አቤል ተፈራ በላይ @abelltefera Channel on Telegram

አቤል ተፈራ በላይ

@abelltefera


አቤል ተፈራ በላይ (Amharic)

አቤል ተፈራ በላይ የቴሌግራም መረጃ ክፍል ነው አፕልኬሽን ላይ። ይህ አፕልኬሽኑ የስራ መከላከያ ለሚሆን የተለያዩ ፈሳሽ አለዎት። አቤል ተፈራ በላይ የቴሌግራም መረጃ ክፍልዎ እንዲሆን የገንዘብና ማህበረሰብን እያሻሹ ይፈልጋል። አቤል ተፈራ በላይ ከላይ እና ከተጠናቀቀው ገጽ ከመምጣቱ ጋር ሲሆኑ፣ እናም ማህበረሰብን ማሻሻት እንደሚችል በስነ-ምልክት መሰረት ነው።

አቤል ተፈራ በላይ

19 Jan, 02:21


ሀገር የሰነበተችው እንዲኽ ነው ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ዛሬ በከተራ በዓል ያስተማሩት ድንቅ ትምህርት ጥር ...
https://youtube.com/watch?v=5xxRnNW3RoU&si=CO2Q6kqbwGkovy1u

አቤል ተፈራ በላይ

07 Jan, 06:56


እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል ይሁንላችሁ።

አቤል ተፈራ በላይ

05 Jan, 03:48


የኃጢአት ሌላኛው ገጽታ

===በአቤል ተፈራ===


https://t.me/Abelltefera

አቤል ተፈራ በላይ

29 Dec, 16:06


https://youtu.be/67m99T5ftS0

አቤል ተፈራ በላይ

24 Dec, 15:29


https://youtu.be/wX_Nw5gmk8o?feature=shared

አቤል ተፈራ በላይ

30 Nov, 15:37


https://youtu.be/sGvz5C0cVNg?si=lZlwURJVHrwZWMwn

አቤል ተፈራ በላይ

29 Nov, 03:33


https://youtu.be/5iixdV9j9Mg?si=PlBRtxF_RMca6wea

አቤል ተፈራ በላይ

24 Nov, 16:35


https://youtu.be/ON2cw58OdqA?si=o24mco0YxBqKfdxO

አቤል ተፈራ በላይ

19 Nov, 07:16


ራሳችንን እንሁን

አንጀሊና ጂሊን ለመምሰል ሞከረች ወደዚህ ተቀይራለች 🙄🙄 ይህች ልጅ sahar tabar የምትባል ሞዴል ኢራናዊት ናት።

ምን ዋጋ አለው እንዲሉ ፈጣሪ ውብ አድርጎ ቢፈጥራትም በጣም ውብ መሆን ፈለገችና በጣም የምታደንቃትን Angelina Jolie መምሰል ፈለገች።

ወደ አንድ ፕላስቲክ ሰርጀሪ ወደሚሰራ ሆስፒታል ሄደችና ሚሊዮን ክፍያዋን ከፍላ አንጀሊና ጆሊን አስመስላችሁ ስሩኝ አለች። ፕላስቲክ ሰርጀሪው ረጅም ጊዜ ወስዶ ተሰራላት።

ለውጡ የሚከተለውን መስሏል !!🙄

ፈጣሪ ሁላችንንም የፈጠረን ራሳችንን እንድንሆን አድርጎ ነው! ውበታችን ጎልቶ የሚወጣውም ሌላን ሰው ስንመስል ሳይሆን ራሳችንን ስንሆን ብቻ ነው!

አቤል ተፈራ በላይ

16 Nov, 04:24


https://youtu.be/xrA_AJiAe6c?si=CkpCCDbyjT5n8wsu

አቤል ተፈራ በላይ

14 Nov, 07:46


ላጤነት በኦርቶዶክስ እይታ

   በአቤል ተፈራ በላይ

https://t.me/Abelltefera

አቤል ተፈራ በላይ

09 Nov, 06:20


ሥራ ሰለሌለኝ እጮኛዬን ላጣት ነው

በአቤል ተፈራ በላይ

https://t.me/Abelltefera

አቤል ተፈራ በላይ

05 Nov, 18:50


https://youtu.be/OpALFifrLD4?si=ymHNQ-IfXDe9fIMe

አቤል ተፈራ በላይ

03 Nov, 07:29


የተወደዳችሁ እህቶች እና ወንድሞች ሁለተኛ ዙር የቅዱሳት መጽሐፍት እቁብ ልንጀምር ዝግጅታችንን አጠናቀናል። እቁቡ ወርሃዊ ሲሆን የብሩ መጠን 1500 ይሆናል።

እቁቡ በስደት እየኖሩ መጽሐፍት ለመግዛት እየፈለኩ ላልቻሉ እህት ወንድሞች ጥሩ አጋጣሚ ነው። የመረጡትን መጽሐፍ ከተገዛላቸው በኋላ ወደ ቤተሰባቸው ወይም መጽሐፉን እንዲቀበልላቸው ወደ ፈለጉት ሰው ማድረስንም ይጨምራል።

ለመመዝገብ የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩኝ። 👉 @Abellteferaaa

አቤል ተፈራ በላይ

01 Nov, 17:37


https://youtu.be/0PyPxHBStiw

አቤል ተፈራ በላይ

29 Oct, 09:53


በዚህ መዳፍ መሻከር ውስጥ ብዙ የለሰለሱ እጆች አሉ። ዛሬን ለእኛ ለማበጀት ሲሉ ትላንታቸውን መሥዋዕት ላደረጉ ሁሉ ክብር ይሁን…!!! የእነዚህን እጆች ውለታ አንርሳ

አቤል ተፈራ በላይ

24 Oct, 22:25


https://youtu.be/4RRo6cIM960?si=ni5iTNpTHYXaBHX6

አቤል ተፈራ በላይ

22 Oct, 04:43


https://youtu.be/28lG5_8T3FI?si=ICJ8uEyN_V_rIMic

አቤል ተፈራ በላይ

21 Oct, 10:52


በሽታ ከሰው ወደ ሰው እንደሚጋባ ሁሉ ጤንነትም ከሰው ወደ ሰው ይጋባል ጤናማ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር መዋል ጤናማ ያደርጋል!

መጽሐፍም እንዲህ ይላል “ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።” መዝሙር 18፥25-26

አብራችሁ የምትውሏቸው ሰዎች በእናተ ሕይወት ላይ በጎም ክፉም ተጽኖ አላቸው። ማንነታችሁ የሚወሰነው አብራችሁ በምትውሏቸው ሰዎች ነውና አብሯችሁ የሚውሉ ሰዎችን ምረጡ ። መልካም ነገር እንኳን ቢኖራችሁ “አትሳቱ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል።” 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥33 እና ተጠንቀቁ

ቴሌ ግራማችንን 👉 https://t.me/Abelltefera

አቤል ተፈራ በላይ

19 Oct, 05:37


« ይህ የአባቶቻችን የሐዋርያት ትእዛዝ ነው። ሰው በልቦናው ቂምንና በቀልን ቅንዓትንና ጠብን በባልንጀራው ላይ በማንም ላይ ቢሆን አይያዝ። »  መጽሐፈ ቅዳሴ

አቤል ተፈራ በላይ

18 Oct, 15:58


የተከበራችው ወንድሞቼና እኅቶቼ እንደምን አላችሁ? በወልድያ ከተማ ለምትኖሩ ኦርቶዶክሳዊያን ለጥቅምት 10/2017 ዓ.ም ማለትም እሁድ ከቀኑ 8:30 አዳጎ ፀደይ ባንክ ላይ ካለው አዳራሽ ለብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ የጽዋ መርሐ ግብር እንድትገኙ ጠርተናችኋል እያንዳንዳችሁ ቢያንስ ሁለት ሁለት ሰዎችን በመጋበዝ ክርስቲያናዊ አደራችሁን እንድትወጡ ስል ጥሪ አስተላልፋለው። አደራ እንዳትረሱ!

አቤል ተፈራ በላይ

16 Oct, 10:32


አባ መፍቀሬ ሰብእ ማረፋቸውን ስሰማ በጣም ነው ያዘንኩት እርሳቸውን ማጣት ከባድ ነው።

አቤል ተፈራ በላይ

16 Oct, 03:31


የባንክ accountsሽ ውስጥ 10ሺ እንኳን ብር ሳይኖር መኪና የሌለው ወንድ አላገባም አትበይ የምታገቢው ድህነትሽን ለማራገፍ አይደለም። መጀመሪያ ራስሽን ቻይ! ይሄ የጥገኝነትሽ መንፈስ ብር ያለው አውሬ ጋር ሳይጥልሽ አይቀርም እና ተጠንቀቂ።

አቤል ተፈራ በላይ

14 Oct, 13:00


በጣም ይገርማል። ክብደታችንን ለመቀነስ የተጨነቅነውን ያህል ኃጢአታችንን ለመቀነስ እና ለማስወገድ ተጨንቀን አናውቅም።

አቤል ተፈራ በላይ

11 Oct, 13:15


እውነተኛ ጓደኛ 😍

ያንተ ጓደኛ ይሄ ነው?! ጦርነቱ ጋብ ካለ በኋላ አንድ ወታደር በውጊያ ሜዳ የወደቀውን ጓደኛውን ለመፈለግ አለቃውን ያስፈቅዳል። አለቃውም መሞቱ ለማያጠራጥር ሰው ብለህ ሕይወትህን አደጋ ላይ እንድትጥል አልፈቅድልህም በማለት ፍቃድ ይነፍገዋል፡፡

ወታደሩ ግን አሻፈረኝ ብሎ ፍለጋውን ይቀጥላል፡፡ ከፍለጋ በኋላ እሱም ሞት አፋፍ ላይ ባደረሰው ሁኔታ ቆስሎ የሞተ ጓደኛውን አስክሬን ተሸክሞ ይመጣል። አለቃውም ይሞታል ብዬህ አልነበረም? ለሚሞት ሰው ብለህ ይህን ሁሉ መሥዋዕትነት መክፈል ነበረብህ፤' በማለት ይወቅሰዋል፡፡

ወታደሩ ግን በሥራው ደስተኛ ነበር ፡፡ አለቃዬ ይህኮ ምንም ማለት አይደለም ጓደኛዬ በሞት አፋፍ ላይ ደርሸበት ያለኝን ብነግርህ ትረዳኝ ነበር። አለቃውም 'ምን አለህ?' ሲለው ወታደሩም እንደምትመጣ እርግጠኛ ነበርኩ

እውነተኛ ጓደኛ ማለት በችግር ውስጥ ሁነህ ምንም አይነት መከራ እና ፈተናዎች ቢያጋጥሙት እንደ ሚመጣልህ እርግጠኛ የምትሆንበት ሰው ነው። መሞትንህ ለሚነግሩት ሰዎች ካላየሁ አላምን ምን አልባት በሕይወት ይኖር ይሆናል የእኔ እርዳታ ያስፈልገው ይሆናል በማለት በነፍሱ ተወራርዶ በሬሳዎች መካከል የሚፈልግህ ድንቅ እና ውድ ሰው ነው።

ሁሉም ሰው ሲሸሽህ እሱ ግን የሚፈልግህ ነው ! ሁሉም ሰው በውድቀትህ ሲሳለቅ እርሱ ግን በቁስሎችህ የሚታመም እና የሚያለቅስ ነው። እውነተኛ ጓደኛ በቃ እንደዚህ ነው።

አቤል ተፈራ በላይ

10 Oct, 10:43


እግዚአብሔር ቢረዳኝ ጥሩ ክርስቲያን ብሆን እመኛለሁ። ከዚህ ውጭ በሕይወቴ ባሳካሁት የምለው ብዙም ምኞት የለኝም። ብዙ ምኞት የለኝም አልኩ እንጂ ምንም ምኞት የለኝም አላልኩም። በዚህም ምድር ሁለት ምኞቶቼ ቢሳኩልኝ ደስ ይለኛል።

1) በፎቶው ላይ በምታዩት ሞተር በብርድ በዝናብ ኢትዮጵያ ከዳር እስከ ዳር መጎብኘት እፈልጋለሁ። ታዳጊ ልጅ ያለሁ ድንግል ውበት የሚል የፍቅረ ማርቆስን ደስታ የልቦለድ መጽሐፍ ስላነበብኩ ነው መሰል ሐመሮችን በተለይ ማየት የተወሰነ ጊዜ ከእነርሱ ጋር ማሳለፍ ምኞቴ ነው።

2) ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እስከ ኃጢአቶቼም ቢሆን በውስጧ እንድኖር ከአባ ገብረ መድኅን ውጭ የአቡነ ሺኖዳ መጻሕፍት በብዙ እረድተውኛል። በዚህ የተነሳ የግብጽ ገዳማትን ማየት የተወሰኑ አመታትን በውስጣቸው መኖር ተዘዋውሬ ገዳማቸውን አገልግሎታቸውን ማየት እመኛለሁ።

አቤል ተፈራ በላይ

09 Oct, 15:12


#መልሰኝ 😭😭😭

ጌታ ሆይ እንድትወደኝ እለምንሃለሁ ብዬ በፍጹም አልጠይቅህም እንደ ምታፈቅረኝ እስከ ኃጢአቴ እንደ ተሸከምከኝ ጠንቅቄ አውቃለሁና። አባቴ ሆይ እኔ የምለምንህ አንተ መፍቀር የሚችል ልብ እንድታድለኝ ብቻ ነው። ጌታ ሆይ አንተን መውደድ ልቤን በፍቅርህ መሙላት እፈልጋለሁ። ከንቱ ነገሮች የሞሉትን ልቤን አጽድተህ የፍቅርህ ዙፋን አንተን በመውደድ እንድታስጌጠው እማጸንሃለሁ።

ጌታ ሆይ ለአንተ ምኑን እደብቅሃለሁ ከአንተ ይልቅ የምወዳቸው ብዙ ኃጢአቶች አሉ። ሕይወቴን የተቆጣጠረው ዓለማዊነት በእርኩሰት ፍቅር ጥሎኛል። ኃጢአት ሰላሜን ቢነሳኝም እርሱን ከመስራት ግን ወደ ኋላ ብዬ አላውቅም። በአመጽ መንገድ እርቄ ከመሄዴ የተነሳ በነውሬ የማጌጥ ደንዳና የዲያብሎስ ባሪያ ሁኛለሁ። ኃጢአቴ እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደ ምድር አሸዋ የበዛብኝ እኔ እጅጉን እፈራለሁ። በደሌን ባሰብኩ ጊዜ ልቦናዬ ይደነግጥብኛል። ወደ አንተም እማጸናለሁ። ተንበርክኬም እለምንሃለሁ ። የነጻነት ሕይወት ወደ ሚሰጥ ወደ ፍቅርህ ሙላት ከፍታ አውጣኝ። በኃጢአት ጨለማ የጠቆረ ልቤን በፍቅርህ ብርሃን አስጌጠኝ።

ጌታ ኢየሱስ ሆይ እንካ እጄን ያዘኝ እኔ አቅም አጥቻለሁ በራሴ ጉልበት ከኃጢአት መውጣት አልችልም እባክህን ጎትተኝ። ለዓለማዊነት የተሰነፈውን እኔነቴን ፈውስ። ወደ ከፍታ ልወጣባቸው የተሰጡኝን ግን በኃጢአት የተሰበሩ ክንፎቼን ጠግን። ለምን እንደወደድከኝ በእድሜዬ ላይ ይችን ቀን ለምን እንደ ጨመርከኝ ሳስበው በጣም እገረማለሁ ይመለሳል ብለህ በትዕግሥት እኔን መጠበቅን ሳስብ እደነቃለሁ። ፍቅርህ ለእኔ ያለህ ውድ ከአእምሮ በላይ ነው። ለፍቅርህ የምመልሰው ጥቂት መልካም ምግባር የሌለኝ ከንቱ መሆኔን ሳስብ በራሴ እናደዳለሁ።

ጌታ ሆይ እባክህ ተመለስ አትበለኝ ። እኔ በራሴ ከኃጢአት መመለስ የምችልበት አቅም የለኝምና ። በኃጢአት የደከምኩ ልምዝምዝ መሆኔን አንተ ታውቀለህ። ግን እንዲህ እልሃለሁ “ አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና መልሰኝ እኔም እመለሳለሁ።” ኤርምያስ 31፥18

ቴሌ ግራም https://t.me/Abelltefera

አቤል ተፈራ በላይ

09 Oct, 06:46


#ቅርንጫፍ_ጓደኞች

በሕይወት ውስጥ ሦስት አይነት ጓደኞች ይኖራሉ። እነርሱም 1) የቅጠል ጓደኞች 2) የቅርንጫፍ ጓደኞች 3) ሥር የሰደዱ ጓደኞች ናቸው። ሰለ ሦስቱም የጓደኞች አይነቶች መስማት ትፈልጋለህ እንግዳውስ ተከተለኝ።

#ቅርንጫፍ_ጓደኞች

ትናት ሰለቅጠል ጓደኞች እያወራን ነበር። ዛሬ ደግሞ እስቲ ቅርንጫፍ ጓደኞች በተመለከ እናውራ። ቅርንጫፍ ቅጠልን የሚሸከም የዛፍ አካል ነው። የሚሸከም ነገር ደግሞ ሽክሙ በራሱ ጠንካራ ያደርገዋል። ቅርንጫፍ ጓደኞችም ጠንካሮች ናቸው። ደካማ ጎንህን በፀባይህ ላይ ያለውን ጉድለት ሁሉ ሊሸከሙልህ ይችላሉ። ግን እነርሱ ቅርንጫፍ እንጂ ግንድ አይደሉምና የማይችሉት ሸክም ይኖራል።  ከክፋት ሳይሆን ከጥንካሬ ጉድለት የተነሳ አንዳንድ ከባድ ሸክሞች ሊሰብራቸው ይችላል።

እነዚህ ጓደኞች በጥበብ ልትይዛቸው በማስተዋልም አብርሃቸው ልትኖር ይገባል። እንዳትሰብራቸው መራራት አትሁንባቸው። ከባድ ፀባይህን መሸከም አይችሉም እና ከሚቻላቸው በላይ ሸካራ ፀባይህን በእነርሱ ፊት መቆጣጠርህን እንዳትረሳ ብዬ አሳስብሃለሁ። ሁላችንም የራሳችን ደካማ ጎን አለብን እና ተሳዝነን መኖር ይጠበቅብናል። አውቀው የሚያጠፉትን እንጂ ተሳስተው የሚያጠፉትን በይቅርታ ልብ መቀበል ያስፈልጋል።

ጓደኝነትን በተመለከ እስቲ ጥቂት ጥያቄዎች ልጠይቃችሁ።

1) እውነተኛ የምትሉት ጓደኛ አለኝ ብላችሁ ታስባላችሁ ?

2) የእውነተኛ ጓደኛ መለኪያ መስፈርትስ ምንድን ነው ?

3) እናተስ የእውነተኛ ጓደኛ መለኪያ መስፈርትስ አሟላለሁ ብላችሁ ታስባላችሁ ?

ቴሌ ግራም 👉 https://t.me/Abelltefera

አቤል ተፈራ በላይ

08 Oct, 06:12


#የቅጠል_ጓደኞች

በሕይወት ውስጥ ሦስት አይነት ጓደኞች ይኖራሉ። እነርሱም 1) የቅጠል ጓደኞች 2) የቅርንጫፍ ጓደኞች 3) ሥር የሰደዱ ጓደኞች ናቸው። ሰለ ሦስቱም የጓደኞች አይነቶች መስማት ትፈልጋለህ እንግዳውስ ተከተለኝ።

#የቅጠል_ጓደኞች

እነዚህ ሰዎች ወቅት ጠብቀው ወደ ሕይወትህ የሚመጡ ሰዎች ናቸው፡፡ ወቅት እንዳመጣቸው ወቅት ነው ከአጠገብህ የሚያጠፋቸው። እንደዚህ ጓደኞች ደካማ ስለሆኑ ልትደገፍባቸው አትችልም፡፡ ምን አልባት ደካማ መሆናቸውን ሳታውቅ ተደግፈሃቸው ከሆነ እንደ ሸንበቆ ሰለሆኑ በጣም ይጎዱሃል። የሚመጡት የሚፈልጉትን ለመውሰድ ሲሆን ነፋስ በመጣ ወቅት ይሸሻሉ። እነዚህ ሰዎች የሚወዱህ ሀብታም ጠንካራ ተፈላጊ በሆንክበት ጊዜ ብቻ ነው። መከራ የስብእና ስብራት ሐዘን ችግር በገጠመህ ወቅት ወይም ሕይወትህ የሚያመሰቃቅል ነፋስ ባገኘህ ጊዜ እነዚህ ቅጠሎችን በፍጹም አታገኛቸውም ።

ቴሌ ግራም 👉 https://t.me/Abelltefera

አቤል ተፈራ በላይ

16 Sep, 10:56


በዚህ ሳምንት ይጠብቁን!!
የክርስቶስ መምጫው ቀርቦ ይሆን?
👇እስከዛው ቻናላችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ! !👇
https://youtube.com/@abelteferabelay?si=0pF6eYW3xalHM3lp

አቤል ተፈራ በላይ

08 Sep, 09:16


ሰላም ተወዳጆች በዚህ ግሩፕ የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህር የሆኑትና አሁን በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ እየተማሩ የሚገኙት
መጋቤ ሐዲስ ኢሳይያስ ሐብቴ
➛ የባህረ ሃሳብ ትምህርት
➛ ወቅቱን መሠረት ያደረጉ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
➛ የቅዱሳን አባቶች እና እናቶች ታሪክ
➛ የንጽጽር ትምህርቶች
➛ ከግሩፑ አባላት ለሚመጡ ማንኛውም ሃይማኖታዊ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠትን ጨምሮ ሌሎች ተከታታይ ትምህርቶችን ማስተማር ይጀምራሉና ሌሎች የዚህ የቴሌግራም ግሩፕ አባል እንዲሆኑ በመጋበዝ የዕድሉ ተጠቃሚዎች ታደርጉልን ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
https://t.me/+UaVD3cV51dMT-HQr

https://t.me/+UaVD3cV51dMT-HQr

አቤል ተፈራ በላይ

05 Sep, 02:24


https://youtu.be/vf4fa6Okigo?si=RyF-KchtR2bLiMXK

አቤል ተፈራ በላይ

02 Sep, 19:23


አስደሳች ዜና ለኦርቶዶክሳዊያን

ከመስከረም ጀምሮ መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ አስባችሁ ከየት ልጀምር ብላችሁ ግራ ለገባችሁ ሰዎች እና የመጽሐፍ ቅዱስ የዓመት የንባብ እቅድ ለመውጣት ፈልጋችሁ ያልቻላችሁ ሰዎች በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀ የጠዋት እና ማታ የመጽሐፍ ቅዱስ የንባብ እቅድ ከቤተ ክርስቲያን በዓላት ጋር በማስማማት የወጣ በቴሌ ግራም 👉 https://t.me/Abelltefera PDF አስቀምጨላችኋለሁ አውርዳችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።