ምዕራፍ ሁለት
ክፍል አራት(ሜርሲ✍️)
"እና እንደዛ ሆና ጥለህ መጣህ?" አቤነዘር በመገረም ጠየቀው::
"ምን ማድረግ ነበረብኝ::ድጋሚ እዛ ቤት መግባት::ድጋሚ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ መጣል::"
"ስለ ሱዚያና ነው?"
አንገቱን በአዎንታ ነቀነቀለት:-
"ስህተት ልትሰራ ከጀመረች ማቆሚያ የላትም::የመጀመሪያ ፍቅረኛዋ በእሷ ምክንያት ነው እራሱን ያጠፋው::"
"ምን!?" ቆሞ ልብሱን ከሚያጥፍበት ከአልጋው ይቀመጣል::
"ቺት አደረገባት::ከዛ ያለውን ሁሉ ቀማችው::ስልህ ምንም እንዳይድን እንዳይሽር አድርጋ ተበቀለችው::በጣም ትወደው ነበር::እሱን በሌላ ሰው መቀማቷ ነው ለበቀል የዳረጋት::ዜን እራሱን ከፎቅ ላይ ወረወረ::"
"እሷ ናት የነገረችህ?"
"የተወሰነውን በስካር ውስጥ ሆና ነገረችኝ::የተቀረውን በእራሴ መንገድ አጣራሁ::የመለያየታችንም ምክንያቱ እሱ ነበር::"
"ቆይ ለምን?... በዚህን ያህል ልክ?"
"አባቷ::አባቷን በጣም ትወደው ነበር::አንድ ቀን እናቷን በገዛ አልጋው ላይ ከሌላ ሰው ጋር አገኘ::የሱዚያናን እጅ ይዞ ነበር::"
"እሷም አየች::"
"አዎ::በነጋታው ጠፋ::ከሁለት ዓመት በኋላ ወታደር ሆኖ ግዳጅ ሄዶ ነገር ኖሯል የሞቱ ዜና ተነገራቸው::ሱዚያና ሕይወት በቀለኛ አድርጓታል::አሁን ላይ ስለ እናቷ አሟሟትም ብዙ ጥያቄዎች አሉኝ::ክላስ ሰዓት ደረሰ መሰለኝ::" በሩ ላይ ቆሞ ከሚያወራበት ወደ ሳሎን ሄደ::
* * *
ሱዚያና ሊያልቅ የደረሰ የቭኦድካ ጠርሙስ በእጇ አንጠልጥላ ጣቷን ከተሰቀለው ከእናቷ ፎቶ ላይ አንጠልጥላ በስካር መንፈስ ውስጥ ሆና ታወራለች:-
"ይሄ ለአንቺ አይገባም ነበር::ይሄ ለሰራሽው ኃጢያት ክፍያ ሊሆን አይገባም ነበር::እንደዚህ በአጭሩ አይደለም የአንቺ ሕይወት መቀጠፍ የነበረበት::ለምን ቀደምሽኝ::" ጠርሙዙን ከፎቶው ላይ ወርውራ ይሰበራል::
"እኔ እንዳቀድኩልሽ ነበር ሞትሽ መሆን የነበረበት::
* * *
"በቀል መሆኑ ነው?.... የእኔን ቃል የናቅከው ልጅነቴን አይተህ ነው አይደል?"
"ዮሂ..." ድጋሚ ድምፁአን በስልኩ ውስጥ አዳመጠው::
"እያለቀስሽ ነው?"
"ለምንድነው ሕይወት የምትጠምብኝ::"
"ዮሂ ስሚኝ::ለእናንተ በማሰብ ነው ሱዚያና አደገኛ ሴት ናት::"
"በእሷ አታሳብ ባክህ::መሸነፍ ስለመሰለህ እንጂ::እህቴ በአንድም ሰው ፊት አልቅሳ አታውቅም::አንተ ምን አይነት ልብ ቢኖርህ ነው::ምን ያህል ክፉ ብትሆን ነው.."
"ዮሂ..." ስልኩን ትዘጋበታለች::ከጆሮው በማንሳት አይቶት ከጠረጴዛው አስቀምጦ ላፕቶፑን በመዝጋት በእረጅሙ ይተነፍሳል::
"ሱዚያና..."
* * *
ሱዚያና ባለማመን አተኩራ እየተመለከተችው:-
"እያበድሽ ነው እያልከኝ ነው::"
"አይደለም::"
"ታዲያ ምን ማለት ነው በሀኪም ትእዛዝ ያቆምኩትን መድሃኒት ቀጥይ ማለት?"
ናትናኤል የካፌውን ግራ ቀኝ አይቶ ወደ እሷ በመዞር:-
"አሁን ላይ ልክ አይደለሽም እያልኩሽ ነው::መድሃኒት መውሰድ ደግሞ እብደት እንዳልሆነ ጠንቅቀሽ ታውቂያለሽ::"
"እያሰብክልኝ ነው?"
"ሱዚያና::" ድምፁ ከፍ ያለ ስለነበር ድጋሚ ግራ ቀኙን አማትሮ ዝግ ባለ ድምፅ:-
"ሰው ነሽ::ስትጠፊ ዝም ብዬ ማየት አልችልም::ያልተነካውን ማንነትሽን አውቀዋለሁ::እሷ ሱዚያና ናት ለአንቺ የምትጠቅምሽ::"
"አመሰግናለሁ ስላሰብክልኝ::ለእኔ የሚበጀኝን እኔ እራሴ አውቀዋለሁ::ባይሆን አንተ ወደ እራስህ ተመለስ::ከማይሆኑ ሰዎች ጋር አትግጠም::ካልሆነ የእኔን ሰው እንዴት እንደማድነው አውቀዋለሁ::"
ተነስታ ስትወጣ በዓይኑ እየተከተላት ሳራ ከበሩ ስትገባ ይገጣጠማሉ::ሱዚያና በዓይኗ ገርምማት ትወጣለች::ሳራ ከቆመችበት ሆና ናትናኤልን ተመልክታው ወደ እሱ በማምራት ወንበር ስባ ትቀመጣለች::ናትናኤል በተደናገጠ ስሜት ሆኖ ወደ እሷ እየተመለከተ:-
"አጋጣሚ ነው ወይስ እየተከተልሽኝ?"
ፈገግ ብላ:-ለምን እከተልሃለሁ::አንተ ነህ ሥራ ቦታዬ ድረስ የመጣሀው::"
"ይሄ ካፌ?"
"የእኛ ነው::እንኳንም አገኘሁህ::ማክ ትላንት ማታ በእንቅልፍ ልቡ ወጥቶ አስፓልት ዳር ለጥቂት ነው መኪና የሳተው::"
"ምን!?"
ይቀጥላል....