ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan @mahberememenan Channel on Telegram

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

@mahberememenan


ዝክረ ቅዱሳን
በጎ/መ/መ/መድኃኔዓለም ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት በመምህር ዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ዝክረ ቅዱሳን የተሰኘ ዘወትር ረቡዕ ከ10 ጀምሮ የሚተላለፍ የየለቱን ቅዱሳን በዓል የሚያዘክር ጉባኤ ነው ።

በ you tube ማግኘት ለምትፈልጉ ሊንኩን ተጫኑት
https://www.youtube.com/channel/UCMVZ5_h0K5_w2EKPxIdNmdw

🔴⭕️⚪️ ለወዳጅ ዘመድዎ በማካፈል ቃለ እግዚአብሔርን ያዳር

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan (Amharic)

እሱ ለኢሕአዴግ እንዲከበርኩ አስረግን የሚል አንድ የቅዱሳን ቤት ነው። ይህ በሌሎች ግማቶችና በአገልግሎት ጊዜ ከ10 ጀምሮ ተሰክቶ የሚሆኑ ጉባኤዎችን ያክሳሉ። ለዝክረ ቅዱሳን ዘር ስትሆን ይመስላሉ። የዝክረ ቅዱሳን ልዩ ፊልም በአይነት ይሰጣል።nnከዚህ በታች መልእክትን ይጠቀሙ፦ [YouTube](https://www.youtube.com/channel/UCMVZ5_h0K5_w2EKPxIdNmdw)nnበመጨረሻው ዓል ደግሞ ለወዳጅ ዘመድዎ በማካፈል ቃለ እግዚአብሔርን ያዳርሯል። እናመሰግናለን ።

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

24 Nov, 03:56


https://youtu.be/Izt7sj2j7Rk?si=uS_3ZphLsLL7V8Q0

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

23 Nov, 21:42


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ኅዳር ፲፭ (15) ❖

+"+ ቅዱስ ሚናስ ምዕመን ሰማዕት +"+

=>ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) በምድረ ግብጽ ተወዳጅ
ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው:: ልክ በሃገራችን ቅዱስ
ጊዮርጊስ ልዩ ቦታ እንዳለው ሁሉ ግብፃውያን ማር
ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም::

+ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም
ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ
ነው:: በተለይ ለታመመ: ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ
ደራሽ: ባለ በጐ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው::

+"ግብጽ ውስጥ ቅዱሱን የማያውቅ ሰው ካገኛችሁ
እርሱ ኦርርቶዶክሳዊ አይደለም ማለት ነው" ሲባልም
ሰምተናል:: በነገራችን ላይ ለቅዱሳን ተገቢውን ክብር
በመስጠት: ታሪካቸውን በመጻፍ: በማጥናት: በመጽሔት:
በፊልምና በመሳሰሉት ለሕዝብ በማስተዋወቅ
ግብጻውያኑ ከእኛ ብዙ ርቀት ሒደዋል:: ዛሬ እንኩዋ
የምንጠቀምበትን ስንክሳር 80 ከመቶ እጁን ያዘጋጁት
እነርሱ ናቸው::

+አባቶቻችንና እናቶቻችን ኢትዮዽያውያን ቅዱሳን ግን
አብዛኞቹ ተረስተው ቀርተዋል:: መጽሐፈ ገድላቸውንም
ብል በልቶታል:: ዛሬም የቤት ሥራው የእኛ ብቻ ነው::

+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ሚናስ (ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው):-

*በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች
ልጅ::
*በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ::
*በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ::
*ሃብትን: ክብርን: ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት
የተወሰነ::
*በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ አላውያን የገደሉት
ሰማዕት ነው::

+እርሱ ሰማዕት ከሆነ ከበርካታ ዘመናት በሁዋላ
ምዕመናን ክቡር አካሉን ፈልገው ያጡታል::
የሚገለጥበት ጊዜ ሲደርስ ግን እርሱ የተቀበረበት ምድረ
በዳ የበጐችና የእረኞች መዋያ ነበርና ተአምራትን
አደረገ::

+አንድ እረኛ በጐቹ ድውያን ሆኑበት:: በዚያ ሰሞን
ከቅዱሱ መቃብር ላይ ጸበል ፈልቆ ነበርና እረኛው ተርታ
ውሃ ነው ብሎ በጎቹን ሲያጠጣቸው አንዱ ድውይ በግ
ወደ ጸበሉ በመዘፈቁ ዳነ::

+በዚህ የተገረመው እረኛ ሁሉንም የታመሙ በጐቹን
አምጥቶ ነከራቸው:: እነርሱም ተፈወሱ:: ይህ ዜና
በምድረ ግብፅ ሲሰማ ድውያን ሁሉ እየመጡ ይፈወሱ
ገቡ:: ግን እነሱም ሆነ እረኛው ምክንያቱን ማወቅ
አልቻሉም:: ነገሩ በሮም ንጉሥ ዘንድ ሲሰማ ሴት ልጁን
ከሠራዊቱ ጋር ላካት::

ምክንያቱም እርሷ ከብዙ ዘመን ጀምራ መጻጉዕ ነበረችና
ፈውስን አጥታ ነበር::

+መጥታ ተጠመቀች: ፈጥናም ተፈወሰች:: እርሷ ግን
እንደ ሌሎች ያዳናትን ማንነት ሳታውቅ መሔድ
አልፈለገችምና ሱባዔ ገባች:: ቅዱስ ሚናስ በሌሊት
ራዕይ መጥቶ ሥጋው እንዳለ ነገራት:: እርሷም መሬቱን
አስቆፍራ የቅዱሱን አካል በክብር አስወጣች::

+ከዚያም በንጉሡ ትዕዛዝ ምድረ በዳው ከተማ
እንዲሆን ተቀየረ:: ስሙም "መርዩጥ" ተባለ:: ጸበሉ
የነበረበት ቦታም ላይ የማር ሚናስ ቤተ ክርስቲያን
ታንጾበት ቅዳሴ ቤ ተከብሯል::

+"+ ቅዱስ ቂርቆስ ሕጻን +"+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካሏት ዐበይት ሰማዕታት አንዱ
ቅዱስ ቂርቆስ ነው:: በተለይ በዘመነ ሰማዕታት ተነስተው
እንደ ከዋክብት ካበሩትም አንዱ ነው:: ቅዱስ ወንጌል
እንዲህ ይላል:- "መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን
ያፈራል::" (ማቴ. 7:17)

+መልካም ዛፍ ቅድስት ኢየሉጣ መልካም ፍሬ ብጹዕ
ቂርቆስን አፍርታ ተገኝታለችና ክብር ይገባታል:: ቡርክተ
ማሕጸንም እንላታለን:: የተባረከ ማሕጸኗ የተባረከ ልጅን
ለ9 ወር ተሸክሟልና::

+በዚያ ክርስቲያን መሆን መከራ በነበረበት ዘመን ይህንን
ደግ ሕጻን እርሷን መስሎ: እርሷንም አህሎ እንዲገኝ
አስችላለችና:: አበው በትውፊት እንዳቆዩልን ከሆነ
በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በዚህች ቀን እናታችን ቅድስት
ኢየለጡ ብጹዕ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስን ወልዳለች::

+ፈጣሪ ቢያቆየን የሰማዕትነት ዜናቸውን ጥር 15 ቀን
የምንመለከት ነንና የዚያ ሰው እንዲለን እንማጸነዋለን::

=>አምላከ ሰማዕታት በምሕረቱ ይማረን:: በይቅርታው
ኃጢአታችን ይተውልን:: ከበረከተ ሰማዕታትም ይክፈለን::

=>ኅዳር 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት
2.ልደተ ቅዱስ ቂርቆስ
3.ብጽዕት ኢየሉጣ
4.አባ ሚናስ ዳግማይ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
2.ቅድስት እንባ መሪና
3.ቅድስት ክርስጢና

=>+"+ አሁንስ ይላል እግዚአብሔር:: በፍጹም ልባችሁ
በጾምም: በለቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ:: ልባችሁን
እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ:: አምላካችሁም
እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ: ቁጣው የዘገየ: ምሕረቱም
የበዛ: ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ:: +"+ (ኢዩ. 2:12)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉https://t.me/mahberememenan
🛑በዩቲብለመከታተል👉 https://youtube.com/@zetewahedo27?si=dci13IKSBSNz5sn

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

22 Nov, 20:21


††† እንኳን ለጻድቃን ቅዱሳን አባ ዳንኤል ወአባ መርትያኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ ዳንኤል ገዳማዊ †††

††† በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ በፋርስ (የአሁኗ ኢራን) ውስጥ ብዙ አስቸጋሪ ነገሥታት ተነስተው ነበር:: ከእነዚህ አንዱ የሆነው የዘመኑ መሪ ክርስቶስን የማያውቅ: መምለኬ ጣኦት የሆነና በጠንቅ ዋዮች ተከቦ የሚኖር ነበር::

እግዚአብሔር ለሁሉም የጥሪ ቀን አለውና ለሕይወት ይጠራው ዘንድ ይህንን ንጉሥ በደዌ ጐበኘው:: የአምላክ ጥሪው አንዳንዴ እንደዚህ: አንዳንዴም እንዲያ ነውና:: ንጉሡ እንደ ታመመ ጠቢባነ ፋርስ ሊያድኑት ሞከሩ:: ግን አልቻሉም:: ሕመሙ እየባሰ ሒዶ ንጉሡ መጻጉዕ ሆነ::

በጊዜው ከመተተኞች ሁሉ በጣም የሚያቀርበው አንድ ጠንቅ-ዋይ በቤተ መንግስት አካባቢ ነበርና ንጉሡ አስጠራው:: "አድነኝ" አለው:: እንደማይችለው ሲያውቅ ዝም አለው:: ንጉሡ መልሶ "ስማ! በቤቴ ውስጥ ከብረህ: ገነህ: የበላሁትን በልተህ: የጠጣሁትን ጠጥተህ የምትኖረው ለዚህ ላትሆነኝ ነው?" ብሎ ተቆጣው::

የንጉሡን ቁጣ ያየው መተተኛ እንደሚገድለው ባወቀ ጊዜ "ንጉሥ ሆይ! እኔኮ አታደርገውም ብዬ ነው እንጂ መድኃኒቱን አውቀዋለሁ:: "ኅሥሥ ሕጻነ ዘዋሕድ ለአቡሁ ወእሙ-ለእናት አባቱ አንድ የሆነ ሕጻን ፈልግ:: እናቱ አስራው አባቱ ይረደውና በደሙ ታጥበህ ትድናለህ" አለው::

መተተኛው እንዲህ ያለው: "ሲሆን ንጉሡ እንዲህ አያደርግም:: ካልሆነ ግን እንዲህ ዓይነት ወላጆች አይገኙም" ብሎ ነው:: ንጉሥ ግን ላስፈልግ ባለ ጊዜ የሚያጣው ነገር የለምና አንድ ልጅ ብቻ ያላቸው ርጉማን ወላጆችን አገኘ::

"1 ሺህ ወቄት ወርቅ ልስጣችሁ እና ልጃችሁን ሰውልኝ" ቢላቸው "እሺ" ብለው ወደ ንጉሡ አደባባይ ወጡ:: በዚያም ሕዝብ ተሰብስቦ: ንጉሡም በዙፋኑ ተቀምጦ ሳለ የ5 ዓመት ሕጻን ልጃቸውን ለገንዘብ ይሰውት ዘንድ ወላጆቹ ቀረቡ:: እናቱ አጥብቃ አሰረችው:: አባቱ ደግሞ ቢላውን አስሎ ቀረበ::

በዚያች ሰዓት ግን ሕጻኑ ወደ ሰማይ ዐይኑን አቅንቶ: እንባው እየፈሰሰ ሲጸልይ ከንፈሮቹ ይንቀሳቀሱ ነበርና ንጉሡ ተመልክቶ ልቡ ራራ:: "እንዳትነኩት" ሲልም ጮኾ ተናገረ:: "ፍቱት" ብሎ ሕጻኑን አስፈትቶ በዙፋኑ ፊት ጠየቀው::

"ምን እያደረክ ነበር?" ቢለው "ለሕጻን ልጅ ጋሻዎቹ ወላጆቹ ናቸው:: በደል ሲያገኘኝ ወደ ወላጆቼ እንዳልጮህ ገዳዮቼ እነሱው ናቸው:: ወደ ዳኛም አቤት እንዳልል አስገዳዩ ዳኛው ራሱ ነው:: ስለዚህም ተስፋየ አንዱ አምላክ እግዚአብሔር ብቻ ነበርና ወደ እርሱ በልቤ ጮህኩ" ሲል መለሰለት:: በዚህ የተገረመው ንጉሡ 1ሺ ወቄት ወርቁን ከወላጆቹ ቀምቶ ለሕጻኑ ሰጥቶ በሰላም አሰናበተው::

ራርቶ ሕጻኑን የፈታው ንጉሥ ሕመሙ ቢጠናበት "የዚህ ሕጻን አምላክ እኔንም እርዳኝ!" ሲል ጮኸ:: በዚህ ጊዜ ጩኸቱ ወደ መንበረ ጸባኦት ደረሰለት:: የእግዚአብሔር ድምጽም ወደ ታላቁ ገዳማዊ ሰው ወደ አባ ዳንኤል መጣ:: "ሒደህ ፈውሰው" አለው::

አባ ዳንኤል ማለት በዘመኑ ከነበሩ ዓበይት ጻድቃን አንዱ ሲሆን መንኖ በርሃ ከገባባት ቀን ጀምሮ በፍጹም ተጸምዶ: በጾም: በጸሎትና በትሕርምት የኖረ አባት ነው:: በዚያች ሰዓትም ጻድቁ በደመና ተጭኖ ከበርሃ ብሔረ ፋርስ ደረሰ:: ከንጉሡም ጋር ተነጋገረ::

ንጉሡ "አድነኝ?" ቢለው "እንድትድን በእውነተኛው አምላክ ማመን አለብህ" አለው:: "ክርስቶስ አምላክ መሆኑን በምን አውቃለሁ?" ብሎ በመጠየቁ ጻድቁ በፊቱ ብዙ ተአምራትን በስመ ክርስቶስ አደረገለት::

ንጉሡም በክርስቶስ አምኖ በተጠመቀ ሰዓት አካሉ ታድሶ: ከደዌው ድኖ ተነሳ:: ሠራዊቱና ሕዝቡም እንዲሁ ተጠመቁ:: አባ ዳንኤልም በደመና ወደ በርሃ ተመልሶ ከተጋድሎ በኋላ በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† አባ መርትያኖስ †††

††† ይህ ቅዱስ ሰው የነበረው በዚያው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን በትውልዱ ሶርያዊ ነው:: ብዙ ጊዜም "መርትያኖስ ካልዕ" (ሁለተኛው) እየተባለ ይጠራል:: ምክንያቱም ቀዳማዊ መርትያኖስ (ታላቁ) ስላሉ ነው::

አባ መርትያኖስ በምድረ ሶርያ ከክርስቲያን ወላጆቹ ጋር አድጐ: የቀናውን የሃይማኖት ትምሕርት ተምሮ: በጐውን ጐዳና መርጧል:: ወቅቱ አርዮሳውያን የበዙበት በመሆኑ ወገኖቹን ይጠቅም ዘንድ ያስተምር ነበር::

በየሥፍራውም እየሔደ ውሉደ አርዮስ (መናፍቃንን) እየተከራከረ ምላሽ ያሳጣቸው ነበር:: በዚህ የተበሳጩ መናፍቃንም አንድ ቀን አሳቻ መንገድ ላይ ጠብቀው በበትር ደበደቡት:: በሞትና በሕይወት መካከልም ትተውት ሔዱ:: እነሱ በዚህ እናስተወዋለን መስሏቸው ነበር::

እርሱ ግን በእግዚአብሔር ኃይል ድኖ እንደ ገና በሰው ፊት ምላሽ አሳጥቶ አሳፈራቸው:: እነርሱም መንገድ ላይ ጠብቀው እየደበደቡ ጐተቱት:: ለብዙ ጊዜም ሲደበድቡት ወደ በርሃ ሸሸ:: በዚያም ገዳማዊ ሰው ሆኖ በጾምና በጸሎት ኖረ:: በዓቱንም በኤርትራ ባሕር ዳርቻ አካባቢ ባለች አንዲት በርሃ አደረገ::

እግዚአብሔር ግን ይህንን ሐዋርያዊ ሰው ይፈልገዋልና እንደ ገና ወደ ከተማ የሚመለስበትን ምክንያት ፈጠረ:: በዘመኑ የሃገሩ ጠራክያ ጳጳስ ዐርፎ "ማንን እንሹም" ብለው ሲጨነቁ ፈጣሪ ጻድቁን በኅሊናቸው ሳለባቸው:: እንደ ምንም ብለው ፈልገው አገኙትና አሥረው አምጥተው የጠራክያ ኤጲስ ቆጶስ አደረጉት::

አሁን ስብከተ ወንጌል ሠመረ:: ምክንያቱም አርዮሳውያኑ እርሱ የመንጋው እረኛ ነውና መንካት አይችሉም:: ቢያደርጉትም እጅግ ተወዳጅ ስለ ሆነ ጠቡ ከሕዝብ ጋር ነው:: በዚሁ መንገድ አባ መርትያኖስ ተጋድሎውን ሳይገታ በሠመረ ስብከቱ ብዙዎችን አሳምኖ ወደ መንጋው ቀላቀለ::

ከሠራቸው ብዙ ተአምራትም አንዱን እነሆ:-
*አንዴ ቅዱሱ መንገድ ሲሔድ ጭቅጭቅ ሰምቶ ቀረበ:: በቦታው የተጋደመ ሬሳ አለ:: "ምንድን ነው ችግሩ?" ቢላቸው የሟች ወገኖች ወደ አንድ ጐረምሳ እየጠቆሙ "አላስቀብር አለን" አሉት::

ያንን ጐረምሳ "ለምን?" ቢለው "ብድር ነበረበትና ካልከፈሉኝ አይቀበርም" አለው:: ጻድቁ ፈጣሪውን ጠይቆ ጐረምሳው በአጋጣሚው ሊያታልል መፈለጉን ተረዳ:: "ልጄ! ተወው ይቀበር" ብሎ ቢለምነው "አይሆንም! ምን ታመጣለህ?" አለው::

ያን ጊዜ አባ መርትያኖስ ጸልዮ የሞተውን "በስመ እግዚአብሔር ተነስ" ሲል አዘዘው:: የሞተውም አፈፍ ብሎ ተነሳ:: በዚህ ጊዜ ያ ሐሰተኛ በድንጋጤ ወድቆ ሞተ:: ለዚህኛው በተዘጋጀው መቃብርም ላይ ቀበሩት:: ከሞት የተነሳው ግን በደስታ ከወገኖቹ ጋር ሔደ:: አባ መርትያኖስም ከዘመናት በኋላ በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† አምላከ አበው ኃይለ ተአምሩን: ረድኤተ ምሕረቱን አያርቅብን:: ከአባቶቻችን በረከትም ይክፈለን::

††† ኅዳር 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ ዳንኤል ገዳማዊ
2.አባ መርትያኖስ ካልዕ (ዘጠራክያ)
3.አባ ዮሐንስ ዘደብረ ቢዘን (ኤርትራ)
4.ቅድስት ደብረ ቀልሞን

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

22 Nov, 20:21


††† ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.አባ ስምዖን ገዳማዊ
3.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
4.እናታችን ቅድስት ነሣሒት
5.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
6.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
7.ቅዱስ ሙሴ መርዓዊ††† "ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ: ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ: ለአንዱም ትንቢትን መናገር: ለአንዱም መናፍስትን መለየት: ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር: ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጐምይሰጠዋል:: ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርገዋል::" †††
(፩ቆሮ. ፲፪፥፱)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉https://t.me/mahberememenan
🛑በዩቲብለመከታተል👉 https://youtube.com/@zetewahedo27?si=dci13IKSBSNz5sn

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

22 Nov, 18:26


https://youtu.be/86UJ2-ocYKQ

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

21 Nov, 20:54


+ይህንን ጸሎት በወሬ ነጋሪ የሰማው ያ መኮንን በጣም ተገርሞ በቅዱሱ ፊት ሔዶ በግንባሩ ተደፋ:: "ስጠላህ የወደድከኝ አባት ሆይ! ማረኝ?" አለው:: ቅዱስ ጢሞቴዎስም አስተምሮ አጠመቀው:: 2ቱም አብረውሲጋደሉ ኑረው ዐርፈዋል::

=>አምላከ ቅዱሳን በረድኤተ መላእክት ጠብቆ በወዳጆቹ ምልጃ ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ኅዳር 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አእላፍ (99ኙ) ነገደ መላእክት
2.ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ
3."13ቱ" ግኁሳን አበው (ሽፍቶች የነበሩ)
4.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘእንጽና
5.አባ ዘካርያስ ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
4.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

=>+"+ ስለ መላእክትም:-
"መላእክቱን መናፍስት: አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ" ይላል . . .
ነገር ግን ከመላእክት:-
"ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ" ከቶ ለማን ተብሏል?
ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ: የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን? +"+ (ዕብ. 1:7-14)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉https://t.me/mahberememenan
🛑በዩቲብለመከታተል👉 https://youtube.com/@zetewahedo27?si=dci13IKSBSNz5sn

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

21 Nov, 20:54


††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን! †††

††† እንኩዋን "ለ99ኙ ነገደ መላእክት": "ቅዱስ አስከናፍር" እና "ቅዱስ ጢሞቴዎስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

††† አእላፍ መላእክት †††

=>እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100): በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጉዋቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በ3 ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጉዋል::

+መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር: ራማና ኢዮር" ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-

1.አጋእዝት (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አህን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው)
2.ኪሩቤል (አለቃቸው ኪሩብ)
3.ሱራፌል (አለቃቸው ሱራፊ)
4.ኃይላት (አለቃቸው ሚካኤል)
5.አርባብ (አለቃቸው ገብርኤል)

6.መናብርት (አለቃቸው ሩፋኤል)
7.ስልጣናት (አለቃቸው ሱርያል)
8.መኩዋንንት (አለቃቸው ሰዳካኤል)
9.ሊቃናት (አለቃቸው ሰላታኤል)
10.መላእክት (አለቃቸው አናንኤል) ናቸው::

+ከእነዚህም *አጋእዝት: *ኪሩቤል *ሱራፌልና *ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው:: *አርባብ: *መናብርትና *ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው:: *መኩዋንንት: *ሊቃናትና *መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው::

+መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::

+ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::

+ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::

*ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ (ዘካ. 1:12)
*ምሥጢርን ይገልጣሉ (ዳን. 9:21)
*ይረዳሉ (ኢያ. 5:13)
*እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ (መዝ. 90:11)
*ያድናሉ (መዝ. 33:7)
*ስግደት ይገባቸዋል (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8)
*በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ (ማቴ. 25:31)
*በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::

+"+ አእላፍ +"+

=>ይህ ዕለት በሊቃውንት አንደበት "አእላፍ" እየተባለ ይጠራል:: በሃይማኖት: በተልእኮትና በምስጋና የሚኖሩ 99ኙ ነገደ መላእክት በአንድ ላይ የሚከበሩበት ቀን ነው:: ምንም እንኩዋን የጐንደሩን ፊት ሚካኤልን ጨምሮ በአንዳንድ አድባራት ታቦቱ ቢኖርም ሲያነግሡ ተመልክቼ አላውቅም::

+ሊቃውንቱ በማሕሌት: ካህናቱም በቅዳሴ እንደሚያከብሯቸው ግን ይታወቃል:: ሕዳር 13 ቀን ዓመታዊ በዓላቸው ነው ማለት በየወሩ በ13 ወርሃዊ በዓላቸው መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልናስባቸው ይገባል::

+ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱሳን መላእክትን በስምና በማዕረግ እንደሚነግረን ሁሉ በማሕበር (በትዕይንት) አገልግሎታቸውም ይነግረናል:: ለምሳሌ:-

*ያዕቆብ= በረዥም መሰላል ሲወጡና ሲወርዱ ተመልክቷል:: (ዘፍ. 28:12)
*ኤልሳዕ ለግያዝ አሳይቶታል:: (2ነገ. 6:17)
*ዳንኤል ተመልክቷል:: (ዳን. 7:10)
*በልደት ጊዜ በዝማሬ መገለጣቸውን ቅዱስ ሉቃስ ጽፏል:: (ሉቃ. 2:13)
*ዮሐንስ በራዕዩ አይቷቸዋል:: (ራዕይ. 5:11)

+ከዚህም በላይ በብዙ የመጻሕፍት ክፍል ተጠቅሰዋል:: ቅዱሳን መላእክተ ብርሃን: መንፈሳውያን: ሰባሕያን: መዘምራን: መተንብላን (አማላጆች) ተብለውም ይጠራሉና ያስቡን ዘንድ ልናስባቸው ይገባል::

+"+ ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ +"+

=>የዚህ ቅዱስ ሰው ሕይወት ታሪክ ደስ የሚያሰኝና የሚያስተምር ነው:: ቅዱሱ የገዳም ሰው አይደለም:: በሮም ከተማ እጅግ ሃብታም: ባለ ትዳር: የአንድ ልጅ አባትና የከተማዋ መስፍን ነው:: ይህ ሰው በጣም ደግና አብርሃማዊ ነው::

+ከጧት እስከ ማታ ነዳያንን ሲቀበልና ሲጋብዝ ነበር የሚውለው:: ነገር ግን አንድና ብቸኛ ልጁ መጻጉዕ (ድውይ) ሆነበት:: ለ35 ዓመታትም ከአልጋ ላይ ተጣብቆ ይኖር ነበር:: ቅዱስ አስከናፍር ግን ፈጣሪውን ያማርር: ደግነቱን ይቀንስ ዘንድ አልሞከረም:: አሁንም ነዳያኑን ማጥገቡን: እንግዳ መቀበሉን ቀጠለ እንጂ::

+በዚያ ወራት ደግሞ በሮም ግዛት ቁዋንጃ የሚቆርጡ: ሰው እየገደሉ የሚዘርፉ 13 ሽፍቶች ነበሩ:: ስለ ቅዱስ አስከናፍር ደግነት ሰምተው ገድለው ይዘርፉት ዘንድ ተማከሩ:: የሠራዊት አለቃ በመሆኑ በማታለል ሔዱ::

+መነኮሳትን ይወዳልና 13ቱም ልብሰ መነኮሳትን ለብሰው: ሰይፎቻቸውን ደብቀው: ከበሩ ደርሰው: "የእግዚአብሔር እንግዶች ነን: አሳድረን" አሉት:: ቅዱስ አስከናፍር ድምጻቸውን ሲሰማ ደነገጠ::

+ብቅ ብሎ አያቸውና "ጌታየ! ምንም ኃጢአተኛ ብሆን አንድ ቀን ወደ ባሪያህ እንደምትመጣ አምን ነበር" ሲል በደስታ ተናገረ:: እንዲህ ያለው ሽፍቶቹ 13 በመሆናቸው ጌታ 12ቱን ሐዋርያት አስከትሎ የመጣ መስሎት ነው::

+ወዲያውም ወደ ቤቱ አስገብቶ እግራቸውን አጠባቸው:: የእግራቸውን እጣቢ ወስዶም በልጁ ላይ አፈሰሰበት:: ድንገትም ለ35 ዓመታት አልጋ ላይ ተጣብቆ የኖረው ልጅ አፈፍ ብሎ ከአልጋው ላይ ተነሳ::

በዚህ ጊዜ ቅዱስ አስከናፍር ለ13ቱ ሽፍቶች በግንባሩ ሰገደ:: ሽፍቶቹ ግን ነገሩ ግራ ቢገባቸው ደነገጡ::

+ጌታ 12ቱን ሐዋርያት አስከትሎ መምጣቱን የሰሙ የሃገሩ ሰዎችም እየመጡ ይሰግዱላቸው ገቡ:: በዚህ ጊዜ ሽፍቶቹ ልብሳቸውን አውልቀው እውነቱን ተናገሩ:: "እኛ ሽፍቶች ነን:: የመጣነውም ልንገልህ ነው:: አምላክ ግን ባንተ ደግነት ይህንን ሁሉ ሠራ:: አሁንም እባክህ ትገድለን ዘንድ ሰይፋችንን ውሰድ" አሉት::

+እርሱ ግን "ንስሃ ግቡ እንጂ መሞት የለባችሁም" ብሎ: ስንቅ ሰጥቶ አሰናበታቸው:: 13ቱ ሽፍቶችም ጥቂት ምሥሮችን ይዘው ወደ ተራራ ወጡ:: ምስሩን በመሬት ላይ በትነው ማታ ብቻ እየቀመሱ በጾምና በጸሎት ተጋደሉ:: በዚህች ቀንም 13ቱም በሰማዕትነት የክብር አክሊልን ተቀዳጁ:: ቅዱስ አስከናፍርም በተቀደሰ ሕይወቱ ተግቶ ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል::

+"+ ቅዱስ ጢሞቴዎስ +"+

=>ይህ ቅዱስ አባት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በዘመነ ሰማዕታት የነበረ የእንጽና (ግብጽ) ክርስቲያን ነው:: በጐ ሕይወቱን የወደዱ አበው በወቅቱ የከተማዋ ዻዻስ: የሕዝቡም እረኛ እንዲሆን መርጠው ሾሙት::

+ጊዜው የመከራ በመሆኑ ከትንሽ ጊዜ በሁዋላ የከተማው መኮንን ክርስቲያኖችን ይገድል ገባ:: ቅዱስ ጢሞቴዎስንም "ክርስትናህን ካልካድክ" በሚል አሠረው:: ጧት ጧት እያወጣም ደሙ እስኪፈስ ድረስ ይገርፈው ነበር:: ደቀ መዛሙርቱንም አንድ አንድ እያለ ፈጀበት::

+ቅዱሱ ግን በትእግስት ሁሉን ቻለ:: በዚህ መካከል ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ነጻ ወጣ:: ያን ጊዜም ሕዝቡን ሰብስቦ ጸሎትን አደረገ:: "ጌታ ሆይ! ይህንን መኮንን እባክህ ማርልኝ? ያደረገው ነገር ሁሉ ባለ ማወቅ ነውና::"

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

21 Nov, 13:04


https://youtu.be/u3uNV3Z1P1c

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

18 Nov, 20:51


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ኅዳር 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

✞✞✞ ቅድስት ሶፍያ ወቅዱሳት አንስት ✞✞✞

✞✞✞ እስኪ ዛሬ በጥቂቱ የተባረኩ (ቡሩካት) እናቶቻችን እንዘክር:: "ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ 'ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን ናትና::

+ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና::

+እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው::
1."ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ሰዎች (ቅዱሳን) ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት::

"ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ ማርያም)

2."ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በኋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና::

"ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ ያሬድ) ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)

3.ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና::

4.እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና::

+የእመ ብርሃን ይቆየንና ደግሞ ሌሎች ቅዱሳት እናቶቻችንን እንመልከት:: እናቶቻችን ስናከብር የምንጀምረው በቅድስት ሔዋን ነው:: ብዙ ጊዜ የእናታችን ሔዋን ጥፋቷ እንጂ በጐ ነገሯ: ደግነቷ: ንስሃዋ አይነገርላትም:: ሆኖም እናታችን ቅድስት ሔዋን ክብር የሚገባት ሴት ናት::

*ክርስቶስ ሰው የሆነ እርሷንና ልጆቿን ለመቀደስ ነውና:: "ከመ ይስዓር መርገማ ለሔዋን ዲበ ዕፅ ተሰቅለ" እንዲል:: (ድጓ)

+ቀጥሎ በብሉይ ኪዳን እነ ሐይከል: እድና: ሣራ: ርብቃ: አስኔት: ሲፓራ: ሐና: ቤርሳቤህን የመሰሉ እናቶቻችን በበጐው መንገድ ፈጣሪን ደስ አሰኝተዋል:: በዘመነ ሥጋዌም ቅዱሳቱ ሐና: ኤልሳቤጥ: ማርያም: ሶፍያ: ሰሎሜ: ዮሐና እና 36ቱ ቅዱሳት አንስት በጐነታቸው ያበራል::

+ከዚያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለ2,000 ዓመታት የተነሱ አእላፍ ቅዱሳት እናቶቻችንን ግን ዘርዝረን አንዘልቃቸውም:: በቅድስናቸው አራዊትን ያሰገዱ: ነገሥታትን ያንቀጠቀጡ: አጋንንቸትን የረገጡ: በዘንዶ ላይ የተጫሙ ብዙ እናቶችን ቤተ ክርስቲያን አፍርታለች::

+ዛሬም ቢሆን በበርሃና በከተማ በጐውን ጐዳና የተከተሉ ብዙ እናቶች እንዳሉን እናውቃለን:: አንድም እናምናለን:: ግን ግን በከተሞች የምንመለከተው ሥርዓቱን የለቀቀው የበርካታ እህቶቻችን አካሔድ ለሃገርም ለቤተ ክርስቲያንም ትልቅ ስጋት ነው:: ክብርና ነውር የማይለይበት ዘመን ይመስላል::

+ይህንን እያነበባችሁ ያላችሁ እህቶቼ! አንድ ነገር ልንገራችሁ:: በመልካቸው ብዙዎችን ያጋጩ: አጊጠው በመታየታቸው ብዙዎችን ያሰናከሉ: ለብዙ ምዕመናንም የጥፋት ምክንያት የሆኑ ብዙ ሴቶች በታሪክ ነበሩ::

+የሚያሳዝነው ግን ዛሬ ያሉት ከመሬት በታች ነው:: አፈር በልቷቸዋል:: ስም አጠራራቸውም ጠፍቷል:: በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ዛሬ በዘለዓለማዊው እሳት እየተቃጠሉ በሲኦል: በጥልቁ ውስጥ አሉ::

+እናም ወገኖቼ! ይህን አውቀን እንንቃ:: ይህ ዓለም ጠፊም: አጥፊም ነውና:: እድሜአችን ቢረዝምና ከዚህ በኋላ ለ100 ዓመታት ብንኖርም እርሱም ማለቁ አይቀርምና:: ምርጫችን ዘለዓለማዊው ሕይወት ይሁን ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን::

+" እለ ቅድስት ሶፍያ "+

+ቅድስት ሶፍያና አብረዋት በዚህ ዕለት የሚከበሩ ቅዱሳት አንስት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም የነበሩ ክረስቲያኖች ናቸው:: አብዛኞቹ መልክ (ደም ግባት) ከጠባይ ጋር የተስማማላቸው ነበሩ:: ነገር ግን ከምድራዊው ክብር ሰማያዊውን መርጠው ለመንፈሳዊው ሙሽርነት ወደ ገዳም ገቡ::

+ከእነዚህ ቅዱሳን መካከል በጸጋና በሞገስ: በትምሕርትም የምትበልጥ ቅድስት ሶፍያ ናትና እመ ምኔት አድርገው ሾሟት:: እርሷም ለገዳሙ በጐውን ሥርዓት ሠራች:: ሁሉም (ደናግሉም መነኮሳይያቱም) በአንድነት ይጾማሉ: ይጸልያሉ: ይሰግዳሉ: የቅዱሳንን ተጋድሎ ያነባሉ:: ሥጋውን ደሙን ይቀበላሉ::

+እርስ በርስ ደግሞ ፈጽመው ይፋቀራሉ:: በዚህ ሕይወት አንዳንዶቹ እስከ 70 ዓመት ቆዩ:: የቅድስናቸው ዜና ሲሰማ በሮም ግዛት ያሉ ወጣት ሴቶች እየመጡ ይቀላቀሏቸው ነበር:: ቅድስት ሶፍያም የሕይወትን መንገድ ታሳያቸው ነበር::

+ከዚህ ሁሉ በኋላ ከሐዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ለጦርነት ወደ ፋርስ ሲሔድ ስላያቸው ባንድነት ሰብስቦ ሁሉንም በሰይፍ አስመታቸው:: ቅድስት ሶፍያም አብራ ሰማዕት ሆነች:: ስለ ቅዱሳኑ የሚበቀል ጌታም ቅዱስ መርቆሬዎስን ልኮ በጦርነቱ መካከል በጦር ወጋው:: ዑልያኖስ ወደ ዘለዓለም ኩነኔ ሲሔድ: ቅዱሳት አንስት ወደ ገነት ሔደዋል::

+" ባሕረ ሐሳብ "+

+ዳግመኛ በዚህ ቀን: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ባሕረ ሐሳብ በዓለማቀፍ ደረጃ ተቀባይነትን አግኝቷል:: ሊቁ ቅዱስ ድሜጥሮስ (የግብጽ 12ኛ ፓትርያርክ) መንፈስ ቅዱስ ቀመረ ባሕረ ሐሳብን ገልጾለት በዓለም ላሉ ሊቃነ ዻዻሳት ልኮላቸው በዚህች ዕለት በሮም ከተማ ተሰበሰቡ::

+ሊቃውንትም ሐዋርያት ካስተማሩት ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ቢያገኙት በደስታ ተቀብለውታል:: እነሆ እስከ ዛሬ ድረስ ለ1,700 ዓመታት ቤተ ክርስቲያን እየተገለገለችበት ይገኛል::

+የቅዱሳት እናቶቻችን አምላክ ዛሬም እንደ እነርሱ ያሉትን አያሳጣን:: በጸሎታቸው ምሮ ከበረከታቸው ይክፈለን::

+ኅዳር 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
2.ደናግለ ሮሜ (ሰማዕታት)
3.ቅዱስ ዻውሎስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቅ
5.ጉቡዓን ኤዺስ ቆዾሳት

ወርኀዊ  የቅዱሳን  በዓላት

1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
7.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ

++"+ ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: +"+ (1ዼጥ. 3:3)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉https://t.me/mahberememenan
🛑በዩቲብለመከታተል👉 https://youtube.com/@zetewahedo27?si=dci13IKSBSNz5sni

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

18 Nov, 09:57


https://youtu.be/xlJcdrGXKJE?si=EWEllMAAW4fibX2D

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

17 Nov, 19:30


††† እንኳን ለአበው ቅዱሳን "318ቱ ሊቃውንት" ዓመታዊ የጉባኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ጉባኤ ኒቅያ †††

††† በዚህች ዕለት (ኅዳር 9 ቀን) በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት ተሰብስበዋል::

የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ::

ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት መስከረም 21 ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ::

እነዚህ አባቶች "ሊቃውንት" ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው::

እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: እስኪ እናውቃቸው ዘንድ የጥቂቶችን ማንነት በስምና በመገለጫ እንመልከት:-
1.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ (በዘመነ ሰማዕታት ለ22 ዓመት ሲቆራርጡት ኖረው በጉባኤው ላይ የተገኘው ያለ እጅ: እግር: ጀሮ: ከንፈር: ቅንድብ ነው)
2.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ (ስለ ቀናች እምነት ለ50 ዓመታት የተጋደለና ለ15 ዓመታት በስደት የኖረ ነው)
3.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ (ከሰማይ ብርሃን ይወርድለት የነበረ አባት ነው)
4.ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ (በጸሎቱ አጋንንትን ያንቀጠቀጠ: ነፍሳትን ከሲዖል የቀማና ከከዊነ እሳት የደረሰ አባት ነው)
5.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ (ስለ ቀናች እምነት መጸዳጃ ጉድጓድ ውስጥ ለ15 ዓመታት ተጥሎ የኖረ ሰማዕት ነው)
6.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሜራ (ከሕጻንነቱ የተቀደሰ: በበርሃ የተጋደለ: በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው)
7.ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን (በደግነቱ ሙታንን ያስነሳ: ወንዝን በጸሎቱ ያቆመ: በንጽሕና የተጋደለ አባት ነው)
8.ቅዱስ ሶል ጴጥሮስ (ቅዱሱን ንጉሥ ያጠመቀ:
ቁስጥንጥንያን በወንጌል ያበራ ሊቅ ነው)
9.ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ (ስለ ቀናች እምነቱ ብዙ ግፍ የደረሰበትና በስደት ያረፈ አባት ነው)

ለአብነት እንዲሆኑን እነዚህን አነሳን እንጂ 318ቱም ሊቃውንት ስለ ቤተ ክርስቲያን ተግተው የተጋደሉ: ብዙ ዋጋም የከፈሉ አባቶች ናቸው::

በወቅቱ ታዲያ ቤተ ክርስቲያንን የበጠበጡ ብዙ መናፍቃን ቢኖሩም የአርዮስ ግን ከመጠኑ አለፈ:: የእርሱ ኑፋቄ (ፈጣሪያችንን ፍጡር ነው ማለቱ) መነሻው ከእርሱ በፊት ነው:: መናፍቃን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያንን ሲያውኩ መኖራቸው ግልጽ ነው::

በተለይ ደግሞ ቢጽ ሐሳውያንና ግኖስቲኮች የወለዷቸው እሾሆች አባቶቻችንን እንቅልፍ ነስተው ነበር:: የሚገርመኝ በዘመኑ እንደ ነበሩ መናፍቃን ኃይለኝነት የእኞቹ ከዋክብት ሊቃውንት ባይኖሩ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ያሳስብ ነበር::

ግን እግዚአብሔር ለሁሉ እንደሚገባ ያዘጋጃልና አበው ብርቱ መናፍቃንን በብርቱ መንፈሳዊ ክንድ እያደቀቁ ከጐዳና አስወገዷቸው:: የዛሬውን ደካማ ትውልድ ደግሞ የአርዮስ ልጆች 2 (3) ጥቅስ ይዘው ሲያደናብሩት ይውላሉ::

ሐረገ መናፍቃን በርጉም ሳምሳጢ ጳውሎስ: በመርቅያንና በማኒ ይጀምራል:: በእርግጥ አርጌንስ እና የግብጹ ቀሌምንጦስም ተቀላቅለዋቸዋል:: ርጉም ሳምሳጢ ድያድርስን በኑፋቄ ወልዶታል:: ድያድርስ ሉቅያኖስን: ሉቅያኖስ ደግሞ አርዮስን ወልደዋል::

ይህ አርዮስ እጅግ ተንኮለኛ በመሆኑ ልክ እንደ ዘመኑ መሰሎቹ ግጥምና ዜማ እየጻፈ በየመንገዱ እያደለ: በየቤቱ እየሰበከ ብዙዎችን በኑፋቄው በከለ:: በመጀመሪያ ተፍጻሜተ ሰማዕት
ቅዱስ ጴጥሮስ (አስተማሪው) መከረው:: ባይሰማው ከአንዴም ሁለት ጊዜ አወገዘው::

ቆይቶ ሰነፉ ጳጳስ አኪላስ ቢፈታውም ሊቁ ቅዱስ
እለእስክንድሮስ እንደ ገና አወገዘው:: እንደ አርዮስ ሐሳብ መድኃኒታችን ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ አይደለም (ሎቱ ስብሐት!) ማለት ክርስትናን ከሥሩ ፈንቅሎ መጣል ነው::

ስለ ክርስቶስ እግዚአብሔርነት ብሉይም ሐዲስም እየመሰከሩ (ኢሳ. 9:6, መዝ. 46:5, 77:65, ዘካ. 14:4, ዮሐ. 1:1, 10:30, ራዕይ. 1:8, ሮሜ. 9:5) አርዮስና የዛሬ መሰሎቹ አንዲት ጥቅስ ይዘው ክርስትናን ከመሠረቱ ለመናድ መሞከራቸው በእርግጥም ከሰይጣን መላካቸውን ያሳያል::

በወቅቱም በመወገዙ "ተበደልኩ" ብሎ የጮኸው አርዮስ ከ2ቱ አውሳብዮሶች ባልንጀሮቹ (ዘቂሣርያና ዘኒቆምድያ) ጋር ሆኖ ወደ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ሔዶ ከሰሰ:: ቅዱሱ ንጉሥም የጉዳዩን ክብደት ተመልክቶ የዓለም ሊቃውነት ይሰበሰቡ ዘንድ አዘዘ::

ከሚያዝያ 21 እስከ መስከረም 21 ተጠቃለው ገቡ:: በ325 ዓ/ም (በእኛው በ318 ዓ/ም) ለ40 ቀናት የሚቆይ ሱባኤን ያዙ:: ሱባኤውን ሲጨርሱም በ4ቱ ፓትርያርኮች (እለእስክንድሮስ: ሶል ጴጥሮስ: ዮናክንዲኖስና ኤዎስጣቴዎስ) መሪነት: በእለእስክንድሮስ ሊቀ መንበርነት: በአትናቴዎስ ጸሐፊነት ጉባኤው ተጀመረ::

በጉባኤው ሙሉ ስልጣን በሰማይ ከፈጣሪ: በምድር ከንጉሡ የተሰጣቸው አበው አርዮስን ተከራክረው ከነ ጀሌዎቹ ምላሽ አሳጡት:: ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: ሥግው ቃል: ራሱም እግዚአብሔር መሆኑን አስረዱት:: በጉባኤው መጨረሻም:-
1.አልመለስም በማለቱ አርዮስን አወገዙ::
2.ጸሎተ ሃይማኖትን "ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም" እስከሚለው ድረስ ተናገሩ::
3.ፍትሐ ነገሥትን ሥጋዊና መንፈሳዊ ብለው አዘጋጁ::
4.ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚገባ አደራጁ::
5.በስማቸው የሚጠራ አንድ ቅዳሴን ደረሱ::

ይህ ሁሉ ሲሆን መድኃኒታችን ክርስቶስ 319ኛ ሆኖና ገሊላዊ ጳጳስን መስሎ ሁሉን አከናውኖላቸዋል:: አባቶችም ሥራቸውን
ከጨረሱ በኋላ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ባርከው ወደየ ሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል::

††† በየዘመኑም ዐርፈው ለክብረ መንግስተ ሰማያት በቅተዋል:: እኛም እነሆ "አባቶቻችን:
መምሕሮቻችን:
መሠረቶቻችን:
ብርሃኖቻችን:
ምሰሶዎቻችን" እያልን እናከብራቸዋለን::

††† አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት በጸሎታቸው እኛንም: ቤተ ክርስቲያናችንንም ከክፉ ጠላት ይጠብቅልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

††† ኅዳር 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን 318ቱ ሊቃውንት
2.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ
3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
4.አባ ይስሐቅ ሊቀ ጳጳሳት
5.ሊቁ አካለ ወልድ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት)
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
3.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
4.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ
5.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ

††† "እውነት እላቹሃለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል:: በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል:: ደግሞ እላቹሃለሁ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል:: ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና::" †††
(ማቴ. ፲፰፥፲፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

17 Nov, 12:39


https://youtu.be/SJnHOd5MfOA

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

16 Nov, 20:52


+የግብጽ አረማውያን ገዢዎች እንደ ትልቅ ሥራ የሚያዩት አድባራትን ማቃጠል: ገዳማትን መመዝበር ነውና እርሱም ለዚሁ ሥራ ተነሳ:: ሠራዊትን አስከትቶ በሠረገላው ተጭኖ ወደ አንድ ገዳም ደረሰ:: ልክ የገዳሙን መሬት ሲረግጥ ግን በአንዴ ልቡናው ተሰበረ::+ሠራዊቱን ወደ ከተማ አሰናብቶ እርሱ ብቻውንወደ ገዳሙ ዘለቀ:: ወደ አበ ምኔቱም ቀርቦ ሰገደላቸውና እንዲያጠምቁት ተማጸናቸው:: እርሳቸውም አስተምረው አጠመቁት:: በዚያውም መንኖ መነኮሰ::

+ለዘመናትም በጠባቡ መንገድ ተጋድሎ ከጸጋ (ከብቃት) ደረሰ:: በአካባቢው ሰውና እንስሳትን የፈጀውን ዘንዶም ባሪያ አድርጐ ለ10 ዓመታት ገዝቶታል:: ከብዙ ተጋድሎ በሁዋላም በዚህ ቀን ዐርፏል::

=>አምላከ ቅዱሳን መላእክት እነርሱን ለረድኤት ይላክልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ኅዳር 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን 4ቱ እንስሳ (ኪሩቤል)
2.ቅዱስ አፍኒን ሊቀ መላእክት
3.አባ ቅፍሮንያ ጻድቅ
4.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ (ዘምስለ ቅዱስ መስቀል)
5.ቅድስት እግዚእ ክብራ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
3.አቡነ ኪሮስ
4.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
5.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

=>+"+ በዙፋኑም መካከል: በዙፋኑም ዙሪያ በፊትና በሁዋላ ዓይኖች የሞሏቸው አራት እንስሶች ነበሩ:: ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል:: ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል:: ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው:: አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል:: አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሏቸው:: +"+ (ራዕይ. 4:6)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉https://t.me/mahberememenan
🛑በዩቲብለመከታተል👉 https://youtube.com/@zetewahedo27?si=dci13IKSBSNz5sni

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

16 Nov, 20:52


እንኩዋን ለቅዱሳን ኪሩቤል (ዐርባዕቱ እንስሳ): ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ወአባ ቅፍሮንያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+"+ ዐርባዕቱ እንስሳ +"+

=>እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100): በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጉዋቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በ3 ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጉዋል::

+መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ 'ኤረር: ራማና ኢዮር' ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-

1.አጋእዝት (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አህን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው)
2.ኪሩቤል (አለቃቸው ኪሩብ)
3.ሱራፌል (አለቃቸው ሱራፊ)
4.ኃይላት (አለቃቸው ሚካኤል)
5.አርባብ (አለቃቸው ገብርኤል)

6.መናብርት (አለቃቸው ሩፋኤል)
7.ስልጣናት (አለቃቸው ሱርያል)
8.መኩዋንንት (አለቃቸው ሰዳካኤል)
9.ሊቃናት (አለቃቸው ሰላታኤል)
10.መላእክት (አለቃቸው አናንኤል) ናቸው::

+ከእነዚህም *አጋእዝት: *ኪሩቤል *ሱራፌልና *ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው:: *አርባብ: *መናብርትና *ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው:: *መኩዋንንት: *ሊቃናትና *መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው::

+መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸው ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::

+ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::

+ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::

*ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ (ዘካ. 1:12)
*ምሥጢርን ይገልጣሉ (ዳን. 9:21)
*ይረዳሉ (ኢያ. 5:13)
*እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ (መዝ. 90:11)
*ያድናሉ (መዝ. 33:7)
*ስግደት ይገባቸዋል (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8)
*በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ (ማቴ. 25:31)
*በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::

+ከእነዚህ ቅዱሳን መላእክት መካከል ደግሞ ትልቁን ሥፍራ ዛሬ የምናከብራቸው ነገደ ኪሩቤል (ዐርባዕቱ እንስሳ) ይይዛሉ:: መንፈሳውያን ከመሆናቸው በላይ መንበረ ጸባኦትን እንዲሸከሙ ስላደላቸው ክብራቸው ታላቅ ነው:: ከመላእክት ወገንም ቅሩባን እነርሱ ናቸው::

+ዘወትርም ስለ ፍጥረታት (ሰዎች: እንስሳት: አራዊትና አዕዋፍ) ምሕረትን ይለምናሉ:: ለዚህም ነው በ4 እንስሳት (በሰው: በንስር: በላምና በአንበሳ) መልክ የተሳሉት:: ቅዱስ መጽሐፍም ስለ እነርሱ ብዙ ይላል:: (ሕዝ. 1:5, ራዕ. 4:6, ኢሳ. 6:1)

+በተለይ ግርማቸው እንደሚያስፈራ ተጽፏል:: "ምሉዓነ ዐዕይንት - ዐይንን የተሞሉ" ይላቸዋል:: ይህንንም መተርጉማን "ምሥጢር አዋቂነታቸውንና ግርማቸውን ያጠይቃል" ሲሉ ተርጉመውታል::

+ዐርባዕቱ እንስሳን 4 ሆነው በስዕል ብናያቸውም "ከመ ርዕየተ እለ ቄጥሩ" እንዲል እያንዳንዱ ከወገብ በላይ አራት በመሆናቸው ተሸካሚዎቹ 16 መልክ አላቸው:: በ2 ክንፋቸው ፊታቸውን: በ2ቱ እግራቸውን ሸፍነው በ2 ክንፋቸው ይበራሉ:: ይህም ብዙ ምሥጢር ሲኖረው ዋናው ግን አርአያ ትእምርተ መስቀል ነው::

+"4ቱ" እንስሳ (ኪሩቤል) በሐዲስ ኪዳንም ልዩ ክብር አላቸው:: 4ቱ ወንጌል ሲጻፍ እየተራዱ ስላጻፉ በስማቸው ተሰይሟል:: ቅዱስ ማቴዎስን ገጸ ሰብእ: ቅዱስ ማርቆስን ገጸ አንበሳ: ቅዱስ ሉቃስን ገጸ ላህም: ቅዱስ ዮሐንስን ገጸ ንስር እየተራዱ ስላጻፏቸው እነሆ እስከ ዛሬ ድረስ "ዘብእሲ ማቴዎስ": "ዘአንበሳ ማርቆስ": "ዘላሕም ሉቃስ" እና "ዘንስር ዮሐንስ" እየተባሉ ይጠራሉ::

+እነዚህ ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን ስለ መራዳታቸውም በብዙ ገድላትና ድርሳናት ላይ ተጽፏል:: የራሳቸውን "ድርሳነ ዐርባዕቱ እንስሳን" ጨምሮ በገድለ አባ መቃርስና በገድለ አባ ብስንድዮስ ላይ በስፋት ግብራቸው ተጽፏል::

+እኛም ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ክብራቸውን: ረድኤታቸውንና ምልጃቸውን አምነን ዘወትር እናከብራቸዋለን:: አባቶቻችን እንዲህ እያሉ እንደ ጸለዩ:-

"ሰላም ለክሙ ኪሩባውያን አፍራሱ:
ለመሐይምን ወጻድቅ እንተ ወርቅ አክሊለ ርዕሱ:
ኀበ ዝ አምላክ ለእለ ትጸውርዎ በአትሮንሱ:
ለእለ ጌገዩ ወለእለሂ አበሱ:
ሰአሉ መድኃኒተ ወምሕረተ ኅሡ::" (አርኬ)

+" ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ "+

=>ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን የፈፀመውን መልካም ተግባር ያሕል መሥራት የቻለ ንጉሥ በሐዲስ ኪዳን የለም:: ጻድቁ ንጉሥ ከቅድስት እናቱ እሌኒና ከአረማዊ አባቱ ቁንስጣ በበራንጥያ ተወለደ::

+ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ /የመከራ ጊዜ/ ወይም የሰማዕታት ዘመን በመሆኑ ክርስቲያኖች በግፍ የሚጨፈጨፉበት ወቅት ነበር:: ክርስቲያኖችን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በተደረገው የ40 ዓመታት ዘመቻ አብያተ-መቃድስና መጻሕፍት ተቃጠሉ::
ብዙዎቹ በየበርሃው ተሰደዱ:: ሚሊየኖች በግፍ አለቁ::

+የዚሕን ዘመን መከራ በውል ያልተረዳ ሰው ቅዱስ ቆንጠንጢኖስን ሊያከብር አይችልም:: ምክንያቱም ይህን የመከራ ዘመን በፈቃደ እግዚአብሔር አስቁሞ: ቀርነ-ሃይማኖት የቆመው: ብዙ ሥርዓት የተሠራው: ቤተ ክርስቲያንም ያበራችው በዘመኑ ነውና::

+ቅዱሱ ንጉሥ ለሁሉም ነቢያት: ሐዋርያትና ሰማዕታት አብያተ ክርስቲያናትን ራሱ በመሠረታት በቁስጥንጥንያ አንጿል:: በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ኖራለት: በኃይለ መስቀሉ ጠላት ጠፍቶለት ኑሮ በዚህች ቀን አርፏል::

+ይህቺ ቀን ታላቁ ንጉሥ በፈለገ ኮቦር ቅዱስ መስቀልን የተመለከተባት ናት:: መክስምያኖስን ሊወጋ ወደ ሮም በተጉዋዘ ጊዜ በሰማይ ላይ መድኅን መስቀል ተዘርግቶ በላዩ ላይ "ኒኮስጣጣን" የሚል በዮናኒ ልሳን ተጽፎበት ተመልክቷል::

+ይህንንም "በዚህ ጠላትህን ድል ታደርጋለህ" ማለት ነው ብለው ተርጉመውለታል:: እርሱም በጋሻው: በጦሩ: በሰይፉ: በፈረሱ ላይ የመስቀል ምልክትን አድርጐ ማሕደረ ሰይጣን መክስምያኖስን ድል ነስቶታል:: እኛንም በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን::

+"+ አባ ቅፍሮንያ ጻድቅ +"+

=>ይህ ቅዱስ ሰው በቀደመ ሕይወቱ አረማዊ ነበር:: ነገር ግን በውስጡ ቅንነት ተገኝቶበታልና እግዚአብሔር በቸር አጠራሩ ወደ ቤቱ አመጣው:: አባቱ አረማዊ: በዚያውም ላይ አገረ ገዢ ነበርና ለቅፍሮንያ ይህንኑ እያስተማረ አሳድጐታል::

+አንድ ቀን ግን ፈጣሪ ጥሪውን ላከለት:: ይኸውም ገና ወጣት ሳለ የገዳም አበው ያዩትና ትንቢት ይናገሩለታል:: "ይህ ሰው በጐ ክርስቲያን: ምርጥ ዕቃም ይሆናል" ሲሉት እንኩዋን ሌሎቹ ለእርሱ ለራሱም ምንም አልመሰለውም ነበር:: በዚህ መንገድ (በአረማዊነቱ) ዓመታት አልፈው ቅፍሮንያ የከተማው መኮንን (አገረ ገዢ) ሆነ::

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

15 Nov, 20:24


እንኩዋን ለቅዱስ "ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዳዊ "*+

=>መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው: አንድም ሞገሳቸው ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ7 ዓመታት ስቃይ በሁዋላ ተሰይፏል:: ይሕስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ:-

+ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ ዘረንቶስ (አንስጣስዮስ) እና ከእናቱ ቴዎብስታ የድሮው ፋርስ ግዛት ፍልስጥኤም (ልዳ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቹ ክርስትናን ጠንቅቀው አስተምረውት አባቱ ይሞታል::

+ቅዱስ ጊዮርጊስ 20 ዓመት ሲሞላው የአባቱን ስልጣን እጅ ለማድረግ ሲሔድ የቢሩት (የአሁኗ ቤይሩት - ሊባኖስ) ሰዎች ዘንዶ (ደራጎን) ሲያመልኩ አገኛቸው:: እርሱ ግን የከተማውን ሕዝብ አስተምሮ: አሳምኖ: ደራጎኑንም በፈጣሪው ኃይል ገድሎ መንገዱን ቀጥሏል::

+ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዱድያኖስና 70 ነገሥታት ዘንድ ሲደርስ ክርስቶስ ተክዶ ለጣዖት ይሠገድ ነበር:: በዚያች ሰዓት ድንግል እመቤታችን ወደ ሰማዕቱ መጥታ መከራውንና ክብሩን ነገረችው:: እርሱም በክርስቶስ ስም መሞት ምርጫው ነበርና ከእመቤታችን ተባርኮ ወደ ምስክርነት አደባባይ (ዐውደ ስምዕ) ደረሰ::

+ከዚያም ለተከታታይ 7 ዓመታት ብዙ ጸዋትወ መከራዎችን ተቀበለ:: 3 ጊዜ ሙቶ ተነሳ:: ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ትዕግስት በላይ የሆነ ስቃይን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በመቀበሉ "የሰማዕታት አለቃቸው" : "ፀሐይና የንጋት ኮከብ" በሚል ይጠራል::
"ተውላጠ ጻማሁ ወሕማሙ::
ዘተለዐለ ሞገሰ ስሙ::" እንዲል መጽሐፍ::

+ከ7 ዓመታት መከራ በሁዋላም ከብዙ ተዓምራት ጋር ተሰይፎ ደም: ውሃና ወተት ከአንገቱ ፈሷል:: 7 አክሊላትም ወርደውለታል::

=>ይህቺ ዕለት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ኃያል ቅዳሴ ቤቱ ናት:: እርሱ በ390ዎቹ አካባቢ ሰማዕት ከሆነ ከጥቂጥ ዓመታት በሁዋላ በዚያው በሃገሩ ደብር አንጸው: አጽሙን አፍልሠው በዚህች ቀን ቀድሰዋታል::

+ቅዱሱ ሰማዕት ከሰማዕትነቱ በፊትም ሆነ በሁዋላ ተአምረኛ ነውና አንዷን እንመልከት:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ሲያፈሱ ከነበሩ አራዊት (ነገሥታት) መካከል አንዱ የሆነው ዲዮቅልጢያኖስ ርጉም የ47 ሚሊየን ክርስቲያኖችን ደም አፍስሶ ነበርና ፈጣሪ ደመ ሰማዕታትን የሚበቀልበት ጊዜ ደረሰ::

+በ305 ዓ/ም አካባቢ አረመኔው ንጉሥ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተአምረኛነት ሰምቶ እንዲያፈርሱት ሠራዊት ላከ:: የሠራዊቱ አለቃም ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ገብቶ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል ላይ ተሳለቀ::

+ከፊቱ የነበረውን ቀንዲል በሰይፍ እመታለሁ ሲል ግን ቀንዲሉ ተገልብጦ መሐል አናቱን መታው:: እንደ እብድ ሆኖ ሞተ:: ሠራዊቱም ሰምቶ ወደ ንጉሡ ሸሸ:: ይሕን ሰምቶ የተበሳጨው ዲዮቅልጢያኖስ ግን ራሱ ሊያፈርሰው ሔደ:: ከቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ ሲደርስ ሚካኤልና ገብርኤል ዐይኑን አጠፉት::

+እገባለሁ ሲል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከላይ መረዋውን (ደወሉን) ለቀቀበት:: ራሱን ቢመታው ደነዘዘ:: የብዙ ቅዱሳንን ደም የጠጣው ርጉሙ ንጉሥም አብዶ ለ7 ዓመታት ፍርፋሪ ሲለምን ኑሮሰ ይጣን ከገደል ጫፍ ወርውሮ ገድሎታል::

=>አምላካችን እግዚአብሔር ከኃያሉ ሰማዕት ጽናትና ትእግስት: ከበረከቱም ይክፈለን::

+"+ ቅዱስ ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ +"+

=>በቤተ ክርስቲያን "ጊዮርጊስ" የሚባሉ ብዙ ቅዱሳን አሉ:: ከልዳዊው ቀጥሎም ይህንን ግብጻዊ ሰማዕት እንጠቅሳለን:: ስሙ ጊዮርጊስ የተባለውም በታላቁ ሰማዕት አማላጅነት ስለ ተገኘ ነው::

+አባቱ ኅዳር 7 ቀን የሊቀ ሰማዕታትን ቅዳሴ ቤት ሊያከብር ሒዶ ስለተማጸኑ የሚስቱ ማሕጸን ተከፍቶለት ልጅ ወልዷል:: ስሙንም ጊዮርጊስ ብሎታል:: ባደገም ጊዜ እጅግ ብርቱ ክርስቲያን ሆነ::

+የግብጻዊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብርታቱ ምንድን ነው ቢሉ:-ንጹሕ አምልኮቱ ጾምና: ጸሎቱ: በጐ ምጽዋቱ ነው:: "ስም ይመርሕ ኀበ ግብር - ስም ወደ ተግባር ይመራል" እንዲሉ አበው የሰማዕቱን ስም ይዞ እሱም ይሔው እድል ገጠመው::

+በአጋጣሚ ወላጆቹ ሲሞቱ የሚኖረው ከከተማው መኮንን ቤት ነበር:: ምክንያቱም የመኮንኑ ሚስት እህቱ ናትና:: ችግሩ ግን መኮንኑ አርማንዮስ ጣዖት አምላኪ: በዚያ ላይ ጨካኝ መሆኑ ነው::

+አንድ ቀን ግብጻዊ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመኮንኑን ሴት ልጅ ወደ በርሃ ወስዶ የደብረ ቁስቁዋም መነኮሳትን ዝማሬ አሰማት:: ክርስትናንም አስተማራት:: ይህንን የሰማው መኮንኑ ግን በብስጭት ቅዱስ ጊዮርጊስንና የራሱን ሴት ልጅ በአደባባይ አሰይፏቸዋል:: የክብርን አክሊልም ተቀዳጅተዋል::

+"+ ቅዱሳን ዘኖቢስና ዘኖብያ +"+

=>እነዚህ ቅዱሳን እናትና ልጅ ናቸው:: ዘኖብያ እናቱ ስትሆን ዘኖቢስ ደግሞ ወጣት ልጇ ነው:: የቅዱሳኑ ሃገር ደግሞ ተበይስ ትባላለች:: በዘመነ ሰማዕታት ድንቅ በሆነ ሕይወታቸውና ተአምራቸው እንደ ኮከብ አብርተዋል:: ከ5 ጊዜ በላይም ከተደገሰላቸው የሞት ወጥመድ በእግዚአብሔር ኃይል አምልጠዋል::

+ " ክርስትናችን አንክድም: ከክርስቶስ ፍቅር አንለይም በማለታቸው:-

1.ልብሳቸውን ገፈው: በዓየር ላይ ሰቅለው: ደማቸው እስኪንጠፈጠፍ ገረፏቸው:: በክርስቶስ ኃይል ተረፉ::

2.የእንጨት መስቀሎችን አሰርተው በአደባባይ ቸንክረው ሰቀሏቸው:: ከዚህም ዳኑ::

3.. 2 ወንበሮች ላይ ችንካሮችን ተክለው በዚያ ላይ አስቀመጧቸው:: አሁንም በፈጣሪ ኃይል ዳኑ::

4.ጥልቅ ጉድጉዋድ ተቆፍሮ: እሳትም ነዶ በዚያ ውስጥ ተጨመሩ:: ቅዱስ መልአክ ግን ወርዶ አጠፋላቸው::

5.አንዴ ደግሞ በቤት (በውሽባ ቤት) እሳት ነዶ በውስጥ ተጨመሩና ተዘጋባቸው:: እግዚአብሔር ግን ከዚህም ታደጋቸው:: ስለ ክብራቸውም ቅዱስ መልአክ ወርዶ እነሱን አክብሮ: መኮንኑን ዙፋኑን አሸክሞ በአደባባይ አዙሮታል::

+አንዴም ጋን አሸክሞ በሁዋላቸው አስከትሎታል:: በነዚህ ሁሉ ድንቆች ብዙ ሕዝብ እያመነ በሰማዕትነት ሙቷል:: በመጨረሻ በዚህ ቀን ዘኖብያና ዘኖቢስ ሲሰየፉ መብረቅ ወርዶ 54 አሕዛብን ገድሏል:: በዚህም መኮንኑ ተገርሞ በክርስቶስ አምኗል::

+"+ አባ ሚናስ ዘተመይ +"+

=>ይህ ቅዱስ አባት ደግሞ ጣዕመ ሕይወቱ ድንቅ ነው:: ክርስቲያን ወላጆቹ በሥርዓት አሳድገው በተክሊል አጋቡት:: ወደ ሙሽራይቱ ገብቶም "እህቴ! ይህ ዓለም ኃላፊ ነውና ለምን በድንግልና አንኖርም?" አላት::

+እርሷም በደስታ "ይሁን" አለችው:: ለበርካታ ዓመታትም ቀን ቀን ሥራቸውን ሲሠሩ: እንግዳ ሲቀበሉ ይውላሉ:: ሌሊት ደግሞ ወገባቸውን ታጥቀው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ያድራሉ::

+ከዓመታት የቅድስና ሕይወት በሁዋላም ቅዱስ ሚናስ ሚስቱን አስፈቅዶ በርሃ ገብቷል:: በተጋድሎ ሳለም እግዚአብሔር ለእረኝነት መርጦት: ተመይ በምትባል የግብጽ አውራጃ ላይ ዽዽስናን ተሹሟል:: በዚያም እስካረጀ ድረስ ተጋድሎ በዚህች ቀን ዐርፏል::

=>እንደ ደመና የከበቡን የእነዚህ ሁሉ ቅዱሳን አምላክ በቸርነቱ ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ኅዳር 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት (ቅዳሴ ቤቱ)
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ
3.ቅዱሳን ዘኖቢስና ዘኖብያ (ሰማዕታት)
4.ቅዱስ ሚናስ ዘተመይ
5.ቅዱሳን መርቆሬዎስና ዮሐንስ (ጻድቃን ወሰማዕት)
6.አባ ናሕርው ሰማዕት

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

15 Nov, 20:24


=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)

=>+"+ የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ:: ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ:: በመጋዝ ተሰነጠቁ:: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ: መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ: በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ:: +"+ (ዕብ. 11:35-38)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉https://t.me/mahberememenan
🛑በዩቲብለመከታተል👉 https://youtube.com/@zetewahedo27?si=dci13IKSBSNz5sni

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

15 Nov, 09:44


https://youtu.be/LhX1nZSSICk

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

13 Nov, 21:37


✝️✝️ እንኩዋን ለታላቁ ጻድቅ "አባ ዮሐኒ" እና "ቅዱስ ለንጊኖስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝️✝️

(በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ትግራይ ውስጥ የሚገኘው አስደናቂው የጻድቁ ገዳም ነው)

+"+ ታላቁ አባ ዮሐኒ +"+

=>በምድረ ኢትዮዽያ ዝናቸው ከወጣና ቀደምት ከሚባሉ ጻድቃን አንዱ ቅዱስ አባ ዮሐኒ ("ኒ" ጠብቆ ይነበብ) ነው:: አበው ሊቃውንት የቅዱሱን ታሪክና ገድል ገና በልጅነት ስለ ነገሩን አንረሳውም:: እጅግ ጣፋጭ ዜና ሕይወት ያለው አባት ነውና:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን በሃገራችን ቅዱስ አፄ ካሌብ ነግሦ ሳለ: አንድ ቅዱስ ሰው ከግብጽ ወደ ኢትዮዽያ መጡ:: እኒህ ሰው "አሞኒ ዘናሕሶ" ይባላሉ:: ቅዱሱ ዓለምን ላለማየት ቃል ገብተው በትግራይ በርሃ ይጋደሉ ነበር::

+በዘመኑ አፄ ካሌብ የናግራን (የመን) ክርስቲያኖችን ለመታደግ ዘመቻ አድርጎ ነበር:: ታዲያ አንድ የንጉሡ ወታደር ወደ ዘመቻ ሲሔድ ሚስቱን ይጠብቅለት ዘንድ ትንሽ ወንድሙን አደራ ይለዋል:: ወንድሙ ግን አደራውን ትቶ የትልቅ ወንድሙን ሚስት አስገድዶ ይደርስባትና ትጸንሳለች::

+ከዘመቻ የተመለሱት ከ1 ዓመት በሁዋላ ነውና ሚስቱን ምጥ ላይ ያገኛት ወታደር ደነገጠ:: ተቆጣ:: የጸነሰችው ከእርሱ እንዳልሆነ ያውቃልና ምጥ ላይ ሆና ሊያዝንላት አልፈለገም::

+ለገልጋይ አስቸግሮ ሚስቱን ይደበድባት ገባ:: በዚህ ምጥ: በዚህ ዱላ ነፍሷን ከሥጋዋ ሊለየው የደረሰችው ያቺ ሴት ግን "ወንድማማችን አላጋድልም" ብላ ቻለችው:: በዚህ ጊዜ ቅዱስ መልአክ ያን ግብጻዊ ባሕታዊ (አባ አሞኒን) አምጥቶ ከሰዎቹ በር ላይ አቆመው::

+"ከእሱ ነው በይ" አላት:: እርሷም "ከዚያ ባሕታዊ ነው" ብላ ተናገረች:: ወታደሩ ባሏም በቁጣ ወጥቶ ቅዱስ አሞኒን በዱላ ስብርብር እስኪል ድረስ ደበደበው:: ልጁ ልክ ሲወለድም ከእናቱ ነጥቆ ለባሕታዊው አሳቅፎ አባረረው::

+ቅዱስ አሞኒም ሕጻኑን አቅፎ ወደ ተምቤን በርሃ አካባቢ ወሰደው:: ግን ምን ምግብ: ምን ልብስ: ምን መኝታ እንደሚሰጠው ጨንቆት ጻድቁ አለቀሰ:: በዚህ ጊዜም ቅዱስ መልአክ የጸጋ ምንጣፍን አነጠፈለት::

+ጆፌ አሞራ መጥቶ ክንፉን ሲያለብሰው አጋዘን መጥታ ጡት አጠባችው:: በዚህ የተደነቀው ቅዱስ አሞኒ ሕጻኑን "ዮሐኒ" ሲል ስም አወጣለት:: ትርጉሙም "ወልደ አራዊት - ወላጆችህ (አሳዳጊዎችህ) አራዊት ናቸው" እንደ ማለት ነው::

+ሕጻኑ ዮሐኒ በዚህ መንገድ ከአሞኒና ከአራዊቱ ጋር አደገ:: 5 ዓመት በሞላው ጊዜም ትምሕርተ ሃይማኖትን: የቅድስና ሕይወትን ተማረ:: ልክ እንደ መንፈሳዊ አባቱ በጾምና በጸሎት ተወሰነ:: ግን እርሱ ከእርሱ: ከአሞኒና ከአራዊቱ በቀር ሌላ ፍጥረት: ዓለም (ብዙ ሰዎች) መኖራቸውን አያውቅም::

+12 ዓመት በሞላው ጊዜ ግን ክህነት ይገባዋል ብሎ መንፈስ ቅዱስ ስላሳሰባቸው ቅዱሱ አሞኒ ዮሐኒን ወደ ዻዻሱ ወሰዱት:: መንገድ ላይም ቅዱስ ዮሐኒ ወጣት ሴቶች ተሰብሰበው ሲጫወቱ ተመልክቶ "አባ! እነዚህ ጸጉራቸው የረዘመ: ደረታቸው ወደ ፊት የወጣ ፍጥረቶች ምንድን ናቸው?" ሲል ጠየቀ::

+አባ አሞኒም "ልጄ! እነዚህ ሴቶች ናቸው:: ግን ለእንደ እኔና አንተ ያሉ የበርሃ ሰዎች አይሆኑምና አትቅረባቸው" አለው:: ቅዱስ ዮሐኒ መልሶ "አባቴ! ድንገት ቢመጡብኝ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀ:: አባ አሞኒም "ልጄ! ከዘለዓለም ርስት ከምትነቀል ሩጠህ ብታመልጥ ይሻላል" አለው::

+ከ6 ዓመታት በሁዋላ (ዮሐኒ 18 ዓመት ሲሞላው ማለት ነው) ቅዱስ አሞኒ ኅዳር 5 ቀን ዐረፈ:: ለ14 ዓመታትም ቅዱስ ዮሐኒ ከአራዊትና አባ አበይዶን ከመሰሉ አባቶች ጋር ኖረ:: ከንጽሕናው የተነሳም ቅዱሳን መላእክት ያነጋግሩት ነበር::

+ስም አጠራሩ በምድረ ትግራይ ሲወጣ ወላጅ እናቱ በሕይወት ነበረችና ሰማች:: የአካባቢዋን ሴቶች ሰብስባም ልትገናኘው ወዳለበት ተራራ ገሰገሰች:: ወደ ተራራው ደርሳ ስትጠራው ቅዱሱ ተመለከታት::

+ወዲያው ትዝ ያለው አባቱ ቅዱስ አሞኒ "ሴት ስታይ ሩጥ" ያለው ነውና እግሩን አንስቶ ሮጠ:: እናቱ ስትከተለው: እርሱ ሲሮጥ ከገደሉ ጫፍ ደረሰ:: ወደ ሁዋላ ሲመለከት ሊደርሱበት ነው::

+በስመ ሥላሴ ፊቱን አማትቦ ወደ ገደሉ ተወረወረ:: በዚህ ጊዜ ግን መንፈሳዊ ክንፍ ተሰጥቶት ተሰወረ:: ቅዱስ መልአክም ብሔረ ሕያዋን አስገብቶታል:: ይህንን ታሪክ ሲያደንቁ አበው እንዲህ ብለዋል::

"ሰላም ዕብል ለዘኮነ ሱቱፈ::
ምስለ እለ ገብሩ ሰብእ ብሔረ ሕያዋን ምዕራፈ::
እምሥርዓተ መላእክት ዮሐኒ ምንትኒ ኢያትረፈ::
ከመ ሕይወቶሙ ሕይወተ ተጸገወ ዘልፈ::
ወከመ ክንፎሙ አብቆለ አክናፈ::" (አርኬ)

+"+ ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት +"+

=>ለንጊኖስ ማለት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስብከት ዘመን የዺላጦስ ወታደር የነበረ ሰው ነው:: ስለ ጌታችን ተአምራት በየጊዜው ይሰማ ነበር:: ሔዶ እንዳያገኘው ግን አይሁድን ይፈራ ነበር:: እነርሱ "በክርስቶስ ያመነ ሁሉ ከምኩራብ ይባረር" ብለው ነበርና:: (ዮሐ. 9:22)

+ጌታችን በተሰቀለባት ዕለተ ዐርብ ግን ጭንቅ ሆነበት:: ጌታን እንዲሰቅሉ ከታዘዙ ወታደሮች እንደ አንዱ ተመርጦ ነበርና በዘዴ አሞኛል ብሎ እስከ 9 ሰዓት ድረስ ቆየ::

+በሁዋላ ግን አይሁድ "በክርስቶስ ሞት ያልተባበረ ሁሉ ወንጀለኛ ነው" የሚል አዋጅ በማስነገራቸው እየፈራ ወደ ቀራንዮ ሲደርስ "ጐኑን ውጋው" ብለው ረዥምና ጥቁር ጦር ሰጡት:: ለንጊኖስ ወደ ጌታችን ዐይን ተመለከተ:: እያየው እንዳልሆነ ገመተ::

+ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ ለይቷልና ጦሩን ጨብጦ ወደ ጌታ ጐን ልኮ ወጋው:: ከጌታ ቀኝ ጐንም በ"ለ" አምሳል ትኩስ ደምና ውሃ ፈሰሰ:: አንዷ ፍንጣቂ ሔዳ የታወረች ዐይኑ ላይ ዐርፋ ዐይኑን አበራች::

+ለለንጊኖስ ታላቅ ደስታ ሆነ:: ለእኛ ግን ማየ ገቦና ደመ ገቦ ፈለቀልን:: የጌታችን ትእግስቱና ቸርነቱ ግን ይደንቃል::
"ከመ ኢየሐስብ ቦቱ ዘኩናተ እዱ ርግዘቶ::
በኃጣውኢሁ ለዘኢፈቀደ ሞቶ::
ምሕረቶ እሴብሕ ወዐዲ ትዕግስቶ::" እንዳሉ ሊቃውንት::

+ጌታችን ከተነሳ በሁዋላ ለንጊኖስ ወደ ቅዱስ ዼጥሮስ ዘንድ ሒዶ ስለ እውነት: ስለ ሃይማኖትም ተማረ:: ተጠምቆ: ምድራዊ ወታደርነቱን ትቶ እየሰበከ ከኢየሩሳሌም ወደ ቀዸዶቅያ ወረደ:: ለዘመናትም ጌታችን ክርስቶስን በሥርዓተ ወንጌል አገለገለ::

+በመጨረሻ በጢባርዮስ ቄሣር ዘመን አይሁድ አሳደዱት:: አንገላቱት:: የነርሱ ወገን ስለነበረም መከራ አጸኑበት:: የጽቅድ አርበኛና የክርስቶስ ሐዋርያ ቅዱስ ለንጊኖስ ግን ጸና:: አይሁድም አንገቱን ቆርጠውት ለሰማዕትነት በቃ:: ቅዱሱ በሕይወቱም በዕረፍቱም ተአምራትን ሠርቷል::

< አስተርዮተ ርዕሱ >

=>ይሕች ዕለት አስተርዮተ ርዕሱ ትባላለች:: እርሱን ከገደሉ በሁዋላ አይሁድ ራሱን ወደ ኢየሩሳሌም ወስደው ጥለዋት ነበር:: የእርሱን ሰማዕትነት ያየች አንዲት ክርስቲያንም ከለቅሶ ብዛት ዐይኗ ቢጠፋ ሕጻን ልጇን ይዛ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች::

+ወዲያው ግን ሕጻን ልጇ ሞተባትና ሐዘኗ ከልኩ አለፈ::
ለአንዲት እናት ዐይንንና ልጅን በአንዴ ማጣት እጅግ ጭንቅ ነው:: በሌሊት ግን ቅዱስ ለንጊኖስ በራዕይ ተገልጦ ደስታ ነገራት::+ "ልጅሽ በገነት ሐሴትን ያደርጋል:: አንቺ ግን ራሴን ከተቀበረችበት አውጪ" አላት:: ወደ ጠቆማት ቦታ በመሪ ስትቆፍር ብርሃን ወጥቶ ዐይኗ በራላት:: በታላቅ ሐሴትም ቅድስት ራሱን ወደ ሃገሯ ወስዳታለች::

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

13 Nov, 21:37


=>አምላከ ቅዱሳን የቀደምቶቻችንን የዋህነት ለእኛም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ኅዳር 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ታላቁ ቅዱስ ዮሐኒ (ዘትግራይ)
2.አባ አሞኒ ዘናሕሶ
3.ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት
5.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)
4.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ

=>+"+ ወደ ጌታ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም:: ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጐኑን በጦር ወጋው:: ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ:: ያየውም መስክሯል:: ምስክሩም እውነት ነው:: እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ: እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል:: ይህ የሆነ:- "ከእርሱ አጥንት አይሰበርም" የሚል የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው:: ደግሞም ሌላው መጽሐፍ:- "የወጉትን ያዩታል" ይላል:: +"+ (ዮሐ. 19:33)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉https://t.me/mahberememenan
🛑በዩቲብለመከታተል👉 https://youtube.com/@zetewahedo27?si=...

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

13 Nov, 00:50


https://youtu.be/FA5i13wKJGU?si=bd7ANEHsSXasrBgO

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

12 Nov, 21:32


እንኩዋን ለቅዱሳን ሰማዕታት "ቶማስ" : "ያዕቆብ ወዮሐንስ" : "አቢማኮስ ወአዛርያኖስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+"+ ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ +"+

=>ቅዱስ ቶማስ በ7ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ተወልዶ ያደገ ሶርያዊ ክርስቲያን ነው:: ከልጅነቱ እንደሚገባ መጻሕፍትን ተምሮ ለዲቁና: ለቅስና: ከዚያም ለዽዽስና በቅቷል:: በወቅቱ የሶርያ ዋና ከተማ በሆነችው ደማስቆ ላይ ተሹሞ ያገለግልም ነበር::

+ታዲያ ዘመኑ በየቦታው ደም የሚፈስበት ነበርና የክርስቶስን መንጋ መጠበቁ ቀላልና የዋዛ ሥራ አልነበረም:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ያፈሱ የነበሩት ደግሞ ተንባላት (የመሐመድ ተከታዮች) ናቸው:: 7ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲደርስም ተንባላት ግብጽንና ሶርያን በቁጥጥር ሥር በማድረጋቸው ክርስቲያኖች ተቸገሩ::

+በወቅቱም ቅዱስ ቶማስ ሲያስተምር የሰማው አንድ መሐመዳዊ "እንከራከር" አለው:: ቅዱሱም ሊቅ ነበርና ስለ መሐመድ ሐሰተኛነት: ስለ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ካስረዳው በሁዋላ ንጹሕና ሰማያዊ ሕግ ቅዱስ ወንጌል እንጂ ቁርዓን እንዳልሆነ ነገረው::

+በአደባባይ በመረታቱ ያፈረው መሐመዳዊም በብሽቀት ሒዶ ለደማስቆው ገዢ ከሰሰው:: ቅዱስ ቶማስም ተይዞ ቀረበ:: "እንዴት እምነታችን እስልምናን ትሳደባለህ?" ቢለው ቅዱሱ "እውነቱን ተናገርኩ እንጂ አልተሳደብኩም" ሲል መለሰለት::

+መኮንኑም "እሺ! ክርስቶስ ማን ነው? ስለ ወንጌልና ቁርዓንስ ምን ትላለህ?" ሲል የተሳለ ሰይፍ አውጥቶ ጠየቀው:: የቀናችው እመነት ክርስትና ክብርነቷ በሰማይ ነውና መጨከንን ትጠይቃለች::

+ቅዱስ ቶማስ ምንም ሳይፈራ "ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይና የምድር ፈጣሪና አምላክ ነው:: ቅዱስ ወንጌል ሰማያዊና የሕይወት ሕግ ሲሆን ቁርዓን ደግሞ የመሐመድ የፈጠራ መጽሐፍ ነው::" ይህንን የሰማው መኮንን በቁጣ አንገቱን እንዲመቱት አዘዘ:: ቅዱስ ቶማስም በዚህች ቀን ስለ ቀናች ሃይማኖቱ አንገቱን ሰጠ::

+"+ ቅዱሳን ያዕቆብ ወዮሐንስ +"+

=>አሁን ደግሞ ወደ 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ተመልሰን: ወደ ምድረ ፋርስ (ኢራን) ወርደን ቅዱሳንን እናዘክር:: እነዚህ ቅዱሳንም በሃገረ ፋርስ (ኢራን): በመንግስተ ሳቦር ዘመን የነበሩ አበው ናቸው:: ሳቦር ማለት ጸሐይንና እሳትን የሚያመልክና እጅግ ጨካኝ የነበረ ንጉሥ ነው::

+ቅዱሳኑ ያዕቆብና ዮሐንስ የሐዋርያትን ስም ብቻ ሳይሆን ግብራቸውን: ቅድስናቸውንም የያዙ ነበሩ:: ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ባይሆንም ፋርስ ግን በዚህ ዘመንም ለክርስቲያኖች የግፍ ከተማ ነበረች::

+ከቅዱስ ጊዮርጊስ እስከ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ: ከቅዱስ መርምሕናም እስከ ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕትነትን የተቀበሉት በዚህችው ሃገር ውስጥ ነው:: ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስም ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በልኩ ተምረው: መጻሕፍትንም ተረድተው ለክህነት ተመርጠዋል::

+በሁዋላም ቤተ ክርስትያን "ይገባቹሃል" ስትል ዻዻሳት አድርጋ ሾመቻቸው:: እነርሱም አላሳፈሯትም:: የክርስቶስን መንጋ እያስተማሩ: እየናዘዙ ጠበቁላት:: ንጉሡ ሳቦር ግን ሕዝቡን ለፀለሐይና ለእሳት ሊያሰግድ ላደረገው ጥረት እንቅፋት ሁነውበታልና ጠላቸው::

+በወታደሮቹ አስይዞም በፍርድ አደባባይ አቆማቸው:: ሕዝቡን በአዋጅ ጠርቶ: አስፈሪ እሳት አስነድዶ "ሕዝቡ ለፀሐይ እንዲሰግድ እዘዙ" ቢላቸው "እንቢ" አሉት::

+ከነ ልብሳቸው አንስተው ወደ እሳቱ ወረወሯቸው:: ቅዱሳኑም በመከራው (በነደደው እሳት) መካከል ሆነው ለሕዝቡ ተናገሩ:: "አምላክ አንድ እግዚአብሔር ነውና እንዲህ በሃይማኖታችሁ ጽኑ" አሏቸው:: እሳቱም አቃጥሎ ገድሏቸው የክብርን አክሊል ተቀዳጁ::

+"+ ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ +"+

=>አሁን ደግሞ ወደ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን: ወደ ዋናው ዘመነ ሰማዕታት እንመለስ:: በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩ ቅዱሳን ሰማዕታት 2ቱ አቢማኮስና አዛርያኖስ ናቸው:: አውሬዎቹ መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ ዓለምን ለ2 ተካፍለው በክርስቲያኖች ላይ ግፍን ሲሰሩ 2ቱ ቅዱሳን በሮም ግዛት ሥር ይኖሩ ነበር::

+በዘመኑ እንኩዋን ቤተ ክርስቲያን ማነጸ: መዘመር: እምነትን መግለጥ ይቅርና ሲያማትቡ መታየት እንኩዋ ያስገድል ነበር:: ነገሥታቱ የሾሟቸው ተከታዮቻቸው ክርስቲያኖችን ከዋሉበት አላሳድር: ካደሩበትም አላውል አሉ::

+ታላቅ ግፍ: ሰቆቃና ጭንቅ በሆነበት በዚያ ወራት የሞተው ሙቶ እኩሉ ሲሰደድ: አቢማኮስና አዛርያኖስ ግን በከተማ መሐል ተረጋግተው ክርስቶስን ያመልኩ ነበር:: ይህም ተደርሶባቸው ተከሰሱና ተይዘው ቀረቡ::

+መኮንኑ 2ቱን ክርስቲያን ወጣቶች ሲመለከታቸው ምንም የፍርሃት ምልክት አልተመለከተባቸውምና ተገረመ:: "ማንን ታመልካላችሁ?" አላቸው:: እነርሱም "የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን!" ሲሉ መለሱለት::

+"ክርስቶስን ትክዳላችሁ ወይስ ትሞታላችሁ?" ቢላቸው "ሰነፍ!" ሲሉ በአደባባይ ገሰጹት:: "የፈጠረ: ያከበረ: ሥጋውን ደሙን የሰጠ ጌታ እንዴት ይካዳል?!" ሲሉም እቅጩን ነገሩት:: በድፍረታቸው የደነገጠው መኮንኑም በዚያች ሰዓት ሞትን አዘዘባቸው:: በዚህች ቀንም አንገታቸውን ተሰይፈው ለክብረ ሰማዕት በቅተዋል::

=>አምላከ ቅዱሳን ሰማዕታት በነርሱ ያሳደረውን ትእግስትና ጽናት በእኛም ላይ ያሳድርልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

=>ኅዳር 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ
2.ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስ
3.ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ
4.አባ አበጊዶ ዘትግራይ
5.ታላቁ አባ ዘካርያስ
6.ጉባኤ ቅዱሳን ሰማዕታት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)

=>+"+ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን'
ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: +"+ (ሮሜ. 8:35-38)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉https://t.me/mahberememenan
🛑በዩቲብለመከታተል👉 https://youtube.com/@zetewahedo27?si=dci13IKSBSNz5sni

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

12 Nov, 09:36


https://youtu.be/20f7EgATCe4

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

11 Nov, 19:31


+በ381 ዓ/ም መቅዶንዮስ: አቡሊናርዮስና ሰባልዮስ በካዱ ጊዜም ለጉባኤው ወደ ቁስጥንጥንያ ከሔዱ ሊቃውንት አንዱ ይሔው ቅዱስ ኪርያቆስ ነው:: ወደ ጉባኤው የሔዱትም ከታላቁ ሊቅና የኢየሩሳሌም ሊቀ ዻዻሳት ቅዱስ ቄርሎስ መንፈሳዊ ጋር ነው::+ሁለቱ እጅግ ወዳጆች ነበሩና:: በጉባኤውም መናፍቃንን ረትተው: ሃይማኖትን አጽንተው: ሥርዓትን ሠርተው ተመልሰዋል:: ቅዱስ ኪርያቆስም በተረፈ ዘመኑ በቅድስና ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል::=>አምላከ አበው የወዳጆቹን የቅድስና ምሥጢር ለእኛም ይግለጽልን:: በረከታቸውንም አትረፍርፎ ይስጠን::

=>ኅዳር 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ጻድቅ (ዘደብረ በንኮል)
2.ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል ጻድቅ (የሠራዊት አለቃ)
3.ቅዱስ ኪርያቆስ ሊቅ
4.ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ንጉሥ (ልደቱ)
5.ቅዱሳን አትናቴዎስና እህቱ ኢራኢ (ሰማዕታት)
6.አቡነ ፍሬ ካህን

=>ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5.አቡነ ዜና ማርቆስ
6.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ (ዓምደ ሃይማኖት)

=>+"+ በረከት በጻድቅ ሰው ራስ ላይ ነው:: የኀጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው:: የኀጥአን ስም ግን ይጠፋል:: +"+ (ምሳሌ 10:6)

   << <ወስብሐት ለእግዚአብሔር>>>

🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉https://t.me/mahberememenan
🛑በዩቲብለመከታተል👉 https://youtube.com/@zetewahedo27?si=dci13IKSBSNz5sni

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

11 Nov, 19:31


=>+"+ እንኩዋን ለቅዱሳን ጻድቃን "አቡነ መድኃኒነ እግዚእ" : "ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል" እና "ቅዱስ ኪርያቆስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+*" አቡነ መድኃኒነ እግዚእ "*+

=>መዘንጋታቸው እጅግ ከሚያስቆጭ ኢትዮጽያውያን አባቶች ትልቁን ሥፍራ እኒህ አባት ይወስዳሉ:: የማር ወለላን በሚያስንቅ ጣዕመ ሕይወታቸው ሃገራችንን ያጣፈጡ: ብርሃን ሆነው ብዙ ቅዱሳንን የለኮሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው::

+አባ መድኃኒነ እግዚእ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ትግራይ (አዲግራት) ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸውም ቀሲስ ሰንበትና ሒሩተ ማርያም ይባላሉ:: በደግነትም እጅግ የታወቁ እንደ ነበሩ ገድላቸው ይናገራል:: "መድኃኒነ እግዚእ" ማለት "ጌታ መድኃኒታችን ነው" ማለት ነው::

+ብዙ ጊዜም "ዘደብረ በንኮል - ሙራደ ቃል" እየተባሉ ይጠራሉ:: "ደብረ በንኮል" ማለት ትግራይ ውስጥ የሚገኝና ጻድቁ በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ያነጹት ገዳም ነው:: "ሙራደ ቃል" ደግሞ "የቃል (የምሥጢር) መውረጃ" እንደ ማለት ሲሆን በቦታው ሱባኤ የያዘ ሰው ልክ እንደ ቅዱስ ያሬድ ምሥጢር እንደሚገጥለት የሚጠቁም ስም ነው::

+ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በልጅነታቸው ከሊቁ ካህን አባታቸውና ከሌሎችም መምሕራን ተምረው: ምናኔን መርጠው ገዳም ገብተዋል:: በጾም: በጸሎትና በስግደት ተግተው ጸጋ እግዚአብሔር ሲሰጣቸው ወደ ደብረ በንኮል ሒደው ገዳም መሠረቱ::

+በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መካከለኛው ዘመን (በተለይ ከ13ኛው እስከ 15ኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ ያለው) የብርሃን ዘመን ይባላል:: ምክንያቱም ዘመኑ
*ክርስትና ያበበበት::
*መጻሕፍት የተደረሱበት::
*ስብከተ ወንጌል የተስፋፋበት::
*ገዳማዊ ሕይወት የሠመረበት ወቅት በመሆኑ ነው::

+ለዚህ ትልቁ አስተዋጽኦ ደግሞ:-
¤አቡነ ተክለ ሃይማኖት::
¤አቡነ ኤዎስጣቴዎስ::
¤አባ ሰላማ ካልዕ::
¤አቡነ ያዕቆብ::
¤ቅዱሱ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ::
¤አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ::
¤አቡነ መድኃኒነ እግዚእን የመሰሉ አበው መነሳታቸው ነው::

+በተጨማሪም:-
¤12ቱ ንቡራነ ዕድ::
¤7ቱ ከዋክብት::
¤47ቱ ከዋክብት::
¤5ቱ ከዋክብት የሚባሉ አበው አስተዋጽኦም ልዩ ነበር:: ከእነዚህ መካከልም የ7ቱ እና የ47ቱ ከዋክብት አስተማሪ: የአበው 3ቱ ሳሙኤሎች (ዘዋልድባ: ዘጣሬጣና ዘቆየጻ): የሌሎችም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን አባት የሆኑት አባ መድኃኒነ እግዚእ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ::

+ጻድቁ ቅዱሳኑን ሰብስበው: አስተምረው: አመንኩሰው: መርቀው ሰደው: ሃገራችንን እንዲያበሩ በማድረጋቸው እንደ አባ ኢየሱስ ሞዐ እርሳቸውም "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን" ይባላሉ:: ታላቁ ጻድቅና ሰባኬ ወንጌል አባ ዓቢየ እግዚእም (ጐንደር ውስጥ እባብና ጅብ እንዳይጐዳ የገዘቱ አባት ናቸው) የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ነበሩ ይባላል::

+ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በተትረፈረፈ የቅድስና ሕይወታቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: አራዊትን ገዝተዋል: በአንበሳ ጀርባ ላይ እቃ ጭነዋል:: ከረዥም የተጋድሎ ሕይወት በሁዋላም ኅዳር 3 ቀን ዐርፈዋል:: እድሜአቸውም 180 ነው::

¤" መድኃኒነ እግዚእ አቡነ መስተጋድል::
ምንኩስናሁ ምዑዝ ከመ ኮል::
በመንፈሰ ጸጋ ክሉል::" (መጽሐፈ ሰዓታት)

¤" ተአምረ ኃይልከ አባ መድኃኒነ እግዚእ አቡነ::
እም አፈ ዜናዊ ሰማዕነ:: ወበዓይነ ሥጋ ርኢነ::
መንክርኬ አእላፈ ቤትከ ንሕነ::
ባሕቱ በዝ ተአምሪከ ርድአነ::
ለሰይፈ አርዕድ ንጉሥ ዘወሀብኮ ኪዳነ::
ከመ ረድኤቱ ታፍጥን ጊዜ ጸብዕ ኮነ::" (አርኬ)

+"+ ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል +"+

=>የዚህ ቅዱስ ኢትዮዽያዊ ዜና ሕይወት ለሁላችንም ትልቅ ትምርትነት ያለው ነው:: በተለይ በምክንያት ከቅድስና ሕይወት እንዳንርቅ ያግዘናል ብየም ተስፋ አደርጋለሁ:: የቅዱሱ ወላጆች ገላውዴዎስና ኤልሳቤጥ ሲባሉ በምድረ ሽዋ በበጐ ምጽዋታቸው የተመሰከረላቸው ነበሩ::

+ፈጣሪ ሰጥቷቸው ኅዳር 8 ቀን (በበዓለ አርባዕቱ እንስሳ) ወልደውታልና "ዓምደ ሚካኤል - የሚካኤል ምሰሶ" ሲሉ ሰይመውታል:: ገና በልጅነቱ ብዙዎችን ያስገርም የነበረው ቅዱሱ አንዴ በ3 ዓመቱ ከቅዳሴ መልስ ጠፋቸው::

+ወላጆቹ እያለቀሱ በሁሉ ቦታ ፈለጉት:: ግን ሊገኝ አልቻለም:: በ3ኛው ቀን የሞቱን መታሠቢያ ሊያደርጉ ካህናትና ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገቡ ግን ባዩት ነገር ተገረሙ:: ሕጻኑ ዓምደ ሚካኤል ከቤተ መቅደሱ መሃል: ከታቦቱ በታች ካለው መንበር (ከርሠ ሐመር ይሉታል) ቁጭ ብሎ ይጫወታል::

+ያየ ሁሉ "ዕጹብ ዕጹብ" ሲልም አደነቀ:: ምክንያቱም በተፈጥሮ ሥርዓት ሕጻን ልጅ ያለ ምግብ 3 ቀን መቆየት ስለማይችልና ሕጻኑ በዚያ የቅድስና ሥፍራ ላይ ምንም ሳይጸዳዳ በመገኘቱ ነው::

+ብጹዕ ዓምደ ሚካኤል ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እየተማረ: በጾምና በጸሎት አደገ:: በ15ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ላይ ንጉሥ የነበረው ጻድቁ አፄ ዘርዓ ያዕቆብም ቅዱሱን የሠራዊት አለቃ (ራስ ቢትወደድ): ወይም በዘመኑ አገላለጽ የጦር ሚኒስትር አድርጐ ሾመው::

+መቼም እዚህ ቦታ ላይ ተቀምጦ መልካምን መሥራት ልዩ ነገርን ይጠይቃል:: በተለይ ደግሞ በዙሪያው የሚከቡትን ተንኮለኞች ድል መንሳቱ ቀላል አልነበረም:: ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል ግን በዘመነ ሲመቱ እነዚህን ሠራ:-

1.በጠዋት ተነስቶ ነዳያንን ይሰበስብና ቁርስ: ምሳ ያበላቸዋል:: ይሕም ዕለት ዕለት የማይቁዋረጥ በመሆኑ ሃብቱ አልቆ ደሃ ሆነ::

2.ከቀትር በሁዋላ ዘወትር ቆሞ ያስቀድስና ጸበል ተጠምቆ ይጠጣል:: ማታ ብቻ እህልን ይቀምሳል::

3.ሽፍታ ተነሳ ሲባል ወደ ዱር ወርዶ: ጸልዮ: ሽፍታውን አሳምኖት ይመጣል እንጂ አይጐዳውም::

4.ጦርነት በሚመጣ ጊዜ ክተት ሠራዊት ብሎ ይወርዳል:: ግን ለምኖ: ጸልዮ: ታርቆ ይመጣል እንጂ ጥይት እንዲተኮስ አይፈቅድም ነበር::

+በዚህ መንገድ በ3ቱ ነገሥታት (በዘርዐ ያዕቆብ: በዕደ ማርያምና እስክንድር) ዘመን ሁሉ አካባቢውን ሰላም አደረገው:: ዓለም ግን ዓመጸኛ ናትና በአፄ እስክንድር ዘመን (በ1470ዎቹ) በሃሰት ተከሶ ስደት ተፈረደበትና ወደ በርሃ ተጋዘ::

+በዚያም ቅዱስ ሚካኤል ሰማያዊ መናን እየመገበው: ሥጋ ወደሙን እያቀበለው ኖረ:: ትንሽ ቆይቶ ግን የሞት ፍርድ ተፈርዶበት በንጉሡ አደባባይ ተገደለ:: ለ30 ቀናትም በመቃብሩ ላይ የብርሃን ምሰሶ ወረደ በዚህም ንጉሡ በእጅጉ ተጸጸተ::

+"+ ቅዱስ ኪርያቆስ +"+

=>ሊቅነትን ከገዳማዊ ሕይወት የደረበው ቅዱስ ኪርያቆስ የቆረንቶስ ሰው ሲሆን አበው "ጥዑመ ቃል - አንደበቱ የሚጣፍጥ" ይሉታል:: ገና በልጅነቱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲያነብ ከአንደበቱ ማማር: ከነገሩ መሥመር የተነሳ ከዻዻሱ እስከ ሕዝቡ ድረስ ተደመው ያደምጡት ነበር::

+በወጣትነቱ ጣዕመ ዓለምን ንቆ ከቆረንቶስ ኢየሩሳሌም ገብቷል:: ቀጥሎም ወደ ፍልስጥኤም ተጉዞ የታላቁ አባ ሮማኖስ ደቀ መዝሙር ሁኖ መንኩሷል:: በገዳሙ ለበርካታ ዘመናት ሲኖርም እጅግ ብዙ ተአምራትን ሠርቷል::

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

11 Nov, 15:30


https://youtu.be/t_jTcaKIuS0?si=hfcxlOJShGlq_Q4Z

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

10 Nov, 21:57


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።

ኅዳር 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+" አባ ዼጥሮስ ሣልስ "+

'ዻዻስ' ማለት 'አባት-መሪ-እረኛ' ማለት ነው:: በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ በሐዲስ ኪዳን የመንፈሳዊ ስልጣን ደረጃዎች በጥቅሉ 3 ናቸው:: እነሱም ዲቁና: ቅስና: ዽዽስና ሲሆኑ በሥራቸው ወደ 9 ያህል ክፍሎች አላቸው:: ከእነዚህም ከፍተኛው ስልጣን ዽዽስና ነው::

+ዽዽስና ማለት የክርስቶስን መንጋ እንደ ባለቤቱ አድርጐ መጠበቅ ማለት ነው:: ሥልጣኑ በምድር 'ሸክም: ዕዳ' ሲሆን በሰማይ ግን 'ክብር' ነው:: ማንም በሥጋው ላይ ካልጨከነ በቀር ዽዽስናን አይመኝም::

+ቅዱስ ዻውሎስ "ሠናየ ግብረ ፈተወ-ማንም ዽዽስናን ቢመኝ መልካም ሥራን ተመኘ" (1ጢሞ. 3:1) ማለቱን ይዞ 'ሹሙኝ' ማለት ወደ ማይጠፋ እሳት የሚያስጥል ከባድ ውሳኔ ነው:: ምክንያቱም አንድ ክርስቲያን የሚጠየቅ በራሱ ኃጢአት ሲሆን አንድ ካህን ደግሞ ስለ ልጆቹ ይጠየቃል:: የከፋው ግን የዻዻሱ ነው::

+አንድ ዻዻስ ቢጾም ቢጸልይም እንኳ ለድኅነቱ በቂ አይደለም:: ምክንያቱም በመንበሩ ላይ ያስቀመጠው መንጋውን እንጂ ራሱን እንዲያድን አይደለምና:: ጌታ እንዳለ መልካም እረኛ "ይሜጡ ነፍሶ ቤዛ አባግኢሁ-መልካሙ እረኛ ስለ በጐቹ ቤዛ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ነው::" (ዮሐ. 10) ስለዚህም ክህነት / ዽዽስና ሐዋርያዊ አገልግሎት ከባድም ኃላፊነት ነው::

+አባቶቻችን ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ሐዋርያውያን ታላላቅ የዽዽስና መንበሮችን መሥርተው: ትምሕርቱን ከነ ወንበሩ አስተላልፈዋል:: ከእነዚህ መንበረ ዽዽስናዎች 4ቱ የበላይ ናቸው:: እነዚህም የቅዱስ ዼጥሮሱ የሮም: የቅዱስ ዮሐንሱ የአንጾኪያ: የቅዱስ ማርቆሱ የእስክንድርያና የቅዱስ ዻውሎሱ የኤፌሶን መናብርት ናቸው::

+እነዚህ መንበሮችም ከክርስቶስ ዕርገት እስከ 443 (451) ዓ/ም: ጉባኤ ኬልቄዶን ድረስ በአንድነት ቆይተው ተለያይተዋል:: ከእነዚህ መናብርት መካከል የእስክንድርያው (የግብጹ) እና የአንጾኪያው (የሶርያው) ዛሬም ድረስ በተዋሕዶ እምነት የጸኑ ናቸው::

+የእኛ ቤተ ክርስቲያንም ሐዋርያዊት እንደ መሆኗ ሐዋርያትን መስለው: ሐዋርያትን አህለው የተነሱ አበው ዻዻሳትን በየጊዜው በበዓላት ታስባለች: ታከብራለች::

+በተለይ ደግሞ የእስክንድርያና የአንጾኪያ በርካታ አባቶችን እናከብራለን:: እነርሱ ለቀናች ሃይማኖትና ለመንጋው ሲሉ ብዙ መከራን በአኮቴት ተቀብለዋልና:: ከእነዚህም መካከል አንዱ አባ ዼጥሮስ ሣልሳዊ ነው::

+ሣልሳዊ መባሉ ከእርሱ በፊት በዚህ ስም ተጠርተው በመንበረ ማርቆስ ላይ የተቀመጡ 2 ፓትርያርኮች ስለ ነበሩ ነው:: ቅዱስ ዼጥሮስ ቀዳማዊ 'ተፍጻሜተ ሰማዕት' (የሰማዕታት ፍጻሜ) የተባለው ሲሆን 17ኛ ሊቀ ዻዻሳት ነው::

+ቅዱስ ዼጥሮስ ካልዕ ደግሞ በ370ዎቹ አካባቢ 21ኛ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ የተሾመና የቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ደቀ መዝሙር የነበረ አባት ነው:: ዛሬ የምናስበው አባ ዼጥሮስ ደግሞ በ470ዎቹ አካባቢ ሊቀ ዽዽስናን በግብጽ ተሹሞ ያገለገለውን ነው::

+ወቅቱ መለካውያን (የኬልቄዶን ጉባኤ አማኞች) የሰለጠኑበት በመሆኑ ሁኔታዎች ትንሽ አስቸጋሪ ነበሩ:: አንደኛ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ከ2 የተከፈለችበት ጊዜ በመሆኑ ፈተናው ለእረኞች ቀላል እንዳይሆን አድርጐታል:: ሌላውና ዋናው ፈተና ግን በዘመኑ የነበሩ ነገሥታት ለመለካውያን (ለመናፍቃን) ወግነው ምዕመናንን ማሳደዳቸው ነው::

+አባ ዼጥሮስ ከተመረጠ በኋላ አስቀድሞ ያደረገው አጋዥ መፈለግ ነበር:: እግዚአብሔር ሲረዳው የታላቂቱ ሃገር የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ የሆነው ቅዱስ አካክዮስን አገኘ:: ከእርሱ ጋርም ደብዳቤ ይጻጻፉ ያዙ::

+ደብዳቤ ሲባል ግን እንዲህ እኛ በዘመኑ እንደምንጽፈው ያለ አይደለም::ይልቁን 5ቱ አዕማደ ምሥጢራትን የተሞሉ ጦማሮች ነበሩ እንጂ:: 2ቱ አበው በየሃገራቸው እየዞሩ እየሰበኩ: አልደርሱበት ባሉበት ቦታ ደግሞ ክታቦችን እየጻፉ በአንድነት ስለ ቀናች ሃይማኖት ደከሙ::

+በእግዚአብሔር ቸርነትም ተሳካላቸው:: አባ ዼጥሮስ በዚህች ቀን ሲያርፍ መሰሉ 'ካልእ አትናቴዎስ' ተክቶታል:: ከፈጣሪውም እሴተ ኖሎትን (የእረኝነት ዋጋውን) ተቀብሏል::

+አምላከ አበው ዻዻሳት መንጋውን በርሕራሔ የሚጠብቁ እረኞችን ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

+ኅዳር 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት ሣልስ
2.አባ ሱንቱዩ ሊቀ ዻዻሳት
3.ቅድስት ሴቴንዋ ነቢይት
4.ቅድስት አንስጣስያ


ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ
7.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

>+"+ ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛልና:: ወንጌልን ብሰብክ እንኩዋ የምመካበት የለኝም:: ግድ ደርሶብኝ ነውና:: ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ:: ይህን በፈቃዴ ባደርገው ደመወዝ አለኝና:: ያለ ፈቃዴ ግን ባደርገው መጋቢነት በአደራ ተሰጥቶኛል:: እንግዲህ ደመወዜ ምንድን ነው? ወንጌልን እየሰበክሁ በወንጌል ካለኝ መብት በሙሉ እንዳልጠቀም ወንጌልን ያለ ዋጋ ብናገር ነው:: +"+ (1ቆሮ. 9:15)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር>>>

https://youtube.com/@zetewahedo27?si=dci13IKSBSNz5sni
https://t.me/mahberememenan

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

09 Nov, 20:56


<<< በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። >>>

"" ኅዳር 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ""

+" ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ "+

+ሃገራችን ኢትዮዽያ በሁሉም ዘርፍ ቅድስና ያላቸው ቅዱሳን ባለቤት ናት:: በዘመኑ ያለን ወጣቶችም ሆነ ጐልማሶች ከቤተ ክርስቲያንና ከቅድስና ሕይወት ለምን እንደራቅን ስንጠየቅ ከምንደረድራቸው ምክንያቶች አንዱ ሥራችን ነው::

+ነገር ግን ሥራው በራሱ ኃጢአት እስካልሆነ ድረስ በየትኛውም የሥራ ዘርፍ ቢሆን ቅድስናን ማስጠበቅ እንደሚቻል አበው አሳይተውናል:: ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም ከእነዚህ ቅዱሳን አንዱ ነው::

*እርሱ ንጉሥ ነው: ግን ገዳማዊ ሕይወትን በቤተ መንግስቱ ውስጥ ያሳየ ጻድቅ ነው::
*ሁሉ በእጁ ነው: እርሱ ግን ንጹሕና ድንግል ነው::
*እርሱ የጦር መሪ ነው: ግን በእጁ ደም አልፈሰሰም::

*እርሱን 'ወደድንህ: ሞትንልህ' የሚሉ ብዙ ሰዎች በአካባቢው ነበሩት:: ለእርሱ ግን ፍቅር ማለት ክርስቶስ ነበር::
*የሃገር መሪ: የኢትዮዽያ ንጉሠ ነገሥት እንደ መሆኑ እጅግ ባተሌ (busy) ነው:: ግን ደግሞ ለክርስትናው ጊዜ ያጣ ሰው አልነበረም::

+እኛ ቤተ ክርስቲያንን "በሐኪ" ለማለት (ለመሳለም) እንኳ 'ጊዜ የለኝም' ስንል እርሱ ግን አብያተ ክርስቲያናትን ይፈለፍል: ያንጽ: በክህነቱ ያገለግል: ማዕጠንት ያጥን: ለረጅም ሰዓትም ይጸልይ ነበር::

+እኛ 'ሥራ ውያለሁና ደክሞኛል' ብለን ከስግደት ስንርቅ እርሱ ግን ንጉሥ ሆኖ ሳለ: ጦር በፊት: በኋላ: በቀኝና በግራ ተክሎ ይሰግድ ስለ ነበር ደሙ እንደ ውሃ በምድር ላይ ፈሷል:: ይህንን ሁሉ ያደረገው ቅዱሱ የኢትዮዽያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ነአኩቶ ለአብ ነው::

"ለመሆኑ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ማን ነው?"

#‎ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ በዛግዌ ሥርወ መንግስት ከነገሡ 11 ነገሥታት አንዱ ሲሆን ከመጨረሻውም 2ኛ ነው:: እርሱን በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን የወለዱት ቅዱሱ ንጉሥ ሐርቤ (ገብረ ማርያም) እና መርኬዛ ናት:: ዘመኑ ቅድስና በላስታ ዙሪያ የመላበት በመሆኑ ቅዱስ ሐርቤ ከመነኑ በፊት ነበር ነአኩቶ ለአብን የወለደው::

+እናቱ መርኬዛ እርሱን ልትወልድ ምጥ ተይዛ ሳለ ጀሮዋ ቅዳሴን ይሰማ ነበር:: ቅዳሴው ሲጀመር የጀመራት ምጥ ድርገት ሲወርዱ (ሥጋ ወደሙ ሲሰጥ) ተፈታላትና ልጇን ተገላገለች:: ሕጻኑን አንስታ ስትታቀፈው ዲያቆኑ ማቁረቡን ፈጽሞ "ነአኩቶ" እያለ ሲዞር ሰማችው::

+እዚያው ላይም 'ነአኩቶ ለአብ' (አብን እናመስግነው) ስትል ስም አወጣችለት:: ወዲያው ግን አባቱ ቅዱስ ሐርቤ መንግስቱን ለቅዱስ ላሊበላ ሰጥቶ በርሃ በመግባቱ ቅዱሱ ሕጻን ወደ አጐቱ ላሊበላ ቤተ መንግስት ውስጥ ገባ::

+የቅዱስ ላሊበላ ቤት ደግሞ በቅድስና ያጌጠ ነውና ከርሱና ከሚስቱ (ቅድስት መስቀል ክብራ) ሕጻኑ ነአኩቶ ለአብ ምናኔና ፍቅረ ክርስቶስን ተማረ:: በዘመኑ ብዙ ሊቃውንት ስለ ነበሩ ቅዱሳት መጻሕፍትን በደንብ አጠና:: ክህነት ተቀብሎ ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግልም እድሜው 30 ደረሰ::

+በወቅቱ ቅዱስ ላሊበላና ባለቤቱ መስቀል ክብራ ልጃቸው ይትባረክ እያለ ንግሥናቸውን ለቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አወረሱ:: ቅዱሱ ነአኩቶ ለአብም ምን እንደሚሠራ ሲያስብ አንድ ነገር ተገለጠለት:: ቤተ መንግስቱን እንደሚገባ ካደራጀ በኋላ በቤት ውስጥ አንድ ጉድጓድን በቁመቱ ልክ አስቆፈረ::

+በውስጡም በ4 አቅጣጫ ጦሮችን ተከለባቸው:: ድንግል ካህን ነበረና ቀን ቀን ሃገር ሲያስተዳድር: ቅዳሴ ሲቀድስ: በጾም ይውላል:: ሌሊት ደግሞ ወዳስቆፈረው ቦታ ገብቶ ያለማቁዋረጥ እየጸለየ ይሰግዳል::

+ወደ ምድር ሲሰግድ በፊቱ ያለው ጦር ይወጋዋል:: ቀና ሲል ደግሞ የጀርባው ይቀበለዋል:: እንዲህ እያለ የፈጣሪውን ሕማማት ይካፈላል:: በተለይ ዐርብ ዐርብ ሲሆን ደሙ: እንባውና ላበቱ ተቀላቅሎ ይፈስ ነበር:: እርሱ መስቀሉን ተሸክሞ ጌታውን ይከተል ዘንድ መርጧልና::

+ከተጋድሎው ጐን ለጐን ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አብያተ ክርስቲያናትንም ያንጽ ነበር:: በተለይ በ1211 አካባቢ ያነጻት አሸተን ማርያም ልዩ ናት:: እርሷን ካነጸ በኋላ ከቤተ መንግስቱ በደመና ሠረገላ ተጭኖ እየሔደ ያጥናት: ይቀድስባትም ነበር::

+ታዲያ አንድ ቀን አጥኖ ከቤተ መቅደስ ሲወጣ ብዙ ሥውራን ቅዱሳን መቅደሱን ከበው ተመለከተ:: እርሱም "ወገኖቼ! ከወዴት መወጣችሁ?" ቢላቸው "መዐዛ እጣንህን አሽተን መጣን" ሲሉ መለሱለት:: በዚህ ምክንያትም እስከ ዛሬ ድረስ "አሽተን (አሸተን) ማርያም" ስትባል ትኖራለች::

+ዛሬ ታቦቱ ያለበት ገዳሙም በእርሱ የታነጸ ሲሆን እጅግ ተአምረኛ ቦታ ነው:: ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ የነገሠ በ30 ዓመቱ ነው:: ለ40 ዓመታት በእንዲህ ያለ ቅድስና ኑሮ 70 ዓመት ሞላው:: በዚህ ጊዜም ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ሰላምታንም ሰጠው::

+"ወዳጄ ነአኩቶ ለአብ! አንተ ስለ እኔ ፍቅር ለ40 ዓመታት መከራን ተቀብለሃልና ሞት አያገኝህም:: ከፍልህ ከነ ኤልያስ ጋር ነውና:: የሚያከብርህን አከብረዋለሁ:: ደጅህን የሳመውን: ይህ ቢያቅተው በሩቁ ሆኖ በአድናቆት የተመኘህን: መታሰቢያህን ያደረገውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው::

+ቀጥሎም "ይሕች ቤት አንተ ስትደማ እንደኖርክባት እርሷም እስከ ምጽዓት ድረስ ለመታሰቢያህ ስትደማ ትኑር" አለው:: እነሆ ዛሬም ድረስ ከመቅደሱ ጸበል ይንጠበጠባል:: ለዚህም ደግሞ እኛ ኃጥአን ምስክሮች ነን:: ሳይገባን የቅዱሱን ደጅ ተመልክተናልና::

+ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም የዚህን ዓለም ተጋድሎውን ፈጽሞ ወደ ብሔረ ሕያዋን መላእክት ወስደውታል:: የተሰወረበትን ዕለት ስንክሳር ሕዳር 1 ሲያደርገው አንዳንድ መዛግብት ደግሞ በ3 ነው ይላሉ:: በዙፋኑም ላይ የአጐቱ የላሊበላ ልጅ አፄ ይትባረክ ተተክቷል::

+አምላከ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ በቃል ኪዳኑ ይማረን:: ከበረከቱም አትረፍርፎ ይስጠኝ::

+ኅዳር 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
2.ቅዱሳን መክሲሞስና ባልንጀሮቹ (ሰማዕታት)

ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር


++"+ ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን: ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን:: ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን:: +"+ (ሮሜ. 6:5)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/mahberememenan

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

09 Nov, 09:04


https://youtu.be/MB52cEWc_EY?si=4E_OABnGq8eqAm4q

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

08 Nov, 19:45


=>ወርኃዊ በዓላት1.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
2.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
3.አባ ሣሉሲ ጻድቅ

++" ... እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተ

ባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ:: ዼጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሏት አንዲት አገልጋይ ትሰማ ዘንድ ቀረበች:: የዼጥሮስ ድምጽ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሳ ደጁን አልከፈተችም:: ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ዼጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች:: +"+ (ሐዋ. 12:12-15)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/mahberememenan

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

08 Nov, 19:45


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ጥቅምት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

+" ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ "+

✞✞✞ በዚሕች ዕለት ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነ: ወንጌላዊ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ ተወልዷል ::

+ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም: አባቱ አርስጥቦሎስ ይባላሉ:: በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ በሚገባ ተምሮ ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል:: የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ120ው ቤተሰብ በእድሜ በጣም ትንሹ /20 ዓመት/ እርሱ ነበር::

+ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል:: በተለይ የግብፅና የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው:: ክህነትን ያገኘን ከርሱ ነውና::

+ቅዱስ ማርቆስ 16 ምዕራፍ ያለውን ወንጌሉን ሲጽፍ ኪሩብ ገጸ አንበሳ በቀኙ: ሊቀ ሐዋርያት በግራው ሆነው ይራዱት ነበር:: ቅዱሱ ክቅዱስ ዻውሎስ: ከበርናባስና ዼጥሮስ ጋር ተጉዟል:: ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ሰሜን አፍሪካ አካባቢ አረማውያን ገድለውታል:: ይህቺ ዕለት የልደቱ መታሠቢያ ናት::

+ዳግመኛ በዚህ ቀን የቅዱስ ማርቆስን ወላጆችን እናስባቸው ዘንድ ይገባል:: ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ) የጌታ ቅን አገልጋይ የነበረ: ቅድስት ማርያም (እናቱ) ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ: ጌታችንን ያገለገለች ቤቷን ለሐዋርያትና ለጌታ በስጦታ ያበረከተች ቅድስት ናት::

+ቤቷም (ጽርሐ ጽዮን) የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ይህች ቤት መንፈስ ቅዱስ ወርዶባታል:: የእመቤታችን ግንዘትም ተከናውኖባታል::

+እግዚአብሔር ከሐዋርያዊው ቅዱስ ቤተሰብ በረከትን ያድለን::

+" ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ "+

+ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

*የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::

*ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

*ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

*የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በኋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

*ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::

*እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::

*ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::

*ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23) ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::

*ከዚህ በኋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::

*ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::

*ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::

*"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው::

*በዚህች ቀንም ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ. 1:6)

*ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በኋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::

*ከዚሕ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::

✞✞✞ ይህች ዕለት ለቅዱሱ 'አስተርዕዮተ ርዕሱ' ወይም ቅድስት ራሱ ከተወረችበት የተገለጠችበት ነው::+ጥቅምት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ)
3.ቅድስት ማርያም (እናቱ)
4.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
5.አባ አብርሃም ገዳማዊ
6 ቅዱስ ይስሐቅ ንጉሥ

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

07 Nov, 20:24


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

=>+"+ እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "ሳሙኤል ዘወገግ": "ጸቃውዐ ድንግል" እና "ድሜጥሮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+"+ አባ ሳሙኤል ዘወገግ +"+

=>ሃገራችን ኢትዮዽያ ማኅደረ ቅዱሳን (ምዕራፈ ቅዱሳን) እንደ መሆኗ ፍሬ ክብር: ፍሬ ትሩፋት ያፈሩ ብዙ አባቶችና እናቶችን አፍርታለች:: ብርሃን ሁነው ካበሩላት ቅዱሳን መካከል አንዱ ደግሞ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ ናቸው::

+በእኛው ሃገር ብቻ ብዙ "ሳሙኤል" የሚባሉ ቅዱሳን በመኖራቸው ስንጠራቸው "ዘእንትን" እያልን ነው:: ለምሳሌም:

*ሳሙኤል ዘዋሊ
*ሳሙኤል ዘወገግ (የዛሬው)
*ሳሙኤል ዘጣሬጣ
*ሳሙኤል ዘቆየጻ
*ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያና
*ሳሙኤል ዘግሺን መጥቀስ እንችላለን:: ሁሉም የመካከለኛው ዘመን ሐዋርያዊ አባቶች ናቸው::

+ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ሃገረ ሙላዳቸው የብዙ ቅዱሳን ቤት የሆነችው ሽዋ ናት:: መንደራቸውም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ብዙም አይርቅም::

+የጻድቁ ወላጆች እንድርያስና አርሶንያ የሚባሉ ሲሆን ደጐች ነበሩ:: ጻድቁ በተወለደ ጊዜ የቤታቸው ምሰሶ ለምልሞ ተገኝቷል:: አቡነ ሳሙኤል ከልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው በጉብዝናቸው ወራት ይህችን ዓለም ንቀዋል::

+የታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሆነው በደብረ ሊባኖስ መንነዋል:: ከ12ቱ ኅሩያን (ምርጦች) አርድእት አንዱ ነበሩና በክህነታቸው ደብረ ሊባኖስን ተግተው ያጥኑ ነበር:: በዚያውም በንጹሕ ልቡና በጾምና ጸሎት ይተጉ ነበር::

+አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ በሁዋላ በደጉ ዻዻስ በአቡነ ያዕቆብ ዘመን 12ቱ ንቡራነ እድ ተመረጡ:: እነዚህ አባቶች በወንጌል አገልግሎት: በተለይ ደቡብና ምሥራቁን የሃገራችን ክፍል ያበሩ ናቸው:: ቅዱሳኑ ሲመረጡም ከአቡነ ፊልዾስ ቀጥለው በ2ኛ ደረጃ የተመረጡ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ ናቸው::

+ሃገረ ስብከታቸውም ሐረርና ሱማሌ ነበር:: ጻድቁ በሃገረ ስብከታቸው ወርደው በሐረርና ሱማሌ አካባቢ ለዘመናት የወንጌልን ዘር ዘርተው እልፍ ፍሬን አፍርተዋል:: አካባቢውንም መካነ ቅዱሳን አድርገውታል::

+ቀጥለው ገዳማዊ ሕይወትን ያጸኑ ዘንድ በምሥራቁ የሃገራችን ክፍል በአፋር ሱባኤ ገቡ:: ቦታውም ደብር ሐዘሎ ነበር:: በቦታው ለ155 ቀናት ከቆሙ ሳያርፉ: ከዘረጉ ሳያጥፉ: እህል ውሃ ሳይቀምሱ ጸለዩ::

+በሱባኤያቸው ፍጻሜ ግን ቅዱስ መልአክ መጥቶ "ሳሙኤል ወደዚያ ተራራ ሒድ:: የስምህ መጠሪያ እርሱ ነውና:: ይህ ግን የሌላ ሰው (የአባ አንበስ ዘሐዘሎ) ርስት ነው" አላቸው:: ጻድቁም ወዳላቸው ተራራ ሒደው ቢጸልዩ ከሰማይ ብርሃን ወረደላቸው::

+በመንፈቀ ሌሊት የበራው ብርሃን እስከ ጐረቤት መንደር ሁሉ በመድረሱ የአካባቢው ሰው "ወገግ አለኮ-ነጋ" ብለውዋል:: በዚህ ምክንያት ዛሬም "ደብረ ወገግ" ይባላል:: ይህ ቦታ ዛሬም ድረስ ንጹሕ ልብ ላላቸው አበው በብርሃን ተከቦ ይታያል::

+ጻድቁ የወለዷቸው ብዙ ሥውራንም በሥፍራው ይገኛሉ:: ቦታው የአንበሶች መኖሪያ በመሆኑ ጠላት መናንያኑን ማጥቃት አይችልም:: ሳሙኤል ዘወገግም የሚጸልዩት በአናብስት ተከበው ነበር::

+በቦታው አንዳንዴም አንበሶች ሲሰግዱ ይታያል ይባላል:: ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ግን እንዲህ በቅድስና ተመላልሰው በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ሱማሌ ክልል ውስጥ በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: የጻድቁ ልደት ሐምሌ 10: ፍልሠታቸው ደግሞ ግንቦት 27 ነው::

+"+ አባ ጸቃውዐ ድንግል +"+

=>እኒህ ጻድቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው:: የስማቸው ትርጉም "የድንግል ማርያም ወለላ ማር" ማለት ሲሆን ዜና ሕይወታቸው እንደ ስማቸው ጣፋጭ ነው::

+የእኒህ ጻድቅ አባታቸው የተመሰከረላቸው ሊቅና የገዳም መምሕር ናቸው:: ምክንያቱም ጸቃውዐ ድንግልን ከወለዱ በሁዋላ መንነዋልና:: አባት የደብረ ዘኸኝ መምሕር ሳሉ ልጃቸው ጸቃውዓ ድንግልን ወደ ገዳሙ ወስደው አሳደጉዋቸው::

+በዚያውም ጾምና ጸሎትን: ትዕግስትና ትሕርምትን አስተማሯቸው:: ቅዱሳት መጻሕፍትንም በወጉ አስጠኗቸው:: አባ ጸቃውዐ ድንከግልም በጐውን የምናኔ ጐዳና ከተማሩ በሁዋላ መዓርገ ምንኩስናን ተቀበሉ::

+40 ዓመት ሲሞላቸው ግን አባታቸው ዐረፉ:: መነኮሳት አበውም ተሰብስበው "ከአንተ የተሻለ የለም" ሲሉ ጸቃውዐ ድንግልን የደብረ ዘኸኝ መምሕር አድርገው ሾሟቸው:: ጻድቁም ቀን ቀን ሲያስተምሩ ይውሉና ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ ያድሩ ነበር::

+በሌሊትም ከባሕሩ ወጥተው የአካላቸው ርጥበት ደርቆ ላበታቸው እስኪንጠፈጠፍ ድረስ ይሰግዱ ነበር:: በዚህ መንገድም ራሳቸውን ገዝተው: መነኮሳትንም ገርተው ያዙ:: እግዚአብሔርም ክብራቸውን ይገልጽ ዘንድ ብዙ ተአምራትን በእጃቸው አሳይቷል::

+አንድ ቀን አባ ጸቃውዐ ድንግል መንገድ ሲሔዱ ሁለመናው በቁስል የተመታ አንድ መጻጉዕ ነዳይ ወድቆ አዩ:: ወደ እርሱ ሲደርሱ ምጽዋትን ለመናቸው:: ጻድቁ ግን "የምሰጥህ ነገር የለኝም:: ግን የፈጣሪየን ስጦታ እሰጥሃለሁ" ብለው: በውሃ ላይ ጸልየው ረጩት::

+ያ መጻጉዕም አካሉ ታድሶ: እንደ እንቦሳ ዘሎ ተነሳ:: ደስ እያለው: ፈጣሪውንም እያከበረ ወደ ቤቱ ሔዷል:: አባ ጸቃውዐ ድንግልም በዚህች ቀን ዐርፈው በገዳማቸው ተቀብረዋል::

+"+ ቅዱስ ድሜጥሮስ ሰማዕት +"+

=>ይህ ቅዱስ በዘመነ ሰማዕታት: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከነበሩ ክርስቲያኖች አንዱ ነው:: ቅዱስ ድሜጥሮስ ስቅጣር ከሚባል ደግ ባልንጀራው ጋር በበጐው ጐዳና ሲኖሩ የመከራው ዘመን ደረሰ:: መወሰን ነበረባቸውና ፈጣሪያቸውን ከሚክዱ ሞትን መረጡ::

+አስቀድሞም ሲያስተምር በመገኘቱ ቅዱስ ድሜጥሮስ በንጉሡ እጅ ወደቀ:: ንጉሡ መክስምያኖስም እሥራትን አዘዘበት:: በዚያ ወራት ደግሞ የንጉሡ ወታደር የሆነና በጣዖት የሚመካ አንድ ጉልበተኛ ነበር::

+ማንም በትግል አሸንፎት ስለማያውቅ ጣዖታዊው ንጉሥ ይመካበት ነበር:: አንድ ቀን ግን አንድ ክርስቲያን ወደ እሥር ቤት ገብቶ ቅዱስ ድሜጥሮስን "ባርከኝና ያንን ጣዖታዊ ጉልበተኛ እጥለዋለሁ" አለው::

+የቅዱሱን ጸሎትና በረከት ተቀብሎም በንጉሡ አደባባይ ታግሎ ጣለው:: ንጉሡና የጣዖቱ ካህናትም በእጅጉ አፈሩ:: በሁዋላ ግን ይህንን ያደረገው ቅዱስ ድሜጥሮስ መሆኑ በመታወቁ ከባልንጀራው ቅዱስ ስቅጣር ጋር በዚህች ቀን ገድለዋቸዋል::

=>አምላከ አበው ቅዱሳን ጸጋ ክብራቸውን ያብዛልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ጥቅምት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ሳሙኤል ጻድቅ (ዘደብረ ወገግ)
2.አባ ጸቃውዐ ድንግል (ዘደብረ ዘኸኝ)
3.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ስቅጣር ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት
2.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
3.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
4.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
5.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ
6.ቅድስት አርሴማ ድንግል

=>+"+ በእሸቅድምድም ሥፍራ የሚሮጡት ሁሉ እንዲሮጡ: ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ:: የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል:: እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው:: እኛ ግን የማይጠፋውን:: +"+ (1ቆሮ. 9:24)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/mahberememenan

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

07 Nov, 06:57


https://youtu.be/0K4AdCjCPU4?si=SHnPu4lCWRA9rzIx

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

27 Oct, 20:18


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ጥቅምት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

+" ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሊቅ "+

✞✞✞ በምድረ ግብጽ ከተነሱና ለቤተ ክርስቲያን አብዝተው ከደከሙ አባቶች አንዱ አባ ቴዎፍሎስ ነው:: የተወለደው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ሲሆን ቴዎፍሎስ (ታኦፊላ) በመባል ይታወቃል:: ገና ልጅ እያለ ቴዎዶስዮስ ከሚባል ባልንጀራው ጋ በተመሳሳይ ሌሊት ተመሳሳይ ሕልምን ያያሉ::

+2ቱ ሕጻናት ያዩት እንጨት ሲለቅሙ ነበር:: ሕልምን የሚተረጉመው ሰውም ቴዎዶስዮስን "ትነግሣለህ" ሲለው ቴዎፍሎስን "ፓትርያርክ ትሆናለህ" አለው:: ለጊዜው አልመሰላቸውም::

+ከዚያም ወደ ት/ቤት ገብተው: መጻሕፍትን ተምረው ቴዎዶስዮስ ወደ ንጉሡ ከተማ ቁስጥንጥንያ ሲሕድ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ግን የታላቁ ሊቅ አባ አትናቴዎስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: በዚያም ከቅዱሱ እየተማረ: እያገለገለ ዘመናት አለፉ::

+ቅዱስ አትናቴዎስ ካረፈ በኋላም ለ2 ፓትርያርኮች ረዳት ሆኖ ተመርጧል:: በመጨረሻ ግን ሕልም ተርጉዋሚው ያለው አልቀረምና ቴዎዶስዮስ 'ታላቁ' ተብሎ በቁስጥንጥንያ ላይ ሲነገሥ ቅዱስ ቴዎፍሎስም ፓትርያርክ (ሊቀ ዻዻሳት) ተብሎ በመንበረ ማርቆስ ላይ ተቀመጠ::

+በ384 ዓ/ም የእስክንድርያ 23ኛው ሊቀ ዻዻሳት ከሆነ በኋላ የመጀመሪያ ሥራው በዘመኑ ገነው የነበሩ መናፍቃንን መዋጋት ነበር:: ለዚህም ይረዳው ዘንድ የእህቱ ልጅ የሆነውን ቅዱስ ቄርሎስን ወስዶ አስተማረው:: 2ቱ አባቶች እየተጋገዙም ቤተ ክርስቲያንን ከአራዊት (መናፍቃን) ጠበቁ:: ዛሬ በሃይማኖተ አበው የምናውቀውን ጨምሮ ቅዱሱ በርካታ ድርሰቶችንም ደረሰ::

+ቅዱስ ቴዎፍሎስን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል ጥቂቶቹን እንመልከት:-

1.ቅዱሱ በዘመኑ ከመንበረ ዽዽስናው በር ቁጭ ብሎ ይተክዝ ነበርና አንዲት ባለ ጸጋ ሴት መጥታ "አባቴ! ምን ያስተክዝሃል?" ስትል ጠየቀችው::

+ሊቁም "ልጄ! እዚህ የቆምንበት ቦታ ውስጥ ወርቅ ተቀብሮ ሳለ ነዳያን ጦማቸውን ያድራሉ:: አባቴ አትናቴዎስ እንዳዘነ አለፈ:: እኔም ያው ማለፌ ነው" አላት:: ባዕለ ጸጋዋም "አባ አንተ ጸሎት: እኔ ጉልበትና ሃብት ሁነን እናውጣው" አለችው::

+"እሺ" ብሏት ሱባኤ ገባና ከመሬት በታች 3 ጋን ሙሉ ወርቅ ተገኝቶ ደስ አላቸው:: ግን በላያቸው ላይ ተመሣሣይ "ቴዳ: ቴዳ: ቴዳ" የሚል ጽሑፍ ነበረውና ማን ይፍታው:: በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ወደ እመቤታችን አመልክቶ ምሥጢር ተገለጠለትና ሲተረጉመው ማሕተሞቹ ተፈቱ::

+ሲተረጐምም ቴዳ 1 "ክርስቶስ" ማለት ሆነ:: ይሔም ለነዳያን ተበተነ:: ቴዳ 2 "ቴዎፍሎስ" ማለት ሆነ:: አብያተ ክርስቲያናት ታነጹበት:: ቴዳ 3 ደግሞ "ቴዎዶስዮስ" ሆነ:: 'የቄሣርን ለቄሣር' እንዲል 3ኛው ጋን የአቡነ ኪሮስ ወንድምና የገብረ ክርስቶስ መርዓዊ አባት ለሆነው ለደጉ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ተላከለት::

+ንጉሡ ግን ከወርቁ ጥቂት ለበረከት ወስዶ ለአባ ቴዎፍሎስ መለሰለት:: አብያተ ጣዖቶችን እያፈረሰ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲያንጽም ስልጣን ሰጠው:: ቅዱስ ቴዎፍሎስም በዚህ ገንዘብ በመቶ የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናትን እንዳነጸበት ይነገራል::

+በተለይ ደግሞ የቅዱስ ሩፋኤልን ቤት በአሣ አንበሪ ጀርባ ላይ ያነጸው እርሱ ነው:: (ድርሳነ ሩፋኤል) የድንግል ማርያምን ሲያንጽም እመቤታችን ተገልጣለታለች::

+የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቁን አጽም አፍልሦ ከነቢዩ ኤልሳዕ ጋር ቤቱን ሲቀድስለትም ተአምራት ተደርገዋል:: የሠለስቱ ደቂቅን ቤተ ክርስቲያን አንጾ የቀደሰ ጊዜ ደግሞ ቅዱሳኑ ከሰማይ ወርደውለታል::

2.ቅዱስ ቴዎፍሎስ እመቤታችንን ይወዳት ነበርና ለ8 ጊዜ ያህል ተገልጣ አነጋግራዋለች:: "ደፋሩ አርበኛ" ስትል ጠርታ: ሙሉ ዜና ስደቷንና ሕይወቷን አጽፋዋለች:: (ተአምረ ማርይም)
3.ሕጻናትን ሲያጠምቅም ከብቃት የተነሳ የብርሃን መስቀል ይወርድለት ነበር:: ቅዱስ ቴዎፍሎስ በሊቀ ዽዽስና በቆየባቸው 28 ዓመታት እንዲህ ተመላልሶ በ412 ዓ/ም ዐርፎ ቅዱስ ቄርሎስ በመንበሩ ተተክቷል:: ነገር ግን አንዳንድ የዘመናችን 'ጸሐፊ ነን ባዮች' የመናፍቃንን መጻሕፍት እየገለበጡ ቅዱሱን ይሳደባሉና ብንጠነቀቅ እመክራለሁ::

+" ቅዱስ ሮማኖስ ሰማዕት "+

✞✞✞ ይህ ቅዱስ ሰማዕት ብዙ ጊዜ "ኃያሉ" እየተባለ ነው የሚጠራው:: በዘመነ ሰማዕታት ከራሱ አልፎ ብዙ ክርስቲያኖችን በድፍረት ያጸናቸው ነበር:: በወቅቱ በምድረ ግብጽ መከራው እጅግ ስለ በዛ ብዙዎቹ አልቀው: እኩሉም ተሰደው: አንዳንዶቹ ደግሞ መካዳቸውን ሲሰማ ቅዱሱ ለጸሎት ከተወሰነበት ቦታ ወጥቶ: ሕዝቡን ሰብስቦ መከራቸው::

+"ወገኖቼ! ልቡናችንን በክርስቶስ ፍቅር ካጸናነው ሞት ቀላልና አስደሳች ነገር ነው" ብሎም አበረታታቸው:: ይህን የሰማ መኮንኑ ግን ተቆጥቶ አስጠራው:: በዓየር ላይ ዘቅዝቆም ኢ-ሰብአዊ በሆነ ጭካኔ ደሙ እስኪንጠፈጠፍ ድረስ አሰቃየው::

+ይህ ሁሉ እየሆነበት ቅዱስ ሮማኖስ ልቡ በአምላኩ ፍቅር ተመስጦ ነበርና አንዳች አልመለሰም:: መኮንኑ ግን ገርሞት "እንዴት ይህ ሁሉ እየሆነብህ ዝም አልክ?" ቢለው የ3 ዓመት ሕጻን ጥራና ስለ እውነተኛው አምላክ ጠይቀው" አለው::

+አንድ ሕጻን አስመጥቶ በአደባባይ ጠየቀው:: ሕጻኑም መለሰና "አዕምሮ የጐደለህ መኮንን ሆይ! አስተውል:: ከክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ሲል ገሰጸው:: መኮንኑ በቁጣ ሕጻኑን በዓየር ላይ አሰቅሎ አስገረፈው:: ሕጻኑ ሕጻኑ ደሙ ሲፈስ እናቱን "ውሃ አጠጪኝ?" አላት:: እርሷ ግን "ልጄ! እኔ ውሃ የለኝም:: ወደ ሕይወት ውሃ ክርስቶስ ሒድ" አለችው::

+በዚያን ጊዜ መኮንኑ የሕጻኑን ራስና የቅዱስ ሮማኖስን ምላስ አስቆረጠ:: ቅዱሱ ግን መንፈሳዊ ልሳን ተሰጥቶት ፈጣሪውን አመሰገነው:: የሚያደርገውን ያጣው መኮንኑም በዚህ ዕለት ቅዱሱን ገድሎታል::

✞✞✞ አምላከ ቅዱሳን ጸጋውን ክብሩን አይንሳን:: የአባቶቻችንንም በረከት ያብዛልን::

+ጥቅምት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሊቅ
2.ቅዱስ ሮማኖስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ዮሐንስ ሰማዕት
4.ቅድስት አስማኒትና 7ቱ ልጆቿ

በ 18 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
 

++"+ ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን: ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን:: ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን:: +"+ (ሮሜ. 6:5)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/mahberememenan

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

27 Oct, 01:23


https://youtu.be/4SsCTW5Mbe0?si=KCt_jmVQSuOqrAkt

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

26 Oct, 21:51


=>አምላከ ቅዱሳን የእስጢፋኖስን ጸጋ: የፊልያስን ማስተዋልና የሐናን በጐነት ያሳድርብን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::=>ጥቅምት 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ወቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ፊልያስ ሰማዕት
3.ቅድስት ሐና ነቢይት
4.ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ
5.የደብረ ሊባኖስ ሰማዕታት (ካቶሊካውያን የገደሏቸው)
6.ቅዱሳን ሔራን ሰማዕታት
7.አባ ዲዮስቆሮስ ካልዕ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
2.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
3.አባ ገሪማ ዘመደራ
4.አባ ዸላሞን ፈላሢ
5.አባ ለትጹን የዋህ
6.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ)

=>+"+ እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር . . . አንዳንዶቹ ተነስተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር:: ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም:: በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ: በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሱ . . . በሸንጐም የተቀመጡት ሁሉ ትኩር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት:: +"+ (ሐዋ. 6:8-15)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/mahberememenan

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

26 Oct, 21:51


+ እንኩዋን ለቅዱስ "እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት": ለቅዱስ "ፊልያስ" እና ለቅድስት "ሐና ነቢይት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+*" ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት "*+

=>በሕገ ወንጌል (ክርስትና) የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ይህ ቅዱስ ነው:: ቅዱሱ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም ይባላሉ:: (ሌሎች ናቸው የሚሉም አሉ) ገና ከልጅነቱ ቁም ነገር ወዳድ የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ እድሜው ሲደርስ ወደ ት/ቤት ገባ:: የወቅቱ ታላቅ መምሕር ገማልያል ይባል ነበር:: ይህ ሰው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5:33 ላይ ተጠቅሷል::

+በትውፊት ትምሕርት ደግሞ ይህ ደግ (ትልቅ) ሰው በርካታ ቅዱሳንን (እስጢፋኖስን: ዻውሎስን: ናትናኤልን: ኒቆዲሞስን . . .) አስተምሯል:: በጌታችን መዋዕለ ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየቀረበ ይጨዋወት ነበር:: በፍጻሜውም አምኗል::

+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ: ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ ወጣ:: ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር::

+በወቅቱ ደግሞ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሃ ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነገሩን መረመረ:: ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: ለ6 ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ::

+ለ6 ወራት ከቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በሁዋላ ለስም አጠራሩ ስግደት ይድረሰውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠመቀ::
በወቅቱ የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ እስጢፋኖስ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ጠየቀው::

+"ከእኔ ይልቅ ከፈጣሪው አንደበት ይስማው" በሚል ላከው:: ቅዱሱም ከጌታ ዘንድ ሔዶ: እጅ ነስቶ ተማረ:: (ሉቃ. 7:18) በዚያውም የጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ:: ጌታም ከ72ቱ አርድእት አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው:: አጋንንትም ተገዙለት:: (ሉቃ. 10:17)

+ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ከዋለበት እየዋለ: ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ:: ምሥጢር አስተረጐመ:: ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ ከተነሳ በሁዋላ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ባርኩዋል::

+በዚህ ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ቅስናን (ዽዽስናን) ተሹሟል:: በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ72ቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት: ምሥጢርም የተገለጠለት የለም:: በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን ይሰብክ ገባ::

+በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ 7 ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: አልፎም የ6ቱ ዲያቆናት አለቃ እና የ8ሺው ማሕበር መሪ (አስተዳዳሪ) ሆኗል::

+8ሺ ሰውን ከአጋንንት ፈተና መጠበቅ ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነ ለማወቅ አባቶቻችንን መጠየቅ ነው:: አንድን ሰው ተቆጣጥሮ ለድኅነት ማብቃት እንኩዋ እጅግ ፈተና ነው:: መጽሐፍ እንደሚል ግን "መንፈስ ቅዱስ የሞላበት: ማሕደረ እግዚአብሔር" ነውና ለእርሱ ተቻለው:: (ሐዋ. 6:5)

+አንዳንዶቻችን ቅዱስ እስጢፋኖስ "ሊቀ ዲያቆናት" ሲባል እንደ ዘመኑ ይመስለን ይሆናል:: እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው:: ዲቁናው ለእርሱ "በራት ላይ ዳረጐት" ነው እንጂ እንዲሁ ዲያቆን ብቻ አይደለም::

+ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በሁዋላ ለ 1 ዓመት ያህል 8ሺውን ማሕበር እየመራ: ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት "እጠፋ እጠፋ": ወንጌል ደግሞ "እሰፋ እሰፋ" አለች:: በዚህ ጊዜ "ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው" ብለው አይሁድ በማመናቸው ሊገልድሉት አስበውም አልቀሩ ገደሉት::

+እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው:: በመጨረሻውም ስለ እነሱ ምሕረትን እየለመነ በድንጋይ ወገሩት:: ደቀ መዛሙርቱም ታላቅ ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት::

+ይህች ዕለት ለቅዱስ እስጢፋኖስ በዓለ ሲመቱ ናት:: ቅዱሱ መጽሐፍ እንደሚል "ምሉዓ ጸጋ ወሞገስ-ሞገስና ጸጋ የሞላለት" (ሐዋ. 6:5, ቅዳሴ ማርያም) ነውና የ6ቱ ዲያቆናት አለቃና የ8ሺው ማሕበር መሪ ሆኖ ተመርጦ እንደሚገባ አገልግሏል:: በሰማይ ባለችው መቅደስም የሚያገለግለው በዚሁ ማዕረጉ ነው::

+"+ ቅዱስ ፊልያስ ሰማዕት +"+

=>ሰማዕቱ የነበረበት ዘመን 3ኛው መቶ ክ/ዘ (ዘመነ ሰማዕታት) ሲሆን ቀምስ ለምትባል የግብጽ አውራጃም ዻዻስ ነበር:: ቅዱሱ እጅግ ጻድቅ በዚያውም ላይ ክቡርና ተወዳጅ ሰው ነበር:: የመከራው ዘመን ሲመጣ በቃሉ ያስተማራቸውን እንደ በጐ እረኝነቱ በተግባር ይገልጠው ዘንድ ወደ መኮንኑ ሔደ::

+ሕዝቡ በአንድነት ተሰብስበው ሳለ መኮንኑ ቁልቁልያኖስ ቅዱስ ፊልያስን 4 ጥያቄዎችን ጠየቀው:: ምላሾቹ ለእኛ ሕይወትነት ያላቸው ናቸውና እንመልከታቸው::

1."የእናንተ እግዚአብሔር ምን ዓይነት መስዋዕትን ይሻል?" ቢለው "ልበ ትሑተ: ወመንፈሰ የዋሃ: ወነገረ ሕልወ: ወኩነኔ ጽድቅ: ዘከመዝ መስዋዕት ያሠምሮ ለእግዚአብሔር-እግዚአብሔርን ትሑት ልቦና: የዋህ ሰብእና: የቀና ፍርድና ቁም ነገር ደስ ያሰኘዋል" ሲል መለሰለት::

2."የምትወዳቸው ሚስትና ልጆች የሉህም?" ሲለው ደግሞ "እምኩሉ የአቢ ፍቅረ እግዚአብሔር - ከሁሉ የእግዚአብሔር ፍቅር ይበልጣል" አለው::

3."ለነፍስህ ትጋደላለህ ወይስ ለሥጋህ?" ቢለው "ለ2ቱም እጋደላለሁ:: አምላክ በአንድነት ፈጥሯቸዋልና:: በትንሳኤ ዘጉባኤም ይዋሐዳሉና" ብሎታል::

4."አምላካችሁ የሠራው ምን በጐ ነገር አለ?" ብሎትም ነበር:: ቅዱስ ፊልያስ መልሶ: "አስቀድሞ ፍጥረታትን በጥንተ ተፈጥሮ ፈጠረ:: በሁዋላም በሐዲስ ተፈጥሮ ያከብረን ዘንድ ወርዶ ሞተልን: ተነሣ: ዐረገ" ቢለው መኮንኑ "እንዴት አምላክ ሞተ ትላለህ!" ብሎ ተቆጣ:: ቅዱሱም "አዎ! በለበሰው ሥጋ ስለ እኛ ሙቷል" ብሎ እቅጩን ነገረው::

+ወዲያውም "እስከ አሁን የታገስኩህ በዘመድ የከበርክ ስለሆንክ ነው" ቢለው ቅዱሱ መልሶ "ክብሬ ክርስቶስ ነው:: መልካምን ካሰብክልኝ ቶሎ ግደለኝ" አለው:: በዚያን ጊዜ የሃገሩ ሰዎች "አትሙትብን! እባክህን ለመኮንኑ ታዘዘው?" ሲሉ ለመኑት::

+ቅዱስ ፊልያስ "እናንተ የነፍሴ ጠላቶች ዘወር በሉ ከፊቴ! እኔ ወደ ክርስቶስ ልሔድ እናፍቃለሁና" ብሎ ገሰጻቸው:: መኮንኑም ወስዶ ከብዙ ስቃይ ጋር ገድሎታል::

+"+ ቅድስት ሐና ነቢይት +"+

=>"ሐና" ማለት "የእግዚአብሔር ስጦታ" ማለት ነው:: እጅግ ከሚታወቁ ሴት ነቢያት አንዷ የሆነችው ቅድስት ሐና ከክርስቶስ ልደት 1,100 ዓመታት በፊት በዚህች ቀን እንደ ተወለደች ይታመናል:: ቅድስቲቱ ልጅ በማጣት ተቸግራ: ከጐረቤት እስከ ሊቀ ካህናቱ ኤሊ ድረስ ሽሙጥና ስድብን ታግሣ ታላቁን ነቢይ ቅዱስ ሳሙኤልን ወልዳለች::
+በሐረገ ትንቢቷም:-
"ኢይጻእ ዐቢይ ነገር እምአፉክሙ: እስመ እግዚአብሔር አምላክ ማዕምር ውዕቱ - እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ አምላክ ነውና ከአንደበታችሁ (ጽኑዕ) ነገርን አታውጡ" ስትል ተናግራለች:: (ሳሙ. 2:3)

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

26 Oct, 14:25


https://youtu.be/MCoLzENIfTI?si=S1FmGBwpAY-zzaHd

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

26 Oct, 11:59


https://youtu.be/W-_A0mrKBJo

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

25 Oct, 19:49


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ጥቅምት ፲፮ (16) ❖

✞✞✞ እንኩዋን አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ 7ቱ ኪዳናት ወአባ ያቃቱ ሊቀ ዻዻሳት +"+

+"+ 7ቱ ኪዳናት +"+

=>"ተካየደ" ማለት "ተስማማ: ተማማለ" እንደ ማለት
ሲሆን "ኪዳን" በቁሙ "ውል: ስምምነት" እንደ ማለት
ነው:: ይኸውም እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር: ሰዎችም
ከሰዎች ጋር የሚያደርጉት ሊሆን ይችላል:: ልዩነቱ
የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ቅዱስና የማይለወጥ መሆኑ ነው::

+እግዚአብሔር አምላክ ከሥነ ፍጥረት ጀምሮ በየጊዜው
ከብዙ ወዳጆቹ ጋር ኪዳንን አድርጉዋል:: ቅድስት ቤተ
ክርስቲያንም እነዚህን ኪዳናት ጥቅልል አድርጋ 7 እንደ
ሆኑ ታስተምራለች:: ስለዚህም ዛሬ ፈጣሪ ቢረዳን
እነዚሁን 7 ኪዳናት በጥቂቱ እንመለከታለን::
"ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ"
"ከመረጥኩዋቸው ጋር ቃል ኪዳንን አደረግሁ" (መዝ. 88:3)

(1) +"+ ኪዳነ አዳም +"+

=>አዳም ማለት የእግዚአብሔር ድንቅ ፍጥረት:
የፍጡራን አስተዳዳሪ: ነቢይ: ካህንና ንጉሥ ነው::
እግዚአብሔር ከአዳም ጋር አስቀድሞ በእጸ በለስ
አማካኝነት ቃል ኪዳን ነበራቸው:: ነገር ግን አባታችን
በዲያብሎስ ሴራ በመረታቱ ኪዳኑ ፈረሰ:: (ዘፍ. 3:1)

+አዳምና ሔዋን ተጸጽተው ቢያለቅሱ ግን አዲስ የኪዳን
ተስፋ: "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ኪዳንን
ተቀበሉ:: (ቀሌምንጦስ: ገላ. 4:4)

(2) +"+ ኪዳነ ኖኅ +"+

=>ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ባሉት 10 ትውልድ ዓለም
በዓመፃ ተሞላች:: ቅዱስ ኖኅ በደግነቱ መርከብ ሠርቶ
ቤተሰቡን ሲያተርፍ ዓለም በማየ ሥራዌ ጠፋች::
ከመርከቡ ከወጣ በሁዋላ ኖኅና እግዚአብሔር በቀስተ
ደመና ምልክትነት ቃል ኪዳን ተጋቡ:: "ኢያማስና
ለምድር ዳግመ በማየ አይኅ" እንዲል:: (ዘፍ. 9:12)

(3) +"+ ኪዳነ መልከ ጼዴቅ +"+

=>መልከ ጼዴቅ የእግዚአብሔር ካህኑ: የክርስቶስም
ምሳሌው የሆነ የሳሌም ንጉሥ ነው:: በ15 ዓመቱ
መንኖ: አጽመ አዳምን ይዞ: በቀራንዮ በሕብስትና በወይን
ያስታኩት ነበር::

+እግዚአብሔር ለመልከ ጼዴቅ: በሐዲስ ኪዳን
ለምትሠራው ክህነትና ምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ አድርጐ
በቃል ኪዳን አትሞታል:: በዚህም ተሰውሮ ይኖራል እንጂ
ሞትን እስካሁን አልቀመሰም:: ይህም ካህኑ መልከ
ጼዴቅ ከአብርሃም ጋር በተገናኙበት ጊዜ ተገልጧል:: (ዘፍ. 14:17, ዕብ. 7:1)

(4) +"+ ኪዳነ አብርሃም +"+

=>ቅዱስ አብርሃም የሕዝብና የአሕዛብ አባት: ሥርወ
ሃይማኖት: የጽድቅም አበጋዝ ነው:: ስለ ፍቅረ
እግዚአብሔር ሲል ከርስቱና ከወገኖቹ ተለይቶ በቅድስና
ኑሯልና እግዚአብሔር "በዘርሕ አሕዛብ ይባረካሉ"
አለው:: (ዘፍ. 12:1) የቃል ኪዳን ምልክትም ይሆነው
ዘንድ ግዝረትን ሰጠው:: (ዘፍ. 17:1-14)

(5) +"+ ኪዳነ ሙሴ +"+

=>ቅዱስ ሙሴ የነቢያት አለቃ: የእሥራኤል እረኛ:
የእግዚአብሔር ሰው እና ፍጹም ትሑት (የዋህ) ሰው
ነው:: በፈጣሪው ትዕዛዝ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት
አውጥቶ ለ40 ዘመናት በበርሃ ሲመራቸው
ከእግዚአብሔር የኪዳንን ጽላትና አሠርቱን ትዕዛዛት
ተቀብሏል:: (ዘጸ. 20:1, 31:18)

(6) +"+ ኪዳነ ዳዊት +"+

=>ቅዱስ ዳዊት ሥርወ ነገሥት: ጻድቅ: የዋህና ቡሩክ
የሆነ አባት ነው:: እግዚአብሔር ከእረኝነት ጠርቶ ንጉሥ
አድርጐ ሹሞት "ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ
አኖራለሁ" (መዝ. 131:11) ሲል ምሎለታል:: አክሎም
ሰፊ ቃል ኪዳን ሰጥቶ "አልዋሰሽህም" ብሎ ሲምልለት
እንመለከታለን:: (መዝ. 88:35)

(7) +"+ ኪዳነ ምሕረት +"+

=>በብሉይ ኪዳን የነበሩ 6ቱ ኪዳናት በዘመናቸው ክቡርና
ሕዝቡን ከመቅሰፍት ይታደጉ የነበሩ ቢሆንም ከሲዖል
ማዳን ግን አልቻሉም:: ስለዚህም አንድ ፍጹም ኪዳን
ያስፈልግ ነበር:: ይህን ፍጹም ኪዳን ይፈጽም ዘንድም
ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል
ማርያም ማሕጸን አደረ::

+በፍጹም ተዋሕዶም በሕቱም ድንግልና ተወልዶ: አድጎ:
ተጠምቆ: አስተምሮ: ሙቶ: ተነስቶና ዐርጐ ሥጋ
ማርያምን በዘባነ ኪሩብ አስቀመጠው:: ኪዳነ ምሕረት
(የምሕረት ኪዳን) የምንለው አንዱ ታዲያ ይሔው ነው::

+የጌታችን መጸነሱ: መወለዱ: መሰደዱ: መጠመቁ:
ማስተማሩ: ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ: መሰቀሉ:
መሞቱና መነሳቱ: ማረጉና መንፈስ ቅዱስን መላኩ
በአንድ ላይ ኪዳነ ምሕረት ይባላል:: ታዲያ ይህ ሁሉ
የተደረገው በሥጋ ማርያም ነውና የኪዳኑ ባለቤት
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት::

+የእርሷ ኪዳን የ6ቱን አበው ኪዳናት ፍጹም በማድረጉ
"የኪዳናት ማሕተም" ይባላል:: የድንግል ማርያም ኪዳኗ
ከሲዖልና ከገሃነም ሊታደገን አቅሙ አለውና::
መድኃኒታችን ክርስቶስ ለድንግል እናቱ ቃል ኪዳኑን
ያጸናላት ደግሞ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ ጐልጐታ ላይ ነው::

+እመ ብርሃን በዚያ ቁማ ስለ ኃጥአን ስታለቅስ "እናቴ
ሆይ! በስምሽ ያመነውን: በቃል ኪዳንሽ የተማጸነውን
እምርልሻለሁ" ብሎ ደስ አሰኝቷታልና:: ይሔው በእመ
ብርሃን ምልጃና ቃል ኪዳን ምዕመናን ከመቅሰፍትና
ከገሃነመ እሳት ማምለጥ ከጀመሩ 2ሺ ዓመታት ሆኑ::
ዛሬም እኛ ኃጥአን ልጆቿ ከእሳት እንደምታድነን አምነን
በጥላዋ ሥር እንኖራለን::

*" ኢትዝክሪ ብነ አበሳነ: ኃጢአተነ: ወጌጋየነ፡፡
ማርያም እሙ ለእግዚእነ፡፡
በኪዳንኪ: ወበስደትኪ ድንግል ተማሕጸነ:: "*

"ድንግል ሆይ! ኃጢአታችን: አበሳችንና በደላችንን
አታስቢብን ዘንድ በስደትሽና በኪዳንሽ ተማጽነናል::"

=>ቸሩ ልጇ ከበረከተ ኪዳኗ አይለየን::

+"+ አባ ያቃቱ ሊቀ ዻዻሳት +"+

=>በምድረ ግብጽ ከተነሱና ለመንጋው ከራሩ አበው
ዻዻሳት አንዱ አባ ያቃቱ ናቸው:: አባ ያቃቱ መጻሕፍትን
የተማሩ: በገዳምም የኖሩ በመሆናቸው እንደ
ቀደምቶቻቸው ቤተ ክርስቲያኗን በቅን መርተዋል::

+ፓትርያርክ ሆነው ከተሾሙ በሁዋላ ብዙ ጭንቅ ያሳለፉ
ሲሆን እግዚአብሔር አቅሎላቸዋል:: ከማረፋቸው
በፊትም ከእርሳቸው ቀጥለው የሚሾሙትን በጸጋ
ተናግረዋል:: አባ ያቃቱ ለግብጽ 49ኛ ሊቀ ዻዻሳት
ናቸው::

=>በረከታቸው ይደርብን::

=>ጥቅምት 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.አባ ያቃቱ ሊቀ ዻዻሳት
2.ጻድቃን እለ ድርቂ
3.አባ ዻውሊ ገዳማዊ
4.አባ ማርቆስ መስተጋድል
5.አባ አሮን መስተጋድል

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ (የቅ/ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዳንኤል ጻድቅ
7.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ጻድቅ (ወንጌሉ ዘወርቅ)

=>+"+ የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ::
ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው::
ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው::
በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . .
በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ::
በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ::
ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ:: +"+ (መዝ.
44:12-17)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/mahberememenan

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

25 Oct, 17:08


https://youtu.be/W-_A0mrKBJo?si=FfWX60UCK77naYe4

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

24 Oct, 22:04


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለአባቶቻችን ቅዱሳን "12ቱ ሐዋርያት" እና ለቅዱስ "ቢላሞን ሰማዕት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ ቅዱሳን 12ቱ ሐዋርያት +"+

=>በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከእመቤታችን በቀር ከቅዱሳን ሐዋርያት የሚበልጥ አልተነሳም:: "ሐዋርያ" ማለት "ፍንው: ልዑክ: የተላከ: የጽድቅ መንገደኛ" እንደ ማለት ነው:: በምሥጢሩ ግን "ባለሟል" ብለው ሊቃውንቱ ተርጉመውታል::

+ይህስ እንደምን ነው ቢሉ:-

¤የፍጥረታት ሁሉ ጌታ: የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ከድንግል ማርያም ተወልዶ: አድጐ: ተጠምቆ: ጾሞ: ከገዳመ ቆረንቶስ ሲመለስ ቀዳሚ ሥራው ያደረገው ደቀ መዛሙርቱን መጥራት ነበር::

+ከተከተሉት የ5 ገበያ ሕዝብ መካከል "ወሐረየ እምሰብአ ዚአሁ አሠርተ ወክልኤተ ሐዋርያተ" እንዲል በመጀመሪያ 12ቱን ሐዋርያት መረጠ::

+እሊህም:-
1.ዼጥሮስ የተባለ ስምኦን
2.እንድርያስ (ወንድሙ)
3.ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
4.ዮሐንስ (ወንድሙ)
5.ፊልዾስ
6.በርተሎሜዎስ
7.ቶማስ
8.ማቴዎስ
9.ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ
10.ታዴዎስ (ልብድዮስ)
11.ናትናኤል (ቀናተኛው ስምዖን) እና
12.ማትያስ (በይሁዳ የተተካ) ናቸው:: (ማቴ. 10:1)

+እነዚህን 12 አርድእቱን ከጠራ በሁዋላ ለ3 ዓመታት ከ3 ወራት ከዋለበት ሲማሩ ይውሉ ነበር:: ሌሊት ደግሞ ምሥጢር ሲያስተረጉሙ ያድሩ ነበር::

+ጌታ እንደሚገባ ካስተማራቸው በሁዋላ ከፍ ያለ ኃላፊነትን ሾማቸው:: ለዓለም እረኞች: የእርሱም ባለሟሎች ሆኑ:: እጅግ ብዙ መከራ እንደሚገጥማቸው ነገራቸው:: (ማቴ. 10:16, ዮሐ. 16:33) በዚያው ልክ ክብራቸውንም አከለላቸው:: (ማቴ. 19:28)
+ሥልጣናቸው ደግሞ እስከዚህ ድረስ ሆነ:: "በምድር ያሠራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል: በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል::" (ማቴ. 18:18) "ይቅር ያላችሁዋቸው ኃጢአታቸው ይቀርላቸዋል: ያላላቹሃቸው ግን አይቀርላቸውም::" (ዮሐ. 20:23)

+የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ (ማቴ. 16:19): እረኝነትን (ዮሐ. 21:15) ተቀበሉ:: ጌታ በንጹሕ አንደበቱ ሐዋርያቱን እጅግ ሲያከብራቸው "ጨው: የዓለም ብርሃናት" (ማቴ. 5:13) አላቸው:: ወንድሞቹም ተባሉ:: (ዮሐ. 7:5) ከዚህም በሚበልጥ በሌላ ክብር አከበራቸው::

+ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ በጌታ ሕማማት ጌዜ ገና ነበሩና አንዳንዶቹ ፈርተው ተበተኑ:: ተመልሰው ግን በጽርሐ ጽዮን ሲጸልዩ ሰንብተው የጌታን ትንሳኤ ተመለከቱ:: እጆቹን: እግሮቹንም ዳስሰው ሐሴትን አደረጉ::

+ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓት: ሌላም በፍጡር አንደበት የማይነገር ብዙ ምሥጢራትን ተምረው: ጌታ ሊቀ ዽዽስናን ሹሟቸው ዐረገ::

+ለ10 ቀናት በእመ ብርሃን ሥር ተጠልለው ሲጸልዩና በአንድ ልብ ሲተጉ ሰንብተው መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው:: በአንዴም ከፍርሃት ወደ ድፍረት ተመልሰው ፍጹማን: ብርሃናውያን ሆኑ:: 71 ልሳናትን ነስተው በአንዲት ስብከት ብቻ 3ሺ ነፍሳትን ማረኩ:: (ሐዋ. 2:41)

+ቅዱሳን ሐዋርያት በኅብረት ለአንድ ዓመት ያህል በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ እየተመላለሱ አስተምረው ብዙ እሥራኤላውያንን ወደ ክርስትና ማርከዋል:: ከዚህ በሁዋላ ግን እንደ ትውፊቱ በዚህች ቀን ዓለምን በእጣ ለ12 ተካፈሏት::

+ይህ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ አብሯቸው ነበርና ለእያንዳንዳቸው እንደሚገባቸው አሕጉረ ስብከቶች ደረሷቸው:: እነርሱም ደቀ መዛሙርቶቻቸውን አስከትለው ለታላቁ መንፈሳዊ ዘመቻ ወረዱ::
+በሔዱበት ቦታም ከተኩላ: ከአንበሳና ከነምር ጋር ታገሉ:: በጸጋቸውም አራዊትን (ክፉ ሰዎችን) ወደ በግነት መልሰው ለክርስቶስ አስረከቡ:: በየሃገሩ እየሰበኩ ድውያንን ፈወሱ:: ለምጻሞችን አነጹ:: እውራንን አበሩ:: አንካሶችን አረቱ:: ጐባጦችን አቀኑ:: ሙታንንም አስነሱ:: እልፍ አእላፍ አሕዛብንም ወደ መንጋው ቀላቀሉ::

+ስለዚህ ፈንታም ብዙዎቹ በእሳት ተቃጠሉ:: ቆዳቸው ተገፈፈ:: በምጣድ ተጠበሱ:: ደማቸው በምድር ላይ ፈሰሰ:: ከአንድ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በቀር ሁሉም ይህችን ዓለም በሰማዕትነት ተሰናበቱ:: ጨው ሆነው አጣፍጠዋልና: ብርሃንም ሆነው አብርተዋልና እናከብራቸዋለን:: "አባቶቻችን: መምሕሮቻችን: ጌቶቻችንና ሊቆቻችን" እንላቸዋለን::

+"+ ቅዱስ ቢላሞን ሰማዕት +"+

=>በዘመነ ሰማዕታት የነበረው ቅዱስ ቢላሞን በወቅቱ ይታወቅ የነበረው በክርስቲያንነቱ ሳይሆን በፈላስፋነቱ ነበር:: እጅግ የተማረ ጥበበኛ: ግን ደግሞ ወገኑ ከኢ-አማንያን በመሆኑ ክርስቶስን አያውቀውም ነበር::

+እግዚአብሔር ግን እንዲጠፋ አልፈቀደምና አንድ ካህንን ላከለት:: ከመቀራረብ የተነሳ ብዙ ስለተነጋገሩ ቢላሞን ወደ ክርስትና እየተሳበ ሔደ:: በመጨረሻም ተምሮ በካህኑ እጅ ተጠምቁዋል:: ቀጥሎም ይጾም: ይጸልይ: ይጋደል ነበር::

+በትንሽ ጊዜም ከጸጋ ደርሶ ድውያንን ይፈውስ ገባ:: ብዙ አሕዛብን እያስተማረ: ከደዌአቸውም እየፈወሰ ወደ ክርስትና መለሳቸው:: አንድ ቀን ግን "ዐይነ ሥውር አብርተሃል" በሚል ተከሶ ሞት ተፈረደበት::

+ከመገደሉ በፍትም ጌታችን ከሰማይ ወርዶ "ወዳጄ!" ሲለው ወታደሮች ሰሙ:: በዚህ ምክንያት አምነው በዚህች ቀን 158 ወታደሮች አብረውት ተሰይፈዋል::
=>አምላከ ቅዱሳን ሐዋርያት ቸርነቱን: ምሕረቱን ያብዛልን:: በምልጃቸው ሃገራችንን ከክፉ ጠብቆ ከበረከታቸው ይክፈለን::

=>ጥቅምት 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1."12ቱ" ቅዱሳን ሐዋርያት
2.ቅዱስ ቢላሞን ሰማዕት
3."158" ሰማዕታት (የቅዱስ ቢላሞን ማሕበር)
4.ቅዱስ ሲላስ ሐዋርያ
5.ቅድስት ጾመታ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
2.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
3.ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ
4.ቅድስት እንባ መሪና
5.ቅድስት ክርስጢና

=>+"+ በዚያን ጊዜ ዼጥሮስ መልሶ:- 'እነሆ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ:: እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን?' አለው:: ጌታ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው:- 'እውነት እላቹሃለሁ! እናንተስ የተከተላችሁኝ በዳግመኛ ልደት: የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእሥራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ:: +"+ (ማቴ. 19:27)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/mahberememenan

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

23 Oct, 19:13


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ጥቅምት 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

✞✞✞ አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ ✞✞✞

✞✞✞ በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው:: ጻድቁ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅና ቅድስት እድና ይባላሉ:: የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው::

+ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው:: ወላጆቻቸው ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረ አምላክ ተብለዋል:: በኢትዮዽያ ደግሞ አረጋዊ ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ::

+በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል:: ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር 7 ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል::

+"የት ልሒድ" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው:: ተመልሰውም ለ8 ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር" ብለው ከ8ቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ::

+በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ:: ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል:: በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ: ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል::

+ለሥራ በተለያዩ ጊዜም አቡነ አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል:: በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት:: የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል::

+እንደ ወጡም "ሃሌ ሉያ ለአብ: ሃሌ ሉያ ለወልድ: ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል:: በዚህም ቦታዋ "ደብረ ሃሌ ሉያ" ተብላለች:: ጻድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው 6ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል::

+ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም "አቡሆሙ ለመነኮሳት ዘኢትዮዽያ-የኢትዮዽያ መነኮሳት አባት" ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል::

+ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ:: በተራራው ግርጌ ያለችውን ኪዳነ ምሐረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች::

+ጻድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው በዚህ ቀን በገዳሙ በስተምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው ብሔረ ሕያዋን ገብተዋል:: ጌታም 15 ትውልድን የሚያስምር የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል::

+" ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ "+

✞✞✞ በዘመነ ሐዋርያት በዚህ ስም የሚጠሩ አባቶች 2 ነበሩ:: አንደኛው ከ12ቱ ሐዋርያት ሲቆጠር ዛሬ የምናከብረው ደግሞ ከ72ቱ አርድእት ይቆጠራል:: ቅዱስ ፊልዾስ ያደገው የኖረውም በቂሣርያ አካባቢ ሲሆን ባለ ትዳር የልጆች አባት ነው::

+ጌታ ሲጠራው እንኩዋ 4 ደናግል ሴቶች ልጆች ነበሩት:: ከጌታ ሕማማት በፊት ተልኮ አስተምሯል:: ከበዓለ ሃምሳ በኋላም 7ቱ ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: (ሐዋ. 6) በቅዱስ እስጢፋኖስ መሪነትም 8ሺውን ማሕበር አገልግሏል::

+ቅዱስ እስጢፋኖስ ተገድሎ 8ሺው ማሕበር ሲበተንም ቅዱስ ፊልዾስ 4ቱን ልጆቹን አስከትሎ ወደ ሰማርያ ወርዷል:: በዚያም መሠሪ ስምዖንን ጨምሮ የሃገሪቱን ሰዎች አሳምኖ አጥምቁዋል::

+መቼም ቢሆን እኛ ኢትዮዽያውያን የማንዘነጋው ግን ጃንደረባውን ባኮስን ማጥመቁን እና ለሃገራችን የወንጌልን ብርሃን መላኩን ነው:: ጃንደረባው ቅዱስ ባኮስ ከጉዞ መልስ ትንቢተ ኢሳይያስን (ኢሳ. 53) ሲያነብ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ቀርቦ ምሥጢረ ሥጋዌን አስረድቶታል::

+ሠረገላውም ቁሞለት ቅዱስ ባኮስን አጥምቆት ተነጥቆ ሔዷል:: (ሐዋ. 8:26) ቅዱስ ፊልዾስ በቀሪ ዘመኑ ከተባረኩ 4 ደናግል ልጆቹ ጋር ሲሰብክ ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል::

+" ሙሽራው ቅዱስ ሙሴ "+

✞✞✞ የዚህ ቅዱስ ወጣት ታሪክ ደስ የሚልም: የሚገርምም ነው:: በሮም ከተማ በምጽዋት: በጾምና በጸሎት ከተቃኙ ሃብታሞች (መስፍንያኖስና አግልያስ) ተወልዶ: በሥርዓቱ አድጐ: መጻሕፍትን ተምሮ በተክሊል አጋቡት::

+በሠርጉ ማግስት ሙሽሪትን ቢያያት በጣም ታምራለች:: "ይህ ሁሉ ውበትና ምቾት ከንቱ አይደለምን!" ብሎ በሌሊት ጠፍቶ: ነዳያንን መስሎ ከሮም ሃገረ ሮሆ (ሶርያ አካባቢ) ሔደ::

+በዚያም በፍጹም ምናኔ: በ7 ቀን አንዲት ማዕድ እየበላ: በረንዳ ላይ እየተኛና እየለመነ ለዓመታት ኖረ:: ሁሌም ቀን የለመነውን ማታ ለነዳያን አካፍሎ እርሱ ሲጸልይ ያድር ነበር:: በአካባቢው ክብሩ ሲገለጽበትም የሐዋርያውን የቅዱስ ዻውሎስን በረከት ፍለጋ ወደ ጠርሴስ ሔደ::

+ነገር ግን ጥቅል ነፋስ መርከቧን ገፍቶ ሮም አደረሳት:: ቅዱስ ሙሴም "የአምላክ ፈቃድ ነው" ብሎ በወላጆቹ ደጅ ተኝቶ ለ12 ዓመታት ተጋደለ:: ወላጆቹ ፈልገው ስላጡት በበራቸው የወደቀው ነዳይ እርሱ ይሆናል ብለው አልጠረጠሩም::

+ከብዙ ተጋድሎም በኋላም ዜና ሕይወቱን ጽፎ በዚህች ቀን: በዕለተ እሑድ ዐርፏል:: ጌታችንም "መታሰቢያህን ያደረገውን ሁሉ ካልተጠራጠረ እምረዋለሁ" ብሎታል::

በዚያም ሕዝቡ: ካህናቱና ሊቀ ዻዻሳቱን ጌታ አዟቸው አግኝተውታል:: ወላጆቹ ማንነቱን በለዩ ጊዜም ታላቅ ለቅሶን አልቅሰዋል:: ሥጋውም ብዙ ተአምራትን አድርጉዋል::

+" ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ "+

✞✞✞ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ በሃገራቸው ልሳን 'አብደል መሲሕ' ይባላል:: ለቅዱስ ሙሴና ለሌሎችም ሙሽርነትን ትቶ መመነንን ያስተማረ እርሱ ነው:: አባቱ ታላቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ሲሆን እናቱ መርኬዛ ትባላለች:: የጻድቃን ትውልድ የተባረከ ነውና (መዝ. 111:1) ታላቁ አቡነ ኪሮስ አጐቱ ናቸው::

+ስለዚህ ቅዱስ ምን እነግራቹሃለሁ! ሙሉ ታሪኩ ከቅዱስ ሙሴ ጋር ተመሳሳይ ነውና:: ልዩነቱ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ በገዛ ፍቃዱ አካሉ በመቁሰሉ ምክንያት ሰዎች ሊለዩት አልቻሉም ነበር::

+በአርማንያ: በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ደጅ ለ15 ዓመታት ሲጋደል ወደ ወላጆቹ ሃገር ቁስጥንጥንያ ተመልሶ ለ15 ዓመታት ተፈትኗል:: ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆንም የአባቱ ባሮች በጥፊ ይመቱት: ጽሕሙን (ጺሙን) ይነጩት: ቆሻሻ ይደፉበት: ሽንታቸውንም ይሸኑበት ነበር::

+ለእርሱ ወዳጆቹ ውሾች ነበሩ:: በአባቱ ደጅ ለ15 ዓመታት መከራን ከተቀበለ በኋላ "ጌታ ሆይ! የአባቴ አገልጋዮች በእኔ ላይ ያደረጉትን ሁሉ በደል አድርገለህ አትቁጠርባቸው" አለ:: በዚህች ቀን ሲያርፍም ጌታችን 7ቱን ሊቃነ መላእክት ከነ ሠራዊታቸው አስከትሎ ወርዶ በክብር አሳርጐታል:: አጠቃላይ የገድል ዓመታቱም 30 ናቸው::

✞✞✞ አምላከ ቅዱሳን ለእነርሱ ካደለው ፍቅራቸው ለእኛም አይንሳን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::

+ጥቅምት 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

23 Oct, 19:13


1.አቡነ ዘሚካኤል (አረጋዊ)
2.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
3.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
4.ቅዱስ ሙሴ መርዓዊ
5.ቅድስት እድና (የአረጋዊ እናት)
6.አባ ማትያስ (የአረጋዊ ረድዕ)
   ወርሃዊ በዓል
1.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
2.እናታችን ቅድስት ነሣሒት

++"+ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም:: +"+ (ማቴ. 10:41)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/mahberememenan

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

23 Oct, 15:22


https://youtu.be/ScMZc4bVbD4?si=na0JoFftk-rvVsTO

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

23 Oct, 11:24


ታላቅ የምሥራች ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች በሙሉ "ኅብረ ሥርዐት ዘቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክሳዊት" በሚል ርእስ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን የሚማሩበት በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ የሚያገኙበት መጽሐፍ ከዚህ በፊት በ ፳፻፲፬ ዓ.ም ታትሞ ገበያ ላይ ከዋለ በኋላ አልቆ ከገበያ መጥፋቱ ይታወቃል። ስለሆነም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በ፳፻፲፯ ዓ.ም ለኹለተኛ ጊዜ ታትሞ ገበያ ላይ መዋሉን ስናበሥርዎ በታላቅ ደስታ ነው።
ከመጽሐፉ ይዘቶች በከፊል፦
✍️የብሉይ ኪዳን መሥዋዕት አቀራረብ ለሐዲስ ኪዳኑ አማናዊ መሥዋዕት ያለው ምሥጢራዊ ምሳሌያዊነት...
✍️ክፍላተ አዝማናት እና ስለ ክርስቶስ አመጣጥ የነቢያት አቆጣጠር ትክክለኛነት..
✍️ስለ "ቤተ ክርስቲያን" እና ስለ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ማብራሪያ...
✍️ስለ ሥጋው ደሙ የሚነሱ ጥያቄዎች መልስ እና በሥጋው ደሙ ዙሪያ ሰለሚሰነዘሩ አሉታዊ አስተሳሰቦች የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ...
ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባት የማይቻለው በምን ጊዜ ነው? ለምን? .. የሚሉ የዘመናችን ወራዙት/ወጣቶች ጥያቄዎች እና መንፈሳዊና አመክንዮአዊ አሳቦች..
✍️ፍትሐት ስለሚደረግባቸው ቀናት ብዛት እና ምሳሌያዊነት የቤ/ክርስቲያን አስተምህሮ ...
እነዚህ ለማሳያ ያክል የተዘረዘሩ ናቸው እንጂ የመጽሐፉ ይዘት በዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም።
ከዚህ በላይ ብዙ ሥርዐት ተኮር ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ተካተውበታል። ያንብቡ "ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋልና" ይማሩ ይወቁ ይህን ይጠብቁ "ካልተማሩ ማወቅ፤ ካላወቁ አውቀውም ካልጠበቁ መጽደቅ" የለምና።

መጽሐፉ አዲስ አበባ ዐራት ኪሎ ቅድስት ማርያም ፊት ለፊት ብራና መጻሕፍት መደብር ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ፦ 09 29 46 47 20
                      0920187906 ይደውሉ ።

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

22 Oct, 20:25


+በነዚህ ዓመታት ሁሉ ይህ አካሉ የተለወጠ ሕጻን ቅዱስ
ዘካርያስ መሆኑን ያወቀ የለም:: እንዲህ የቆሰለውም
አሲድነት ካለው የጉድጉዋድ ውሃ ውስጥ ሰጥሞ ለ40
ቀናት በመጸለዩ ነው::

+በመጨረሻ ግን አባቱ በምልክት ለይቶት አለቀሰ::
"ልጄ! አንተ ለእኔ አባቴ ነህ" ብሎታል:: አበው
መነኮሳትም ተሰብስበው እጅ ነስተውታል:: በ7 ዓመቱ
የመነነው አባ ዘካርያስ በ52 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፎ
በክብር ተቀብሯል::

=>አምላከ አፈ ወርቅ ዮሐንስ የድንግል እመ ብርሃንን
ፍቅሯንና ውዳሴዋን ይግለጽልን:: ከአባቶቻችን ክብርና
በረከትንም ያሳትፈን::

=>ጥቅምት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
2.አባ ዘካርያስ ገዳማዊ
3.አባ ማርዳሪ ጻድቅ
4.ቅዱስ አብጥማዎስ ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

=>+"+ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ
የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ
ልትሠወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ
በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት
ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው
በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ
እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: +"+ (ማቴ. 5:13-16)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/mahberememen

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

22 Oct, 20:25


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ጥቅምት ፲፫ (13) ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለዓለም ሁሉ መምሕር "ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ" እና ለአባ "ዘካርያስ ገዳማዊ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ ዮሐንስ አፈ ወርቅ +"+

=>ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ
ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ?
ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና
ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን
እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር "አፈ ወርቅ"
መሆን ያስፈልጋል:: እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት
ልሞክር::

+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው?

=>ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ
ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ::
እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር
ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና
በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን
ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል::

+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት
ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ
በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ
የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2 ወገን የተሳለ ሰይፍ
በመሆኑ ስንኩዋን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን
ትልቅ የራስ ምታት ነው::

+ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና
እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ
መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ
ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ
ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ
ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ
ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ
ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት::

+ከዚህች እለት በሁዋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ
ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት
እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ
ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ
አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ
ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት
ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ
ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና
ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር::

+ከዚህ በሁዋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ
በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው
ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት::
አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኩዋን የሚያወራ
ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ
በተደሞ ይሰሙት ነበር:: ሲያስተምር ምድራዊው ሰው
ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር::
አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል "አፈ ወርቅ" ብላ
ጠርታዋለች:: ለዛም ነው "አፈ ወርቅ" የሚባለው::
ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ 10 ዓመት
አቁሞታል::

+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ
ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም
ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ
ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ "አልመልስም"
በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና
መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት
ሃገር ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/ም
አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት
እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና
ለቅሶ ተደረገ::

=>ከዕረፍቱ አስቀድሞ አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ
አርቃድዮስ ግብር አገባ:: (ግብዣ አዘጋጀ)

በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ:
አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ 12ቱ ሊቃነ
መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) ከሰማይ በግርማ
ሲወርዱ ተመለከተ::

+ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ:
ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን
እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ
እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንገለጥልኝ መርቁኝ"
አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን
ቀጠሉ::

+በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ:
መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ
በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ
ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ
አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል
ጠየቀው::

+"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ
አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ
ድረስ አላወቃትም' ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?"
ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ
ይተረጉምለት ጀመር::

+"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ
የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ
ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ
መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኩዋ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ
ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር::

+'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው?' እያለ
ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በሁዋላ ግን አንድ
ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች
አላወቀም::

+አሁን ግን ልጇ አምላክ ዘበአማን: እርሷም ወላዲተ
አምላክ መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም
ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ
"አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች::

+ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ
አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ!
እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ
ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ
አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው
እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል::

=>ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:-
¤ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
¤አፈ በረከት
¤አፈ መዐር (ማር)
¤አፈ ሶከር (ስኩዋር)
¤አፈ አፈው (ሽቱ)
¤ልሳነ ወርቅ
¤የዓለም ሁሉ መምሕር
¤ርዕሰ ሊቃውንት
¤ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)
¤ሐዲስ ዳንኤል
¤ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)
¤መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ
¤ጥዑመ ቃል - - -

+"+ አባ ዘካርያስ ገዳማዊ +"+

=>ይህ ታላቅ ጻድቅ ባለ ጥዑም ዜና ነው:: ወላጆቹ
እሱንና አንዲት ሴትን ከወለዱ በሁዋላ አባቱ መንኖ
ገዳም ገባ:: ከዘመናት በሁዋላ ረሃብ በሃገሩ ሲገባ እናቱ
ወስዳ ለአባቱ ሰጠችው:: ይህን ጊዜ ዕድሜው 7 ዓመት
ነበር::

+በገዳም ከአባቱ ጋር ሲኖር ከመልኩ ማማር የተነሳ
አባቶች መነኮሳት "ይህ ልጅ ይህን መልክ ይዞ እንዴት
መናኝ መሆን ይችላል!" ሲሉ ሰማ:: በሌሊትም ተነስቶ
በሕጻን አንደበቱ "ጌታየ! መልኬ ካንተ ፍቅር ከሚለየኝ
መልኬን አጠፋዋለሁ" አለ:: ከገዳሙም ጠፋ::

+አባትም በጣም አዘነ:: ከ40 ቀናት በሁዋላ ግን ሊያዩት
የሚያሰቅቅ: አካሉ ሁሉ የቆሳሰለ አንድ ነዳይ ሕጻን
መጥቶ ወደ ገዳሙ ተጠጋ:: ይህ ሕጻን በጾም: በጸሎትና
በትሕትና ተጠምዶ ለ45 ዓመታት አገለገለ::

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

21 Oct, 21:03


=>አምላከ ዳዊት ፍቅሩን: አምላከ ማቴዎስ
አገልግሎቱን: አምላከ ድሜጥሮስ ንጽሕናውን
ያሳድርብን:: ጸጋ በረከታቸውን ደግሞ ያትረፍርፍልን::=>ጥቅምት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ (የነገሠበት)
2.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቅ
4.ቅድስት ልዕልተ ወይን
5.ቅዱስ ሳሙኤል ነቢይ
6.ጻድቃን ዼጥሮስ ወዻውሎስ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
6.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

=>+"+ ከሕዝቤም የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግሁ::
ባሪያየን ዳዊትን አገኘሁት::
ቅዱስ ዘይትም ቀባሁት::
እጄም ትረዳዋለች::
ክንዴም ታጸናዋለች::
ጠላት በእርሱ ላይ አይጠቀምም::
የዓመጻ ልጅም መከራ አይጨምርበትም::
ጠላቶቹን ከፊቱ አጠፋለሁ::
የሚጠሉትንም አዋርዳቸዋለሁ:: +"+ (መዝ. 88:20)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/mahberememenan

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

21 Oct, 21:03


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ጥቅምት ፲፪ (12) ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለልበ አምላክ "ቅዱስ ዳዊት":
ለቅዱስ "ማቴዎስ ሐዋርያ" እና ለቅዱስ "ድሜጥሮስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*" ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ "*+

=>ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ይላል:-
"እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ:
አይጸጸትም::" (መዝ. 131:11) አሁን በእግዚአብሔር
መጸጸት ኑሮበት አይደለም:: ቅዱስ ዳዊት የማያጸጽት
ፍጹም ወዳጅ መሆኑን ሲገልጥ ነው እንጂ:: ጌታ ቅዱስ
ዳዊትን "እንደ ልቤ የሆነ: ፈቃዴን የሚፈጽም: ባሪያየን
ዳዊትን አገኘሁት" (መዝ. 88:19) ብሎ ሲናገር ሰምተን
እጅግ አደነቅን::

+እንደ አምላክ ልብ ሆኖ መገኘት ምን ይረቅ?! ምንስ
ይደንቅ?! ለዚህ አንክሮ ይገባል !! ጌታ ይቀጥልና ደግሞ
"ዳዊትን እንዳልዋሸው አንድ ጊዜ በቅዱስነቴ
ማልሁ" (መዝ. 88:35) ይላል:: *" አቤት አባታችን
ዳዊት!!! . . .
ክብር: የክብር ክብር: ውዳሴና ስግደትም ላንተ በጸጋ ይገባል "* እንላለን::

+ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ዳዊት 7 ሃብታት ሲኖሩት:-
1.ሃብተ ትንቢት
2.ሃብተ መንግስት
3.ሃብተ ክህነት
4.ሃብተ በገና (መዝሙር)
5.ሃብተ ፈውስ
6.ሃብተ መዊዕ (ድል መንሳት)
7.ሃብተ ኃይል ተብለው ይታወቃሉ::

+በ7ቱ ስሞቹም:-
1.ጻድቅ
2.የዋህ
3.ንጹሕ
4.ብእሴ እግዚአብሔር
5.ነቢየ ጽድቅ
6.መዘምር እና
7.ልበ አምላክ ተብሎ ይጠራል::

+ይህች ቀን ለእሥራኤል የነገሠባት ቀን ናት::
እግዚአብሔር ሳዖልን ከናቀው በሁዋላ ከእሴይ ልጆች
መካከል "እንደ ልቤ የሆነውን ቀብተህ አንግስልኝ"
ቢለው በዚህች ቀን ነቢዩ ሳሙኤል ቤተ ልሔም
ገብቷል::

+በዚያም ከኤልያብ እስከ አሚናዳብ: 7ቱን የእሴይን
ልጆች ቢፈትን አልሆነም:: በቅዱስ ሚካኤል ጠቁዋሚነት
ግን ከእረኝነቱ ዳዊት ተጠራ::
ገና ከርቀት ሲመጣ የዘይት ቀርኑ ቦግ ብሎ ተከፈተ::

+በቅዱስ ዳዊት ራስ ላይም እንደ እሳት ፈላ:: በአምላክ
ምርጫም በ12 ዓመቱ ንጉሥ ተባለ:: የቅዱሱ ዜና ብዙ
ነውና ለታሕሳስ 23 ይቆየን:: በቸር ቢያደርሰን በዚያው
ቀን ከክብሩ እንካፈላለንና::

+"+ ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ +"+

=>ቅዱሱ በቀዳሚ ስሙ "ሌዊ": በቀዳሚ ግብሩ ደግሞ "ቀራጩ" ይባል ነበር:: ወንጌል እንደሚል ጌታችን የጠራው ከሚቀርጥበት ቦታ ሲሆን (ማቴ. 9:9) ከ12ቱ ሐዋርያት ደምሮ (ማቴ. 10:1) ስሙን "ማቴዎስ" ብሎታል:: ትርጉሙም "ኅሩይ" (ምርጥ) እንደ ማለት ነው::

+ጌታችንን በዘመነ ሥጋዌው በፍጹም ምናኔ ከማገልገሉ
ባለፈ ከዋለበት እየዋለ: ካደረበት እያደረ: የእጁን
ተአምራት ተመልክቷል:: የቃሉንም ትምሕርት ሰምቷል::
በጌታ ሕማማት ጊዜ ምንም በፍርሃት ከተበተኑት አንዱ
እሱ ቢሆን አመሻሽ ላይ ወደ ማርቆስ እናት ቤት (ጽርሐ ጽዮን) ሒዶ ወንድሞቹን ሐዋርያትን ተቀላቅሏል::

+የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ከሙታን ተነስቶ ትንሳኤውን ሲገልጥም ቅዱስ ማቴዎስ
ነበረ:: ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን
ተምሮ በጌታ ዕርገት ጊዜ ሊቀ ዽዽስናን ተሹሟል::
በ50ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜም ጸጋውንና
71 ልሳናትን ተቀብሎ በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ወንጌልን
ሰብኩዋል::

+ሐዋርያት ወንጌልን ለዓለም ለማዳረስ እጣ በተጣጣሉ
ጊዜ ለቅዱስ ማቴዎስ ምድረ ፍልስጥኤም ደረሰችው::
ሃገረ ስብከቱን ካዳረሰ በሁዋላም ወደ ሌሎች ሃገራት
ተጉዞ ሰብኩዋል::

+ለምሳሌ በገድለ ሐዋርያት ላይ በኢትዮዽያ: በፋርስና
በባቢሎን አካባቢ ማስተማሩን ይገልጻል:: የሚገርመው
ደግሞ ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆን ነገር ሃገራችን ውስጥ
መኖሩ ነው::

+ወደ አክሱምና አካባቢዋ ቅዱሳት መካናትን ለመሳለም
በሔድንበት ወቅት በጻድቃነ ዴጌ/ዶጌ ገዳም ውስጥ
(አክሱም አካባቢ የሚገኝ የ3ሺ ስውራን ቦታ ነው)
የቅዱስ ማቴዎስን በትረ መስቀል መመልከት ችለናል::
አባቶችም ቅዱስ ማቴዎስ በዘመነ ስብከቱ አክሱም
አካባቢ መጥቶ እንደ ነበር ነግረውናል::

+ቅዱሱ ሐዋርያ በአይሁድ: በአሕዛብና በአረሚ መካከል
እየተመላለሰ አስተምሮ በርካታ ተአምራትን ሠርቷል::
የጣዖት ካህናትንና ነገሥታትን ጨምሮ እልፍ አእላፍ
ነፍሳትን ወደ ክርስትና መልሷል::

+ስለዚህ ፈንታም እጅግ ብዙ መከራዎች
ተፈራርቀውበታል:: ጌታችንም በየጊዜው እየተገለጸ
ያጽናናው ነበር:: በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያውን
ወንጌል በምድረ ፍልስጥኤም ሲጽፍ: ዘመኑም ጌታ ባረገ
በ8ኛው ዓመት (ማለት በ43 ዓ/ም) አካባቢ ነው::

+ወንጌሉ 28 ምዕራፎች ሲኖሩት በጌታ የዘር ሐረግ
ጀምሮ የጌታችንን ትምሕርቱንና ተአምራቱን በሰፊው
ያትታል:: በመጨረሻም ከምሴተ ሐሙስ እስከ ትንሳኤ
ድረስ አትቶ ይጠናቀቃል::

+ቅዱስ ማቴዎስ ከ12ቱ ሐዋርያት በአንድ ነገሩ
ይለያል:: ከ5ቱ ዓለማት አንዱን (ብሔረ ብጹዓንን)
ያስተምር ዘንድ ተመርጧል:: ዘወትር እሑድ በደመና
እየተነጠቀ ኃጢአት ወደ ሌለበት ዓለም ገብቶ ብጹዓንን
ያስተምር ነበር::
"ሰላም ለማቴዎስ በደመና ሰማይ ዘተነጥቀ:
ኅሩያነ ይርዓይ ዘብሔረ ብጹዓን ደቂቀ::" እንዲል::

+በዚያም ዘወትር ጌታችንን ያየው ነበር:: ቅዱስ ማቴዎስ
እንዲህ ከተመላለሰ በሁዋላ በፍጻሜው ለጊዜው
ባልለየናት አንዲት ሃገር ውስጥ አረማውያን አስረው
አሰቃይተውታል:: በዚህች ቀንም ገድለውታል::

+"+ ቅዱስ ድሜጥሮስ +"+

=>ቅዱስ ድሜጥሮስ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ:
በመንፈሳዊ ለዛ ከአጐቱ ደማስቆስ ጋር ያደገ የዘመኑ
ደግ ሰው ነበር:: በዘመኑ ክርስቲያኖች በሰማዕትነት
ያለቁበት በመሆኑ ቤተሰቦቹ የአጎቱን ልጅ ልዕልተ ወይንን
እንዲያገባ ግድ አሉት::

+ቅዱስ ድሜጥሮስ የነርሱን ፈቃድ ለመፈፀም ጋብቻውን
በተክሊል ፈፀመ:: የፈጣሪውን ፈቃድ ለመፈፀም ደግሞ
ከቅድስት እናታችን ልዕልተ ወይን ጋር ተስማምተው ለ48
ዓመታት በአንድ አልጋ ላይ እየተኙ: አንድ ምንጣፍና
ልብስ እየተጋሩ በድንግልና ኑረዋል:: ቅዱስ ሚካኤልም
ስለ ክብራቸው ከመካከላቸው ሆኖ ቀኝ ክንፉን ለርሱ:
ግራ ክንፉን ለርሱዋ ያለብሳቸው ነበር::

+ከ48 ዓመታት በሁዋላ ቅ. ድሜጥሮስ የግብፅ 12ኛ
ሊቀ ዻዻስ ሆኖ ተሹሞ ምስጢር በዝቶለት ባሕረ-
ሐሳብን ጽፎ ሠርቷል:: ሰይጣን በሰዎች አድሮ ቅዱሱን
ሚስት አለው በሚል ቤተ ክርስቲያን ላይ ሁከት
በመፈጠሩ ቅዱስ ድሜጥሮስ በመልዐኩ ትእዛዝ ሕዝቡን
ሰብስቦ: እሳት አስነድዶ: ከቅድስት ልዕልተ ወይን ጋር
እሳቱ ውስጥ ገብተው ለረዥም ሰዓት ጸልየዋል::

+ሕዝቡም ይሕን ተአምር አይተው: የቅዱሳኑን ንጽሕና
ተረድተው: ማረን ብለው በፍቅር ተለያዩ:: መጋቢት 12
ቀን ድንግልናው ተገልጧል::

+ቅዱስ ድሜጥሮስና እናታችን ልዕልተ ወይን ተረፈ
ዘመናቸውን በቅድስና አሳልፈዋል:: በተለይ ሊቀ ዻዻሳቱ
ድሜጥሮስ ብዙ ድርሳናትን ደርሷል:: እነ አርጌንስ
(Origen) ና ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ (Clement of Alexandria) የመሰሉ መናፍቃንንም አውግዟል::

+ከጣዕመ ስብከቱም የተነሳ አርጅቶ እንኩዋ ምዕመናን
እየተበሰቡ ይማሩ ነበር:: በአልጋ ተሸክመውም
ይባርካቸው ነበር:: ቅዱሱ በ107 ዓመቱ ያረፈው በ3ኛው
መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ በዚህች ቀን ነው::

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

20 Oct, 23:41


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ጥቅምት ፲፩ (11) ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለአባ "ያዕቆብ ስዱድ" እና ለእናታችን "ቅድስት ዺላግያ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ አባ ያዕቆብ ስዱድ +"+

=>"ዻዻስ" ማለት "አባት - መሪ - እረኛ" ማለት ነው::
በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ በሐዲስ ኪዳን
የመንፈሳዊ ስልጣን ደረጃዎች በጥቅሉ 3 ናቸው::
እነሱም ዲቁና: ቅስና: ዽዽስና ሲሆኑ በሥራቸው ወደ 9
ያህል ክፍሎች አላቸው:: ከእነዚህም ከፍተኛው ስልጣን
ዽዽስና ነው::

+ዽዽስና ማለት የክርስቶስን መንጋ እንደ ባለቤቱ
አድርጐ መጠበቅ ማለት ነው:: ሥልጣኑ በምድር
"ሸክም: ዕዳ" ሲሆን በሰማይ ግን "ክብር" ነው::
ማንም በሥጋው ላይ ካልጨከነ በቀር ዽዽስናን
አይመኝም::

+ቅዱስ ዻውሎስ "ሠናየ ግብረ ፈተወ - ማንም
ዽዽስናን ቢመኝ መልካም ሥራን ተመኘ" (1ጢሞ. 3:1)
ማለቱን ይዞ "ሹሙኝ" ማለት ወደ ማይጠፋ እሳት
የሚያስጥል ከባድ ውሳኔ ነው:: ምክንያቱም አንድ
ክርስቲያን የሚጠየቅ በራሱ ኃጢአት ሲሆን አንድ ካህን
ደግሞ ስለ ልጆቹ ይጠየቃል:: የከፋው ግን የዻዻሱ
ነው::

+አንድ ዻዻስ ቢጾም ቢጸልይም እንኩዋ ለድኅነቱ በቂ
አይደለም:: ምክንያቱም በመንበሩ ላይ ያስቀመጠው
መንጋውን እንጂ ራሱን እንዲያድን አይደለምና:: ጌታ
እንዳለ መልካም እረኛ "ይሜጡ ነፍሶ ቤዛ አባግኢሁ -
መልካሙ እረኛ ስለ በጐቹ ቤዛ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ
ነው::" (ዮሐ. 10) ስለዚህም ክህነት ( ዽዽስና)
ሐዋርያዊ አገልግሎት ከባድም ኃላፊነት ነው::

+አባቶቻችን ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ሐዋርያውያን
ታላላቅ የዽዽስና መንበሮችን መሥርተው: ትምሕርቱን ከነ
ወንበሩ አስተላልፈዋል:: ከእነዚህ መንበረ ዽዽስናዎች
4ቱ የበላይ ናቸው::

እነዚህም የቅዱስ ዼጥሮሱ የሮም: የቅዱስ ዮሐንሱ
የአንጾኪያ: የቅዱስ ማርቆሱ የእስክንድርያና የቅዱስ
ዻውሎሱ የኤፌሶን መናብርት ናቸው::

+እነዚህ መንበሮችም ከክርስቶስ ዕርገት እስከ 443
(451) ዓ/ም: ጉባኤ ኬልቄዶን ድረስ በአንድነት ቆይተው
ተለያይተዋል:: ከእነዚህ መናብርት መካከል
የእስክንድርያው (የግብጹ) እና የአንጾኪያው (የሶርያው)
ዛሬም ድረስ በተዋሕዶ እምነት የጸኑ ናቸው::

+የእኛ ቤተ ክርስቲያንም ሐዋርያዊት እንደ መሆኗ
ሐዋርያትን መስለው: ሐዋርያትን አህለው የተነሱ አበው
ዻዻሳትን በየጊዜው በበዓላት ታስባለች: ታከብራለች::

+በተለይ ደግሞ የእስክንድርያና የአንጾኪያ በርካታ
አባቶችን እናከብራለን:: እነርሱ ለቀናች ሃይማኖትና
ለመንጋው ሲሉ ብዙ መከራን በአኮቴት ተቀብለዋልና::
ከእነዚህም መካከል አንዱ አባ ያዕቆብ ሲባሉ በ5ኛው
መቶ ክ/ዘመን አካባቢ የአንጾኪያ መንበር ፓትርያርክ
ነበሩ::

+ቅዱሱ በገዳማዊ ሕይወት የተመሠከረላቸው:
በትምሕርት የበሰሉና ለመንጋው የሚራሩ በመሆናቸው
በምዕመናን ይወደዱ ነበር:: ነገር ግን ተረፈ
አርዮሳውያንና መለካውያን ከነገሥታቱ ጋር አብረው ብዙ
አሰቃዩዋቸው:: በመጨረሻም ከመንበራቸው አፈናቅለው
ወደ በርሃ አሳድደዋቸዋል:: ከስደት በሁዋላም አባ
ያዕቆብ በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

+"+ ቅድስት ዺላግያ ገዳማዊት +"+

=>ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚል እግዚአብሔር የኃጥኡን
መመለስ እንጂ ሞቱን አይፈልግም:: በጠፋው በግ
መገኘት ደስ ይለዋል:: በእግርህ ሒድ እንኩዋ
አይለውም:: ይልቁኑ በትከሻው ተሸክሞ ከጐረቤቶቹ ጋር
ደስ ይለዋል እንጂ::

+ቤተ ክርስቲያን ካፈራቻቸው ቅዱሳን አንዳንዶቹ ጭንቅ
ከሆነ የኃጢአት ሕይወት የተመለሱ ናቸው::

ግን ድንቅ በሆነ ንስሃቸው "ቅዱሳን" ከመባል ደርሰዋል::
ከእነዚህም አንዷ ቅድስት ዺላግያ ናት::

=>ይህቺ ቅድስት እናት በልጅነቷ በመልኩዋ ምክንያት
ስሕተት ያገኛት ናት:: አምላክ የፈጠረውን መልክና ገላ
እንዴት መጠቀም እንዳለብን እየተማርን አይደለምና
በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረውን ገላችን ለዲያብሎስ
ሰጥተነዋል::

+ይህቺ እናትም ችግሯ ይኼው ነበር:: ስለ ገጽታዋና
ገላዋ የነበራት የተሳሳተ አመለካከት መጀመሪያ ወደ
ትውዝፍት (ምንዝር ጌጥ): ቀጥሎም ወደ ዝሙት
ከተታት:: ለዘመናትም የሰይጣን ወጥመድ ሆና ኑራለች::

+ፈጣሪ ግን ለሁላችንም የመዳን ቀን ጥሪ አለውና
እሷንም ጠራት:: ምናልባትም በዘመኗ የብዙ ሰባክያንን
ትምሕርት ሰምታለች:: አንዱም ግን ወደ ልቧ አልገባም::

+ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ያላደረበት አስተማሪ በጥሩ
አማርኛ ልባችን ደስ ያሰኝ ይሆናል እንጂ ሊለውጠን
አይችልም::

+በዘመኑም የሚታየው ትልቁ ችግር ይኼው
ይመስለኛል:: እግዚአብሔር የሾማቸው አባቶቻችን
ተቀምጠው ወጣቶች መድረኩን የሙጥኝ ብለነዋል::

+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ዺላግያ አንድ ቀን
የሰማችው የደጉ ዻዻስ ትምሕርት ግን ፈጽሞ ዘልቆ
ተሰማት:: ተጸጸተች: አለቀሰች:: ወደ ዻዻሱ ሔዳ
"ማረኝ" አለች: ንስሃ ሰጣት:: እርሷም ንብረቷን ሁሉ
መጽውታ በርሃ ገባች::

+አንገቷን ደፍታ በጾምና በጸሎት ሰይጣንን ድል ነሳችው::
ከሃገሯ ሶርያ ወደ ቀራንዮ ደርሳ ተመልሳ ለ30 ዓመታት
ዘጋች:: ተባሕትዎዋን ስትፈጽም በጸጋ እግዚአብሔር
ተአምራትን ሠርታ: ለኃጥአን መንገድ ጧፍ ሆና አብርታ
በዚህች ቀን ዐርፋለች::

=>አምላከ ቅዱሳን የሚያስተውለውን የንስሃ አእምሮን
ያድለን:: ከወዳጆቹ በረከትም አያርቀን::

=>ጥቅምት 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ቅዱስ አባ ያዕቆብ (ስደተኛው ሊቀ ዻዻሳት)
2.ቅድስት ዺላግያ ገዳማዊት
3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
4.ቅዱስ አርማሚ ሰማዕት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ብፁዐን ኢያቄምና ሐና
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ

=>+"+ መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና
ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ
ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም
ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም
በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ
'የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ
ይበላችሁ' ይላቸዋል:: እላችሁአለሁ: እንዲሁ ንስሃ
ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ
በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል:: +"+
(ሉቃ. 15:3-7)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/mahberememenan

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

20 Oct, 08:56


https://youtu.be/iIxln0wd8Ow

ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan

19 Oct, 19:43


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ጥቅምት ፲ (10) ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱሳን ሰማዕታት "ባኮስ ወሰርጊስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ ቅዱሳን ባኮስ ወሰርጊስ +"+

=>ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል
የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው
ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል::
ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

+ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል::
የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ
ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ
በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም
ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ
እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

+እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር
ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ!
በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ
በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ
መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

+እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን
መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: (ማቴ.
5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና
በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር
ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ
ይመጣል::

+በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል
ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን
እንድንጸና ነውና::

¤እስኪ ለዛሬ ደግሞ በአጭሩ የቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስን
ዜና እንካፈል::

+እነዚህ ቅዱሳን የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ናቸው::
ባኮስ እና ሰርጊስ (ሰርግዮስ) ከልጅነት ጀምሮ ባልንጀሮች
ናቸው:: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር
መክስምያኖስና ዲዮቅልጢያኖስ እስከ ነገሡበት ዘመን ድረስ በአንጻሩም ቢሆን ሰላም
ነበር::

+ታዲያ በዚህ የሰላም ጊዜ 2ቱ ቅዱሳን ሥራ
አልፈቱም:: ጾምን: ጸሎትንና በጐ ምግባራትን ሁሉ
ይከተሉ ነበር:: ለመከራ ዘመን ስንቅ የሚሆነን በሰላሙ
ዘመን የተያዘ ስንቅ ነውና::

+በዚያው አንጻር ደግሞ ሠርቶ መብላት ይገባልና ሥራ
ሲፈልጉ መክስምያኖስ ሠራዊት መሰብሰብ ጀመረ::
እነርሱም ከሠራዊቱ ዘንድ ተቆጥረው የምድራዊ ንጉሥ
ጭፍሮች ሆኑ:: በእርግጥ በዘመናችን ለክርስትና
አይመቹም ከሚባልላቸው ሥራዎች አንዱ ውትድርና
ነው::

+ነገር ግን ብዙ ቅዱሳንን ስትመለከቷቸው ሙያቸው
ይሔው ነበር:: ቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስ ጊዜው የሰላምም
ይሁን የጦርነት ይጾማሉ: ይጸልያሉ: ይመጸውታሉ::
እንዲህ እንዲህ እያሉም ዘመናት አለፉ::

+ከቆይታ በሁዋላ ግን ሰይጣን ያደረበት ንጉሡ
መክስምያኖስ ጣዖት አመለከ:: አዋጅም አውጥቶ
ክርስቲያኖችን ያሰቃይ: ይገድልም ያዘ:: ቅዱሳኑ ይህንን
ሲሰሙ አዘኑ::

+ቁጭ ብለውም ተወያዩ:: በልባቸው ፍቅረ ክርስቶስ
ይነድ ነበርና ወጣትነታቸው: መልካቸው: ተወዳጅነታቸው
ሁሉ ሊያታልላቸው አልቻለም:: እንደ አንድ ልብ መካሪ:
እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ስለ ሃይማኖት ሊሰው ወሰኑ::

+በማግስቱም ንጉሡ ወደ ሾመው የቅርብ አለቃቸው
ቀረቡና "የምንነግርህ ነገር አለን" አሉት:: "እሺ"
ሲላቸው በወገባቸው ያለውን የክብር መታጠቀያና የክብር
ልብሳቸውን በፊቱ ወረወሩለትና "እኛ የክርስቶስ ጭፍሮች
ነንና ከዚህ በሁዋላ ላንተ: ለጣዖት አምላኪው
አንታዘዝም" አሉት::

+መኮንኑ ነዶታልና አስገረፋቸው: አሳሰራቸው:: በረሃብና
በጥም: በብዙ መክፈልተ ኩነኔም አሰቃያቸው:: እነርሱ
ግን ጽኑዓን ነበሩና አልቻሏቸውም:: ጥቅምት 4 ቀን በሆነ
ጊዜ ግን 2ቱን ለያዩዋቸው::

ቅዱስ ባኮስን ለብቻው ወስደው ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ
ላይ አሠሩበትና ባሕር ውስጥ አሰጠሙት::

+ነፍሱም ከስጋው ስትለይ ባሕር ወደ ዳር
አስወጣችው:: በአካባባቢውም "ባባ" እና "ማማ"
የሚባሉ ባሕታውያን ነበሩና እግዚአብሔር እንዲገንዙት
አዘዛቸው:: ሲሔዱም ቅዱስ ሥጋውን አንበሳና ተኩላ
ሲጠብቁት አግኝተው: በታላቅ ዝማሬ ገንዘው: በራሳቸው
ተሸክመው ወስደው: በበዓታቸው ውስጥ ቀበሩት::

+ቅዱስ ሰርጊስን ደግሞ ለ6 ቀናት ካሠሩት በሁዋላ
በዚህች ቀን እጁንና እግሩን በእንጨት ላይ ቸንክረው:
በእንስሳት ጭራ ላይ አስረው ሲጐትቱት ውለዋል::
አንገቱን በሰየፉት ጊዜም አንዲት ወጣት ደሙን ተቀብላ
በረከትን አግኝታለች:: የመከራ ዘመን ካለፈ በሁዋላም
ለቅዱሳኑ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ በዚህች ቀን ተቀድሷል::
ተአምራትም ታይተዋል::

=>አምላከ ሰማዕታት ጽንዓት: ትእግስታቸውን አሳድሮ
ከበረከታቸው ይክፈለን::

=>ጥቅምት 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስ (ሰማዕታት)
2.ቅዱስ ዮሐንስ መስተጋድል
3.አባ አውማንዮስ ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
6.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
7.ቅዱስ እፀ መስቀል

=>+"+ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ
ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት:
ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች
ተቈጠርን'
ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች
እንበልጣለን:: +"+ (ሮሜ. 8:35-38)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/mahberememenan
https://t.me/mahberememenan

12,333

subscribers

2,052

photos

1

videos