሮች ኹሉ የመጋፈጥና የማሸነፍ ብርታታችን ታላቅ ይኾናል። የብዙ ዓመታት ሕማም ቢኾን፣ ወይም የገንዘብ እጦት ችግር ቢኾን፣ ወይም ከሰዎች ዘንድ ፍቅር አጣኹኝ ብሎ የማሰብ ፈተናም ቢኾን እንሻገረዋለን። መጀመሪያ መስተካከል ያለበት አስተሳሰብ እና ነገሮችን የምንረዳበት መንገድ ነው። ሲቀጥልም የመኖር ትርጒሙና ዓላማው ግልጽ ኾኖ ሊገባን ያስፈልጋል። ይህ በትክክል ሲገባን ያን መፈጸም ዋና ዓላማችን እየኾነ ይመጣል። ስለዚህ ሰይጣን ሊጥለንና ጥቅም አልባ ሊያደርገን የሚፈጽምብን ጥቃት ኹሉ ይከሽፋል። በበጎነት ጽናታችንም ድል ይነሣል። ስለዚህ ስንኖር ለምንድን ነው የምኖረው? እንዴትስ እንድኖር ነው ፈጣሪ የሚፈልገው? ፈጣሪስ እንደሚፈልገው መኖር ያልቻልኩት ለምንድን ነው? ለመኾኑ በበጎነት ጸንቼ እንዳልኖር የሚከለክለኝ ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ለራሴ እየጠየኩ ሕይወቴን እያስተካከልኹኝ ልኖር ይገባኛል። በምን መመሪያ እንዳንል ከላይ ማር ወግሪስ ያስቀመጠልን ድንቅ የሕይወት መመሪያ አለልን።
ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው

ለመኖር የተፃፈ📜

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

14 Oct, 05:05


ሰዎች ውስጣቸው ክርስቶስ ባለመኖሩ ባዶ ሲሆኑ ብዙ ሺ ነገሮች መጥተው ይሞሏቸዋል: ቅናት፣ ሃሜት፣ ጥላቻ፣ ድብርት፣ ጥልቅ ኅዘን፣ እልህ፣ ዓለማዊ ዕይታ፣ ምድራዊ ደስታ ወዘተ... ነፍሳችን ባዶ እንዳትሆን ነፍሷ የሆነው ክርስቶስን አንከልክላት🤲

ማቴዎስ 11
²⁸ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
²⁹ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ቸር ዋሉልኝ🤗

አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

13 Oct, 18:44


በዚህኛው የበእንተ ወንጌል ቆይታችን በዮሐንስ ወንጌል ላይ ካሉ ዐበይት ታሪኮች ውስጥ አንዱ የሆነውን ጌታችን ከሣምራዊቷ ሴት ጋር ያደረገውን ንግግር ቃኝተናል።

በውይይታችን ውስጥ እነዚህን ሦስት መሠረታዊ ነጥቦችን አንስተናል።

1) ይህንን የወንጌል ክፍል ለመረዳት አስፈላጊ የሆነውን አይሁዳውያን ከሣምራውያን ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ሰፋ ባለው ታሪካዊ አውዱ ለማንሳት ሞክረናል።

2) የዚህ ታሪክ መሠረታዊ ነገረ ቤተክርስቲያናዊ ጭብጥ አንስተናል።

3) በዚህ ታሪክ ላይ ፈጽሞ ታሪካዊ አውዱንም ሆነ የወንጌሉን መሠረታዊ ጭብጥ ያልተገነዘቡ ፣ በዘመናችን ከሉ ሊቃውንትም ሆነ ከአበው ምስክርነት የማይገኝላቸውን ወፍ ዘራሽ "ትርጓሜዎች" ሞግተናል።

መልካም ቆይታ።

https://youtu.be/f2aunKpPPBY?si=NhrzAV9-_TZj6ifC