Ethio engineering Group @metecofficial Channel on Telegram

Ethio engineering Group

@metecofficial


አዳዲስና ወቅታዊ ዜናዎችና መረጃዎችን ማግኘት ከፈለጉ እኛን ይቀላቀሉ!!

Ethio Engineering Group (Amharic)

ኢትዮ ኢንግአንሼንግ ግሩፕ አስተካክለን ነው፡፡ ከጥንትና በዓለም ኢንግአንሼንግ ብሄኮችን እና በልላዊትሸፌርስ አበባሺን መሠረቴን ይጠቀሙ፡፡ ይህ ግሩፕ ጽሁፍ የጊዜውን የስነ-ችግር ዜናዎችንና መረጃዎችን እንዴት ይጠቀሙ፡፡ በተጨማሪም እኛን ከእያንዳንዳችን መረጃዎችን ይፈልጋሉ፡፡

Ethio engineering Group

22 Nov, 03:43


በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ የህፃናት ማቆያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
"I can" በሚል የተሰየመው የህፃናት ማቆያ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አገልግሎት ሀላፊ ወ/ሮ ቅድስት አርአያ፣ የኢንዱስትሪው የቀድሞ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ያደኑ ተርፌሳ እና የአሁኑ የኢንዱስትሪው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ቀናቴ ሪቫን በመቁረጥ መርቀው ከፍተውታል።
የግሩፑ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አገልግሎት ሀላፊ ወ/ሮ ቅድስት አርአያ ኢንዱስትሪው  ካለው ሀብት ላይ በመቀነስ ይህን ማቆያ በመገንባት  ለሴት ሰራተኞች ምቹ የስራ ከባቢን መፍጠር ችሏል። ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሁሉም የኢንዱስትሪው ማህበረሰብ አስተዋፅኦ  ማድረግ እንዳለበትም ጠቁመዋል።በመጨረሻም ይህ ማቆያ እውን እንዲሆን ለተሳተፉ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።
"I can" የህፃናት መቆያ የመመገቢያ ፣መጫወቻ፣ መኝታ እንዲሁም መፀዳጃ ክፍል ያካተተ ነው።

Ethio engineering Group

20 Nov, 13:10


ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢኢግ) ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በ2017 አ.ም 1ኛ ሩብ አመት ያስመዘገበው ውጤት ተስፋ ሰጪ መሆኑን የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር አሰታወቀ፡፡
አስተዳደሩ የግሩፑን የ3 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ሲገመግም የገንዘብ ሚኒስቴር አባላትና የግሩፑ ስራ አመራር ቦርድ አባላት ተገኝተዋል፡፡
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባደረገው የሪፎርም ስራ የ2017 1ኛ ሩብ አመትን ጨምሮ  ባለፉት ሁለት አመታት ትርፍ ማስመዝገቡ ቀርቧል፡፡
የውጭ ምንዛሪ እጥረት የፈጠረው የግብአት ችግር  ለግሩፑ ፈተና ቢሆንም የውስጥ አቅምን አሟጦ በመጠቀም ግሩፑን ትርፋማ ማድረግ መቻሉም ተብራርቷል፡፡
ከግል ባንኮች ጋር በመቀራረብ የተሰራው ስራም ግሩፑ የተወሰኑ ግብአቶችን እንዲያገኝ አስችሎታል፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እንዳብራሩትም መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ በማስቀጠል ግሩፑ የተጣለበትን ተልእኮ እንዲወጣ ማድረግ ይገባዋል፡፡
ከግሩፑ ጋር እየሰሩ የሚገኙ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትም እያደረጉ ያሉትን ድጋፍ በማጠናከር የተሻለ አፈጻጸም እንዲመዘገብ  ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደርም አፈጻጸሙን መሰረት ያደረገ ግብረ መልስ አቅርቧል፡፡
በዚህም ግሩፑ ምቹ የስራ አከባቢን ከመፍጠር አኳያ ዋና መ/ቤቱን አድሶ ስራ መጀመሩ፤የሰው ሃይል አደረጃጀቱ ጾታን ያማከለ መሆኑ በጥንካሬነት የታዩ ናቸው፡፡
ትርፋማነቱን ለማሰቀጠል ምርቶች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅበትና አስተማማኝ እና ዘላቂ የፋይናንስ ምንጭ ሊኖረው እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡
የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ም/ል ዋና ዳይሬክተርና የስርአት ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ዝናቡ ይርጋ በማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የህዝብ ተቋም የሆነውን ግሩፑን ተወዳዳሪና ትርፋማ ለማድረግ ርብርብ  ማድረግ ይገባል፡፡
አሁን ላይ ተስፋ ሰጪ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝም በመግለጽ ውስጣዊና ውጫዊ ተጽእኖዎችን በመቋቋም  በቀጣይ የተሻለ ደረጃ ላይ ማድረስ ይገባል ብለዋል፡፡

Ethio engineering Group

16 Nov, 06:01


ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከኤስ ጂ አዉቶሞቲቭ ግሩፕና ከሚስተር ሉታ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰሩ ተሸከርካሪዎችን ለማስፋፋትና የሃይል አቅርቦቱ ተደራሽነት ላይ በጋራ ለመስራት ነው፡፡
የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመገጣጠም እና በቴክኒክ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስራት ያለመ ስምምነት ነው፡፡
የቻርጂንግ ፋሲሊቲዎች ግንባታን ያካተተው የመግባቢያ ስምምነቱ ገበያ ላይም አብሮ ለመስራት ያተኩራል፡፡
በዚህም ገበያውን እስከ ምስራቅ አፍሪካ ተደራሽ ያደርጋል ተብሏል፡፡