Federal Public Procurement Service @h6eqa_bquqdmzgy8s Channel on Telegram

Federal Public Procurement Service

@h6eqa_bquqdmzgy8s


Federal Public Procurement Service (FPPS) Ethiopia

Federal Public Procurement Service (English)

Welcome to the Federal Public Procurement Service (FPPS) Ethiopia Telegram channel! FPPS is the leading procurement agency in Ethiopia, dedicated to promoting transparency, efficiency, and integrity in public procurement processes. Our channel provides you with the latest updates on government tenders, procurement opportunities, and best practices in the field. Whether you are a government agency looking to procure goods and services or a supplier interested in bidding for contracts, FPPS is your go-to resource for all things procurement-related. Stay informed about upcoming procurement events, training sessions, and policy changes that may impact your business. Join our channel today to connect with like-minded professionals, share insights, and stay ahead of the curve in the world of public procurement. Let FPPS be your partner in achieving procurement excellence and driving sustainable development in Ethiopia.

Federal Public Procurement Service

06 Dec, 11:35


ህገ መንግስት ስርዓት የሚከበረው የህዝቦችን ተጠቃሚነት እኩልነትና አንድነት ለማረጋገጥ መሆኑን የገለፁት ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ፤ይህ የሚረጋገጠው አንዱ በመንግስት ዘርፍ ውስጥ በሚሰሩ ስራዎች መንግስት ኢትዮጵያን እንዲመስል በማድረግ እና በምንሰጣቸው አገልግሎቶች የኢትዮጵያን ህዝቦች የጋራ ፍላጎትና እኩል ተጠቃሚነት መርህን ተከትለን ስንሄድ ነው ብለዋል ።
በፕሮግራሙ ህብረ ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት ግንባታ ሂደት ላይ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን አስመልክቶ የመወያያ ጽሑፍ የቀረበ ሲሆን ተሳታፊዎች የቀረበውን ሰነድ መሠረት በማድረግ የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ በመጪው እሁድ ህዳር 29/2017 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአርባምንጭ ከተማ በድምቀት የሚከበር ይሆናል።

Federal Public Procurement Service

06 Dec, 11:35


19ኛው የብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የአገልግሎቱ ፣የገንዘብ ሚኒስቴርና ሌሎች ተጠሪ ተቋማት አመራርና ሰራተኞች በተገኙበት በጋራ ተከበረ
***************************************
ኅዳር 27/2017 ዓ.ም
የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት ” በሚል መሪ ሃሳብ ከገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች ጋር በሚኒስቴር መ/ቤቱ አዳራሽ በጋራ አክብረዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፋት መልዕክት በዓሉ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በማንነታቸው ኮርተው ራሳቸውን በራሳቸው እያስተዳደሩ በህገ መንግስታዊ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሀገረ መንግስቱን በአዲስ መልክ መገንባት የጀመሩበት ዕለት መሆኑን አስታውሰው፤ዕለቱ በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ የሚታሰብና የሚከበር በዓል ነው ብለዋል።
ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው በዓል “ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ህብረ ብሔራዊነታችን ፤ አንድነታችንን በሚያጠናክር እና ብሔራዊ ትርክትን በሚያሳድግ መልኩ እየተከበረ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

Federal Public Procurement Service

06 Dec, 08:36


በሽያጭ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች ጨረታ ሊከፈት ነው
************************
የመንግስት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የ17 ፌዴራል መ/ቤቶች የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ለማስወገድ ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የጨረታ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡
በዚህ መሰረት ጨረታው ሰኞ ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ
4፡15 ሰዓት ላይ በአገልግሎቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

Federal Public Procurement Service

05 Dec, 12:47


አገልግሎቱ እንኳን ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል
አደረሳችሁ በማለት መልዕክት አስተላለፈ
***************************
ህዳር 26/2017 ዓ.ም
ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ በሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች በልዩ ልዩ ሁነቶች እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራርና ሠራተኞችም ይህንን በዓል በነገው ዕለት ከገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች ጋር በጋራ እንደሚያከብሩ በመግለጽ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
በዓሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም በአርባምንጭ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበርም ከተለያዩ የሚዲያ ምንጮች በተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Federal Public Procurement Service

05 Dec, 07:39


የንብረት ማስወገድ ሥርዓቶች
የመንግስት መ/ቤቶች ንብረት ለምን ማስወገድ እንዳስፈለገ ለይተው የማወቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ንብረት ሲያስወገዱ፡-
. የንብረቱ ህጋዊ ባለቤትነት ማን እንደሆነ መለየትና የመስሪያ ቤቱ ንብረት እንደሆነ ማረጋገጥ፣
. ህንፃና ተመሳሳይ ግንባታዎች ማስወገድ ቢፈልጉ ሚኒስቴሩን (ገንዘብ ሚኒስቴርን) ማስፈቀድ እና
. የሚወገዱ ንብረቶች ልዩ ጠቀሜታ ያላቸው ወይም ጉዳት የሚያስከትሉ ንብረቶች ሲሆኑ አግባብ ካላቸው መ/ቤቶች ጋር መነጋገር ይኖርባቸዋል፡፡

Federal Public Procurement Service

02 Dec, 13:57


ለግንዛቤዎ!
የተፈቀዱ የንብረት ማስወገጃ ዘዴዎች
በማናቸውም የመንግስት መ/ቤት ይዞታ ስር ያለን ንብረት ለማስወገድ እንደ ንብረቱ ባህርይ የሚከተሉትን የንብረት ማስወገጃ ዘዴዎች ስራ ላይ ይውላሉ፡፡
• ለሌላ የመንግስት መ/ቤት በማዛወር ወይም በማስተላለፍ፣
• ባሉበት ሁኔታ ወይም እንደ ሁኔታው ፈታቶ ለሕዝብ በኤሌክትሮኒክ ሥርዓት
መሠረት በጨረታ ወይም በሐራጅ በመሸጥ፣
• ንብረቱን በስጦታ በማስተላለፍ፣
• ንብረቱን በመቅበር ወይም በማቃጠል፣
• ንብረቱን በማፈን፣በማምከን ወይም በመቀየጥ ማስወገድ ናቸው፡፡
ምንጭ፡- የፌዴራል የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ
(ተሻሽሎ የፀደቀው)
ሆኖም የመንግስት ግዥ አገልግሎት በመቋቋሚያ ደንቡ (በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 184/2002 ዓ.ም) በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት ንብረቶችን የሚያስግደው የመ/ቤቶች የበላይ ኃላፊዎች ውሳኔ ሰጥተው ወደ ተቋማችን የሚልኳቸውን ንብረቶች በጨረታ በመሸጥ ነው፡፡

Federal Public Procurement Service

02 Dec, 11:37


የጨረታን ሂደት በሚስጥር ስለመጠበቅ
******************************
ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ ከጨረታ ምርመራ፣ ከማብራሪያ፣ ከግምገማ እና አሸናፊውን ተጫራች በሚመለከት ከቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ጋር የተያያዙ መረጃዎች በሚስጥርነት መጠበቅ ያለባቸው ሲሆን፣አሸናፊው ተጫራች እስከሚገለፅ ድረስ ለተጫራቾች ወይም ከሥራው ሂደት ጋር ግንኙነት ለሌላቸው ሰዎች መገለፅ የለባቸውም፡፡
ምንጭ፡- የተሻሻለው የፌዴራል የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ

Federal Public Procurement Service

30 Nov, 12:57


በደንበኞች አያያዝና በስነ ምግባር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ
********************************************
ህዳር 21/2017 ዓ.ም
በደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥና አያያዝ ፣በመልካም የስራ ስነ ምግባር እንዲሁም በመረጃ አያያዝና በኢ-ሜይል አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለአገልግሎቱ ሠራተኞች ተሰጠ ።
የመድረኩ ዓላማ አገልግሎቱ ለተገልጋዮች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ እያደረገ ያለውን ከፍተኛ እንቅስቃሴ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ መሆኑን በመንግስት ግዥ አገልግሎት የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኢቲሳ ደሜ ተናግረዋል።
በቀጣይም ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ተገልጋዩ ባለበት ሆኖ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ኢቲሳ ፤ ለዚህ ስኬታማነት ሁላችንም የተጣለብንን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ይኖርብናል ብለዋል።
ለግማሽ ቀን በተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ከደንበኞች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሠራተኞችን ጨምሮ ሾፌሮች ፣ የፅዳትና የጥበቃ ሠራተኞች እና ሌሎች ባለሙያዎች የተሳተፋ ሲሆን በመድረኩ የአገልግሎት አሠጣጥና አያያዝ በአቶ መስፍን ሞላ የመሠረታዊ አገልግሎቶች ስራ አስፈፃሚ ፤ የስራ ላይ ስነምግባር በወ/ሮ አዲስ አለም የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ስራ አስፈፃሚ እንዲሁም የመረጃ አያያዝና አጠቃቀምን በተመለከተ በወ/ሮ ማርታ አሰፋ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ባለሙያ ሠነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል።

Federal Public Procurement Service

29 Nov, 18:25


የአስፓልት ግዥ ለመፈጸም የጨረታ ማስታወቂያ ወጣ
***************************
ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም
የመንግስት ግዥ አገልግሎት ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን አገልግሎት የሚውል አስፓልት በመንግስት የኤሌክትሮኒክ የግዥ ዘዴ (e-GP) ግዥ ለመፈፀም በe-GP ፖርታል ላይ ጨረታ አውጥቷል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በመንግስት የኤሌክትሮኒክ የግዥ ዘዴ በአቅራቢነት በመመዝገብ የወጣውን የጨረታ ሰነድ ከe-GP ፖርታል ላይ በመመልከት በሲስተም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚችል መሆኑን አገልግሎቱ አሳውቋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-1-22-37-53 ወይም 011-1-22-37-40 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የሚቻል መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል፡፡

የመንግስት ግዥ አገልግሎት

Federal Public Procurement Service

27 Nov, 12:28


የተፈቀዱ የግዥ ዘዴዎች
በማናቸውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ግዥ
አፈፃፀም የሚከተሉት የግዥ ዘዴዎች ሥራ ላይ
ይውላሉ፡-
ሀ) ግልፅ ጨረታ፣
ለ) በማጣሪያ የሚከናወን ጨረታ፣
ሐ) ውስን ጨረታ፣
መ) በቀጥታ የሚፈፀም ግዥ፣
ምንጭ፡- የተሻሻለው የፌዴራል የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ

Federal Public Procurement Service

26 Nov, 17:19


ለግንዛቤዎ!
ንብረትን በማስወገድ ሂደት ሊወሰዱ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች
ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ንብረትን በማስወገድ ሂደት የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ማድረግ አለበት፡፡
1 የንብረቱ ሕጋዊ ባለቤት ማን እንደሆነ መለየት፣ በይዞታው ሥር ለሚገኝ ንብረት የባለቤትነት ማስረጃ ማቅረብ የማይችል ከሆነ በገዥው ላይ ለሚቀርብ የይገባኛል ጥያቄ ዋቢ በመሆን ንብረቱን ማስወገድ፣
2/ ሕንፃና ተመሳሳይ ግንባታዎች የባለቤትነት መብት የተሰጠው ለፌዴራል መንግሥት በመሆኑ እነዚህን ንብረቶች ማስወገድ የሚፈልግ ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሚኒስቴሩን (ገንዘብ ሚኒስቴርን) ማስፈቀድ፣
3/ የሚወገዱት ንብረቶች በባህሪያቸው ልዩ ጠቀሜታ ያላቸው ወይም በጤና ወይም በአካባቢ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ኬሚካሎች፣ የኬሚካል ውጤቶች እና ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች፣መድኃኒቶች፣ ጨረራ አመንጪ ወይም የመሳሰሉት ሲሆኑ በአወጋገዱ ላይ ከሚመለከተው አካል ጋር በመመካከር ወይም አስፈላጊውን እገዛ በመጠየቅ ማስወገድ፡፡

Federal Public Procurement Service

15 Nov, 13:57


ለግንዛቤዎ!
ውልን ስለማስፈፀም
ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት፡-
ሀ) የውልን አፈፃፀም የሚከለክል ወይም የሚያስተጓጉል የተለየ ሁኔታ ካላጋጠመው በስተቀር ከአቅራቢዎች ወይም ከሚወገድ ንብረት ገዥዎች ጋር የተደረጉ ውሎች በፍጥነት ተፈፃሚ አንዲሆኑ ማድረግ፣
ለ) በአቅራቢው ወይም የሚወገድ ንብረት ገዥው ሊከናወኑ የሚገባቸውን
ተግባራት በመለየት አቅራቢው ወይም የሚወገድ ንብረት ገዥው በውሉ መሠረት ተግባራቱን በወቅቱ መፈፀሙን ተከታትሎ ማረጋገጥ፣
ሐ)የውሉ ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተው ውሉ ተፈፃሚ መሆን የጀመረበትን ቀን መዝግቦ መያዝ እና እንደአስፈላጊነቱ አቅራቢው ወይም የሚወገድ ንብረት ገዥው
እንዲያውቀው ማድረግ አለበት፡፡

Federal Public Procurement Service

14 Nov, 07:28


የአገልግሎቱ ሠራተኞች የደም ልገሳ አካሄዱ ።

ህዳር 05/2017 ዓ.ም

የመንግስት ግዥ አገልግሎት ሠራተኞች በደም እጦት የተቸገሩ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ የደም ልገሳ አካሂደዋል።

የደም ልገሳ መርሐ ግብሩ ከመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ጋር በመተባበር የተካሄደ ሲሆን በዕለቱም ከ16 ዩኒት ደም መሰብሰብ ተችሏል ።

Federal Public Procurement Service

13 Nov, 19:31


የመንግስት ግዥ አገልግሎት ከ2017-2018 በጀት ዓመት ለፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የአምስት ሎት የጋራ መጠቀሚያ ዕቃዎችን በመንግስት የኤሌክትሮኒክ የግዥ ዘዴ ግዥ ለመፈፀም በe-GP ፖርታል ላይ አለም አቀፍ ግልፅ ጨረታ አውጥቷል፡፡ ሎቶችም
1. የተለያዩ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ዕቃዎች፣
2. የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ማሽን ቶነሮች፣
3. የጽህፈት መሳሪያዎች፣
4. የፅዳት ዕቃዎች እና
5. የደንብ ልብሶች ናቸው፡፡

Federal Public Procurement Service

13 Nov, 08:53


የ5 ሎት የጋራ መጠቀሚያ ዕቃዎችን በe-GP ሲስተም ግዥ ለመፈፀም
የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
Forwarded From Ethiopian Broadcasting Corporation

Federal Public Procurement Service

13 Nov, 07:53


የፕሮግራም ጥቆማ !!
****************
አገልግሎታችን ከ2017-2018 በጀት ዓመት ለፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጋራ መጠቀሚያ ዕቃዎችን በመንግስት የኤሌክትሮኒክ የግዥ ዘዴ በአምስት ሎት የማዕቀፍ ስምምነት ግዥ ለመፈፀም በe-GP ፖርታል ላይ አለም አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡
በዚህ መሰረት የጨረታ ማስታውቂያውን ለተጫራቾች የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ ማስታወቂያው ህዳር 3 እና 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽት ሁለት ሰዓት ዜና በፊት ለሁለት ተከታታይ ቀናት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ቴሌቪዥን የሚተላለፍ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

Federal Public Procurement Service

13 Nov, 07:23


የዋስትና አይነቶች
ዋና ዋና የዋስትና አይነቶች ሶስት ናቸው፡፡
1. የጨረታ ማስከበሪያ
o አሸናፊው ተጫራች ውሉን ካልፈረመ ወይም በውሉ ላይ የተገለፀውን ተጨማሪ የውል ማስከበሪያ ማቅረብ ካልቻለ በድጋሚ ለሚወጣው ጨረታ ከወጭ ለመዳን፣
o አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ አቅርቦ ውል ከተፈረመ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያው ለአሸናፊው ተጫራችና ለሌሎችም ተጫራቾች ይመለሳል፡፡
2. የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና
o ለተቋራጩ የተከፈለውን ማንኛውንም የቅድሚያ ክፍያ አስተማማኝ ለማድረግ ይጠቅማል፣
o ዋስትናው ከመቅረቡ በፊት ክፍያ አይፈፀምም
o የሚቀርበው የዋስትና መጠን ለቅድሚያ ክፍያ ከሚከፈለው ገንዘብ ጋር እኩል መሆን አለበት፣
3. የውል ማስከበሪያ
o ተጫራቹ የውል ግዴታውን ሳይወጣ ሲቀር ገዥውን ከጉዳት (ከኪሳራ) ለመጠበቅ ይጠቅማል፣
o ብዙ ጊዜ ለውሉ ውጤታማ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡
o ተቋራጩ ስራውን ሳያከናውን ቢቀር የግዥ ፈፃሚው አካል በተያዘው የዋስትና ገንዘብ ስራውን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልጉ ተጨማሪ ወጭዎችን ይሸፍንበታል፡፡

Federal Public Procurement Service

12 Nov, 18:02


የተፈቀዱ የንብረት ማስወገጃ ዘዴዎች
በማናቸውም የመንግስት መ/ቤት ይዞታ ስር ያለን ንብረት ለማስወገድ እንደ ንብረቱ ባህርይ የሚከተሉትን የንብረት ማስወገጃ ዘዴዎች ስራ ላይ ይውላሉ፡፡
• ለሌላ የመንግስት መ/ቤት በማዛወር ወይም በማስተላለፍ፣
• ባሉበት ሁኔታ ወይም እንደ ሁኔታው ፈታቶ ለሕዝብ በኤሌክትሮኒክ ሥርዓት
መሠረት በጨረታ ወይም በሐራጅ በመሸጥ፣
• ንብረቱን በስጦታ በማስተላለፍ፣
• ንብረቱን በመቅበር ወይም በማቃጠል፣
• ንብረቱን በማፈን፣ በማምከን ወይም በመቀየጥ ማስወገድ ናቸው፡፡
ሆኖም የመንግስት ግዥ አገልግሎት በመቋቋሚያ ደንቡ (በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 184/2002 ዓ.ም) በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት ንብረቶችን የሚያስግደው የመ/ቤቶች የበላይ ኃላፊዎች ውሳኔ ሰጥተው ወደ ተቋማችን የሚልኳቸውን ንብረቶች በጨረታ በመሸጥ ነው፡፡

Federal Public Procurement Service

08 Nov, 11:14


ያገለገሉ ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች ጨረታ ተከፈተ
*******************
ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
የመንግስት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የ15 ፌዴራል መ/ቤቶች የሆኑ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ለማስወገድ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የጨረታ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት ጨረታው በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በአገልግሎቱ አዳራሽ ተከፍቷል፡፡

Federal Public Procurement Service

07 Nov, 18:44


55 ሞተር ሳይክሎችን ግዥ ለመፈጸም የጨረታ ማስታወቂያ ወጣ
*********************
ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
የመንግስት ግዥ አገልግሎት በኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ጠያቂነት በገጠር ለሚገኙ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት አገልግሎት የሚውሉ 55 ሞተር ሳይክሎችን ግዥ ለመፈጸም በማንዋል የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች የወጣውን የጨረታ ሰነድ፡
በአገልግሎቱ የቴሌግራም ገጽ- Federal Public Procurement Service
በአገልግሎቱ የፌስቡክ ገጽ Federal Public Procurement Service-PPS
በድረ -ገጽ WWW.ppa.gov.et በመመልከት መሳተፍ የሚችል መሆኑን አገልግሎቱ አሳውቋል፡፡ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-1-22-37-53 ወይም 011-1-22-37-40/011-223722 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የሚቻል መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል፡፡

Federal Public Procurement Service

31 Oct, 09:43


የ540 የአሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ግዥ የቴክኒክ ሰነድ በኦንላይን ተከፈተ
*******************************
ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም
የመንግስት ግዥ አገልግሎት በገንዘብ ሚኒስቴር ትዕዛዝ ለባለበጀት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 540 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በኤሌክትሮኒክ የመንግስት ግዥ (e-GP) ሲስተም ግዥ ለመፈፀም ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ የቴክኒክ ሰነዱን በኦንላይን የከፈተ ሲሆን ተጫራቾችም የጨረታ አከፋፈት ሂደቱን ባሉበት በኦንላይን እንዲከታተሉ ተደርጓል፡፡

Federal Public Procurement Service

30 Oct, 14:03


የአገልግሎቱ፣ የገንዘብ ሚኒስቴርና ሌሎች ተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄደ
***********************
ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም- የመንግስት ግዥ አገልግሎት፣ የገንዘብ ሚኒስቴር እንዲሁም የሌሎች ተጠሪ ተቋማት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው፣ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ፣ ም/ዋና ዳይሬክተሮች፣ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስቴር እና የሌሎች ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በገንዘብ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱም ከሩብ ዓመት አፈፃፀሙ በተጨማሪ ሀገራዊ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዝርዝር የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም በዋና ዋና ዘርፎች የተገኙ ውጤቶችን ጨምሮ ለተሳታፊዎች ቀርቧል፡፡

Federal Public Procurement Service

30 Oct, 13:27


የአገልግሎቱ አመራርና ሠራተኞች መንግስት ባደረገው የደመወዝ  ጭማሪ መደሰታቸውን ገለፁ
******
ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም
የኑሮ ውድነቱ በመንግስት ሰራተኛው ላይ የሚያደርሰውን ጫና በመገንዘብ መንግስት ከጥቅምት 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የደመወዝ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ 
ይህን ተከትሎ መንግስት በዚህ ፈታኝ ወቅት ኑሮውን በተወሰነ ደረጃ እንዲቋቋም የደመወዝ ጭማሪ ማድረጉ ደስታ እንደፈጠረላቸው የአገልግሎቱ ሠራተኞች ተናግረዋል።
የተደረገው ጭማሪም ስራቸውን በአግባቡ እንዲሰሩ የሚያበረታታ መሆኑን ሠራተኞቹ ጨምረው ገልጸዋል።

Federal Public Procurement Service

29 Oct, 07:54


ለግንዛቤዎ!
የተፈቀዱ የንብረት ማስወገጃ ዘዴዎች
በማናቸውም የመንግስት መ/ቤት ይዞታ ስር ያለን ንብረት ለማስወገድ እንደ ንብረቱ ባህርይ የሚከተሉትን የንብረት ማስወገጃ ዘዴዎች ስራ ላይ ይውላሉ፡፡
• ለሌላ የመንግስት መ/ቤት በማዛወር ወይም በማስተላለፍ፣
• ባሉበት ሁኔታ ወይም እንደ ሁኔታው ፈታቶ ለሕዝብ በኤሌክትሮኒክ ሥርዓት
መሠረት በጨረታ ወይም በሐራጅ በመሸጥ፣
• ንብረቱን በስጦታ በማስተላለፍ፣
• ንብረቱን በመቅበር ወይም በማቃጠል፣
• ንብረቱን በማፈን፣በማምከን ወይም በመቀየጥ ማስወገድ ናቸው፡፡
ምንጭ፡- የፌዴራል የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ
(ተሻሽሎ የፀደቀው)
ሆኖም የመንግስት ግዥ አገልግሎት በመቋቋሚያ ደንቡ (በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 184/2002 ዓ.ም) በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት ንብረቶችን የሚያስግደው የመ/ቤቶች የበላይ ኃላፊዎች ውሳኔ ሰጥተው ወደ ተቋማችን የሚልኳቸውን ንብረቶች በጨረታ በመሸጥ ነው፡፡

Federal Public Procurement Service

28 Oct, 13:04


ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶች ጨረታ ተከፈተ
*******************
ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም
የመንግስት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የ4 መ/ቤቶች ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን እና የ1 መ/ቤት ንብረት የሆነ የቁም ጽድና ፓቹላ ዛፎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በሽያጭ ለማስወገድ ጥቅምት 02 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
ስለሆነም ጨረታው በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በአገልግሎቱ አዳራሽ ተከፍቷል፡፡

Federal Public Procurement Service

28 Oct, 12:22


በሽያጭ የሚወገዱ የ15 መ/ቤቶች ያገለገሉ ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች የጨረታ ማስታወቂያ
Forwarded From Ethiopian Broadcasting Corporation
ማስታወሻ፡ ጨረታው የወጣው ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ሲሆን
የሚከፈተው ደግሞ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ነው፡፡

Federal Public Procurement Service

27 Oct, 11:22


ዜና!
ለ228 የኤሌክትሮኒክ ተሽከርካሪዎች ግዥ የ1.6 ቢሊየን ብር የአሸናፊነት ደብዳቤ ተሰጠ
************************
ጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ.ም
የመንግስት ግዥ አገልግሎት በገንዘብ ሚኒስቴር ትዕዛዝ ለባለበጀት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በኤሌክትሮኒክ የመንግስት የግዥ ሲስተም (e-GP system) ግዥ ለመፈፀም ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት 228 የኤሌክትሮኒክ ተሽከርካሪዎችን ለማቅረብ አሸናፊ ለሆኑ ሶሰት አቅራቢዎች ቫትን ጨምሮ በጠቅላላ ዋጋ ብር 1,682,873,095.29 የአሸናፊነት ደብዳቤ ተሰጥቷል፡፡

Federal Public Procurement Service

27 Oct, 10:49


#ኢትዮጵያ

ለባለ በጀት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከ195 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ወጥቶባቸው ተገዙ የተባሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ገቡ።

በገንዘብ ሚኒስቴር ትዕዛዝ ለባለበጀት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 30 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ተገዝተው መግባታቸው ተሰምቷል።

ተሽከርካሪዎቹ በ195 ሚሊዮን 286 ሺህ 516 ብር ከ76 ሳንቲም ነው የገቡት።

በገንዘብ ሚኒስቴር ትዕዛዝ የመንግስት ግዥ አገልግሎት 30 ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በመንግስት የኤሌክትሮኒክ የግዥ ስርዓት በዋጋ ማቅረቢያ የግዥ ዘዴ ለመፈፀም ጨረታ አውጥቶ ነበር።

በዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት ዋጋ ማቅረቢያ ተወዳድረው አሸናፊ የሆኑ ሁለት አቅራቢዎች ፦

➡️ ባለ 7 መቀመጫ የሆኑ Volkswagen ID 6 Electric Vehicles ብዛት 20 units

➡️ ባለ 5 መቀመጫ የሆኑ Kia e5 Electric Vehicles ብዛት 10 units

ለማቅረብ ከአገልግሎቱ ጋር በገቡት አጠቃላይ የውል መጠን ከነቫቱ ብር 195,286,516.76 መሰረት አቅርበዋል ተብሏል።

@tikvahethiopia

Federal Public Procurement Service

26 Oct, 20:12


በፀደቁ የውስጥ አሰራር ሰነዶች ላይ ውይይት ተደረገ
**********************************
ጥቅምት 16 ቀን 2107 ዓ.ም
በእውቀት ላይ ተመስርቶ ስራ ለማከናወንና ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን የአሰራር ስርዓት መዘርጋት ለአንድ ተቋም ቁልፍ ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት በአገልግሎቱ የንብረት ማስወገድ እና የሰራተኞች እውቅናና ማበረታቻ የውስጥ አሰራር ስርዓት ሰነዶች ተዘጋጅተው በአገልግሎቱ የስራ አመራር ቦርድና በማኔጅመንት አባላት ፀድቀው ወደ ስራ ተገብቷል፡፡
በዛሬው ዕለትም የአገልግሎቱ ሠራተኞች እነዚህን የውስጥ አሰራር ስርዓት ሰነዶች አግባቡ ተረድተው ስራቸውን ማከናወን እንዲችሉ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ቀደም ሲል በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ማሻሻያ የተደረገበት የንብረት ማስወገድ የውስጥ አሰራር ስርዓት ሰነድ በንብረት ማስወገድ መሪ ስራ አስፈጻሚ በአቶ ሹንቃ አዱኛ የቀረበ ሲሆን፤ ወ/ሮ አዲስ አለም በአገልግሎቱ የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ስራ አስፈጻሚ ደግሞ የሰራተኞችን እውቅናና ማበረታቻ የውስጥ አሰራር ስርዓት ሰነድን አቅርበው በቀረቡ ሰነዶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ እንደተቋም የአሰራር ስርዓት መዘርጋት ለስራ ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታትና ስራን ለማቅለል ወሳኝ መሆኑን አውስተው ይህንንም ሰራተኛው መገንዘብና ስራውን በእውቀት ላይ ተመስርቶ ማከናወን አለበት በለዋል፡፡
የተሻለ የፈፀመን ስራ መሪና ሰራተኛን ለማበረታታትና እውቅና ለመስጠትም የሰራተኞች እውቅናና ማበረታቻ የውስጥ አሰራር ስርዓት ሰነድ መዘጋጀቱን አድንቀዋል፡፡

Federal Public Procurement Service

26 Oct, 17:12


አገልግሎቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ
********************
(ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ/ም) የመንግስት ግዥ አገልግሎት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙን የገመገመው ዋና ዳይሬክተሩ ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ፣ የግዥና ውል አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ክፍሌ ገ/ማርያም፣ የንብረት ማስወገድና ገበያ ጥናት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ነጂባ አክመል እንዲሁም ሁሉም የተቋሙ የስራ አስፈጻሚዎች እና ሰራተኞች በተገኙበት ነው፡፡
የአፈጻጸም ሪፖርቱን የአገልግሎቱ የስትራቴጅክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ረድኤት ተክሉ ያቀረቡ ሲሆን በሁሉም ስራ ክፍሎች የተከናወኑ አጠቃላይ ተግባራትን፣ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና መፍትሄያቸው እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቷቸው የሚከናወኑ ተግባራትን ባካተተ መልኩ ቀርቧል፡፡
በቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ ከሠራተኞች ሃሳብ እና አስተያየቶች ቀረበው በበላይ አመራሮችና በሚመለከታቸው የስራ ክፍል ኃላፊዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡
በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተሩ ክቡር አቶ አስማረ በቀረቡ ሃሳብ አስተያየቶች ዙሪያ ተገቢውን ማብራሪያ በመስጠት የሩብ ዓመቱ አፈጻጸም ለአብነት በንብረት ማስወገድ፣ በውስጥ ግዥም ሆነ በማዕቀፍ ስምምነት ግዥ፣ ተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦችን ማወራርድ ላይ ያለው አበረታች ስራ፣ በአገልግሎቱ የተጀመረው የበጎ አድራጎት ስራ፣ የተቋሙ የህጻናት ማቆያ ስራ መጀመር እና ሌሎችም ተግባራት አፈጻጸም ጥሩ የሚባል ደረጃ የሚገኝ መሆኑን በማንሳት በቀጣይ ሁለተኛ ሩብ ዓመት በግዥም ሆነ በንብረት ማስወገዱ ዘርፍ እንዲሁም በሌሎች የስራ ክፍሎች የታቀዱ እቅዶችን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ሰራተኛን አሳትፈን በረትተን መስራት ይጠበቅብናል በማለት ገልጸዋል፡፡

Federal Public Procurement Service

26 Oct, 17:12


አቶ አስማረ አክለውም እንደ ሀገር እየተተገበረ ያለውን የሲቪል ሰርቪስ የሪፎርም ማሻሻያ ስራ ሁሉም የአገልግሎታችን ስራ መሪ እና ሰራተኛ ግንባር ቀደም ሆኖ እና ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት ያመላከቱ ሲሆን ሰራተኛው የሚፈልገውን የተሻለ ደመወዝም ሆነ ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን ጥያቄ ለመፍታት ለተግባራዊነቱ ርብርብ ማድረግ እንደሚጠብቅም አጽንኦት በመስጠት መርሐ ግብሩን አጠቃለዋል፡፡

Federal Public Procurement Service

25 Oct, 06:37


የፕሮግራም ጥቆማ!
**************
የመንግስት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የ15 መ/ቤቶች የሆኑ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በሽያጭ ለማስወገድ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የጨረታ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡
ስለሆነም የጨረታ ማስታውቂያውን ለተጫራቾች የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ ማስታወቂያው ከዛሬ ጥቅምት 15 እስከ እሁድ ጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽት ሁለት ሰዓት ዜና በፊት ለሶስት ተከታታይ ቀናት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ቴሌቪዥን የሚተላለፍ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

Federal Public Procurement Service

24 Oct, 12:06


ለግንዛቤዎ!
ውልን ስለማስፈፀም
ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት፡-
ሀ) የውልን አፈፃፀም የሚከለክል ወይም የሚያስተጓጉል የተለየ ሁኔታ ካላጋጠመው በስተቀር ከአቅራቢዎች ወይም ከሚወገድ ንብረት ገዥዎች ጋር የተደረጉ ውሎች በፍጥነት ተፈፃሚ አንዲሆኑ ማድረግ፣
ለ) በአቅራቢው ወይም የሚወገድ ንብረት ገዥው ሊከናወኑ የሚገባቸውን
ተግባራት በመለየት አቅራቢው ወይም የሚወገድ ንብረት ገዥው በውሉ መሠረት ተግባራቱን በወቅቱ መፈፀሙን ተከታትሎ ማረጋገጥ፣
ሐ)የውሉ ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተው ውሉ ተፈፃሚ መሆን የጀመረበትን ቀን መዝግቦ መያዝ እና እንደአስፈላጊነቱ አቅራቢው ወይም የሚወገድ ንብረት ገዥው
እንዲያውቀው ማድረግ አለበት፡፡

Federal Public Procurement Service

23 Oct, 19:13


በ1.2 ቢሊየን ብር የአሸናፊነት ደብዳቤ ተሰጠ
************************
የመንግስት ግዥ አገልግሎት በገንዘብ ሚኒስቴር ትዕዛዝ ለባለበጀት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 296 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በኤሌክትሮኒክ የመንግስት የግዥ ሲስተም (e-GP system) ግዥ ለመፈፀም ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት 143 units of Electric Pick UP D/CAB 4WD and 47 Units of Electric Midi Bus (13-16 Seats) አሸናፊ ለሆነው ድርጅት የ1,263,032,100.00 ብር የአሸናፊነት ደብዳቤ ሰጥቷል፡፡

Federal Public Procurement Service

23 Oct, 17:56


ያገለገሉ ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች በሽያጭ ሊወገዱ ነው
******************
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት የ15 መ/ቤቶች ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም በወጣው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የተቀመጡ ዝርዝር መስፈርቶችን በመመልከት የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመክፈል በጨረታው ላይ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የመንግሥት ግዥ አገልግሎት

Federal Public Procurement Service

23 Oct, 17:38


የጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር PPS/VP-15FBI/04/02/2017
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የግብርና ሚ/ር፣ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአርዳይታ ግብርና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ፣ የማዕድን ሚ/ር፣ የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚ/ር፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን፣ የጉሙሩክ ኮሚሽን፣ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ፣የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚ/ር፣ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል፡፡
1. በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆኑ ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
2. ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ህንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 007 በመምጣት የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመንግሥት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ላይ ገቢ በማድረግና ያስገቡበትን የባንክ ስሊፕ ይዘው በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሸከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
5. የጨረታው የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል፡፡ ይሁንና የተሽከርካሪውን የመነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
6. ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ እና የጉምሩክ ቀረጥ ግብር እዳ ካለበት በባለንብረቱ መሥሪያ ቤት የሚሸፍን ሲሆን የስም ማዛወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው የሚሸፈን ይሆናል፡፡
7. የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም፡፡
8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል::
9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ተሽከርካሪዎች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
10. አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል፡፡
11. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሽከርካሪውን በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
12. አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት
ሐውልት አደባባይ ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-122 37-08 ወይም 011-122 37 36 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት
አዲስ አበባ

Federal Public Procurement Service

23 Oct, 17:33


ስለሆነም ለዚህ የንቅናቄ ዘመቻ መሳካት የሚመለከታቸው የተቋምዎ አመራርና ሠራተኞች ትብብር ወሳኝ በመሆኑ ተገቢውን መረጃ በመስጠት ትብብር እንድታደርጉ ከወዲሁ ምስጋናችን እናቀርባለን፡፡

Federal Public Procurement Service

23 Oct, 08:32


ለግንዛቤዎ!
ንብረትን በማስወገድ ሂደት ሊወሰዱ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች
ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ንብረትን በማስወገድ ሂደት የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ማድረግ አለበት፡፡
1 የንብረቱ ሕጋዊ ባለቤት ማን እንደሆነ መለየት፣በይዞታው ሥር ለሚገኝ ንብረት የባለቤትነት ማስረጃ ማቅረብ የማይችል ከሆነ በገዥው ላይ ለሚቀርብ የይገባኛል ጥያቄ ዋቢ በመሆን ንብረቱን ማስወገድ፣
2/ ሕንፃና ተመሳሳይ ግንባታዎች የባለቤትነት መብት የተሰጠው ለፌዴራል መንግሥት በመሆኑ እነዚህን ንብረቶች ማስወገድ የሚፈልግ ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሚኒስቴሩን ማስፈቀድ፣
3/ የሚወገዱት ንብረቶች በባህሪያቸው ልዩ ጠቀሜታ ያላቸው ወይም በጤና ወይም በአከባቢ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ኬሚካሎች፣የኬሚካል ውጤቶች እና ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች፣መድኃኒቶች፣ጨረራ አመንጪ ወይም የመሳሰሉት ሲሆኑ በአወጋገዱ ላይ ከሚመለከተው አካል ጋር በመመካከር ወይም አስፈላጊውን እገዛ በመጠየቅ ማስወገድ፡፡

Federal Public Procurement Service

23 Oct, 07:22


ለግንዛቤዎ!
ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ንብረት ማስወገድ የሚችለው ከሚከተሉት ሁኔታዎች አንዱ ተሟልቶ ሲገኝ ብቻ ነው፡-
1/ ንብረቱ ለመሥሪያ ቤቱ ዓላማዎች የማይፈለግ ሲሆን፣
2/ ንብረቱን ይዞ መቀጠል የሚያስከትለው ወጪ ከፍተኛ በመሆኑ ንብረቱን ማስወገድ የተሻለ አማራጭ ሆኖ ሲገኝ፣
3/ በልዩ ልዩ ምክንያት ንብረቱ የሚፈለግበትን አገልግሎት በብቃት መስጠት የማይችል ወይም ከአገልግሎት ውጪ ሲሆን፣
4/ መሥሪያ ቤቱ ከሚኖረው የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የሥራ ዕቅድ ንብረት ትርፍ መሆኑ ሲታመን ነው፡፡

Federal Public Procurement Service

19 Oct, 20:35


በአገልግሎቱ የግዥና ውል አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ክፍሌ ገ/ማርያምም በዚህ ስልጠና ላይ የተገኙ ሲሆን ባሳለፍነው 2016 በጀት ዓመት ከንብረት ማስወገድ የተገኘው ገቢ የሚያበረታታ እንደሆነና ይህም አገልግሎቱ በንብረት ማስወገድ ዘርፉ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አመላካች እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ አገልግሎታችን በቀጣይ የማስወገዱ ስራውን ዲጅታላይዝ በማድረግ እና በኤሌክትሮኒክ ስርዓት በማከናወን አሰራሩን የበለጠ ቀልጣፋ ማድረግና ለመንግስት የተሻለ ገቢ ማስገኘት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንዳለበት አቶ ክፍሌ አስገንዝበዋል፡፡
በመጨረሻም የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ስልጠናውን ያጠቃለሉ ሲሆን አገልግሎታችን የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ እንዲወጣ ባለስልጣን መ/ቤቱ እያደረገ ላለው ድጋፍ እና እየተሰጠ ባለው ስልጠና ምስጋናቸውን አቅርበው የተሻሻለውን አዋጁ መነሻ በማድረግ በሚዘጋጀው የንብረት አስተዳደር መመሪያ ላይ አገልግሎቱ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊ ግብዓቶችን እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡
አቶ አስማረ አክለውም እንዳለፈው በጀት ዓመት “ፅዱ ተቋምን በመፍጠር፤ ሀብትን እንፍጠር” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የዘንድሮው የንብረት ማስወገድ የንቅናቄ መርሐ ግብር ወሳኝና በበጀት ዓመቱ በሽያጭ ከሚወገዱ ንብረቶችና ተሽከርካሪዎች 240 ሚሊየን ብር ለመንግስት ገቢ ለማስገኘት ያቀድነውን እቅድ ለማሳካት ቁልፉ ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ በንቅናቄው የተቋማት ትብብር ወሳኝ መሆኑን ገልጸው ያለ አገልግሎት የተከማቹ ንብረቶችን በማስወገድ ተቋማቸውን ሙሉ በሙሉ ፅዱ ላደረጉ ተቋማት አገልግሎታችን የምስጋና እና እውቅና የመስጠት ፕሮግራም እንደሚኖረውም አቶ አስማረ አመላክተዋል፡፡

Federal Public Procurement Service

19 Oct, 20:35


በተሻሻለው በዚህ አዋጅ በንብረት አስተዳደር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡት በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የግዥ ንብረት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ገበያው ይታየው ሲሆኑ በተሰጠው ስልጠና ዙሪያ ከሰልጣኞች የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በአገልግሎቱ የንብረት ማስወገድ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሹንቃ አዱኛ የ2017 በጀት ዓመት የንብረት ማስወገድ ንቅናቄ መርሐ ግብርን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡ ሲሆን የንቅናቄውን ዓላማ፣ በዚህ ንቅናቄ የተመረጡ ተቋማትን፣ በንቅናቄ ፕሮግራሙ ላይ የሚሳተፉ ኮሚቴዎች ተግባርና ኃላፊነትና እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የንብረት ማስወገድና ገበያ ጥናት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ነጂባ አክመል የንቅናቄ መርሀ ግብሩን አስመልክተው እንደተናገሩት ባሳለፍነው በጀት ዓመት በተሰራ የንብረት ማስወገድ ንቅናቄ ፕሮግራም አገልግሎቱ ከዕቅዱ በላይ ገቢ ማግኘቱን አውስተው ለዚህም ትልቅ ገቢ መገኘት የሁሉም የአገልግሎቱ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች አስተዋጽኦ ያለበት መሆኑን በማንሳት ለተሳተፉ አመራርና ሰራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ወ/ሮ ነጂባ አክለውም እንደ ሀገር በንብረት አወጋገድ ዙሪያ ብዙ ያልተሰራ ስራ እንዳለ በማንሳት፤ ሆኖም አሁን ላይ መንግስት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ስራውን ለመስራት የተዘጋጀ መሆኑን በመግለጽ አገልግሎታችንም የዚህ እቅድ አካል በመሆን ይህን የንቅናቄ ፕሮግራም በርተትን በማስቀጠል ዕቅዳችን ማሳካት ይጠብቅብናል ብለዋል፡፡

Federal Public Procurement Service

19 Oct, 20:33


በተሻሻለው የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ እና በንብረት ማስወገድ ንቅናቄ ፕሮግራም ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ያገለገሉ ንብረቶችን በማስወገድ “ተቋማቸውን ሙሉ በሙሉ ፅዱ ላደረጉ ተቋማት” የምስጋና እና እውቅና የመስጠት ፕሮግራም እንደሚካሄድ ተገለጸ
********************************
ጥቅምት 09 ቀን 2017 ዓ.ም
ተሻሽሎ በጸደቀው የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ላይ ከንብረት አስተዳደር አንፃር በተደረጉ ማሻሻያዎች ዙሪያ ለአገልግሎቱ የበላይ አመራሮችና ስራ አስፈፃሚዎች፣ ለንብረት ማስወገድ፣የገበያ ጥናት እና ንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰልጠና ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ላይ የተገኙት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ ስልጠናውን በማስመልከት እንደተናገሩት፤ አገልግሎታችን ከተቋቋመበት ዋና ዓላማ አንዱ ያገለገሉ ተሽከርካዎችንና ልዩ ልዩ ንብረቶችን በሽያጭ በማስወገድ ለመንግስት ገቢ ማስገኘት መሆኑን ገልፀው በዚህ ስራ ላይ ያሉ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞችም በእውቅት ላይ ተመስርተው ስራቸውን ለመፈጸም የተሻሻለውን አዋጅ ከንብረት አስተዳደር አንጻር በደንብ መረዳትና ማወቅ እንዳለባቸው አመላክተዋል፡፡
አቶ አስማረ አክለውም ባሳለፍነው 2016 በጀት ዓመት በተደረገው የንብረት ማስወገድ ንቅናቄ ስራ በሽያጭ ከተወገዱ ንብረቶችና ተሽከርካሪዎች በአገልግሎቱ ታሪክ ከፍተኛ የሆነው ገቢ መገኘቱን አውስተው፤ በዚህ በጀት ዓመትም ሰፊ የንብረት ማስወገድ የንቅናቄ ስራ በመስራት ለመንግስት ከፍተኛ ገቢ ለማስገኘት እና በመንግስት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት ያለበት መሆኑን አስገንዝበዋል።

Federal Public Procurement Service

17 Oct, 20:25


ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶች፣ የቁም ጽድና ፓቹላ ዛፎች በሽያጭ ሊወገዱ ነው
************************
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት የ4 መ/ቤቶች (የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጂማ ዲስትሪክት፣ አርዳይታ ግብርና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ አርዳይታ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ) ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን እንዲሁም የ1 መ/ቤት (በእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት የበደሌ የእንስሳት ጤና ማዕከል በደሌ) ንብረት የሆኑ የቁም ጽድና ፓቹላ ዛፎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ጥቅምት 02 ቀን 2017 ዓ.ም በወጣው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የተቀመጡ ዝርዝር መስፈርቶችን በመመልከት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በጨረታው ላይ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የመንግሥት ግዥ አገልግሎት
አዲስ አበባ

Federal Public Procurement Service

17 Oct, 19:08


የጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገሉ የተለያዩ ንብረቶች እና የቁም ጽድ እና ፓቹላ ዛፎች በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር PPS/NVP-4FBI/03/01/2017
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግስት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸዉ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጂማ ዲስትሪክት፣ አርዳይታ ግብርና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ አርዳይታ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶች እንዲሁም ንብረትነታቸዉ በእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት የበደሌ የእንስሳት ጤና ማዕከል በደሌ የሚገኙ የቁም ጽድ እና ፓቹላ ዛፎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
1. በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆን ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
2. ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢ.ፌ..ዲ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ህንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 007 በመምጣት የንብረቶቹን/ዛፎችን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመንግስት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ላይ ገቢ በማድረግ ና ያስገቡበትን የባንክ ስሊፕ ይዘው በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ክወጣበት ቀን ጅምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶችን/ዛፎችን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
4. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች/ዛፎች በእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 10% (10 በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታ ሳጥን መዝጊያው ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
5. የጨረታው የመገምገሚያ መስፈርቱ ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል፡፡ ይሁንና የንብረቶቹን/ዛፎቹን የመነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ ) ያላስያዘ እንዲሁም በሰነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
6 . የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 16 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም፡፡
7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለጸላቸው ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
8. በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች/ዛፎች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ደረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
9. አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
10 . አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን/ዛፎቹን በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
11. አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በክፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፦ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግስት ግዥ አገልግሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት አደባባይ ፊትለፊት
ለበለጠ መረጃ ፦ በስልክ ቁጥር 011-122 37-08 ወይም 011-122 37 36 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ግዥ አገልግሎት
አዲስ አበባ

Federal Public Procurement Service

16 Oct, 13:08


አገልግሎታችን የሚያበረታታ የበጎ አድራጎት ስራ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ
**************************************************
የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች ከግንቦት ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ የኢኮኖሚ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የአገልግሎታችን ሠራተኞች ህጻናት ልጆችን ለመደገፍ በፈቃደኝነት ከደመወዛቸው ላይ እንዲቆረጥ በወሰኑት መሠረት በየወሩ ለአምስት ህፃናት ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት በሩብ ዓመቱ ከአገልግሎቱ አመራሮችና ሰራተኞች የተሰበሰበ ጠቅላላ ብር 13,380.00 ሲሆን ለእያንዳንዳቸው በየወሩ 892.00 ብር በመስጠት ድጋፍ የተደረገላቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
ይህም ተግባር ቀጣይነት ያለውና አገልግሎታችን የሚያበረታታ የበጎ አድራጎት ስራ እየሰራ እንደሆነ የሚያመላክት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈፃፀም ውይይት ላይ በነበረው የማኔጅመንት ስብሰባ የተገኙት የአገልግሎታችን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ለዚህ በጎ አድራጎት ስራ ለተሳተፉ አመራርና መላው ሠራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Federal Public Procurement Service

16 Oct, 11:14


በ504.8 ሚሊዮን ብር ውል መፈረሙ የውል አስተዳደር ውጤታማነትን ያሳያል ተባለ
*******************************
አገልግሎታችን በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ለፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች እና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች አገልግሎት የሚውል የፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ማሽን ቶነሮችን፣ የፅዳት ዕቃዎችን፣ የተሽከርካሪ ጎማዎችን እና የተሽከርካሪ የመድን ዋስትና አገልግሎት ግዥዎችን ለማቅረብ አሸናፊ ከሆኑት 5 አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በ504,845,010.78 ብር አምስት ውሎች ተፈርመዋል፡፡
ይህም በሩብ ዓመቱ ከላይ የተገለጹ ግዥዎችን የግዥ ሂደት በማጠናቀቅ ለአሸናፊ ድርጅቶች የአሸናፊነት ደብዳቤ በተሰጠው መሰረት ሙሉ ለሙሉ ውሎቹን መፈራረም መቻሉ ውጤታማ የግዥና የውል አስተዳደር ስራ የተሰራ መሆኑን አመላካች እንደሆነ ተገልጿል፡፡

Federal Public Procurement Service

16 Oct, 11:13


በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎችና ልዩ ልዩ ንብረቶች የተገኘው ገቢ
የ92 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተገለፀ
******************************
የመንግስት ግዥ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 39 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ ሎት ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ ሽያጭ በማስወገድ 38,422,745.90 ብር ገቢ አግኝቷል፡፡ ይህ ገቢ ከ2016 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ18.4 ሚሊዮን ብር ብልጫ ወይም የ92% በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡
አገልግሎታችን ባሳለፍነው 2016 በጀት ዓመት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎችና ልዩ ልዩ ንብረቶች በአገልግሎቱ ታሪክ ከፍተኛ የሆነውን 213.9 ሚሊየን ብር ለመንግስት ገቢ ማስገኘቱ የሚታወስ ነው፡፡

Federal Public Procurement Service

16 Oct, 09:29


በሙስና ምንነትና መከላከል ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
******************************************
ጥቅምት 06/2017 ዓ.ም
ለመንግስት የግዥ አገልግሎት ሠራተኞች በሙስና ምንነት እና መከላከያ ስልቶች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዛሬው ዕለት ተሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማ ሠራተኛው በተለይም ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ የስራ ክፍሎች የሙስናን ምንነትና ልዩ ባህሪያት ተገንዝበው፤ከሙስናና ብልሹ አሠራር የፀዳ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን በአገልግሎቱ የስነምግባርና ፀረ ሙስና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አዲስ አለም ተናግረዋል።

Federal Public Procurement Service

15 Oct, 09:03


ለግንዛቤዎ!
• “የመንግሥት ግዥ” ማለት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የመንግሥት ገንዘብን በመጠቀም የሚያከናውኑት ግዥ ነው፤
• “ጨረታ” ማለት የግዥ ወይም የንብረት ሽያጭ ማስታወቂያ ይፋ ከሆነበት ወይም ጥሪ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ አሸናፊው ተለይቶ ውል እስኪፈረም ድረስ ያለው የግዥ አፈፃጸም ወይም የንብረት ሽያጭ ሂደት ነው፤
• “ተወዳዳሪ” ማለት በመንግሥት ግዥ ወይም በንብረት ሽያጭ ላይ እንዲሳተፍ የተጋበዘ ወይም በጨረታ ለመሳተፍ ፍላጎት ያሳየ ሰው ነው፣
• “ተጫራች” ማለት የመጫረቻ ሰነድ ያቀረበ ሰው ነው፤
• “አቅራቢ” ማለት ለመንግሥት መሥሪያ ቤት ዕቃ ለማቅረብ ከምክር ውጭ የሆነ አገልግሎት ወይም የምክር አገልግሎት ለመስጠት ወይም የግንባታ ዘርፍ ሥራን ለማከናወን ውል የገባ ሰው ነው፤
• “የጨረታ ሰነድ” ማለት በመደበኛ የጨረታ ሰነድ ላይ በመመስረት በመንግሥት መሥሪያ ቤት የሚዘጋጅ ዝርዝር የግዥ ፍላጎት መግለጫን ወይም በጨረታ የሚሸጡ ንብረቶችን ዓይነት እና ያሉበትን ሁኔታ እንዲሁም የመወዳደሪያ መስፈርቶችን የያዘ ሰነድ ነው፤
• “የመጫረቻ ሰነድ” ማለት የመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መሰረት በማድረግ ተጫራች በግዥው ወይም በሽያጩ ለመሳተፍ የሚያቀርበው የመወዳደሪያ ሀሳብ የያዘ ሰነድ ነው፤
• “መደበኛ የጨረታ ሰነድ” ማለት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች አጠቃላይ ይዘቱ አንድ ወጥ የሆነ ወይም ተመሳሳይ የሆነ የጨረታ ሰነድ በቀላሉ ማዘጋጀት እንዲችሉ የሚረዳ በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የሚዘጋጅ ሰነድ ሲሆን፣ ለዲዛይን እና ግንባታ፣ ለኮንስትራክሽን ማኔጅመንት እና ለመሳሳሉ ውሎች የሚያገለግሉ ሰነዶችን ያካትታል፤

Federal Public Procurement Service

14 Oct, 08:06


የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች 17ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበሩ
**************
ጥቅምት 04 ቀን 2017 ዓ.ም
የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች 17ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ከመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች ጋር “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ሃሳብ በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል፡፡
በእለቱም የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብር አቶ በረከት ፍስሐጽዮን፣ የመንግስት ግዥ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ፣ በአገልግሎቱ የንብረት ማስወገድና ገበያ ጥናት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ነጂባ አክመል እና ሌሎች አመራር እና ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡
ዕለቱን በማስመልከትም ሰንደቅ ዓላማችን የሀገራችን ክብርና ነጻነት እንዲሁም የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን መገለጫ እና የአብሮነታችንና የሉዓላዊነታችን ዓርማ መሆኑን የሚያንፀባርቅ መልዕክት የተላለፈ ሲሆን፤ በሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሃላ በመፈፀም እና ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ መዝሙር በመዘመር የሰንደቅ ዓላማ መስቀል ስነስርዓት በማካሄድ ተጠናቋል፡፡