በምስራቅ ጉራጌ ዞን የምስራቅ መስቃን ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት አመታዊ ጉባኤ አካሄደ!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ነሃሴ 01፣ 2016 ዓ,ም ሀሙስ ገበያ (የምስራቅ መስቃን ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት) በምስራቅ ጉራጌ ዞን የምስራቅ መስቃን ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት አመታዊ ጉባኤዉን አካሂዷል።
ፅ/ቤቱ ባካሄደዉ ጉባኤ በወረዳዉ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት በ2016 ዓ.ም የተከናወኑ አበይት የስራ አፈፃፀምን በመገምገም የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ግምገማና የስራ አቅጣጫ አስቀምጧል።
በፕሮግራሙ የምስራቅ መስቃን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አወል፤ የምስራቅ መስቃን ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሸህቾ ኢብራሂም ፤ የምስራቅ መስቃን ወረዳ ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ አለሙ ግዛው ፤ የቀበሌ ሊቀመንበሮች የወረዳዉ አመራሮች ፣ የሀሙስ ገበያ ማዘጋጃ ቤት ኃላፊዎችና ባለሞያዎች እንዲሁም ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የምስራቅ መስቃን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አወል መድረኩን በመሩበት ወቅት እንደተናገሩት ከከተማ ልማትና መሰረተ ልማት ስራዎች አንፃር ባለፈው በጀት አመት ጠንካራ ስራዎች መስራት መቻሉን ጠቅሰዉ በቀጣይ በጀት አመት የተጀመሩ መልካም ስራዎችን ማስቀጠልና በወረዳዉ የሃሙስ ገበያ ከተማን በማዘመን ረገድ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
የመሬት አሰባሰብ ስራ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ከፈታ ፤ የቆሻሻ አወጋገድ ባህልን ማሳደግ ፣ የቄራ ግንባታ ስራና ሌሎችም የገፅታ ግንባታ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዉ ህገወጥ የመሬት አጠቃቀም እና ከዘርፉ ጋር የተያያዙ ሲስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን ከወዲሁ መቅረፍ እንደሚገባም አመላክተዋል።
ዋና አስተዳዳሪዉ አክለዉም በከተማው ግንባር የሚገኙ ቦታዎች ላይ ጥራት ያላቸው ግንባታ እንዲገነቡ በማድረግ ከተማው ለኢንቨስትመንት ምቹ እንዲሆን በመስራት እና ተጨማሪ ኢንቨስተሮችን በመሳብ የከተማዋን ገቢ ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።
በተለይም በማህበር በመደራጀት እና በተለያዩ አማራጭ ቤት የማልማት ፍላጎትና አቅም ያላቸው አካላት መሬቱን በህግ አግባብ የማግኘታቸው ሁኔታ ላይ በቀጣይ በጀት አመት በትኩረት መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል።
በተጨማሪም ከተማዉን ከማልማት አኳያ ለመስራት የታሰቡ ተግባራቶችን እስከታችኛው የቀበሌ መዋቅሮች በማቀናጀት እና በማጠናከር ሰው ተኮር ስራዎችን መስራት እንደሚገባ ገልፀው ማህበረሰባችን በማስተባበር ሊረዱ የሚገቡ አቅመ ደካማ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች በመርዳት የበጎነት ተግባራት ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።
ፕሮግራሙን አስመልክቶ የእንኳን ደና መጣቹ መልዕክት ያስተላለፉት የምስራቅ መስቃን ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድኑር ስርሞሎ እንደተናገሩት የጉባኤዉ ዋና አላማ በ2016 በጀት አመት በፅ/ቤቱ የተከናወኑ ጠንካራ ስራዎችና በጉድለት የታዩ ተግባራትን በመገምገም ለ2017 በጀት አመት የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያበቃ እና ችግርችን ለይቶ የዕቅድ አካል ለማድረግ የተዘጋጀ መድረክ እንደሆነ ገልፀዋል።
ስለሆነም በቀጣይ የተጀመሩ ጠንካራ ተግባራትን ማስቀጠልና በጉድለት የተለዩ ስራዎችን በቀጣይ በጀት አመት የዕቅድ አካል ተደርገዉ እንደሚሰሩ ገልፀው በተለይም ለቤት መስሪያ ቦታ በማህበር ለተደራጁ አካላት የመሬት አቅርቦት ስራ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የፅ/ቤቱ ምክትልና የመሬት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነስሩ ሙዜ ለጉባኤዉ የተዘጋጀ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት በበጀት አመቱ ተግባራትን በጥራት ለማከናወን የነዋሪዎችን አደረጃጀት የማጥራትና መልሶ የማደራጀት ስራ መሰራቱን ተናገረዋል።
ከዕቅድ አንፃር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ከማሻሻል፣ የተገልጋዮችን እርካታ ከማሳደግ ፤ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል መሬት በማዘጋጀት አቅርቦትን ማሳደግ ፤ በመሬት ላይ የሚፈፀም የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር እንዲቀረፉ በማድረግ ፤ የኢሌ ወጃ እና ዶበና ጎላ ቀበሌዎች የማጠናከር ስራ እንደሚሰራ አመላክተዋል።
በዕለቱ ፕሮግራሙን አስመልክቶ የወረዳዉ አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አወል እንዲሁም ሌሎችም አመራሮች የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናዉነዋል።
በመጨረሻም በወረዳዉ የከተማ ልማት ስራን በማገዝ ረገድ የተሻለ አፈፃፀም ላከናወኑ ባለድርሻ አካላት የእዉቅናና የሽልማት ፕሮግራም በማካሄድ የነበረዉ የጉባኤ መድረክ ተጠናቋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ t.me/misrakmeskanworedacommunication
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/mesrakmeskan/
ኢ-ሜይል፦
[email protected]ዩትዩብ፦https://youtube.com/channel/UCH3dI7vy2ULtrlosd_GtqcQ