ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት @meseretemedia Channel on Telegram

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

@meseretemedia


ይህ የሀገረ ማርያም ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሠረተ ተዋሕዶ ሰንበት ት/ት ቤት አባላት መማሪያና መልእክት መጋሪያ ብቻ ይሆን ዘንድ የተዘጋጀ አውታር ነው።

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት (Amharic)

የሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የተዋሕዶ ስራዎችን ለማግኘት ለማስታወቂያ እና ለማስተብረያ ማግኘት ይችላሉ። ይህ የሀገረ ማርያም ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሠረተ ተዋሕዶ ሰንበት ት/ት ቤት አባላት የታዘጋገ ስራ ነው። ይህ በትግራይ ህዝባዊ ቤተሰብ እና በመስከረም ህዝባዊ ቤተሰብ ከሚከተሉ እና ከሚሆንኩበት የቤተ ክርስቲያን በተመለከተ በመንግስት መንፈሳዊ ተከታይ ስማቸውን ስላዘጋ። ትምህርት ለቤተ ክርስቲያኖች እና በሩቅነህም እርምጃ እንደሌሎች ህክምናዊ ለሚያስተምር መልእክቱ አጋጥሞ እንኳት አበራርጅረቃል።

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

02 Dec, 14:40


በአገልግሎታችሁ ምንም ፈተና ካልገጠመችሁ ሰይጣን ንቋቸዋል ማለት ነው።
ኮሽ ማለት ከጀመረ ግን አገልግሎትህ ሰይጣንን አደጋ ላይ እየጣለ ነው ማለት ነው።


ዲን ሄኖክ ኃይለ

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

01 Dec, 18:46


በኮርሱ ዙርያ ያላችሁን ሃሳብ አስተያየት እና መልእክት በዚህ
👉
@Ye_tewahido አድርሱን

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

01 Dec, 17:57



መች ተለወጣችሁ

ምናልባት አንዳዴ በትምህርት እንዳልተለወጥን አድርጎን ለሚያስቡን ሰዎች እነርሱ እንደሚሉት ባንለወጥ እንኳን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቂ እንዲህ ይመክረናል
"አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤
💠ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር።
💠ላትስተካከል ትችላለህ፤
💠ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር፤
💠ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን 💠ባትኾን ራስህን ለመውቀስ
💠የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ፤
💠ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፤
💠ስለዚህ ተማር ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለና፤
💠ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፤
አንድ ቀን ወደ ንስሐም ትመራሃለች"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ







የሀገረ ማርያም የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት ሚዲያ(መሠረተ ሚዲያ )

                  ⬇️

➡️      መሰረተ ሚዲያ   ⬅️

                  ⬆️

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️
⤵️ ⬇️
https://t.me/Meseretemedia

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

01 Dec, 17:38


ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት pinned «በኮርሱ ዙርያ ያላችሁን ሃሳብ አስተያየት እና መልእክት በዚህ 👉@Ye_tewahido አድርሱን»

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

01 Dec, 17:18


በኮርሱ ዙርያ ያላችሁን ሃሳብ አስተያየት እና መልእክት በዚህ
👉
@Ye_tewahido አድርሱን

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

01 Dec, 14:48


ለኮርስ ተማሪዎች

ዛሬ በአጋጣሚ በተፈጠረው መርሐ ግብር መደራረብ ኮርሱ በመስተጓጐሉ ይቅርታ እንጠየቃለን ።
ለቀጣይ ቀን ኮርስ መርሃ ግብር ያለውን ሁኔታ አስተካክለን የሚናሳውቃችሁ ሲሆን እስከዛ በትዕግሥት እንድትጠብቁን እናሳስባለን ።

ከትምህርት ክፍል

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

01 Dec, 07:06


ዛሬ 9 ሰዓት ትምህርትም ፈተናም ስላላችሁ የ1ኛ እና 2ኛ ዓመት ኮርስ ተማሪዎች በጊዜ እንድትገኙ ።

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

29 Nov, 06:19


እንኳን ለእናታችን ጽዮን ማርያም ታላቅ አመታዊ ክብረ በዓል አደረሠን #ኅዳር 21 #ጽዮን #ማርያም
****

#በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ መሠረታቸው ስትሆን ነች።  #አክሱም በሕገ ልቡና የጸናች፣ ሕገ ኦሪትን የፈጸመች፣ በሕገ ወንጌል ያመነች ናት፡፡ ለዚህም ነው «ሕግ ይወጽእ እምጽዮን፤ ከጽዮን ሕግ ይወጣል»
***በዓለ ልደትን በላሊበላ፣ ጥምቀትን በጎንደር፣ ኅዳር ጽዮንን በአክሱም ጽዮን ሲያከብሩት ልዩ የሆነ ሥርዓት ስለሚቀርብባቸው ምእመናን መንፈሳዊ ደስታ ይሰማቸዋል፡፡

****ኅዳር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል ነው ብለን #በተለየ መልኩ  #የምናከብርበት #ምክንያት፡-

**
1. በ
ብሉይ ኪዳን ታቦተ ጽዮን የፈጸመችውን ልዩ ልዩ ገቢረ ተአምራትን ለማሰብ
2. ቀዳማዊ ምኒልክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛርያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበት ዕለት በመሆኑ
3. በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ ምሕረት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ይሁን ተብሎ ዐዋጅ የታወጀበት
4. ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ምሳሌ ራእይ ያየበት
5. ነቢዩ ሕዝቅኤል በተቆለፈች ቤተ መቅደስ
6. ዕዝራ በቅድስት ሀገር ምሳሌ ራእይ ያየበት
እና የመሳሰሉት አበይት ምክንያቶቻችንን መሰረት በማድረግ በመላ ሀገራችን ህዳር 21 ቀን በድምቀት ይከበራል።

ለመቀላቀል

✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ

:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮

    የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን 
              ➡️      መሰረተ ሚዲያ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
     ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ

👇👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
https://t.me/Meseretemedia

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

28 Nov, 17:57


ሰንበት ትምህርት ቤት

ክፍል 2

ህዝቤ ዕውቀት በማጣት ጠፍቷል” (ሆሴ 4፥6) የተባለው በእኛ ላይ እንዳይፈጸም ዕድሜያችን በሚፈቅድልን ሁሉ ሃይማኖታዊ ዕውቀትን እንድንማር ቤተ ክርስቲያን በቅዱሳን ጸሎት በእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ሰንበት ት/ቤትን አቋቋመች።
✣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ልጆቿ ጽድቅን ይማሩ ዘንድ በሰንበት ት/ቤት አሰባስባ ቃለ እግዚአብሔርን አውቀው፣ ባሕርየ እግዚአብሔርን ተረድተው እንዲያመልኩ፣ ሕጉን ጠብቀው፣ በሃይማኖት፣ በምግባርና በትሩፋት ፀንተው አምላካቸውን መስለው እንዲኖሩ የእርሱ የሆነችውን መንግስተ እግዚአብሔርን እንዲወርሱ በብሉይ ከአምላኳ የተቀበለችውን ሕግጋተ እግዚአብሔርን አስተምራ በሐዲስ ኪዳንም በ40 እና በ80 ቀን እያጠመቀች ለምዕመናን እንደ እድሜያቸው እና እንደ አዕምዕሮ ብስለታቸው ቃለ እግዚአብሔርን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል ታስተላልፋለች።

❖ በስብከት፣ በዝማሬ፣ በቅዳሴ፣ በስዓታት፣ በማሕሌት የቅኔውን ምሥጢር በትርጓሜ እያስተማረች ምዕመናንን በእምነት አንፃ ለመንግስተ ሰማያት እያዘጋጀች ዛሬ ላይ ደርሳለች።


✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ

:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮

    የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን 
              ➡️      መሰረተ ሚዲያ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
     ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ

👇👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
https://t.me/Meseretemedia

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

28 Nov, 17:05


ሰንበት ትምህርት ቤት

ክፍል 1

እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ በአርያውና በአምሳሉ ከፈጠረ በኋላ ሰው ከፈጣሪው ጋር በጥብቅ እንዲናገናኝ ልዩ ልዩ የአገልግሎት መንገዶችን አዘጋጀ። እያንዳንዱ በተሰጠው መክሊት ያተርፍና በጸጋው ያገለግል ዘንድ በመጀመርያ ዕድሜው በፈቀደለት ሁሉ መማርና ማገልገል ይኖርበታል። እግዚአብሔር አምላክ መመለክ በአለበት አግባብ ለማምለክ እምነት ያስፈልጋል፤ ከእምነት እንዳንወጣ ደግሞ ስለምናምነው ነገር በቂ ዕውቀት ሊኖረን ይገባል፤ እምነትን፣ ተስፋና ፍቅርን ሰንቆ እስከመጨረሻ ድረስ ለመጽናት መንፈሳዊ ዕውቀት መሠረታዊ ነው።

ክፍል 2 ይቀጥላል

✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ

:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮

    የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን 
              ➡️      መሰረተ ሚዲያ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
     ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ

👇👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
https://t.me/Meseretemedia

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

24 Nov, 17:04


‘’ሥራህን ሥራ ! ’’
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል፣ ያንን መሥራት የእሱ ፈንታ ነው፡፡ ቢቻለው እሱን ማገድ የዲያቢሎስ ሥራ ነው፡፡ በእርግጥ ሥራው እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይጥራል፡፡ ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል፡፡ በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል፡፡የሐሜት ጐርፍ ያስወርድብሃል፡፡

ደራስያን እንዲጠይቁህ እጅግ ስመ ጥር ሰዎችም በክፉ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል፡፡ ጲላጦስ፣ ሄሮድስ፣
ሐና፣ ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ፡፡ ይሁዳም በአጠገብህ ቆሞ በሠላሳ ብር ሊሸጥህ ይከጅላል፡፡ ይሄ ሁሉ የደረሰብህ ሰይጣን በዚህ ከሥራህ ሊስብህና እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ሊያሰናክልህ መሆኑን ልትገነዘብ አትችልምን? አንተ ግን ሥራህን ሥራ!

አንበሳው ሲያጓራ ፍንክች አትበል፣ የሰይጣንን ውሻዎች ለመውገር አትቁም፡፡ ጥንቸሎቹንም በማባረር ጊዜህን አታጥፋ፡፡ ሥራህን ሥራ! ዋሾች ይዋሹ፣ ጠበኞች ይጣሉ፣ ማኀበሮችም ይወስኑ፣ ደራሲዎችም ይድረሱ፣ ሰይጣንም የፈለገውን ያድርግ፣ አንተ ግን ምንም ነገር እግዚአብሔር የሰጠህን ሥራ ከመፈጸም እንዳያግድህ ተጠንቀቅ፡፡

ገንዘብ እንድታተርፍ አልተላክም፣ እንድትበለጽግም አልታዘዝክም፣ ለክብርህ ተከላከል ብሎ አልነገረህም፣ ሰይጣንና አገልጋዮቹ የሚነዙትን የሐሰት ወሬ እንድታስተባብል አልተጠየቅክም፣ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ብታደርግ ሌላ ሥራ ልትሰራ አትችልም፣ ይህም ብቻ ሳይሆን ለራስህ እንጂ ለእግዚአብሔር አልሠራህም፡፡

ዓላማህ እንደ ኮከብ የጸና ይሁን ፤ ተወው ዓለም እንደፈለገው ይነታረክ፣ ይጨቃጨቅ፣ ጥቃት ይደርስብህ ትበደል፣ ትሰደብ፣ ትታማ፣ ትቆስልና፣ ትናቅ ይሆናል፡፡ ኃይለኛ ያጐሳቁልህ፣ ወዳጆች ይተውህ፣ ሰዎችም ይንቁህ ይሆናል፡፡

አንተ ግን በጸና ውሳኔ የማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላይ ጸንተህ፣ የሰጠኸኝን ሥራ ፈጸምኩ ሃይማኖትንም ጠበቅሁ ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማ እና የተፈጠርክበትን ግብ ተከተል!

ሥራህን ሥራ!

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ


    
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ

:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮

    የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን 
              ➡️      መሰረተ ሚዲያ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
     ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ

👇👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
https://t.me/Meseretemedia

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

23 Nov, 09:24


ለምን ትቀናለህ? +

በዜና አበው ላይ አጋንንት አንድን መነኩሴ ለማሰናከል ሲማከሩ የሚያሳይ ታሪክ ተጽፎአል፡፡ መነኩሴው ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ አሳልፎ ከብቃት የደረሰ መናኝ ነበር፡፡ የአጋንንቱ ጭፍራ በአለቃቸው ተመርተው ይህንን መነኩሴ ለማሳት ዘመቱ፡፡ ተራ በተራ ወደ እርሱ እየሔዱ የፈተና ወጥመዳቸውን ዘረጉበት፡፡ በዝሙት ሊፈትኑት ሞከሩ፡፡ አልተሳካም፡፡ በምግብም ሞከሩ ድል ነሣቸው፡፡ የሚያውቁትን የፈተና ስልት በተለያየ መንገድ እየተገለጹ አንዴ ሰው አንዴ መልአክ እየመሰሉ ሊጥሉት ቢሞክሩም አልቻሉም፡፡

አለቃቸው ይኼን ጊዜ በሉ እኔ የማደርገውን ተመልከቱ አላቸውና መንገደኛ መስሎ ወደ መነኩሴው ቀረበ፡፡ በጆሮው የሆነ ነግሮት ወዲያው ተሰናብቶት ወጣ፡፡ ይህንን ጊዜ አጋንንቱ እያዩት መነኩሴው መንፈሳዊ ገጽታው ተገፍፎ ፊቱ በቁጣና በንዴት ሲለዋወጥ ተመለከቱት፡፡ በዚህም ተደንቀው ምን ብለህ ነው ያሸነፍከው? ብለው አለቃቸውን ጠየቁት፡፡ እርሱም እንዲህ አላቸው፦ ‘ከአንተ ጋር ያደገውና ከአንተ ጋር የተማረው ጓደኛህ እኮ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ’ ብዬ ነገርኩትና ወጣሁ፡፡ አሁን ልቡ በቅናት እየነደደ ነው አላቸው፡፡ አጋንንቱ በደስታ ጨፈሩ፡፡

ሰይጣን የቅናትን ኃይል ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ መጽሐፈ ቅዳሴ ሞትን ሲገልጸው ‘በሰይጣን ቅናት ወደ ዓለም የገባ’ ይለዋል፡፡ ሰይጣን በሰው ልጅ ጸጋ ቀንቶ አዳምና ሔዋንን በፈጣሪያቸው እንዲቀኑና አምላክ መሆን እንዲመኙ አድርጎ ዓለምን ያመሰቃቀለ ነውና ይህንን መነኩሴ ለመጣል ለሺህ ዓመታት ብዙዎችን ወግቶ የጣለባትን ሰይፉን መዘዘበት፡፡ መነኩሴው የእኩያውን መሾም ሲሰማ ቅናቱን መቋቋም አቃተው::

ቅናት እጅግ ክፉ ኃጢአት ነው፡፡ ሰው ቢዘሙት ቢሰክር በሥጋው ነው:: ቅናት ግን በምታስተውል ነፍሱ ውስጥ የሚበቅል መርዝ ነው፡፡ ቃየልን በየዋህ ወንድሙ ላይ ያስጨከነው ቅናት ነበር፡፡ የአቤል ስኬት ለቃየል ውድቀት መስሎ ስለተሰማው በግፍ ሊገድለው በቃ፡፡

ዮሴፍ የለበሳት ቀለምዋ ብዙ የሆነ ጌጠኛ ቀሚስ በወንድሞቹ ዘንድ የመረረ ጥላቻን አትርፋለት ነበር፡፡ አንዱ አጊጦ አምሮ ሲታይ ቢሞትና ቢገላገሉት ደስ የሚላቸው የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡

ዮሴፍም አርፎ አልተቀመጠም፡፡ እየሔደ ሕልሙን ይነግራቸው ነበር፡፡ ስለ ሕልሙም የበለጠ ጠሉት ይላል፡፡ ወዳጄ ሕልምህን ዝም ብለህ ለሰዎች አትዝራ፡፡ ሕልም ስልህ ተኝተህ የምታየውን ብቻ ማለቴ አይደለም፡፡ ራእይህን ፣ ተስፋህን ዕቅድህን ሲያውቁ የሚንገበገቡ የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡ ፍቺው ባይገባቸውም ባልተፈታ ሕልም ይጠሉሃል፡፡ ምንም ነገር ሳታደርግ እንኳን "ለምን አለምከው?" ብለው ጥርስ ይነክሱብሃል፡፡ ዮሴፍ ግን ይኼ ስላልገባው ነገራቸው፡፡ ወዳጄ አንተም ሕልምህን እንደ ዮሴፍ በየዋህነት የምትዘራ ከሆንህ እንግዲህ የዮሴፍ አምላክ ይጠብቅህ፡፡

ቅናት እጅግ ከባድ ነው፡፡ እረኛው ዳዊት ጎልያድን የገደለ ዕለት የተዘፈነለት መዘዘኛ ዘፈንም ነበረ፡፡ ‘ሳኦል ሺህ ገደለ ዳዊት እልፍ ገደለ’ ብለው ዘፈኑለት፡፡ ይህች ዘፈን በሳኦል ጆሮ ስትደርስ ዳዊት ላይ ብዙ ጦር አስወረወረች፡፡ ሳኦሎች ሌላ ሰው ከእነርሱ በላይ ሲመሰገን የሰሙ ዕለት በቅናት ታውረው ገበታ ላይ ሳይቀር ሰይፍ ይመዛሉ፡፡

የጠፋው ልጅ ወንድምን አስበው፡፡ (ሉቃ 15:20) ወንድሙ ከጠፋበት ተመልሶ ደስታ ሲደረግ እርሱ ግን ከፍቶት ውጪ ቁጭ አለ፡፡ ወዳጄ ቅናት ከቤተ ክርስቲያንና ከእግዚአብሔር መንግሥት ያስወጣል፡፡ የሌላው ስኬት ካበሳጨህ እንደጠፋው ልጅ ወንድም ውጪ ቁጭ ብለህ አፈር እየጫርክ ‘እምቢየው አልገባም’ እያልክ እያልጎመጎምክ ትቀራለህ፡፡

ክርስቶስ ላይ አይሁድ ያቀረቡት ትችት ሁሉ ለሕግ ከመቆርቆር ሳይሆን ከቅናት ነበር፡፡ ጲላጦስ እንኳን ‘በቅናት አሳልፈው እንደሠጡት ያውቅ ነበር’ ይላል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ቅናታቸውን በሌላ ነገር እንደ አይሁድ ሸፍነው ትችት ያቀርባሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ሕግ እንደተቆረቆሩ ፣ ለሥርዓቱ እንዳዘኑ መስለው ውስጣቸው ያለውን ቅናትና ጥላቻ ያንጸባርቃሉ፡፡

የሰንበት መሻር ፣ ለቄሣር ግብር መከፈል ፣ የመቅደሱ በሦስት ቀን ፈርሶ መሠራት እንዳንገበገባቸው እርር እያሉ ቢናገሩም እውነታው ግን ቅናት ነው፡፡ ‘የቤትህ ቅናት በላኝ’ እንዳለው ጌታ በየዘመኑ የሰዎች ቅናት ብዙ ንጹሐንን ትበላለች፡፡

ወዳጄ በሌላው ትቀና እንደሆን አሁኑኑ ከዚህ ውስጥን በልቶ ከሚጨርስ ካንሰር ራስህን አድን፡፡

ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፡፡ በምድር ላይ እግዚአብሔር የፈጠረው አንተን የሚመስል ሌላ ሰው የለም፡፡ ካንተ ቀድሞም በትክክል አንተን የሆነ ሰው አልተፈጠረም ለወደፊትም አይፈጠርም፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞ ያልሠራው ደግሞም የማይሠራው ምርጥ ዕቃው ነህና ራስህን ከሌላ ጋር አታወዳድር፡፡

ለአንተ ብቻ የሠጠው ጸጋ አለና ሌሎችን መመልከት ትተህ ውስጥህ ያለውን ውድ ማንነት ቆፍረህ አውጣ፡፡ ያንተ ሕይወት ቁልፍ የተቀበረው አንተው ውስጥ ነው፡፡ ሌሎችን ረስተህ ወደ ራስህ ጠልቀህ ግባ፡፡ መብለጥ ከፈለግህም አሁን ያለውን ራስህን ብለጠውና ሌላ ትልቅ አንተን ሁን፡፡

በቅናት እንዳትቃጠል ሌሎችን ሰዎችንም ውደዳቸው፡፡ ከወደድሃቸው ‘ፍቅር አይቀናም’ና የእነርሱ ስኬት የደስታህ ምንጭ ይሆናል፡፡ የቅናት ስሜት ሲሰማህም ‘ቀናተኛ ልቤን ፈውስልኝ’ ብለህ ለምነው፡፡

‘በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን’ ሮሜ 13፡13

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
አለታ ወንዶ ኢትዮጵያ
ጥር 5 2013 ዓ.ም.

መነሻ ሃሳብ:- የአንድ በቅናት ጦስ ሊያበሩ ሲችሉ ብዙ ዋጋ የከፈሉ ቤተሰቦች ታሪክ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ
https://t.me/Meseretemedia

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

23 Nov, 07:31


የ2ኛ ዓመት ኮርስ ተማሪዎች ዛሬ 9 ሰዓት በተነገራችሁ መሠረት በጊዜ ሰዓቱን አክብራችሁ እንድትገኙ

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

23 Nov, 07:10


እንኳን ለጾመ ነቢያት በሰላም አደረሳችሁ

#ጾመ_ነቢያት_ነገ_እሑድ_ኅዳር_15_ይገባል።
አቤቱ ጌታ ሆይ የነቢያትህን ጾም ጸሎት ሰምተህ የወረድህ የተወለድህ ጌታ ሆይ በእኔም ሕይወት ውረድ ተወለድና እኔም ከመላእክት ጋር አብሬ ልዘምር ፣ ከሰብአ ሰገል ጋር ሥጦታህን ልቁጠር ፣ ከእረኞች ጋራ ልደነቅ:: ልደትህ ሳይገባኝ ምጽዓትህ እንዳይደርስብኝ እርዳኝ።


    
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ

:✧๑♡๑✧❀|: ═══╮

    የመሰረተ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት መገናኛ ብዙሃን 
              ➡️      መሰረተ ሚዲያ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
     ቻነሉን share በማድረግ
መሠረተ ሚዲያ አብረን እናሳድግ

👇👇👇👇👇👇👇👇

የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
https://t.me/Meseretemedia

1,153

subscribers

1,521

photos

5

videos