🟠 ብዙ ሰዎች ቲክቶክን ወይም ፌስቡክን እየተጠቀሙ በሀጢያት ይቸገራሉ። ያን አፀያፊ ምስል የሚመለከቱት በቲክቶክ ወይም በፌስቡክ ነው። ከዚህ ሀጢያት ጋር ሲታገሉ ለማድረግ የሚሞክሩት የሚያዩትን ቻናል፥ ቪዲዮ ወይም የሚከተሉትን ሰውና ገፅ ማስተካከልና ያን በማድረግም ሀጢያቱን ማሸነፍ የሚችሉ ይመስላቸዋል። ስለዚህ ተመልሰው በዚያው ሀጢያት ይወድቃሉ። እንዲህ አይነት ሰዎች ማድረግ ያለባችሁ ሙሉ በሙሉ ፌስቡክን መጠቀም ማቆም ነው። ማድረግ ያለባችሁ ሙሉ በሙሉ ቲክቶክን መጠቀም ማቆም ነው። ይሄ ማለት ፌስቡክና ቲክቶክ አይጠቅሙም ማለት አይደለም። ይሄን ፅሁፍ እንኳን አንዳንዶች እያነበባችሁ ያላችሁት በፌስቡክ ነው። ነገር ግን በፌስቡክ ላይ እናንተን የሚያሰናክል ነገር ካለ ከነጥቅሙ ቆርጣችሁ መጣል አለባችሁ። ኢየሱስ የሚመክራችሁ እንደዛ ነው። ኢየሱስ አስተካክላችሁ ተጠቀሙ አይደለም የሚላችሁ። አስተካክዬ እጠቀማለሁ የሚለው ሃሳብ የሰይጣን ማታለያ ነው። የሚያሰናክላችሁ ነገር ያለበትን ነገር እስከ ጥቅሙ ቆርጣችሁ መጣል አለባችሁ። ከኢየሱስ የተሻለ ጠቢብ ለመሆን አንሞክር። ዝም ብለን እሱ ያለንን እንተግብር።
🟠 ኢየሱስ በምሳሌው ላይ “ቀኝ አይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት” ሲል የማየትን ጥቅም የሚሰጠን ሌላ ግራ አይን ስላለ እሱን ተጠቀሙ የሚያሰናክላችሁን ግን ከነጥቅሙ ቆርጣችሁ ጣሉት እያለ ነው። ፌስቡክ ወይም ቲክቶክ ላይ ያለውን የሚጠቅም ነገር ሌላ ቦታ ታገኙታላችሁ። ስለዚህ የሚያሰናክላችሁ ነገር ያለበትን አስተካክላችሁ መጠቀም ሳይሆን ቆርጣችሁ መጣል አለባችሁ። አንዳንዶች የሚያሰናክላቸው ሶሻል ሚዲያ ሳይሆን ሌላ ነገር ነው። በሚያሰናክላቸው ነገር ላይ ተመሳሳይ ውሳኔ መውሰድ አለባቸው። ችግሩ ከእግዚአብሔር ሳይለያችሁ ቀድማችሁ ግደሉት። ቀን ሳለ መንገዳችሁን አቅኑ።
📱 የአምላኬ ቃል አፕሊኬሽንን በማውረድ የየእለት ዲቮሽኛል ታገኛላችሁ @Lovedface