🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤 @zena_tewahido Channel on Telegram

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

@zena_tewahido


ኦርቶዶክስ ኖት????

የዚህ ቻናል ዋና ዓላማ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮችን እና ትምህርቶችን ለሕዝብ ክርስቲያ ማስተላለፍ ነው።
ቤተሰብ ለመሆን ምንም መስፈርት አያስፈልግም ኦርቶዶክስ መሆን በቂ ነው ::
ለመረጃ
🤳🤳🤳🤳🤳
OWNER 🕺👉 @temaye

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤 (Amharic)

ኦርቶዶክስ ኖት????nnየዚህ ቻናል ዋና ዓላማ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮችን እና ትምህርቶችን ለሕዝብ ክርስቲያ ማስተላለፍ ነው። ቤተሰብ ለመሆን ምንም መስፈርት አያስፈልግም ኦርቶዶክስ መሆን በቂ ነው:: ለመረጃ 🤳🤳🤳🤳🤳 OWNER 🕺👉 @temayennለበለጠ መረጃዎችን እና ተመልከቱን ለማግኘት እናመሰግናለን! በስሜት ለብርቱጤ ኦርቶዶክስ ኖቶች ከተወሰኑትና ከተከበሩት ጋር እንገልጻለን።

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

21 Nov, 16:27


✝መስቀሉን  ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቻናል ለህይወታችሁ ጠቃሚ ስለሆነ መስቀሉን  ይጫኑ Join ይበሉት
/Start      

                  🔳🔳
                  🔳🔳
         🔳🔳🔳🔳🔳🔳
         🔳🔳🔳🔳🔳🔳
                  🔳🔳
                  🔳🔳
                  🔳🔳
                  🔳🔳

         መስቀሉ አርማችን ነው።

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

21 Nov, 15:59


💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

20 Nov, 04:10


ቅዱስ ሚካኤል በኃይላት መላእክት ላይ የተሾመበት በዓለ ሢመቱ ኅዳር ፲፪ ቀን በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ይከበራል፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ‹ሚካኤል ሥዩም በዲበ ኃይላት፤ በኃይላት ላይ የተሾምክ ሚካኤል› ሲል ያመሰገነው (መጽሐፈ አክሲማሮስ)

ሚካኤል ማለት መሐሪ ወመስተሣህል ዕፁብ ማለት ነው ።
አንድም፦ መኑ ከመ አምላክ (እንደ አምላክ ማን አለ) ማለት ነው።

✝️ የመላእክት አለቃ ስለመሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልጿል: -
" ለሰው ባደረገው በጎነት ላይ ለሕዝቡ ታዛዥ ነውና ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ሚካኤል ነው። " መ. ሄኖ 6 እንዲል

“እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ”(ኢያ.5፡13)

" በዚያም ዘመን ስለሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል ... ." ( ት.ዳን 12፥1)

" ከዋነኛዎቹ አለቃዎች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ " ( ት.ዳን 10፥13 )

"የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር። ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።" (የይሁዳ መልእክት 1፥9)

እኛንም መልአኩን ልኮ ከዕለት ዕኪት ከዘመን መንሱት ይጠብቀን

https://t.me/zena_tewahido

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

20 Nov, 04:08


ምግባችንን አውጥተን ለነዳያን መስጠትና መንፈሳዊ ጉዞ በምናከናውንበት ወቅት አውጥተን መጠቀም እንዳንችል ተደርጓልም ብለዋል፡፡ 

የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ኀላፊ አቶ አበበ በዳዳ ዩንቨርሲቲው በመጀመሪያው ረቂቅ መመሪያ ያወጣቸው ሕጎች ለኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች በጣም አስቸጋሪ ነበሩም ብለዋል፡፡

ነገር ግን በተማሪዎች በተቋቋመ ኮሚቴ በመመሪያው አንዳንድ አንቀጾች ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ በቀረበው አስተያየት መሠረት ከበፊቱ የተሻለ ቢሆንም አሁንም ግን የተማሪዎችን ሃይማኖታዊ መብት የሚጋፋ መመሪያ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የማስተባበሪያው ኀላፊ አክለውም በተለይም ነጠላን አላስፈላጊ ልብስ በማለት የተገለጸው መመሪያ አግባብነት የሌለው ነውም ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ይህ አካሄድ ሀገርን የማይጠቅም በመሆኑ ሊታሰብበት እንደሚገባ አሳስበው ዩንቨርሲቲው አሳማኝ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሰዎች በልዩ ሁኔታ ሃይማኖቱ የሚፈቅደውን አለባበስ መልበስ ይችላሉ የሚል መመሪያ ስላለው የሚመለከታቸው አካላት ውይይትና ምክክር እንዲያደርጉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

20 Nov, 04:08


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሃይማኖታዊ ነጻነታችንን የሚጋፋ መመሪያ አውጥቷል ሲሉ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ገለጹ፡፡

ተማሪዎቹ ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ያወጣውን የሥነ መግባርና ዲሲፕሊን መመሪያ ተከትሎ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ወደ መመገቢያ አዳራሽ ሲሄዱ ነጠላ እንዳይለብሱና ምግብ እንዳያወጡ ሃይማኖታዊ መብታቸውን የሚጋፋ የሥነ ምግባርና ዲሲፕሊን መመሪያ መውጣቱን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ኀላፊ አቶ አበበ በዳዳ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል።

አቶ አበበ በዳዳ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ኦርቶዶክሳውያን የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ሃይማኖታዊ የመብት ጥሰት እንዳይፈጸምባቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መወያየት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ዩንቨርሲቲው በ2017 ዓ.ም ባወጣው የሥነ ምግባር ዲስፕሊን መመሪያ የተለያዩ እምነት ተከታይ ተማሪዎች በግቢው ስለሚያስተናገዱ ከሃይማኖትና ከበዓላት ጋር የተያያዙ የአለባበስ ሥርዓቶች የማንነትና የእምነት መገለጫዎች በመሆናቸው ሊከበሩ ይገባቸዋል ይላል፡፡

በሌላ በኩል የኒቨርሲቲው ሃይማኖታዊ ነጻነታችንን የሚጋፋ መመሪያ አውጥቷል ሲሉ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በምግብ ሰዓት የህሊና ጸሎት ካልሆነ በቀር ጸሎት እንዳናደርግና ከዳቦ ውጭ ምግብ እንዳናወ እንዲሁም በመመግቢያ አዳራሽ ውስጥ ነጠላ እንዳንለብስ መመሪያ ወጥቷል ብለዋል፡፡

ተማሪዎች አክለውም የወጣውን መመሪያ ምክንያት በማድረግ በአንዳንድ የጥበቃ አካላትና ግለሰቦች ጫና እየተደረገብን ነው ሲሉም ጠቁመዋል፡፡

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

19 Nov, 07:15


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ  አሜን

ስንክሳር  ኅዳር 10

ቅድስት ሶፍያ ወቅዱሳት አንስት

እስኪ ዛሬ በጥቂቱ የተባረኩ (ቡሩካት) እናቶቻችን እንዘክር:: "ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ 'ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን ናትና::

+ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና::

+እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው::
1."ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ሰዎች (ቅዱሳን) ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት::

"ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ ማርያም)

2."ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በኋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና::

"ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ ያሬድ) ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)

3.ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና::

4.እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና::

+የእመ ብርሃን ይቆየንና ደግሞ ሌሎች ቅዱሳት እናቶቻችንን እንመልከት:: እናቶቻችን ስናከብር የምንጀምረው በቅድስት ሔዋን ነው:: ብዙ ጊዜ የእናታችን ሔዋን ጥፋቷ እንጂ በጐ ነገሯ: ደግነቷ: ንስሃዋ አይነገርላትም:: ሆኖም እናታችን ቅድስት ሔዋን ክብር የሚገባት ሴት ናት::

*ክርስቶስ ሰው የሆነ እርሷንና ልጆቿን ለመቀደስ ነውና:: "ከመ ይስዓር መርገማ ለሔዋን ዲበ ዕፅ ተሰቅለ" እንዲል:: (ድጓ)

+ቀጥሎ በብሉይ ኪዳን እነ ሐይከል: እድና: ሣራ: ርብቃ: አስኔት: ሲፓራ: ሐና: ቤርሳቤህን የመሰሉ እናቶቻችን በበጐው መንገድ ፈጣሪን ደስ አሰኝተዋል:: በዘመነ ሥጋዌም ቅዱሳቱ ሐና: ኤልሳቤጥ: ማርያም: ሶፍያ: ሰሎሜ: ዮሐና እና 36ቱ ቅዱሳት አንስት በጐነታቸው ያበራል::

+ከዚያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለ2,000 ዓመታት የተነሱ አእላፍ ቅዱሳት እናቶቻችንን ግን ዘርዝረን አንዘልቃቸውም:: በቅድስናቸው አራዊትን ያሰገዱ: ነገሥታትን ያንቀጠቀጡ: አጋንንቸትን የረገጡ: በዘንዶ ላይ የተጫሙ ብዙ እናቶችን ቤተ ክርስቲያን አፍርታለች::

+ዛሬም ቢሆን በበርሃና በከተማ በጐውን ጐዳና የተከተሉ ብዙ እናቶች እንዳሉን እናውቃለን:: አንድም እናምናለን:: ግን ግን በከተሞች የምንመለከተው ሥርዓቱን የለቀቀው የበርካታ እህቶቻችን አካሔድ ለሃገርም ለቤተ ክርስቲያንም ትልቅ ስጋት ነው:: ክብርና ነውር የማይለይበት ዘመን ይመስላል::

+ይህንን እያነበባችሁ ያላችሁ እህቶቼ! አንድ ነገር ልንገራችሁ:: በመልካቸው ብዙዎችን ያጋጩ: አጊጠው በመታየታቸው ብዙዎችን ያሰናከሉ: ለብዙ ምዕመናንም የጥፋት ምክንያት የሆኑ ብዙ ሴቶች በታሪክ ነበሩ::

+የሚያሳዝነው ግን ዛሬ ያሉት ከመሬት በታች ነው:: አፈር በልቷቸዋል:: ስም አጠራራቸውም ጠፍቷል:: በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ዛሬ በዘለዓለማዊው እሳት እየተቃጠሉ በሲኦል: በጥልቁ ውስጥ አሉ::

+እናም ወገኖቼ! ይህን አውቀን እንንቃ:: ይህ ዓለም ጠፊም: አጥፊም ነውና:: እድሜአችን ቢረዝምና ከዚህ በኋላ ለ100 ዓመታት ብንኖርም እርሱም ማለቁ አይቀርምና:: ምርጫችን ዘለዓለማዊው ሕይወት ይሁን ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን::

+" እለ ቅድስት ሶፍያ "+

+ቅድስት ሶፍያና አብረዋት በዚህ ዕለት የሚከበሩ ቅዱሳት አንስት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም የነበሩ ክረስቲያኖች ናቸው:: አብዛኞቹ መልክ (ደም ግባት) ከጠባይ ጋር የተስማማላቸው ነበሩ:: ነገር ግን ከምድራዊው ክብር ሰማያዊውን መርጠው ለመንፈሳዊው ሙሽርነት ወደ ገዳም ገቡ::

+ከእነዚህ ቅዱሳን መካከል በጸጋና በሞገስ: በትምሕርትም የምትበልጥ ቅድስት ሶፍያ ናትና እመ ምኔት አድርገው ሾሟት:: እርሷም ለገዳሙ በጐውን ሥርዓት ሠራች:: ሁሉም (ደናግሉም መነኮሳይያቱም) በአንድነት ይጾማሉ: ይጸልያሉ: ይሰግዳሉ: የቅዱሳንን ተጋድሎ ያነባሉ:: ሥጋውን ደሙን ይቀበላሉ::

+እርስ በርስ ደግሞ ፈጽመው ይፋቀራሉ:: በዚህ ሕይወት አንዳንዶቹ እስከ 70 ዓመት ቆዩ:: የቅድስናቸው ዜና ሲሰማ በሮም ግዛት ያሉ ወጣት ሴቶች እየመጡ ይቀላቀሏቸው ነበር:: ቅድስት ሶፍያም የሕይወትን መንገድ ታሳያቸው ነበር::

+ከዚህ ሁሉ በኋላ ከሐዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ለጦርነት ወደ ፋርስ ሲሔድ ስላያቸው ባንድነት ሰብስቦ ሁሉንም በሰይፍ አስመታቸው:: ቅድስት ሶፍያም አብራ ሰማዕት ሆነች:: ስለ ቅዱሳኑ የሚበቀል ጌታም ቅዱስ መርቆሬዎስን ልኮ በጦርነቱ መካከል በጦር ወጋው:: ዑልያኖስ ወደ ዘለዓለም ኩነኔ ሲሔድ: ቅዱሳት አንስት ወደ ገነት ሔደዋል::

+" ባሕረ ሐሳብ "+

+ዳግመኛ በዚህ ቀን: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ባሕረ ሐሳብ በዓለማቀፍ ደረጃ ተቀባይነትን አግኝቷል:: ሊቁ ቅዱስ ድሜጥሮስ (የግብጽ 12ኛ ፓትርያርክ) መንፈስ ቅዱስ ቀመረ ባሕረ ሐሳብን ገልጾለት በዓለም ላሉ ሊቃነ ዻዻሳት ልኮላቸው በዚህች ዕለት በሮም ከተማ ተሰበሰቡ::

+ሊቃውንትም ሐዋርያት ካስተማሩት ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ቢያገኙት በደስታ ተቀብለውታል:: እነሆ እስከ ዛሬ ድረስ ለ1,700 ዓመታት ቤተ ክርስቲያን እየተገለገለችበት ይገኛል::

+የቅዱሳት እናቶቻችን አምላክ ዛሬም እንደ እነርሱ ያሉትን አያሳጣን:: በጸሎታቸው ምሮ ከበረከታቸው ይክፈለን::

+ኅዳር 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
2.ደናግለ ሮሜ (ሰማዕታት)
3.ቅዱስ ዻውሎስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቅ
5.ጉቡዓን ኤዺስ ቆዾሳት

ወርኀዊ  የቅዱሳን  በዓላት

1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
7.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ

++"+ ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: +"+ (1ዼጥ. 3:3)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

https://t.me/zena_tewahido

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

19 Nov, 06:38


https://youtu.be/qz7rCqNsepk

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

15 Nov, 08:00


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ስንክሳር ኅዳር 6

በዓለ ደብረ ቁስቁዋ

የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች:: በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት ወርቅ: እጣን: ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት::

+ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች::

+ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ: በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም: በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች::

*የአምላክ እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
*ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
*የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
*የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
*የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
*እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች: እግሯ ደማ: ተንገላታች::

+ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኳ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ::

+አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና::

+"መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ? ለምን ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ?"

1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7)

2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል): ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::

3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1)

4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::

5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: (ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበር:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና:: )

6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና

7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::

+እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት (ወይም ለ42 ወራት) በስደት የቆየችባቸው ቦታዎች አሉ:: ድንግል ማርያም ከርጉም ሔሮድስ ስትሸሽ መጀመሪያ የሔደችው ከገሊላ ወደ ሶርያ ደንበር (ደብረ ሊባኖስ) ነው::

+በዚያ የሸሸጋት ቅዱስ ጊጋር መስፍኑ በሔሮድስ ሲገደል ወደ ምድረ ግብጽ ወረደች:: በግብጽም ለብዙ ጊዜ ከአንዱ ወደ ሌላው ስትሸሽ ቆየች::
"እንዘ ከመ በግዕት ግድፍት አመ ሳኮይኪ ውስተ ምድረ በዳ" እንዲል:: (እሴብሕ ጸጋኪ)

+ቀጥላም በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ገብታ ደብረ ቢዘን ላይ (አሁን ኤርትራ ውስጥ ነው) ዐረፈች:: ከደብረ ቢዘን በደብረ ዳሙ: አክሱም: ደብር ዓባይ: ዋልድባ አድርጋ እየባረከች ጣና ደርሳለች:: በጣና ገዳማትም: በተለይ በጣና ቂርቆስ ለ100 ቀናት ቆይታ ቀጥታ በጐጃም ወደ ሽዋ ሒዳ ደብረ ሊባኖስን ቀድሳለች::

+ቀጥላም እስከ ደብረ ወገግና ደብረ ሐዘሎ ደርሳለች:: በእግሯ ያልደረሰችባቸውን የሃገራችን ክፍሎች በደመና ተጭና ዐይታ ባርካቸዋለች:: ከልጇም በአሥራትነት ተቀብላለች:: ሔሮድስ መሞቱን መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የነገራትም እዚሁ ኢትደዮዽያ ውስጥ መሆኑን ትውፊት ያሳያል::

+እመ ብርሃንም ከሃገራችን ሰዎች (ከሰብአ ኦፌር) የተቀበለችውን ስንቅና ስጦታ በ5 ግመሎች ጭና ከቅዱሳኑ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በዚህች ቀን ደብረ ቁስቁዋም ውስጥ ገብተው ከድካም ዐርፈዋል:: ሐሴትንም አድርገዋል::

+ዳግመኛም ከክርስቶስ ስደት 400 ዓመታት በኋላ በዚህች ቀን የግብጿ ደብረ ቁስቁዋም ታንጻ ተቀድሳለች:: የቅዱሳን ማደሪያም ሁናለች:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ390ዎቹ አካባቢ ድንግል እናቱን: ቅዱሳን ሐዋርያትን: አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን: አስከትሎ ወረደ::

+የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎፍሎስና ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ቤተ ክርስቲያኑን አንጸው: ሕዝቡን ሰብስበው ይጠብቁት ነበርና ወርዶ ቀድሶላቸው ታላቅ ደስታ ሁኗል::

+ስደቷን መሳተፍን ሽተው አበው:-
"እመ ኀሎኩ በጐይዮቱ ውእተ መዋዕለ:
እምተመነይኩ ኪያሁ በዘባንየ ሐዚለ:
ወበልሳንየ እልሐስ ዘአእጋሪሁ ጸበለ:
ወከመ አዕርፍ ምስሌሁ በትረ ዮሴፍ ኀበ ተተክለ:
ለወልደ ማርያም በሐጸ ፍቅሩ ልቡናየ ቆስለ::" እንዳሉ:: (ሰቆቃወ ድንግል)
እኛም እመ ብርሃንን ልንሻት ያስፈልገናል::

+ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ:: የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ በዚህች ቀን ተመልሷልና:: ስደቷን አስበን ካዘንን: መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና::

"አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ:
ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ" ልንልም ይገባል::

+" 🌷አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ🌷 "+

+ጻድቁ አቡነ ጽጌ ድንግል በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ሊቅና ገዳማዊ ናቸው:: የዘር ሐረጋቸው ምንም ከቤተ እሥራኤል እንደሚመዘዝ ቢታወቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው:: አስቀድመው አይሁዳዊ በመሆናቸው ኢየሱስ ክርስቶስንና ድንግል እናቱን አያምኑም ነበር::

+የተማሩትም ብሉይ ኪዳንን ብቻ ነበር:: በጊዜውም "ክርስቶስ አልተወለደም: ትክክለኛው እምነት ይሁዲ ነው" እያሉ ከክርስቲያኖች ጋር ይከራከሩ ነበሩ:: አንድ ቀን ግን ከታላቁ ሊቅና ገዳማዊ አቡነ ዜና ማርቆስ ጋር ተገናኙ::

+ጻድቁን ስላልቻሏቸው ተሸንፈው በክርስቶስ አመኑ:: አቡነ ዜና ማርቆስም አስተምረው ክርስትና ሲያነሷቸው /ሲያጠምቁዋቸው 'ጽጌ ድንግል' አሏቸው:: ሲመነኩሱም 'ጽጌ ብርሃን' ተብለዋል:: ቀጥለውም በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ: እመቤታችንንም ሲለምኑ ምሥጢር ተገለጠላቸው::

+የእመ ብርሃንን ስዕለ አድኅኖ በአበባ ተከባ: በብርሃንም ተውጣ ተመለከቱ:: በዚህ ምክንያትም ዛሬ በጣፋጭነቱ የሚታወቀውን ማኅሌተ ጽጌን 150 ዓርኬ አድርግው ደረሱ:: እስከ ዕለተ ዕረፍታቸውም እመቤታችንና ልጇን በገዳማቸው (ወለቃ አካባቢ የሚገኝ) ሲያመሰግኑ ኑረዋል:: ጻድቁ ያረፉት ጥቅምት 27 ሲሆን ዛሬ የቃል ኪዳን በዓላቸው ነው::

✞✞✞ ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::

✞✞✞ ኅዳር 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም (ሚጠታ ለማርያም)
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
3.ቅድስት ሰሎሜ ቡርክት
4.ቅዱስ ዮሳ (ወልደ ዮሴፍ)
5.ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሊቅ
6.አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ
7.አባ ፊልክስ ዘሮሜ


https://t.me/zena_tewahido

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

14 Nov, 09:25


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን


ስንክሳር  ኅዳር 5

ታላቁ አባ ዮሐኒ

በምድረ ኢትዮዽያ ዝናቸው ከወጣና ቀደምት ከሚባሉ ጻድቃን አንዱ ቅዱስ አባ ዮሐኒ ("ኒ" ጠብቆ ይነበብ) ነው:: አበው ሊቃውንት የቅዱሱን ታሪክና ገድል ገና በልጅነት ስለ ነገሩን አንረሳውም:: እጅግ ጣፋጭ ዜና ሕይወት ያለው አባት ነውና:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን በሃገራችን ቅዱስ አፄ ካሌብ ነግሦ ሳለ: አንድ ቅዱስ ሰው ከግብጽ ወደ ኢትዮዽያ መጡ:: እኒህ ሰው "አሞኒ ዘናሕሶ" ይባላሉ:: ቅዱሱ ዓለምን ላለማየት ቃል ገብተው በትግራይ በርሃ ይጋደሉ ነበር::

+በዘመኑ አፄ ካሌብ የናግራን (የመን) ክርስቲያኖችን ለመታደግ ዘመቻ አድርጎ ነበር:: ታዲያ አንድ የንጉሡ ወታደር ወደ ዘመቻ ሲሔድ ሚስቱን ይጠብቅለት ዘንድ ትንሽ ወንድሙን አደራ ይለዋል:: ወንድሙ ግን አደራውን ትቶ የትልቅ ወንድሙን ሚስት አስገድዶ ይደርስባትና ትጸንሳለች::

+ከዘመቻ የተመለሱት ከ1 ዓመት በሁዋላ ነውና ሚስቱን ምጥ ላይ ያገኛት ወታደር ደነገጠ:: ተቆጣ:: የጸነሰችው ከእርሱ እንዳልሆነ ያውቃልና ምጥ ላይ ሆና ሊያዝንላት አልፈለገም::

+ለገልጋይ አስቸግሮ ሚስቱን ይደበድባት ገባ:: በዚህ ምጥ: በዚህ ዱላ ነፍሷን ከሥጋዋ ሊለየው የደረሰችው ያቺ ሴት ግን "ወንድማማችን አላጋድልም" ብላ ቻለችው:: በዚህ ጊዜ ቅዱስ መልአክ ያን ግብጻዊ ባሕታዊ (አባ አሞኒን) አምጥቶ ከሰዎቹ በር ላይ አቆመው::

+"ከእሱ ነው በይ" አላት:: እርሷም "ከዚያ ባሕታዊ ነው" ብላ ተናገረች:: ወታደሩ ባሏም በቁጣ ወጥቶ ቅዱስ አሞኒን በዱላ ስብርብር እስኪል ድረስ ደበደበው:: ልጁ ልክ ሲወለድም ከእናቱ ነጥቆ ለባሕታዊው አሳቅፎ አባረረው::

+ቅዱስ አሞኒም ሕጻኑን አቅፎ ወደ ተምቤን በርሃ አካባቢ ወሰደው:: ግን ምን ምግብ: ምን ልብስ: ምን መኝታ እንደሚሰጠው ጨንቆት ጻድቁ አለቀሰ:: በዚህ ጊዜም ቅዱስ መልአክ የጸጋ ምንጣፍን አነጠፈለት::

+ጆፌ አሞራ መጥቶ ክንፉን ሲያለብሰው አጋዘን መጥታ ጡት አጠባችው:: በዚህ የተደነቀው ቅዱስ አሞኒ ሕጻኑን "ዮሐኒ" ሲል ስም አወጣለት:: ትርጉሙም "ወልደ አራዊት - ወላጆችህ (አሳዳጊዎችህ) አራዊት ናቸው" እንደ ማለት ነው::

+ሕጻኑ ዮሐኒ በዚህ መንገድ ከአሞኒና ከአራዊቱ ጋር አደገ:: 5 ዓመት በሞላው ጊዜም ትምሕርተ ሃይማኖትን: የቅድስና ሕይወትን ተማረ:: ልክ እንደ መንፈሳዊ አባቱ በጾምና በጸሎት ተወሰነ:: ግን እርሱ ከእርሱ: ከአሞኒና ከአራዊቱ በቀር ሌላ ፍጥረት: ዓለም (ብዙ ሰዎች) መኖራቸውን አያውቅም::

+12 ዓመት በሞላው ጊዜ ግን ክህነት ይገባዋል ብሎ መንፈስ ቅዱስ ስላሳሰባቸው ቅዱሱ አሞኒ ዮሐኒን ወደ ዻዻሱ ወሰዱት:: መንገድ ላይም ቅዱስ ዮሐኒ ወጣት ሴቶች ተሰብሰበው ሲጫወቱ ተመልክቶ "አባ! እነዚህ ጸጉራቸው የረዘመ: ደረታቸው ወደ ፊት የወጣ ፍጥረቶች ምንድን ናቸው?" ሲል ጠየቀ::

+አባ አሞኒም "ልጄ! እነዚህ ሴቶች ናቸው:: ግን ለእንደ እኔና አንተ ያሉ የበርሃ ሰዎች አይሆኑምና አትቅረባቸው" አለው:: ቅዱስ ዮሐኒ መልሶ "አባቴ! ድንገት ቢመጡብኝ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀ:: አባ አሞኒም "ልጄ! ከዘለዓለም ርስት ከምትነቀል ሩጠህ ብታመልጥ ይሻላል" አለው::

+ከ6 ዓመታት በሁዋላ (ዮሐኒ 18 ዓመት ሲሞላው ማለት ነው) ቅዱስ አሞኒ ኅዳር 5 ቀን ዐረፈ:: ለ14 ዓመታትም ቅዱስ ዮሐኒ ከአራዊትና አባ አበይዶን ከመሰሉ አባቶች ጋር ኖረ:: ከንጽሕናው የተነሳም ቅዱሳን መላእክት ያነጋግሩት ነበር::

+ስም አጠራሩ በምድረ ትግራይ ሲወጣ ወላጅ እናቱ በሕይወት ነበረችና ሰማች:: የአካባቢዋን ሴቶች ሰብስባም ልትገናኘው ወዳለበት ተራራ ገሰገሰች:: ወደ ተራራው ደርሳ ስትጠራው ቅዱሱ ተመለከታት::

+ወዲያው ትዝ ያለው አባቱ ቅዱስ አሞኒ "ሴት ስታይ ሩጥ" ያለው ነውና እግሩን አንስቶ ሮጠ:: እናቱ ስትከተለው: እርሱ ሲሮጥ ከገደሉ ጫፍ ደረሰ:: ወደ ሁዋላ ሲመለከት ሊደርሱበት ነው::

+በስመ ሥላሴ ፊቱን አማትቦ ወደ ገደሉ ተወረወረ:: በዚህ ጊዜ ግን መንፈሳዊ ክንፍ ተሰጥቶት ተሰወረ:: ቅዱስ መልአክም ብሔረ ሕያዋን አስገብቶታል:: ይህንን ታሪክ ሲያደንቁ አበው እንዲህ ብለዋል::

"ሰላም ዕብል ለዘኮነ ሱቱፈ::
ምስለ እለ ገብሩ ሰብእ ብሔረ ሕያዋን ምዕራፈ::
እምሥርዓተ መላእክት ዮሐኒ ምንትኒ ኢያትረፈ::
ከመ ሕይወቶሙ ሕይወተ ተጸገወ ዘልፈ::
ወከመ ክንፎሙ አብቆለ አክናፈ::" (አርኬ)

+"+ ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት +"+

=>ለንጊኖስ ማለት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስብከት ዘመን የዺላጦስ ወታደር የነበረ ሰው ነው:: ስለ ጌታችን ተአምራት በየጊዜው ይሰማ ነበር:: ሔዶ እንዳያገኘው ግን አይሁድን ይፈራ ነበር:: እነርሱ "በክርስቶስ ያመነ ሁሉ ከምኩራብ ይባረር" ብለው ነበርና:: (ዮሐ. 9:22)

+ጌታችን በተሰቀለባት ዕለተ ዐርብ ግን ጭንቅ ሆነበት:: ጌታን እንዲሰቅሉ ከታዘዙ ወታደሮች እንደ አንዱ ተመርጦ ነበርና በዘዴ አሞኛል ብሎ እስከ 9 ሰዓት ድረስ ቆየ::

+በሁዋላ ግን አይሁድ "በክርስቶስ ሞት ያልተባበረ ሁሉ ወንጀለኛ ነው" የሚል አዋጅ በማስነገራቸው እየፈራ ወደ ቀራንዮ ሲደርስ "ጐኑን ውጋው" ብለው ረዥምና ጥቁር ጦር ሰጡት:: ለንጊኖስ ወደ ጌታችን ዐይን ተመለከተ:: እያየው እንዳልሆነ ገመተ::

+ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ ለይቷልና ጦሩን ጨብጦ ወደ ጌታ ጐን ልኮ ወጋው:: ከጌታ ቀኝ ጐንም በ"ለ" አምሳል ትኩስ ደምና ውሃ ፈሰሰ:: አንዷ ፍንጣቂ ሔዳ የታወረች ዐይኑ ላይ ዐርፋ ዐይኑን አበራች::

+ለለንጊኖስ ታላቅ ደስታ ሆነ:: ለእኛ ግን ማየ ገቦና ደመ ገቦ ፈለቀልን:: የጌታችን ትእግስቱና ቸርነቱ ግን ይደንቃል::
"ከመ ኢየሐስብ ቦቱ ዘኩናተ እዱ ርግዘቶ::
በኃጣውኢሁ ለዘኢፈቀደ ሞቶ::
ምሕረቶ እሴብሕ ወዐዲ ትዕግስቶ::" እንዳሉ ሊቃውንት::

+ጌታችን ከተነሳ በሁዋላ ለንጊኖስ ወደ ቅዱስ ዼጥሮስ ዘንድ ሒዶ ስለ እውነት: ስለ ሃይማኖትም ተማረ:: ተጠምቆ: ምድራዊ ወታደርነቱን ትቶ እየሰበከ ከኢየሩሳሌም ወደ ቀዸዶቅያ ወረደ:: ለዘመናትም ጌታችን ክርስቶስን በሥርዓተ ወንጌል አገለገለ::

+በመጨረሻ በጢባርዮስ ቄሣር ዘመን አይሁድ አሳደዱት:: አንገላቱት:: የነርሱ ወገን ስለነበረም መከራ አጸኑበት:: የጽቅድ አርበኛና የክርስቶስ ሐዋርያ ቅዱስ ለንጊኖስ ግን ጸና:: አይሁድም አንገቱን ቆርጠውት ለሰማዕትነት በቃ:: ቅዱሱ በሕይወቱም በዕረፍቱም ተአምራትን ሠርቷል::

< አስተርዮተ ርዕሱ >

=>ይሕች ዕለት አስተርዮተ ርዕሱ ትባላለች:: እርሱን ከገደሉ በሁዋላ አይሁድ ራሱን ወደ ኢየሩሳሌም ወስደው ጥለዋት ነበር:: የእርሱን ሰማዕትነት ያየች አንዲት ክርስቲያንም ከለቅሶ ብዛት ዐይኗ ቢጠፋ ሕጻን ልጇን ይዛ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች::

+ወዲያው ግን ሕጻን ልጇ ሞተባትና ሐዘኗ ከልኩ አለፈ::
ለአንዲት እናት ዐይንንና ልጅን በአንዴ ማጣት እጅግ ጭንቅ ነው:: በሌሊት ግን ቅዱስ ለንጊኖስ በራዕይ ተገልጦ ደስታ ነገራት::+ "ልጅሽ በገነት ሐሴትን ያደርጋል:: አንቺ ግን ራሴን ከተቀበረችበት አውጪ" አላት:: ወደ ጠቆማት ቦታ በመሪ ስትቆፍር ብርሃን ወጥቶ ዐይኗ በራላት:: በታላቅ ሐሴትም ቅድስት ራሱን ወደ ሃገሯ ወስዳታለች

https://t.me/zena_tewahido

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

12 Nov, 05:03


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ስንክሳር ኅዳር 3

አቡነ መድኃኒነ እግዚእ

መዘንጋታቸው እጅግ ከሚያስቆጭ ኢትዮጽያውያን አባቶች ትልቁን ሥፍራ እኒህ አባት ይወስዳሉ:: የማር ወለላን በሚያስንቅ ጣዕመ ሕይወታቸው ሃገራችንን ያጣፈጡ: ብርሃን ሆነው ብዙ ቅዱሳንን የለኮሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው::

+አባ መድኃኒነ እግዚእ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ትግራይ (አዲግራት) ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸውም ቀሲስ ሰንበትና ሒሩተ ማርያም ይባላሉ:: በደግነትም እጅግ የታወቁ እንደ ነበሩ ገድላቸው ይናገራል:: "መድኃኒነ እግዚእ" ማለት "ጌታ መድኃኒታችን ነው" ማለት ነው::

+ብዙ ጊዜም "ዘደብረ በንኮል - ሙራደ ቃል" እየተባሉ ይጠራሉ:: "ደብረ በንኮል" ማለት ትግራይ ውስጥ የሚገኝና ጻድቁ በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ያነጹት ገዳም ነው:: "ሙራደ ቃል" ደግሞ "የቃል (የምሥጢር) መውረጃ" እንደ ማለት ሲሆን በቦታው ሱባኤ የያዘ ሰው ልክ እንደ ቅዱስ ያሬድ ምሥጢር እንደሚገጥለት የሚጠቁም ስም ነው::

+ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በልጅነታቸው ከሊቁ ካህን አባታቸውና ከሌሎችም መምሕራን ተምረው: ምናኔን መርጠው ገዳም ገብተዋል:: በጾም: በጸሎትና በስግደት ተግተው ጸጋ እግዚአብሔር ሲሰጣቸው ወደ ደብረ በንኮል ሒደው ገዳም መሠረቱ::

+በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መካከለኛው ዘመን (በተለይ ከ13ኛው እስከ 15ኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ ያለው) የብርሃን ዘመን ይባላል:: ምክንያቱም ዘመኑ
*ክርስትና ያበበበት::
*መጻሕፍት የተደረሱበት::
*ስብከተ ወንጌል የተስፋፋበት::
*ገዳማዊ ሕይወት የሠመረበት ወቅት በመሆኑ ነው::

+ለዚህ ትልቁ አስተዋጽኦ ደግሞ:-
¤አቡነ ተክለ ሃይማኖት::
¤አቡነ ኤዎስጣቴዎስ::
¤አባ ሰላማ ካልዕ::
¤አቡነ ያዕቆብ::
¤ቅዱሱ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ::
¤አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ::
¤አቡነ መድኃኒነ እግዚእን የመሰሉ አበው መነሳታቸው ነው::

+በተጨማሪም:-
¤12ቱ ንቡራነ ዕድ::
¤7ቱ ከዋክብት::
¤47ቱ ከዋክብት::
¤5ቱ ከዋክብት የሚባሉ አበው አስተዋጽኦም ልዩ ነበር:: ከእነዚህ መካከልም የ7ቱ እና የ47ቱ ከዋክብት አስተማሪ: የአበው 3ቱ ሳሙኤሎች (ዘዋልድባ: ዘጣሬጣና ዘቆየጻ): የሌሎችም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን አባት የሆኑት አባ መድኃኒነ እግዚእ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ::

+ጻድቁ ቅዱሳኑን ሰብስበው: አስተምረው: አመንኩሰው: መርቀው ሰደው: ሃገራችንን እንዲያበሩ በማድረጋቸው እንደ አባ ኢየሱስ ሞዐ እርሳቸውም "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን" ይባላሉ:: ታላቁ ጻድቅና ሰባኬ ወንጌል አባ ዓቢየ እግዚእም (ጐንደር ውስጥ እባብና ጅብ እንዳይጐዳ የገዘቱ አባት ናቸው) የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ነበሩ ይባላል::

+ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በተትረፈረፈ የቅድስና ሕይወታቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: አራዊትን ገዝተዋል: በአንበሳ ጀርባ ላይ እቃ ጭነዋል:: ከረዥም የተጋድሎ ሕይወት በሁዋላም ኅዳር 3 ቀን ዐርፈዋል:: እድሜአቸውም 180 ነው::

¤" መድኃኒነ እግዚእ አቡነ መስተጋድል::
ምንኩስናሁ ምዑዝ ከመ ኮል::
በመንፈሰ ጸጋ ክሉል::" (መጽሐፈ ሰዓታት)

¤" ተአምረ ኃይልከ አባ መድኃኒነ እግዚእ አቡነ::
እም አፈ ዜናዊ ሰማዕነ:: ወበዓይነ ሥጋ ርኢነ::
መንክርኬ አእላፈ ቤትከ ንሕነ::
ባሕቱ በዝ ተአምሪከ ርድአነ::
ለሰይፈ አርዕድ ንጉሥ ዘወሀብኮ ኪዳነ::
ከመ ረድኤቱ ታፍጥን ጊዜ ጸብዕ ኮነ::" (አርኬ)

+"+ ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል +"+

=>የዚህ ቅዱስ ኢትዮዽያዊ ዜና ሕይወት ለሁላችንም ትልቅ ትምርትነት ያለው ነው:: በተለይ በምክንያት ከቅድስና ሕይወት እንዳንርቅ ያግዘናል ብየም ተስፋ አደርጋለሁ:: የቅዱሱ ወላጆች ገላውዴዎስና ኤልሳቤጥ ሲባሉ በምድረ ሽዋ በበጐ ምጽዋታቸው የተመሰከረላቸው ነበሩ::

+ፈጣሪ ሰጥቷቸው ኅዳር 8 ቀን (በበዓለ አርባዕቱ እንስሳ) ወልደውታልና "ዓምደ ሚካኤል - የሚካኤል ምሰሶ" ሲሉ ሰይመውታል:: ገና በልጅነቱ ብዙዎችን ያስገርም የነበረው ቅዱሱ አንዴ በ3 ዓመቱ ከቅዳሴ መልስ ጠፋቸው::

+ወላጆቹ እያለቀሱ በሁሉ ቦታ ፈለጉት:: ግን ሊገኝ አልቻለም:: በ3ኛው ቀን የሞቱን መታሠቢያ ሊያደርጉ ካህናትና ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገቡ ግን ባዩት ነገር ተገረሙ:: ሕጻኑ ዓምደ ሚካኤል ከቤተ መቅደሱ መሃል: ከታቦቱ በታች ካለው መንበር (ከርሠ ሐመር ይሉታል) ቁጭ ብሎ ይጫወታል::

+ያየ ሁሉ "ዕጹብ ዕጹብ" ሲልም አደነቀ:: ምክንያቱም በተፈጥሮ ሥርዓት ሕጻን ልጅ ያለ ምግብ 3 ቀን መቆየት ስለማይችልና ሕጻኑ በዚያ የቅድስና ሥፍራ ላይ ምንም ሳይጸዳዳ በመገኘቱ ነው::

+ብጹዕ ዓምደ ሚካኤል ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እየተማረ: በጾምና በጸሎት አደገ:: በ15ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ላይ ንጉሥ የነበረው ጻድቁ አፄ ዘርዓ ያዕቆብም ቅዱሱን የሠራዊት አለቃ (ራስ ቢትወደድ): ወይም በዘመኑ አገላለጽ የጦር ሚኒስትር አድርጐ ሾመው::

+መቼም እዚህ ቦታ ላይ ተቀምጦ መልካምን መሥራት ልዩ ነገርን ይጠይቃል:: በተለይ ደግሞ በዙሪያው የሚከቡትን ተንኮለኞች ድል መንሳቱ ቀላል አልነበረም:: ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል ግን በዘመነ ሲመቱ እነዚህን ሠራ:-

1.በጠዋት ተነስቶ ነዳያንን ይሰበስብና ቁርስ: ምሳ ያበላቸዋል:: ይሕም ዕለት ዕለት የማይቁዋረጥ በመሆኑ ሃብቱ አልቆ ደሃ ሆነ::

2.ከቀትር በሁዋላ ዘወትር ቆሞ ያስቀድስና ጸበል ተጠምቆ ይጠጣል:: ማታ ብቻ እህልን ይቀምሳል::

3.ሽፍታ ተነሳ ሲባል ወደ ዱር ወርዶ: ጸልዮ: ሽፍታውን አሳምኖት ይመጣል እንጂ አይጐዳውም::

4.ጦርነት በሚመጣ ጊዜ ክተት ሠራዊት ብሎ ይወርዳል:: ግን ለምኖ: ጸልዮ: ታርቆ ይመጣል እንጂ ጥይት እንዲተኮስ አይፈቅድም ነበር::

+በዚህ መንገድ በ3ቱ ነገሥታት (በዘርዐ ያዕቆብ: በዕደ ማርያምና እስክንድር) ዘመን ሁሉ አካባቢውን ሰላም አደረገው:: ዓለም ግን ዓመጸኛ ናትና በአፄ እስክንድር ዘመን (በ1470ዎቹ) በሃሰት ተከሶ ስደት ተፈረደበትና ወደ በርሃ ተጋዘ::

+በዚያም ቅዱስ ሚካኤል ሰማያዊ መናን እየመገበው: ሥጋ ወደሙን እያቀበለው ኖረ:: ትንሽ ቆይቶ ግን የሞት ፍርድ ተፈርዶበት በንጉሡ አደባባይ ተገደለ:: ለ30 ቀናትም በመቃብሩ ላይ የብርሃን ምሰሶ ወረደ በዚህም ንጉሡ በእጅጉ ተጸጸተ::

+"+ ቅዱስ ኪርያቆስ +"+

=>ሊቅነትን ከገዳማዊ ሕይወት የደረበው ቅዱስ ኪርያቆስ የቆረንቶስ ሰው ሲሆን አበው "ጥዑመ ቃል - አንደበቱ የሚጣፍጥ" ይሉታል:: ገና በልጅነቱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲያነብ ከአንደበቱ ማማር: ከነገሩ መሥመር የተነሳ ከዻዻሱ እስከ ሕዝቡ ድረስ ተደመው ያደምጡት ነበር::

+በወጣትነቱ ጣዕመ ዓለምን ንቆ ከቆረንቶስ ኢየሩሳሌም ገብቷል:: ቀጥሎም ወደ ፍልስጥኤም ተጉዞ የታላቁ አባ ሮማኖስ ደቀ መዝሙር ሁኖ መንኩሷል:: በገዳሙ ለበርካታ ዘመናት ሲኖርም እጅግ ብዙ ተአምራትን ሠርቷል

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

12 Nov, 05:02


ባእታ ለማርያም ማለት

እመቤታችን የብጸሐት ልጅ ናት ( የስለት ልጅ) 3 ዓመት ሲሆናት አፍዋ እህል ሳይለምድ ሆድዋ ስው ሳይውድ ብለው እናት አባትዋ ውስደው ለቤተ እግዚአብሔር ስጡዋት ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ይባላል የእመቤታችን መልኳ እንደ ፅሀይ ሲያበራ አይቶ ይእችን የመስለች ውብ ብላቴና ተረክቤ እንደምን አድርጌ አኖራታለው ብሉ ደውል አስምቶ ካህናትን ስብስቦ የምግቧን ነግር ሲማከሩ መልአኩ ቅዱስ ፋኖኤል ዕብስት ስማያዊ ጸዋ ስማያዊ ይዞ ከላይ እርቦ ታየ
ሊቀ ካህናቱ ዛሬ ሀብቴን ክብሬን በስው መካከል
ሊገልጥልኝ መስለኝ ብሎ ሊቀበል ቀርበ መልአኩ ወደ ላይ ስቀቀበት
ካህናቱም ሊቀበሉ ቀርቡ መልአኩ ወደ ላይ ስቀቀባቸው
እህሩገ እስራኤልም ቀርቡ መልአኩ ወደ ላይ ስቀቀባቸው
ሐና እያቄምም ሊቀበሉ ቀርቡመልአኩ ወደ ላይ ስቀቀባቸው
ሐና ምን አልባት ለዚህች ብላቴና የውርደ መንፈስ ቅዱስ ሳይሆን አይቀርምና እስኪ ትተሻት ጥቂት እልፍ በይ አሏት ትታት ትንሽ እልፍ ብትል መልአኩ ውርዶ ግራክንፉን አንጥፋ ቀኝ ክንፈን አጉናጸፏ በቆመ ብዕሲ አድርጉ መግቧት አርጓል

ይህም ምግቧ ሰማያዊ ነው ሲል ነው
የምግቧ ነግር ከተያዘልን ይህችን ውብ ብላቴ ከስው ጋራ ምን ያጋፈታል ኖሮዋ ከቤተ መቅደስ ይሁን ብለው ከቤተመቅደስ አግብተው አኖርዋት ሄደዋል
እመቤታችንም መላእክት ሊቃነ መላዕክት አያጫውትዋት እያርጋጓት 12ዓመት በቤተ መቅደስ ተቀምጠች ከእናት አባትዋቤት 3ዓመት በአጠቃላይ 15ዓመት ሲሆናት ከቤተ መቅደስ ወጣች...


ረድኤት እና በረከቷን ታካፍለን

አሜን🙏

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

11 Nov, 05:06


ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር
🌹🌹🌹…🌹🌹🌹…🌹🌹🌹

"…ድንግል ሆይ…! ርጉም በኾነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ ጋራ ካገር ወደ አገር ስትሸሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ረኀቡንና ጥሙን፣ ችግሩንና ጒዳቱን ከርሱ ጋራ የደረሰብሽን ጸዋትወ መከራ ኹሉ አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ከዐይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ፤ ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ፣ መዐትን ያይደለ ምሕረትን አሳስቢ፤ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥኣን አሳስቢ ለንጹሓን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ።

"…ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ሆይ ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን፤ አእምሮውን ጥበቡን ፍቅርሽን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን፡፡"

"…የእመቤታችንን ፍቅሯን በልቦናችን ጣዕሟን በአንደበታችን ያሳድርብን። ምልጃና ጸሎቷ ረድኤት በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን። የአሥራት ሀገሯን ኢትዮጵያን በምልጃዋ ትጠብቅልን።

https://t.me/zena_tewahido

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

11 Nov, 05:06


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ስንክሳር ኅዳር 2

አባ ዼጥሮስ ሣልስ

✝✞✝ 'ዻዻስ' ማለት 'አባት-መሪ-እረኛ' ማለት ነው:: በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ በሐዲስ ኪዳን የመንፈሳዊ ስልጣን ደረጃዎች በጥቅሉ 3 ናቸው:: እነሱም ዲቁና: ቅስና: ዽዽስና ሲሆኑ በሥራቸው ወደ 9 ያህል ክፍሎች አላቸው:: ከእነዚህም ከፍተኛው ስልጣን ዽዽስና ነው::

+ዽዽስና ማለት የክርስቶስን መንጋ እንደ ባለቤቱ አድርጐ መጠበቅ ማለት ነው:: ሥልጣኑ በምድር 'ሸክም: ዕዳ' ሲሆን በሰማይ ግን 'ክብር' ነው:: ማንም በሥጋው ላይ ካልጨከነ በቀር ዽዽስናን አይመኝም::

+ቅዱስ ዻውሎስ "ሠናየ ግብረ ፈተወ-ማንም ዽዽስናን ቢመኝ መልካም ሥራን ተመኘ" (1ጢሞ. 3:1) ማለቱን ይዞ 'ሹሙኝ' ማለት ወደ ማይጠፋ እሳት የሚያስጥል ከባድ ውሳኔ ነው:: ምክንያቱም አንድ ክርስቲያን የሚጠየቅ በራሱ ኃጢአት ሲሆን አንድ ካህን ደግሞ ስለ ልጆቹ ይጠየቃል:: የከፋው ግን የዻዻሱ ነው::

+አንድ ዻዻስ ቢጾም ቢጸልይም እንኳ ለድኅነቱ በቂ አይደለም:: ምክንያቱም በመንበሩ ላይ ያስቀመጠው መንጋውን እንጂ ራሱን እንዲያድን አይደለምና:: ጌታ እንዳለ መልካም እረኛ "ይሜጡ ነፍሶ ቤዛ አባግኢሁ-መልካሙ እረኛ ስለ በጐቹ ቤዛ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ነው::" (ዮሐ. 10) ስለዚህም ክህነት / ዽዽስና ሐዋርያዊ አገልግሎት ከባድም ኃላፊነት ነው::

+አባቶቻችን ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ሐዋርያውያን ታላላቅ የዽዽስና መንበሮችን መሥርተው: ትምሕርቱን ከነ ወንበሩ አስተላልፈዋል:: ከእነዚህ መንበረ ዽዽስናዎች 4ቱ የበላይ ናቸው:: እነዚህም የቅዱስ ዼጥሮሱ የሮም: የቅዱስ ዮሐንሱ የአንጾኪያ: የቅዱስ ማርቆሱ የእስክንድርያና የቅዱስ ዻውሎሱ የኤፌሶን መናብርት ናቸው::

+እነዚህ መንበሮችም ከክርስቶስ ዕርገት እስከ 443 (451) ዓ/ም: ጉባኤ ኬልቄዶን ድረስ በአንድነት ቆይተው ተለያይተዋል:: ከእነዚህ መናብርት መካከል የእስክንድርያው (የግብጹ) እና የአንጾኪያው (የሶርያው) ዛሬም ድረስ በተዋሕዶ እምነት የጸኑ ናቸው::

+የእኛ ቤተ ክርስቲያንም ሐዋርያዊት እንደ መሆኗ ሐዋርያትን መስለው: ሐዋርያትን አህለው የተነሱ አበው ዻዻሳትን በየጊዜው በበዓላት ታስባለች: ታከብራለች::

+በተለይ ደግሞ የእስክንድርያና የአንጾኪያ በርካታ አባቶችን እናከብራለን:: እነርሱ ለቀናች ሃይማኖትና ለመንጋው ሲሉ ብዙ መከራን በአኮቴት ተቀብለዋልና:: ከእነዚህም መካከል አንዱ አባ ዼጥሮስ ሣልሳዊ ነው::

+ሣልሳዊ መባሉ ከእርሱ በፊት በዚህ ስም ተጠርተው በመንበረ ማርቆስ ላይ የተቀመጡ 2 ፓትርያርኮች ስለ ነበሩ ነው:: ቅዱስ ዼጥሮስ ቀዳማዊ 'ተፍጻሜተ ሰማዕት' (የሰማዕታት ፍጻሜ) የተባለው ሲሆን 17ኛ ሊቀ ዻዻሳት ነው::

+ቅዱስ ዼጥሮስ ካልዕ ደግሞ በ370ዎቹ አካባቢ 21ኛ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ የተሾመና የቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ደቀ መዝሙር የነበረ አባት ነው:: ዛሬ የምናስበው አባ ዼጥሮስ ደግሞ በ470ዎቹ አካባቢ ሊቀ ዽዽስናን በግብጽ ተሹሞ ያገለገለውን ነው::

+ወቅቱ መለካውያን (የኬልቄዶን ጉባኤ አማኞች) የሰለጠኑበት በመሆኑ ሁኔታዎች ትንሽ አስቸጋሪ ነበሩ:: አንደኛ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ከ2 የተከፈለችበት ጊዜ በመሆኑ ፈተናው ለእረኞች ቀላል እንዳይሆን አድርጐታል:: ሌላውና ዋናው ፈተና ግን በዘመኑ የነበሩ ነገሥታት ለመለካውያን (ለመናፍቃን) ወግነው ምዕመናንን ማሳደዳቸው ነው::

+አባ ዼጥሮስ ከተመረጠ በኋላ አስቀድሞ ያደረገው አጋዥ መፈለግ ነበር:: እግዚአብሔር ሲረዳው የታላቂቱ ሃገር የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ የሆነው ቅዱስ አካክዮስን አገኘ:: ከእርሱ ጋርም ደብዳቤ ይጻጻፉ ያዙ::

+ደብዳቤ ሲባል ግን እንዲህ እኛ በዘመኑ እንደምንጽፈው ያለ አይደለም::ይልቁን 5ቱ አዕማደ ምሥጢራትን የተሞሉ ጦማሮች ነበሩ እንጂ:: 2ቱ አበው በየሃገራቸው እየዞሩ እየሰበኩ: አልደርሱበት ባሉበት ቦታ ደግሞ ክታቦችን እየጻፉ በአንድነት ስለ ቀናች ሃይማኖት ደከሙ::

+በእግዚአብሔር ቸርነትም ተሳካላቸው:: አባ ዼጥሮስ በዚህች ቀን ሲያርፍ መሰሉ 'ካልእ አትናቴዎስ' ተክቶታል:: ከፈጣሪውም እሴተ ኖሎትን (የእረኝነት ዋጋውን) ተቀብሏል::

+አምላከ አበው ዻዻሳት መንጋውን በርሕራሔ የሚጠብቁ እረኞችን ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

+ኅዳር 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት ሣልስ
2.አባ ሱንቱዩ ሊቀ ዻዻሳት
3.ቅድስት ሴቴንዋ ነቢይት
4.ቅድስት አንስጣስያ


ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ
7.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

>+"+ ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛልና:: ወንጌልን ብሰብክ እንኩዋ የምመካበት የለኝም:: ግድ ደርሶብኝ ነውና:: ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ:: ይህን በፈቃዴ ባደርገው ደመወዝ አለኝና:: ያለ ፈቃዴ ግን ባደርገው መጋቢነት በአደራ ተሰጥቶኛል:: እንግዲህ ደመወዜ ምንድን ነው? ወንጌልን እየሰበክሁ በወንጌል ካለኝ መብት በሙሉ እንዳልጠቀም ወንጌልን ያለ ዋጋ ብናገር ነው:: +"+ (1ቆሮ. 9:15)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

10 Nov, 20:00


https://youtu.be/qE-CX-_SDY4

🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤

09 Nov, 17:06


#ሐዋርያው_ቅዱስ_ማርቆስ

ጥቅምት 3ዐ ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ የተወለደበት ቀን ነው ፤ ሚያዚያ 3ዐ ቀን ጣኦት አምላኪዎች በበሬ አስጎትተው ሰማዕትነትን ተቀብሏል።

ቅዱስ ማርቆስ ትውልዱ ዕብራዊ ነው፤ ቤተሰቦቹ ግን ይኖሩ የነበሩት በሰሜን አፍሪካ ሲረኒካ  (ቀሬና) በተባለችውና በዛሬዋ ሊቢያ ምዕራባዊ ጠረፍ በተቆረቆረችው ደማቅ በተባለች ቦታ ነበር፡፡ ነገር ግን የሰሜን አፍሪካ  ዘላን ጎሳዎች የሆኑት በርበሮች በየጊዜው በከተማዋ ጥቃት እየነሰዘሩ ሀብት ንብረታቸውን እየዘረፉ ስላስቸሯቸው እናቱ ማርያምና አባቱ አርስጦቡሎስ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ኢየሩሳሌም በመመለስ ቤት ሠርተው ተቀመጡ፡፡

የማርቆስ እናት ማርያም ባውፍልያ ቤቷን ለክርስቲያኖች መሰብሰቢያነት የሰጠች ደግ ሴት ነበረች፡፡ ጌታችንም የመጀመሪያውን የሐዲስ ኪዳን ቁርባን ለሐዋርያት ያቆረባቸው በእርሷ ቤት የላይኛው ፎቅ ላይ ነበር፡፡ በበዓለ ኀምሳም ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደላቸው በእርሷ ቤት ተሰብስበው ሲጸልዩ ነው፡፡ ሐዋ 2፤1 12፤1

ቅዱስ ማርቆስ የቀድሞ ስሙ ዮሐንስ ይባል ነበር   ቁጥሩ ከ 72ቱ አርድእት ነው፤ እናቱ ማርያምም ቁጥሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ነው። ሐዋ 12፥12

በርናባስ ለቅዱስ ማርቆስ አጎቱ ነው፡፡ የቅዱስ ማርቆስ አባት አርስጦብሎስና በርናባስ በእናት የሚገናኙ ወንድማማቾች ናቸው፡፡ የእነርሱን እኅት ደግሞ ቅዱስ ጴጥሮስ ስላገባት ቅዱስ ማርቆስ አክስቱን ለመጠየቅ ሲሔድ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ተዋወቁ፡፡

ቅዱስ ማርቆስ ገና በልጅነቱ ኢየሩሳሌም ለመኖር በመታደሉ በዚያን ዘመን ይሰጥ የነበረውን መንፈሳዊ ትምህርት የማግኘት ዕድል ገጥሞታል፡፡ የላቲን የግሪክና የዕብራይስጥ ቋንቋዎችን አሳምሮ ያውቅ ነበር፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በይሁዳ አውራጃዎች እየተዘዋወረ ሲያስተምር ማርቆስ ገና ሕፃን ነበር፡፡ በምሴተ ኀሙስ ለሐዋርያት (ወደ ከተማ ሂዱ፤በማድጋ ውኃ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ፤ ተከተሉትም) በማለት ፋሲካን ሊያዘጋጁለት የመረጠውን ቤተ እንዲያሳያቸው የጠቆማቸው ወጣት ቅዱስ ማርቆስን መሆኑ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ይመሰክራሉ፡፡ (ማር.፲፬፥፲፫)

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቀራንዮ በሚጓዝበት ዕለት ቅዱስ ማርቆስ ዕርቃኑን በነጠላው ሸፍኖ ይከተለው ነበር፡፡ ነገር ግን አይሁድ ሊይዙት ባሰቡ ጊዜ ጨርቁን ጥሎ ራቁቱን ሸሽቷል፡፡ ይህም በዚያ ጊዜ ገና ልጅ እንደነበር ያመለክታል፡፡ (ማር.፲፫፥፶)

ሐዋርያት በዕጣ  በሀገረ ስብከታቸው በሚሄዱበት ጊዜ መጀመሪያ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ከዚያም ከቅዱስ ጴጥሮስ ወደ ሮም አስከትሎት ሄዷል። ከዚያም ቅዱስ ጴጥሮስ በሚያስተምርበት ጊዜ ከቃሉ እየተቀበለ በመጻፍና በትርፍ ጊዜውም በማስተማር በጣም ትጉህ ነበር። ይህን ትጋቱንና ተአማኝነቱን ተመልክቶ ቅዱስ ጴጥሮስ ለመላው አፍሪቃ ወንጌልን እንዲያዳርስና እንዲያስተምር ሊቀ ጳጳስ ብሎ በእስክንድርያ ከተማ ሹሞታል።

ኢትዮጵያ በዚህ በማርቆስ መንበር የተሾሙ 111 ጳጳሳትን ከግብጽ ስታስመጣ ኖራለች።


#በአንበሳ_መመሰሉ ፦

አንበሳ ለላም ጌታዋ ነው በክርኑ በመታት ጊዜ ያደቃታል እርስም በግብፅ ይመለክ የነበረውን አምልኮተ ላዕምን በክስቶስ ወንጌል አጥፍቷልና በአንበሳ ይመስላል

ቦ ፦  አንበሳ ኑሮው ከሰው ርቆ በምድረ በዳ ነው ከዚያ ሆኖ ድምጹን ባሰማ ጊዜ እንስሳት ይገሠጻሉ አራዊት ይደነግጣሉ እርሱም ከትምህርት ምድረ በዳ ከነበረች ሀገረ ግብፅ ገብቶ የክርስቶስን ወንጌል ማስተማር በጀመረ ጊዜ እንደ እንስሳ ያለ ምዕመናን ተገሥጸዋል እንደ አራዊት ያሉ ከሃድያን ደንግጠዋልና

ቦ፦ አንበሳ ኃያል እንደሆነ እርሱም ከሌሎቹ በተለየ የጌታችንን የኃይል ሥራ ( ያደረገውን ተአምራቱን) አብዛቶ በወንጌሉ ይጽፋልና

ቦ፦ አንበሳ ኑሮው በምድረ በዳ እንደሆነ እርሱም ወንጌሉን የምድረ የምድረ በዳ በማንሳት (በምድረ በዳ የሚጮህ የሰው ድምፅ ) በመጻፍ ይጀምራልና። በአንበሳ ተመሰለ።

ቅዱስ ማርቆስን ሚያዚያ 3ዐ ቀን ጣኦት አምላኪዎች በበሬ አስጎትተው ሰማዕትነትን ተቀብሏል።

የበረከት በዐል ያድርግልን ፡፡

ምንጭ ፦ ወንጌል ትርጓሜ
-> www.eotcmk.org

https://t.me/zena_tewahido

17,115

subscribers

1,065

photos

61

videos