በአዶላ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ከደብሩ ኦርቶዶክሳዊ ወጣቶች ማኅበር ጋር በመተባበር ከፊታችን በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ በቀን 07/05/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11:00-12:30 ድረስ "መጽሐፍ ቅዱሳዊ የምሥጢረ ጥምቀት አስተምህሮ" በሚል ርእስ ሥልጠና ይሰጣል።
በሥልጠናው ላይ
➤ምሥጢረ ጥምቀት
➤የጥምቀት ምንነት?
➤በብሉይ ኪዳን ስለጥምቀት የተነገሩ ትንቢቶችና ምሳሌያት
➤የጥምቀት መሥራች ማነው?
➤በማን ስም እንጠመቃለን? ሐዋርያት በማን ስም አጠመቁ?
➤የጥምቀት አይነቶች
➤በጥምቀት የምናገኛቸው መለኮታዊ ሥጦታዎች
➤ለጥምቀት የተወሰነ እድሜ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀበት መልኮታዊ ዓላማ ምንድነው?
የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎችን የሚመለሱ ይሆናል።
ስለሆነም የከተማችን ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በሥልጠናው ላይ በመገኘት ስለምናከብረው የጥምቀት በዓል ምንነት እና የምሥጢረ ጥምቀትን ትምህርት ይማሩ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!