ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media @yeweketmaed Channel on Telegram

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

@yeweketmaed


በተለያዬ ጊዜ ወደዚህ ቡድን የምትቀላቀሉ አባላት በሙሉ
➺ ለጀማሪዎች
➺ ለማዕከላውያን
➺ ለ ቅኔ ጀማሪዎች መግቢያ
ትምህርት መስጠት ጀምረናል።
አስተያየት ወይም ጥያቄ ካላችሁ በ 0913514905 ያግኙን።
ስልካችን በማይሠራበት ሰዓት በ Telegram (@ethiogeezmedia) ጻፉልን።

ኢትዮ ግእዝ ሚድያ ንባብ ቤት
https://t.me/EthiogeezmediaNibab

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media (Amharic)

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ ተጠቀምን! ይህ ቡድና ለሁሉንም ኢትዮጵያውያን ብቻ ነው። አስተያየትዎን በራሱ እና በዋጋው ስለሚኖሩ አገልግሎታችን በምታደርጉበት ቀናት ላይ ይሁኑ። በማንኛውም ሜዳ እና ቀጥሎ የተከታተሉ ጀማሪዎች እና የመዝናኛዎች ለእርስዎ እንዴት በቡድኑ እንዳይመለስ ከፈለገ በኋላ ተጨማሪ ነበር። ሰልፍ ግምት, መረጃዎቻችን እና ሌሎች አጤ ምንጭ እንዲባላስ ከተ በለጠን መጽሐፍና ቁምፊዎች አሉ። ምሳሌ, ማስተዋል ፈቃድ እና ትምህርት ታሪኩን ከማግኘት ለማህበረሰብ ከተማዋን በማሰብ ሥራን በመምራት እና ቃለ ምልልስ በርካታ በመጠቀም የሚከተሉ ነው። አለገኝ ለበፎቹንና አገልግሎታችንን የጽሁፉን መልስ እና ከሌሎች ተጠቃሚዎች እንዴት በቡድኑ ተተኮረብናል ይህን በዚህዚህ ቡድን በ (@ethiogeezmedia) ላይክፍላችሁ ግብፅ።

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

01 Nov, 09:32


https://youtu.be/EuYLIC_gUgs

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

30 Oct, 08:07


.
.
.
    ◆የ8ቱ አርእስተ ግሶች ርባታ◆

◆ ትምህርቱ የሚሰጥበት ቴሌግራም ገጽ
[
@Ethiogeezmedianibab ]

◆ ቴሌግራም መወያያ
[
@Ethiogeezmediachat ]

   ለሐሳብ  አስተያየትዎ
◎ ስልክ =[
0913514905]
◎ Telegram =[
@Ethiogeezmedia]
◎ ኢሜል= [
[email protected]]
.
.
.

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

25 Oct, 00:36


.
.
.
  ◆ማኅሌተ ጽጌ◆

◆ ትምህርቱ የሚሰጥበት ቴሌግራም ገጽ
[
@Ethiogeezmedianibab ]
◆ ቴሌግራም መወያያ
[
@Ethiogeezmediachat ]

   ለሐሳብ  አስተያየትዎ
◎ ስልክ =[0913514905]
◎ Telegram =[
@Ethiogeezmedia]
◎ ኢሜል= [
[email protected]]
.
.
.

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

19 Oct, 20:53


◎ ርእስ = ስንክሳር በልሳነ ግእዝ [ከዓመት እስከ ዓመት]
◎ የገጽ ብዛት = ፲፻፵፮

▪️የግእዝ ንባብ ትምህርት መማር ከፈለጉ
@Ethiogeezmedianibab ላይ ይግቡ።

◎ ሌሎች የግእዝ መጻሕፍትን ለማግኘት
@EGMGeezBookStore ላይ ያገኛሉ።

.
.

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

12 Oct, 05:31


◎ ርእስ = ድርሳነ ሰንበት
◎ የገጽ ብዛት = ፺፬
የግእዝ ንባብ ትምህርት መማር ከፈለጉ
@Ethiogeezmedianibab ላይ ይግቡ።

◎ ሌሎች የግእዝ መጻሕፍትን ለማግኘት
@EGMGeezBookStore ላይ ያገኛሉ።

.
.

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

08 Oct, 09:33


.
.
.
ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ ንባብ ቤት!
[@Ethiogeezmedianibab]

የሚሰጡ ትምህርቶች

◎ የዘወትር ጸሎት
◎ ውዳሴ ማርያም
◎ አንቀጸ ብርሃን
◎ መልክአ ማርያም
◎ መልክአ ኢየሱስ
◎ መዝሙረ ዳዊት
◎ ገድለ ቅዱሳን
◎ ድርሳነ መላእክት
◎ ስንክሳር እንዲሁም ሌሎች የንባብ ትምህርቶች እንደ ተማሪው ምርጫ ይሰጣል። መማር ከፈለጉ ይጻፉልን።

ለሐሳብ አስተያየትዎ
   ኅብስቱ ዘለዓለም መንግሥቴ
               አስተባባሪ!
◎ ስልክ =[0913514905]
◎ Telegram =[
@Ethiogeezmedia]
◎ ኢሜል= [
Ethiogeezmedia@gmail.com]

   መስከረም ፳፰፡፳፻፲፯ ዓ.ም
.
.
.

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

27 Sep, 07:47


.
.
#Share!
#Share

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችኹ!
[እንቋዕ አብጽሐክሙ ለበዓለ መስቀል።]


           ◎ የበዓል ልዩ ስጦታ ◎

ይህን መልእክት
   ◎ የትምህርት ፍላጎት ላላቸው ሰዎች በሙሉ በግል
   ◎ በምታውቁት የ ቴሌግራምፌስቡክቲክታክ እንዲኹም ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ለኹሉም ሰው በማጋራት ኃላፊነታችንን እንወጣ።

    [ኢትዮ ግእዝ ሚድያ ንባብ ቤት]

       🔴 የሚሰጡ ትምህርቶች 🔴

◆ ከዘወትር ጸሎት እስከ መዝሙረ ዳዊት
◆ ድርሳን እና ገድል

   ◎ ድርሳነ ሚካኤል
   ◎ ድርሳነ ገብርኤል
   ◎ ገድለ ጊዮርጊስ
   ◎ ገድለ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
   ◎ ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሌሎችም።
ወንጌል
     ◎ ወንጌል ዘማቴዎስ
     ◎ ወንጌል ዘማርቆስ
     ◎ ወንጌል ዘሉቃስ
     ◎ ወንጌል ዘዮሐንስ
መልክዕ
      ◎ መልክዐ ማርያም
      ◎ መልክዐ ኢየሱስ
      ◎ መልክዐ ጊዮርጊስ
      ◎ መልክዐ ተክለ ሃይማኖት ሌሎችም።
◆ ስንክሳር

🔴 የመማሪያ ዕለታት
        ◎ ኹሌም ከ ሰኞ እስከ እሑድ
🔴 የመማሪያ ሰዓት
        ◎ 1:00 - 4:00 ሰዓት
🔴 የትምህርቱ አሰጣጥ
        ◎ Live በ Telegram ወይም የድምፅ ቅጂ በመላክ።

🔴 የትምህርቱ ክፍያ
    ◎ ኹሉም ዐቅሙ እንደፈቀደው ተመጣጣኝ ክፍያ እየከፈለ መማር ይችላል።

🔴 ትምህርቱ የሚሰጥበት ቻነል
   ◎https://t.me/EthiogeezmediaNibab

🔴 የትምህርቱ መወያያ ገጽ
◎https://t.me/+8pISmdZIvXQ0YmQ8
ለጥያቄ እና አስተያየት
◆ ስልክ =
0913514905
◆ Telegram =
@Ethiogeezmedia
◆ Email =
[email protected] ላይ ያገኙናል።
.
.
.

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

17 Aug, 06:42


.
.
.
   "የክፍል ዘጠኝ ጥያቄዎች"

◆ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ስምንት ያሉትን ጥያቄዎች እስከ መልሳቸው ለማግኘት ከታች ያለውን ይጫኑ። 

📌 https://t.me/yeweketmaed/759

፩] አአትብ ገጽየ በመስቀል።

በባዶ ቦታው የሚገቡት ቃላት ትክክለኛ አጻጻፍ የቱ ነው?

አ) ወኵለንተናየ / በትምህርተ
ቡ) ወኵለንታየ/ በትምህርተ
ጊ) ወኵለንታየ/ በትእምርተ
ዳ) ወኵለንተናየ/ በትእምርተ

፪] ወንጌላዊው "ሉቃስ" ___ ነበር። 

አ) ሠዐሊ
ቡ) ሰአሊ
ጊ) ሠዓሊ
ዳ) ሰኣሊ

፫]  ከሚከተሉት ውስጥ ውስጠዘ የሚባለው የትኛው ነው?

አ) ቅቱላት
ቡ) ቅዱስ
ጊ) ቅቱል
ዳ) ቅትልት
ሄ) ኵሎሙ


፬] _ _ _ በበይናቲክሙ

አ) ተአምኁ
ቡ) አምኁ
ጊ) አምኀ
ዳ) አምኀት

፭] ከቅዳሴ መጨረሻ የሚባለው ትክክለኛው አጻጻፉ የቱ ነው?

አ) እትው በሰላም
ቡ) እትዉ በሰላም
ጊ) ዕትው በሰላም
ዳ) ዕትዉ በሠላም

ማስታወሻ:-

◎ በጥያቄ እና መልሱ ለምትሳተፉ አባላት ቃል በገባኹላችኹ መሠረት ምናልባት የንባብ ትምህርት መማር የምትፈልጉ ካላችኹ ከታች ባለው Link መግባት ትችላላችኹ።

ንባብ ቤት :-
👉https://t.me/+nF5N-biCtTwyMjQ0

የሚሰጡ ትምህርቶች:-

ዘወትር ጸሎት
◎ ውዳሴ ማርያም
◎ አንቀጸ ብርሃን
◎ መልክዐ ማርያም
◎ መልክዐ ኢየሱስ
◎ ዳዊት
◎ ገድላት
◎ ድርሳናት
◎ ወንጌል
◎ ስንክሳር እንዲሁም ሌሎች የንባብ ትምህርቶች እንደ ተማሪው ምርጫ ይሰጣል።
.

.
.
◆ መልሱን በውስጥ መስመር ማለትም @Ethiogeezmedia [0913514905] የሚለውን ጠቅ አድርጋችኹ ላኩልኝ።

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ!
የበለጠ ለማግኘት
[
https://t.me/Yeweketmaed]

ቅዳሜ : ነሐሴ ፲፩ /፳፻፲፮ ዓ.ም
.
.
.

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

15 Aug, 20:12


.
.
.
   "የክፍል ስምንት ጥያቄዎች"

◆ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ሰባት ያሉትን ጥያቄዎች እስከ መልሳቸው ለማግኘት ከታች ያለውን ይጫኑ። 

📌 https://t.me/yeweketmaed/759

፩] አ
◆ እግዚአብሔር ይሰባሕ
[እግዚአብሔር ይመስገን።]

◎ ተሰብሐ ➜ ተመሰገነ
◎ ይሴባሕ ➜ ይመሰገናል
◎ ይሰባሕ ➜ ይመሰገን ዘንድ
◎ ይሰባሕ ➜ ይመስገን

፪] ጊ
◆ ሌሎቹ በይእቲ መራሒ የረቡ ሲኾን ቀተሉ የሚለው ግን በውእቱ የረባ ነው።

፫] ዳ
ቀተለ የሚለው ግስ በ "አንቲ" መራሒ ፊደል ሲረባ የግሱን መድረሻ ወደ ሳድስ ቀይሮ "ኪ" የሚል ባለቤት አመልካች መጨመር ነው።

፬] ቡ እና ጊ
መኑ ውእቱ ስምኪ = ስምሽ ማን ነው?
እፎ ውእቱ ስምኪ = ስምሽ እንዴት ነው?

፭] ቡ

◆ "ኢትፈር" የሚለው ግስ የወጣው "ወፈረ" ከሚለው ግስ ሲኾን :-

◎ ወፈርከ ➜ ተሰማራኽ
◎ ትወፍር ➜ ትሰማራለኽ
◎ ትፈር ➜ ትሰማራ ዘንድ
◎ ፈር ➜ ተሰማራ
በአሉታ ሲኾን ደግሞ :- "ኢትፈር" ይኾናል።

ማስታወሻ:-

◎ በጥያቄ እና መልሱ ለምትሳተፉ አባላት ቃል በገባኹላችኹ መሠረት ምናልባት የንባብ ትምህርት መማር የምትፈልጉ ካላችኹ ከታች ባለው Link መግባት ትችላላችኹ።

ንባብ ቤት :-
👉https://t.me/+nF5N-biCtTwyMjQ0

የሚሰጡ ትምህርቶች:-

ዘወትር ጸሎት
◎ ውዳሴ ማርያም
◎ አንቀጸ ብርሃን
◎ መልክዐ ማርያም
◎ መልክዐ ኢየሱስ
◎ ዳዊት
◎ ገድላት
◎ ድርሳናት
◎ ስንክሳር እንዲሁም ሌሎች የንባብ ትምህርቶች እንደ ተማሪው ምርጫ ይሰጣል።
.

.
.
◆ መልሱን በውስጥ መስመር ማለትም @Ethiogeezmedia [0913514905] የሚለውን ጠቅ አድርጋችኹ ላኩልኝ።

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ!
የበለጠ ለማግኘት
[
https://t.me/Yeweketmaed]

ቅዳሜ : ነሐሴ ፬ /፳፻፲፮ ዓ.ም
.
.
.

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

13 Aug, 15:07


.
.
.
   "የክፍል ስምንት ጥያቄዎች"

◆ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ሰባት ያሉትን ጥያቄዎች እስከ መልሳቸው ለማግኘት ከታች ያለውን ይጫኑ። 

📌 https://t.me/yeweketmaed/759

፩] ሀ) እፎ ኀደርኪ ሰሎሜ።
    ለ) እግዚአብሔር__ _

አ) ይሰባሕ
ቡ) ይሴባሕ
ጊ) ተሰብሐ
ዳ) ሰብሐት

፪] ከሚከተሉት ውስጥ ልዩ የኾነው የቱ ነው?

አ) ቀደሰት
ቡ) ቀተለት
ጊ) ቀተሉ
ዳ) ሰብሐት

፫]  አንቲ ___አንበሳ። ባዶ ቦታውን የሚያሟላው ቃል የቱ ነው።

አ) ቀተላ
ቡ) ቀተልክን
ጊ) ቀተለት
ዳ) ቀተልኪ

፬] _ _ _ ውእቱ ስምኪ። ባዶ ቦታውን የሚያሟላው ቃል የቱ ነው።

አ) ማእዜ
ቡ) መኑ
ጊ) እፎ
ዳ) አልቦ አውስኦት

፭] "ኢትፈር" ኀቤሃ ለጥበብ በክልኤ ልብ። ለተሰመረበት ግስ ቀዳማይ አንቀጹ ___ ነው።

አ) ኀፍረ
ቡ) ወፈረ
ጊ) ተርፈ
ዳ) አልቦ አውስኦት

ማስታወሻ:-

◎ በጥያቄ እና መልሱ ለምትሳተፉ አባላት ቃል በገባኹላችኹ መሠረት ምናልባት የንባብ ትምህርት መማር የምትፈልጉ ካላችኹ ከታች ባለው Link መግባት ትችላላችኹ።

ንባብ ቤት :-
👉https://t.me/+nF5N-biCtTwyMjQ0

የሚሰጡ ትምህርቶች:-

ዘወትር ጸሎት
◎ ውዳሴ ማርያም
◎ አንቀጸ ብርሃን
◎ መልክዐ ማርያም
◎ መልክዐ ኢየሱስ
◎ ዳዊት
◎ ገድላት
◎ ድርሳናት
◎ ስንክሳር እንዲሁም ሌሎች የንባብ ትምህርቶች እንደ ተማሪው ምርጫ ይሰጣል።
.

.
.
◆ መልሱን በውስጥ መስመር ማለትም @Ethiogeezmedia [0913514905] የሚለውን ጠቅ አድርጋችኹ ላኩልኝ።

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ!
የበለጠ ለማግኘት
[
https://t.me/Yeweketmaed]

ቅዳሜ : ነሐሴ ፬ /፳፻፲፮ ዓ.ም
.
.
.

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

13 Aug, 09:05


.
.
.
"የክፍል ሰባት ጥያቄዎች መልስ"

◆ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ስድስት ያሉትን ጥያቄዎች እስከ መልሳቸው ለማግኘት ከታች ያለውን ይጫኑ። 

📌 https://t.me/yeweketmaed/759

፩) ጊ
◆ በመጀመሪያ ጥያቄው የጽሑፍ ስሕተት ስላለበት ይቅርታ። ለማለት የታሰበው እንዲህ ነበር።

[ "ቀተለ" ብሂሎ "ይቅትል" እመ ይቤ "ቀደሰ" ብሂሎ ____ይብል።]

◆ መልሱ የተሠራውም በዚህ ነው።
ይቅትል የሚለው የቀተለ ዘንድ ወይም ትእዛዝ አንቀጽ እንደ ኾነ ኹሉ ይቀድስ የሚለው ደግሞ የ ቀደሰ ትእዛዝ አንቀጽ ነው ለማለት ነው።

◎ ቀተለ = ገደለ
   ◎ ቀተለ = ይቀትል
   ◎ ቀተለ = ይቅትል
   ◎ ቀተለ = ይቅትል

   ◎ ቀደሰ = አመሰገነ
   ◎ ይቄድስ = ያመሰግናል
   ◎ ይቀድስ = ያመሰግን ዘንድ
   ◎ ይቀድስ = ያመስግን

፪] ዳ

◆ ከዘር ዐይነቶች አንዱ ጥሬ ዘር ይባላል።
◎ ጥሬ ዘር የሚጨርሰው በ ራብዕ ፣ በ ኀምስ ፣ እና በሳብዕ ነው።
◎ ከግሱ ያልነበረ ፊደል አይጨምርም።

◎ ቀደሰ ➼ ቅዳሴ
◎ ሰብሐ ➼ ስባሔ
◎ ደመነ ➼ ደመና እያለ ይወጣል።

◆ ስብሐት የሚለው ግን ሳቢ ዘር ይባላል።

፫]  ዳ

◆ አሥራው ቀለማት የሚባሉት ፬ ናቸው። እነሱም #ተ#ነ#አ#የ ናቸው።
◎ እነዚህም በ ግእዝ [ተ ፣ ነ ፣ አ ፣ የ]
    ◎ እነዚህም በ ሳድስ [ት ፣ ን ፣ እ ፣ ይ]
    ◎ እነዚህም በ ራብዕ [ታ፣ ና ፣ኣ፣ ያ] ነው ለአገልግሎቶ የሚውሉት።

፬] ጊ

◆ ስምንቱ አርእስተ ግሶች የሚባሉት :-
        ◎ ቀተለ
        ◎ ቀደሰ
        ◎ ተንበለ
        ◎ ባረከ
       ◎ ማሕረከ
        ◎ ሴሰየ
        ◎ ክህለ
        ◎ ጦመረ ናቸው።

፭]

➼ ዛሬ ርእየ'ን ስለሚመስሉ ግሶች ርባታ ልንገራችኹ።
◎ ባለ ሦስት ፊደል ኾነው አቀማመጣቸው [ሳድስ ፣ ሳድስ ፣ ግእዝ] የኾኑ እና በመድረሻ #የ ያለባቸውን ነው:-
ምሳሌ የሚኾኑ ግሶች
◈ ርእየ = አየ
◈ ልህየ = ወዛ
◈ ጥዕየ =ዳነ

➺ እነዚህ  ዐይነት ግሶች በዐሥሩ መራሕያን ሲረቡ  በ ሦስተኛ መደብ መራሕያን ማለትም  በ
        ◈ ውእቱ 
        ◈ ይእቲ
        ◈ ውእቶሙ እና በ ውእቶን የምድብ ፩ ግሶችን ስናረባ በምናውቀው በመደበኛው  የርባታ መንገድ ይረባሉ። 
⓵ #ውእቱ                      
◈ ርእየ=አየ     
◈ ጥዕየ= ዳነ 
 
⓶ #ውእቶሙ
◈ርእዩ =አዩ
◈ ጥዕዩ = ዳኑ

⓷ #ይእቲ         
◈ ርእየት =አየች    
◈ ጥዕየት= ዳነች  

⓸ #ውእቶን
◈ ርእያ =አዩ
◈ ጥዕያ= ዳኑ
➺ ነገር ግን በ አንደኛ እና በ ኹለተኛ መደብ  መራሕያን አካሄዳቸው ይለያል።
➺ ይኸውም የግሱን መካከለኛ ሳድስ ፊደል ወደ ሣልስ መቀየርና የመድረሻውን #የ ፊደል በማጥፋት በምድብ ኹለት ያየናቸውን ቅጥያዎች መጨመር ነው።

ኹለተኛ እና አንደኛ መደብ መራሕያን

#አንተ 
◈ ርኢከ=አየኽ
◈ ጥዒከ= ዳንኽ      

#አንትሙ
◈ ርኢክሙ =አያችኹ
◈ ጥዒክሙ= ዳናችኹ 

#አንቲ
◈ ርኢኪ =አየሽ
◈ ጥዒኪ=ዳንሽ

#አንትን
◈ ርኢክን =አያችኹ
◈ ጥዒክን= ዳናችኹ  

#አነ                  
◈ ርኢኩ =ዳንኹ  
◈ ጥዒኩ= ዳንኹ

#ንሕነ
◈ ርኢነ =አየን
ጥዒነ= ዳን

   አስተውሉ:-

➺ በ ኹለተኛ እና በ አንደኛ መደብ መራሕያን ጊዜ መካከል ላይ ያለውን ሳድስ ፊደል ወደ ሣልስ መቀየር እንዳትዘነጉ።
➺ በ ኹለተኛ እና በ አንደኛ መደብ መራሕያን ጊዜ መድረሻ ላይ የነበረው ፊደል (#የ) ሙሉ በሙሉ ይጠፋል።


ማስታወሻ:-

◎ በጥያቄ እና መልሱ ለምትሳተፉ አባላት ቃል በገባኹላችኹ መሠረት ምናልባት የንባብ ትምህርት መማር የምትፈልጉ ካላችኹ ከታች ባለው Link መግባት ትችላላችኹ።

ንባብ ቤት :-
👉https://t.me/+nF5N-biCtTwyMjQ0

የሚሰጡ ትምህርቶች:-

ዘወትር ጸሎት
◎ ውዳሴ ማርያም
◎ አንቀጸ ብርሃን
◎ መልክዐ ማርያም
◎ መልክዐ ኢየሱስ
◎ ዳዊት
◎ ገድላት
◎ ድርሳናት
◎ ስንክሳር እንዲሁም ሌሎች የንባብ ትምህርቶች እንደ ተማሪው ምርጫ ይሰጣል።
.

.
.
◆ መልሱን በውስጥ መስመር ማለትም @Ethiogeezmedia [0913514905] የሚለውን ጠቅ አድርጋችኹ ላኩልኝ።

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ!
የበለጠ ለማግኘት
[
https://t.me/Yeweketmaed]

ማክሰኞ : ነሐሴ ፯ /፳፻፲፮ ዓ.ም
.
.
.

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

10 Aug, 16:55


.
.
.
   "የክፍል ሰባት ጥያቄዎች"

◆ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ስድስት ያሉትን ጥያቄዎች እስከ መልሳቸው ለማግኘት ከታች ያለውን ይጫኑ። 

📌 https://t.me/yeweketmaed/759

፩] ውእቶን ብሂሎ "ይቅትል" እመ ይቤ "ቀደሰ" ብሂሎ ____ይብል።

አ) ይቅድስ
ቡ) ይቄድስ
ጊ) ይቀድስ
ዳ) ቀደሰት

፪] ከሚከተሉት ውስጥ ልዩ የኾነው የቱ ነው?

አ) ቅዳሴ
ቡ) ስባሔ
ጊ) ደመና
ዳ) ስብሐት

፫]  እም ዘይተልው ቀለማት አይ ውእቱ ዘኢኮነ አሥራው ቀለም።

አ) ና
ቡ) ታ
ጊ) አ
ዳ) ኢ

፬] ከሚከተሉት ወስጥ "አርእስተ ግስ" ያልኾነው የቱ ነው?      

አ) ቀደሰ
ቡ) ቀተለ
ጊ) ቀበንጦሰጠ
ዳ) ተንበለ

፭] ውእቱ ብሎ "ርእየ" ካለ አንተ ብሎ ____ይላል።

አ) ርእይከ
ቡ) ርኢከ
ጊ) ርይከ
ዳ) ርእየከ

ማስታወሻ:-

◎ በጥያቄ እና መልሱ ለምትሳተፉ አባላት ቃል በገባኹላችኹ መሠረት ምናልባት የንባብ ትምህርት መማር የምትፈልጉ ካላችኹ ከታች ባለው Link መግባት ትችላላችኹ።

ንባብ ቤት :-
👉https://t.me/+nF5N-biCtTwyMjQ0

የሚሰጡ ትምህርቶች:-

ዘወትር ጸሎት
◎ ውዳሴ ማርያም
◎ አንቀጸ ብርሃን
◎ መልክዐ ማርያም
◎ መልክዐ ኢየሱስ
◎ ዳዊት
◎ ገድላት
◎ ድርሳናት
◎ ስንክሳር እንዲሁም ሌሎች የንባብ ትምህርቶች እንደ ተማሪው ምርጫ ይሰጣል።
.

.
.
◆ መልሱን በውስጥ መስመር ማለትም @Ethiogeezmedia [0913514905] የሚለውን ጠቅ አድርጋችኹ ላኩልኝ።

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ!
የበለጠ ለማግኘት
[
https://t.me/Yeweketmaed]

ቅዳሜ : ነሐሴ ፬ /፳፻፲፮ ዓ.ም
.
.
.

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

10 Aug, 01:19


.
.
.
   "የክፍል ስድስት ጥያቄዎች መልስ"

◆ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ስድስት ያሉትን ጥያቄች እስከ መልሳቸው ለማግኘት ከታች ያለውን ይጫኑ። 

📌 https://t.me/yeweketmaed/759

፩] ዳ

◆ "አእመራ" ለሚለው ቃል  ትክክለኛው ሥርዐተ ንባቡን ለመናገር የቃሉን አመጣጥ በዐረፍተ ነገር ውስጥ ማየት አለብን።
◆ "አእመራ" የሚለው ቃል ኹለት ትርጕም አለው።
፩] ውእቶን አንስት አእመራ =እነዚያ ሴቶች ዐወቁ
◎ በዚህ ጊዜ ሥርዐተ ንባቡ "ተነሽ" ይኾናል።
፪] ኹለተኛ ትርጕሙ ደግሞ " አእመራ = ዐወቃት" ማለት ሲኾን ሥርዐተ ንባቡ ወዳቂ ነው።
◎ ማን? = እሱ።
   ◎ ማንን? = እሷን።
◆ ከዚህ በፊት እንዳየነው ይህ ዐይነት የርባታ መንገድ መሠሪ (ዝርዝር) ርባታ ይባላል። ወደፊቱ በሰፊው እንማማራለን።

◆ ስለዚህ አእመራ የሚለውን ቃል በገድላትበድርሳናት ፣ ወይም በተለያዩ መጻሕፍት ላይ ብናገኘው በትክክል ለማንበብ አገባቡን ማወቅ አለብን ማለት ነው። በዚህ ተመሳሳይም ሌሎች የግስ ርባታ ተመኵሳይያን አሉ ወደፊት ቀስ በቀስ እናያቸዋለን።




፪] ዳ
ቀተሉ = ገደሉ
    ◎ እነማን? = እነሱ።
    ◎ ማንን? = አይታወቅም
ቀተሎ = ገደለው
◎ ማን? = እሱ።
    ◎ ማንን? = እሱን።
አእመሮ = ዐወቀው
    ◎ ማን? = እሱ።
    ◎ ማንን? = እሱን።
◆ ስለዚህ ትክክለኛው "መሠሪ ርባታ" ማለት ደግሞ ባለቤቱን እና ተሳቢውን በግልጽ የሚያሳውቅ የርባታ መንገድ ስለኾነ ትክክለኛ መልሱ "ዳ= ቀተሎ እና አእመሮ" ይኾናል ማለት ነው።

፫]  አ
◆ አንድ ቃል በኀምስ ፊደል ከጨረሰ (ከደረሰ) ሥርዐተ ንባቡ ኹሌም ወዳቂ ነው። ማብራሪያው ከዚህ በፊት ባሉት ጥያቄ እና መልሶች ተገልጿል።

፬] ቡ

◆ ከዚህ በፊት ከግስ የሚወጡ ዘሮች ብለን ዘመድ ዘር እና ምእላድ ዘር'ን ተመልክተናል።
◆ ዛሬ ደግሞ ባዕድ ዘር የሚለውን እንመልከት።
"ባዕድ ዘር" የምንለው ከግስ የሚወጣ እና እንደ ስም የሚያገለግለን ፤ ከስሙ መጀመሪያ ላይ ከግሱ ያልነበረ ዐዲስ ፊደል የሚጨምር ነው።
ለምሳሌ:-
ኀደረ = ዐደረ
[በዚህ ግስ ላይ ያሉ ፊደላት "ኀ" ፣ "ደ" እና "ረ" ናቸው።] ከነዚህ ውጭ የኾነ ፊደል ከስሙ በፊት ካመጣ "ባዕድ ዘር" ይባላል።
◎ "ማ" + ኀደረ = ማኅደር ➼ ማደሪያ
ማኅደር በሚለው ውስጥ "ማ" የተባለች ባዕድ ፊደል ከግሱ ቀድማ በመገኘቷ ባዕድ ዘር ይባላል ።

፭] ቡ እና ጊ ኹለቱም መልስ መኾን ይችላሉ።

◆ ቀተለከ ➜ "ገደለ" ሳይኾን "ገደለኽ" ነው።
◆ ቀተሎ ➜ ገደለው
◆ ቀተለነ ➜ ገደለን
◆ ይቅትለነ ➜ ይገድለናል
[◎ "ይቅትለነ" የሚለው ትክክለኛ ትርጕሙ "ይገድለን ዘንድ" ወይም "ይግደለን" ነው።

ማስታወሻ:-

◎ በጥያቄ እና መልሱ ለምትሳተፉ አባላት ቃል በገባኹላችኹ መሠረት ምናልባት የንባብ ትምህርት መማር የምትፈልጉ ካላችኹ ከታች ባለው Link መግባት ትችላላችኹ።

ንባብ ቤት :-
👉https://t.me/+nF5N-biCtTwyMjQ0

የሚሰጡ ትምህርቶች:-

ዘወትር ጸሎት
◎ ውዳሴ ማርያም
◎ አንቀጸ ብርሃን
◎ መልክዐ ማርያም
◎ መልክዐ ኢየሱስ
◎ ዳዊት
◎ ገድላት
◎ ድርሳናት
◎ ስንክሳር እንዲሁም ሌሎች የንባብ ትምህርቶች እንደ ተማሪው ምርጫ ይሰጣል።
.

.
.
በጥያቄ እና መልሱ ላይ ጥያቄ ወይም አስተያየት ካላችኹ በ 0913514905 Telegram ላይ ጻፉልን።
👉 [
@Ethiogeezmedia]

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ!
የበለጠ ለማግኘት
[
https://t.me/Yeweketmaed] ላይ ይግቡ።

ቅዳሜ : ነሐሴ ፬ /፳፻፲፮ ዓ.ም
.
.
.

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

08 Aug, 22:11


.
.
.
   "የክፍል ስድስት ጥያቄዎች"

◆ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል አምስት ያሉትን ጥያቄች እስከ መልሳቸው ለማግኘት ከታች ያለውን ይጫኑ። 

📌 https://t.me/yeweketmaed/759

፩] "አእመራ" ለሚለው ቃል  ትክክለኛው ሥርዐተ ንባብ የቱ ነው?

አ) ወዳቂ
ቡ) ተነሽ
ጊ) ተጣይ
ዳ) አ እና ቡ

፪] ከሚከተሉት ውስጥ "መሠሪ ርባታን" የሚያመለክተው የቱ ነው?

አ) ቀተሉ
ቡ) ቀተሎ
ጊ) አእመሮ
ዳ) ቡ እና ጊ

፫]  ኹሌም ሥርዐተ ንባቡ "ወዳቂ" የሚኾን ቃል የቱ ነው?

አ) በ ኀምስ የደረሰ
ቡ) በ ሳድስ የደረሰ
ጊ) በ ሳብዕ የደረሰ
ዳ) አልቦ አውስኦት (መልስ የለም]

፬] "ማኅደር" የሚለው ቃል  "ኀደረ" ከሚለው ግስ የወጣ __ነው።     

አ) ዘመድ ዘር
ቡ) ባዕድ ዘር
ጊ) ጥሬ ዘር
ዳ) ጉልት

፭] ከሚከተሉት ውስጥ በትክክል የተቀመጠው የቱ ነው?

አ) ቀተለከ ➜ ገደለ
ቡ) ቀተሎ ➜ ገደለው
ጊ) ቀተለነ ➜ ገደለን
ዳ) ይቅትለነ ➜ ይገድለናል

ማስታወሻ:-

◎ በጥያቄ እና መልሱ ለምትሳተፉ አባላት ቃል በገባኹላችኹ መሠረት ምናልባት የንባብ ትምህርት መማር የምትፈልጉ ካላችኹ ከታች ባለው Link መግባት ትችላላችኹ።

ንባብ ቤት :-
👉https://t.me/+nF5N-biCtTwyMjQ0

የሚሰጡ ትምህርቶች:-

ዘወትር ጸሎት
◎ ውዳሴ ማርያም
◎ አንቀጸ ብርሃን
◎ መልክዐ ማርያም
◎ መልክዐ ኢየሱስ
◎ ዳዊት
◎ ገድላት
◎ ድርሳናት
◎ ስንክሳር እንዲሁም ሌሎች የንባብ ትምህርቶች እንደ ተማሪው ምርጫ ይሰጣል።
.

.
.
◆ መልሱን በውስጥ መስመር ማለትም @Ethiogeezmedia [0913514905] የሚለውን ጠቅ አድርጋችኹ ላኩልኝ።

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ!
የበለጠ ለማግኘት
[
https://t.me/Yeweketmaed]

ኀሙስ : ነሐሴ ፪ /፳፻፲፮ ዓ.ም
.
.
.

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

08 Aug, 03:34


.
.
.
   "የክፍል አምስት ጥያቄዎች መልስ"

◆ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል አራት ያሉትን ጥያቄች እስከ መልሳቸው ለማግኘት ከታች ያለውን ይጫኑ። 

📌 https://t.me/yeweketmaed/759

፩] ጊ

በደቂቅ ርባታ ጊዜ ማለትም ግሶች በመራሕያን በቀዳማይ አንቀጽ ብቻ በሚረቡበት ጊዜ ሥርዐተ ንባባቸው እንደ መራሒው ይለያያል።

◆ንባባቸው ተነሽ የኾኑ
   ◎ አነ ➜ ቀተልኩ
   ◎ ንሕነ ➜ ቀተልነ
   ◎ ውእቱ ➜ ቀተለ
   ◎ ውእቶሙ ➜ ቀተሉ
   ◎ አንተ ➜ ቀተልከ
  ◎ አንትሙ ➜ ቀተልክሙ
   ◎ አንቲ ➜ ቀተልኪ
   ◎ ውእቶን ➜ ቀተላ ናቸው።

◆ንባባቸው ሰያፍ የኾኑ
   ◎ ይእቲ ➜ ቀተለት

◆ንባባቸው ተጣይ የኾኑ
   ◎ አንትን ➜ ቀተልክን


፪]  ጊ

◆ ሦስት ዐይነት የግስ ርባታ አለ።
    ◎ ደቂቅ ርባታ ➜ አንድን ግስ በዐሥሩ መራሕያን ቀዳማይ አንቀጹን ብቻ የማርባት ሒደት ነው። ከላይ እንዳረባነው ማለት ነው። በዚህ ርባታ ባለቤቱ ብቻ እንጅ ተሳቢው አይታወቅም።
    ◎ ንኡስ ርባታ ➜ አንድን ግስ በዐሥሩ መራሕያን ከ ቀዳማይ እስከ ትእዛዝ የማርባት ሒደት ነው። በዚህ ርባታ'ም ባለቤቱ ብቻ እንጅ ተሳቢው አይታወቅም።
    ◎ ቀተለ = ገደለ
    ◎ ይቀትል = ይገድላል
    ◎ ይቅትል = ይገድል ዘንድ
    ◎ ይቅትል = ይግደል
◎ ዝርዝር (መሠሪ) ርባታ ➜ ይህ ግስ በአንድ ጊዜ ባለቤቱን እና ተሳቢውን የሚይዝ የርባታ ዐይነት ነው።
ምሳሌ:-
      ◎ ቀተለከ  = ገደለኽ
      ◎ ይቀትለከ  = ይገድልኻ
      ◎ ይቅትልከ   = ይገድልኽ ዘንድ
      ◎ ይቅትልከ  = ይግደልኽ

◆ በዚህ ግስ ላይ ባለቤቱን ለማወቅ ማን? ብለን እንጠይቃለን መልሱም "እሱ" ይኾናል።
◆ ተሳቢውን ለማወቅ ደግሞ ማንን? ብለን እንጠይቃለን መልሱም አንተን ይኾናል።

◆ ስለዚህ ባለቤቱን እና ተሳቢውን በአንድ አስተባብሮ የሚይዝ የርባታ ዐይነት ዝርዝር ( መሠሪ) ርባታ ይባላል ማለት ነው።

፫]  ዳ
◆ ማብራሪያውን ከክፍል ፬ ይመልከቱ።

፬] አ
ዘመድ ዘር በግስ ርባታ ጊዜ ከምናገኛቸው ዘሮች ውስጥ አንዱ ሲኾን የነገሮች ስም በመኾን ያገለግላል።
◆ ከግሱ ላይ ያልነበረ ፊደል አይጨምርም።
◆ ኹሌም በሳድስ ብቻ ይጨርሳል።

፭]
◆  ከአንድ ግስ የሚወጡ ዘሮች መድረሻ ፊደላቸውን ፣ አገልግሎታቸውን ፣ ከግሱ ያልነበረ ተጨማሪ ፊደል መያዝ አለመያዛቸውን በመመልከት የተለያዩ ስያሜዎች አላቸው።
◆ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ምእላድ ዘር ይባላል።
◆ ምእላድ ዘር ከግሱ ያልነበረ ፊደል በቃሉ መጨረሻ ብቻ እየጨመረ የሚመሠረት የዘር ዐይነት ነው።
◆ ስላዚህ መሬት የሚለው ዘር "አግመረ=ቻለ" ከሚለው ግስ የወጣ ምእላድ ዘር ነው።
መሬት ኹሉን ነገር ስለምትሸከም እና ስለምትችል በምስጢር የተገናኘ አወጣጥ ነው።


ማስታወሻ:-

◎ በጥያቄ እና መልሱ ለምትሳተፉ አባላት ቃል በገባኹላችኹ መሠረት ምናልባት የንባብ ትምህርት መማር የምትፈልጉ ካላችኹ በውስጥ መስመር ጻፉልኝ።

የሚሰጡ ትምህርቶች:-

ዘወትር ጸሎት
◎ ውዳሴ ማርያም
◎ አንቀጸ ብርሃን
◎ መልክዐ ማርያም
◎ መልክዐ ኢየሱስ
◎ ዳዊት
◎ ገድላት
◎ ድርሳናት
◎ ስንክሳር እንዲሁም ሌሎች የንባብ ትምህርቶች እንደ ተማሪው ምርጫ ይሰጣል።
.

.
.
◆ መልሱን በውስጥ መስመር ማለትም @Ethiogeezmedia [0913514905] የሚለውን ጠቅ አድርጋችኹ ላኩልኝ።

የበለጠ ለማግኘት ከዚህ ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ!
👉 https://t.me/yeweketmaed

ኀሙስ : ነሐሴ ፪/፳፻፲፮ ዓ.ም
.
.
.

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

06 Aug, 04:40


.
.
.
   "የክፍል አምስት ጥያቄዎች"

◆ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል አራት ያሉትን ጥያቄች እስከ መልሳቸው ለማግኘት ከታች ያለውን ይጫኑ።

📌 https://t.me/yeweketmaed/759

፩] "ቀተልክን" ለሚለው ቃል ትክክለኛው ሥርዐተ ንባብ የቱ ነው?

አ) ወዳቂ
ቡ) ሰያፍ
ጊ) ተጣይ
ዳ) ተነሽ

፪] "ባለቤቱን" እና "ተሳቢውን" በአንዴ የሚያሳይልን የ "ርባታ" ዐይነት የቱ ነው?

አ) ንዑስ
ቡ) ደቂቅ
ጊ) ዝርዝር (መሠሪ)
ዳ) አልቦ አውስኦት [መልስ የለም]

፫]  የቃሉ መድረሻ ሳድስ ኾኖ ድምፁ "ቆጣ" እና "ከፍ ባለ ድምፅ ከተነበበ የቃሉ "ሥርዐተ ንባብ" ____ነው።

አ) ተነሽ
ቡ) ተጣይ
ጊ) ወዳቂ
ዳ) ሰያፍ

፬] "ጦማር" የሚለው ቃል "ጦመረ" ከሚለው ግስ የወጣ __ነው።

አ) ዘመድ ዘር
ቡ) ባዕድ ዘር
ጊ) ጥሬ ዘር
ዳ) ጉልት

፭] "መሬት" የሚለው ቃል ____ነው።

አ) ምእላድ ዘር
ቡ) ባዕድ ከምእላድ
ጊ) ዘመድ ዘር
ዳ) ጥሬ ዘር

ማስታወሻ:-

◎ በጥያቄ እና መልሱ ለምትሳተፉ አባላት ቃል በገባኹላችኹ መሠረት ምናልባት የንባብ ትምህርት መማር የምትፈልጉ ካላችኹ በውስጥ መስመር ጻፉልኝ።

የሚሰጡ ትምህርቶች:-

ዘወትር ጸሎት
◎ ውዳሴ ማርያም
◎ አንቀጸ ብርሃን
◎ መልክዐ ማርያም
◎ መልክዐ ኢየሱስ
◎ ዳዊት
◎ ገድላት
◎ ድርሳናት
◎ ስንክሳር እንዲሁም ሌሎች የንባብ ትምህርቶች እንደ ተማሪው ምርጫ ይሰጣል።
.

.
.
◆ መልሱን በውስጥ መስመር ማለትም @Ethiogeezmedia [0913514905] የሚለውን ጠቅ አድርጋችኹ ላኩልኝ።

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ!
[
@Yeweketmaed]

ሠሉስ : ሐምሌ ፴/፳፻፲፮ ዓ.ም
.
.
.

ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ➺Ethio Geez Media

04 Aug, 18:53


.
.
.
በነገራችን ላይ የቅኔ ትምህርት መማር የምትፈልጉ ከዚህ ቡድን ብትገቡ የበለጠ ተጠቃሚ ትኾናላችኹ!

https://t.me/p09Geez
መምህር ጳውሎስ ብርሃኔ!
.
.
.