ETV መዝናኛ @etv_meznagna_from_ebc Channel on Telegram

ETV መዝናኛ

@etv_meznagna_from_ebc


Etv meznagna official channel from @ebc99

ETV መዝናኛ (Amharic)

ኢቲቪ መዝናኛ ቡድኖችን እና አለምዳሎቻችንን በተነሳ ከ @ebc99 ጋር በማይታይ አባላት እንዲወቁ ለማነጋገል እናውቃለን። ይህ ቱርክ የኢቲቪ መዝናኛ ሙሉ አባላት ማህበረሰብና ጥቅሞችን በማስደነግ ይሁኑ። በመመዝገብና ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጡበት የቱርክ አዲሱ ቡድን ነው። ስለዚህ በዚህ መረጃ የኢቲቪ መዝናኛ አባላት ከ አምለሰት ጋር ሲጠቀሙ፣ ከካሜልሽም ከአትሌት እንሞታለን። እጅግ ያሳያ።

ETV መዝናኛ

28 Sep, 08:33


2ቀን Church ከተመላለስክ በሓላ ቸከስህ ደውላ እንገናኝ የት ልጠብቅህ? ስትልህ😳😳
.
.
.
ጠባቂዬ ቸሩ መድሀኒያአለም ብቻ ነው😁😁
@etv_meznagna_from_ebc

ETV መዝናኛ

16 Jan, 17:25


ከዚህም በተጨማሪ የንጉስ ተክለሀይማኖትን ሴት ልጅ(ንግስት ተክለሀይማኖትን)ለማግባት የተፈጠረን የ 2 መኳንንቶች ፀብ ለ1 አመት ሲዳኙ...በስተመጨረሻም የፈለገችውን እንድታገባ አድርገው አንደኛውን መኳንንት አዲስ አበባ ድረስ አስመጥተው ሲቀጡ የነበረው ያለፍላጎቷ ሊያገባት በመሞከሩ አይደል?(አስቡት እንግዲህ ይህ ሁሉ የሆነው ያኔ ሴቶች ለራሳቸው እንደማያውቁ ተደርጎ የትዳር አጋራቸውን ቤተሰብ በሚመርጥላቸው በዛ ዘመን ነበር።)ይሄ ለኔ ያሳየኝ የዛን ጊዜ ንጉሱ እንቅስቃሴአቸው የሴቶችን ችሎታ፣የመወሰን አቅም ከግምት የከተተ እንደነበር ነው።አሁን ስለ እኩልነት ብዙ በምናወራበት በዚህ ዘመን በሀገራችን በከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ ሴቶች የማይታዮት ለምንድን ነው??ፕሮፖዛል ቀርፀን እኩል ያልሆኑ ነገሮችን እኩል ለማድረግ በጀት ከመጨረስ እና እኩል ነን አይደለንም እልህ ከመጋባት ይልቅ ጥንካሬና ድክመታችንን ለይተን ለጋራ ጥቅም በጋራ የምንሰራበት እንዲሁም ሴቶች በአመራር ቦታ ላይ በመገኘት የአደዋን ታሪክ የሚደግሙበት ጊዜ ያምጣልን እላለው......የገጣሚ እዮብን ግጥም እየጋበዝኩ እኔ ግን በዚሁ ተሰናበትኳችሁ።

እግዜር ዲሞክራቱ
እግዜር ዲሞክራቱ
ሄዋንን ሲሰራት ካዳም አካል ወስዶ
አጥንት አልፈለገም
ወይ ካናቱ ወጥቶ ወይ ከእግሩ ወርዶ
ሄዋን በፍጥረቷ
እንዳትሆን የበታች እንዳትሆን የበላይ
አጥንት ወስዶ ሰራት ከመሀከሉ ላይ።
👉 @etv_meznagna_from_ebc ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
© የብዝሀነትና የህዳሴ ድምፅ
:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::

ETV መዝናኛ

15 Jan, 15:10


ኢትዮጵያ

እናትክን በሉልኝ . . .
ሽሙንሙን አያት አለችኝ። ፊደል አታዉቅም። ፖለቲካ አታዉቅም።
ነፍፍ አፈ-ታሪክ ታዉቃለች። ደግ ነች። የዋህ ልብ አላት። ልጆች
ታፈቅራለች። ቤተስኪያን ትስማለች። ምርቃት ስፈልግ እሄዳለሁ።
አያታለሁ። ወሬ እፈጥራለሁ። እንቀዳለን። ፀጉሬ እንዳደገ
ትነግረኛለች። ለመቶ ግዜ ያወራችዉን ለመቶ አንድ ግዜ
ትደግማለች። አልጠላዉም። እወደዋለሁ። ታሪኩን አዉቀዋለሁ።
ዝምምም ብዬ እሰማታለሁ።
የሆነ ሰሞን ነዉ። ፌዴሬሽን ምክር ቤት ቅማንት ኢሹ ነበር። በወሬ
መሃል ትዝ አለኝ። ጠየኳት፡፡ "ስለቅማንት ንገሪኝ" አልኳት፡፡ "አንድ
ሰካራም ሰው በጠራራ ፀሃይ ሰክሮ ከእንጨት ጋር ተዳከለ፡፡ ከሱ
የተወለዱ ልጆች ናቸው አለችኝ፡፡" ገረመኝ፡፡ አሰብኩኝ፡፡
ያወራችው ፖለቲካ አይደለም፡፡ አፈ-ታሪክ ነው፡፡ አለማወቅ ነው፡፡
ከደነዝክ ፖለቲካ ታረገዋለህ፡፡ ተጮቁነሃል፥ ተንቀሃል፥ ተዋርደሃል
ትለዋለህ፥ ትጀነጅነዋለህ፥ ታሰምጠዋለህ፥ ገንዘብ ትሰራበታለህ፡፡
መሐይም ነው ይጋደላል፡፡ ከመጀመሪያው ጥፋት ሁለተኛው
በለጠ፡፡
፩ . . .
ጎጃሜ ቡዳ ነው፡፡ ትግሬ ለማኝ ነው፡፡ ኦሮሞ ጅል ነው፡፡ ጉራጌ
ገብጋባ/ሌባ ነው፡፡ ጎንደሬ አዝማሪ ነው፡፡ ደቡብ ባሪያ ነው፡፡
ሶማሊ ሽርጣም ነው፡፡ አማራ ቆማጣ ነው፡፡ ወሎ ሸርታታ ነው፡፡ .
. . ምናምን ምናምን ነፍፍፍፍ ሐጠራው ሃሳቦች ፒፓው ተሸክሞ
ይኖራል፡፡ ይናናቃል፡፡ በሩን ዘግቶ፥ አንሶላ ውስጥ ተሸሽጎ
ይናገረዋል፡፡ ያምንበታል፡፡ ይኖረዋል፡፡ ሲመቸው ይጋባል፥
ይጠብሳል፥ ይጣበሳል፥ ዘር ይተካል፥ ይገበያያል፥ ያመልካል፡፡
ፖለቲካ አይደለም፡፡ የአደባባይ እውነት ነው፡፡ የማህበረሰብ ህፀፅ
ነው፡፡
እንዲህ የሚያስብ ብሽቅ ነው፡፡ ወፍራም መሐይም ነው፡፡ ደነዝ
ነው፡፡ የሚል አሳቢ ይነሳል፡፡ ፒፓውን ያስተምራል፡፡ ያነቃል፡፡
በሐሳቡ እንዲሸማቀቅ ያረጋል፡፡ በጓዳ የምትበጠረቀውን አደባባይ
አውጥቶ ይሞግታል፡፡ 'ላይህ ላይ የሰፈረ ድድብና በቀጭኑ
ይጠረጋል፡፡
* "ሰው ሁሉ እኩል ነው" ትላለህ !
፪ . . .
ሊሸቅልብህ ካሰበ፥ ፖለቲካ ያረገዋል፡፡ ቡቱቶ ርዕዮተ ዓለም
ያለብሰዋል፡፡ ብሔር፥ መደብ፥ ጨቋኝ፥ ተጨቋኝ፥ ፊውዳል፥
ቡርዧ፥ ከበርቴ፥ ንዑስ ከበርቴ፥ ገንጣይ፥ አስገንጣይ ምናምን
የሚል ለዛ ቢስ ስም ያወጣል፡፡ ለሁለት ይከፍልሃል፡፡ ይጀነጅንሃል፡፡
ያሰምጥሃል፡፡ ያናክስሃል፡፡ የችግሩ ምንጭ፥ መናናቁ፥ መጠራጠሩ፥
ፈሪነቱ ከየት እንደመጣ አይነግርህም፡፡ ይደብቅሃል፡፡ መሐይምነት
መሆኑን አታውቅም፡፡ 'ርግጥ እሱም መሐይም ነው፡፡
አንተም ደነዙ ብሔሬ፥ ዘሬ፥ ቅብርጥሴ ትላለህ፡፡ የተደከለ ጭንቅሌ
ይዘህ ትሟገታለህ፡፡ ትጋደላለህ፡፡ ሚስጥሩ መሐይምነት መሆኑ
አይገባህም፡፡ የትም ዓለም ያለ ችግር እንደሆነ አታስብም፡፡
አትመረምርም፡፡ እቺኑ ፖለቲካ አርገህ፥ በሽመል፥ በድንጋይ፥
በቆንጨራ ትጫረሳለህ፡፡ መድሃኒቱ ፖለቲካ ይመስልሃል፡፡ እውቀት
እንደሆነ አይገባህም፡፡ ስልጣኔ እንደሚጠርገው አታውቅም፡፡
* ያንተ ፖለቲካ የሚቀዳ ከዚህ ተራ ሃሳብ ነው !
፫ . . .
ከዛ ሰፈር "እንገነጠላለን" ከዚህ ሰፈር "ተገንጠሉ" ምናምን
የምትባባል ወናፍ ሁላ፤ ይሄ መገናኛ ድልድይ ስር፥ አንባሳደር
መውጫ ላይ፥ ቡናና ሻይ በር ላይ፥ ፒያሳ መውጫ ላይ፥ አራት
ኪሎ ማዕዘን ላይ ጨለም ሲል፥ ሰው አየኝ አላየኝ ብለህ፥ በ50
ብር የገዛኸው የሸሚዝ ቁልፍ አይደለም፡፡ ዝምምምምም ብሎ
የሚበጠስ፥ የሚገነጠል፡፡
* ሐገር ነው፥ ህዝብ ነው፥ ባህል ነው፥ ማንነት ነው፥ ታሪክ ነው፥
ደም ነው !

በዮሀንስ

@etv_meznagna_from_ebc

ETV መዝናኛ

15 Jan, 14:50


ኢትዮጵያ

• ሰው ከእንስሳ የሚለይበት በሁለት እግሩ ቆሞ መሄዱ አይደለም።
ዶሮም በሁለት እግር ነው የሚሄድው እንግዲያ ቋንቋ ስላለው ነው አይደለም እንስሳትም እርስ በርሳቸው የሚግባቡበት ቋንቋ አላቸው።
ሰው ከእንስሳ የሚለይበት አይነተኛ መለዮው እራሱን መግዛት የሚችል መሆኑ ነው ሰው ከእንስሳ የሚለይበት ረሀብን ስስትን ሴሰኝነትንና እነሱን የመሳሰሉትን ከእንስሳ ጋር የሚያጋራቸውን ባሃሪዎች ለመግታት መቻሉ ነው፡፡

በረሀብ ተገፍቶ የተመኘውን ሁላ ልብላ ካለ በስስት ተገፍቶ ያየውን ሁላ የኔ ይሁን ካለ በሴሰኝነት ተገፍቶ ከሚመኛት ጋር ግብረ ዝሙት የሚፈፅም ከሆነ ሰው መሆኑ ቀርቶ በሁለት እግሩ የሚሄድ እንስሳ ይሆናል።

© ሄኖክ ዮሐንስ
👉 @etv_meznagna_from_ebc
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

© የብዝሀነትና የህዳሴ ድምፅ ©

ETV መዝናኛ

11 Jan, 09:11


Channel photo updated

ETV መዝናኛ

10 Jan, 14:05


Channel created