የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

@mrtababl


🔥ድንቅ አዝናኝና አስተማሪ አባባሎች
🔥የሳይኮሎጂ ምክሮችን ለማግኘት
ይቀላቀሉ

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

27 Sep, 14:31


1. ‹‹ ሠላምን በጉልበት ማስጠበቅ አይቻልም፡፡ ሠላምን ማስጠበቅ የሚቻለው በመግባባት ብቻ ነው፡፡ ››

2. ‹‹ ስህተት ሠርቶ የማያውቅ ሠው ምንም ነገር ሞክሮ አያውቅም ማለት ነው፡፡ ››

3. ‹‹ ሁሉም ሠው ብሩህ ጭንቅላት አለው፡፡ ነገር ግን አሣን ዛፍ መዝለል አይችልም ብለህ ችሎታውን ካጣጣልከው በህይወትህ ሙሉ አሣ ደደብ እንደሆነ ታስባለህ፡፡ ››

4. ‹‹ ዓይነ ሕሊና ከዕውቀት የላቀ አስፈላጊ ነው፡፡ ››

5. ‹‹ ትምህርት አዕምሯችን የበለጠ እንዲያስብ እንጂ ጥሬ ሃቆችን ለመለማመድ አይደለም፡፡ ››

6. ‹‹ ሙከራህን እስከምታቆም ድረስ በህይወት አትሸነፍም፡፡ ››

7. ‹‹ አንድን ነገር በቀላል ቋንቋ መግለፅ ካልቻልክ ነገሩን አልተረዳኸውም ማለት ነው፡፡ ››

8. ‹‹ እብደት ማለት አንድን ነገር በተመሳሳይ ዘዴ ደግሞ ደጋግሞ በመስራት የተለየ ውጤት መጠበቅ ነው፡፡ ››

9. ‹‹ ደስተኛ ሕይወት ለመኖር ከፈለግክ አንተነትህን ከሠዎች ወይም ከነገሮች ጋር ከማወዳደር ይልቅ ከግብህ ወይም ከዓላማህ ጋር ራስህን እሠር፡፡ ››

10. ‹‹ ስኬታማ ለመሆን ከፈለግክ የስኬት ፍላጎትህ እወድቃለሁ ብለህ ከምትፈራው ፍርሃትህ በእጅጉ የበለጠ መሆን አለበት፡፡ ››

11. ‹‹ መቀራረብ በፍቅር ለመውደቅ ዋስትና አይሆንም፡፡ ››

12. ‹‹ ዋጋ ያለህ ሠው ለመሆን ሞክር እንጂ ስኬታማ ብቻ ለመሆን አትሞክር፡፡ ››

13. ‹‹ ምክንያታዊነት ከአንድ ቦታ አንስቶ ወደሌላ ቦታ ሊወስድህ ይችላል፡፡ ዓይነ ሕሊና ግን የትም ይወስድሃል፡፡ ››

14. ‹‹ ጎበዝ ሠው ችግሮችን ይፈታል፡፡ ብልህ ሠው ግን ችግሮቹ መልሠው እንዳይፈጠሩ ያስወግዳቸዋል፡፡ ››

15. ‹‹ ተፈጥሮን በጥልቀት ተመልከት፡፡ ያን ጊዜ ሁሉንም ነገሮች በተሻለ ትረዳለህ፡፡ ››

16. ‹‹ ሴቶች ብዙ ጊዜ የሚጨነቁበት ወንዶች ጨርሠው በረሷቸው ነገሮች ላይ ነው፡፡ ወንዶችም ብዙ ጊዜ የሚጨነቁበት ጉዳይ ሴቶቹ በማያስታውሷቸው ነገሮች ላይ ነው፡፡ ››

17. ‹‹ ቅዱሱን ጉጉትህን አትጣለው፡፡ ››

18. ‹‹ የአመለካከት ድክመት እየቆየ ሲሄድ የባህሪ ድክመት ይሆናል፡፡ ››

19. ‹‹ ሞትን መፍራት ማለት ተገቢ ባልሆኑ ፍርሃቶች መንቦቅቦቅ ነው፡፡ ምንም ስጋት የሌለበት ሠው ቢኖር የሞተ ሠው ብቻ ነው፡፡ ››

20. ‹‹ ፍፁም የማይመስለውን የሚሞክሩ የማይቻለውን የሚችሉ ናቸው፡፡

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

18 Jun, 18:22


እንድን ሰው ለመለወጥ ካልወሰነ በቀር ማንም ሰው ሊለውጠው አይችልም።

https://t.me/mrtababl

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

14 Jun, 17:58


ጠዋት ከእንቅልፍ ስንነቃ ሁለት ቀላል ምርጫዎች አሉን ተመልሰን ተኝተን ማለም ወይንም ነቅተን ህልሞቻችንን ማሳደድ።
ምርጫው የእኛ ነው


https://t.me/mrtababl

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

20 May, 13:43


ሁሉም ነገር ትልቅ ይመስለናል ስለማናውቀው። የሆነ ጊዜ ስለ እዛ ነገር አለማወቃችን፤ ያን ነገር አለማድረጋችን አስፍረናል ሲገባን ግን እናፍርበታለን። ከዛሬ 6 7 አመት በፊት የዩንቨርስቲ ተማሪ ሆኜ ስለ ኳስ ብዙም እውቀቱ አልነበረኝም እና በራሴ አፍር ነበር ። ልጆች ስለ ኳስ ስያወሩ እንደ ማውቅ ሆኜ ከእነሱ ቁጭ ብዬ አወራ ነበር። የሆነ ተጫዋች ስም ሲጠሩ ኦ አውቀዋለሁ እል ነበር ግን በጭራሽ አላውቀውም የጠሩትን ተጫዋች።

ከሆነ ጊዜ በኋላ ኳስ ማየት ጀመርኩ ትንሽም እዉቀቱ ኖረኝ...... ከሆነ ጊዜ በኋላ ግን ኳስ በማየቴ ማፈር ጀመርኩ ሰዎች ኳስ ታያለህ ሲሉኝ አይ ማለት ጀመርኩ ግን እመለከት ነበር።

አንዳንዴ ትልቅነት የሚመስሉን ነገር ግን ስብዕናችንን የሚያወርዱት ነገሮች ትልቅ መስሎ እርድና መስሎ ይታየናል። መጠጣት፣ መቃም፣ ሴት ማተራመስ ፣ማጨስ የመሳሰሉት። እርድና ሳይሆን ውድቀት ነው ለኛ።

source የመፅሐፍ መንደር

https://t.me/mrtababl

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

18 May, 22:54


እውነት ከሚናገር ሰው ይበልጥ የሚጠላ የለም።

ኘሌቶ

https://t.me/mrtababl

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

17 May, 05:38


💙 May is mental health awareness month. Mental health is essential to your overall well-being, and is just as important as your physical health.

If you’re experiencing distress:
🗣 Talk to someone you trust
🧘🏻‍♀ Look after your physical health
📖 Do activities you enjoy
🚭 Avoid harmful substances
🫱🏼‍🫲🏾Seek help from a professional

From WHO
https://t.me/mrtababl

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

15 May, 12:41


ከአጉል ሰዎች ጋር ያለን ወዳጅነት

የአንዳንድ ችግሮቻችን ምንጭ ከአጉል ሰዎች ጋር ያለን ወዳጅነት ወይም ግንኙነት ነው።አንዳንድ ሰዎች በህይወታችን ምንም አይነት value add ሳያደርጉ ጊዜያችንን እና እድሜያችንን ይሰርቃሉ።

የማይሆን ጓደኛ፣የማይሆን ፍቅረኛ፣የማይሆን የስራ ባልደረባ ከህይወታችን ዉድ ጊዜያችንን እና ማንነታችንን ማባከን የለበትም።

ስለዚህም አንዳንድ ጊዜ ችግሮች እንዲቀረፉና ሁኔታዎች እንዲለወጡ የግድ ከአንዳንድ ሰዎች የመለየትን እርምጃ መውሰድ ሊኖርብን ይችላል።

ይህንን ማድረግ ደግሞ ብዙም ላይቀለን ይችላል።መደረግ ካለበት ግን መደረግ አለበት።

Source Good Personality

👇👇👇👇join👇👇👇👇
https://t.me/mrtababl

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

13 May, 10:13


በሌሎች ደስታ መደሰት ስትጀምር ልብህ ያኔ ጤነኛ እንደሆነ ታረጋግጣለህ

https://t.me/mrtababl

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

09 May, 14:46


የ93 አመት እድሜ ባለጸጋ አዛውንት በድንገት ራሳቸውን ይስቱና መተንፈስ አቅቷቸው ወደ ሆስፒታል ይወስዳሉ። እናም ለ 24 ሰዓታት ኦክስጅን ተሰጥቷቸው ይቆያሉ። ከጥቂት ሰዓት በኋላ ተሽሏቸው ወደቤታቸው እንዲመለሱ ተወሰነ።  ዶክተሩም ‘’እስካሁን ለተደረገልዎት የህክምና እርዳታ 5000 ዶላር መክፈል ይጠበቅብዎታል’’ ይልና ሂሳቡን ያሳያቸዋል። 

አዛውንቱም ሂሳቡን አይተው ማልቀስ ጀመሩ።  ዶክተሩ በሂሳቡ ምክንያት ከሆነ እንዳያለቅሱ ነገራቸው። አዛውንቱ ግን "በገንዘብ ምክንያት አላለቅስም።  ገንዘቡን በሙሉ መክፈል እችላለሁ።  ያለቀስኩበት ምክንያት ለ 24 ሰአታት ኦክሲጅን በመጠቀሜ 5000 ዶላር መክፈል አለብህ አላችሁኝ።  ነገር ግን 93 አመት ሙሉ ፈጣሪዬ የሰጠኝን አየር ስተነፍስ ቆይቻለሁ።  ግን ይህን ያህል ዘመን ምንም አልከፍልም ነበር። ከፈጣሪዬ ምን ያህል ዕዳ እንዳለብኝ ታውቃለህ? ይህ ቸርነቱ ነው ያስለቀሰኝ።’’ ብለው መለሱለት።

ዶክተሩም አንገቱን ደፍቶ ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ።

ይህን ለምታነቡ ሁሉ፣ ለፈጣሪ ምንም የምንከፍለው ነገር ሳይኖር ለዓመታት ነፃ አየር ስንተነፍስ ኖረናል፣ እንኖራለንም።  

በህይወታችን ውስጥ ይህን ሁሉ በገንዘብ የማይተመን አገልግሎት በነፃ ለሰጠን ፈጣሪያችን 2 ሰከንድ ብቻ ወስደን ማመስገን ይከብደናል?

እስቲ ፈጣሪያችንን እናመስግነው!
--------------
ምንጭ የላቀ ዕይታ

https://t.me/mrtababl

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

06 May, 17:14


1. “ሁል ጊዜ አንተው ያመንክበትን ሕይወት መኖርህን እርግጠኛ ሁን፡፡”

2.  “ልክህን እወቅ፣ ለስራህና ለሕይወትህ መርህና ገደብ ይኑርህ፡፡”

3.  “ማንነትህን፣ ኑሮህንም ሆነ የሰራሃቸውን ስህተቶች አሻሽላቸው እንጂ አትፈርባቸው፡፡”

4.  “ከወዳጆችህ ጋር ነጻ የሆነን ግንኙነት መስርት፣ ግልጽነትና የቀረበ ወዳጅነት ቢጎዳህም ከጉዳቱ ጥቅሙ ይበልጣልና በፍጹም አትሽሽ፡፡”

5.  በመጨረሻ፣ ሁል ጊዜ ደስተኛ መሆንን ምረጥ፡፡ የሕይወት ቀንደኛ ዓላማዎች ከሚባሉት ውጤቶች መካከል ደስተኛነት አንዱ ነውና፡፡

(“የሕይወት ጸጸቶች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

https://t.me/mrtababl

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

04 May, 19:45


“እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።”
  — ማቴዎስ 28፥6

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

https://t.me/mrtababl

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

04 May, 15:34


ቻርሊ ቻፕሊን አንድ ቀን ህዝብ ተሰብስቦ ወደሚጠብቀው አዳራሽ አመራ።  በጭብጨባ ከተቀበሉት በኋላ ወደ መድረክ እንዲወጣ ተጋበዘ።

#በመጀመርያ የሚያምር ቀልድ ነገራቸው። አዳራሹ በፉጨት ተቀወጠ በሳቅ ደመቀ።

ከዚያም ያንኑ ቀልድ #ለሁለተኛ ጊዜ ደገመላቸው። ግማሾቹ ሳቁ፤ ግማሾቹ ደግሞ ግራ ተጋቡ....

#ለሶስተኛ ጊዜ አሁንም ያንኑ ቀልድ ደገመው። በዚህ ጊዜ ግን አንድም የሚስቅ ሰው አልነበረም።

ያኔ ቻርሊ በጣም ደስ አለው። ከዛም የሚከተለውን ንግግር ተናገረ..

"በአንድ ቀልድ ደጋግማችሁ እንደማትስቁ ሁሉ ስለምን በአንድ ነገር ደጋግማችሁ ታለቅሳላችሁ?

ህይወትኮ እጅግ ውብ ናት" ዛሬ በህይወት ካላችሁ ነጋችሁን ማስተካከል ትችላላችሁ።

በትላንት ውስጥ ስላጣችሁት ነገር አታስቡ ዛሬን ብቻ በህይወት በመኖራችሁ ፈጣሪን አመስግኑ።

ዛሬ ጠንካራ ከሆናችሁ ነጋችሁ የተዋበ ይሆናል፤ ነጋችሁ የሚጥም ይሆናል። አሁንም አሁንም አሁንም በህይወት መኖራችሁን ብቻ እያያችሁ  ፈጣሪን አመስግኑ!

#ወዳጆቼ ከተሰጠን ስጦታዎች ሁሉ ህይወታችን ይበልጣልና በህይወት ካላችሁ በነጋችሁ ላይ ለውጥ መፍጠር ትችላላችሁ።"
---------------------------------
ምንጭ የላዕቀ ዕይታ

https://t.me/mrtababl

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

30 Apr, 18:02


ምንም ነገር ለዘለዓለም አይቆይም!

ምንም እንኳን ብዙ ዓመታትን ቢያስቆጥር፣ አንበሳ ተጎሳቁሎ መሞቱ አይቀርም። ይህ የዓለም እውነታ ነው። አንበሶች በዘመናቸው ገዥ ናቸው። ሌሎች እንስሳትን ያሳድዳሉ፣ ይይዛሉ፣ ይጎትታሉ፣ ይበላሉ፤ ትራፊያቸውንም ለጅቦች ሳይቀር ትተውላቸው ይሄዳሉ።

ነገር ግን እድሜ ፈጣኑ እገሰገሰ ከች ይላል። ያረጀው አንበሳ ማደን አይችልም። መግደል አይችልም፣ ራሱን እንኳን መከላከል አይችልም።  ከቦታ ቦታ ይዘዋወራል፣ ያገሳል። ግን እድል አይቀናውም።  በጅቦች መንጋ ውስጥ ይወድቅና ከነ ሕይወቱ ይበላል። ጅቦቹ እስኪሞት እንኳን አይጠብቁትም።

ሕይወት አጭር ናት። ኃያልነትም ጊዚያዊ ነው። አካላዊ ውበትም ጊዜው  እጅግ አጭር ነው። በአንበሳ ማየት ይቻላል። እርጅና በተጫጫናቸው ሰዎችም ማየት ይቻላል። ማንኛውም ረጅም እድሜ የኖረ ሰው የደካማነትና አቅመቢስነት ጊዜው ላይ የሆነ ወቅት ላይ መድረሱ አይቀርም።

ስለዚህም፣
ምንም እንኳን አንበሶቹ በተፈጥሯቸው አዳኝ ስለሆኑ የሕይወት መስመራቸውን መቀየር የማይችሉ ቢሆንም፣ የሰው ልጅ ግን በተሰጠው ከፍተኛ የአስተሳሰብ ጥበብ ሁሉን ነገር መቀየርና ማስተካከል የሚችል ፍጡር ነው። እናም ትሕትናን እንላበስ፣ የደከሙትን፣ የታመሙትን፣ የተጠቁትን እንርዳ። ከሁሉ በላይ መርሳት የሌለብን አንድ ቀን መድረኩን ለቀን እንሄዳለን።

ምንጭ psych addis

https://t.me/mrtababl

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

29 Apr, 13:32


ጥናት!

ተመራማሪዎች በቀን ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ የእግር ጉዞ ማድረግ የአዕምሯችንን አቅም ለማሳገድ እንደሚረዳ አስታወቁ።

አዲስ የተሰራ የኒውሮሳይንስ ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ ለ20 ደቂቃ የእግር ጉዞ ማድረግ የአዕምሯችን አዲስ መረጃ ለመውሰድና ለመያዝ እንዲዘጋጅ ያደርገዋል።

በተለይም ውሳኔ ለመስጠት፣ ጭንቀትን ለመቆጣጠርና፣ በባህሪያችን ዙሪያ የሚያቅደው የአእምሯችን ክፍል ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ እንዳለው ነው ተመራማሪዎች ያስታወቁት።

ሌሎች አይነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች የአዕምሮ ጤናን ለመጠበቅ እንደሚረዱ የሚታወቅ ቢሆንም፤ ይህኛው ጥናት ግን የግር ጉዞ እና የአእምሮ አቅም ላይ ትኩረትን ያድረገ እንደሆነም አስታውቀዋል።

በዚህም በቀን ለ20 ደቂቃ እና ከዚያ በላይ የእግር ጉዞ ማድረግ የአእምሮን አቅም እንደሚያሳድግ እና ምንም እንቅስቃሴ ካለማድረግ የተወሰነ የእግር ጉዞ ማድረግ እንደሚሻልም ጥናቱ አመላክቷል።

የሳንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ጥናቱን ባከናወኑበት ወቅት ተሳታፊዎች የእግር ጉዞ የሚያደርጉ እና የማያደርጉትን በመለየት ክትትል ያደረጉ ሲሆን፤ በዚህም ለ20 ደቂቃ የእግር ጉዞ የሚያደርጉ ሰዎች ተቀምጠው ከሚውሉት የተሻለ ሆነው ተገኝተዋል።

ተመራማሪዎች የአእምሮ እንቅስቃሴን በኤሌክትሮኤንሴፋሎግራፊ (ኢኢጂ) መለካት ምን እየተፈጠረ እንዳለ የተመለከቱ ሲሆን፤ በዚህም የእግር ጉዞ የሚያደርጉ ሰዎች ላይ ተጨባጭ እና አወንታዊ ተፅእኖዎችን አይተዋል።

ምንጭ Psychology zone

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

11 Apr, 07:56


ገንዘብ ቁጥር ነው። ቁጥር ደግሞ መጨረሻ የለውም።

ደስታን በገንዘብ በኩል የምትፈልግ ከሆነ ፍለጋህ መጨረሻ የለውም።

https://t.me/mrtababl

የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ምርጥ አባባሎች

04 Apr, 04:20


 
‹‹ ጎበዝ ሠው ችግሮችን ይፈታል፡፡ ብልህ ሠው ግን ችግሮቹ መልሠው እንዳይፈጠሩ ያስወግዳቸዋል፡፡ ››

https://t.me/mrtababl