ህዳር 04/2017 ዓ.ም ሐረር
**
ወጣቱ ትውልድ ለልማት እና እድገት ካላው ቁልፍ ሚና አንፃር በጋራ እና በትብብር መስራት ለሀገር ግንባታ ሚናው ከፍተኛ ነው ።
የጋራ ትብብር እና ትስስር በሚሹ በተለይ እንደ ሰላም ባሉ ጉዳዮች ላይ የወጣቶች ተሳትፎ የጎላ መሆን እውን ነው ።
ይህንንም መሰረት በማድረግ በሐረሪ ክልል ወጣቶች ምክር ቤት አዘጋጅነት የሐረሪ ክልል ፣ የሱማሌ ክልል እና ድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶች ምክር ቤት አባላት የተሳተፉበት የምስራቅ አጎራባች የወጣቶች ምክር ቤት የሰላም መድረክ ተካሔደ ።
የእለቱ ክብር እንግዳ የሐረሪ ክልል የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እና የምክር ቤቶቹ ፕሬዝዳንቶች ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በመድረኩም ዘላቂነት ያለው ሰላም ለማስቀጠል የወጣቱ ሚና ምን መሆን አለበት በሚል ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረደገ ሲሆን የቀጣዩን የምስራቅ ኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት የሰላም መድረክ የድሬዳዋ ወጣቶች ምክር ቤት እዲያዘጋጅ በመወሰን ተጠናቋል ።