አብዛኞቻችን ሰዎችን በንፅፅራዊ እይታ ውይይት ለማድረግ በምንቀርብ ጊዜ ከያዝናቸው የተገደቡ ጥቅሶች በስተቀር ለሙግታችን አንጠቀምም የዚህም እንደ ችግር ሆኖ ሊነሳ የሚችለው በሁለቱ መፅሐፍት ላይ የተገለጸውን ሀሳብ ጠንቅቆ ተረድቶ በሚዛናዊነት ለማየት አለመቻል ነው!
...
ለዚህም ሲባል ሙስሊሞች መፅሐፍ ቅዱስን ከዘፍጥረት ጀምሮ ያለውን ጥቅስ በጥቅስ ያለውን ሀሳብ በሰፊ እይታ እና በሚዛናዊነት ለመመልከት ሲኖርባቸው፤ከዚሁ በተቃራኒው ክርሰቲያን ወገኖቻችን ቁርአንን ከአል-ፋቲሃ ጀምሮ መልዕክቱን ጠብቀው መረዳት አለባቸው!
...
መፅሐፍ ቅዱስን ለሚያነቡ:
- የአውደ ምንባብ(Contextual Passage)
- መሰረታዊ ቋንቋ (Strong's Concordance)
- የማብራሪያ(Commentary)
- የተለያዩ የመፅሐፍ ቅዱስ እትሞች(Version)
- የጥቅሱ ታሪካዊ ዳራ(Historical Background)
...
ቁርአንን ለሚያነቡ:
- የአውደ ምንባብ(Contextual Passage)
- የመሰረታዊ ቋንቋ(Classical Arabic)
- ሰዋስዋዊ አወቃቀር(Grammatical Structure)
- የማብራሪያ(Tafsir)
- የጥቅሱ ታሪካዊ ዳራ(Historical Background)
...
እነዚህን በመጠቀም ጥቅስን ቆርጦ ትከሻ የመለካካት ሙግት ከመጠቀም መቆጠብን በማሳሰብ ነው፤ይህንን ለማድረግ ግሩፕ የሚከፈት ሲሆን በ3 ቀን አንድ ጊዜ ጥያቄ እና መልስ ይኖረናል ሀሳቡ ከተመቻችሁ Like ማድረግዎን አይርሱ።
T.me/TheComparator
— ከወንድም አህመድ(አነፃፃሪው)