መምህር አካለወልድ @memiheraka Channel on Telegram

መምህር አካለወልድ

@memiheraka


የመምህር አካለወልድ ONLINE

መምህር አካለወልድ (Amharic)

ስለ ጥያቄዎች እና መረጃዎች የመምህር አካለወልድ ONLINE ቻናሎችን ስኬት ከዚህ ጋር ላይ በአማርኛ ለመሆን መምህር አካለወልድ ጠቃሚ መሆኑን እና መዝገበ ጉዳዮችን በነጻ ወስኖ ሆኖ ነው። መምህር አካለወልድ የጠቃሚ ቻናል እና መረጃዎችን ከሰኞ እስከ ቅዳሜ የተለያነ በገጽ ይቀላቀሉ። የመምህር አካለወልድ ቻናል ለመመልከት የምንከፈለውን መርሃ ግብር ቻናል ቅርብ ከሆነ አጭጭር ፕሮም ፉበርክ እገዛና እየቀረበ እንደሆነ ይመልሳል።

መምህር አካለወልድ

20 Nov, 10:06


Dear Andarge please share this Unit 1 Grade 10 IT work sheet for my students on "Memihir Akalewold" group. Berhanu Tesfaye https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfHQE20VEpEAXdJEsMUKdsHfp1n3fjmZZBcuBo3b_fD95Wuaw/viewform?usp=sharing

መምህር አካለወልድ

18 Nov, 17:02


በደሴ ከተማ አስተዳደር በትምህርት ቤቶች ከ16 ሽ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የምገባ መርሀ ግብር ተጀመረ።

ደሴ- ህዳር 9/2017/ደሴ ፋና/በከተማ አስተዳደሩ በሚገኘው መርሀ ጥበብ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ምገባውን ያስጀመሩት የደሴ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ፍቅር አበበ እንደገለፁት በ2016 ዓ.ም 7 ሺህ ለሚሆኑ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት ተሰጥቷል።

ዘንድሮ ከ16 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት ለመስጠት መታቀዱንም ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት 8 ሺህ 800 ተማሪዎችን  በከተማዋ ባሉ 27 ትምህርት ቤቶች የምግባ አገልግሎት መሰጠት ተጀምሯል ያሉት አቶ ፍቅር በርካታ ትምህርት ቤቶች ላይ የወተትና ዳቦ ምገባ ሲካሔድ በሶስት ትምህርት ቤቶች ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ ምግቦችን ለተማሪዎች የማቅረብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የምገባ ስርአቱ መዋቅር አለመኖር እና በትምህርት መምሪያው አማካኝነት ብቻ የሚከወን መሆኑ እንዲሁም የበጀት እጥረት ችግሮች መሆናቸው ተነስቷል።

በዚህም ግዜያዊ የሆኑ አደረጃጀቶችን ፈጥሮ መምህራን እና ተማሪዎችን በማሳተፍ እየተሰራ ሲሆን በጀትን በተመለከተ ከተማ አስተዳደሩና የከተማዋን ባለሀብቶች በማስተባበር እየተሰራ ነው ብለዋል።

የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሽመልስ ጌታቸው በበኩላቸው መንግስት ሰው ተኮር ስራዎችን እየሰራ በመሆኑ በተለይ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቷል።

በከተማ አስተዳደሩ ባሉ ትምህርት ቤቶች የሚከወነውን የምገባ ፕሮግራም ለመደገፍ ማህበረሰቡን፣ ባለሀብቱን እና የራሱን አቅም ይጠቀማል ብለዋል።

ተማሪዎች ጥራት ያለው ምግብ እስከ አመቱ መጨረሻ ድረስ እንዲመገቡ መሰራት ያለባቸውን ስራዎች እንሰራለን ያሉት አቶ ሽመልስ ህዝቡ በከተማዋ ልማት ላይ በስፋት እንደተሳተፈ ሁሉ ለተማሪዎች ምገባ ለሚያስፈልጉ ነገሮች ወደኋላ እንደማይል አንስተዋል።

ለምገባ ማስጀመሪያው 25 ሚሊየን ብር የተመደበ ሲሆን በቀጣይ ተጨማሪ በጀት ተይዞ ተጠናክሮ ይሰራል ተብሏል።

       ስንታየሁ አራጌ

መምህር አካለወልድ

18 Nov, 09:41


ቀን 9/03/2017 ዓ.ም
ለልዩ ክፍል ተማሪዎች
📢📢📢📢📢📢📢📢
ከሰኞ ገበያ እና አራዳ የምትመላሉ የልዩ ክፍል ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ስለተጀመረ ከህዳር 10/03/2017 ዓ.ም ሰኞ ገበያ 1:120 እንድሁም አራዳ ያላችሁ ፒያሳ ላይ 1:30 እንድትገኙ እናሳውቃለን ።
ለበለጠ 0914736342 በመደወል አረጋግጡ።
ትምህርት ቤቱ!!

መምህር አካለወልድ

18 Nov, 03:12


ልክ የዛሬ 104 ዓመት በዚህች እለት ኅዳር 9 ቀን
(1912) ታላቁ #ኢትዮጵያዊ ምሑር: የሊቆች ሁሉ ሊቅ: ደግና ሐዋርያዊ አባት *#የኔታ #አካለ #ወልድ ዐርፈዋል::

=>ሊቃውንት #የቀለም_ቀንድ ሲሏቸው
#አፄ #ቴዎድሮስ ደግሞ:-
"ይማሯል እንደ አካልዬ::
ይዋጉዋል እንደ ገብርየ::" ብለው ፎክረውላቸዋል::

¤የቦሩ ሜዳው ኮከብ ይልቁኑ ለወሎ ሕዝብ ትልቅ አባት ነበሩ::

<<< የሊቁ አካለ ወልድ በረከታቸው ይደርብን::

መምህር አካለወልድ

15 Nov, 17:05


9ኛው አመታዊ የሳይንስ እና ምህንድስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር ተስፋ ሰጭ የፈጠራ ባለሙያዎችን ለማግኘት እድል የፈጠረ እንደነበር ተገለጸ
ህዳር 6/2017 ዓ.ም
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ከህዳር 3-6/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሲካሄድ የቆየው 9ኛው ሃገር አቀፍ የሳይንስና ምህንድስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር በተማሪዎችና መምህራን የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች ለእይታ የቀረቡበት ነበር፡፡ ለተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ውድድር አሸናፊ የሆኑ የፈጠራ ስራዎችን እና ማዕከላትን በመሸለም ተጠናቋል፡፡
ዶ/ር ቀናቱ አንጋሳ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አሳታፊነት ዳይሬክተር ይህ ውድድር በዩኒቨርሲቲው ለአራተኛ ጊዜ የተዘጋጀ መሆኑን በመጥቀስ ይህም ዩኒቨርሲቲው ለሳይንስ፤ቴክኖሎጂ፤ምህንድስና እና ሂሳብ ትምህርት ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም ይህን የመሰለ የሳይንስና ምህንድስና ውድድር መደረጉ ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎችን ለማግኘት መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አጋር አካላት በዚህ ዘርፍ ላይ ተባብረው መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ላይ በተለያዩ ዘርፎች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተወዳዳሪዎች የማበረታቻ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል ፡፡
ይህን ውድድር በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለአበረከቱ ተቋማት አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፤ስቴም ፓወር፣ ስቴም ሲነርጂ፣ጃይካ እና ትምህርት ለኢትዮጵያ የተሰኙ አጋር አካላት ለአደረጉት አስተዋጽኦ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡