► ጊዜው፥ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር የጀመረበት፣ሐዋርያት በምልዓት ያልተጠሩበት፣ የዮሐንስ መጥምቅ ትምህርት የተፈጸመበት ወቅት ነው።
በዚያ ዘመን በገሊላ ናይን(Nain) ከተማ ይኽ ከዚኽ ቀረሽ የማትባል 'የደም ገምቦ' መልከ መልካም ሴት ነበረች። ውበቷ የኀጢኣትም የገንዘብም 'ትርፍ' ኾኗት ብዙ ጊዜ ቆይታለች።
ከዕለታት አንድ ቀን እንደልማዷ በመስታዎት ፊት ቆማ ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ጠጕሯ ውበቷን ተመለከተች። ነገር ግን የመስታወቱ ምልሰት ላይ ከፊት ያለው ውበቷን ያይደለ ሞቷንና ኀጢኣቷን የነፍሷንም ድካም ተመለከተች።
ይኽም ራስን በጥልቀት የማየት ጉዳይ በሥጋ ዐይን አይኾንም። መጽሐፍ "ወብነ ክልኤቲ አዕይንት ውሳጣውያት ህየንተ አዕይንት ሥጋውያት" ብሎ በነገረን በነፍስ ዐይን እንጂ በመስታዎቷ ፊት ቆማ በዘመን ፀሓይ ለሚረግፈው አበባነቷ እንዲኽ አለች፦
"ዘወትር ወደ ዝሙት የምትሮጡ እግሮቼ ኾይ ሞት በሚያሥራችኹ ጊዜ እንደምን ትኾናላችኹ? ልታመልጡ ትወዳላችኹ አይቻላችኹም፣ ባንተ ብዙ ያጣኹ አንደበቴ ኾይ፦ ትመልስለት ዘንድ የማይቻልኽ የዐለም ኹሉ ገዥ የሚኾን ሞት ዝም ባሰኘኽ ጊዜ እንደምን ትኾናለኽ?'' ከድምፅ አልባው ምስሏ ጋር እንዲኽ ስታለቅስ ቆይታ ከኀጢኣት ወደ ጽድቅ የሚመልሳትን ጌታ ልትፈልግ ወጣች።
ግን ደገሞ ባዶ እጇን መኼድ አልወደደችም። ሃድኖክ ወደሚባል ነጋዴ ኼዳ ውድ ሽቱ ለመግዛት ጠየቀችው። የዘወትር ፈገግታዋን በፊቷ ላይ ያጣው ነጋዴም
ጠየቃት። እንዲኽ ስትል መለሰችለት
እቀብረው ዘንድ እወዳለኹ፡፡"
"ማርያም! ምን ኾነሽ አዝነሻል? ከሚወዱሽ ወንዶች የሞተ አለን?" ብሎ "እወ ብዙኅ ኀጢኣትየ ሞተ ወእፈቅድ እቅብሮ፤ ብዙ ኀጢኣቴ ሞተ እቀብረው ዘንድ እወዳለኹ፡"
[ማስታወሻ፦ ይቺ ማርያም የአልዓዛር እኅት ማርያም ወይም መግደላዊት ማርያም አይደለችም።]
ጸሎታ ወበረከታ የሀሉ ምስሌነ።